የአጋርነት መግለጫ ለጎንደር ሕዝብ እንቅስቃሴ (አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ከሎስ አንጅለስ እና አካባቢው)

አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ከሎስ አንጅለስ እና አካባቢው

በ7/24/2016 በሎስ አንጅለስ እና አካባቢዋ የምንኖር አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ተገናኝተን በአሁኑ ሰዓት በጎንደር የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነታቸውን በአግባቡ በመጠየቃቸው እየደረሰባቸው ስለአለው ስቃይ እና በሌሎችም አካባቢዎች እንዲሁ መሰረታዊ መብታቸው እንዲከበርላቸው ጥያቄ በማንሳታቸው እየደረሰባቸው ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት በሰፊው ተወያይተንበታል።'Long Live Ethiopia' poster at Gondar protest

በተለይ በአሁኑ ሰዓት የወልቃይት ሕዝብ መሬቱን በግፍ ተቀምቶ የበይ ተመልካች መሆኑ ሳያንሰው የማንነቱ መግለጫ የሆነውን አማራነቱን በመካድ ያልሆነውን ነህ ተብሎ የተጫነበትን የማንነት ተፅእኖ በመቃወም በሚአደርገው የሞት የሽረት ትግል ይህ ጀግና ሕዝብ እያደረገልን ለአለው ጥሪ ዝምታን የሚመርጥ ህሊና ስለማይኖረን የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል።

ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምእራብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመሰረታዊ መብቱ በመታገሉ ምክንያት እየደረሰበት ያለውን ማንኛውንም ኢሰብአዊ ድርጊት በጥብቅ እናወግዛለን። እየሞተ፣ እየተደበደበ፣እየታሰረ፣ ከቦታው እየተሰደደ እና ተዘርዝረው የማያልቁ ግፎች እየተፈጸሙበት  በእነዚህ ድርጊቶች ሳይበገር እየአደረገ ያለውን ተጋድሎ  ማድነቅ ብቻ ሳይሆን ለሚአደርገው ተጋድሎ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ብለን የምናስባቸውን ሁሉ በየጊዜው እየተመካከርን ወደተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት ብሎም ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚአደርጉትን በማንኛውም መንገድ ለመርዳት ወስነናል።FBC's news report on Gondar protest

በአገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም አካባቢ እየተፈፀመ ያለው ግፍ የሚካሄደው በጭካኔው፣ ከባእድ የሱዳን ወታደሮች ጋር ወግኖ ወገኖቹን በማጥቃት፣በመካከላችን ያለውን ትስስር ለማላላት በማከፋፈል ስራው እና ለግድያ በአሰለጠነው አግአዚ በመመፃደቅ ሽብር በመፍጠር ተወዳዳሪ በሌለው የወያኔ ስርዓት ስለሆነ መፍትሄው ይህን ስርዓት ከስሩ ገርስሶ መጣል ብቻ መሆኑን ተረድቶ ሕዝቡ ትግሉን በሁሉም አቅጣጫ አቀጣጥሏል፡፡ እኛም በየቦታው የተነሳው  የፃነት ጥያቄ መልስ የሚአገኘው እና የዜጎች ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ተጠብቆ በሰላም መኖር የሚቻለው የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው ስርዓት ሲወገድ ነው ብለን እናምናለን። በአንድ አካባቢ የሚፈፀመው አስከፊ ክስተት ነገ በሌላ አካባቢ የሚፊፀም እኩይ ተግባር ስለሆነ ይህንን ኃይሉን አሰባስቦ በተናጠል በሕዝብ ላይ ጉዳት እያስከተለ ያለውን ስርዓት ለማስወገድ የትግሉን አድማስ በማስፋት በሁሉም አቅጣጫ በአንድነት ስሜት ኃይሉን አሰባስቦ በጋራ እንዲነሳ ጥሪ እናስተላልፋለን። የሁላችንም ጠላት የሆነውን ወያኔ አስወግደን ሁላችንም ተጠቃሚ የምንሆንበትን ነፃነት ማግኘት የምንችለው አንድነት ኃይል መሆኑን ተረድተን በመቀራረብ በጋራ ስንሰራ ብቻ በመሆኑ ይህንን በመረዳት እየተቀራረቡ  ለመስራት ወስነናል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

ሞት ለወያኔ

አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ከሎስ አንጅለስ እና አካባቢው

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s