የቂም በቀል እርምጃ በሃብታሙ አያሌው ላይ – ግርማ ካሳ

 

habtamu 33

ዶክተሮች “ሃብታሙን ለማከም መሳሪያው ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለሌለ ማከም አንችልም” የሚል ማረጋገጫም ቢሰጡም፣ ህወሃቶች በሃብታሙ ላይ ያስቀመጡትን ከአገር የመዉጣት እገደ ለማንሳት ባለመቻላቸው፣ ይህ ወጣት እንደገና በጠና ታሞ ወደ ሆስፒታል ገብቷል። ከባለቤቱ ጋር ሆኖ በቅርብ የሚያስታምመው የትግል አጋሩና ዬስር ቤት ጓዲ፣ ዳንኤል ሺበሺ

“በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለን ነበር ሀብታሙ በድንገት (ከጧቱ ወደ 4:30 ገደማ) ራሱን ስቶ ሲያሸልብ ያስተዋልነው፡፡ እኔን ጨምሮ ሌሎች ጓደኞቻችን የሀብታሙ ፊት በላብ ሰምጥ ሲል እና ትንፋሹ ሲያጥር ጥምልምል ብሎ ከራሱ ጋር ሲታገል ስናይ ሰማይ ፈርሶ እላያችን ላይ የተደፋ መሰለን፡፡ ከዚያም መሯሯራጥ ጀመርን፡ ላልሰሙና የሀብታሙን ደህንነት በቅርብ ርቄት ለሚከታተሉ ሁሉ በየአቅጣጫዉ ስልክ በማንጫረር ተጠመድን፤ አስራት አብርሃ፡ ግርማ ሰይፉ እና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ከንፋስ ፈጥነዉ ደረሱልኝ፡፡ ለቅሶና ሰቀቀን ካደከማቸዉ ሚስቱ አና እህቱ ጋር ተያይዘን ከሶስት ቀናት በፊት ወዳሰናበተን ሆስፒታል ወደ ካዲስኮ አመራን” ሲል ጦምሯል።

“እገዳው ለምንድን ነበር?” የሚል ጥያቄ አንዳንዶች ሊያነሱ ይችላሉ። ሃብታሙና ሌሎች ጎደኞቹ(አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ ሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ ….) በሽብርተኛ ክስ ተከሰው ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት “መከላከል አያስፈልጋቸውም፣ ሽብርተኛ ስለመሆናቸው የቀረበ መረጃ የለም” በሚል “ነጻ ናቸሁ” ብሏቸው ነበር። ሆኖም አቃቢ ሕግ ይግባኝ በማለቱ ጉዳዩ ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተወሰደ።

የከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ተመልከቶ ዉሳኔ እስኪሰጥ ድረስ፣ በሰበር ችሎት “ትእዛዝ” ተከሳሾች በዉጭ ሆነው እንዲከላከሉና እስከዚያው ከአገርም እንዳይወጡ ይወስናል። ወደ ዉጭ የመዉጣት እገዳው እንግዲህ ከዚህ የተነሳ ነው።

ፍርድ ቤቱ በተለይም ዳኛው አቶ ዳኜ መላኩ፣ ይኸው ከአንድ አመት በላይ ጉዳዩን እያጓተቱ ዉሳኔ ለመወሰን አልቻሉም። በዚህም መሃል ሃብታሙ በመታመሙ፣ በቶሎ ዉሳኔ እንዲወስኑ ተማጽኖ ቀረበላቸው። ጭራሽ ከአራት ወራት በኋላ ለጥቅምት 11 2009 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጡ። ፈረንጆች “justice delayed is justice denied” ይላሉ። የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነጻ ናቸው ባለበት እና አቃቢ ሕግም ምንም የተለየ መረጃ ባላቀረበበት ሁኔታ የይግባኝ ዉሳኔ ለማሳለፍ ከአንድ አመት በላይ ጊዜ መዉሰድ ምን ያህል በኢትዮጵያ የፍትህ ስርአት እንደሌለ ፍንትው አድርጎ በድጋሚ ያሳየ ነው። የሃብታሙ በጠና መታመም፣ ይሄ እጅግ ረጅም ጊዜ የወሰደን ዉሳኔ እንዲሰጡ ዳኛውን ሊገፋፋቸው ይገባ ነበር። ግን ዳኛው የአራት ወር ቀጠሮ ሰጡ። ዳኛው ዉሳኔ እንዲወስኑ አልተፈቀደላቸውም።

