የፃድቃንና ጆቤ የውድቀት ሌጋሲ በኢትዮጵያ አየር ኃይል

ከቀድሞው አየር ኃይል ዓለም አቀፍ ህብረት

“እናንተ ዛሬ የአየር ኃይላችንን የጥራት መመዘኛ አሟልታችሁ በውጪ አገር ትምህርታችሁን ለመከታተል የምትሄዱ ወጣቶች ፤ በቅድሚያ እንኳንMajor general Amha Desta ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ። በቆይታችሁ ወቅትም ትምህርታችሁን በሚገባ ቀስማችሁ አገራችን ኢትዮጵያን ለማገልገልና ለህዝባችን ዋጋ ለመክፈል መዘጋጀት እንደሚኖርባችሁ ለአፍታም መዘንጋት የለባችሁም ። ትልቅ አደራም ተሸክማችኋል ። ምንም እንኳ የከፋ ድህነት ያለባት አገር ዜጐች ብንሆንም በአያት ፣ ቅድመ አያቶቻችን ተጋድሎና መስዋዕትነት የቀደምት ነፃነት ባለቤት አገር ዜጐች በመሆናችን እራሳችንን በኩራት ቀና አድርገን እንድንሄድ አስችሎናል ። በርከት ያሉ አገሮች ዜጐቻቸውን የሚያስተምሩበት ት/ቤት ውስጥ ከመጨረሻዎቹ ደሃ አገሮች መካከል ብንገኝም ጊዚያዊ የሆነውን ቁሳዊ ድህነትን ተቋቁሞ የአገር አደራን መወጣትን የመሰለ ታላቅ ክብር እንደ ሌለ ለኛ ለኢትዮጵያውያኖች ማንም ሊያስተምረን አይችልም ። በዕውቀት በልፅጋችሁ ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመማር ከጊዜው ጋር አብሮ ለመጓዝ የምትችል ኢትዮጵያን ለትውልድ የማስተላለፍ ክቡር የዜግነት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ።

ከሚገጥሟችሁ የብዙ አገር ተማሪዎች መካከልም ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶች በዚሁ ት/ቤት ውስጥ ዜጐቻቸውን ያስተምራሉ ። ንቀት ፣ ጥላቻና ትንኰሳ ሊደረግባችሁ ይችላል ። እንደዚህ አይነት ሁኔታዎችን በተቻለ መጠን በትዕግስትና በአስተዋይነት ማሳለፍ ያስፈልጋል ። ምክንያቱም አገራችሁ ከሰጠቻችሁ አደራና ከሄዳችሁበት ዓላማ በምንም መንገድ ዝንፍ ማለት አይገባችሁም ። እንዲህ ስላችሁ ግን የዜግነት ክብርን የሚነካ ፣ ህሊናን የሚያቆስል ትንኰሳ ከሆነ ግን በምንም ዓይነት ዝም ብሎ ማለፍ አይገባም ፤ አፀፋውን መመለስ ይኖርባችኋል ። በዚህ ጉዳይ ለሚመጣ ማናቸውም ነገር ከጐናችሁ ነን ። መልካም የትምህርት ዘመን”። 

ሜ/ጄ አምሃ ደስታ፣ ታህሳስ 1976 ዓም፣ ደብረ ዘይት – ሃረር ሜዳ

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s