ሀገራችንን ከህወሓት እኩይ እቅድ እንታደጋታለን! (የጋሻ ለኢትዮጵያ የአቋም መግለጫ)

የጋሻ ለኢትዮጵያ የአቋም መግለጫ

ጋሻ ለኢትዮጵያውያን ተብሎ የሚታወቀው የሲቪክ ማህበር፤ ሕወሓት ሲፈጠር ጀምሮ፤ ላለፉት በርካታ አመታት፣ ኢትዮጵያን እንደጠላት ኢላማ አድርጎ የተነሳ መሆኑን ሳይታክት ለህዝብ ሲገልጽ ቆይቷል።በተጨማሪም ኢትዮጵያን በዘር በተመሰረተ ክልል ሸንሽኖ የተከለዉ አስከፊ የአገዛዝ እና የአስተዳደር ስርአት ለኢትዮጵያ ህዝባችን የማይበጅ መሆኑን አስታዉቀናል፤ አጥብቅንም ተቃውመናል።

ዛሬ በኦሮሚያ፣ በጎንደርና በሌሎች የአማራ ክልል፣ እንዲሁም በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ እምቢተኝነት፤ በጠመንጃ ኃይል ለመጨፍለቅ፣ ብሎም ለማጥፋት ህወሓት/ኢህአዴግ እንቅልፍ አጥቶ ሲኳትን እየታየ ነው። እስካሁን የፈጸማቸው ወንጀሎቹ አልበቃ ብለውታል። ሕወሓት ባለፉት ዘጠኝ ወራት፤ እጅግ ዘግናኝ የሆኑ ግድያዎች፣ እስራት እና መጠነ ሰፊ ወከባን በኦሮሞ ህዝባችን ፈጽሟል። በቅርቡ ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን አስታኮ የፈነዳውን የጎንደር፣ የአማራ ህዝብ አመጽ ለማምከን ገዢው ፓርቲ መላውን ዓለም ትኩረት በሳበ መልኩ እየተቅበዘበዘ ይገኛል። ጉዳዩ ያሳሰበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሳይቀር፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብቶ ምን እየተሰራ እንዳለ የሚያጣራ ነፃ የመርማሪ ቡድን እንዲገባና የተፈፀሙ ወንጀሎች እንዲያጣራ በድጋሚ ጠይቆ ሳይፈቀድለት ቀርቷል።

የህወሓት/ኢህአዴግን ጭካኔ የተሞላበት አካሄድ በሚገባ የተገነዘበው የኦሮሞውና የአማራው ህዝባችን፤ የጋራ ትግል አጋርነት መፍጠሩ፤ ገዢውን ቡድን የሚይዘውና የሚጨብጠው እንዲያጣ አድርጎታል። ህዝባዊ ትግሉ በየቀኑ እየተጠናከረ መሄዱን የተገነዘበው አምባ ገነን ድርጅት፤ ከስልጣን የመውረድ ስጋቱ እያዬለ ስለመጣ፤ የትግራይን ህዝብ ወደ እሳቱ ለመማገድ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

“አማራ መጣብህ፣ ሊፈጅህ ነው፣ ህወሓት ከሌለ ይጨርሱሃል!” በሚለው ፕሮፓጋንዳ ፤ በቅንጅት ጊዜ ተሳክቶልኛል ብሎ በማሰብ፤ ዛሬ ደግሞ ያን የቆረፈደ ፕሮፓጋንዳ እንደገና ሊተገብር እየተውተረተረ ይገኛል። ዓላማውን ለማሳካትም በጎንደር፣ በባህር ዳር እና በሌሎች ከተሞች በሰላም ሰርተው በመኖር ላይ ባሉት የትግራይ ተወላጆችና እንዲሁም በልዩ ልዩ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት በሚማሩ ወጣት የትግራይ ተወላጆች ልክ የተቀረው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው የተነሳባቸዉ ለማስመሰል “ለቃችሁ ካልሄዳችሁ ለህልውናችሁ ጠያቂዎች አይደለንም” የሚል አጉል ፕሮፓጋንዳ እያናፈሰ ይገኛል።

ወድ ወገናችን የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ –

ይህ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ ሳትገነዘብ አልቀረህም። ህወሓት ስልጣኔን እንዳላጣ፤ ብቸኛው መንገድ በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል የርስ በርስ ጦርነት መለኮስ ብቻ ነው ብሎ ያምናል። ለዚህ ደግሞ አማራውና ኦሮሞው በትግራይ ተወላጆች ላይ ተነስተዋል እያለ ለትግራይ ህዝብ እወጃውን ተያይዞቷል። በግድም ይሁን በውድ “ተፈናቅለው” በትግራይ ከተሞች ላይ እየፈሰሱ ያሉት የትግራይ ተወላጆች በህወሓት ሳይሆን በሌሎች ኢትዮጵያውያን ተገፍተው እንደወጡ ተደርጎ እየተነገረ ነው ። ምንም አይነት ነፃ መረጃ የማያገኝን ህዝብ ፤ ማታለል እና ወደ አቀደው ወጥመድ የማስገባቱ ሰፊ ልምድ ላለው ሕወሓት ፤ ይህ ምን ያህል ቀላል እንደሆነ ተደጋግሞ የታዬ ጉዳይ ነው።

ስለዚህ የጎንደር፣ የባህር ዳር እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ ወገናችን፤ የህወሓትን መሰሪ ፕሮግራም እስካሁን ድረስ እንዳከሸፍከው ሁሉ፣ አሁንም “ጠባችን ከገዢው ቡድን ጋር እንጂ ከወገናችን ከትግራይ ህዝብ ጋር አይደለም!”

የሚለውን አቋምህን አጠናክረው ቀጥልበት። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር የትግራይ ህዝብም አንድ ቀን “ሆ !” ብሎ በደመኛ ጠላቱ በህወሓት ላይ መነሳቱ የማይቀር ነው።

የጋሻ ለኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበር አባላትም ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ጋር በማበር፤

1. በህዝባችን የሚካሄድውን የዴሞክራሲያዊ መብትና የነጻነት ትግል በሙሉ ልብ የምንደግፍ መሆናችንን እንገልጻለን።

2. የፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን።

3. ህወሕት/ኢህአዴግ የኢትዮጵያ ህዝብ ዓላማውን ከግብ ሳያደርስ እንደማይቆም ተገንዝቦ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በሌሎች እያካሄደ ያለውን ግድያና እስራት እንዲቆም በፅኑ እንጠይቃለን።

4. አገሪቱ ወደ ባሰ ችግር ሳትገባ የሽግግር ጊዜውን ሰላማዊ ለማድረግ ገዢው ቡድን የሽግግር መንግስት ለመመስረት የሚያስችሉ ቅድመሁኔታዎችን እንዲያመቻች

5. የትግራይ ህዝብም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚበጅ ዴሞክራሲያዊ ስርአትና ፍትህ የሠፈነባት ሀገር ለመመስረት በሚደረገው አገራዊ ትግል ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ ትሆን ዘንድ በጥብቅ እናሳስባለን።

6. ሠላምና ዴሞክራሲ የሰፍነባት ለነጌቱ ኢትዮጵያ ግንባታ እጅግ መሠረታዊ ነውና፤ ከዘረኝነት እና ከጥላቻ የፀዳ ትግል በሙሉ ልብ እንደግፋለን! በአንፃሩ ደግሞ ህወሓት/ኢህአዴግ ከሚያካሄደው የጥላቻ ዘመቻ ባልተናነሰ መልኩ ግለሰቦች በተለያዩ የሚድያ መድረኮች የሚዘሩትን ጥላቻ አጥብቀን እናወግዛለን።

በዚሁ አጋጣሚም የተቃዋሚ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ታጋይ ድርጅቶች ለአይቀሬዉ የሕወሓት ከስልጣን መገርሰስ እና ለኢትዮጵያ ግንባታ በሚደረገዉ የሽግግር መንግስት መቋቋም ጠንቅቀዉ መስራት እንዳለባቸዉ፣ አገራዊና ወገናዊ ግዴታቸዉን ይፈጽሙ ዘንድ አጥብቀን እናሳስባለን።

“እምቢኝ በቃ! አንገሸገሸን!” ብሎ ከአጥናፍ አጥናፍ ህዝባችን ተነስቶአል፤ ይህ የሰላም የዴሞክራሲና የአገር ሉዓላዊነት ትግል ፍጹም እስኪከበር ድረስ ጋሻ ለኢትዮጵያዉያን አቅማችንን የፈቀደውን ሁሉ እናደርጋለን።

ኢትዮጵያ በልጆችዋ የተባበረ ሀይል ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!

ጋሻ ለኢትዮጵያዉያን
ነሃሴ 18, 2008

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/16842/#sthash.2LoYGjkl.dpuf

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s