የግዢ እና ሽያጭ ማቆም አድማ ጥሪ [#OromoProtests]

ከጷግሜ 1- መስከረም 2፣ 2009

oromo-students-fresh-protestቀደም ብለን እንዳስታወቅነው ለቀጣዩ ዘመቻ የተመረጠው ሳምንት በሃገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ነው። ስለሆነም ዘመቻው የስርዓቱን ኢኮኖሚ ከማድቀቅም አልፎ የኦሮሞ ህዝብ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ግንድ መሆኑን የሚያሳይበት ይሆናል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ከተሞች ውስጥ ለጨቋኙ ስርዓት ያደሩ ነጋዴዎችንም ለመለየት ይጠቅማል ዘመቻው። በዚሁ መሰረት ከጳጉሜ አንድ እስከ መስከረም ሁለት 2009 ዓ.ም የሚቆይ በስርዓቱ ኢኮኖሚ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ይደረጋል። ዓላማውም የስርዓቱን ኢኮኖሚ በመምታት የጭቆና አቅሙን ማንኮታኮት ይሆናል። ወቅቱ የዘመን መለወጫና የኣረፋ በዓላት ወቅት ነው። ባሮጌው ዓመት የኦሮሞ ህዝብ ለነጻነቱ ባደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ብዙ ልጆቹን ሰውቶ ሺዎችን ላይ ደግሞ የኣካል ጉዳት ደርሷል። በኣስር ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ በስርዓቱ አስቃቂ እስር ቤቶች አሁንም እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ስለሆነም በዓሉ እነዚህን ጀግኖቻችንን እያሰብንና እነርሱ የተሰውለትን ዓላማ ለማሳካት በሚያስችል መልኩ ትግላችንን እየቀጠልን ነጻነታችንን የምናፋጥንበት እንጂ በጭፈራና በከበርቻቻ የምናሳልፈው አይሆንም። በዚሁ መሰረት የሚወሰዱት እርምጃዎች፥

1) አርሶ አደሮቻችን እህል፣ የእርድ ከብት፣ ዶሮ፣ እንቁላል፣ ቂቤ፣ ቅመማ ቅመሞች፣ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች የመሳሰሉትን በሳምቱ ለገብያ ባለማቅረብ (ጨው፣ ስኳር ፣ዘይትና ሌሎች መሰረታዊ የቤት ውስጥ ፍጆታዎችን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀድሞ ባሉት ቀናት በመግዛት)፤

2) ነጋዴዎቻችንም ከላይ የተጠቀሱትን የበዓል ፍጆታዎች ፊንፊኔን ጨምሮ ወደ ሌሎቹ ትልልቅ ከተሞች ከማቅረብ በመቆጠብ፤

3) ይሄን ዘመቻ ለማክሸፍ የሚንቀሳቀሱ ለስርዓቱ ያደሩ ነጋዴዎችንም መንገድ በመዝጋት ጨምሮ በተቻለው መንግድ ሁሉ በማደናቀፍ፤

4) በከተሞችም ሆነ በገጠር የሚኖረው ህዝባችን በነዚህ ቀናት ምንም ነገር ከመሸመት መቆጠም። ምግብ ቤቶች፣ መዝናኛ ቤቶች፣ ሻይ ቤቶች፣ መጠጥ ቤቶች ወዘተ….ሁሉ ገብቶ ምንም ዓይነት ወጪ አለማውጣት። በቤት ውስጥ ከዘመድ ወዳጅ ጋር ተስብስቦ ሰማዕቶቻችንን ማሰብ። እነሱ የተሰውለትንም ትግል እንዴት በፊጥነት ወደፊት ማስቀጥል እንደሚቻል መወያየት። እንደየእምነታችን ወደ እምነት ቤቶች ሄደን ጸሎት ማድረግ። እዛም በጉዳዩ ላይ በጋራ ሆነን መወያየት።

ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው፣ ሳምንቱ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ወቅት ስለሆነ፣ እነዚህን እርምጃዎች በመውሰድ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በማድረስ የጭቆና ጉልበቱን ማሽመድመድ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞን ህዝብ የኢኮኖሚ ዋልታነት ከማሳየትም አልፎ ለስርዓቱ ያደሩና የህዝብ ወገንተኘት ያላቸውን ነጋዴዎች ለመለየት ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል።

ስለሆነም በህዝባችን ላይ እየተካሄደ ያለውን የግፍ የጅምላ ግድያ እና እስራት የምትቃወሙ ሁሉ በዚህ ሰላምዊ ግን ውጤታማ የትግል ስልት እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጠይቃለን

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20198#sthash.sOUIV3Pb.dpuf

የወልቃይት ጥየቄ ሕገ መንግሥታዊነት፤ [ይገረም አለሙ]

Welkeit mapየወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ መነሳት የጀመረበት ገዜ ጠያቂዎቹ እንደሚሉት ከወያኔ የሥልጣን እድሜ በላይ ነው፡፡ ስሙን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ብሎ ዓላማውን ተግራይን ነጻ ማውጣት አደርጎ የተነሳው ቡድን በለስ ቀንቶት ትግራይን መቆጣጠር ሲችል ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ወደ ቀሪው የኢትዮጵይ ክፍል መስፋፋትን ነው የመረጠው፡፡ አንደኛው ምክንያት ማሸነፍ ከተቻለ በትግራይ ሳይወሰኑ ማእከላዊ ሥልጣን ለመያዝ ሁለተኛው ደግሞ “ነጻ ሊያወጧት የታገሉላትን” ትግራይ ግዛት ለም መሬቶቸን በማጠቃለል ማስፋት ናቸው፡፡ የትግራይ አጎራባጅ የሆኑት ለም የጎንደርና የወሎ ወረዳዎች በወረራ የተያዙት ወያኔ ምንይልክ ቤተ መንግሥት ሳይደርስ ነው፡፡ ይህን ወረራ ዜጎች በዝምታ አልተመለከቱም በእሽታ አልተቀበሉም፣ ነገር ግን ወያኔ አንደም በጡንቻ ሁለትም በህግ ሽፋን በወሰዳቸው የማሰር የመግደልና የመሰወር ርምጃ ተቃውሞውን ለማዳን ችሎ ነበር፡፡

ነገር ግን የመብት ጥያቄ በጠመንጃ የማያዳፍኑት፣ ግንባር ቀደም ጥያቄ አቅራቢዎችንም በመግደል  የማያጠፉት በመሆኑ ይሄው ዛሬ የተዳፈነው ተገልጦ፣ በሀይል የተረገጠ የመሰለው ፈንቅሎ፣ገለን ቀብረነዋል ያሉት ህይወት ዘርቶ ህዝቡን በአንድ ደምጽ  ለተቃውሞ ያነሳሳ በአንጻሩ ገዢዎችን ያሸበረ ለመሆን በቅቷል፡፡

የጥያቄው መሰረት ወልቃይት ጠገዴ ወደ ትግራይ  መካለሉ ሆኖ የጥያቄው አቀራረብ እና  የሚሰጠው ምላሽ ግን የተለያየ መልክ እየያዘ ብዙ ዘርፎች አውጥቷል፡፡ በጠያቂዎች በኩል ሕገ መንግሥታዊ መብታችንን ነው የጠየቅነው፣በሕገ መንግሥቱ መሰረት ምላሽ ይሰጠን፣በማለት እስከ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አቤት ሲሉ ተጠያቂዎቹ  በአሁኑ ወቅት ምላሽ ያላገኘ የማንነት ጥያቄ የለም ፣የወልቃይት ጥያቄ ጸረ ህገ መንግሥት ነው ከማለት አልፈው ጥያቄውን ለማዳፈን የሀይል ርምጃ መውሰደን  ነው የመረጡት፡፡ ህገ መንግሥታዊ  የመብት ጥያቄ ሲቀርብ ትክክል ነው ብሎ ምላሽ ለመስጠትም ሆነ ህገ ወጥ ነው ለማለት ጠመንጃ ማንሳት ሳይሆን ህገ መንግስቱን መሰረት ማድረግ ነበር የሚገባው፡፡

