ሰበር ዜና፤ ከድንገተኛው የህወሃት ፓርላማ መወያያ አጀንዳዎች የተቀነጨበ

Parliament2ህወሃቶች ፓርላማው ከህዝብ የተመረጠ ነዉ ይላሉ። ነገር ግን አንድም ቀን ፓርላማው ለህዝብ ተቆርቁሮ ወይም ቆሞ አያውቅም።  ህወሃት ባሻው ወቅትና ባሻው ሰዓት የሚስማማዉን ህግ ሲያረቅ በማጨብጨብ ያልተሳተፉ የፓርላማ አባላት ላይ የሞት ፍርድ የሚፈረድባቸው እስኪመስል ድረስ ነው የፓርላማ አባላቱ ድጋፋቸውን የሚሰጡት። ለይስሙላ አልፎ አልፎ ረቂቅ ተቃውመናል የሚሉት የፓርላማ አሻንጉሊቶች እንኳ ቆመዉ ነው እጃቸዉን የሚያላትሙት። በጣም ይገርማል፣ያሳዝናልም። 100 ሚሊዮን ህዝብ ባላት አገር ላይ መቀላድና መሳለቅ!

ዛሬ እንደለመዱት ተጠራርተው አንድ ነገር ሊያጸድቁ እያደቡ ነው። በዚህ የፓርላማ አጣዳፊ ኛ ስብሰባ የጎንደሩ አማራ ኢትዮጵያዊ ዋነኛ አርእስት ሆኖ ይቀርባል። በህወሃት ብሔራዊ መረጃ መስሪያ ቤት አማካይነት ይቀርባሉ ተብለው ከሚጠበቁት አጀንዳዎች ውስጥ የሚከተሉት ዋነኞቹ ናቸው።

  • የፈዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ለያዘ ህጋዊ አካል ማናኛዉም የክልል መንግስት  የመታዘዝ ግዴታ አለበት፣
  • የፌደራል ፖሊስ ወይም የመረጃ ሰራተኞች የፍርድ ቤት ትእዛዝ ይዘዉ የትኛዉም ክልል ላይ የአፈና ተግባር የመፈጸም ፍቃድ እንዲረጋገጥላቸውና ይህም በአስቸኳይ ሥራ ላይ እንዲውል፣
  • ከፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተገኘ የማስገደጃ ፍቃድ በቁጥጥር ስር የሚዉል ግለሰብ ወይም ቡድን የሚታሰረው በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ብቻ ይሆናል። ክልል መንግሥታት ጥርሳቸው የረገፈ ውሾች መሆናቸ ይሰመርበታል፣
  • የነፍስ ወከፍ ትቅጥ መሳሪያን በተመለከተ የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ መሳሪዎች በህዝብ ላይና በመንግስት ላይ የሚያደርሱት ተጽእኖ በሚል የተቀመመ ዘዴያዊ ረቂቅ ለመወያያ የሚቀርብ ሲሆን አስተያየትና ጥያቄ የሚሰነዝሩ የፓርላማ አባላት የተመረጡና መረጃ የደረሳቸው ብቻ ይሆናሉ፣
  • ወልቃይትን በተመለከተ ጥቅል ሐሳብ ሲኖር ክልል አንድ እንዲሁም ክልል ሶስት”ወልቃየት ራስ ገዝ” በሚል የወልቃይት አማራን ጥያቄን የማዳፈን ሴራም በረቂቁ ሁኒታው ታይቶ የሚቀርብ ይሆናል
  • የፓርላማዉን ጥሪ ወገንተኛ ላለማስመሰልና ህዝባዊነት የሽፋን ምስል ለመለጠፍ የነ አቦይ ወልዱ ደህንነቶች ወደ ክልል ሶስት እየመጡ የሚወስዱትን እርምጃ በተመለከተ የማወናበጃ ምላሽ ለመስጠት ረቂቆች ተነድፈዋል።

ውድ ኢትዮጵያዊያን የብሐራዊ መረጃ ድርጅት ከፓርላው ስብሰባ ቀደም ባለ ሁኔታ ጥቂት የሚባሉ አማራ ወገንተኛ ኢትዮጵያዊያን ሊያነሱ ይችላሉ የሚላቸዉን ጥያቄዎች ከግለሰቦቹ አመለካከትና አንጻራዊ ሁኔታ በመነሳት ሊያቀርቡ የሚችሉት ጥያቄና ሊሰጥ የሚገባው መልስ በሚል የተዘጋጀ ጽሁፍ ቀደም ብሎ ለአፈ ህወሃቱ አባ ዱላ የሚሰጥ ይሆናል።ይህ ህወሃቶች ዘወትር ትዕይንት የሚለማመዱበትና የሚያቀርቡበት እንዲሁም እረፍት የሚያደርጉበት የፓርላማ ቲያትር ቤት መረጃ ነዉ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s