ህዝብ ወደ ሰልፍ እየተመመ ነው- እነ ደብረ ጽዩን ግን ኢንተርኔት በጎንደር ዘጉ – ግርማ ካሳ  

 

121
ዛሬ እሁድ ሐመሌ 24 ቀን በጎንደር ሊደረግ የታቀደው ሰላማዊ ሰልፍ በአስደናቂ ሁኔታ ተጀምሯል። ሕዝቡ ግልብጥ ብሎ ወደ መስቀል አደባባይ እየተመመ ነው። በማስፈራራትና በዛቻ ሕዝቡ ፈርቶ እንዳይወጣ፣ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር በሕወሃቶች እና የህወሃት አሽከር በሆኑ ብአዴኖች ሲደረግ የነበረው ጸረ-ሕዝብ፣ ጸረ-ሕገ መንግስታዊና ጸረ-ሰላም እንቅስቃሴዎች ሙሉ ለሙሉ ከሽፈዋል።

የጎንደር ሕዝብ በአገሩ፣ በምድሩ ድምጹን ለማሰማት በተነሳበት ጊዜ ሕዝቡን የወከሉ ሽማግሌዎች በሕጉ መሰረት ለባለስልጣናቱ ሰልፍ እንደሚያደርጉ ማሳወቃቸው ይታወቃል። ባለስልጣናቱ ለአሥር ቀናት ይራዘም ብለው ስለጠየቁና ለሰልፉ ዝግጅት እንዲደረግ በሚል ሐምሌ 17 ሊደረግ የታሰበው ሰልፍ ወደ ሐምሌ 24 እንደሚዞረም ተገልጾ ነበር። ሆኖም ግን የሕወሃቱ ፋና ሰልፉ እውቅና አላገኘም በሚል ርካሽ ፕሮፖጋንድ እንዲረጭ ከማድረጉ በተጨማሪ ህወሃቶችና አፍቃሪ ሕወሃቶች በየቤቱ እየሄዱ የህዝቡን ስሜት ለማዳከም ሞክረዋል።

ሆኖም ግን ሕዝቡ በነቂስ ወደ አደባባይ መዉጣቱ የህወሃት ፖለቲካ መክሰሩን የሚያመለክት ነው።

በሕወሃቱ ደብረ ጽዮን የሚመራውም ቴሌ ፣ ሕዝቡ ሕግ መንግስታዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱን በማስከበር እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ከጎንደር ዉጭ ያለው ሕዝብ እንዳይሰማው፣ ፍጹም አሳፋሪና ነገሮች ከሕወሃት ቁጥጥር ዉጭ እንደሆኑ፣ ህወሃቶች ተስፋ እንደቆረጡ የሚያመላክት ተግባራት እየፈጸሙ ነው። በጎንደር ከተማ የኢንተርኔት አገግሎት በአሁኑ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል። በጎንደር እየታየ ያለው ኢንተርኔት እንደተከፈተ መለቀቁ አይቀሬ ነው። ሰዎቹ ራሳቸውን አስገመቱ እንጂ። ተሞኙ እንጅ።
እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው የአማራው ክልል መንግስት የሚቆጣጠረው ራዲዮና ቴሌቭዥን ሰልፉ እንዳልተፈቀደና እውቅና እንዳላገኝ የተናገረው ነገር እንደሌል ነው። ሕወሃት የሚቆጣጠረው ራዲዮ ፋና ነው ሰልፉ እውቅና የለውም እያለ ሲለፍፍ የነበረው። ኢንተርኔቱንም የዘጋው ብአዴን ሳይሆን እነ ደብረ ጽዩን ናቸው። በአጭሩ ህወሃት ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል የጎንደር ህዝብን ጥቅም ሆን ብሎ በበቀል ለመጉዳት ቆርጦ እየሰራ እንደሆነ ነው።

አሁንም ለሕወሃቶች ከጎንደር ህዝብ ጋር ከሚታገሉ የሕዝቡን ጥያቄ እንዳያከበሩ እመክራቸዋለሁ።ከእሳት ጋር ባይጫወቱ ጥሩ ነው። የብአዴን አባላት ከሕዝቡ ጎን የተሰለፉበት ሁኔታ ነው ያለው።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s