ስለ ፌዴራል አከላል የሚገልጸው የህገ መንግሥቱ አንቀጽ 46/1 “ ክልሎች የሚዋቀሩት በሕዝብ አሰፋፈር ፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ በመመስረት ነው፣” ይላል፡፡በተገለጸት  መስፈርች መካከል እና ወይም  የሚል ቃል ባለመኖሩ አለበለዛም  እነዚህን ባገናዘበ መልኩ ተብሎ ባለመገለጹ  ክልሎች ሲዋቀሩ አራቱም መስፈርቶች በሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል፡፡ነገር ግን አሁን ያለው አከላለል የተሰራው  አነዚህን መስፈርቶች ባሟላ ሳይሆን የህውኃትን ፍላጎት ባማከለ ሁኔታ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ መስፈርቶቹን በሙሉ ስራ ላይ ማዋል አንደማይቻል የክልሎችን  ይዘት በአንክሮ  ማየት ብቻ ይበቃል፡፡

የወልቃይትን ጥያቄ ከዚህ የህገ መንግሥቱ አንቀጽ አንጻር ሲታይ፤

በህገ መንግሥቱ የሰፈሩት አራት መስፈርቶች ተግባራዊ አለመሆናቸውን  በተናጠል አንያቸው፤

በሕዝብ አሰፋፈር፤

አሰፋፈር ሲባል  ሰፋሪውን ሰውና የሚሰፈርበትን መሬት የሚመለከት ይመስለኛል፡፡ ከዚህ አንጻር ሕገ መንግሥቱ ወደ ወጣበት  1987 ተመልሰን  የወልቃይት ጠገዴን አካባቢ አሰፋፈር ስናስታውስ የምናገኘው የነዋሪውም ሆነ የመሬቱ አሰፋፈር ቤጌምድር ጎንደር እንደነበረ ነው፡፡ የመሬቱ አቀማመጥም ሆነ የአካባቢው ህብረተሰብ ባህል፣ ሥነ-ልቦና ፣ ትስስር ወዘተ ከትግራይ ይልቅ  ለትናንቱ ጎንደር ለዛሬው አማራ ሚዛን ይደፋል፡፡ የወልቃይትን ወደ ትግራይ መከለል የሚቃወሙ ወገኖች  የሚያቀርቡትና  ተቃውሞውን የሚቃወሙት ወገኖች በማስረጃ ሊቋቋሙት ያልቻሉት በኢትያጵያ ታሪክ ትግሬ ሰዉ አንጂ ትግራይ መሬቱ ተከዜን ተሸግሮ አያውቅም የሚለው መከራከረያ የህዝቡን የቀደመ አሰፋፈር እንዴትነት የሚያሳይ ነው፡፡  በተለያየ መንገድና ሁኔታ ከቦታ ቦታ ተንቀሳሶ የሚደረግ ሰፈራ አካባቢውን የእኔ ለማለት አያበቃም፡፡ በህገ መንግሥቱ የተገለጹትን መስፈርቶች ባላሟላ መልኩ ወልቃይት ወደ ትግራይ መስተዳድር ከተጠቃለለ በኋላ በርካታ የትግራይ ተወላጆች በአካባቢው እንዲሰፍሩ የተደረገው  የህዝቡን አሰፋፈር ቅድመ ይዘት በመለወጥ የሚነሳውን ጥያቄ ለመከላከል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ የወልቃይት ጉዳይ በሕዝበ ውሳኔ አይፈታም የሚለው መከራከሪያ የሚነሳውም ህገ መንግስቱ ስራ ላይ ከዋለ በኋላ በሀይል በተካሄደ ሰፈራ ከነዋሪዎቹ ሰፋሪዎቹ አንዲበልጡ በመደረጉ   ነው፡፡

ቋንቋ፤

ይህ መስፈርት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አከላል አብይ መገለጫ ነው፡፡ ይሁን አንጂ በህገ መንግሥቱ የተገለጹ መስፈርቶች አስከመኖራቸው ተርስተው  ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝም ይባል እንጂ  አከላለሉ ይህንንም  ያሟላ ላለመሆኑ የደቡብ ክልልን ማየት ብቻ ይበቃል፡፡ደቡብ የሚባል ቋንቋም ሆነ  “ብሔር ብሔረሰብ ህዝብ” የለም፡፡ ወልቃይት ላይ ስንመለስም የአካባቢው ሰዎች እንደሚናገሩት ሌሎችም የምርምርም ሆነ የአይን ምስክርነት ሲሰጡ እንደሚሰሙት በአካባቢው  አማርኛ ትግረኛ አረብኛ (በእኩል ደረጃም ባይሆን ) ይነገራል፡፡  ይህ ከሆነ  አንድን ሶስት ቋንቋ የሚናገር ሰው የግድ ወደ አንድ ብሔር ማስጠጋት ሲፈለግ ከግለሰቡ ምርጫ ውጪ በሌላ ሀይል ሊወሰን አይችልም፡፡ ፈቃድ ደግሞ በህገ መንግስቱ የተገለጸ አንድ መስፈርት ነው፡፡ የዚህ አብይ ችግር ደግሞ አማራ ትግሬ የሚባል ክልል መፈጠሩ ነው፡፡

ማንነት፣

የሰዎች የማንነት መታወቂያቸው ብሄራቸው /ጎሳቸው፣  የብሄሩ መለያ ደግሞ  ቋንቋ  በሆነበት ሥርዓት  እንደ ወልቃይቴ ያለ ከአንድ በላይ ቋንቋ የሚናገር ማህበረሰብ  ያለ ፈቃዱና ፍላጎቱ  ቋንቋውን ስለመናገሩ ብቻ የዚህኛው ወይንም የዛኛው ብሄር ነህ ተብሎ ሲጫንበት አድራጎቱ የጉልበት እንጂ የህግ አይሆንም፡፡በጉልበት የተፈጸመ ነገር ደግሞ ተግባራዊ ሆኖ የሚቆየው ገዢው ጠንካራ ተገዢው  ደካማ እስከሆነ ድረስ ብቻ ነው፡፡ለሁሉም ግዜ አለውና ነገሮች ሲለወጡ ጥያቄው እንዲህ ፈታኝ ይሆናል፡፡

ትግረኛ መናገራችን ብቻ ትግሬ አያደረገንም የሚሉት ተከራካሪዎች በደስታ ግዜ የምንዘፍነው፣ በሀዘን ግዜ የምናለቅሰው፣  በስር ቋንቋችን በአማርኛ ነው፡፡ ወግ ባህላችን፣ አሰራር ልምዳችን የአማራ እንጂ የትግሬ አይደለም ይላሉ፡፡ ከዚህ አለፍ ብለውም ወያኔ የፈለገው እኛን ሰዎቹን ሳይሆን ለም መሬታችንን ነው፡፡  መሬታችንን የትግራይ ለማድረግ  ነው የግድ ትግሬ ሁኑ የተባልነው በማለት ክርክራቸውን ያጠናክራሉ፡፡ የፌዴራል አከላለሉ ዜጎችን በብሔር/ጉሳ የማይከፋፍል  ቢሆንና የክልሎቹ መጠሪያም በብሔር /ጎሳ ባይሆን ይህ ጥያቄ ባልተነሳ ነበር፡፡  በጎሳ/በብሔር ስም የሚጠራ ክልል ፈጥሮ ከፈቃቸዳው ውጪ የዜጎች ማንነት  በባለሥልጣኖች ተወስኖ አንተ አማራ ነህ አንተ ትግሬ ነህ ወዘተ ማለት ቢዘገየም የሚያስገኘው ውጤት እየታየ ነው፡፡

ፈቃድ፤

ለፌዴራል አከላለል ፈቃድ አንዱ መስፈርት ሆኖ ቢገለጽም የአፈጻጸሙ እንዴትነት ግልጽ አይደለም፡፡ ፈቃድ የሚጠየቀው ማነው? እንዴት ነው የሚጠየቀው? ጠያቂውስ ክልሉ ወይንስ ፌዴራል መንግሥቱ? ክልል ነው ቢባል በሁለት ክልሎች መካከል ያለ የወልቃይት አይነቱ ጉዳይ እንዴት ይሆናል ? ፈቃድ የሚለው መስፈርት ያልተብራራ በመሆኑ አፈጻጸሙ አንዴትም ይሁን በማን የአካባቢው ነዋሪ ፈቃደኝነት የማይታለፍ  እንደውም ወሳኙ መስፈርት ነው፡፡ በህገ መንግሥቱ የተገለጹት ሶስት መስፈርቶች  ተሟልተው የማይገኙ በመሆናቸው የነዋሪውን ፈቃድ መጠየቅ ሌሎቹን ጉድለቶች ሁሉ ያሟላል፣ ይሸፍናል፡፡ ነገር ግን ገዢዎች በህዝብ ፈቃድ ፍላጎታቸንን አናሳካም ብለው ገና ሳይሞክሩት ስለሚፈሩት ተግባራዊ አያደርጉትም፡፡ ተግባራዊ የማያደርጉትን ለምን ህገ መንግሥት ውስጥ ይጽፋሉ የሚል ጥያቄ ማንሳት ስለ ገዢዎች አለማወቅ ይሆናል፡፡