የሕወሃት የደህንነት ጽ/ቤት ” ክስ ላይ ነን እያሉ በፍርሃት የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከማድረግ ይቆጠባሉ” በሚል ሂሳብ መሰለኝ ክሱን ማጓተተ የፈለጉት። ግን የሚሳካላቸው አይመስለኝም። ሃብታሙ አያሌውው፣ በሕመም ላይ ሆኖም አንገቱን አልደፋም። እነ ዳንኤል ሺበሺም ለመብት ፣ ለነጻነት ከመታገል ወደ ኋላ ያሉበትና ፈርተው የተቀመጡበት ሁኔታ የለም። ክስ አለብን ብለው አይሸማቀቁም። ጀግኖችና ለአላማቸው የቆሙ ናቸው።

ዳኛው ዉሳኔያቸው በትክክልና በሰዓቱ ቢወስኑ ኖሮ፣ ሃብታሙ እንደማንም ዜጋ፣ እግዱ እንዲነሳለት የሃኪም ወረቀት ሳያስፈልገው፣ ከአገር ወጥቶ መታከም ይችል ነበር። ዳኛው ስራቸውን ባለመስራታቸው፣ ፍትህ ባለመኖሩ. የፍርድ ሂደት በመንዛዛቱ፣ የደህንነት ክፍሉ ፍርድ ቤቶችን እንደ ኳስ የሚጫወትባቸው በመሆኑ፣ የሃብታሙ ጠበቃ፣ በሃብታሙ ሕክምና ላይ በማተኮር ብቻ ፣ ወጥቶ እንዲታከም ፣ ፍርድ ቤቱ እግዱን እንዲያነሳለት መማጸን ጀመሩ።

የነሃብታሙ ጉዳይ ከአመት በላይ ያጓተተው ዳኛ፣ ከሃኪም ደብዳቤ ይጻፍልኝ የሚል ሰበብ አቀረበ። ከሐኪም ደብዳቤ ተጽፎ ቀረበለት። “ከአንድ ሐኪም ሳይሆን ከቦርድ መሆን አለበት” የሚል ምላሽ ሰጠ። በአጭሩ የተለያዩ ምክንያቶች እየሰጠ፣ ዳኛው እስከአሁን ድረስ እገዱን ለማንሳት አልቻለም።(ለምን ከላይ እንዳሉኩት ህወሃቶች ፍቃድ አልሰጡም)

እንግዲህ ያለው ሁኔታ ይሄ ነው። ሃብታሙ አያሌው የሕዝብ ጀግና፣ በዚህ መልኩ ነው በሕወሃት የበቀልና የጥላቻ እርምጃ እየተወሰደበት ያለው።

አንዳንዶች ይሄ የዳኞች ችግር እንጂ ከሕወሃት ጋር ምንም አገናኘው ሊሉ ይችላሉ። መልሴ ቀላል ነው። ዳኛ የሚባሉት በተለይም ደግሞ ዳኜ መላኩ የተባሉት ዳኛ፣ በቀጥታ ከሕወሃቶች መመሪያ እየተቀበሉ የሚሰሩ ስለመሆናቸው ጥርጥሬ የለኝም። ለዚህም ነው፣ በቅርቡ ሹመት አግኘተው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ለመሆን የበቁት።

ሃብታሙ አያሌው፣ ይሄ አሁን እየተሰቃየበት ያለውን ስቃይና በሽታ ያተረፈው በማእከላዊ በደረሰበት ቶርቸር ነው። አሁን ደግሞ እየተሰቃየ ያለው፣ ሕወሃቶች ሆን ብለው ሕክምና እንዳይገኝ ስላደረጉት ነው።

ይህ ወጣት ብዙ ተሰቃይቷል። ሰዎቹ ፍላጎታቸው መንፈሱንም ለመሰባበር ነው። እግዚአብሄር ያስበው። ብርታትና ጥንክሬ፣ እንዲሆን ፈዉሱን ይሰጠው። የዉስጥ፣ የመንፈስ ጥናክሬንም ይሰጠው።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: