ስደተኞች ወደ ምዕራብ አገሮች እንዳይፈልሱ ለመከላከል የአውሮፓ ህብረት ለወያኔ አገዛዝ የሰጠው የገንዘብ ስጦታ ውጤት አይኖረውም ተባለ (የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች)

 

ሐምሌ 22 ቀን 2008 ዓ.ም.
ርዕሰ ዜና
 ስደተኞች ወደ ምዕራብ አገሮች እንዳይፈልሱ ለመከላከል የአውሮፓ ህብረት ለወያኔ አገዛዝ የሰጠው የገንዘብ ስጦታ ውጤት አይኖረውም ተባለ
 ባለፈው ማክሰኞ በካይሮ ከተማ ከተመድ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሁለት ኢትዮጵያውያን በእሳት ተቃጠሉ
 በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ናቸው
 በሶማሊያ ሶስት የወያኔ ወታደሮች በአልሸባብ ተገደሉ
 ተመድ በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ የሚሰጠውን የሰብአዊ እርድታ ለጊዜው አቋረጠ
 10 የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ተመድ በደቡብ ሱዳን ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቁ
 የዚምባብየው ፓስተር ሰላማዊ የሆነ ሕዝባዊ ተቃውሞ ጠሩ
ዝርዝር ዜናዎች

Mediterranean-troubles
 ወደ ደቡብ አፍሪካም ሆነ ወደ ምዕራብ አገራት በብዛት ከሚሰደዱት መካከል ጎላ ያለ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች የሚመጡት ከኢትዮጵያ መሆኑ ሲታወቅ የስራ ዘርፎችን በመክፈት የስደተኛውን ቁጥር ለመቀነስ በወሰደው ፖሊሲ የአውሮፓው ህብረት 20 ሚሊዮን ዶላር ለወያኔ አገዛዝ የሰጠ መሆኑ ታውቋል። በኑሮ ችግር ምክንያት በ ስደተኞች አገር ለቀው መውጣታቸው የማይካድ ቢሆንም ከኢትዮጵያ የሚወጡት በርካታዎቹ አገዛዙ በሚያደርስባቸው በደልና ግፍ መሆኑ የሚታወቅ
በመሆኑ የተሰጠው ገንዝብ ስደተኞችን ለማስቀረት እምብዛም የማይረዳ መሆኑን ብዙዎቹ ይናገራሉ።

 ባለፈው ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2008 ዓም. በግብጽ የተመድ ጽ/ቤት ፊት ለፊት በእሳት የተቃጠሉት ኢትዮጵያውን ቁጥር ሁለት መሆኑን የተላያዩ የግብጽ ጋዜጦች በአምዶቻቸው ላይ አስፍረው አውጥተዋል። በእሳቱ አደጋ የተጎዱት ጥገኝነት የሚጠይቁ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውንና የሁለት ልጆች እናት የሆነች ሴት ራሱን አቃጥሎ የነበረውን ሌላ ሰው ለማዳን ባደረገችው ሙከራ ተቃጥላ የሞተች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ካይሮ የሚገኘው የተባበሩት መንግስት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት ረቡዕ ሐምሌ 20 ቀን ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በሴትዮዋ መሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለስደተኞች ብስጭትና ቁጣ የማመልከታችዎች ጊዜ መጓተና መሆኑንና ችግሩ ሊከሰት የቻለውም ቁጥራችው በጣም ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ለማብራራት ሞክሯል። በግብጽ ውስጥ በተመድ የስደተኞች ኮሚሽን በኩል የጥገኛነት ማመልከቻ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግና ሂደቱን ለማስጀመር በርካታ ወራት አንዳንዴም ዓመታትን እንደሚወስድ ይታወቃል።

 በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱት ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች አሁንም እንደቀጠሉ እየተነገረ ነው። በምዕራብ ሀረርጌ በግራዋ የወያኔ አግአዚ ጦር አባላት በተኮሱት ጥይት የተመታ አንድ ወጣት የሞተ መሆኑ ተዘግቧል። በምዕራብ አርሲ በአዳባ በዛሬው ቀን ተመሳሳይ ህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ መካሄዱ ተዘግቧል።

