ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ማን ናቸው ? ( ጎንደር በተከሰተው ቀውስ ዙሪያ ) By Girma Kassa 

13620218_10157410545075354_8618586224164870803_n
በወልቃይት ጠገዴ በዘር ሳይለያዩ ኢትዮጵያዉይን በፍቅርን እና በደስታ ለዘመናት ኖረዋል። ትግሬ፣ አማራ ሳይባባሉ፤ እርስ በርስ ተዋልደው፣ ሲያሻቸው ሽሬ ፣ ሲያሻቸው ጎንደር እየነገዱ፣ ሲያሻቸው በአማርኛ ፣ ሲያሻቸው በትግሪኛ እየተናገሩ።
 
ሆኖም ሕወሃት ስልጣን ሲያዝ የዘር ፖለቲካን አመጣ። አማራ፣ ትግሬ፣ ኦሮሞ እያለ ህዝቡን መከፋፈል ጀመረ። በወልቃይት ጠገዴ የሚኖረው ማህበረሰብ ከአማርኛ ጋር ትግሪኛም ተናጋሪ በመሆኑ፣ “ትግሬ ነህ” አሉት። ከተከዜ በስተምእራብ ያለውን የበጌምድር አካል የነበረውን ለምለሙን የወልቃይት ጠገዴ ግዛት ወደ ትግራይ በኃይል ቀላቀሉት። ወልቃይቱን እያፈናቀሉ እንደ አድዋ ካሉ ቦታዎች ይኖሩ የነበሩ ነዋሪዎች ማስፈር ጀመሩ። ማንም ኢትዮጵያዊ በማናቸዉም የአገሪቷ ግዛቶች የመኖር መብት አለው። ዜጎች ከአድዋ መጥተው በወልቃይት ጠገዴ መስፈራቸው ችግር ኖሮት አያውቅም። ለዘመናት ከትግራይ እየመጡ በወልቃይት ጠገዴ የትግራይ ሰዎች ኖረዋል። ወደፊትም ይኖራሉ።
 
ሆኖም የሕወሃት አላማ፣ የትግራይ ልጆች በተቀረው የአገሪቷ ግዛቶች የመኖር መብታቸው እንዲከበር ሳይሆን ( ለምን መኖር ያልቻሉበት ጊዜ ኖሮ ስለማያውቅ) ግን በወልቃይት ጠገዴ የሚኖሩት ጎንደሬ (አማራዎች) ላይ የዘር ማጽዳት በማድረግ፣ አካባቢው ሙሉ ለሙሉ የትግሬ አካባቢ እንዲሆን ለማድረግ ነው። አላማቸው ሕዝብን ለመጥቀም ሳይሆን ዘረኛ ፖሊሲን ለማስፋፍት ነው። ህዝቡ የሌለዉን ማንነት በሃይልና በጉልበት ለመጫን ነው። አላማው ልማት፣ አላማው ብሄራዊ አንድነት ፣ አላማው የሕዝብ ጥቅም ሳይሆን አላማው ዘረኝነት ነው።
 
ይሄንን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ተቃወመ። “ትግሬ ነህ” ሲባል “አይደለም ትግሬ አይደለሁም፣ ጎንደሬ ነኝ፤ አማራ ነኝ ” አለ። ከትግራይ ክልል ወጥተን ወደ ጎንደር መቀላቀል እንደሚፈልግ አሳወቀ። ህዝቡ ይወክልኛል ያላቸውን ግለሰቦች መርጦ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ጥያቄዎችን ማቅረብ ጀመረ። የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ የሚባል ተቋቁሞ፣ ማመልከቻዎችን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ሳይቀር በማስገባት ፣ መሰረታዊ የሆነ የመብት ጥያቄዎችን ማንሳት ጀመረ። ሆኖም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚባሉት ሕወሃትን ስለፈሩ የወልቃይቶች ጥያቄ፣ ክልሉ ይፍታው ብሎ አጣጣሉት።
 
የሕወሃት አገዛዝ ሰላማዊና ዘመናዊ በሆነ መልኩ የሕዝቡን ጥያቄ ከማስተናገድ ይልቅ፣ በነዚህ የኮሚቴ አባላት ላይ ዘመቻ ጀመረ። የአማራን ክልል አስተዳደር በመናቅ፣ የጎንደር የከንቲባ ጽ/ቤትን ወደ ጎን በማድረግ በሌሊት የሕወሃት ታጣቂዎችን በመላክ የኮሚቴ አባላትን ማፈን ጀመረ። ከኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ ኮሎኔል ደመቀ በዘዉዱ ናቸው።
 
ኮሎኔል ደመቀ ጋር ሲደርሱ ኮሎኔሉ “ለምን በሌሊት ትመጣላችሁ ? ፤ ጠዋት አነጋግሩኝ” የሚል ምላሽ ቢሰጡም ታጣቂዎች በሩን ገንድሰው ሊገቡ ሲሉ ኮሎኔሉ ራሳቸውን ለመከላከል በተኩሱት ጥይት አንዱ የሕወሃት ታጣቂ ወደቀ። ሌላው ሁለተኛውም ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስድ ሲል እንደዚሁ። በዚህ መካከል ሕዝቡ የተኩስ ድምጽ ሰምቶ ወዲያው የኮሎኔሉን ቤት ከበበ። ኮሎኔሉ ከታፈኑ በኋላ እርሳቸዉን ለመዉሰድ ተዘጋጅቶ የነበረው ኮብራ የወታደር መኪና በሕዝቡ ተቃጠለ። ነደደ።
 
ሕወሃቶች በሌሊት የፈጸሙትን የዉንብድና ዘመቻ የሰማው የጎንደር ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ተነቃነቀ። ጎንደር ከተማ ከቁጥጥር ዉጭ ሆነች። የወያኔ ደጋፊዎች ሱቆችና ንብረቶችን በንዴትና በቁጣ ወጣቶች ማቃጠል ጀመሩ። የኤፈርት ንብረት የሆኑት የሰላም ባሶች ተቃጠሉ። የአስፋልት መንገዶች በሙሉ ተዘጉ። የመከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማዋ ቢገባም፣ ባንኮችን እና አንዳንድ መስሪያ ቤቶች ከመጠበቅ ዉጭ ምንም ማድረግ አልቻለም።
 
የጎንደር ነዋሪዎች በነቂስ በመዉጣት ነበር የተቃዉሞ ድምጻቸውን ያሰሙት። ኮሎኔል ደመቀ በዘዉዱም እስከአሁን በሕዝብ ጉልበት ያልተያዙ ሲሆን ፣ ህዝቡም ነቅቶ እየጠበቃቸው ነው።
 
ጦማሪ ልያ ፋንታ እንዳቀረበችው፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ፣ አባታቸው ቄስ ዘውዱ ብሩ ይባላሉ። የተወለዱት በጠገዴና ወልቃይት መካከል ጠለሎ በምትባል አውራጃ ነው። ልዩ ስሟ ማለትም የትውልድ መንደሩ አዲገረት ይባላል። ኮሎኔል ደመቀ ለሃያ አመታት የወያኔ ታጋይ የነበሩ ሲሆኑ፣ “ደርግን ለመጣል ነው ከናንተ ጋር የተሰለፍኩት እንጅ ትግሬ ለመሆን አይደለም” በሚል ነው የተለያቸው። በጣም ኩሩና ትሁት ሰው ናቸው። ሁሌም ረጋ ያሉ ሰው ናቸው።
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: