” እኛ ከህወሓት እንጅ ከትግራይ ህዝብ ጉዳይ የለንም። ዛሬም ድረስ በንፅህና ሰርተው ፎቅ የሰሩ ትግሬዎች ጎንደር መሬት ላይ አሉ። ማንም እነሱን አልነካም” የጎንደሬ ኣንደበት (ተክሌ በቀለ)

 

Tekeleጎንደሬ ህብረ ብዙ ነዉ፤የኣንድነት ኃይልም ነዉ(ዘላቂ ሰላም በፍትህ እንጂ በጉልበት ኣይፀናም)!
ጎንደር ራሱን ችሎ ክልል የሚወጣዉ የታላቅ ህዝብ ምድር ነዉ፡፡በጎንደር ትግራዋይ፤ቅማንት፤ወልቃይቴዉ፤ፈላሻዉ፤ኣማራዉ…ተከባብረዉ፤ተዛምደዉና ተዋልደዉ ይኖሩ ነበር፡፡መዋዋጥ እንኳን ቢኖር ወቅቱ በሚፈቅደዉ ሁኔታ ነበር፡፡ዛሬ በ21ኛዉ ክ/ዘመን የዘር ልዩነትን ሲምስ በኖረዉ ስርኣት ዉስጥ ግን ኣብሮ መኖር ቀርቶ በጠብ እንዲፈላለጉ እየተደረገ ነዉ፡፡ለመሬታቸዉ ሲባል እየጠፉ ያሉ ወልቃይቶች ላለፉት 26 ኣመታት ሲጮሁ ደራሽ ኣጥተዉ ኖረዋል፡፡ዛሬ ዛሬ ሰሚ ወገኖችን ያገኙ ይመስለኛል፡፡ጥያቄኣቸዉን ለመደፍጠጥ ግን የጭካኔ እርምጃ እየተሞከረ ነዉ፡፡ጥያቄዉን ከመመለስ ዉጪ የሚደረገዉ ኣፈና በሂደት የሚፈነዳ ፈንጂ እንደመቅበር ነዉ የሚቆጠረዉ፡፡የወልቃይትን ጥያቄ ለወልቃይታዉያን መተዉ ይበጃል፡፡በኔ እምነት ወልቃይት የወልቃይታዉያን ነዉ፡፡ምድሩ የኢትዮጵያ ይዞታዉም የወልቃይተዋዉያን ሆኖ የኖረ ነዉ፡፡በዚህ ኣፋኝ ስርኣት ህዝበ ዉሳኔ ማሰጠት ቢቻል እንኳ ፍትሃዊ የሚሆን ኣይመስለኝም፡፡ድምጽ ሚሰጠተዉ ማነዉ የሚለዉም ጉዳይ ላይ የሚነሳዉ ጥያቄ በመላ ኢትዮጵያ ኣዲስ ችግር የሚፈጥር ይሆናል፡፡ጥያቄ የሚነሳባቸዉ በርካታ ኣካባቢዎችና ከተሞች ይኖራሉና ነዉ፡፡
ሰሞኑን በተከሰተዉ ግጭት ጉዳዩን ለራሳቸዉ የፖለቲካ ፍጆታ ሊያዉሉት የሞከሩ ጠርዘኞችን ታዝበናል፡፡ሰርግና ምላሽ ሁኖላችዋል፡፡ቢሆንላቸዉ ኣገሪቷን በጣጥሰዋል፡፡ፍቺ የጠየቁም ጭምር ኣይተናል፡፡ኢትዮጵያን ኣለማወቅ፤ የጠባብ ቤተሰብ ኣስተምህሮት ያመጣባቸዉ ጣጣ ይመስለኛል፡፡በሂደቱ ቀጣይ ትምህርትም ተወስዶበታል ብየ ኣስባለሁ፡፡ቡድኖችም ሆነ ሰዎች ተለይተዉበታል፡፡ የሆነዉ ሆኖ ጎንደሮች ግን እንደዛ ኣይደሉም፡፡ኢርትራዉያን ወንሞቻችን በተፈጠረዉ የሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ጦርነት ሰበብ በዚህ ስረኣት በግፍም