አስቸኳይ ወቅታዊ መልእክት! – ነፃነት ዘለቀ

 

ነፃነት ዘለቀ (ኢትዮጵያ) nzeleke35@gmail.com

strugleአሁን ያለንበት ወቅት ለወሬና ለፍልስፍና አመቺ አይደለም፡፡ በሞቀንና በበረድን ቁጥር ከያለንበት ሸጥና ጎጥ እየተነሣን በብዕርም ይሁን በአንደበት የምንወራከብበት ወይም እንካስላንትያ የምንገጥመት ወቅት ላይ አይደለንም፡፡ ጊዜው የጣር መጨረሻ ነው፤ ዘመኑ የነፃነት ትግል ወቅት ነው፡፡ ስለሆነም ከሚያናቁረን ይልቅ የሚያስማማንን ንግግርና ሃሳብ የምንወረውርበት ሊሆን ይገባል፡፡ ከእልህና ከስድብ ይልቅ መቻቻልና መግባባት የሠፈነበት የመጨረሻ ምዕራፍ ሊሆን ጊዜው ግድ ይለናል፡፡

ከቅርብ ወራት ወዲህ የሕዝብ ትግል እየተጋጋለና በስፋትም በጥልቀትም እየጋመ የመጣበት ሁኔታ በግልጽ እየታዬ ነው፡፡ የዘመናት የተናጠል ወያኔያዊ ግፍና በደል የፈጠረውን ይህን አጋጣሚ አለመጠቀም ምን ማለት እንደሆነ ሁላችንም ልናውቀው ይገባል፡፡ ወደሚያስማሙን ነገሮች ይልቅ ወደሚያቆራቁሱን ነገሮች የሚያዘነብል ማናቸውንም ዓይነት ተፃራሪ ሃሳብና አሠራር መቀበል የለብንም፡፡ የተበዳደልን እንኳን ብንሆን፣ የተቀያየምን እንኳን ብንሆን የግል ቂማችንንና ከሀገር ኅልውና አኳያ ተራ ሊባል የሚችል የግል ቁርሾኣችንን አስወግደን ለጋራ ሀገራዊ ነፃነት በጋራ መሰለፍ ይገባናል፡፡ የማይደገምን አጋጣሚ ለበጎ ነገር መጠቀም ተገቢ ነው፡፡ ጅልነት ይብቃ፡፡

እስካሁን በከንቱ ያጠፋነው ጊዜና ኃይል በቁጭት ሊያንገበግበን ይገባል፡፡ ወደራሳችን እንመለስ፡፡ በዘርና በጎሣ፣ በሃይማኖትና በቋንቋ እየተናከስን ወያኔዎች በቀደዱልን ፈር ስንተም እነሆ 25 ዓመታትን ዘለቅን፡፡ እነሱ እንጂ እኛ የተጠቀምነው ነገር ምንም የለም፡፡ በነዚህ ቀጣፊዎች ተበልጠን ለአገዛዛቸው ብዙ አስተዋፅዖ አደረግን፡፡ ለነሱ ዕድሜ መራዘም እነሱ ካደረጉት ይልቅ እኛ ያገዝናቸው በእጅጉ ይበልጣል፡፡ “እንትና ጨቁኖሃልና በለው!” ስንባል ግር ብለን በመታዘዝ ብዙ ጥፋት አድርሰናል እነሱ ራሳቸው በሞኝነታችን እስኪስቁና ቀሪው ዓለም ጉድ እያለ እስኪታዘበን ድረስ፡፡ “የእነእንትና ሃይማኖት እንዲህ ያለ መንግሥት ሊያቆምብህ ነው” ስንባል ውሸት ይሁን እውነት ከሁለተኛና ሦስተኛ ወገን ሳናጣራ በጭፍን በመቀበል ከወንድሞቻችን ጋር ጥላቻና ቂም በቀል አትርፈናል፤ አንዳችን አንዳችንን በጥርጣሬ ዐይን እንድናይም ተገደናል፡፡ ተዘርዝርሮ በማያልቅ የቆረጣ ሥልት እየተመታን ከሰውነት በታች ሆነን እንድንቀር ተደርገናል፤ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂ ወያኔ ብቻ ሣይሆን ራሳችንም ነን፡፡

እስካሁን የነበረን አካሄድ አስቂኝና አስገራሚ ነበር – እንደጭፍግ(ትራጄዲ) ቲያትርም ሊታይ ይችላል፡፡ የአንዲት ሀገር ልጆች መሆናችንን ረስተን ነበር፡፡ የጋራ ዕጣ ፋንታ ያለን መሆናችንን ዘንግተን ነበር፡፡ አንዳችንን የሚያጠፋ ኃይል ሌላኛችንን የሚምረን ይመስለን ነበር፡፡  የሚያጣሉና የሚያጋጩን ለኛው ብለውና ከእውነት ተቆርቁረውልን ይመስለን ነበር፡፡ በዘርና በጎሣ ሲከፋፍሉን፣ በሃይማኖትና በዘውግ ለያይተው ሲያራኩቱን ለኛ ብለውና አዝነውልን ይመስለን ነበር፡፡ ከ25 ዓመታት የጅልነትና የቂልነት ቆይታ በኋላ ግን እውነቱ የተገለጠልን ይመስላል፡፡

የወለጋ ሕዝብ በወያኔ ላይ ሲያምፅ ለጎንደሩ ምንም የማይመስለው ጊዜ ነበር፤ የሸዋው ሕዝብ በዘረኛው አገዛዝ ላይ ሲያምፅ ለወለጋው ምንም የማይመስለው ወቅት ነበር፡፡ በሴቶች ላይ መቅሰፍት ሲታወጅ ወንዶች ምንም የማይመስላቸው ጊዜ ነበር፡፡ “ክርስትናን አጠፋን!” ተብሎ ሲፎከር ይህ ፉከራ ወደ እስልምናም ሊዛመት እንደሚችል የሚጠረጥር ሙስሊም አልነበረም፡፡ የአዲስ አበባ መሬት ከኗሪው እየተቀማ ለሀብታም ሲቸበቸብ የናዝሬትና የደብረ ብርሃን ነዋሪዎች ነገሬ ሳይሉት እንደሙዚቃ ያዳምጡት ነበር፡፡ ኦሮሞው ከይዞታው የመፈናቀሉ ዜና ለዐማራው የአውሮፓ ዜና ያህል ይሰማው ነበር፡፡ አንዳችም ነገር ሊጎድልበት የማይጠበቅበት አብርሃ ደስታ በኢትዮጵያዊነቱ ሰበብ ለእሥርና እንግልት ግደይ ተስፋጋብርም ለሞት ሲዳረግ ለባሌውና ለጎጃሙ ምስኪን ዜጋ የቅብጠት ያህል ይቆጠር ነበር፡፡ ተመስገን ደሳለኝና እስክንድር ነጋ ለሕዝብ መብት በመጮሃቸው ሳቢያ ዘብጥያ ሲወርዱ ለደቻሳና ለአላምረው ደንታ የማይሰጣቸው ጊዜ ነበር፡፡ ብዙ ዕንቆቅልሾችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ችግሩ ቀስ በቀስ የሁሉንም በር ማንኳኳቱ ተደረሰበትና ይሄውና አሁን የዐመፁ ቋያ እንደ ቋቁቻ በየክልሉ ይፈነዳዳ ጀመር፡፡ ይህ ደግሞ የምጡ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻው ገና ነው፤ የሚጠበቀው መጨረሻ ደግሞ እግዚአብሐየር ካልተጨመረበት እጅግ ዘግናኝ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ከእያንዳንዱ የዳመና ጉርምርምታ በኋላ ዶፍ አለ፡፡ ምንጮችና ኩሬዎች እየሞሉ አነስተኛ ወንዞችን ያጠግባሉ፤ አነስተኛ ወንዞችም አገር አቋራጭ ትላልቅ ወንዞችን ይመግባሉ፡፡ ያኔ የሚከሰተው ጎርፍ አደገኛና በቀላሉ የማይበርድ ነው፡፡ መጠንቀቅ ያን መሰሉን ጎርፍ ነው፡፡ ልብ በሉ – እኛ ካልተጠነቀቅን ደግሞ ወያኔ ስለጎርፍ የመጨነቅ ባሕርይ የለውም፡፡

እኛ ኢትዮጵያውያን በብልህነታችን እንታወቃለን፡፡ ሰው በቀደደልን የተንኮል ቦይ ገብተን በሚያስከፋ ደረጃ የተጎዳነው በዚህ ክፍለ ዘመን ብቻ ይመስለኛል፡፡ አሁን ግን ወደ ኅሊናችን እየተመለስን ነን ብዬ አስባለሁ፡፡ ዕድሜና መከራ አስተማሪዎች ናቸው፡፡ ባሳለፍናቸው የወያኔ መሪር የአገዛዝ ዘመናት ብዙ ተምረናል፡፡ ጠላትን ከወዳጅ የሚያስለይ በቂ ግንዛቤ ጨብጠናል፡፡ የበደለን ወያኔ እንጂ የተለዬ ዘር እንደሌለ ተረድተናል፡፡ ምክንያቱም ከሞላ ጎደል ሁላችንም ተጎጂዎች ነበርንና፡፡ አንጻራዊ የጥቅም መለያየት ቢኖር ሥርዓ የፈጠረው ሸውራራ የአገዛዝ ዘይቤ እንጂ ከሕዝብ የመነጨ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሕዝብና ሕዝብ መቼም ቢሆን ተለያይቶ አይለያይምና አጓቱን ሳይሆን ዐይቡን ማየት ያስፈልጋል፡፡ እናም መቼም ቢሆን ፍርዳችንና ተግባራችን ፍትሃዊ ይሁን፡፡

አሁን ማድረግ ያለብን ብዙ ነገር አለ፡፡ ጠላት ምን ጊዜም ጠላት ነውና መቼም አይለቀንም፡፡ እንኳንስ በነፃነት ትግል ወቅት ከነፃነት ማዶም ተሻሮ ብዙ ሊያምሰን እንደሚሞክር ግልጽ ነው፡፡ መፍትሔው ግን ቀላል ነው – እሱም መሣሪያና ትጥቅ ሣይሆን ዕውቀትንና ጥበብን መታጠቅ ነው፡፡ ከአንድ ታንክና ከብዙ ሚሣይል ይልቅ “ወንድምህን እንደራስህ ውደድ” የምትለዋ ዐረፍተ ነገር ብዙ ዋጋና ትርጉም አላት፡፡ ከአሥር የጦር አውሮፕላን ይልቅ “ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን፣ ነብርም ዥንጉርጉርነቱን ሊለውጥ ይቻለዋልን?” የምትለዋ ነባር መጽሐፍ ቅዲሣዊ ብሂል የበለጠ ፈውስ ናት፡፡ ከእልህና ከበቀል ስሜት ይልቅ “ወንድሜ/ጓደኛዬ ሰባት ጊዜ ቢበድለኝ ሰባት ጊዜውን ሁሉ ይቅር ልለው ነውን?” ተብሎ ለተጠየቀ ጥያቄ “ሰባት ጊዜ ሰባም ቢሆን ይቅር በለው” የተባለው የይቅር ባይነት ክርስቶሳዊ አስተምህሮ የቆረፈደን ፍቅር ያለሰልሳል፣ በጥላቻ የደነደነን ልብ ያሟሽሻል፡፡ እስካሁን የሆንነውን ሁሉ የሆንነው አንዳች የፀላዔ ሠናያት መንፈስ በመካከላችን – ወያኔን ተመስሎ – ናኝቶብን እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ፍቅራችንና መተዛዘናችን እንኳንስ ለኛ ለሌላም ይተርፋል፡፡ ስለሆነም ከስሜታዊነት ፀድተንና ከቂም በቀልና ጥላቻ ራሳችንን አስወግደን ፍትሃዊ ትግል እናካሂድ፡፡ የዘሩት መብቀሉ አይቀርም፤ ተኝተው ተፉት ወደራስ መመለሱም እንዲሁ፡፡ የደም ፍላት የትም አያደርስም፡፡ አስተዋይነት ግን ብዙ ወንዞችን ያሻግራል፡፡

ስለሆነም ከሰው በኋላ የመጡ ልዩነቶቻችንን ወደጎን እንተውና ለጋራ ኅልውናችን ተባብረን እንነሳ፡፡ ከአሁን በኋላ በዘርና በጎሣ፣ በሃይማኖትና በሰው ሰራሽ ድንበር እየተቧደንን አንተላለቅ፡፡ የጠላትን ዕቅድ ከመፈጸምና ከማስፈጸም እንቆጠብ፡፡ የተጀመረው ትግል ግቡን እንዲመታ በቀናነትና በጨዋነት በቻልነው መንገድ ሁሉ እንሳተፍ፡፡ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፣ ዕውቀት ያለው በዕውቀቱ፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ … ሁሉም በየሚችለው ተባብሮ ሳይታክትና ሳይለግም ከታገለ ነፃነታችን ቅርብ ብቻ ሣትሆን እንደሚባለውም በየበራችን ሥር ናት፡፡ እነዚህ ጥቂት አሰለጦች ይህን ያህል ሊጫወቱብን የቻሉት ልዩነቶቻችንን እያራገቡ መሆኑ ተደጋግሞ የተነገረ ግልጽ እውነት ነው፡፡

ሙስሊሙ በመጀመሪያ ሰው ነው፡፡ ክርስቲያኑ በመጀመሪያ ሰው ነው፡፡ ፕሮቴስታንቱም ሆነ ብሃኢው ወይም ሌላው በሺዎች በሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ሥር የተኮለኮለው ምዕመን ሁሉ በመጀመሪያ ሰው ነው፡፡ ዐማርኛና ትግርኛ ወይም ፈረንሣይኛና እንግሊዝኛ የሰው ናቸው እንጂ ሰዎች አይደሉም፡፡ እነዚህ ሰብኣዊ ፍጠራን ናቸው – እንደሸሚዝ፣ እንደከናቴራና እንደጫማ፡፡ በቃ – ባሕርያዊ ያልሆኑ ከትውልድ ወደ ትውልድ በደም የማይተላለፉ የመገልገያ መሣሪያዎች ናቸው፤ በመገልገያ መሣሪያ ሰበብ ደግሞ ሰብኣዊ ፍጡር ሊተላለቅ አይገባውም፡፡ ከፈጣሪ ቀጥሎ ሰው ከምንም በላይ ነው፡፡ ቋንቋ የሚኖረው ሰው ሲኖር ነው፡፡ ሃይማኖት የሚኖረው ሰው ሲኖር ነው፡፡ ባህልና ወግ የሚኖረው ሰው ካለ ነው፡፡ ሰው የሚኖረው ደግሞ ሀገር ሲኖር ብቻ ነው፡፡ አንዳንድ ዕብዶች ብዙ ነገሮችን – የራሳቸውን ቁሣዊ ሕይወት ጭምር – ከሀገር አስበልጠው ሲመለከቱ ቢስተዋሉም እውነታው ግን ይህ ነው – ሀገር ከምንም ነገር በላይ መሆኑ፡፡ መቀመጫ ሳይኖር የት ላይ ተሁኖ ምን ነገር ማድረግ እንደሚቻል ራሳችሁ አስቡት፡፡ … መፈላሰፍ ይቅር ብዬ ነበርና ይቅርታ፡፡

ከሰው ደረጃ ደግሞ ትንሽ ዘቀቅ እንበል፡፡ ኢትዮጵያ የሰዎች መኖሪያ ናት፡፡ አላለልን ሆኖ እንጂ ወርቅ ምድር አለችን፡፡ ከእሥር ቤትነት አውጥቶ ወደ ተደላደለ የፍትህና ርትዕ ሕይወት የሚመልሰን ሰው አጣን፡፡ ከነልዩነቶቻችን እንደሰው ተቀብሎ በእኩልና በፍትህ የሚያስተዳድረን ሰው አጣን፡፡ ልዩነቶቻችንን ለመጠፋፊያነት ሳይሆን ለጌጥነት የሚጠቀምበት በብልኆች የተሞላ መንግሥት አጣን፡፡ አንዱን ከአንዱ እየለዬ የሻጉራ ሳይመለከት በእኩል የሚሰበስበን ሰው እስካሁን ማግኘት አልቻልንም፡፡ እንደ ዐወሬና እንደእንስስሳ እየቆጠረን የሚገዛና የሚነዳ ጭራቅ እንጂ እንደሰውና እንደራሱ ዜጋ ዐይቶ የሚያስተዳድር ብቁ ሰው ጠፋ፡፡ ችግራችን ይህ ነው፡፡ በተረፈ አንዱ በሌላው ላይ፣ በተለይ አንደኛው ሕዝብ በሌላ ወንድም በሕዝብ ላይ ምንም ቅራኔና ጥላቻ የለውም – ይህን እናውቃለን፡፡ ችግሩ ከላይ እንጂ ከታች አይደለምና፡፡

ነፃነታችንን የምናገኘው ከፍ ሲል የተጠቀሱትን የመሰሉ ነባር ችግሮቻችንን ስናስወግድ ነው፡፡ የአንዳችን ችግር ለሌላኛችን ሊሰማን ይገባል፡፡ ያኔ ነው አንድነት የምንፈጥረውና ኃይላችን የሚፈራው፡፡ ለተናጠል ጥቃት ከተመቻቸን ግን ሁሉም ገዢ ኃይል እየተፈራረቀ እንደእስካሁኑ መቅኖ ያሳጣናል፡፡ ሀገር አልባ ሆነን መቅረት ደግሞ የምንፈልግ አይመስለኝም፡፡

ወያኔን በሁሉም ቦታዎችና በአንድ ወቅት መወጠርና ወደ ድርድር (የማይመስል አማራጭ ነው) ወይም ወደ ሽግግር መንግሥት የሚገባበትን(የምንገባበትን) ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ የትም የምትኖሩ ምሁራን ዜጎቻችን እንቅልፍ ሊወስዳችሁ አይገባም –  ሲቻል በግልጽ ያ ሳይቻል ሲቀር በኅቡዕም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብዙ መሥራት ይጠበቅባችኋል፡፡ በኋላ ሠርገኛ መጣ እንዳይሆንና የሕዝብ መስዋዕትነት በሌሎች ጭልፊቶች እንዳይሞጠለፍ መጠንቀቅ ይገባል፡፡

የነበሩንንና ወያኔ የዘራብንን ማኅበራዊ ቅራኔዎች በአፋጣኝ አስወግደን ወደጋራ መድረክ ካልገባን ከዚህ በባሰ እንጠፋለን፡፡ ላለመጥፋት አብነቱ ለመሠሪዎች ተንኮል አለመንበርከክና የተደራብንን የአፍዝ አደንግዝ ሰይጣናዊ ድር በጣጥሶ መጣል ብቻ ነው፡፡ የአዳምና የሔዋን ዘር ሆኖ፣ የአደምና የሃዋ ልጅ ሆኖ አንተ ትግሬ አንተ ኦሮሞ መባባል ከአለማወቅ የሚመነጭ እንጂ ከብልኅ አእምሮ የሚፈልቅ አይደለም፡፡ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ይባላልና እንወቅበት፡፡…

በቀደም ለት በኢሳት አንድ ዝግጅት ተከታትያለሁ – በዋሽንግተን የኢሳት ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ያዘጋጀው ነው፤ በዚያ ስብሰባ የሀገራችንን ሕዝብ የሚያኮራ አንድ ማለፊያ ትዝብት አለኝ፡፡ ከተናገሩት ሰዎች አንዱ ሌሊሳ የተባሉ በዋሽንግቶን የኦሮሞ ኮሚዩኒቲ ማኅበር አንድ አባል ይገኙበታል፡፡ የተናገሩት በዐማርኛ ነበር፡፡ ኢትዮጵያውን ካሏቸው የጋራ መሣሪያዎች አንዱ ዐማርኛ መሆኑ ስለሚሰማኝ በእጅጉ ተደስቻለሁ፡፡ የስሜቴ ምንጭ ዐማርኛ መነገሩ አይደለም – ያስደሰተኝ ጠላት የተበተበባቸውን ወጥመጥ በጣጥሰው ኢትዮጵያውያን ለመቀራረብ መቁረጣቸወ ነው፡፡ ባፉት ጥቂት አሠረት ዓመታት በውነቱ እኛን ዐይጥና ድመት አድርጎ በተናጠል ቀጥቅጦ ለመግዛት ያልተሸረበብን ተንኮል የለም፡፡ ከነዚህ ተንኮሎች አንደኛው አንዳችን ለአንዳችን እሬት መስለን እንድንታይና የወል ዕሤቶቻችን ላይም ጥላቻ እንዲያድርብን የተደረገው ትልቁ ዘመቻ ነው፡፡ የጠላትን መንገድ ተከትለን አላስፈላጊ ኩርፊያ በመፍጠር እየተገፈታተርን መኖራችንን ለሚረዳ ሰው ይህ ወርቃማ ጅምር ምን ዓይነት ዘላቂ መልካም ነገርን እንደሚወልድ መገመት አያቅተውም፡፡ ቋንቋ በሥነ ልቦና ልክፍት ተጠምደው የሚወዛገቡበት የማንነት መገለጫ ሣይሆን ከልደት በኋላ የሚገኝ (acquired or learned) ተራ የመግባቢያ መሣሪያ ነው ብዬ ከፍ ሲል በገደምዳሜ እንደጠቀስኩት ተፈጥሯዊ ሥነ ልሣናዊ ሂደቱን ጠብቆ ነገና ከነገ ወዲያ ኦሮምኛ ወይም ትግርኛ የኢትዮጵያ ኦፊሴላዊ ቋንቋ ሊሆኑ ይችላሉ – በዐዋጅና በሌላ ሕገ ወጥ “መንግሥታዊ” ተፅዕኖ ከሆነ ግን አሁን እያስተዋልነው እንዳለው ዓይነት ችግር መከሰቱ አይቀርም፡፡ ቋንቋን ከጠቀሜታው አንጻር እንጂ ከቀዳሚ ተናጋሪዎቹ ማንነትና ምንነት ጋር እያስተያየን አመለካታችንን የምንለዋውጥ ከሆነ ደግሞ የጋራ የሚባል ነገር ይጠፋና ልክ እንደባቢሎናውያን ሆነን እንቀራለን፡፡ “የኔ ያንተ ነው፤ ያንተም የኔ ነው” በሚል የአንድነት ስሜት ከተዋዋጥን ግን አንድም ችግር የለብንም፡፡ ስለሆነም ይህ ጅማሮ በጣም ድንቅ ነውና ሁላችንም ከያለንበት የግል ዓለም እየወጣንና በተቻን መጠን  ግማሽ ግማሽ መንገድ እየተጓዝን መሀል ላይ እንገናኝ፡፡ በቃ፡፡ ያኔ ችግራችን ሁሉ ታሪክ ይሆናል፡፡

 

በጥቂቶች የተማረከው የኢትዮጵያ “አስደናቂ” እድገት (ዶ/ር አክሎግ ቢራራ)

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

(ከቀለም ቀንድ ጋዜጣ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ)

የቀለም ቀንድ

1. ኢትዮጵያ ላለፉት ዐሥርት ተከታታይ ዓመታት ባለሁለት አሃዝ እድገት ማስመዝገቧ በመንግሥት በኩል ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ በመንግሥት በሚገለጸው አሃዝ ባይስማሙም ዓለም አቀፍ ተቋማትም እድገት መኖሩን ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ ተቋሞች መረጃውን ከየት ያገኛሉ፤ እንዴት ያረጋግጣሉ፤ ተመሳሳይ የሆኑ አገሮች አሉ፤ ማለትም በመረጃ በኩል በመሬት በሚ ታየውና አበዳሪዎችና ደጋፊዎች በሚሉት መካከል?

ዶር/አክሎግ

Dr. Aklog Birara

ይኼን ቁልፍ ጥያቄ ለመመለስ መጀመሪያ ሕዝብ የእድገቱ ውጤት ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው መብነቱና ነጻነቱ በሕግ አስተማማኝ ሲሆን ብቻ ነው በሚለው እንስማማ። በተደጋጋሚ በማስረጃ እንዳሳየሁት፤ በነጻነትና በፍትሃዊ እድገት መካከል ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አለ። ነጻነት የሌለው ሕዝብ የንብረቱ ብቻ ሳይሆን የህይወቱ ባለቤት ሊሆን አይችልም። ነጻነት የሌለው ሕዝብ በቀላሉ ለኪራይ ሰብሳቢዎች፤ ለጉቦኞች፤ ለሙሰኞች፤ ከሃገር በገፍ ኃብት ሰርቀው ለሚያሸሹ ክፍሎች ሰለባ የሚሆነው ድምጽና ነጻነት ስለሌለው ነው። በሌላ አነጋገር ሕዝቡ በራሱ የተፈጥሮ ኃብት ተገዥ እንጅ አዛዥ አይደለም። የመሬት ነጠቃ ይኼን ሃቅ በየቦታው ያሳያል። ወደ ጥያቄው ስመለስ፤ ስለ እድገታዊ መንግሥት ሚና በአጭሩ ለማቅረብ እገደዳለሁ። ለእኔ፤ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት ማለት የጋራ አገርን የተፈጥሮ፤ የሰውና ሌሎች ጥሪቶችንና ኃብቶችን ኃላፊነትና ዘላቂነት ባለው መልክ ተጠቅሞ የጋራ ህይወትን (የሁሉምን ዜጎች)፤ የግልና የጋራ ኑሮን ማሻሻል ማለት ነው። የአገር ጥቅላላ ገቢ አድጓል የሚለው ብቻውን የኑሮን መሻሻል አያሳይም። ለምሳሌ፤ ድርብ አሃዝ እድገት አለ የሚለው ለኦሞ ሸለቆ ወይንም ለጋምቤላ ሕዝብ ትርጉም የለውም። ምክንያቱም፤ በአብዛኛው ይህ ሕዝብ የራሱ የተፈጥሮ ኃብት እድገት ውጤት ተጠቃሚ አልሆነም። በኢትዮጵያ ሕዝብን ያማከለአና ዋና ኢላማ ያደረገ እድገት የለም። በሌላ አነጋገር፤ ፍትሃዊ የእድገት ውጤት ስርጭት የሚባል ነገር ኢትዮጵያ የለም። ነጻነት ከሌለ ምንም አይታሰብም። የእድገቱ ውጤት ስርጭት ፍትሃዊ ነው ሊባል የሚችለው በተቻለ መጠን ሁሉም ዜጎች መብታቸውና ነጻነታቸው ተከብሮ የእድገቱ ተጠቃሚ ሲሆኑ ብቻ ነው። እድገት ዘላቂነት የሚኖረውም ሕዝብን በሙሉ ለማሳተፍና አቅሙን ለማጎልመስ ሲቻል ነው፤ ነጻነትና ሙሉ ተሳትፎ ለፍትሃዊ እድገት መሰረት ነው የምለው ለዚህ ነው። የፍትሃዊነትና የዘላቂነት መሰረት ያለው እድገት በተፈጥሮና በሌላ ችግር ወቅት (ለምሳሌ የተፈጥሮ ርሃብ) በራሱ ሊተማመንና ተመልሶ ሊያንሰራራ ይችላል (Resliency) ይኖረዋል። ራስን በራስ የመጠገንና የማሻሻል አቅም ይኖረዋል። አለያ፤ እድገቱን ለመቀጠል መበደር አስፈላጊ ይሆናል። ተበድሮ መክፈል የሚባል ነገርም አለ። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ሕዝበ ኢትዮጵያ ከዳር እስከ ዳር ለለውጥ ተንቀሳቅሷል

Unity - satenaw

ባይነቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በሰሜን ጎንደር በወያኔና በአማራ ሕዝብ መካከል ፍጥጫው እየተባባሰ ነው፥
በመሃል ኢትዮጵያ፥ በአርሲ፥ በባሌ፥ በሓረር እና በቦረና የኦሮሞ ወጣት ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ ላይ ነው፥ በደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለወንበዴ መንግሥት አንገዛም  ።
ዘረኛው የወኔ መንግሥትም በበኩሉ ሕዝብ ማሸበሩንና ሰላማዊ ዜጎችን ማዋከቡን ተያይዞታል፥
ከሰሜን ጎንደር ወደ መሃል ኢትዮጵያ ኦሮምያ እና ወደ ደቡቡ ኢትዮጵያ የትግሉ ግለት እየተዛመተ፥ የለውጥ እሳት በኢትዮጵያ እየተቀጣጠለ ነው።
ጀግናው የኦሮሞ ልጅና ጀግናው አማራ ሕዝብ፥ የፋሺስት ወያኔ ሥርዓት በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለው በደል በቃ በማለት፥ ዘርና ኃይማኖት ሳይለየው በአንድነት ሊታገል፥ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር መቃብር ላይ የነጻነት ችቦ ሊያበራ ቆርጦ ተነስቷል።
በኦሮሞ ሕዝብ የተጀመረው የመረረ አንገዛም ባይነት ጎንደር ላይ ወደ ለየለት ፍልሚያ ተቀይሮ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ የወያኔን ዙፋን እያንቀጠቀጠው ይገኛል፥
ኢትዮጵያውያን ለአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ ከእያቅጣጫው የትግል ጥሪ እያቀረቡ ነው፥ ጠላት ወያኔን አቅፎ፣ ደግፎና፣ ሸፋፍኖ የያዘው የአዲስ አበባ ነዋሪ፥ ወጣቱ፣ ተማሪውና ወዛደሩ ተባብሮ አራት ኪሎ ላይ የተንሰራፋውን የወያኔ መንግሥት ገልብጦ በመጣል ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ያስተላልፋሉ፥
Gondar Ethiopia

ብአዴን በህወሃት እያስገደለ እና እያስገዛን የሚኖረው እስከ መቼ ነው? (አንተነህ ገብረየ)

Ethiopia Satenaw

እንደ መግቢያ፦ኢህአፓን ማን መሠረተው? ብለን ስንጠይቅ ዛሬ ዛሬ ላይ ብዙዎቻችን የተግባባንበት ሀሳብ ነው ብየ አምናለሁ።በአፄ ኃይለሥላሤ ዘመነ መንግሥት የመጨረሻዎቹ ዓመታት አገዛዙ እየዛለና እየተንዘላዘለ ሲመጣ በርከት ያሉ ሥልጣን ናፋቂ ድርጅቶች ተፈጥረዋል ከነዚህም ዋና ዋናዎቹ፦ጀበሃ፤ኦነግ፤ሻእብያ፤ህወሃት፤መኢሶንና ኢህአፓ ይገኙበታል።እነዚህ ሁሉም ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተመሠረቱ ድርጅቶች ነበሩ አሁንም ናቸው። መኢሶንና ኢህአፓ ሕብረ-ብሔራዊ ሆነው የተደራጁ እና ኢትዮጵያን ከፊውዳላዊ አገዛዝ ነፃ አውጥቶ ዲሞክራሲያዊ ሥርአት ለመትከል በሚል ሲሆን ሌሎች ደግሞ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ይዛናለች በማለት ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለመውጣት ወይም ለመገንጠል አልመው የተነሱ ነበሩ።እነዚህ ድርጅቶች ለአርባና ሃምሳ ዓመታት ያህል ሲታገሉ የተወሰኑት በለስ ቀንቷቸው ኤርትራን ከኢትዮጵያ በመገንጠል አዲስ አገር መሥርተዋል ገሚሶቹ ደግሞ የቀረውን የኢትዮጵያ ግዛት ተቆጣጥረው እየገዙን ይገኛሉ።

በለስ ያልቀናቸው አሁንም በትግል ላይ ናቸው።በሁሉም ዘንድ ጡረታ መውጣት የለም ወይም አይታሰብም።ሥልጣን ያዙም አልያዙም ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው አንድ ጉምቱ አመለካከት አላቸው ግትሮችና ጀብደኞች ከእኛ ወዲያ ለአሳር የሚሉ ደረቆችና ርህራሄ የሚባል ያልፈጠረላቸው ዜጎቻቸው በደም ጨቅይተው ሥልጣን መያዝ ወይም በሥልጣን ለመኖርና ዜጎቻቸውን በኃይል ጨቁነውና ረግጠው ለመግዛት የሚመኙ ናቸው።የቀኝ ዘመምነትና የግራ ዘመምነትን አስተናግደዋል።ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ግን የሁሉም ዝንባሌዎች ካርድ በኪስ ሆኖ ሁሉም እንደ ሚመቻቸው ከሚለጠፉበት ተለጥፈው እናገኛቸዋለን።የአሥመራን ሆነ የአዲስ አበባ ገዥዎችንና በሕዝባቸው ላይ እየፈፀሙት ለሚገኘው አረመኔያዊ ተግባር መዘርዘር ለእያንዳንዱ ከሚገባው በላይ ሞልቶ እየፈሰሰ ስለሆነ ከዚህ ላይ የመግቢያ ፁሑፌን ቋጭቸ ወደ ተነሳሁበት አርእስት ልመለስ።

ከላይ በመግቢያየ ለመጠቆም እንደሞከርኩት ኢህአፓን ማን መሠረተው መቸ ተመሠረተ?የሚለውን ስንመለከት ኢህአፓን የመሠረቱት ትውልደ ኤርትራውያንና ትግራውያን ለመሆናቸው ምንም ማቅማማት የሚያስፈልገው አይደለም ምን አልባት ጥቂት የሌላ ዘውግ ያላቸው ሊኖሩበት ይችላሉ ስውር ደባውን ግን ያውቁታል ማለት አይቻልም።ዓላማው ለምን ነበር ሲባል አንዳንዶቹ በየዋህነት ፊውዳላዊ ሥርአቱን በማስወገድ አዲስ ሥርአት እንመሰርታለን ብለው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ በብሔር ለተደራጁት ድርጅቶች ነዳጅ ሆኖ የሚያገለግል ኃይል በመሐል አገር ለመፍጠርና ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ይዛን አለች ከሚሉት ነፃ ለመውጣት እንደሆነ አሁን ያለው ገሃድ(ሀቅ)በግልጽ እያሳየን ነው።ወደ ኋላ ላይ ዘር ማንዝራታቸውን እየቆጠሩ የተጠቃለሉ ሲሆን ተሸውደናል የሚሉት ደግሞ በቁጭትና በፀፀት የሚታገሉ አሉ አብዛኛዎቹም በብስጭት አልኮሆል በመጠጣት ራሳቸውን በማጥፋትና ከተራ ሰውነት ወጥተው የሜገኙ አሉ።

ኢህአፓ አባላቱን በውስጡ በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት ከመበተኑ በፊት ትግሉን የሚቀጥለው ከኢህአፓ አብሮ ትግሉን እንዲቀጥል የማይችለው ወደ የሚፈልገው እንዲሄድና ጥሪ ሲደረግለት እንዲሰባሰብ በሚል አባላቱን እንዲበተኑ ሲያደርግ ሪጅን ሦስት የነበረው ኃይል ግን የወሰደው ርምጃ ቀደም ሲል አንጃ በመፍጠር ማስፈራራት በኋላ ደግሞ ወደ ትግራይ መሄድና ህወሃትን መማፀን አማራጩ አድርጎ መውሰድ ነበር። በዚህም መሠረት ህወሃት በራሱ አምሳል ነገር ግን ሕብረ-ብሔራዊ ሽፋን ያለው ኢህዴን የሚባል ቅርንጫፍ ፈጥሮ የወረራ  አድማሱን ለማስፋት እድል አጋጠመው።ህወሃት ይህን ኃይል በሚፈልገው መንገድ ተጫውቶበታል ዛሬም ስሙን ብአዴን ብሎ በመሰየም በአማራ ሕዝብ ስም አደራጅቶ በአማራ ሕዝብ ላይ ህልቆ መሳፍርት የማይገኝለት መጠነ ሰፊ ዘር የማጥፋት፤ዘር የማጽዳትና የሀብት፤የመሬት ወረራውን ቀጥሎበት ይገኛል።

ብአዴን በአማራ ስም ይደራጅ እንጅ በዚህ ድርጅት ውስጥ ትርጉም ያላቸው ወይም አማራ ነን ብለው የሚኮሩ የአማራውን ብሔር ሕዝብ ብሶትና እንግልት ብሶቴ ነው ብለው የሚሰማቸው የሚያማቸው የአማራው ብሔር ተወላጆች የሉበትም። በዚህ ሁኔታም እነሆ ለ26 ዓመት ብአዴን ራሱ እየተገዛ የአማራውን ሕዝብ እያስገዛ ሊቀጥል ራሱን ያመቻቸበት ወቅት ላይ እንገኛለን።የአማራው ብሔር ሕዝብ ይህን የህወሃት/ብአዴን አምባገነናዊ እና ጨፍጫፊ አገዛዝ ተቀብሎ እልቂቱን መርጦ ይቀጥላል ወይስ ሌላ አማራጭ አለው? ብለን ስንጠይቅ መልሱ አንድና አንድ ሲሆን ነገር ግን አማራ ሆነው አማራነታቸውን የካዱ ብአዴን እንዳደረገው የህወሃት ስርአት ሲወገድ አማራው አሁን በህወሃት የሚደርስበት ግፍና በደል አይነት ተመሳሳይ ውስብስብ ችግር ውስጥ እንዲገባ የሚያደርጉ አመለካከት ካላቸው ከሃዲ ድርጅቶች ጋር በመቧደን አማራው በአማራነቱ ተሰባስቦና ተደራጅቶ እንዳይታገል የሚያደርጉትን ጣልቃ እንዳይገቡበትና በአማራው ማእቀፍ ውስጥ ሆኖ በመታገል አማራውን ሆነ መላ ኢትዮጵያን ሊታደግ እንደሚችልና ኢትዮጵያን አሁን ከምትገኝበት ማእጥ አውጥቶ ወደ ኢትዮጵያዊነቷ እንደሚመልሳት ደፍሮ መናገር ይቻላል።

ህወሃት ከጠባብነቱ የተነሳ በደርግ ዘመነ መንግሥት ወቅት ከራሱ ከህወሃት ውጭ ማንም የትጥቅ ትግል ለማካሄድ በትግራይ መሬት መንቀሳቀስ እንደማይችልና ለማድረግ የሞከሩትን ጦርነት ከፍቶ ማስወጣቱ የሁላችንም ትውስታ ነው።ህወሃት ከትግራይ ምድር ዘሎ ወደ አማራው ምድር ሲያቀና የበጌምድር ጠቅላይ ግዛት ሕዝብ በሩን ከፍቶ እንደማያስገባው ለህወሃት ግልጽ ነበር።ነገር ግን በደርግ ውስጥ የነበሩ የህወሃት ሰርጎ ገቦች(ትግሬዎች)ህወሃት ሊገባበት ባቀደው አካባቢ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የሚኖረው ሕዝብ የኮሚሳርያት አዛዥ በነበረው ሻለቃ ገብረህይወት አማካኝነት ትጥቅ እንዲፈታ ተደረገ።ህወሃት ተከዜን ተሻግሮ ወደ በጌምድር ለመግባት ፈተናው ቀላል አልነበረም ትጥቃችን አንፈታም ያሉት ጀግኖች ህወሃትን 3ወር ከተከዜ ማዶ ገትረው አቆይተውታል።ያልተደራጀ በግብርና ኑሮ የተሰማራ ሕዝብ በመሆኑ ምክንያት ህወሃትን ወደ ነበረበት መመለስ አልተቻለም ህወሃት ተከዜን ተሻግሮ የበጌምድርን መሬት ለመርገጥ ቻለ።ከዚያም ህወሃት የአማራውን ክልል ሊመራ የሚችልበት ሁኔታ ጠባብ ስለነበር በአምሳሉ ቀርጾ ወደ አማራው ክልል ያስገባውን ብአዴን/ኢህዴንን እያስመራ ከበስተኋላ ደግሞ የራሱን ሕዝባዊና ወታደራዊ ዝግጅት እንዲያጠናክር ሰፊ እድል አጋጥሞታል።

ከጎልጉል ድሕረ-ገጽ እንደምንረዳው ድርጊቱን በስፋት ለማሳየት የተቻለ ሲሆን አሁንም ብ.አ.ዴ.ን የህወሃት አሽከርነቱን አሽቀንጥሮ በመጣል ከአማራ ሕዝብ እስካልወገነ ድረስ ህወሃት እንደ እባብ ራስ ራሳችን እያለ ሊያኖር ስለማይችል ብ.አ.ዴ.ን ከጌታው ከህወሃት ጋር በሕዝባዊ ማእበል መጠረግ አለበት ትግላችን ይጠንክር።

ፍ/ቤቱ ያለ ይግባኝ የራሱን ትእዛዝ ራሱ ሻረ፤ (ዳንዔል ሺበሽ)

Habtamu 34
ሀብታሙ አያለው

ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2008 ዓ.ም፡፡

በሐብታሙ ጉዳይ ላይ ለዛሬ ቀጠሮ ነበር ፤ በዛ መሰረት በሰዓቱ በቦታው የተገኙይ የሐብታሙ ቤተሰቦች እና ጓዶቹ ዛሬም መልስ ሳያገኙ ተመልሰዋል ።

የአቃቤ ህግን በቃል ይከራከራል በተባለው መሰረት ዛሬ ጉዳዩ ለመስማት ፍርድ ቤት ቢቀርብም ችሎቱ በጽሁፍ እንዲቀርብለት ለሐምሌ 22 ዳግመኛ ቀጠሮ ሳቷል።

የአቶ ሐብታሙ በቶሎ ወደ ውጭ ሄዶ አስፈላጊው ህክምና ካላገኘ በሸታው ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያደርሰው ዶክተሩ የፃፈለት እና ፍርድ ቤቱ በጠየቀው መሰረት የሆስፒታሉ ቦርድ (3 ዶክተሮች ) የፈረሙበት ወረቀት ቢቀርብም ጉዳዩ ምንም ተስፋ ወደሌለው ወደ ዳግም ቀጠሮ መዘዋወሩ አገዛዙ አቶ ሐብታሙ ላይ የሞት ፍርድ እንደፈረደበት እና ቀኑን እየቆጠረለት መሆኑን መቀበል ግድ እየሆነብን መቷል !!

የሰርዓቱ አባላት እና ደጋፊዎች ለሽርሽር እና ለገበያ በዓለም ይዞራሉ ፤ ሃገር ደበረን ብለው ለ2 ሳምንት ከሃገር ይወጣሉ፤ ለተለያየ ህክምና ከመንግስት ድጋፍ በማግኘት ወደ ውጭ እየሄዱ ይታከማሉ ። አቶ ሐብታሙ በህመም እየተሰቃየ ህክምና እንኳን ማግኘት አልቻለም ።

አቶ ሐብታሙ አልሰረቀም ፤ ሰው አልገደለም ፤ ሀገር አልሸጠም ፤ አቶ ሐብታሙ ግብ አንድ ትልቅ ጥፋት አጥፍቷል ። ሐገሬን ፤ ወገኔን ፤ ነፃነቴን ብሏል ። ይህ የሀገር እና የወገን ልክፍት ደግሞ ዛሬ ላለበት ደረጃ ዳርጎታል ።

አቶ ሐብታሙ ለዚህ እየከፈለ ላለው መስዕዋትነት የኢትዮጵያ ህዝብ ውለታውን በምን ይመልስለታል ? ዛሬ ከሐብታሙ ጎን ቆመን ህይወቱን ካላዳንን ፤ ዛሬ የ4 ዓመቷን የህፃን አሜንዳን አባት ካላዳንላት እኛስ በታሪክ ተጠያቂ አንሆንም ? መቼ ነው ግን ለኛ ነፃነት ብለው በየእስር ቤቱ እና በየሆስፒታሉ ለሚማቅቁት ወገኖቻችን በሚሊዮን ከጎናቸው ቆመን የምንታየው ? እኛስ ድርሻችን ምንድነው !!

በበኩሌ ወያኔ በአቶ ሐብታሙን እንዲሞት መፈለጉን ዛሬ አረጋግጫለሁ ! ዳኛ ዳኜ መላኩም ህሊናቸውን ሸጠው በዚህ ጉዳይ ላይ ድርሻቸውን እየተወጡ ነው ከማለት ወደኋላ አልልም ! ከዛሬ ጀምሮ ሌላ አማራጭ ካለ መፈለግ ነው እንጂ በ22 ለሚንነው ምንም አልጠብቅም ።

 

“ከዚህ በላይ ምን ትሆናለህ? ክተት! አትነሳም እንዴ?” አለ ዘረኛው ኒዮ ፋሺስት ዶናልድ ትረምፕ በሪፑብልካኑ ጉባዬ ላይ 

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

በጁሊየስ ቄሳር ተውኔት ውስጥ የቄሳርን ሞት ተከትሎ ጣሊያንን ሽባ የሚያደደርግ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊከሰት እንደሚችል ሸክስፒር የማርክ አንቶኒን ገጸ ባህሪነት በመላበስ እንዲህ በማለት አስጠንቅቀው ነበር፡

“…እናም አቴ በእርሱ በኩል ከጋነም እሳት ሆኖ በመምጣት የቄሳርን መንፈስ በመላበስ የንጉሱን ድምጽ በመያዝ ለበቀል ተዘጋጅቷል፡፡ እናም እናልቅስ፣ እናም እነዚህን የጦርነት ውሾች እናስወግድ“ ብለው ነበር፡፡

 ባለፈው ሳምንት በሬፐብሊካን ጉባኤ ላይ በመገኘት ዶናልድ ትረምፕ የርፑብልካኑ እጩ ፕሬዚደንት “ለዚህ የስልጣን ቦታ ብቁ የሆንኩት መሲህ እኔ ብቻ ነኝ“ በማለት በቁጣ ለበቀል እና ለአስከፊ አደጋ መከሰት ሽንጡን ገትሮ ጮኸ!

Trump RNC jpg

የባዶ ጩኸት ባለቤቱ ትራምፕ የሬፐብሊካን ፓርቲ እጩ ፕሬዚዳንት ሆኖ መሾሙን ከተቀበለ በኋላ ድምጹን ከፍ በማድረግ የውሻ ፊሽካውን እንዲህ በማለት ነፋ፡

“እኔ የእናንተ ድምጽ ነኝ፡፡ ለሁላችሁም መልዕክት አለኝ፡ በፖሊሶቻችን ላይ የተፈጸመው ጥቃት እና በከተሞቻችን ላይ እየተደረገ ያለው ሽብርተኝነት ህልውናችንን በአስጊ ሁኔታ ላይ ጥሎት ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እያሰቃዩ ያሉት ወንጀሎች እና የኃይል ጥቃቶች በቅርብ ጊዜ ውስጥ ፍጻሜ ያገኛሉ፡፡ እ.ኤ.አ ከጥር 20/2017 ጀምሮ የደህንነት ዋስትናችን ድሮ ወደነበረበት ሰላማዊ ቦታው ይመለሳል፡፡

በዚህ ዓመት የሀገሪቱን ወሰን በማቋረጥ የገቡ የአዲስ ሕገ ወጥ ስደተኞች ቁጥር እ.ኤ.አ በ2015 ከነበረው ጠቅላላ ብዛት በልጧል፡፡

በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ሕገ ወጥ ስደተኞች በህዝባችን ደህንነት እና በሀገሪቱ ሀብት ላይ የሚያስከትሉት አሉታዊ እንደምታ ሳይታሰብ እንዲገቡ እየተደረጉ ነው፡፡

የውጭ ንግድ ክፍተታችን 800 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ እስቲ ይህንን አስቡ፡፡ ባለፈው ዓመት ብቻ 800 ቢሊዮን ዶላር፡፡ ይህንን መወሰን አለብን፡፡

በአሁኑ ጊዜ በጀቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል፡፡ ፕሬዚዳንት ኦባማ የብድር እዳችንን በእጥፍ ደረጃ በማሳደግ ከ19 ትሪሊዮን ዶላር በላይ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ እንዲሁም ዕዳው ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡

መንገዶቻችን እና ድልድዮቻችን እየተሰነጣጠቁ ነው፣ እንደዚሁም ሁሉ የአውሮፕላን ማረፊያዎቻችን የሶስተኛው ዓለም ሀገሮች ካሉበት ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

በሊቢያ የሚገኘው እና በዓለም ላይ የአሜሪካውያን የኩራት ቀንዲል የነበረው የቆንስላ ጽ/ቤታችን በእሳት እንዲጋይ ተደርጓል፡፡

አሜሪካ ደህንነቷ ተቃውሷል፣ እንደዚሁም ኦባማ ሂላሪ ክሊንተንን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሚኒስትር እንድትሆን ከወሰነ በኋላ ዓለም የተረጋጋች አይደለችም፡፡

የሂላሪ ክሊንተን ትሩፋት የሚከተሉት ናቸው፡ ሞት፣ ውድመት፣ ሽብርተኝነት እና ደካማነት፡፡

ትራምፕ  “የእናንተ ድምጽ ነኝ” በማለት ድምጹን ከፍ አድርጎ ጮኸ፡፡“  (ማለቱም የትራምፕ ድምጽ የእግዚአብሄር ድምጽ ነው፣ የእግዚአብሄር ድምጽ ደግሞ የሕዝብ ድምጽ ነው!)

በክሌቬላንድ ርፑብልካን ጉባኤ ላይ  ባደረገው ንግግር ትራምፕ በእውነት እና በእውነታ፣ በአሜሪካ ሕገ መንግስት፣ በጨዋነት ላይ በሂላሪ ሮድሀም ክሊንተን ላይ ቆሻሻ ፖለቲካ በማራመድ የቃላት ጦርነትን አውጇል፡፡

በተግባር ደግሞ ትራምፕ የእርስ በእርስ ጦርነትን አውጇል፡፡

በሬፐብሊካን ጉባኤ ላይ የተደረገው የጦርነት ጩኸት ሂላሪ ክሊንተንን አለህግ ትሰቀል የሚል ነበር፡፡

ትራምፓውያን ጥላቻን ባዘለ፣ ንዴትን በተላበሰ መልኩ የድንጋይ “አጥሩን ገንቡ” በማለት ጮኸዋል፣ አቃስተዋል! (ግንቡም ከውጭ ዓለም የሚመጡትን የነጭ ዘር ያልሆኑትን አሜሪካ አንዳይገቡ ለማድረግ ነው፡፡)

ይህ ቀን የሬፐብሊካን ጉባኤ የምጻት ቀን ነበር፡፡
የትራምፕ አማካሪ እና የሀምፕሻየር ግዛት ተወካይ ላንቃው እስኪነቃ ጮኋል! እናም ሂላሪ ክሊንተን የሀገር ክህደት ወንጀል የፈጸመች እና በከፍተኛ ደረጃ መጠየቅ ያለባት ሰው ናት በማለት የሞት ቅጣት ፈርዶባታል፡፡ በቀጣይነትም እንዲህ በማለት ጨመረ፣ “እኔ እስከማውቀው ድረስ ይህ ድርጊት የሀገር ክህደት ጉዳይ ነው፡፡ እናም ለሀገር ክህደት ቅጣቱ አሁኑኑ በታጣቂ ወታደሮች በጥይት መደብደብ ወይም ደግሞ በኤሌክትሪክ አቃጥሎ መግደል ነው፡፡“ 

“ወንድም” ቤን ካርሰን ስለፖለቲካ ምንም ዓይነት እውቀት የሌለው እና አቅመቢሱ ጨካኝ የሂላሪ ክልንተንን ስም ካጠለሸ በኋላ እንዲህ የሚል ተመሳሳይ ንግግር አሰምቷል፣ “ከባርነት ዘመን ወዲህ የኦባማ የጤና አጠባበቅ ድንጋጌ በሀገራችን የተፈጸመ የመጨረሻ መጥፎው ነገር ነው“ ብሏል፡፡ 

ካርሰን ሂላሪ “የጽንፈኞች መመርያ/Rules for Radicals” እየተባለ የሚጠራው መጽሐፍ ደራሲ የሳውል አሊንስኪ ተከታይ ናት በማለት አውጇል፡፡ በመጽሐፉ የመቅድም ገጽ ላይ የእራሱን ግዛት የያዘውን እና ዋነኛ ጽንፈኛ ለሆነው ለሉሲፈር (ዳቢሎስ) እውቅና ሰጥቷል፡፡ ስለሆነም ለእነርሱ ተከታይ አርአያ የሆነችን ሰው እና ለሉሲፈር እውቅና ለምትሰጥ ሰው ለፕሬዚዳንትነት ለመመረጥ መፍቀድ ይኖርብናልን? (በፍጹም! ካርሰን የውሸት የሬፐብሊካንን ፖለቲካ በማነብነብ በየትኛው የአንድሮማ ጋላክሲ ፕላኔት አብዛኛውን ጊዜውን እንደሚያጠፋ የማውቀው ነገር የለም፡፡)

ሳውል አሊነስኪ በድህረ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ የአፍሪካ አሜሪካውያንን የመኖሪያ አካባቢ እና የደኃ ማህበረሰቦችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከችጋጎ እስከ ኒዮርክ፣ ከዚያም እስከ ሎስ አንጀለስ ድረስ ማህበረሰቡን ሲያደራጅ እና ሲያስተባብር የነበረ ታሪካዊ ሰው ነው፡፡

የአሊንስኪ “የጽንፈኞች መመርያ/Rules for Radicals” መንገድ ጠራጊ መጽሐፍ ማህበረሰብን ለማደራጀት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚቆጠር መጽሐፍ ነው፡፡

አሁን በህይወት የሌለው እና የወግ አትባቂ ምሁራን ምሳሌ የሆነው ዊሊያም በክለይ (ለአዲሱ የአሜሪካ ወግ አጥባቂነት መሰረት ለመጣል ብቸኛ የሆነው ሰው) በአንድ ወቅት አሊንስኪን “እጥፍ ድርብ ተደናቂ የሆነ እና የአደራጅነት ልህቅናን የተጎነጸፈ ሰው“ በማለት አወድሶታል፡፡

ግልጽ በሆነ መልኩ ካርሰን ጭካኔን በተሞላ መልኩ ሂላሪ ክሊንተንን እንደ ሰይጣን፣ ጽንፈኛ  ኢሞራላዊ የጾታ ግንኙነት ፈጻሚ አሜሪካዊ አድርጎ የመቁጠር ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡

ከሬፐብሊካን (ሀሳብ የለሾች አምሮ ቢስ አላልኩም) መሪዎች ስም ዝርዝር መካከል ውስጥ ያለ እና የሂላሪ ክሊንተንን ስም በማጠልሸት ላይ የሚገኘው ያገኘውን ምግብ ሁሉ አግበስባሹ ሆዳም እና በሕግ እና ስርዓት ዕጩው (ትራምፕ) ስም ሆኖ ሂላሪን በመወንጀል፣ ከስብዕና ውጭ ለማድረግ እና ስም በማጠልሸት ላይ የሚገኘው የኒው ጀርሲ ገዥ የሆነው ክሪስ ክሪስቲ አንዱ እና ዋናው ነው፡፡

ክሪስቲ እንዲህ በማለት እንደ አቡጀዲ ተቀዷል፣ “በሶሪያ እና በሊቢያ ውስጥ ጥፋተኛ፣ በቻይና እና በሶሪያ ውስጥ ጥፋተኛ፣ እንዲሁም በዚህ በሀገር ቤት ውስጥ ደግሞ የአሜሪካንን ሚስጥሮች ለግሏ የማድረግ አደጋን ደቅና ትገኛለች“ብሏል፡፡

የትራምፕ አራያውያን (የጀርመን ናዚ ምርጥ ዝርያ ነን ይሉ የነበሩት) በጉባኤው ላይ ያለ የሌ የዘለፋ ዓይነት መዓት አውርደዋል! መታሰር አለባት! መታሰር አለባት! መታሰር አለባት! መታሰር አለባት! በማለት ላንቃቸው እስኪደርቅ ድረስ ሲጮሁ ነበር፡፡

የአዮዋ ግዛት ተወካይ የሆነው ስቴቭ ኪንግ ስለነጮች የበላይነት እና ነጮች ለሰው ልጆች ስልጣኔ ሁሉ ብቸኛ አበርካቾች እንደሆኑ እና ሌሎችን ህዝቦች ሁሉ በማግለል እንዲህ በማለት ሲጮህ ነበር፣ “ታሪክን ወደ ኋላ መለስ ብላችሁ እንድትቃኙ እጠይቃለሁ፣ እናም ሌሎች ከነጭ ህዝቦች ውጭ የሆኑ ህዝቦች ያበረከቱት ስልጣኔ እስቲ የት አለ ንገሩን፣ ከነጭ ህዝቦች ውጭ ሌላ የህብረተሰብ ክፍል ያበረከተው ስልጣኔ የት አለ?“ ነበር ያለው የዘር ቫይረስ በደም ስሩ ውስጥ ተሰራጭቶ የሚገኘው ዘረኛ ሰይጣን፡፡

Trump RNC 2 jpgእውነት ለመናገር የትራምፕ የዘለፋ ሰለባዎች ከሌላ ፓርቲ እና ከአናሳ የህብረተሰብ ክፍሎች ምንም ዓይነት ተቃውሞ አልደረሰባቸውም፡፡ ትራምፕ የእርሱ የፕሬዚዳንትነት ዕጩነት እንዳይጸድቅ ከሚታገሉት እና ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ይፋ ድጋፍ ለማያደርጉለት ሬፐብሊካውያን ወንድሞቹ ምንም ዓይነት ጊዜ አላጠፋም፡፡ ትራምፕ የኦሂኦ ግዛት ገዥ የሆነውን ጆን ካሲች እና በጉባኤው እና በትራምፕ ደደብ የልኡካን አባላት ላይ ምንም ዓይነት የድጋፍ ምልክት ያላሳዩትን ሌላ የፓርቲ መሪዎች፣ ሴናተሮች እና ገዥዎች ሙልጭ አድርጎ ዘልፏል፡፡ ጉባኤው ከተጠናቀቀ በኋላ የጉባኤው አባላት በጉባኤው መድረክ ላይ ለምን እንዳልተሳደቡ በመናገር የተሰማውን ጸጸት ግልጽ አድርጓል፡፡

እ.ኤ.አ በ2016 የተካሄደው የሬፐብሊካን ጉባኤ ሁለተኛውን የአሜሪካንን የእርስ በእርስ ጦርነት ለማካሄድ ትራምፕ ያደረገው ጥሪ ነውን?

ትራምፕ ሀገራችንን ከአፍሪካ አሜሪካውን፣ ከሙስሊሞች፣ ከአይሁዶች፣ ከስደተኞች፣ ከሴቶች፣ ከሰራተኛ ማህበራት እና ከሌሎች እናጽዳ በማለት በዕጩ ፕሬዚዳንትነት ማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ ላይ ባልተጠቀሱት ላይ ሁሉ ቆጥቋጭ የሆነ ዘለፋ እና ቅጥፈቱን በመልቀቅ የጎሳ፣ የኃይማኖት እና የዘር ጦርነት ለመቀስቀስ ሙከራ በማረግ ላይ ነውን?

የትራምፕ የውሻ ፊሽካዎች አሜሪካ እራሷን በእራሷ የምታጠፋበት ሂደት ላይ የምትገኝ መሆኗን የሚያመላክት የምጻት ቀን ጥሪ ነው፡፡

ትራምፕ ዕጩ ፕሬዚዳንት መሆኑን ካወጀበት ጊዜ ጀምሮ በአሜሪካ ውስጥ ስላለ ሞት እና ጠቅላላ ውድመት እንዲህ በማለት በመናገር ላይ ይገኛል፡

“በ18 ትሪሊዮን ዶላር ዕዳ ውስጥ ተዘፍቀን እንገኛለን፡፡ ምንም ያገኘነው ነገር የለም፣ በችግሮች ብቻ ነው ተተብትበን ያለነው… እየሞትን ነው፡፡ ገንዘብ እንፈልጋለን፡፡ ያጣን ሆነናል፡፡ ምንም የሌለው ህዝብ ሆነናል፡፡ በሞራል ስብዕና የበከተ ህዝብ ነው ያለን፡፡  ሀገሩን የሚሸጥ ህዝብ ነው ያለን…የአሜሪካ ህልም ሞቶ ተቀብሯል“ ነበር ያለው፡፡

ትራምፕ ለወራት ያህል የእርሱን የውሻ ፊሽካ ፖለቲካ ሲነፋ ቆይቷል፣ ሆኖም ግን ይህንን ለማድረግ በአሁኑ ጊዜ ያለው ብቸኛው ዕጩ ፕሬዚዳንት እርሱ ነው፡፡

ለአራት አስርት ዓመታት ያህል የሬፐብሊካን ፓርቲ የውሻ ፊሽካ ፖለቲካን በማራመድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሕግ እና ስርዓትን ለማስከበር ቃል ይገባሉ (በአፍሪካ አሜሪካውያን ላይ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ የሚስጥር መግባቢያ ኮድ መሆኑ ነው)፡፡ የመንግስትን አዲሱን ስምምነት ለመሰረዝ ቃል ይገባሉ (የጤና ጥበቃን ድንጋጌ፣ የጤና እርዳታን፣ የማህበራዊ ዋስትናን እና የኦባማን የጤና ድንጋጌ ለመሰረዝ የሚደረግ የሚስጥር መግባቢያ ኮድ መሆኑ ነው) እንደዚሁም ግብር ለመቀነስ (በአሁኑ ጊዜ የናጠጡ ህብታሞች ሆነው የሚገኙትን የህብረተሰብ ክፍሎች ለመጥቀም ሲባል የሚስጥር መግባበቢያ ኮድ መሆኑ ነው፡፡)

ነገሮችን ከመጠን በላይ አጋኖ እና አግዝፎ በመናገር ሕገ ወጥ የውጭ ዜጎችን መስመር ማስያዝ (ለስደተኞች በተለይም ላቲኖችን እንደ ወንጀለኛ ለመቁጠር የሚደረግ የሚስጥር መግባቢያ ኮድ መሆኑ ነው) እናም አሁን በቅርቡ ደግሞ “የሻሪያን ሕግ” መዋጋት (ሙስሊሞች ሽብርተኝነትን ያስፋፋሉ በማለት ለማስፈራራት የሚደረግ የሚስጥር መግባቢያ ኮድ መሆኑ ነው) በማለት በዜጎች ላይ ፍርሀትን ለማንገስ ነው፡፡

ሮናልድ ሬጋን “ደህንነቷ የተጠበቀችው ንግስት” የሚል ምዕናባዊ ሀሳብ በማራመድ የማህበራዊ ደህንነቱን ስርዓት እንዲደርቅ ያደረጉ ጥቁር ሴቶች ናቸው የሚል ሀሳብ ያራምዱ ነበር፡፡

እ.ኤ.አ በ1968 ትልቁ ጆርጅ ቡሽ የዊለ ሆርቶንን የውሻ ፊሽካ በመጠቀም (ጥቁር ጥፋተኛ ሆኖ ሲገኝ የእድሜ ልክ እና የሞት እንዲሁም ለዘለቄታው ከስራ የማባረር ቅጣት እንዲኖር የማድረግ) እና ጉዳዩን የዴሞክራቲክ ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንት ሆነው ከተሾሙት ከሚካኤል ዱካኪስ ጋር በማስተሳሰር የወንጀለኛ ፍትህ ስርዓቱን ተዘዋዋሪ ለማድረግ ነበር፡፡

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የሬፐብሊካን የድምጽ ሰጭዎች ማንነት እውቅና ግፊት ደኃ አፍሪካ አሜሪካውያንን እና ሂስፓኒኮችን ከድምጽ መስጠት መብታቸው ለመከላከል የተዘየደ ዘዴ ነው፡፡ አሁን ባለፈው ሳምንት ሬፐብሊካኖች በቪርጂኒያ ግዛት የዴሞክራት ገዥ የሆኑት ቴሪ ማካሊፍ የእራሳቸውን የምህረት መብት ተጠቅመው ቀደም ሲል ወንጀለኛ የነበሩትን ዜጎች በቡድን ሆነው የመምረጥ መብታቸውን መጠቀም እንዲችሉ በማድረጋቸው በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡

ለዓመታት በዘለቁት በሬፐብሊካን ውሾች ፊሽካ እና በትራምፕ መካከል ያለው ልዩነት በጣም ትንሽ ነው፡፡ ብቸኛ ልዩነት ሆኖ የሚቀርበው የትራምፕ የውሻ ፊሽካ ለእርሱ ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንትነት ድምጽ ለመስጠት ለሚችሉ በተወሰኑ የሬፐብሊካን ፓርቲ አባላት የሚደመጡ እና የሚታቀፉ የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡

ትራምፕ ሞላጫ ውሸታም እና ስሜታዊ አምባገነን ነው፡፡ መንከን እ.ኤ.አ በ1926 “የዴሞክራሲ ማስታዋሻዎች/Note on Democracy“ በሚል ርዕስ ባሳተሙት መጽሐፋቸው ማንም በአሜሪካ ዴሞክራሲ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖረው የፈለገ ሰው መጽሀፉን ማንበብ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ መንከን በባዶ ጭንቅላት አታላይ ባዶ ቃላት ፖለቲከኛ አሜሪካንን እንደገና ታላቅ እናደርጋታለን በሚል አስመሳይ የብሄርተኝነት ስሜትን በሚሰብክ ቀጣፊ አሜሪካውያን ሰበብ አሜሪካውያን መታለል እንደሌለባቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ነበር!

ከአንድ መቶ ዓመታት ገደማ በፊት መንከን የአሜሪካንን ፕሬዚዳንታዊ የፖለቲካ መንገድ አቅጣጫ በሚገባ አስተዋሉ፡፡

መንከን (“የባልቲሞር ብልህ ሰው” “የአሜሪካ ቮልታየር”) ስለአሜሪካ ፖለቲካውያን ወይም ደግሞ ስለድምጽ ሰጭዎችም ቢሆን ብዙ ነገር የሚያስቡ አልነበሩም፡፡ የአሜሪካ የፖለቲካ ሂደት መቋጫ የሌለው እርባና ቢስ ንግግር በሚያደርጉ እና የውሸት ፖለቲከኞች የተሞላ መሆኑን ያስቡ ነበር፡፡ የአሜሪካ ድምጽ ሰጭዎች ትክክለኛ ያልሆኑ መርሆዎችን ለሚሰብኩ እና ደደብ ለሆኑ ስሜታዊ አምባገነን ሰዎች ሰለባ እንደሚሆኑ ያምናሉ፡፡ መንከን ስሜታዊ የሆኑ አምባገነን ሰዎች የህዝቡን ፍርሀት እንዴት አድርገው ማነሳሳት እንደሚችሉ ብቻ አይደለም የሚያውቁት፣ ሆኖም ግን ከዚህም በተጨማሪ ምቀኞችን እንዴት ማፍራት እንደሚችሉ፣ ደህና ሰዎችን እንዴት መጥላት እንደሚቻል እና በደህና ሰዎች ላይ እንዴት አድርጎ ጥላቻን መፍጠር እንደሚቻል ጭምር ነበር፡፡

መንከን በነጻነት ጉዳይ ላይ ትንሽ ፍላጎት ስላለው ህዝብ እና በእርግጠኝነት ነጻ ሲሆን ደስተኛ በማይሆነው፣ ምቾት በማይሰማው እና በመጠኑም ቢሆን በፍርኃት በተዋጠው እና ተስፋ በሌለው መልኩ ብቸኝነት ተጠናውቶት በሚገኘው የአሜሪካ ድምጽ ሰጭ ህዝብ ላይ እምነት ሊጣልበት የሚችል አይነት አመለካከት የላቸውም፡፡ አብሮ ረዥም ጉዞ የሚጓዝ እና የመንጋዎቹን ሽታ የሚያሸት ከእረኞች ጋር አብሮ የመጓዝ ፈቃደኝነት ይኖረዋል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የተግባራዊ ፖለቲካ አጠቃላይ ዓላማም ህዝቡን እንዲፈራ በማድረግ (ስለሆነም ጫጫታው በሰላም እንዲመራ ማስቻል ነው) እና ፍርሀትን ማለቂያ በሌለው መንገድ በመልቀቅ ሁሉም ምዕናባዊ በሆነ መልኩ እንዲመራ ማድረግ ነው፡፡

በነብያዊ የቋንቋ አጠቃቀም መንከን እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገዋል፣ “ዴሞክራሲ ፍጹም እየሆነ በሚሄድበት ጊዜ የፕሬዚዳንቱ ቢሮ ወካይ ይሆናል፣ በርካታዎች እና በርካታዎችን ይቀርባል፣ የህዝቡን የልብ ትርታም ያዳምጣል፡፡ ወደ መልካሙ እና ትክክለኛው ሀሳብ እንሄዳለን፡፡ በአንድ ታላቅ እና ታዋቂ በሆነ ቀን በአሜሪካ ያሉ ህዘቦች  በመጨረሻው የፍላጎታቸውን ያገኛሉ፡፡ እናም ኋይት ሀውስ ዉስጥ ደደቦች  ይገባሉ”  ነበር ያሉት፡፡

እዩልኝ እመኑልኝ ከሚለው ፍጡር በቴሌቪዥን ከሚታይ ተውኔት ሰሪ እና በቀጣይ ወደ ኋይት ሀውስ ለመግባት ከሚቅበጠበጠው ከዶናልድ ትራምፕ የበለጠ ማንም ቢሆን ታላቅ ደደብ ሊታሰብ አይችልም፡፡

የዶናልድ ትራምፕ የፍርሀት፣ እና ስም የማጠልሸት፣ ዘረኛ፣ የውጭ ዜጎችን የሚፈራ፣ ሴቶችን የሚጠላ እና ውሸታም ቀጣፊ ስሜታዊ አምባገነናዊነት ለአሜሪካ እርባና ቢስ እና ደደብ ፕሬዚዳንትነት መንከን ከሰጡት ማስጠንቀቂያ ጋር አንድ ሆኖ ይገኛል፡፡

ሆኖም ግን ትራምፕ አደገኛ የሆነ ስሜታዊ አምባገነን ነው፡፡ ዘረኝነቱን በፓርቲው ውስጥ ለብሶታል፡፡ ሆኖም ግን በዋናነት አዲሱን የፋሽስት ባህሪ የተላበሰ ኒዮ ፋሽስት ነው፡፡ በቀውስ ውስጥ ስላለች አሜሪካ እና በወንጀል፣ በኃይል እና በድህነት የወደቀች ሀገር እያለ ይናገራል፡፡ በአሁኑ ጊዜ አሜሪካ በምጻት ቀን ውስጥ እንደሆነች አድርጎ ለማሳየት በመሞከር ህዝቡን ለማሳመን ይፈልጋል፡፡

ትራምፕ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደተዋረደች አድርጎ በማቅረብ የኒዮ ፋሽስት ፕርፓጋንዳ በመዝራት፣ አሜሪካ ሀያል ሀገር እንደሆች እና ዓለምን በኃይል እንደምታንበረክክ በመግለጽ በዘር፣ በጎሳ አናሳነት እና በስደተኞች እና በሕገ መንግስቱ ላይ ያለውን ንቀት በመግለጽ በኃይል ማስተካከል እንደሚችል አድርጎ በመናገር ቃል ይገባል፡፡ ትራምፕ የዘር፣ የጎሳ እና የኃይማኖት ጥላቻን በፖለቲካ ቅስቀሳ ዘመቻው እና ፐሮግራሙ ውስጥ በማስገባት ወደ ፕሬዚዳንትነት መሰላል ጫፍ ለመውጣት ይፈልጋል፡፡

በምጻት ለተያዘቸው አሜሪካ የትራምፕ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲህ የሚል አዋጅ እና ቃልኪዳን ማወጅ ነው፡ “ለሁሉም አሜሪካውያን በዛሬው ምሽት በሁለም ታላላቅ እና ታናናሽ ከተማዎቻችን፡ አሜሪካንን እንደገና ጠንካራ እናደርጋታለን፡፡ አሜሪካንን እንደገና እንድትኮራ እናደርጋታለን፡፡ አሜሪካንን እንደገና ሰላም የሰፈነባት እናደርጋታለን፡፡ እናም አሜሪካንን እንደገና ታላቅ እናደርጋታለን!“ ነበር ያለው፡፡

የእርሱን የኒዮ ፈሽስት ዘመቻ ለማራመድ የናዚው ጆሴፍ ጎቤል በደብዳው የገለጸውን እና እንዲህ የሚለውን መልዕክት ይከተላል፡

“ውሸት የምትዋሽ ከሆነ እና ይህንንም ውሸት የምተደጋግመው ከሆነ ህዝቡ ቀስ በቀስ ወደ ማመን ይመጣል፡፡ ይህ ውሸት ሊቆይ የሚችለው መንግስት ህዝቡን ከፖለቲካ፣ ኢከኖሚ እና/ወይም ወታደራዊ ውሸት እንደ ጋሻ ሆኖ እስከጠበቀው ድረስ ነው፡፡ እውነት የውሸት የሞራል ልዕልና ጠላት ስለሆነ መንግስት ሁሉንም ሰላማዊ አመጾች ለመቆጣጠር ኃይልን ይጠቀማል፡፡ እውነት የመንግስት ታላቁ ጠላት ነው“ ነበር ያለው፡፡ 

በአሁኑ ጊዜ ታላቁ ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበው ትክክለኛው ደደብ እ.ኤ.አ በ2016 የኋይት ሀውስን ሊቆጣጠር ይችላል ወይ የሚለው ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ታላቁ ጥያቄ ሆኖ የሚቀርበው የ229 ዓመታት ዕድሜ ያለው ሕገ መንግስት በአዲሶቹ የኒዮ ፋሽስት ደደቦች ድንፋታ የኋት ሀውስን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ሽኩቻ ሊፈርስ ይችላልን የሚለው ነው፡፡

መንከን ለዚህ እንዲህ የሚል የተዘጋጀ መልስ አላቸው፡

“እኔ እስከማውቀው ድረስ እና በምርምርም ለበርካታ ዓመታት እዳረጋገጥኩት እና እንደመዘገብኩት እንዲሁም እኔን እንዲያግዙኝ ከቀጠርኳቸው ሰዎች እስከምገነዘበው ድረስ ከሆነ በዓለም ላይ እስከ አሁን ድረስ የብዙሀኑን ህዝብ ግንዛቤ በመናቅ ገንዘቡን የከሰረ የለም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ማንም ቢሆን ቢሮውን ያጣ የለም“ ነበር ያሉት፡፡

በሌላ አገላለጽ እስከ አሁን ድረስ የአሜሪካንን ህዝብ የመረዳት ግንዛቤ በመናቅ የከሰር ሰው ምንም የለም፡፡

መንከን እንዲህ በማለት ገልጸው ነበር፣ “ሁልጊዜ የሚፈጸመው ስህተት በሌላ መንገድ ይሄዳል፡፡ ምክንያቱም ብዙሀኑ ህዝብ የመናገር እና የመገንዘብ ከዚህም በላይ በበርካታ ጉዳዮች ማንበብ እና መጻፍ የሚችል ስለሆነ በጭንቅላታቸው ውስጥ ሀሳብ አለ፣ እናም የበለጠ ፍላጎት አላቸው፡፡ ይህ ታሳቢ ኢምክንያታዊ ነው“ ነበር ያሉት፡፡

የአሜሪካንን ህዝብ ከትራምፕ ኢምክንያታዊነት ሊጠብቀው የሚችል ማን ነው?

ሂላሪ ክሊንተን፣ በእርግጥ!

ታላቁን እና የመጨረሻዋን የሰብአዊነት ተስፋ ከትራምፓውያን አደጋ እንጠብቅ!

[1] የ”ውሻ ፊሽካ ፖለቲካ” መልዕክት ለጠቅላላው ህዝብ አንድ ነገር የሚል በሚስጥር የተያዘ ቋንቋን ያካትታል፡፡ ሆኖም ግን ዒላማ ለተደረገ የህብረተሰብ ክፍል በተጨማሪ ልዩ የሆነ ወይም ደግሞ ውስን የሆነ ትርጉም ይኖረዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  

ሀምሌ 20 ቀን 2008 ዓ.ም

ከንቲባውን ጨምሮ የከተማዋ ባለስልጣናት በቆሻሻው ጉዳይ በስብሰባ ተወጥረዋል

ከንቲባውን ጨምሮ የከተማዋ ባለስልጣናት በቆሻሻው ጉዳይ በስብሰባ ተወጥረዋል

Addis Admass:   የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማን ጨምሮ ዋና ዋና የከተማዋ ባለስልጣናት፤ በተለያዩ አካባቢዎች ከሳምንት ባላይ ሳይነሱ ለቆዩት የደረቅ ቆሻሻ ክምችቶች መፍትሄ ለማግኘት በስብሰባ ተወጥረው መሰንበታቸው ተገለፀ፡፡
በጉዳዩ ላይ የአስተዳደሩን ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ከንቲባው ቢሮ በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም፤ “ኃላፊዎቹ ከቢሮ ውጪ በኦሮሚያ ክልል በስብሰባ ላይ ናቸው” በሚል ሙከራችን ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰንደፋ ከተማ አካባቢ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ የአዲስ አበባ ቆሻሻ እንዳይጣል በአካባቢው አርሶአደሮች መከልከሉን ተከትሎ ከሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ የከተማዋን ቆሻሻ ወደ ስፍራው ወስዶ መጣል አልተቻለም። ይሄን ተከትሎ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች (ዋና ዋና ጎዳናዎችና አደባባዮችን ጨምሮ) የቆሻሻ ክምር ተቆልሎ ሰንብቷል፡፡ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ የከተማዋ አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ጋር ሲያደርግ የነበረው ውይይትና ድርድር ሳይሳካ መቅረቱ የተገለፀ ቢሆንም ባለስልጣናቱ ትላንት ድረስ በዚሁ ጉዳይ በስብሰባ ላይ እንደነበሩ ከንቲባው ፀሃፊ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከሳምንት በላይ በየአካባቢው ተጠራቅሞ የቆየው የደረቅ ቆሻሻ፤ ነዋሪውን ለከፍተኛ የጤና ችግር እየዳረገው መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ በፒያሳ፣ በመርካቶ፣ በአትክልት ተራ፣ በካዛንቺስና ሳሪስ አካባቢዎች ተዘዋውረን ለመመልከት እንደቻልነው፤ የደረቅ ቆሻሻ ክምሩ በየአስፋልቱና በየ ጥጋጥጉ ከመጠን በላይ ተቆልሏል፡፡
ወቅቱ የክረምት ጊዜ በመሆኑም የቆሻሻው እጣቢ በፍሳሽ መልክ በየጎዳናው ሲፈስ ያስተዋልን ሲሆን ይሄም በከተማዋ ከተከሰተው የአተት በሽታ ጋር ተያይዞ ነዋሪውን ለከፍተኛ ስጋት እንደዳረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡
‹‹የአገሪቱ ዋና ከተማና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እየተባለች የምትሞካሸው አዲስ አበባ፤ የቆሻሻ ማከማቻ ሆና መሰንበቷ አስደንጋጭ ነው” ያሉ አንድ ነዋሪ፤ ሁኔታው እንደ ኮሌራ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች እንዲስፋፉ ዕድል ይሰጣል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
ትምህርት ቤቶች የተዘጉበትና ህፃናት በየሰፈሩ የሚጫወቱበት ወቅት መሆኑ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል ያሉት ሌላ አስተያየት ሰጪ፤ በዚህ ከቀጠለ የህፃናቱ ህይወት ለአደጋ መጋለጡ አይቀርም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ “ስለ ኦሮሞና አማራ ትክክለኛ የዘር ምንጭ” ያብራራሉ!!

• ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች ነው
• አዳም የተፈጠረው ጎጃም፤ ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው
• ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አጥንቼ አለሁ ይላሉ …

Addis Admass
ኑሮአቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ታዋቂው የሥነፅሁፍ ምሁር ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ፤ የፃፉት‹‹የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ›› የተሰኘ አዲስ አነጋጋሪ የታሪክ መፅሐፍ ዛሬ ለገበያ ይቀርባል፡፡ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ ማን እንደሆነ በጥናት ደርሼበታለሁ
የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ እስከ ዛሬ የተለያዩ የታሪክ ምሁራን ከተናገሩት ፍፁም የተለየና አዲስ የጥናት
ውጤት ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡ የሁለቱ ቋንቋዎች አመጣጥም በጥናቱ ተካቷል ብለዋል፡
፡ በሊንከን ዩኒቨርሲቲ በሂዩማኒቲስ የትምህርት ዘርፍ የሚያስተምሩት ፍቅሬ ቶሎሳ ፤ከዚህ ቀደም
‹‹Heaven to Eden›› እና ‹‹The Hidden and untold History of the Jewish People and
Ethiopians›› የሚሉ መጽሐፍትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሙ ሲሆን ሁለቱም በኢንተርኔት
“አማዞን” በተባለ የመፅሃፍ ሽያጭ ድረገፅ ላይ ከተፈላጊ መፃህፍት ተርታ ተሰልፈዋል፡፡ በሙያቸው
ፀሃፌ-ተውኔትና የሥነ ፅሁፍ ምሁር ሲሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምሮችን
በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ አንጋፋው ምሁር ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በቅርቡ ለንባብ ባበቁት
“አዳፍኔ” የተሰኘ መፅሃፋቸው ላይ፤“የኦሮሞን ታሪክ ሙሉ አደርጎ ሊፅፍ የሚችለው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ብቻ ነው” ሲሉ ለብቃታቸው ምስክርነትና ዕውቅና መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ በርካታ ቲያትሮችን ለደረክ ያበቁ ሲሆን ከእነዚህም መካከል “ጓደኛሞቹ”፣ “ፍቅር በአሜሪካ” እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በቅርቡም ‹‹ላሟ›› የተሰኘ ባለ ሁለት ገቢር ቲያትር ፅፈው ማጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሠሩ ለአጭር ጊዜ ዕረፍት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበረ ሲሆን ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር በታሪክ ጥናቶቻቸው ዙሪያ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡

በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሟቸው “Heaven to Eden” እና “The Hidden and untold History of the Jewish People and Ethiopians›› የሚሉት መፃህፍት በአለማቀፍ ደረጃ ሰፊ ተቀባይነት ያገኙበት ሚስጥር ምንድነው? በምን ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው የሚያተኩሩት?
የመፅሐፍቱ ይዘት ነው ወሳኙ፡፡ ተቀባይነት ያገኙት በቋንቋ አጠቃቀም ለአንባቢያን ምቹ ስለሆኑ ይመስለኛል፡፡
በአይሁዶች ታሪክ ላይ የሚያተኩረው መፅሐፍ፤በጉዳዩ ላይ ከተጻፉ ሌሎች መጻህፍትና በተለምዶ ስለ አይሁዶች ከሚታወቀው ምን የተለየ ነገር ይዟል?
ብዙ ጊዜ ስለ አይሁዳውያን ሲወራ፣ቀዳማዊ ሚኒልክ የዛሬ 3ሺህ ዓመት፣ 40ሺህ አይሁዳውያንን ይዞ መጣ የሚለውን ነው የምናውቀው፡፡ ከመጡት መካከል 12ሺህ ያህሉ ንፁህ እስራኤላውያን ናቸው። 28ሺህ ያህሉ እነሱን በሥራ ያገለግሉ የነበሩ ኢያቡሳውያን የሚባሉ ነገዶች ናቸው፡፡ ቀዳማዊ ሚኒልክ ለ12 ሺህዎቹ ልዩ ቦታ ሰጥቷቸው፣ በሀገሪቷ ላይ ካህናት አድርጎ ታቦት እያስቀረፀ፣ ኢትዮጵያ ላይ በዚህ መልክ ሾሟቸው ነበር፡፡ ኢያቡሳውያን ደግሞ ንጉሱን በእጅ ስራና በውትድርና ያገለግሉት ነበር፡፡ ይሄ እንግዲህ አይሁዳውያን ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት ሁለተኛው ፍልሰት ነው፡፡
የመጀመሪያውና ብዙም የማይነገረው የአይሁዳውያን ፍልሰት፣ የእስራኤላውያኑ መሪ ሙሴ በህይወት እያለ አባ ብሄር የሚባል ልኡል ነበር። የሙሴ አማች ነው፡፡ አባ ብሄር የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሊሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፣አይሁዳውያን ተከትለውት መጥተው ነበር፡፡ ምክንያቱም አባ ብሄር ያገባት ልጅ የሙሴ እህት ነበረች፡፡ ሙሴ በወቅቱ ለአባ ብሄር ፅላት ቀርፆ እንዲሁም ቀይ ባህርን የከፈለባትን በትር ሰጥቶት፣ወደ ሳባ ከተማ መጥቶ ነግሷል፡፡ በወቅቱ ብዙ አይሁዳውያንም ተከትለውት መጥተው ነበር፡፡
ሶስተኛው ፍልሰት የምንለው፣የኢራቁ ናቡከደነፆር አሸንፏቸው በሚያሳድዳቸው ጊዜ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ አይሁዳውያን ወገኖች አሉን” ብለው ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፡፡ አይሁዳውያን በነዚህ መንገዶች ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፡፡
ትክክለኛዎቹ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ ያሉት ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ…?
የሃይማኖታቸውን ስርአት፣ መፅሃፍትና ህግጋት ከመጠበቃቸው አንፃር ከሌላ ህዝብ ጋር ስላልተደባለቁ ትክክለኛው ያለው እነሱ ጋ ነው፡፡ ሌሎቹ ወደ አውሮፓ፣ እስያ፣ አሜሪካ የተሰደዱት እነዚህን ነገሮች በተለያዩ ጫናዎች የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ጠብቀው አላቆዩትም፡፡ ወደዚህ የመጡት ግን በግድ ባህላችሁን ሃይማኖታችሁን ለውጡ ተብለው በኢትዮጵያውያን አልተረበሹም፤ነፃነት ነበራቸው፡፡ መሬትና ሁሉ ነገር የተመቻቸላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነበር፡፡ ሌላ አገር ላይ ቦታ እንዳይኖራቸው ተደርገው በየጊዜው ይሰደዱ ነበር፡፡ እንደውም በሩሲያ ውስጥ በድንገት አይሁዳውያንን የመግደል ድርጊት ይፈፀም ነበር። ሩሲያውያኑ ተሰባስበው፤“ዛሬ አይሁዳውያንን ገድለን እንምጣ” እያሉ ይዘምቱባቸው ነበር፡፡ ወደ መንደራቸው ሄደው አውድመዋቸው ይመለሳሉ፡፡ ማንም ስለማይበቀልላቸው ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ ነበር የሚቀረው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከተሰጣቸው ክብር የተነሳ በትንንሽ ንጉስነት ጭምር ይሾሙ ነበር፡፡ በርካቶቹም ካህናትና ሊቀ-ካህናት ተደርገው ለአይሁድ እምነት ተሹመል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የሰለሞን ዘር ነን በሚሉት ውስጥም ገብተው፣ ስርወ መንግስት እስከ መመስረት የደረሱ ነበሩ፡፡ በዓለም ላይ አይሁዳውያን ደልቷቸው የኖሩት ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ነው፡፡ በጠቅላላው በኢትዮጵያ ሀገራት ማለትም፡- በግብፅ፣ የመን፣ ኑቢያ—ኢትዮጵያ ባስተዳደረቻቸው አካባቢዎች በሙሉ በክብር ተይዘው ነው የኖሩት፡፡ ትልቁ ማስረጃ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ፣ እናቱ ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ በስደቱ ዘመኑ እኛ ጋ ብቻ ነው ጥገኝነት ያገኙት። በወቅቱ ግብፅ ለሁለት ተከፍሎ ነበር፡፡ አንዱ ክፍል በሮማውያን ቁጥጥር ስር ነበር፡፡ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነው፡፡ ኢየሱስ ከመወለዱ ከ880 ዓመት በፊት አማራዎች፤ አማሩላ ደልታ ወደሚባል ቦታ ሄደው፣ አክሱማይት የተባለውን ህፃን ልጅ ዙፋን በመጠበቅ ያገለግሉ ነበር፡፡ በኋላ በ800 ዓመታት ውስጥ አማሩላ ደልታ የሚባል መንደር መስርተው ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ጋርና ከቅዱስ ዮሴፍ ጋር ሲሸሹ፣ እዚያ ነው ማረፊያ ያገኙት፡፡ ይሄ መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፤እኛ ግን ከተለያዩ መዛግብት እናገኘዋለን፡፡ በወቅቱ የአካባቢው ንጉስ አማናቱ ተትናይ ይባላሉ፡፡ ከጎጃም ከጣና አካባቢ ነው ወደዚያ የሄደው፡፡ ሌላው አይሁዳውያኑ መፅሐፍ ቅዱሳቸው ሲጠፋባቸው ከኛ ነው የወሰዱት፡፡ አፄ ደንቀዝ የተባለው ንጉሰ ነገስት ነው ከግዕዝ ወደ እብራይስጥ አስተርጉሞ የሰጣቸው፡፡
ትክክለኛውን የአይሁድ ባህልና እምነት በመጠበቅ በኢትዮጵያ ያሉት አይሁዳውያን ብቸኞቹ ናቸው ማለት ይቻላል?
አዎ! ኦሪትን ይዘዋል፡፡ ግን በደማቸው ከኛ ተደባልቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ሃበሻ የተባሉት። ሃበሻ ማለት የተደባለቀ ነው፡፡ “አበሳ” ያለበት ወይም እንከን ያለበት ማለት ነው፤ ሃበሻ ማለት፡፡ በቀዳማዊ ሚኒልክ ጊዜ የመጡት ከኛ ጋር ተደባልቀው 560 ዓመት ከቆዩ በኋላ በባቢሎን ስደት ጊዜ ሶስተኛዎቹ ሲመጡ፣ነባሮችን ሲያዩአቸው በመልካቸው አይሁዳውያንን አልመስል አሏቸው። ስለዚህ፤“እናንተማ ክልስ ናችሁ፤አበሳ አለባችሁ” ብለው ይሰድቧቸዋል፡፡  ነባሮቹ አይሁዶች ደግሞ፤ “እናንተ ፈላሾች፤እኛ ሀገር አለን” እያሉ ይሰድቧቸው ነበር፡፡ በዚህም “አበሻ” እና “ፈላሻ” የሚለው መጠሪያቸው ሆነ፡፡ “ሀበሻ” የሚለው ቃል እኛን አይወክለንም የምለው ለዚህ ነው፤ሀበሻ አይሁዳውያኑን ነው የሚወክለው፡፡ እኛ የኢትዮጰያ ልጆች ነን፤ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡
“በሃበሻነቴ እኮራለሁ” ስንል የከረምነውስ—–ቀለጠ ማለት ነው?
አዎ! እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ ሀበሻ አይደለሁም። ሀበሻ የሚለው ቃል የስድብ ቃል ነው፡፡ እኛን አይወክለንም፡፡ አይሁዳዊ ካልሆነ በስተቀር አንድ ሰው ራሱን “ሀበሻ ነኝ” ብሎ ሊጠራ አይገባውም። ስድብ አያኮራም፡፡ ብዙ ሰው ስለማያውቅ ነው በሀበሻነቴ እኮራለሁ የሚለው፡፡ በአረብኛም ብናየው “የተደባለቀ”፤ “ንፁህ ያልሆነ” ማለት ነው። ይሄ መልካም ቃል አይደለም፡፡ ግን ሀበሻ የሚለው “አበሳ” ከሚለው እንጂ ከአረብኛ የመጣ አይደለም። ሁለቱ አይሁዳውያን መሃል ያለ የመሰዳደቢያ ቃል ነው እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያንን አይመለከተንም፡፡
‹‹ኢትዮጵያ›› የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
ኢትዮጵያ የሚለው ‹‹ኢትዮጵ›› ከተባለው ሰው የመጣ ነው፡፡ ኢትዮጵ ማን ነው ካልን፣ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰው መልከፀዴቅ የሚባል የሳሌም ንጉሰ ነገስትና ሊቀካህን ነበር፡፡ ይህ ሰው ሃገር ያስተዳድራልም፤ሃይማኖትም ይመራል፡፡ እሱም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነበር፡፡ ይሄ እንዴት ይሆናል ከተባለ፣ኢየሱስ በምፅአት ቀን ሲመጣ፣ የንጉስ ንጉስ፣ የካህን  ካህን ሆኖ ነው፤መልከፀዴቅም የዚህ ምሳሌ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ከዚሁ ጋር ምን ያገናኛታል ሊባል ይችላል፡፡ በጣም የሚያኮራ ግንኙነት አለው፡፡ የመልከፀድቅ ልጅ ኢትኤል ይባል ነበር፡፡ እግዚአብሔር ኢትኤልን ካለህበት የሳሌም ምድር ለቀህ ጣና ላይ ስፈር አለው፡፡ ‹‹ከዚያም ያንተ የልጅ ልጆች፣ እኔ ከ2000 አመታት በኋላ በምወለድበት ጊዜ በኢትዮጵያ  ግዛት ላይ ስለ መወለዴ ኮከብ አሳይሃለሁ” ይለዋል (እንደኔ ምርምር፤ይሄ ኮከብ የተባለው መልአኩ ገብርኤል ነው) በዚህ ሁኔታ ኢትኤል አሁን ወዳለችው ኢትዮጵያ ሲደርስ እግዚአብሔር፤‹‹ኢትዮጵ›› ተብለህ ተጠራ አለው፡፡ ‹‹ኢት›› – ስጦታ ማለት ነው፡፡ ‹‹ዮጵ” – ማለት ደግሞ ቢጫ ወርቅ ነው፡፡ ስለዚህ “ቢጫ ወርቅ ስጦታ” ተባለ፡፡ በኋላ ሃገሪቷን ኢትዮጵያ አሠኛት፡፡
በመፅሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ተብሎ የሚጠቀሰው ስም የትኛዋን ኢትዮጵያ ነው የሚወክለው?
እሱ አሁን ያለችውን ኢትዮጵያን ነው የሚወክለው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ እስከ 13ኛው ክ/ዘመን ድረስ ለመላዋ አፍሪካ መጠሪያ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ በኋላም የመጣው አፍሪካ የሚለው ስም ከዚሁ ከኢትዮጵያ የተገኘ ነው፡፡ ከአፋሮች ነው አፍሪካ መጠሪያዋን ያገኘችው፡፡ በመፅሃፈ እዝራ ምዕራፍ ስድስት ላይ፤‹‹አፍሪካንሳውያን›› ይላል፡፡ ይሄ አፋሮችን ነው የሚወክለው፡፡ በመርከብ ስራ በቀይ ባህር ላይ የተራቀቁ ሰዎች ነበሩ፡፡ የዛሬ 3ሺህ አመት ንጉስ ሰለሞን ቤተመቅደሱን ሲሰራ፤ልዩ እንጨት፣ እጣን፣ ወርቅ (ኦፊር የተባለ ታዋቂ ወርቅ- በነሱ የተሰየመ) ጭምር ይነግዱና ለንጉሡ ያቀርቡ ስለነበር፣ስማቸው የገነነ ሆኖ አፍሪካንሳውያን የተባሉት፡፡ በሳይንሱም አፋር የሰው ዘር መገኛ እያልን ነው፡፡ ኢስያውያንም ስያሜያቸውን ያገኙት ከሣባ ቀድሞ ከነገሰው ‹‹ኢስአኤል›› ከተባለው ንጉስ ነው፡፡ ምድሪቱን ያስተዳድር ስለነበር ኢስያ ተባለች፡፡ ‹‹አፄ” የሚለውም ከዚህ የመጣ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሚለው ከግሪክ ቃል የመጣ ነው የሚለውስ —?
ኢትዮጵያ የሚለው ከግሪክ ቃል  የመጣ ነው የሚለው ውሸት ነው፡፡ ይሄን አጣርቻለሁ፡፡ በነሱ መዝገበ ቃላት ውስጥ ይሄ ቃል የለም፡፡ ‹‹ፊቱ የተቃጠለ›› የሚለው ቃል በግሪክ ቋንቋ ኢትዮጵያ የሚለውን ሳይሆን ሌላ ትርጉም ነው የሚኖረው፡፡ ግሪኮቹ ከኛው ሰምተው ነው መልሠው ኢትዮጵያ ያሉን፡፡ እኛ ከነሱ በፊት ነበርን እንጂ እነሱ ከኛ በፊት አልነበሩም፤ ስማችንን ሊያወጡልን አይችሉም፡፡
በምርምርዎ አዳምና ሄዋን የተፈጠሩበት ቦታ የት ሆኖ አገኙት?
ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ጎጃም፤ ዳሞትና ጣና አካባቢ ያለ ቦታ ነው፡፡
ለዚህ ድምዳሜ ማስረጃዎ ምንድን ነው?
አንደኛ ኤደንን ከሚያጠጡ አራት ወንዞች ውስጥ አባይ የምንለው ነው ኤፌሶን የሚባለው። በኦፌር ወርቅ ዙሪያ የሚዞር መሆኑ ተፅፏል፡፡ በኔ ድምዳሜ፣የኤፌሶን ወንዝ የአሁኑ ዋቢ ሸበሌ ነው። ጤግሮስና ኤፈራጥስ ደግሞ ጊዮን ራሱ ጥንት ሜዲትራኒያን ባህር ይገባ ነበር፡፡ ድሮ ሜድትራኒያን “ኪቲ” ይባል ነበር፡፡ ጥንት ጊዮን ወንዝ ሜድትራኒያን ሲደርስ ተራራ ስለነበር ተጋጭቶ ይመለስ ነበር፡፡ ከዚያ ነው መሬት ተነቃንቆ፣ቦታው ተቆራርጦ አሁን ወዳለበት ኢራቅ የሄደው እንጂ አካባቢው እዚሁ ነበር፡፡
አዳም የት ተፈጠረ ለሚለው በመፅሃፈ ሄኖክ ላይ “ኤልዳ” በሚባል ቦታ ተፈጠረ ይላል፡፡ ኤልዳ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም አስሌዳውያን ወይም ኤልዳውያን የሚባሉ አሁንም ድረስ ጎጃም ውስጥ አሉ፡፡ ሄኖክ በመፅሃፉ ኤልዳ ነው የተፈጠረው ይላል፡፡ ከዚያ ወስዶ ነው እግዚአብሄር በ40 ቀኑ ወደ ኤደን ገነት የከተተው ይላል፡፡ ሄዋንን ደግሞ ከአዳም ጎን አውጥቷት ነው በ80 ቀኗ ወደ ኤደን ገነት የከተታት፡፡ ከዚህ ተነስቶ ነው ወንድ በ40፣ ሴት በ80 ቀን ክርስትና የሚነሱት። ይሄ አይነቱ ስርአት በዓለም ላይ የትም የለም፤እና ይሄ በሄኖክ መፅሃፍ የተፃፈውና አሁን ያለው እውነታ ይገኛል፡፡
ሌላው ኮሬብ የሚባል ዋሻ ውስጥ አዳም ተቀበረ ይላል፡፡ በእርግጥ በሲናይ በረሃ አካባቢ ኮሬብ የሚባል ቦታ አለ፤ ግን በተመሳሳይ ይህ ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥም አለ፡፡ ሌላው ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው ይላል፡፡ አራራት ተራራን ለመፈለግ ወደ ቦታው ሄጄ ነበር፤ በታንኳ ጣናን አቋርጬ፡፡ አራራት ተራራ የሚባለውን ሳገኘውና አቀማመጡን ሳጠናው፣ ለመርከብ ማሳረፊያነት በአናቱ ላይ ምቹ ሜዳ አለው፡፡ ኖህ ወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር ይላል፤መፅሃፍ ቅዱስ፡፡ በእርግጥም ቦታው የወይን ጠጅ ፍሬ ለማብቀል ተስማሚ ነው፡፡ አሁንም አትክልቶችና ጌሾ ይበቅልበታል፡፡ ከዚሁ ማስረጃ ሳልወጣ፣አዲስ አመትን አበቦች አብበው አከበረ፤የእንጨት መስዋዕትም አደረገ ይላል፡፡ ይሄ እንግዲህ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ ያለው የአዲስ ዓመት መቀበያ ስርአት፣ ከየት መጣነትን ሊያስረዳ ይችላል። በኋላ ወደ ክርስትናው የመስቀል በዓል ደመራነት ተለወጠ እንጂ በፊት ደመራ የሚነደው በአዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃው አሁንም ድረስ ክርስቲያን ያልሆኑ የሀገራችን ሰዎች የደመራ ስርአት አላቸው። ይሄ የአባታቸው የኖህ ትዝታ (ማስታወሻ) ነው ሲወረስ ሲዋረስ የመጣው፡፡ በዚህና በኖህ ጉዳይ ሰፊ ጥናት እያደረግሁ ነው፤ወደፊት ይፋ ይሆናል፡፡ አንድ እዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው፣ሌላ አራራት የሚባል ተራራ አርመን ውስጥ አለ፡፡ ተራራው ግን በረዶ ያለበት፣ ገደላገደል፣ እንኳን መርከብ ሊያሳርፍ ለሰው ልጅ የማይመችና የማያብብ ቦታ ነው፤ ስለዚህ ያ ሊሆን አይችልም፡፡
በሰንደቅ አላማው ላይም የተለየ መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡ ለኢትዮጵያ የተሰጠ ስጦታ ነው ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?
ሰንደቅ አላማው ለኖህ ከተሰጠው ምልክት የመጣ ነው፡፡ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የጎሉበት ቀለማት ሰማይ ላይ ታይተዋል፡፡ እነዚያ ቀለማት ናቸው ዛሬ ያሉት፡፡ ከንግስት ሳባ በፊት የነገሰው አፄ ኢሲአኤል ነው ሰንደቅ አላማ እንዲውለበለብ ያደረገው፡፡ ሰንደቅ አላማ የሚለው የመጣው የኢስአኤል መንግስት “ሰንደቅ አለማ” ከሚለው ነው፡፡ ከዚያ የመጣ ነው። እሱ በወቅቱ የመረጠው፡- አረንጓዴ ቢጫ፣ቀይና ሰማያዊ ቀለማት ነበር፡፡ ለሰንደቅ አላማው ያልተገዛና ያላውለበለበ ይቀጣል ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ አስገዳጅ ህግ ያወጣውም እሱ ነበር፡፡ በሰንደቋ አናት ላይ ኮከብ ነበር የሚቀመጠው፡፡ ኢየሱስ ሲወለድ የሚጠቁመውን ኮከብ ለማስታወስ ይጠቀም ነበር፡፡ በዓለም ላይ ሰንደቅ አላማን የፈለሰፈ የመጀመሪያው ሰውም ሊሆን ይችላል፡፡
የኢትዮጵ የልጅ ልጅ የሆነው ኢስአኤል ከፈለሰፈው ሰንደቅ አላማ ነው፣ዛሬ ያሉት የሰንደቅ አላማ ቀለማት የመጡት፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰንደቅ አላማው ላይ ከዚህ ተነስቶ አንድ አይነት አቋም ቢይዝ መልካም ነው፡፡ ኢስአኤል ለኦሮሞውም፣ ለአማራውም፣ ለትግሬውም፣ለአፋሩም ለሌላውም ብሄረሰብ ሁሉ አባት ነው፡፡ ከአባቶቻችን የወረደ ሰንደቅ አላማ እንጂ ከባዕድ የመጣ አይደለም፡፡
ሰውየው እጅግ ጠቢብ ነበር፤ልእለ ሰብዕ (superman) ነበር፡፡ 150 አንበሳ መግደሉን ለማስታወስ ጭምር አፄ ኢስአኤል የሰብዕ እና የአውሬዎች ንጉሰ ነገስት ብሎ ነበር ራሱን የሚጠራው፡፡ ሰውየው እጅግ ጠቢብ ከመሆኑ የተነሳ የጀነቲክ ኢንጅነሪንግን የፈለሰፈውም እሱ ነው፡፡ እንስሳን ከእንስሳ፣ ዘርን ከዘር እየቀላቀለ የፈለሰፈ የመጀመሪያው የጀነቲክ ኢንጅነር ነበር። በቅሎን የፈጠረውም እሱ ነው፡፡ አህያንና ፈረስን አዳቅሎ፡፡ ይህ ሰው የሁሉም ኢትዮጵያውን አባት ነው፡፡ የኢትዮጵ ልጅ ነው፡፡ የኢትዮጵ 10 ወንዶች ልጆች ናቸው፤ አሁን የምናያቸውን የኢትዮጵያውያን ጎሳዎች ሁሉ የፈጠሩት፡፡
ሰሞኑን ለአንባቢያን የሚቀርብ መፅሃፍ እንዳዘጋጁም ሰምቼአለሁ፡፡ የመፅሐፉን ይዘት በአጭሩ ሊነግሩኝ ይችላሉ?
መፅሐፉ፤“የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የሚል ነው፡፡ አሁን ያሉት ኢትዮጵያውያን በሞላ የኢትዮጵ ልጆች መሆናቸውን ከላይ አስረድቻለሁ፡፡
አሁን እንደምናው በሁላችንም ላይ የማንነት ቀውስ አለ፡፡ የማንነት ቀውሱ የመጣውም እኛ ማን እንደሆንን በትክክል ባለማወቃችን ነው፡፡ ስለዚህ ይህ መፅሐፍ እኛ ማን እንደሆንን፣በርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎችና ሰነዶችን አስደግፎ፣ግልጥልጥ አድርጎ  ያስረዳናል፡፡ ይህ የማንነት ቀውሳችን ከተስተካከለና ራሳችንን ካወቅን፣ በመካከላችን ግጭቶች ሊኖሩ አይችሉም፡፡ መፅሐፉ፤ፍቅር፣ ሰላምና ህብር ሊፈጥር ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እኛ የትልቅ ሰው ዘር ነን የሚለውን በማስረጃ የሚያሳየን ነው፡፡ የሰው ዘር ምንጭ ናሙናዎች መሆናችን ይተነትናል፡፡ ማንነታችንን በትክክል ተረድተን፣ አንድ ላይ ለመጓዝ ያስችለናል ብዬ አስባለሁ – ይህ ብዙ የተደከመበት የምርምር ውጤት፡፡
የኦሮሞና የአማራ የዘር ሀረግ አንድ ነው የሚለውን ነው መፅሃፉ የሚያስረዳው?
አማራና ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በኢትዮጵያ ግዛት ያለው ብሄር፣ ጎሳ ከ10ሩ የኢትዮጵ ልጆች ነው የመጣው፡፡ ዝቅ ሲል ደግሞ የኢትዮጵ የልጅ ልጅ የሆነ፣ ጎጃም ላይ አዳምና ሄዋን ተፈጥረዋል ብዬ ባልኩት አካባቢ አንድ ጠቢብ ሰው ነበር፡፡ “ደሴት” ወይም “ደሸት” ይባላል፡፡ እሱ ነው የኦሮሞና የአማራ አባት፡፡ የዛሬ 3600 ዓመት 4 ወንዶች ልጆች ወለደ፡- መንዲ፣ መደባይ፣ ማጂ፣ ጅማ የሚባሉ፡፡ እነዚህ 4ቱም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሀገር መጠሪያ ሆነዋል። ማጂ ደግሞ ማራ እና ጀማን ይወልዳል። ዛሬ አማራ የምንለው ማራ ነው፡፡ “ማራ” ማለት “እውነተኛ ብርሃን” ማለት ነው፡፡ አማራ ያሉት አጋዚያን ወይም የግዕዝ ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ ማጂ ማራን ወለደ ካልን፤ ጀማ እና ማራ ወንድማማቾ ናቸው፡፡ ሁለቱ ወንድማማቾች በአካባቢው ካሉት ጋፋቶች ጋር መዋጋት ሰልችቷቸው፣ ሃገር ለቀው ወደ ሸዋ ሲመጡ አንድ ወንዝ ያገኛሉ፡፡ ወንዙን ጀማ አሉት። አሁን የጀማ ወይም የ“ዠማ” ወንዝ ማለት ነው። ከአካባቢው እየራቁ ሲሄዱ የጥንት አባቶቻቸውን ቋንቋ “ሱባ”ን ትተዉ አማርኛን መፈልሰፍ ጀመሩ፡፡ መደባይ፣ ጅማና መንዲ ደግሞ ግማሾቹ ጎጃም ላይ ቀሩ፤ ግማሾቹ ወለጋ ሄዱ፤ሌሎቹም እየራቁ በምስራቅ አፍሪካ ተሰራጩ፡፡ ኦሮሚኛ ቋንቋ የሚባለውንም ፈጠሩ፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው ዛሬ ያሉት ኦሮሞና አማራ የመጡት፡፡ ዘረ ደሸት ይባላሉ፡፡ የደሸት ልጆች ናቸው። የዘር ሀረጋቸው አንድ ነው፡፡ ቋንቋቸው የተለያየ የሆነው በሂደት ነው፡፡
ኦሮሞው የኩሽቲክ፣ አማራው የሰሜቲክ ዘር ናቸው፤ የመጡትም ከውጭ ነው የሚለው ለዘመናት የዘለቀ ታሪክስ …?
እሱ ፈፅሞ ውሸት ነው፡፡ ሁለቱም ከውጭ አልመጡም፡፡ እንዳስረዳሁት እዚሁ የበቀሉ ናቸው። የአማራም የኦሮሞም አባት ደሸትም ሆነ ታላቁ አባት ኢትዮጵ ኩሽ ነው፡፡ መልከፀዴቅም ኩሽ ነው። ኦሮሞና አማራ ሁለቱም ኩሽ ናቸው፡፡ አማራ ሴም አይደለም፤ ኩሽ ነው፡፡
እስከ ዛሬ ሲነገር የነበረው ውሸት ነው። ምናልባት የአማርኛ ቋንቋ ከሌሎች ጋር ሲደበላለቅ ሴሜቲክ ቤተሰብ ውስጥ ተገኝቶ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ኢትዮጵያውያን የኩሽ ዘሮች ናቸው። በዚሁ መፅሐፌ ላይ ስለ ቋንቋም አስረድቻለሁ፡፡ በእብራይስጥም ሆነ በአረቢክ የሌሉ እንደ ጨ፣ቀ፣ፀ ያሉ ድምጾች በአማርኛና በኦሮሚኛ ቋንቋ ውስጥ አሉ። ይሄን በዝርዝር በመፅሐፉ አስቀምጫለሁ፡፡
ኦሮሞና አማራ አንድ ነው የሚለው አመለካከት በተለይ በኦሮሞ ምሁራን ዘንድ እምብዛም ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም፡፡ በግድ ኦሮሞን አማራ ለማድረግ ነው በሚል ወቀሳ የሚሰነዝሩ አሉ …
እንዲህ የሚሉት ሁሉም ከኢትዮጵ ዘር የመጣው የደሸት ልጆች መሆናቸውን ባለማወቃቸው ነው። ይሄ መረጃ ስለሌላቸው ራሳቸውን እንደ ባዕድ አግልለው ስለሚያዩ ነው እንጂ አሁን ይሄ እኔ ያቀረብኩትን ማስረጃ በቅን ልቦና አገናዝበው ለመረዳት ከሞከሩ፣ የትልቁ ሰው የኢትዮጵ፣ የጠቢቡና የሊቀካህናቱ የደሸት ልጅ እንደሆኑ በሚያውቁ ጊዜ፣ እነሱ እንደተሳሳቱ ተገንዝበው ወደ ማንነታቸው ላይ አተኩረው ይኮሩበታል ብዬ አስባለሁ፡፡ የመጣነው ከትልቅ ዘር ነው፡፡ ኦሮሞውም አማራውም የመጣው ከዚህ ትልቅ ሰው ነው፡፡ በዚህ ሁላችንም ልንኮራ ይገባናል፡፡
የአሁኗ እና የቀድሞዋ ኢትዮጵያ ልዩነታቸውና አንድነታቸው ምንድን ነው?
በግዛት ከሄድን ጥንት መላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ነው የሚባለው፡፡ ከየመን አልፎ ሁሉ ይሄዳል፡፡ ግብፅ ውስጥ ፈርኦኖች የሚባሉት ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአባይ ላይ ከመርከብ ወርደው ሜዳ አግኝተው የሰፈሩበት ቦታ ነው፤ ግብፅ፡፡ የአፍሪካ ሁሉ ነገር ከኛ አይወጣም፡፡
የኢትዮጵያ ታሪክ የ3ሺህ ዘመን ነው ይባላል፡፡ እርሶ የደረሱበት የጥናት ውጤት ምን ይላል?-
አዎ፤ በተለምዶ 3ሺህ አመት ይባላል እንጂ ከ7ሺ በላይ ነው፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፡፡ ኖህ ኢትዮጵያ ላይ ነግሷል፤ ከዚያ ጀምሮ 7ሺህ አመት ነው፡፡
እስካሁን በነገሩን ታሪክ ውስጥ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው በማስረጃነት የሚጠቅሱት፡፡ መፅሐፍ ቅዱስን ብቻ የታሪክ ምንጭ ማድረግ ይቻላል?
መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ አይደለም፡፡ 42 ሰነዶችን አሁን በሚወጣው መፅሐፌ ላይ በግልፅ አስቀምጫለሁ። እነዚህ ሰነዶች በተለያዩ ሰዎች በጥንት ጊዜ የተፃፉ ናቸው፡፡ ኑቢያ ውስጥ ጀበል ኑባ በተባለ ቦታ ተቀብረው የቀሩ፣በጥንት ፍርስራሽ የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን (ከእስልምና በፊት የነበረ) ድንጋይ ሳጥን ውስጥ ተቀብረው የነበሩ የብራና ሰነዶች አግኝቻለሁ፡፡  በዚያ ላይም የተመሰረተ ነው። ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ 42 ተጨማሪ የታሪክ ሰነዶችን ተጠቅሜያለሁ፤ይሄን መፅሐፍ ሳዘጋጅ፡፡
ቀጣይዋ ኢትዮጵያ ምን መምሰል አለባት ይላሉ?
አሁን ማንነታችንን አውቀን፣ የማንነት ቀውሳችንን ፈትተን፣ሁላችንም የኢትዮጵያ ዘር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች—–መሆናችንን ተገንዝበን፤ በፍቅር፣ በሰላም፣ በመከባበር፣ በእኩልነት መኖር አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ ሁላችንንም ኢትዮጵ ያገናኘናል፡፡

ተቃዋሚዎች፤ የሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮች አሳሳቢ ሆነዋል አሉ

· ኢዴፓ የብሄራዊ እርቅ መድረክ እንዲፈጠር ጠየቀ

የአገሪቱን ወቅታዊ ችግሮች በመጥቀስ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ ማበጀት እንዳለበት የገለፁት ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ ችግሮቹ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሰዋል ሲሉ አስጠነቀቁ የመላ ኢትዮጵያውያን አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ለፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በፃፈው ደብዳቤ፤ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በጥልቀት መገምገሙን ጠቅሶ፤ መንግስት በመላ ሀገሪቱ ሰላምና ዲሞክራሲ በማስፈን፣ ለህዝቡ የተረጋጋ ህይወት ማስፈን አልቻለም ብሏል፡፡
በኦሮሚያ የተፈጠረው ግጭትና ተቃውሞ፣ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ላደረሰው ጥፋት እስካሁን ዘላቂ መፍትሄ አለመቀመጡን የጠቀሰው ፓርቲው፤ በአማራ ክልልም በወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ መነሻነት የተፈጠረው ግጭት በተመሳሳይ መልኩ ለሰው ህይወት መጥፋትና ለብረት መውደም ምክንያት መሆኑ ተገቢ አይደለም ብሏል፡፡ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክ/ከተሞች ህገ ወጥ እየተባሉ ቤቶች በመፍረሳቸው፣ ዜጎች ያለ መጠለያ መቅረታቸውን ያወገዘው መኢአድ፤ ለእነዚህ ወቅታዊ ችግሮች መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግ ጠይቋል፡፡
ፓርቲው ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና ለፌደሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤዎችም ደብዳቤውን እንደላከ ገልጿል፡፡  ፓርቲው እነዚህን በመሳሰሉ ወቅታዊ ችግሮች ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ ደብዳቤ ሲፅፍ መቆየቱን አስታውሶ፤ ለሚፅፋቸው ደብዳቤዎች አንድም ጊዜ ምላሽ እንዳልተሰጠው ይገልፃል፡፡ የአሁኑን ደብዳቤ ለመጨረሻ ጊዜ ለ4ቱ የመንግስት አካላት መላኩን የጠቆመው መኢአድ፤ “ለዚህ ደብዳቤ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ፣ በሌላ መንገድ ጥያቄውን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብሏል፤ ለአዲስ አድማስ በሰጠው መግለጫ፡፡
የሀገሪቱ ወቅታዊ ችግሮችና ግጭቶች በእጅጉ እያሳሰበኝ ነው ያለው ኢዴፓ በበኩሉ፤ በአስቸኳይ የብሄራዊ እርቅ መድረክ እንዲፈጠር ጥሪ አቅርቧል፡፡
“ለሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ብሄራዊ እርቅ ወሳኝ ነው” ያለው ኢዴፓ፤ መንግስት ለተቃውሞዎች የሃይል እርምጃ መጠቀሙ ተገቢ እንዳልሆነ ገልፆ፣ ህዝቡም ሀገርን ከሚያፈርስ እንቅስቃሴ እንዲቆጠብና ልዩነቶች በሰላም እንዲንፀባረቁ ጠይቋል፡፡ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚተላለፉ የመንግስትና የግል መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያዎች ልዩነትን ከማራገብ ተቆጥበው፣ ሰላምን ለማምጣት ሙያዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም ፓርቲው ጠይቋል፡፡
ቀደም ሲል ተመሳሳይ መግለጫዎችን ሲያወጣ መቆየቱን የጠቆመው ፓርቲው፤ መንግስት መግለጫዎቹን ቸል በማለቱና የእርምት እርምጃዎች ባለመውሰዱ በየጊዜው በሚፈጠሩ ግጭቶች፣ የሰው ህይወት ከማለፉም ባሻገር ሀገሪቱን ወደ አስከፊ ሁኔታ እየመራት ነው ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በበኩሉ፤ መንግስት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ህገ ወጥ ያላቸውን ቤቶች ያለ አማራጭ ማፍረሱና በክረምት ዜጎችን ለብርድና ለእንግልት መዳረጉ ኢ-ሰብዓዊ እርምጃ ነው በማለት እንደሚያወግዘው አስታውቋል፡፡
በጎንደር የተፈጠረው ችግር ለህዝብ ጥያቄዎች በህገ መንግስቱ አግባብ ፈጥኖ መልስ አለመስጠት ያስከተለው መሆኑን በመግለጫው ጠቅሶ፤ መንግስት ይህን ለመሳሰሉ የህዝብ ጥያቄዎች ፈጥኖ ምላሽ እንዲሰጥ አሳስቧል፡፡ በክልሉ በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት በእጅጉ ማዘኑን የገለፀው መድረክ፤ ነዋሪነታቸው በጎንደር ደባርቅ ከተማ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ተለይተው ንብረታቸው እንዲወድም መደረጉንም አጥብቆ ኮንኗል፡፡
በተመሳሳይ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት (መዐሕድ)፤ በአገሪቱ እየተከሰቱ ያሉት ግጭቶች እንደሚያሳስበው የገለፀ ሲሆን የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይም በሰላም እንዲፈታ በአፅንኦት ጠይቋል። በመዲናዋ ቤታቸው የፈረሰባቸው ዜጎች ጉዳይም እንደሚያሳስበውና መንግስት የመጠለያ ቦታ ሊሰጣቸው እንደሚገባ መዐሕድ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

መሪ (ሪዳ) እና ገዥ (ሐጉካይ-ሻ) “ገዥ ጉልበት ይፈልጋል፤ መሪ ግን ጥበብ ይፈልጋል” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

መሪ (ሪዳ) እና ገዥ (ሐጉካይ-ሻ) “ገዥ ጉልበት ይፈልጋል፤ መሪ ግን ጥበብ ይፈልጋል” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የሩቅ ምሥራቆቹ ጃፓኖች እንዲህ የሚል ለዓለም የተረፈ ታሪክ አላቸው፡፡
በ17ኛው (መክዘ) ላይ በዓይን ሕመም የሚሰቃይ ጎ- ሳይ የተባለ አንድ የጃፓን ንጉሥ ነበረ፡፡ በሀገረ ጃፓን የሚገኙ ሐኪሞችን ሁሉ ጠርቶ ለስቃዩ መድኃኒት እንዲፈልጉለት ቢያዝም ሊያገኙ ግን አልቻሉም፡፡ በኮርያ፣ በቻይና፣ በሞንጎልያና በሩሲያ ሳይቀር ታዋቂ የሆኑ ባለ መድኃኒተኞችን እየጠራ፣ ገንዘብና ሥልጣን ለመሸለምም ቃል እየገባ፣ ሕመሙን ለማዳን ሞከረ፡፡ ግን አልተቻለውም። በመጨረሻም ሞንጎልያ ውስጥ በኡውስ ሐይቅ አጠገብ፣ ዑላንጎም በተባለ መንደር እጅግ የታወቀ ባለ መድኃኒት መኖሩ ተሰማ፡፡
ንጉሥ ጎ- ሳይም ኦይራት የተባሉትን የሞንጎልያ ሲራራ ነጋዴዎች፤ ይህን ባለመድኃኒት እንዲያመጡለት ወርቅ ሰጥቶ ላካቸው፡፡ ከአራት ወራት በኋላም ኦይራት የሚባሉት ሲራራ ነጋዴዎች፤ ባለመድኃኒቱን በድንክየዎቹና ፀጉራሞቹ ግመሎች ጭነው አመጡለት፡፡ ንጉሥ ጎ-ሳይ ባለ መድኃኒቱ መምጣቱን ሲሰማ የመዳን ተስፋው ለመለመ፡፡
ሞንጎልያዊው ባለመድኃኒተኛ ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብቶ ንጉሡን አገኘው፡፡ ንጉሡም ከሚያሰቃየው የዓይን ሕመም ከፈወሰው የፈለገውን ሁሉ እንደሚሰጠው ቃል ገባለት፡፡ ሞንጎልያዊው ባለመድኃኒተኛ፤ የንጉሡን ሕመም ለማዳን የሚችል መድኃኒት እንዳለው ነገር ግን ንጉሡ መዳን የሚችለው አንድ ነገር ሲያሟላ መሆኑን ተናገረ። ንጉሥ ጎ-ሳይ የተባለውን ሁሉ ለማሟላት ቃል ገባ፡፡ ሞንጎልያዊው ባለመድኃኒትም ‹‹ሐኩጋይ-ሻ› (ገዥ) ከሆንክ አትድንም፤ ‹ሪዳ› (መሪ) ከሆንክ ግን ትድናለህ› ሲል ነገረው፡፡ ንጉሥ ጎ-ሳይ የባለመድኃኒቱ ነገር ስለገረመው በገዥና በመሪ መካከል ያለውን ልዩነት ጠየቀው፡፡ ባለመድኃኒቱም፤ ‹ገዥ ጉልበቱንና ሀብቱን ብቻ የሚጠቀም አለቃ ነው፤ መሪ ግን አእምሮውንና ክሂሎቱን የሚጠቀም አለቃ ነው› ሲል በአጭሩ መለሰለት፡፡ ንጉሥ ጎ-ሳይም መሪ መሆኑን አረጋገጠለት፡፡
ሞንጎልያዊው ባለመድኃኒት ለዓይን ሕመም የሚሆነውንና በየቀኑ የሚቀባውን መድኃኒት ከሰጠው በኋላ እንዲህ ሲል አዘዘው፡- ‹ሕመሙ እስኪሻልህ ድረስ የምታየው ነገር ሁሉ አረንጓዴ መሆን አለበት፡፡ ከአረንጓዴ ቀለም ውጭ የምታይ ከሆነ ያገረሽብሃል› ሲል አስጠነቀቀው፡፡ ንጉሥ ጎ-ሳይም ያን ማድረግ ቀላል መሆኑን ነግሮት ተለያዩ። ሞንጎልያዊው ባለ መድኃኒትም ከ3 ወር በኋላ ተመልሶ ሊመጣ ቃል ገብቶ፣ ኦይራት ከተባሉት ሲራራ ነጋዴዎች ጋር ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡
ንጉሥ ጎ-ሳይ ባለሟሎቹን ሁሉ ጠራ፡፡ ባለመድኃኒቱ የነገራቸውን በማስታወስም ከቤተ መንግሥቱ ጀምሮ ያሉ ዕቃዎች፣ ግድግዳዎች፣ ዛፎች፣ ተራሮችና ኮረብቶች ሁሉ አረንጓዴ ቀለም እንዲቀቡ አዘዘ፡፡ የከተማው ነዋሪም ቤቶቹን ሁሉ አረንጓዴ እንዲቀባ ዐዋጅ ወጣ፡፡ ከአረንጓዴ ልብስ ውጭ መልበስም ተከለከለ፡፡ እንስሳትም አረንጓዴ ቀለም እንዲቀቡ ተለፈፈ፡፡ ለዚህ ዐዋጅ የሚውል በሚሊዮን የሚቆጠር ወርቅ ወጭ ሆነ፡፡ ከኮርያ፣ ከቻይና፣ ከሩሲያና ከሕንድ ሳይቀር ቀለም በገፍ ወደ ጃፓን ገባ፡፡ ሰውና እንስሳውም መሬት ተተክሎ የበቀለ እስኪመስል ድረስ አረንጓዴ ሆነ፡፡
ከሦስት ወራት በኋላ ሞንጎልያዊው ባለመድኃኒት ቃል በገባው መሠረት ወደ ጃፓን መጣ፡፡ የንጉሥ ጎ-ሳይ የዓይን ሕመም ለውጥ አላመጣም፡፡ ሀገሪቱ ግን አረንጓዴ በአረንጓዴ ሆናለች፡፡ ባለመድኃኒቱም ወደ ጃፓን ከገባበት ቀን ጀምሮ ባለማቋረጥ ይስቅ ነበር፡፡ በመጨረሻም ወደ ቤተ መንግሥቱ ሲቃረብ የንጉሡ ልብሶች አረንጓዴ ቀለም ሲቀቡ ደረሰ። ይህንን ሲመለከትም ሳቁን ፈጽሞ መቆጣጠር አልቻለም ነበር፡፡ ንጉሡም የባለመድኃኒቱን ሁኔታ ተመልክቶ ግራ ተጋባ፡፡
ንጉሡ ለምን እንደዚያ እንደሚስቅ ባለመድኃኒቱን ጠየቀው፡፡ ሕመሙም እንዳልተሻለው ገለጠለት። ባለመድኃኒቱም እንደዚያ የሚያስቀው የንጉሡ ሞኝነት መሆኑን ገለጠለት፡፡ ሕመሙ ያልተሻለው ግን ገዥ እንጂ መሪ ባለመሆኑ እንደሆነ ነገረው። ንጉሡም ሞኝነቱንም ገዥነቱንም አብራርቶ እንዲነግረው ሞንጎልያዊውን ባለመድኃኒት ጠየቀው፡፡ ባለ መድኃኒቱም፤ ‹አንተ ሁሉን ነገር በሥልጣንና በገንዘብ ብቻ ነው የምታስበው። ይህ ደግሞ የ‹ሐኩጋይ-ሻ› (ገዥ) መለያ ጠባይ ነው። ሁሉንም በጉልበቱና በገንዘቡ ብቻ ማድረግ እንደሚችል ያስባል፡፡ በርግጥ የምታየው ነገር ሁሉ አረንጓዴ መሆን አለበት ብየ ነግሬህ ነበር፡፡ አንተም አገልጋዮችህንና ሕዝብህን እያስጨነቅህ አገሩን ሁሉ አረንጓዴ ቀለም ለመቀባት ሞከርክ፡፡ ለመሆኑ በዚህ አያያዝህ ቢበዛ ከዚህ ከተማ ውጭ ልትሻገር ትችላለህን? ዓለምንስ ሁሉ አረንጓዴ ቀብተህ ትጨርሳለህን? ሰማዩን፣ ፀሐይን፣ ጨረቃን፣ ከዋክብትንና ታላላቅ ተራሮችን ምን ልታደርጋቸው ነው? ከሁሉም በላይ እሳትን ምን ልታደርገው ነው? አየህ የገዥነት(‹ሐኩጋይ-ሻ›) ትልቁ ችግሩ ሁሉንም ነገር በጉልበቴና በገንዘቤ እቆጣጠረዋለሁ ብሎ ማሰብ ነው፡፡ ይህንን በተወሰኑ ነገሮች ላይ ተግባራዊ ማድረግ ሲችል፣ ገዥ በዚያ ይታለላል፡፡ የተወሰነ ጊዜ ይሳካልሃል፡፡ ያም የበለጠ ገዥነትህን ይጨምረዋል። እየቆየህ ስትሄድ ግን በገንዘብህና በጉልበትህ የማትደርስበት ኃይል መኖሩን ታውቃለህ፡፡ ልክ እንደ ፀሐይ፣ ጨረቃና እሳት፡፡
አእምሮ ቢኖርህ ኖሮ ‹ሪዳ› (መሪ) ትሆን ነበር፡፡ ሪዳ (መሪ) ብትሆን ኖሮ ደግሞ ችግሩን ለመፍታት ጉልበትህንና ገንዘብህን ለመጠቀም ከምትሮጥ ይልቅ አእምሮህን ትጠቀም ነበር፡፡ ዓይንህ አረንጓዴ ነገር ብቻ እንዲያይ ከፈለግህ ነገሩ በጣም ቀላል ነው። ያኔ እኔ አንተን ሳዝህ ‹በጣም ቀላል ነው› ስትለኝ፣ እውነትም አእምሮ ያለህ ‹ሪዳ› (መሪ) ነህ ብዬ አስቤ ነበር፡፡ አሁን ግን ተሳስቼ እንደነበር ገባኝ።
‹ቀላሉ መንገድ ምን ነበር?› አለ ንጉሥ ጎ-ሳይ በሁኔታው እየተደነቀ፡፡
‹ቀላሉ መንገድ› አለ ሞንጎልያዊው ባለ መድኃኒት፡፡ ‹ቀላሉ መንገድ የምታየውን ነገር ሁሉ አረንጓዴ አድርጎ የሚያሳይ መነጽር በሁለት ‹ስየሶ ገንቦ› ገዝተህ ዓይንህ ላይ ማድረግ ነው፡፡ ይህንን መነጽር ብታድርግ ኖሮ አገልጋዮችህንና ዜጎችህን ማስጨነቅ፣ ላንተ ሲባል ምድሩን ሁሉ አረንጓዴ ቀለም ማስቀባት፣ አረንጓዴ ልብስ ማስለበስና አገሩንም ማበላሸት አይጠበቅብህም ነበር፡፡ ገዥ(ሐኩጋይ-ሻ) ስለሆንክ እንጂ መሪ(ሪዳ) ብትሆን ኖሮ ለሀገርህና ለሕዝብህ ስትል አንተ ትሰቃያለህ እንጂ ለአንተ ስትል አገርህንና ሕዝብህን አታሰቃይም ነበር፡፡ ገዥ(ሐኩጋይ-ሻ) ስለሆንክ እንጂ መሪ(ሪዳ) ብትሆን ኖሮ አገርህን አረንጓዴ ለማድረግ ስታስብ፣ ሕዝብህን ማሳመን ይጠበቅብህ ነበር፡፡
ገዥ(ሐኩጋይ-ሻ) ስለሆንክ እንጂ መሪ(ሪዳ) ብትሆን ኖሮ ያኔ እኔ ‹አረንጓዴ ነገር ብቻ ማየት አለብህ› ብዬ ሳዝህ ‹ቀላል ነው› ከምትል ይልቅ ‹እንዴት አድርጌ› ብለህ መጠየቅ ነበረብህ፡፡ ገዥ ተገዥ ይፈልጋል፡፡ መሪ ግን አማካሪ ይሻል፡፡ ገዥ ጉልበት ይፈልጋል፤ መሪ ግን ጥበብ ይፈልጋል። ገዥ ሁሉም ነገር ቀላል ነው ይላል፡፡ መሪ ግን እንዴት ቀላል ሊሆን እንደሚችል ያስባል፣ ይጠይቃል፡፡ ገዥ የሚመስለውንና የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል። መፍትሔው ቢመጣ ባይመጣ፣ ችግሩ ቢፈታ ባይፈታ፣ ሌላ ችግር ቢመጣ ባይመጣ ግድ የለውም። መሪ ግን ማድረግ የሚችለውንና የሚመስለውን ሁሉ አያደርግም፡፡ ለውጥ የሚያመጣውን ነገር ብቻ እንጂ፡፡ ቢችልም፣ ዐቅም ቢኖረውም፣ ሥልጣን ቢኖረውም ለውጥ የሚያመጣ መሆኑን ካላረጋገጠ አያደርገውም፡፡ ለመሆኑ ይህንን ውሳኔ ስትወስን የሀገርህን ኬንጃ (ጠቢባን) አማክረሃቸዋል፡፡ ብታማክራቸው ኖሮ እንዲህ አገሩን ሁሉ አረንጓዴ አታደርገውም ነበር፡፡
ታድያ አንተ እንዴት ትድናለህ? ራስህን መቀየር ሲገባህ ዓለምን ልትቀይር ተነሣህ፡፡ መቀየር የነበረብህ የምታየውን ነገር ሳይሆን አንተ የምታይበትን መንገድ ነበር፡፡ አረንጓዴውን መነጽር ብትገዛ ኖሮ አንተ ዓለምን አረንጓዴ አድርገህ ታያታለህ። ሌላው ደግሞ እንደሚፈልገው ቀይም፣ ጥቁርም፣ ነጭም፣ ቢጫም አድርጎ ያያታል፡፡ አሁን ግን አንተ አረንጓዴ ስለምትፈልግ ብቻ ዜጎችህ ሁሉ አረንጓዴ እንዲያዩ፣ አረንጓዴ እንዲለብሱና አረንጓዴ እንዲበሉ አደረግካቸው፡፡ ካሚ(ፈጣሪ) ልዩ ልዩ አድርጎ የፈጠረውን ሕዝብ አንተ አንድ ዓይነት ልታደርገው ፈለግክ፡፡ ያውም ላንተ ሲባል፡፡
መሪ(ሪዳ) ለሕዝብ ነው፡፡ ገዥ(ሐኩጋይ-ሻ) ስትሆን ግን ሕዝቡ ያንተ ነው፡፡ እንደፈለግክ ታደርገዋለህ፡፡ ለገዥ ሕዝብና ኪያሜሩ(ግመል) አንድ ነው፡፡ ለገዥ ሁለቱንም እንደፈለጉ ማድረግ ይቻላል። ለገዥ ሁለቱም ሀብት ናቸው፡፡ ገዥ ስለ ሕዝቡ እርሱ ያውቃል፡፡ የሕዝቡም ጭንቅላት በእርሱ ላይ ነው፡፡ እርሱ አሰበ ማለት፣ ሕዝቡ አሰበ ማለት ነው፡፡ እርሱ ፈለገ ማለት፣ ሕዝቡ ፈለገ ማለት ነው፡፡
ታድያ አንተ እንዴት ትድናለህ? ወርቅህን አልፈልግም፡፡ ሽልማትህም ለራስህ ይሁን? እንካ አረንዴውን መነጽር፡፡ ከቻልክ ያበላሸኸውን አስተካክለው፡፡ ያጠፋኸውን መልሰው፡፡ ካልቻልክ ሌላ ጥፋት ሳይደርስ ባለበት እንዲቆም አድርገው፡፡ እኔ ግን ወደ ሀገሬ ወደ ኡቭስ ሐይቅ፣ ወደ ዑላንጎም መንደር እሄዳለሁ፡፡ በረግረጉ ሥፍራም ይህንን ሞኝነትህን እያሰብኩ ስስቅ እኖራለሁ፡፡ ኮክ-ኦህ-ሩኽ (ልቡና) ካገኘህና ከገዥነት ወጥተህ መሪ መሆን ስትጀምር ጥራኝ፡፡ በሕይወት ካለሁ እመጣለሁ። ያኔ ሕመምህን ፈጽሞ እንዲድን አደርገዋለሁ፡፡ ላሁኑ ግን ገን-ኪ-ደ (ደኅና ሁን፣ ራስህን ጠብቅ)፡፡
ሞንጎልያዊው ባለመድኃኒት ከጃፓን እስከ ሞንጎልያ፣ እስከ ኡቩስ ረግረጋማ ሥፍራ ድረስ በየደረሰበት ሁሉ ይህንን የንጉሡን ታሪክ እየተረከው ሄደ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ ታሪክ ከኢራን እስከ ጃፓን ድረስ በየቋንቋው ይተረካል ይባላል፡፡