በጥቅሉ በሀገራችን የተከናወነው የፌዴራል አከላለል ሌሎች ችግሮቹ እንደተጠበቁ ሆነው በህገ መንግሥቱ የሰፈሩትን  መስፈርቶች አንኳን ያላሟላ ነው፡፡ በዚህ መልኩ የተሰራውና ክልሎችን በብሄር/ብሔረሰብ ስም አንዲጠሩ ያደረገው  ፌዴራላዊ አከላለል  ( ደቡብ የሚባል ብሄርም ብሄረሰብም ህዝብም አለመኖሩን ልብ ይሏል) ትግራይና አማራ የተባሉትን ክልሎች  ለመለየት የሄደበት መንገድ መሬቱን አንጂ ነዋሪውን ያላማከለ ፣ የወያኔን ፍላጎት እንጂ ህገ መንግሥቱን መሰረት ያላደረገ  በመሆኑ ነው ጥያቄው  ከላይ በመጠኑ ለማሳየት እንደተሞከረው አንዱንም የህገ መንግሥቱን መስፈርቶች አልተከተለም፡፡  ለአመታት ያላባራውና አሁን ገንፍሎ የወጣው፡፡

የወልቃይት ችግር አንዴት ይፈታል፡፡

ጥያቄው በተጠያቂዎቹ በኩል የተለያየ ስምና ፍረጃ ቢሰጠውም በዚህ ጽሁፍ ለማሳየት አንደተሞከረው ህገ መንግሥታዊ ጥያቄ ነው፡፡ በመሆኑም ትናንት በከላዩ ጉልበተኛነትና በተከላዩ ደካማነት የተፈጠረውን ህገ መንግሥቱን ያላከበረ አከላለል  በህገ መንግስቱ የሰፈሩትን አራት መስፈርቶች ባገናዘበ ሁኔታ ማስተካከል አንዱ መፍትሄ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለወያኔ አንደም ሽንፈት ሁለትም ለትግራይ ትልቅ የኢኮኖሚ መሰረት የሆኑ ቦታዎችን ማጣት ስለሚሆን ተግባራዊነቱ አይታሰቤ ነው፡፡ ሁለተኛው መፍትሄ  መሬት ላይ ያለውን አከላለል በሚያጸና መልኩ ህገ መንግሥቱን መቀየር ነው፡፡ ይህ ቢሆን ህግ  ወደ ኋላ ተመልሶ አይሰራም የሚለው ለህገ መንግስት መስራት አለመስራቱ የባለሙያዎች ምላሽ የሚያሻ ሆኖ  ጥያቄው ህገ መንግስታዊ ነው የሚለውን ክርክር ያስቀረው ካሆነ በስተቀር የወያኔን ፍላጎት የሚያስቀጥል አንጂ የህዝቡን ጥያቄ የማይመልስ በመሆኑ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ ስለሆነም መፍትሄው አንድና አንድ ነው፡፡ ወያኔዎች ለወሳኝ ሀገራዊ ጉዳዮች የሚሰጡት “ይህ ሊሆን የሚችለው በመቃብራችን ላይ ብቻ ነው” የሚሉት ምላሽ ነው በአስተማማኝ ወደ ዴሞክራሲ ሊያደርሰን የሚችለው መፍትሄ፡፡ በግልጽ አነጋገር ከአገዛዝ ወደ ህገ መንግሥታዊ ሥርዓት መሸጋገር፡፡

 

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20200#sthash.tP5BbHwZ.dpuf

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ በተለይ ለአዲስ አድማስ Written [አለማየሁ አንበሴ]

Mesfin 9 - satenaw
ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

 ስለ ህዝባዊ ተቃውሞዎችና መንስኤያቸው ያብራራሉ
ጭቆናን ለማጥፋት የሚደረግ ትግል ኖሮ አያውቅም
ህዝብ ቋቱ ሲሞላ ነው አልችልም፤ በቃኝ ያለው
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የተናገረው የሚያስደንቅ ነው

በሦስት መንግስት ውስጥ አልፈዋል – ታዋቂው ምሁርና አንጋፋው ፖለቲከኛ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፡፡ በአገራቸው ፖለቲካ ውስጥ ዛሬም በሽምግልና ዕድሜያቸው ንቁ ተሳታፊ ናቸው፡፡ በሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸውም ይታወቃሉ፡፡ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም በኦሮሚያና በአማራ ክልል በተነሱ ተቃውሞዎችና ግጭቶች፣ በተቃውሞዎቹ መንስኤና ባህሪያት እንዲሁም በመንግስት ምላሽ አሰጣጥና በችግሮቹ መፍትሄ ዙሪያ ሃሳባቸውንና ዕይታቸውን ለአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በቃለ-ምልልስ መልክ አጋርተውታል፡፡ እነሆ፡-

በእርስዎ ዕይታ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለተቀሰቀሱ ተቃውሞዎች መንስኤው ምንድን ነው?

የህዝቡ ጥያቄ 25 ዓመት የፈጀ ነው፡፡ አንድ የፖለቲካ ቡድን በፈለገው መንገድ የህዝቡን ግንኙነት በጎሳ ብቻ እንዲሆን፤ በኑሮውም (በቤት፣ በመሬት፣ በስራ፣ወዘተ—) መቶ በመቶ ቁጥጥር አድርጎ ሰውን ነፃነት የነሳበት፤ ጋዜጣ፣ መፅሄት፣ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን በአንድ አገዛዝ ስር የወደቀበት ጊዜ ነው ያለፈው፤25 ዓመት፡፡ አሁን ግን እዚህ ላይ ሲደርስ የታመቀው መተንፈሻ ሲያጣ ገንፍሎ ፈነዳ። እየሞቀ … እየሞቀ … እየሞቀ ሲሄድ ድንጋይም ይቀልጣል፡፡ ቀልጦ ቀልጦ ሲሞቅ ይፈነዳል፡፡ እሳተ ገሞራ ሆኖ የሚወጣው የቀለጠው ነው፡፡ አሁን በሀገሪቱ የምናየው ይሄንኑ ነው፡፡

ተቃውሞዎቹ የተነሱት በምርጫ ሙሉ በሙሉ ማሸነፉን ባወጀ ማግስት መሆኑ አንደምታው ምንድን ነው?
ምን ምርጫ አለና! ይሄ መቶ በመቶ አሸንፈናል ያሉበትን ነው የምትለው?

አዎ! የ2007 ምርጫ—-
በ“ወያኔ” ዘመን ምርጫ አልነበረም፤ የለም፡፡ ከደርግ ጊዜ የተሻለ አይደለም፡፡ በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ደግሞ ከሁለቱም የተሻለ ነበር፡፡ ፓርቲዎች ባይኖሩም ምርጫው በጣም ጥሩ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ምርጫ የሚባል ነገር የለም፤እንዲሁ ለይስሙላ ነው።

በኦሮሚያ የተቃውሞው መነሻ ማስተር ፕላን ሲሆን  በአማራ ክልል ደግሞ የወልቃይትና የኮሚቴው ጉዳይ ነው፡፡ እርስዎ እውነተኛ ምክንያቶቹ እነዚህ ናቸው ብለው ያምናሉ?

ኦሮሚያ ለተነሳው ተቃውሞ ምክንያቱ ማስተር ፕላን ነው ተባለ… ማስተር ፕላኑ ከዚህ በፊት አልነበረም? አዲስ ነው? ቤቶች ሲፈርሱ አልነበረም? ሰዎች መንገድ ላይ እንዲሁ እንደዋዛ ሲጣሉ አልነበረም? አሁን በቃ ቋቱ ሞላ፤ ይሄ ነው ምክንያቱ። ቋቱ ሲሞላ ህዝብ አልችልም፤ በቃኝ ነው ያለው፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ግፍ መቀበል አንችልም ነው፡፡ የወልቃይትም ጉዳይ ቢሆን በተለይ የታሰረው ኮ/ል ደመቀ ጎበዝ ሰው ነው፡፡ እሱ ነው ይሄን ነገር የጫረው፡፡ ግን የወያኔ ኮሎኔል ነው እሡ፡፡ በስርአቱ የነበረ የስርአቱ መሳሪያ ሆኖ የቆየ ሰው ነው፡፡ እንግዲህ ቋቱ ሲሞላ እሱም በቃኝ አለ፤ ሌሎችም በቃን እንዲሉ አደረገ፡፡ እና ምንም አዲስ ነገር የለም። ሁሉም ቋቱ ሲሞላ ነው ወደዚህ ደረጃ የደረሰው፡፡ የማስተር ፕላንና የወልቃይት ጉዳይ ብቻ አይደለም።

አሁን ያለው ተቃውሞና ግጭት ከቀጠለ የአገሪቱ እጣ ፈንታ ምን የሚሆን ይመስልዎታል?
ይሄ የሚያስፈራ ጥያቄ ነው፡፡ “ወያኔ” ተቃዋሚ ድርጅቶች እንዳይዳብሩ እንዳይበረቱ አድርጎ፣ አሁን ተቃዋሚ አለ የማይባልበት ደረጃ ላይ ነው ያለው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በእንደዚህ አይነቱ ጊዜ ድምፃቸው ሊሰማ የሚችል፣ የሚከበሩ የሚደመጡ ሽማግሌዎች  እንዳይኖሩ አድርገዋል፡፡ አሁን ታዲያ ማንን ይስማ? ወያኔ አሁን ቢሰማ፣ የሚሰማው ፈረንጆቹን አሜሪካንን፣ እንግሊዝን ነው፡፡ ቸርችል በ2ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ያለው አንድ ጥሩ አባባል ነበር፡- “let dog eat dog.” (እርስ በርሳቸው ይባሉ ምንም አይደለም) ፈረንጆቹም በተመቻቸው ሁኔታ እንድንሆንላቸው ይፈልጋሉና ምንም አያደርጉም። ስለዚህ አስታራቂ ሊኖር አይችልም፡፡ ወያኔም የሚሰማው ጡንቻው መሳሪያው ብቻ ነው፡፡ ያንን መሳሪያ እስከያዝኩ ድረስ አልሸነፍም በሚለው አስተሳሰቡ ፀንቷል፤ከደርግ አልተማሩም፡፡ ደርግ የትየለሌ መሳሪያ ነበረው፤ህዝብ ግን አልነበረውም። ህዝብ ከሌለ የትም መድረስ አይቻልም፡፡ እነሱም ይሄንን አልተረዱትም፡፡ አሁንም ለእርቅ፣ ለሰላም የተዘጋጁ አይመስለኝም፡፡ እንደ በፊቱ በጡንቻችን ረግጠን እንቀጥላለን፤ብለው ነው የሚያስቡት። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ደግሞ አገዛዙና ህዝቡ ደም ተቃብቷል። ይሄ ወደ ኋላ የሚመለስ አይመስለኝም። እየባሰ እየከረረ የሚሄድ ይመስለኛል፡፡
በዚህ መሃል ግን አጠቃላይ የትግራይ ተወላጆች ጉዳይ አለ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በተገቢው መንገድ ውይይት እየተደረገ አይደለም፡፡ ልንወያይበት ልንነጋገርበት የሚገባ ነገር ነው፡፡ የትግራይ ተወላጆች በደቡብ በኩል በጎንደር፣ በወሎ ወንድሞቻቸው ድሮ ችግር ሲመጣ የሚሄዱበትን ቦታ ሁሉ አሁን ጠላት እንዲሆኑ አድርጓል ወያኔ፤ በሰሜን በኩል ያሉ ኤርትራውያን ወንድሞቻቸውን ጠላት አድርጓል። የትግራይ ህዝብ በዚህ መሃከል ነው ያለው፤ እንደ ቡሄ ዳቦ፡፡ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡

ለዚህ ችግር መፍትሄው ምንድን ነው ይላሉ?
ህዝቡ ራሱን ሊያወጣ ይችላል፡፡ ህወሓትን በመቃወምና ከሌላው ጋር በአጋርነት በመቆም ከዚህ አጣብቂኝ ራሱን ሊያወጣ ይችላል፡፡ “ትግሬ ህውሓት ነው፤ ህውሓት ትግሬ ነው” የሚባለው ለኔ ትክክል አይደለም፡፡
ህዝባዊ ተቃውሞው ባለቤት የለውም፣ እንቅስቃሴዎቹ ጎልቶ የወጣ መሰረታዊ ጥያቄ የላቸውም የሚሉ አስተያየቶች ይደመጣሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?
እንቅስቃሴው ዋና እምቡጥ የለውም የሚለው ጉዳዩን ካለመገንዘብ የመጣ ነው፡፡ 25 ዓመት ሙሉ ሲጠራቀሙ የመጡ በርካታ ጥያቄዎች ናቸው የእምቡጡ መሰረቶች፡፡

በየተቃውሞዎቹ የሚነሱ የማንነትና የብሄር መብት ጥያቄዎችስ አቅጣጫቸው ወዴት ነው?
የማንነት ጥያቄ የተምታታ ነው፡፡ እንኳን በአጠቃላይ በህዝቡ ቀርቶ ተማርን በሚሉት፣ አስተማሪ ነን ምሁራን ነን በሚሉትም ዘንድ ብዙ ውዥንብር አለ፡፡ ኢትዮጵያ መቼም የምታስደንቅ ሀገር ነች፤ በዚህ ውዥንብር፣ ተማርኩ የሚለው ሰው ሁሉ በተወናበደበት ጊዜ ሯጩ ፈይሳ ሌሊሳ የተናገረው ነገር የሚያስደንቅ ነው፡፡ ብዙ ምሁራንን ዜሮ ያደረገ ንግግር ነው የተናገረው፡፡ “እኔ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ ነኝ” ነው ያለው፡፡ ሌሎቹ የማይሉትን ነው የተናገረው፡፡ ምሁራ ነን የሚሉት ሁለቱን ማገናኘት አይፈልጉም፡፡ ይሄ አትሌት ግን ድርቅ ያለውን እውነት አውጥቶታል፡፡ ሁሉም ሰው እርስ በእርሱ የተጋባባት፣ የተዋለደባት ሀገር ነች ኢትዮጵያ፡፡ ብዙዎች ዛሬ አለን የሚሉት ማንነት ሲፋቅ ሌላ ማንነት ይወጣዋል፡፡
በብሄር ተቧድኖ የሚቀርቡ ተቃውሞዎችና ጥያቄዎች ሀገሪቱን አደጋ ላይ አይጥሏትም?
አደጋ ሊፈጥር ይችላል፡፡ ግን እንደ ፈይሳ አይነት ሰዎች በብዛት የሚኖሩ ከሆነ ምንም አይፈጠርም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እውነት የሚገባቸው እንደ ፈይሳ ያሉ ሰዎች ካየሉ ስጋት አይኖርም፡፡ ዘር ከፋፋዮች ከሆነ የሚመሩት የተሰጋው ሊደርስ ይችላል፡፡ እንደኔ ግን 90 በመቶ የሚሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ኦሮሞ፣ እንደ ፈይሳ የሚያስብ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ እኔ የማገኛቸው ኦሮሞዎች ሁሉ እንደዛ ናቸው፡፡

ከ97 ምርጫ በኋላ ያለው የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ እንዴት ይገለጻል?
“ወያኔ” ብልሃት ብሎ ሃገር ውስጥ ተቀናቃኝ ቡድኖች እንዳይፈጠሩ እንዳያድጉ አደረገ፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ተቃዋሚዎቹን ከሃገር አስወጣቸው። አንዳንዱ ፈርቶ ስደት ወጣ፡፡ ያኔ ኢህአዴግ ይጠቅመኛል ብሎ ያመጣው ብልሃት አሁን የሚጎዳው ነገር ሆኗል። ትልቁ የተቃዋሚ ጎራ ያለው ውጭ ሃገር ነው፡፡ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራሊያ ደቡብ አፍሪካ ነው የተቃውሞው መቀመጫ፡፡ ተቃውሞው በጣም ከመጠንከሩ የተነሣ አሁን እነሱም ወደ ውጭ ሃገር ሄደው መስራት አልቻሉም፡፡ እዚያም ተቃውሞ ይገጥማቸዋል። የበለጠ ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ተቃውሞ ነው ከውጭ ሃገር እየገጠማቸው ያለው። እዚህ ሊቆጣጠሩት ይችሉ የነበረውን ተቃውሞ ገደልን ብለው ወደ ውጪ እንዲሄድ አደረጉት። ወደ ውጭ የገፉት ተቃውሞ ደግሞ ጊዜውን ጠብቆ እነሱኑ ሽባ አደረጋቸው፡፡ ሆቴል እየተከተሉ ማዋረድ ሆነ ነገሩ። ‹‹ተንጋሎ የተፋው ለራሱ ከረፋው›› አይነት ነገር ነው የሆነው፡፡ የተፉት መልሶ መጣባቸው፡፡ አሁን ያንን ሊያቆሙት አይችሉም። እነሱ ካልተለወጡ ያኛው እየተባባሠ ይሄዳል እንጂ በምንም መንገድ አይለወጥም፡፡ ሊደርሱበት ሊቆጣጠሩት አይችሉም።

በአገር ውስጥ ያለው የተቃውሞ እንቅስቃሴስ?
አገር ውስጥ ስላሉ የፖለቲካ ቡድኖች ምንም የምናገረው ነገር የለም፡፡ ማን አለና ነው የምናገረው? ማንም የለም፡፡ ሠማያዊም ሌላውም የሉም፤ የሚረቡ አይደሉም፡፡ አላማቸውም ሌላ ነው፡፡
በሦስት ስርዓቶች ውስጥ ያሣለፉ እንደመሆንዎ ተቃውሞዎች በንጉሡ፣ በደርግና በኢህአዴግ መንግስታት ያላቸው አንድነትና ልዩነት እንዴት ይገለጻል?
በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ህዝቡ አልተንቀሳቀሰም። ተቃዋሚ የሚባለው ተማሪውና አስተማሪው ነበር፡፡ እሱም በአብዛኛው የዩኒቨርሲቲ ተማሪና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡ ህዝቡ ግን አብዛኛው የአፄ ኃይለስላሴ ደጋፊ ነበር፡፡ ግፉንም በደሉንም አልተረዳም ወይም የበደሉ አካል ነበር ማለት ይቻላል። ጭቆና፤ ጨቋኝና ተጨቋኝ በሚል ርዕስ በመፅሃፌ ገልጨዋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ጭቆናን ለማጥፋት የሚፈልግ የለም፤ትግሉ ሁሉ ተጨቋኙ ጨቋኝ ለመሆን ነው፡፡ ጨቋኙ ደግሞ ጨቋኝ መሆኔን አልለቅም እያለ ጨቋኝ ለመሆን ተጨቋኝና ጨቋኙ ይታገላሉ እንጂ ጭቆናን ለማጥፋት የሚደረግ ትግል ኖሮ አያውቅም፡፡ አሁንም የሚደረገው ጨቋኙን ወያኔን አውርደን፣ እኛ ጨቋኝ እንሁን ነው፡፡ ጭቆናን እናስወግድ የሚል ትግል አይደለም፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ተጨቋኙ ከጨቋኙ ጋር የተባበረ ነው፡፡ ፈልጎ ነው ያንን የሚያደርገው፡፡ ስንት ሺህ ሰው ባለበት 5 ፖሊሶች አንዱን መንገድ ላይ ይዘው ይደበድቡታል፡፡ እንደዚያ ሲያደርጉ 1ሺ ሰው ምንም አያደርግም፡፡ ይሄ ለኔ የጨቋኝ ተጨቋኝ ስምምነት ነው፡፡ “ለምን ትመታዋለህ?” የሚል የለም። ያ ሁኔታ እስካለ ድረስ ጭቆና ይቀጥላል፡፡

መንግስታቱ ለተቃውሞዎች የሚሰጡት ምላሽስ በንጽጽር ምን ይመስላል?
በአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ከመጠን ያለፈ የኃይል እርምጃ አይታሰብም፡፡ ንጉሱ የኢትዮጵያ ስምም ሆነ የሳቸው ስም በውጭ ሀገራት በክፉ እንዲነሳ አይፈልጉም፡፡ ራሳቸውን ስለሚያከብሩ ሀገሪቱንም ያከብራሉ፡፡ ለራሳቸው የሚሰጡት ክብር ነው ሀገሪቱን እንዲያስከብሩ የሚያደርጋቸው፡፡ አሁን ያ የለም። የአትሌት ፈይሳ ድርጊት በስንት የዓለም ሚዲያ ነው የተነገረው? ግን ምን ተሰማቸው? ፈይሳ የበለጠ ነገሩን አፈነዳው፡፡ ይሄ ውርደት ግን አይሰማቸውም። ይሄ ህዝቡ የሚደበደበውና አስከሬኑ በየሚዲያው የሚታየው ያሳፍራቸዋል? በአፄ ኃይለስላሴ ጊዜ ይሄ በጣም የሚያሳፍር፣ ሀገሪቱን ህዝቡን ክፉኛ የሚያዋርድ ነገር ነበር፡፡ ንጉሡ ይሄን አይፈልጉትም ነበር፡፡ ፖሊስ ከተማሪ ጋር ይጣላ የነበረው በዱላ ነው እንጂ በመትረየስ አልነበረም፡፡ እንግዲህ የሁለቱ የአፀፋ መልስ አሰጣጥ ከክብር ጉዳይ የሚመነጭ ነው፡፡ አፄ ኃይለሥላሴ ታሪካቸውን ራሳቸውን የሚያስከብሩ ስለነበሩ ክብራቸውን ይጠብቃሉ፡፡ አሁን ያሉት ራሳቸውንም ህዝቡንም አያከብሩም፤ታሪካቸውንም አያከብሩም፤ የሚታያቸው ጡንቻ ብቻ ነው፡፡

በአፄ ኃይለሥላሴ ጊዜ የሰብአዊ መብት ጉዳይ በጨዋነት የተያዘ ነው እንጂ በወረቀት ላይ ብቻ የሰፈረ አልነበረም፡፡ ይሄን ማድረግ ሀጢያት ነው፤ ብልግና ነው፤ ነውር ነው—ነበር የሚባለው፡፡ ከሥነ-ምግባር የሚመነጭ ሰብአዊነት ነበር፡፡ ጡንቻ የተጀመረው በደርግ ዘመን ነው፡፡ በጥይት መጋደል ተጀመረ። እውነት ለመነጋገር ከሆነ፣ ያንን ያመጣው ደርግ አልነበረም፡፡
የስልጣን ተቀናቃኝ ሆነው የገቡት ኢህአፓና መኢሶን ነበሩ ግብግቡን የጀመሩት፡፡ እነዚህ አካላት የሶስትዮሽ ድብድብ ሲገጥሙ መሳሪያ ያደረጉት ወጣቶችን ነበር፡፡ #ወያኔ”ም የኢህአፓ የመኢሶንና የደርግ ርዝራዥ ነው፡፡ እምነታቸውም የጡንቻ ነው፤ እስካሁን የሰሩትም በዚያው ነው። የሚለያየው የያዛቸው የውጭ እጅ ብቻ ነው፡፡ ሶቭየት ህብረት ደርግን መሳሪያ እየሰጠ ለግድያ ነፃ አድርጎት ነበር፡፡ እነዚህ ደግሞ በአሜሪካ ይደገፋሉ። አሜሪካ ደግሞ ግልፅ ግድያ አይፈልግም ነገር ግን እነዚህ በኃይል እየወጡ ጉልበታቸውን እያሳዩ ነው፡፡

በእንዲህ ያለ የፖለቲካ ቀውስ ወቅት የምሁራን ሚና ምን መሆን አለበት?
መጀመሪያ ፍርሃት መወገድ አለበት፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለህዝብ ነፃነት መቆም ያለባቸው ምሁራን፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ግን አሁን በፍርሃት ቆፈን የተያዙ ናቸው፡፡ እነዚህ ራሳቸውን ነፃ ካላወጡ ሌላው ነፃ አይወጣም። የምሁራኑ በዚህ ውስጥ ነው ያለው፡፡

በአገሪቱ ላይ መረጋጋት እንዲፈጠር መፍትሄው ምንድን ነው ይላሉ?
ከኃይለኛ ጋር ስትጋፈጥ መፍትሄው ሁሉ የሚኖረው በኃይለኛው እጅ ነው፡፡ መፍትሄው ሁሉ ያለው በ“ወያኔ” እጅ ነው፡፡ ከ“ወያኔ” በስተጀርባ ደግሞ በአሜሪካ እጅ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ልስበር ካለ መጥፎ ነው፤መጫረስ ነው የሚሆነው፡፡ በተለይ ደግሞ ወያኔን ትግሬ እያደረጉ፣ ትግሬን ሁሉ ወያኔ እያደረጉ የሚኬድበት ሁኔታ መታረም አለበት፤ አደገኛ መርዝ ነው፡፡ ሀገሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው፡፡ መፍትሄው ግን በ“ወያኔ” እጅ ነው ያለው፤ ህዝቡን ማዳመጥ አለባቸው፡፡

 

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20203#sthash.ToqrdtF8.dpuf

ዛሬም እዚያው ነን፤ አንሰለችም {ግርማ በቀለ}

unity 898ሥራችንን ትተን የሙሉ ጊዜ ‹ፖለቲከኛ› ያደረገን — ለራሳችን ክብር፣ ለአገራችን ፍቅር፣ ለልጆቻችን አገር . . . ስንል፣ በአገራችንና ህዝባችን ላይ የሚያርፈውን የጥቃት በትርና የሚደርሰውን ውርደት፣ በህዝብ መካከል የሚዘራውን አጥፊ የዘረኝነት ሴራ የመመከት ተልዕኮ እንጂ ሥራ ፈትነትና የመቃወም አባዜ አይደለም፡፡ የጽናታችን ምስጢርም የትግላችን መስመር በግልጽ የተሰመረ መሆኑ ነው፤ የዘርና የጥላቻ ፖለቲካን የሚጸየፍ፣ በማንም ኢትዮጵያዊ ላይ በየትም ጊዜና ቦታ የሚፈጸም በደልና ግፍ ፣ የሚደረግ አድልኦ በእኩል የሚያመን፣ የአስተሳሰብና አመለካከት ልዩነትን የሚያስተናግድና በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት የማይጠራጠርና ለዚህና ለዜጎች ክብር የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል ከራስ ጋር የተገባ ቃልኪዳን ፡፡ አዎን ዛሬም ስለቀጣይ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታችንንና እንደ አገር የመቀጠል ዕጣ ፈንታችን በእጅጉ ስለሚያሳስበን ነው እኛ የምንጽፈውና የምንጮሄው እያለን ለአንባቢና አድማጭ እስከሚሰለች ስለ ብሄራዊ ዕርቀ-ሰላምና አካታች የሽግግር መንግስት ምስረታ ያለመታከት የምንጎተጉተው ፤ለረጅም ጊዜና በተደጋጋሚ ለህወሃት ዘረኛ ቡድን ስንመክርና ስንጸልይ የደከምነው፣ ወደ ኅሊናቸው የተመለሱትን ‹‹ እንኳን ደህና መጣችሁ›› እያልን ስናበረታታ የነበረውና ዛሬም ለህወኃት ምርኮኛ የኢህአዴግ አባል ድርጅት አመራሮች ወደኅሊናቸው እንዲመለሱ ማሳሰቢያ መስጠት ውስጥ የገባነው፡፡

ይህን ሁሉ ስንል ዛሬ ላይ የተቀጣጠለው አገር አቀፍ ህዝባዊ እምቢተኝነት ለደቂቃም ሳይቆም ፣ ይህም የለውጥ ትግሉ በህወኃት ፕሮፖጋንዳ ሳይበረዝ ህወኃትንና ንኪኪና ተጠቃሚ ጋሻጃግሬዎቹን (እነርሱ አንድ ካደረጉት) ከትግራይ ህዝብ ነጥለን፣ ህወኃት መራሹን ገዢ ፓርቲ ከመንግስታዊ ሥርዓት ( የማይመጥነው ቢሆንም፣ በመቻቻል መርህ ስለቀጣዩ ጉዞ ሲባል ) በመለየት ህዝባዊ ትግሉ የበለጠ ተጠናክሮ በትብብር ተቀናጅቶ መቀጠል አለበት የምንለው፡፡ በህዝብ እየተመራ ያለው ህዝባዊ ትግል ለውጡን አይቀሬ ቢያደርገውም ለመጪው ጊዜ እንዴትነት ግልጽና የጋራ ተቀባይነት ያለው አመራር ሊያመጣ አይቻለውምና – ስለቀጣዩ የሽግግር ወቅት ከወዲሁ የምክክርና የዝግጅት ተግባር በማከናወን ሽግግሩን በተረጋጋ አሳታፊ መንገድ ለማከናወን አካታች የለውጥ ማዕከል የሚሆን ጠንካራ አገራዊ ኃይል እንዲፈጠር ያለማሰለስ የምንጎተጉተው፡፡

ቴዲ አፍሮ ‹‹ …በልዩነታችሁ ይያያዝ እጃችሁ… ›› እንዲል ከተባበርን በተረጋጋና አሳታፊ መንገድ መጪውን ጊዜ ብሩህ እንደርጋለን ፤ ከተለያየንና በየፊናችን ከቆምን መጪውን ጊዜ ጥያቄ ውስጥ እንከታለንና የጎንዮሹን እርግጫ ፣የተናጠሉን ሩጫ አቆይተን በአገራዊው ወቅታዊ አጀንዳ ‹‹ …በልዩነታችን እጃችንን እንያያዝ… ›› ፣ እንሰባሰብ// መልዕክታችን ነው፡፡

‹‹ የ25 ዓመታትን ዘረኛ የከፋፍለህ ግዛ ሴራ ሰብሮ ያለምክክርና ፈቃዳችን አንድ ላይ ያቆመን ከሸክማችን በላይ የሆነው የጥቂት ዘረኞች ጭቆናና ይህን ተከትሎ ያነሳናቸው ህገመንግስታዊ የመብትና ክብር ጥያቄዎች እስከሚመለሱ ህዝባዊ ትግሉ፣ ለመጪው የሽግግር ወቅት ዝግጅት ጋር ጎን ለጎን ተጠናክሮ ይቀጥል ፣ በዚህ ከማናችንም ግምት ውጪ በሁነ ፍትነት በሚለዋወጠው ክስተት ጊዜ እንዳይቀድመን በቪዥን-ኢትዮጵያና ኢሳት የተጀመረው የውይይት መድረክ ይቀጥል፣ሰፍቶና ተጠናክሮ በተደጋጋሚና በተከታታይ ይደረግ ›› አስቸኳይ ጥሪያችን ነው፡፡

በቸርና በድል ያገናኘን፡፡ ነሃሴ 23/2008 ዓ.ም. UNITE.

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20207#sthash.vZCB5ax6.dpuf

The Brutal Crackdown of Peaceful Protesters in Ethiopia and A Call for U.S. Sanction Against the Rogue Regime in Ethiopia

Dear Secretary Kerry:

In the last nine months, spontaneous protests have erupted in many regions of Ethiopia – specifically in the Oromo region and most recently in Gondar and other Amhara regions that accounts for 75% of the Ethiopian population.  It is widely reported that many peaceful protestors with legitimate grievances have been killed by government forces. According to the statement issued on August 13, 2016   by Human Rights Watch as many as 100 people have been killed.[1]

Secretary Kerry Shakes Hands With Ethiopian Prime Minister Hailemariam

More than 500 demonstrators are now estimated to have been killed by security forces in largely peaceful protests since November 2015. [2]Ethiopian Advocacy Network (EAN) is deeply troubled and outraged by the persistent killing of peaceful protesters by the repressive regime in Ethiopia.  The regime’s security forces have very well documented history of using excessive lethal force to stifle any type of dissent.

Choking off all peaceful and legitimate avenues for dissent coupled with unaccountable institutions fuels violent extremism and increases the likelihood of long-term instability in Ethiopia.

In 2006 Vicki Huddleston, the Charge d’ Affairs at the U.S. embassy in Addis Ababa, announced the cancellation of future sales of Humvee military vehicles to Ethiopia because they were being misused to “disperse demonstrations.”  Almost ten years later, it has come to our attention that guns and bullets supplied by the U.S. are being used

to kill peaceful demonstrators. We understand that there is a strong high level relationship between the Pentagon and Ethiopian Defense Forces. It is imperative for the U.S. to stop supplying tools of repression to the Ethiopian regime. In fact, we strongly believe that the mass killings at the hands of the brutal security forces should trigger the Leahy Law.

At this point, we urge the Obama Administration to sanction the Ethiopian regime by immediately cutting U.S. military aid and other forms of assistance except humanitarian aid that the regime uses to bolster its arsenals of repressions in many ways, including the recent massacre of hundreds of peaceful protesters.

While we are astounded by the deafening silence of the Obama Administration, the minority regime in Ethiopia is interpreting U.S. acquiescence as endorsement of its criminal actions in Ethiopia.  We, therefore, urge the U.S. to publicly condemn the carnage in the strongest possible terms and demand that the state sponsored terror against Ethiopian citizens and the egregious human rights violations come to an immediate halt.

On August 10, 2016 Zeid Raad Al Hussein, UN High Commissioner for Human Rights stating that “the use of live ammunition against protesters in Oromia and Amhara of course would be a very serious concern for us,”[3]  has called for an international investigation into the killings which the regime has promptly rejected. Such is the lawless nature of a regime that has a seat in the Security Council. The UN, the U.S., UK and EU should pressure the regime to allow international observers access to Ethiopia to investigate the murders.

Amnesty International in a statement issued on August 8, 2016 has called for “the prompt, impartial and effective investigation of the crimes and all those suspected of criminal responsibility must be brought to justice.”[4]

We firmly believe that there can be no sustainable economic growth, peace and stability in Ethiopia without political reforms. respect for human rights and the rule of law. The U.S. should pursue a constructive policy that would advance fundamental reform that would lead to a genuine constitutional democracy through an all-inclusive transitional process. The U.S. should also use its leverage to pressure the regime to stop the bloodshed and enter into a constructive dialogue with all stakeholders.

The violent response to the peaceful protests is intolerable and the campaign of

repression by the brutal regime must end immediately to avert wide spread chaos that is bound to engulf the country and the region.  All peaceful protesters that are being held for simply exercising their rights to freedom of expression and assembly must be immediately and unconditionally released.

In March of 2013 you stated that “it’s no coincidence that the places where we face some of the greatest national security challenges are the places where governments deny basic human rights to their nation’s people.

Ethiopia, the most populous country and the regional power in the strategic Horn of Africa is the key player for the maintenance of peace and stability in the region. It is time for the U.S. to take a principled stand and reassess its “unholy alliance” with the repressive regime that is widely viewed as illegitimate in the eyes of the vast majority of the 100 million Ethiopian citizens.

The U.S., as the principal ally of the Ethiopian regime, should take the lead and issue a strongly worded public denouncement of the mass killings in Ethiopia and impose sanctions (visa restriction, asset freeze) against senior government officials – both civilian and military- who are implicated in the mass killings

In the absence of strong actions on the part of the U.S., Ethiopians are inclined to believe U.S. complicity in the massive human rights abuse and state sponsored terror being committed by the minority ethnic dictatorship in Ethiopia. U.S. policy makers should understand that, short of a serious commitment and intervention to avert an impending tragedy, the current volatile political situation in Ethiopia could potentially slide into civil war, ethnic cleansing and even genocide; thus, threatening peace and stability in Ethiopia and in the Horn of Africa.

Thank you for your prompt attention to this very urgent matter.

We look forward to hearing from you very soon

Sincerely,

Araya Amsalu, Ph.D.

Ethiopian Advocacy Network is a grassroots organization that was formed in January 2015 by Ethiopian-Americans, Ethiopian activists and community organizers to promote democracy, human rights, and justice in Ethiopia through advocacy, civic education and grass roots mobilization. EAN has a global presence with members in the USA, Africa, Canada and Europe.

[1] https://www.hrw.org/news/2016/08/13/ethiopian-forces-kill-100-protesters

[2] ibid

[3] http://www.aljazeera.com/news/2016/08/calls-probe-ethiopia-protesters-killings-160810163517810.html

[4] https://www.amnesty.org/en/latest/news/2016/08/ethiopia-dozens-killed-as-police-use-excessive-force-against-peaceful-protesters/

 

– See more at: http://ecadforum.com/2016/08/29/a-call-for-u-s-sanction-against-the-rogue-regime-in-ethiopia/#sthash.9gEhvER7.dpuf

ወይ አብረን እንሳቅ ካልሆነም አብረን እናልቅስ! [ከይገርማል]

Laugh-or-cry-...-Bothበየአካባቢው እየተደረጉ ያሉት ጸረ-ወያኔ እንቅስቃሴወች ክልላዊ ባህሪ መያዝ ያሳሰባቸው ግለሰቦች የሰሞኑ የአማራ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያውያን እንጅ የአማሮች መባል የለበትም ብለው ሲከራከሩ እየተደመጡ ነው:: ከኢትዮጵያዊነት ደረጃው ዝቅ ብሎ የማያውቀው አማራ ዛሬ ላይ በአካባቢው የታጠረ የሚመስል ትግል እያደረገ መሆኑ ግልጽ ነው:: “ወልቃይት የአማራ ነው! በአማራ ላይ ያነጣጠረ የዘር ምንጠራ ይቁም! የወያኔ የበላይነት ይብቃ!—” እያለ ድምጹን ከፍ አድርጎ መፈክር እያሰማ ነው:: ይህን እንዲል ያስገደደው በራሱ ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ ስለተከፈተበት እንደሆነ በበኩሌ እረዳለሁ:: በህልውናው ላይ የተጀመረውን የጥፋት ዘመቻ ለመመከት ደፋ ቀና እያለ ያለው አማራ የሌሎች ወገኖቹ ህይወት አሳስቦት በኦሮሚያና በሌሎች ክልሎች የሚፈጸመውን የወያኔ የዕብሪት ጭፍጨፋ እያወገዘ ኢትዮጵያዊነቱን ማስመስከሩም አልቀረም::

የአማራውን ትግል ፍጹም ኢትዮጵያዊ መልክ ለመስጠት የሚደረገው ሙከራ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው:: የአማራው ትግል በሀገራችን እንደቅንጦት የሚታዩት የዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበሩ በማለት የሚደረግ ትግል ሳይሆን ከወያኔ የዘር ማጥፋት ዕቅድ ለማምለጥ የሚደረግ የሞት ሽረት ትግል ነው:: አማሮች በሰላም ከሚኖሩበት አካባቢ እየተለቀሙ ሲታረዱ አንድም ክልል ሀዘናቸውን የተጋራ: የተቃውሞ ድምጹን ያሰማ አልነበረም:: ወደፊት ጊዜ ፍንትው አድርጎ የሚያወጣው ሀቅ የሚጠበቅ ሆኖ አሁን ባለን ግርድፍ መረጃ መሰረት በግላጭ ከተገደሉት በተጨማሪ ሦስት ሚሊዮን ያህል አማራ ያርግ ወይ ይስረግ ሳይታወቅ ዳብዛው ጠፍቶ ቀርቷል:: ይህንን አማራ-ተኮር እልቂት ሲያቀነባብሩ ከነበሩት ወያኔወች ጎን በመሰለፍ የአማራ ወኪል ነኝ የሚለውን ብአዴንን ጨምሮ ሁሉም ክልሎች በአማሮች ላይ የተለያየ የግፍ አይነት ፈጽመዋል:: ዛሬ ላይ እኒህ የጥፋት ሰለባ የሆኑት መከረኞች እየደረሰባቸው ያለው የዘር ማጽዳት ዘመቻ እንዲገታ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው:: ከእኛ የሚጠበቀው የእነዚህ ወገኖቻችንን ስሜት ተጋርተን ጩኸታቸውን አብረን እየጮህን በደላቸው እንዲሰማ የድርሻችንን ማበርከት እንጅ በጥቃት ስሜት እየተንተከተከ ያለውን የሕዝብ እንቅስቃሴ የሚያጠፋ ቀዝቃዛ ውሀ መቸለስ አይደለም::

ኢትዮጵያን ከወያኔ የጭቆና አገዛዝ ነጻ ለማድረግ የሚደረገው ግብግብ በአማሮች ላይ ብቻ የተጣለ ሸክም እንዲሆን የማይፈቅዱ አማሮች መኖራቸውን አምነን መቀበል ከስህተት ያድነናል:: ስለዚህ መተያየት እንዳይፈጠርና ወደኋላ ማለትን እንዳያስከትል በሚተላለፉት መልእክቶች ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ ተገቢ ነው:: የሚሻለው: እንቅስቃሴ በማይታይባቸው አካባቢወች የጸረ-ወያኔው የአመጽ እንቅስቃሴ እንዲጀመር አመቻችቶ ሀገራዊ ገጽታ እንዲላበስ የተቀናጀ ትግል ለማድረግ መጣር ነው::