 በሱማሊያ የባኮል ግዛት ዋና ከተማ ከሆነው ከሁዱር 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሞራጋቤ በተባለው ቦታ ላይ የአልሸባ ኃይሎች በሶማሌ መንግስት ወታደሮችና በአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ላይ ባካሄዱት ጥቃት አምስት ወታደሮች መገደላቸውና ከአምስቱ ሶስቱ የወያኔ ወታደሮች መሆናችው ሸበሌ ኒውስ የተባለው የዜና ምንጭ የአይን እማኞችን መረጃ ዋቢ በማደረግ ገልጿል። በውጊያው ምክንያት ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን ለበርካታ ሰዓቶች
ከተደረጉ በቀላልና በከባድ መሳሪዎች የተኩስ ልውውጦች በኋላ የአልሸባብ ኃይሎች ቦታውን ለቀው የሄዱ መሆናችው ተገልጿል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሶማሊያ ውስጥ የሚሞቱና አካለ ስንኩላን የሚሆኑ የወያኔ ወታደሮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን ምንጮች እየገለጹ ነው፡:

 በናይጄሪያ ሰሜን ምስራቅ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ ኮንቬይ ላይ ጥቃት ፈጽመው ጉዳት ያደረሱ መሆናቸው ታውቋል። በጥቃቱ የተመድ የእርዳታ ሰጭ ድርጅት አባል የሚገኝበት ሶስት ሰላማዊ ሰዎች ሁለት ወታደሮች የቆሰሉ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ተመድ ወደ ቦርኖ ግዛት የሚያደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ለጊዜው ያቋረጠ መሆኑ ታውቋል። በቦኮ ሃራም ጥቃት ምክንያት ከቤት ንብረታችው ተፈናቅለው በስደተኛ ጣቢያዎች የሚኖሩት ዜጎች ቁጥር
ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሲሆን አብዛኞች ህጻናት በምግብ እጥረት እንደሚሰቃዩ ተነግሯል። ላለፉት ሰባት ዓመታ የሽብር ተግባሮችን ሲያካሂድ የቆየው ቦኮሃራም ባካሄዳቸው ተከታታይ ጥቃቶች ከ20 ሺ ሰዎች በላይ ህይወታቸውን ያጡ መሆናቸውንና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ መስደዳቸው ይታወቃል።

 በደቡብ ሱዳን እርዳታ በመስጠት ላይ የሚገኙ አስር የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል በደቡብ ሱዳን ጠንካራ እርምጃ እንዲወስድ በመጠየቅ የጋራ መግለጫ አወጡ። ኦክስፋም፤ ኬር፤ ኢንተርናሽናል ሬስኩ ኮሚቴ የተባሉት የሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የሚገኙበት ይኸው ስብስብ ባወጣው የጋራ መግለጫ የመንግስት ኃይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚወስዱት የግፍና የጭካኔ እርምጃ በተለይም ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑንና
ለችግሮችም እርዳታ ለማድረስ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን በመጥቀስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል ኃይሉን አጠናክሮ እርምጃ መውሰድ አለበት ብለዋል። በደቡብ ሱዳን ውስጥ የሚገኙ 12 ሺ የተመድ ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ የኃይል እርምጃ እንዲወስዱ የተፈቀደላችው ቢሆንም ኃይላቸውን ተጠቅመው ሰላማዊ ሰዎችን ሲጠብቁ አልታዩም ብለዋል። በደቡብ ሱዳን 4.8 ሚሊዮን ሕዝብ በምግብ እጥረትና ረሃብ የሚሰቃይ ሲሆን ይህም ከሕዝቡ ቁጥር ግማሹ ነው ተብሏል። ሁኔታው በዚህ የሚቀጥል ከሆነ እርዳታ ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ እንደሌለ መግለጫው ገልጾ ከፍተኛ እልቂት ሊከተል እንደሚችል አስጠንቋል።

 ህይወታቸውን ከአደጋ ለመጠበቅ ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙት ፓስተር ኢቫን ማዋሪሬ ሐሙስ ሐምሌ 21 ቀን 2008 ዓም በአንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለተሰበሰቡ በርካታ የዚምባብዌ ዜጎች ባደረጉት ንግግር ዚምባዊ ውስጥ ያለው ሁኔታ በጣም አሳዛኝ መሆኑን ጠቅሰው ሕዝቡ በትግሉ ነጻነቱን መጎናጸፍ አለበት ብለዋል። ከአገራቸው የወጡት በህይወታችው ላይ አደጋ በመምጣቱ መሆኑን ገልጸው ሰላማዊ የሆነው ተቃውሞ መቀጠል አለበት የሚል መልክት አስተላልፈዋል። በዚምባዌ
የታወቀው የአርበኞች ማህበር ቃል አቀባይ በመንግስት ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s