በደብረ ማርቆስ የተቃውሞ ሰልፍ የሕወሃት ቅጥረኞች በርካታ ሰዎችን በጥይት መተዋል፣ ሕዝቡም መጠነኛ የሃይል ምላሽ ሰጥቷል

የደብረ ማርቆስን የተቃውሞ ሰልፍ ውሎ በተመለከተ የኢሳት ዘገባን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ

(ECADF)— በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች ተጠናክሮ የቀጠለው ሕዝባዊ ተቃውሞ ያሰጋው ሕወሃት ወታደሮችን ከኤርትራ ግንባርና ከወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች ሳይቀር ሕዝባዊ ተቃውሞ ወደ ጠነከሩባቸው አካባቢዎች በገፍ እያጓጓዘ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት ዛሬ የደብረ ማርቆስ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ወደ አደባባይ እየወጡ ሳለ የገጠማቸውን ሲገልጹ “ለአንድ የደብረ ማርቆስ ነዋሪ 10 ወታደር የተመደበ ነው የሚመስለው” ብለዋል። ይሁንና የተቃውሞ ሰልፈኞቹ የሕወሃት/አጋዚ ጦርን ተኩስ እና ከበባ ከመጤፍ ሳይቆጥሩ “ግደሉን እንጂ አንበተንም” በማለት አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

የሕወሃት/አጋዚ ወታደሮች በቀጥታ ወደ ተቃውሞ ሰልፈኞቹ በመተኮሳቸው በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል። በምላሹም በድርጊቱ የተቆጣው የደብረ ማርቆስ ሕዝብ መጠነኛ የኃይል እርምጃ በመውሰዱ አንድ የፌደራል ፖሊስ ሲገደል ሌላ የፌደራል ፖሊስ ደግሞ ክፉኛ ተደብድቦ መትረፉን ምንጮቻችን ገልጸዋል።

ከተኩሱ ባሻገር ፖሊስ እና ወታደሮቹ ሰልፈኛውን ለመበተን አስለቃሽ ጭስ በሰልፈኛው ላይ በመተኮስ ላይ ይገኛሉ።

የደብረ ማርቆስ የተቃውሞ ሰልፈኞች ባለፈው ሳምንት በጎንደር እና ባህርዳር እንደታየው ከራሳቸው አንገብጋቢ ጉዳይ አልፈው ሕወሃት በኦሮምያ ክልል በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋም አውግዘዋል።

Debre Markos protest

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s