ህወሃት/ኢህአዴግ በአማራው ሕዝብ ላይ የዘር ዕልቂት (genocide) አወጀ

unnamed (3)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

በአማራ ክልል እየተቀጣጠለ የመጣውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት (#AmharaResistance) ፖለቲካዊ መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ የመከላከያ ኃይል እርምጃ እንዲወስድ ሃይለማርም ደሳለኝ በኦፊሴል አዟል፡፡

በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) ሙሉ ቁጥጥር ሥር ያለው የሃይለማርያም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣን በየቦታው “በቃን፤ አንፈልግም” የተባለውን የህወሃት የበላይነትን እንደገና ለማስፈን የጦርነት አዋጅ አውጇል፡፡

በኦሮሚያ (#OromoProtests) ለ10 ወራት የዘለቀው የኦሮሞን ሕዝብ የመፍጀት ሥልታዊ ጥቃት አሁንም የበርካታዎችን ደም እያፈሰሰ ባለበት ባሁኑ ወቅት በአንድ ክልል ሕዝብ ላይ የተነጣጠረው ይህ በሃይለማርያም ትዕዛዝ የተሰጠው የህወሃት እርምጃ ታሪክ የማይረሳው፣ ሰላም ሊያመጣ የማይችል፣ የዕድሜ ልክ ቁርሾ የሚያስከትል የዘር ማጥፋት (genocide) ወንጀል ነው፡፡

ውሳኔውን ተወደደም ተጠላም “የአማራውን ሕዝብ ጨርሱት” የሚል ነው!

የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ያቀናበረውን ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

በሸገር ኤፌ.ም. የተሰራጨው መረጃ እንዲህ ይነበባል

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተለያዩ አካባቢዎች ባለፉት 3 ቀናት ዳግም የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት የፀጥታ ሃይሉን ማዘዙ ተሰማ፡፡

የክልሉ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሶስት ቀናት በነበረው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት መቀጠፉንና ንብረት መውደሙን ለሸገር ዛሬ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የተለያዩ ከተማዎች ውስጥ የአገልግሎት መስጪያ ተቋማት አገልግሎት ተቋርጦ ነበር ሲሉም ነግረውናል፡፡

ህዝቡ የሚያሳቸውን ህጋዊ የመብት ጥያቄዎችን በሌላ መንገድ የሚወስዱ ወገኖች በክልሉ ያለውን ጥፋት በማባባሳቸው የመከላከያ ኃይል እርምጃ እንዲወስዱ በክልሉ መንግስት መታዘዙንም አቶ ንጉሱ ይናገራሉ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስር ከሚገኙ በደብረ ታቦር፣ በባህር ዳር፣ በጎንደርና በደብረ ታቦር የተነሱ ተቃውሞዎች ብዙ ንብረት መውደሙንና ህይወት መጥፋቱን የተለያዩ ወገኖች ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡

ከ3 ቀናት በፊት በተነሳው ዳግም ግጭት ምክንያት በደብረ ታቦር ብቻ ስድስት ሰዎች ሞተዋል ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሲናገር ተሰምቷል፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አቶ ንጉሱ በበኩላቸው በ3ቱ ቀናት በታዩት ግጭቶች ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱና ንብረት እንደወደመ ተጠይቀው “ለጊዜው የሚባል ነገር የለም በቅርቡ ጥቅል መረጃዎች ይወጣሉ” ብለዋል፡፡ (የኔነህ ሲሳይ – SHEGER FM 102.1 RADIO)

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20262#sthash.8Eoj4PeZ.dpuf

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s