ጭምር ካገር ሲባረሩ የጎንደር ህዝብ እያለቀሰ እንጂ እንደገዥዉ ቡድን ኣባላትና ደጋፊ ነጋዴዎች ንብረታቸዉን ለመቀማት ቋምጦ የለበሱት ጫማ ስር ያለን ኣፈር እያራገፈ በስድብ ኣላባረራቸዉም፡፡ጥለዉት የሄዱትን ንብረት የገዥዉ ቡድን ቤተሰብና ኣጃቢ እንደዘረፈዉ እናዉቃለን፡፡ጎንደሬማ የተወሰኑትን ሰዎች ንብረት ባደራ ጠብቆም ቀን ሲወጣ ኣስረክቧቸዋል፡፡የዚህ ስርኣት እርሾ የሆኑ ሰዎች ከገዥዎች ጋር ፈርጀዉ የተነሱበት ብሄረሰብ እንደነበራቸዉ ይታወቃል፡፡የነዚያ ያለፉ ስርኣቶች ደገፊ ነበር በሚሉት የጎንደር፤ የእንደርታ፤የተምቤን የኣንድነት ሃይል እንዲሁም ከኦነግ የወቅቱ መሪዎች ጋር በመሆን በሸዋ ኦሮሞ ላይ የተቀነባበረ የብተናና የማዳከም ስራ ሲሰሩ እንደነበር መሬት ላይ ያለ እዉነታ ነዉ፡፡ዛሬ ፋሽኑ ኣልፎበት ሁሉም ነቅቷል፡፡ያንድነት ሃይሉ(ኢህኣዴግ ዉስጥም ያለዉ ጭምር ማለት ነዉ) ይህችን ኣገር ተሸክሞ ቆሟል፡፡ጎንደሬም በደመነፍስ ማንንም ኣያጠቃም፡፡ለኣብሮነቱ የሚጨነቅ ህዝብ ነዉና፡፡ጠባቦች ከራሱ ዉረዱ!!ባመጽና ሰላማዊ ተግል ሂደቶች ዉስጥ ልዩነቶች ይኖራሉ፡፡ህዝብ ሲያምጽ ሃይል ይጨመራል፤ምክንያታዊነት ጉልበቱ ይቀንሳል፡፡ይህ እንዳይሆን ብዙ ዋጋ ተከፍሏል፡፡ኣመጽ እንዲወለድ ይህ ስርኣት ተግቶ እየሰራ መሆኑን በርካታ ወገኖች እየተናገሩ ባለበት ሁኔታ የህዝብ ኣመጾች ሲፈጠሩ እያየን ነዉ፡፡ለዚህም ተጠያቂዉ ኣገዛዙ ነዉ፡፡የዉሸት ፕሮፓጋንዳ ጋጋታ እዚህ ቢያደርሰንም ዛሬም ድራማዉ ቀጥሏል፡፡እነዚህ ሰዎች ሰላምን እየጠበቁ ሳይሆን ኣርቀዉ እየቀሩበሯት ነዉ፡፡ዘላቂ ሰላም በፍትህ እንጂ በጉልበት ኣይጸናም፡፡
ደግሞ ሰሞኑን ከገዥዉ ቡድን ደጋፊዎች ሰፈር የተለቀቀች ዜማ ኣለች፡፡ብኣዴን ኢህኣፓ ነዉ ከኢሃኣዴግ ይዉጣ….ኣንጀቴ!! በማን ላይ ቁመሽ ማንን ታሚያለሽ ነዉ ነገሩ፡፡የዚህ ስርኣት ሞተር ማን ሆነና ነዉ???ብኣዴን ወደ ኢህኣፓነት ቢቀየር ብዙ ተምሮ ስለሚሆን በምን እድሉ! ነገሩ ወዲህ ነዉ፤በለመዱት መንገድ ማሸማቀቅ እናም ለጨቋኝነት እንደገና ማዘጋጀት፡፡ይህ ደግሞ የተገራበት መሰለኝ፤ለዉጥ ካለ መጪዉን ኣብረን እናያለን!!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: