እኛ ተናግረናል አልተሰማንም..አሁን ጊዜው የሕወሃት ደጋፊዎች ነው – #ግርማ_ካሳ

13932703_846561085478848_6658846469192689771_nብዙ የሕወሃት ደጋፊዎችና ካድሬዎች እንደ ሮቦት የተሞሉትን ነው ዝም ብለው የሚተፉት። አንዳንድ ግን አሉ ትንሽም ቢሆን በሪዝን የሚያምኑ። ጦማሪ ዳንእል ብርሃኔ ከነዚህ መካከል ያለ ሞደሬት የሆነ አፍቃሪ ህወሃት ነው። አንዳንድ የሚጽፋቸው ነገሮች ይመቹኛል።

አንዳንዴ ግን ልክ እንደሌሎቹ ወርዶ ጭፍን የሆነ አስተያየት የሚሰጥበት ጊዜ አለ።

ያለፈው እሁድ በሸዋና በወሎ ሰላማዊ ሰልፎች ተጠርተው ነበር። ሕወሃት እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የወታደር ሃይል አሰማርቶ፣ ህዝቡ ከቤቱ እንዳይወጣ አድርጎ፣ መንገዶችን ሁሉ ዘግቶ ፣ በሺሆች የሚቆጠሩ ወጣቶችን አፍሶ ባለበት ሁኔታ፣ እንደ ባህር ዳርና እንደ ጎንደር ሰልፍ አልተደረገም በሚል “ከጥንት ከጥዋቱም ቢሆን ጎንደርና ትግራይ ሲጣላ፤ ወሎ ይገላግላል እንጂ ዱላ አያቀብልም ” ሲል ጽፏል።
ይህ አባባል ሁለት መሰረታዊ ግድፈቶች ያሉበት አባባል ነው። አንደኛው ይህ ጦማሪ ጎንደርና ትግሬ እንደተጣሉ አድርጎ ነው ያቀረበው። ትልቅ ስህተት። ጎንደር እና ትግሬ አልተጣሉም። ጠቡ በሕወሃት እና በሕዝብ መካከል ነው።

“አይደለም ይኸው ትግሬዎች እየተፈናቀሉ አይደለም ወይ ? ጠቡ ከትግሬዎች ጋር ነው” የሚል መከራከሪያ ሊቀርብ ይችላል። የትግራይ ተወላጆች ልክ አማራዎች ከኦሮሚያና ከሌሎች ክልሎች በግፍና በጭካኔ ሲፈናቀሉ፣ በእግራቸው፣ አሥር ኪሎሜትሮች ሲሰደዱ እንደነበረው አይነት አላየንም። የተወሰኑ የትግራይ ተወላጆች ማንም ሳይነካቸው፣ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው፣ ራሱ ሕወሃት ካልወጣችሁ ብሎ ቦይንግ አዘጋጅቶ እንዲለቁ ሲያደርግ ነው ያየነው።

በሌሎች ቦታዎች በትግሬዎች ላይ ጥቃት ተደረገ ከተባለ ደግሞ ልክ በኦሮሚያና በአማራው ክልል የተሰሩ ግፎች በመረጃ እንደሚቀርቡት፣ በትግራይ ወገኖቻችን ላይ የደረሰ ግፍ ካለ በመረጃ ይነገረንና እኛ በሌላው ላይ የደረሰውን እንዳወገዝነው በትግሬዎች ላይ የደረሰዉንም እናወግዛለን። በትግራይ ልጆች ላይ እየተፈጸ ያለ ጥቃት ካለ፣ ነገሩን በቶሎ ለማስቆምና  ጥቃት የፈጸሙትን ተጠያቂ ለማድረግ ይቻል ዘንድ መረጃዎች ያላችሁ በቶሎ ለሕዝብ አሳወቁ። በየትም ቦታም በማን ላይ ግፍ ሲፈጸም ዝም መባል የለበትም።

13962724_167168567041318_7615931692195659232_n

ሌላው የጎንደር እና የጎጃም ህዝብ፣ ከሕወሃት ጋር እያደረገ ባለው ግብግብ የወሎ ሕዝብ ከጎንደርና ጎጃም ህዝብ ጎን እንዳልቆመ ነው ጦማሪ ዳንኤል ለማሳየትም የሞከረው። “በደሴ፣ ደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከተሞች የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች ፀረ ሰላም ኃይሎች የጠሩትን ሰልፍ ባለመቀበል ላሳዩት የልማትና የዴሞክራሲ አጋርነት የላቀ አድናቆት አለኝ አለ ፖሊስ።” ሲል ፋና ራዲዮ የተናገረዉን አይነት መንፈስ የያዘ መልእክት።

በዚህ ዙሪያ ብዙም የምለው የለኝም። ወንድም ዳንኤል የሚከተለውን ፎቶዎች እንዲያይ ከመጋበዝ ዉጭ። እነዚህ ፎቶዎች በወሎ የተነሱ ፎቶዎች ናቸው። በአንደኛው ፎቆቹ ላይ ዜጎች ተኩሶ ለመግደል ስናይፐር የያዙ ወታደሮችን ያሳያል። ሌላው ደግሞ ምን ያህል የወታደር ብዛት እንደነበረ የሚያመላከት ነው። ታዲያ በዚህ መልኩ ሰልፍ አለመደረጉ ነው የወሎ ህዝብ ለጎንደርና ጎጃም ህዝብ አጋርነቱን አላሳየም ተብሎ ሊነገር የሚችለው?

በወሎም በሸዋም ያለው ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነው። እንደወም ህዝቡ ሰልፍ ወጥቶ ትንሽ ቢተነፍስ ኖሮ ጥሩ ነበር። አሁን የበለጠ ነው ወያኔዎች ሰዉን እልህ ዉስጥ የከተቱት። ትላንት ራሱ በቆቦ አካካቢ ችግሮች ተፈጥረው ነበር። ለማረጋገጥ አልቻልኩም እንጅ ከትግራይ ወደ ወልዲያ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሕወሃት ታጣቂዎች  ላይ በደረሰ ጥቃት ሁሉም እንደተገደሉ ነው።  ከዚህ በኋላ በወታደር ኮንቮይ ታጅበው ካልሆነ በቀር ሌሎች የንግድ ሆነ የግል መኪናዎች ለ ፍርሃትና ያል ሰቀቀን በሰላም በአዲስ አበባ መቀሌ መንገድ ይጓዛሉ ማለት አስቸጋሪ

እንደ ዳንኤል ብርሃኔ ያሉ የሕወሃት አፍቃሪዎችንና ደጋፊዎች የሁኔታውን አሳሳቢነት ተረድተው፣ ራዲዮ ፋና የሚያራግበውን መልሰው ከማራገብ፣ እርስ በርስ በሚገናኙበት መስመር በቁም ነገርር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የሚገኝበትን ሁኔታ እንዲመቻች ቢያደረጉ ጥሩ ነው እላለሁ። ለሁላችንምም የሚበጄው ፍቅቅር ነው። መግባባት ነው። ዉሸት፣ ዛቻ፣ ማስፈራራት የትም አያደርሱም። ሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ነን ቁጭ ብለን እንነጋገርር።

አዎን ሕወሃቶች ከሕዝቡ ጋር እየተነጋአገርረን ነው እያሉ ነው። የምናየው ግን ሕዝቡ ላይ መትረይስ ሲደቅኑ ነው። በአስቸኳይ የፌዴራል አጋዚ ሰራዊት ተቃዉሞ ከሚሰማባቸው ቦታዎች ለቆ መውጣት አለበት። ብሄራዊ መግባባትና እርቅ የሚያመጣ ተቃዋሚዎችንም ያካተተ ጉበዬ እንደሚደረግ መታወጅ አለበት። የሽግግር መንግስት መቋቋም አለበት። የሽግግር መንግስት ማቋቋም ሕግ መንግስታዊ ስርአቱን ማፍረስ ነው ከተባለ ደግሞ ሕግ መንግስቱን  በጠበቀ መልኩ የአንድነት መንግስት ማቋቋምም ይቻላል። አሁን ያለው ካቢኔ ፈርሶ ሌላ ተቃዋሚዎችን ያካተተ ካቢኔ በመመስረት። ብቻ ትልቁ ነገር ችችግሮችን በስለም ለመፍትታት የይስሙላና የዉሸት ሳይሆን የምር የሆን ፍላጎትና ቁርጠኝነት መያዝ ነው፤፡ ያ ከሆነ እርግጠኛ ነን ችግሮቻችንንን በሰላም መፍታት እንችላለን:

እንግዲህ እኛ ብለን፣ ብለን፣ ጽፈን ፣ ጽፈን አልተሰማንም። አሁን ጊዜውና ሰዓቱ የሕወኃት ደጋፊዎች ነው። አሁን እነርሱ ናቸው ግፊት  ማድረግ ያለባቸው። ይሄንን እንዲያደረጉ የምንጠይቃቸው፣ አንድ ለአገር፣ ሁለ ለሕዝብ ሶስት ደግሞ ለራሳቸው ሲሉ ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s