ባህርዳር የከባድ መሳሪያ ድምጽ ይሰማባታል;; ከፍተኛ ግጭት ተቀስቅሷል::

#‎BahirDar‬ ‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Amharaprotests‬ ባህርዳር የከባድ መሳሪያ ድምጽ ይሰማባታል;; ከፍተኛ ግጭት ተቀስቅሷል;; ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች መገደላቸው ይነገራል;; ባህር ዳር የስልክ መስመር ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል። ከፍተኛ ተኩስ በባህር ዳር ተጀምሯል። በባህርዳር ፍልሚያው ቀጥሎአል። በአባይ ማዶ ታንኮች ወጥተዋል። አጋዚ በጭካኔ እርምጃ እየወሰደ ነው። ህዝቡ በአንድነት እየተዋደቀ ነው።

የቆሰሉና የሞቱ ሰዎች ቁጥር አይታወቅም፤ ዓባይ ማዶ ኮበል በቃጠሎ ወድሟል ከጎንደር የሚሔዱ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ መታገዳቸው ለግጭቱ መንስኤ ሆኗልበጎጃም እምብርት ባሕር ዳር ዐማሮች በጠዋት ነበር ወደ ተጋድሎ ሰልፍ የወጡት፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ በዐማራ ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን በደል እና የጅምላ ግድያ በማውገዝ ወደ መስቀል አደባባይ ሕዝቡ በአንድነት ሔደ፡፡ በዚህ መካከል ከጎንደር ለተጋድሎ የሚመጡ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ በወያኔ ጦር ወደ ባሕር ዳር መግባት እንዳይችሉ መታገዳቸው ተሰማ፡፡ ሕዝቡ ተመልሶ ከጎንደር አካባቢ የመጡትን ወገኖችን ለማስለቅ ወደ ዓባይ ማዶ መንገድ አመራ፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ተሳታፊዎች እግረ መንገዳቸውን ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ (ፖሊ ካምፓስ)፣ ክልል ምክር ቤት፣ አማራ ብድርና ተቋምና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች አካባቢ ያሉ የወያኔን ድሪቶ ባንዲራ የአባቶቻችን ደም በፈሰሰባት ትክክለኛ ሰንደቅዓላማ በመቀየር እንዲሁም የክልሉ ምክር ቤት ፊት ለፊት የነበረውን የመለስ ቢል ቦርድ በማቃጠል ወደ ዓባይ ማዶ ነገዶ፡፡ ባሕር ዳር ከተማ የቀረ አንድም ዐማራ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡
የዓባይን ድልድልይ ተሻግረው ወደ ዘንዘሊማ ለመሔድ መንገድ ሲጀምሩ አዲስ ዓለም ገበያ አካባቢ ‹‹ኮበል›› የሚባል የወያኔ ምልስ ወታደሮች ንብረት የሆነ ስጋ ቤትና ግዙፍ የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት አለ፡፡ ይህ ድርጅት በተለምዶም ‹‹ዳሸን ቢር ጋርደን›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከዚህ ግቢ ውስጥ በሰለማዊ መልኩ ተጋድሎውን ሲቀጥል በነበረው ሕዝብ ላይ የተኩስ እሩምታ ተከፈተ፡፡ ኮበል ማዶ ካሉ ኮንዶሚኒየም ሕንጻዎች ፎቅ ላይ የወጡ የወያኔ አልሞ ተኳሾች በተቃራኒ አቅጣጫ ከሕዝቡ ላይ ጥይት አርከፈከፉ፡፡ ባዶ እጃቸውን የነበሩ ዐማሮችን ደም ወያኔዎች አፈሰሱ፡፡

በዚህ የተበሳጨው የዐማራ ነበልባል ወጣት ከማደያ ነዳጅ እየቀዳ የኮበል ኢንዳስትሪን ሙሉ በሙሉ በእሳት አጋዬ፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዐማሮች ሌሎችን ለማኖር ሲሉ ተሰውተዋል፡፡ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ አሁን በዓባይ ማዶ መካከለኛ ክሊኒክና በአዲስ ዓለም ጠቅላላ ሆስፒታል በርካታ እስረኛና ቁስለኛ እንዳለ ነው ከቦታው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡ ባሕር ዳር በአሁኑ ሰአት ዝናብ ቢሆንም ወጣቶች ተጋድሏቸውን አላቆሙም፡፡ ‹‹ደም ሰፈስ ደም ይፈላል›› እንዲሉ አበው፤ የዐማራ ወጣቶች ተጋድሎ ያለምንም ጥርጥር በሰማእት ወንድሞቻችን አጥንት ካስማ መሠረት ላይ ይገነባል፡፡ ይህ ሁሉ ግን የመጀመሪያው መጨረሻ ነው!!

እስካሁን ከ40 በላይ ወጣቶች ተጎድተው በፈለገ ህይወት እና በጋምቢ ሆስፒታሎች መተኛታቸውን ነዋሪዎች እየተነጋሩ ነው። ዳባትም ተቃውሞም በርትቷል። በአዲስ አበባም በርካታ ወጣቶች እየታፈሱ ነው።የአጋዚ ወታደሮች ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መውሰዳቸውን ተከትሎ የባህርዳር ህዝብ መላው ኢትዮጵያዊ እንዲነሳ ጥሪ እያቀረቡ ነው።የሕወሃት ታጣቂዎች በሕዝቡ ላይ መተኮስ ጀመረዋል። ሰዎቹ መግደል ሲጀመሩ ኔትዎርኩን እንዳለ ዘጉት።

አባይ ማዶ ላይ የጀመረው የተኩስ ናዳ ወይን ቤት አካባቢ የታሰሩትን ለማስለቀቅ በተደረገው ሙከራ ላይ በጣም የከፋ አደጋ እንዳደረሰ ገልፀውል። ከአስር የማያንሱ የቀይ መስቀል ተሽከርካሪዎች የተጎጅዎችን አስከሬን እና ቁስለኛ ሲያመላልሱ ታይተዋል። ሰልፈኛው አሁንም እንዳልተበተነ የሚገልፀው የአይን እማኝ ሰልፉ በዚህ እንደማይቆም የህዝቡን ስሜት በማየት አረጋግጦል። ቀጣይ ለሚደረጉት ሰልፎች የታጠቁ አካላት ከህዝብ ጋር በመሆን የሚደርሰውን ጉዳት መከላከል እንዳለባቸው የጠቆመው እማኝ ለዛሬው ከፍተኛ ጉዳት ዋና ምክንያት በመካከላችን ምንም አይነት የታጠቀ ሃይል አለመኖሩ ነው ሲል ተናግሯል።

Image may contain: one or more people
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s