የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የመጨረሻዉን ጦርነት በጎንደር ህዝብ ልይ ከፈተ! (ጎንደር ሕብረት)

ጎንደር ሕብረት

አጥፍቶ ለመጥፋት በጭፍን የሚጓዘዉ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር፤ የመቃብር ጉድጓዱን በጎንደር በመቆፈር ላይ ይገኛል። በኢትዮጵያን ህዝብ ላይ ጦርነት መክፈት ሃላፊነት የጎደለዉ የእልቂት ዘመቻ ነው። እንደ ኢትዮጵያዊነት፤ ስህተትን ቆሞ ከማሰብ ይልቅ፤ ሥራዓቱን መሸከም ያንገፈገፈውን ሕዝብ በጥይት መረፍረፍ፤ የራሱን ዘረኛ ስርዓት ዉድቀት ከማፋጠን ሌላ አንድም የሚፈይደዉ ነገር የለም። በታሪክ እንዳየነው፤ ህዝባዊ መዓበልን የሚያቆመው ምንም ኃይል እንደሌለ ሁሉ፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ያለ ጥርጥር ያሸንፋል። ሃላፊነት የጎደለዉ ዘራፊዉ ወያኔ ከ800,000 በላይ የጎንደር ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ወደ ትግራይ በጉልበት የተከለለውን የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት የጎንደር መሬት እና የህዝቡንም የአማራ ማንነት አስቸኳ ምላሽ እንዲያገኝ ጠይቆ፤ በስርዓቱ ላይ ያለዉን ጠንካራ ተቃዉሞ ባሰማ ማግስት፤ የአገር መሪ ነዉ ተብሎ ለይስሙላ የተቀመጠዉ ጠቅላይ ሚኒሲተር፤ የሚሊዮን ህዝብ ጥያቄ ዋጋ የለዉም ብሎ በወያኔ ተገዶ ሲናገር፤ መንግስት እንደሌለ ይፋ ማረጋገጫ ሆኗል።

Renewed Gondar protest August 5, 2016

ዛሬ በጎንደር ህዝብ ላይ የተከፈተዉ፤ ጦርነት በትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የተቀነባበረ፤ በምድርም ሆነ በአየርም ጥቃት ሰንዝሮ የህዝብ ወገን የሆነዉን ኮሎኔል ደመቀን አፍኖ ለመዉሰድ ሌተ እና ቀን ሲሳራ የዋለ ያደረው መሰሪ ተንኮል ውጤት ነው። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ፤ የጎንደሬው ብቻ ሳይሆን፤ የወልቃይት ጠገዴን መሬት ጎንደሬነት፤ ሕዝቡም አማራ መሆኑን መሰረት አድርጎ ጠንክሮ የታገለ እና ትግሉን የመራ፤ የማንነት ምሳሌ የሆነ ቆራጥ የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ነው። በመሆኑም፤ ይህን ጀግና፤ ለወያኔ አሳልፎ ላለመስጠት የሚደረገውን ግብግብ፤ የጎንደሬው ብቻ መስሎ የሚታየው ዜጋ ካለ፤ ነገም በአገሪቱ ያሉትን ጀግኖቻችን፤ እየተነጣጠልን አሳልፈን ልንሰጣቸው እንደምንችል ለወያኔ የልብ ልብ መሥጠት መሆኑን ተገንዘበን፤ ትግሉን ከጫፍ እስከ ጫፍ አቀጣጥለን፤ የወያኔን ፍፃሜ እንድናውጅ ጥሪያችን እናቀርባለን።

በመጨረሻም፤ ንብረት ማውደም፤ ድልድይ ማፍረስ፤ የአገራችንን ቋሚ ንብረቶች ማውደም የወያኔ ቋሚ ባህሪ እንጂ፤ የጨዋው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህሪ አይደለም! በመሆኑም በየትኛውም አገራችን ዙሪያ ትግሉን የምትመሩ ድርጅቶችም ሆነ ሰልፉን አቀነባባሪ ኮሚቴዎች፤ የወያኔን እና ደጋፊዎቹን ንብረት፤ ከጊዚያዊ አገልግሎት ውጭ ማድረግ እንጂ፤ ቋሚ ውድመት ማድረስ፤ ወያኔ ሲያልፍ ለአገራችን እና ለሕዝባችን በቀጣይነት አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለውን መሰረት መናድ ነው እና ጥንቃቄ ይደረግበት ዘንድ እናሳስባለን።

ወቅታዊ መፈክሮቻችን!!Renewed Gondar protest

1. መለዮ ለባሾች ሆይ! የበሰበሰውን ከፋፋይ ሥራዓት ለማስቀጠል ወንድሞቻችሁን መጨፍጨፋችሁን አቅማችሁ፤ ወደ ካምፓችሁ ተመለሱ!! ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ኮኔረል ደመቀና ታፍነዉ የተወሰዱ የኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ይፈቱ!

2. በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እነ አንዷለም አራጌ ፤ እነ በቀለ ገርባ እና የሃይማኖት አባቶች ባስቸኳይ ይፈቱ!

3. በጾረና፤ በሱማሌ፤ በሱዳን የሰፈረዉ የሰራዊት ደሞዙ በአብዛኛ ወራት ሳይከፈለዉ የቆየዉ ገንዘብ በአስቸኳ ተጠቃሎ ይከፈለዉ!

4. ከ60 በላይ የታሰሩ፤ የቅማንት ማንነት አስከባሪ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ ይፈቱ!!

5. የአማራና ኦሮሞ የትግራይ ያልሆኑ መለዮ ለባሽ ሰራዊት አባላትን በአፈና አስሮ የማሰቃየት ዘመቻ በአስቸኳይ ያቁም!

6. በአማራ ክልል የታሰሩ 180,000 እስረኞችና በአለፉት ስድስት ወራት ከ10,000 በላይ የታሰሩ የኦሮሞ ወንድም እና እህቶቻችን ያለምንም ቅደመ ሁኔታ በአስቸኳይ ይፈቱ!

7. ሕዝባዊ እንቅስቃሴዉ በሰፊዉ ለወያኔ ፋታ ሳይሰጥ በየቀኑ እና በተከታታይ ያለምንም ማቋረጥ ይቀጥል!

8. ከህዝብ አብራክ የወጣዉ ሰራዊት የህዝብ አጋር ሁኖ በመቆም የህዝብ የበላይነትን ያረጋግጥ!

9. የሰባቱ የጎንደር አዉራጃ የታጠቀ የህዝብ ሃይል ጎንደር ከተማን በሃላፊነት ይቆጣጠር!

መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጾታ ሃይማኖት እድሜ ሳይለይ ያለዉን ሁሉ ለለዉጥ የቆመዉን ሃይል በመመገብ፤ በማጠጣት እንዲሁም አስፈላጊዉን ሁሉ በማቅረብ የትግሉ ተሳታፊ እንዲሆን ከልብ የመነጨ ጥሪያችን እናቀርባለን!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ጎንደር ሕብረት

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s