እንደሚገመተው ከሆነ ዛሬ ላይ የሕዝባቸው ሰቆቃ ያንገፈገፋቸው  በብአዴን ውስጥ ያሉ የአማራ ልጆች ከወገናቸው ጋር መስዋእትነትን ለመቀበል ወስነው በጽናት እንደቆሙ ነው:: እኒያ የወያኔን የጥፋት አላማ በአማራ ላይ ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ የነበሩት የቀድሞ የብአዴን አመራሮች ከታች እየተሳቡ በወጡ እውነተኛ የአማራ ልጆች የተተኩ መሆኑን የሚያሳይ የተግባር እንቅስቃሴ እንዳለ ለመገንዘብ አያዳግትም::

በአማራ ላይ የሚፈጸመው ሰቆቃ ያብቃ ብላችሁ የሕዝባችሁን የትግል እንቅስቃሴ ደግፋችሁ እየታገላችሁ ያላችሁ እናንተ የአማራ ልጆች ብርቱ ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል:: ወያኔወች በክፋትና በተንኮል የተራቀቁ ናቸው:: ሌት ከቀን የሚያስቡት ጠላት ነው ብለው የፈረጁትን አማራ ከማጥፋት ጎን ለጎን የሕዝቡን አንድነት ሸርሽረው የተቃውሞውን እንቅስቃሴ ማርገብና ለማይጠረቃ የንዋይ ፍላጎታቸው ለብዝበዛ የተመቸ ሜዳ መፍጠር ነው:: የሚደክሙት ለዳር ድንበር መከበርና ለሀገር ብልጽግና: ለህዝብ ሰላም: ፍቅርና አንድነት አይደለም:: እነርሱን የሚያሳስባቸው  ከፈረሹበት የእርዝቅ መንበር ላይ የሚቀመጥ የልጅ ልጅ ተክተው ትግራይ-መር ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ምን እናድርግ የሚለው ጥያቄ ብቻ ነው::

ይህን እነርሱ በጎ የሚሉትን አላማቸውን ለማደናቀፍ የሚነሳን ማንኛውም አካል ከማጥፋት ወደኋላ አይሉም:: ቂመኞች በመሆናቸው ይቅርታን አያውቁም:: ሽንፈትን አምኖ እንደ እንግዳ ዶሮ አንገትን ቀብሮ ከነርሱ ስር ማደር ከመጠቃት አያድንም:: በህይወት ላሉ አማራወች ይቅርና ለሞቱ አባቶቻችን ያልተኙ መርዘኞች መሆናቸውን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት አያስፈልግም:: የሚሻለው “ከውርደት ሕይወት-የኩራት ሞት!” ይመረጣል ብሎ ከህዝብ ጎን ተሰልፎ እስከመጨረሻው ድረስ እየተፋለሙ ጥሎ መውደቅ ነው:: ነካክቶ ማፈግፈግ የረባ ነገር ሳይሰሩ ቀስ በቀስ ከምድረገጽ መጥፋትን ያስከትላል:: የሚያሸንፉን አንድ ሆነው በአንድ ልብ ስለተሰለፉ እንጅ በምናቸውም ከእኛ ስለሚበልጡ አይደለም:: ልብ አድርጉ! ይህንን የተነቃቃ የህዝብ ትግል እንዲበርድ አድርጎ ማፈግፈጉ ጉዳቱ ቀላል አይሆንም:: በቅንጅት አመራሮች የተሳሳተ አካሄድ የሕዝባችን የትግል መንፈስ የተቀዛቀዘበት ሁኔታ ተከስቶ እንደነበር ማንም አይስተውም:: አሁን ገንፍሎ እየወጣ ያለውን የሕዝብ አመጽ በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ጭራሹኑ የተሰበረ መንፈስ ፈጥሮ ዳግም ይህን እድል የማናገኝበት ሁኔታ ሊያስከትል ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው::

ትግሉን ለማቀላጠፍ ዝግጁ ሆኖ መጠበቅ ኋላ ላይ ከመደናበር ያድናል:: ለዚያም ነው እስከቀበሌ ድረስ ወርዶ ሕዝብን የማንቃት: የማደራጀትና የማስታጠቅ ስራ ለይደር የሚተው የማይሆነው::  ስለሀገር አንድነትና ስለሕዝብ ነጻነት የሚጨነቁ ግለሰቦችና ፓርቲወች ድጋፋቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል በራችሁን ብትከፍቱ የተሻለ ነገር አቅዶ ለመተግበር ይጠቅማል:: እናንተ ለማስተባበር ከቆረጣችሁ ጥሎ ለመውደቅ ፈክሮ የሚነሳው አማራ ድፍን ኢትዮጵያን እንደጉድ ማጥለቅለቁ የማይቀር ነው:: ይህን ለማድረግ ስትነሱ በቅድሚያ ከመሀላችሁ ተሰግስገው ለወያኔ አይንና ጆሮ ሆነው እየሰሩ ያሉትን ባንዳወች በማጽዳት መሆን አለበት::

አማራ ሲፈጥረው በሞራል የተገነባ ሕዝብ ነው:: ከሌላ አካባቢ መጥተው ተመሳስለው ለሚኖሩ ሰዎች ያለው ፍቅርና ክብር የተለየ ነው:: በሆነ ምክንያት ከሌላ አካባቢ ከመጡት ሰዎች ጋር የተጋጨ ያገር ሰው ቢኖር ይወቀሳል:: “የሰው አገር ሰው እንዴት ለማስቀየም ደፈርህ? ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ እኛን አምኖ እኛኑ ዘመድ አድርጎ ተጠግቶ የሚኖርን ሰው ማስቀየም ደግ ነው?” ተብሎ ውግዘት ይደርስበታል:: በዚህም የተነሳ በአማራ ክልል የሚኖሩ የሌሎች ክልሎች ኗሪወችም ሆኑ የውጭ ሀገር ሰዎች ከአካባቢው ተወላጅ በተሻለ ሁኔታ ያለሀሳብ ተከብረው በሰላም ይኖራሉ:: ይሁንና “ያልበደለ ሰው ለምን ይቀጣል!” የሚሉ ተቆጭ ሽማግሌወች በሌሉባቸው አካባቢ የሚኖሩ ዘረኞች ከሌላ አካባቢ የመጡ ናቸው በሚሏቸው ምንም ጥፋት በሌላቸው ሰላማዊ አማራወች ላይ አማራ በመሆናቸው ብቻ ሀብታቸውን ይዘርፏቸዋል: ያፈናቅሏቸዋል: አስረው ያሰቃይዋቸዋል: ይገድሏቸዋል:: ይህን ከሞራልና ከሐይማኖታዊ ባህሪይ ያፈነገጠ ወንጀል ሲሰሩ ጠያቂ ሕግ: ወቃሽ ህሊናም ሆነ የሚፈሩት አምላክ የላቸውም:: እንዲህ ያለውን የሕዝብ ሰቆቃ ማስቆም የሚቻለው አንገትን ደፍቶ በመኖር ሳይሆን ግንባር ለግንባር ገጥሞ በመፋለም ነው::

አማራው ከአማራ ክልል ውጭ ሲኖር በየትኛውም ደረጃ በፖለቲካ አመራርነት መሰየም ቀርቶ የግልም ሆነ የሲቭል ስራውን በሰላም ሰርቶ መኖር አልፈቀድለት ብሎ ፍዳ ሲያይ ኖሯል:: በሌላ በኩል በአማራ ክልል የሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች በክልሉ የፖለቲካ ሀላፊነት ሳይቀር ከታች እስከላይ ድረስ ተሰግስገው ያለሀሳብ እየፈረዱ እያስፈረዱ ተቀምጠዋል:: በግል ስራ የሚተዳደሩትም ቢሆኑ ከኗሪው በላይ ሆነው ስለያንዳንዱ ግለሰብ መረጃ በማቀበል ሲያሳፍኑና ሲያስገድሉ እስካሁን ድረስ ዘልቀዋል:: በዚህ የተዛባ ተግባራቸው ለማፈር ያልታደሉት እኒህ ሰዎች ይባስ ብለው በአንድ ድምጽ “አህያ: ደደብ: የማይመጥኑ—” ናቸው ብለው የአማሮችን ተግባርና ባህሪ የማይገልጽ የስድብ ስም ሰጥተው አማሮችን በማንቋሸሽ እየጠሯቸው ነው:: ከአሁን በኋላ አማራው ግፍ ተሸክሞ አህያ የሚባልበት የትግሬ ወያኔወች የሀገር ሀብት እየዘረፉ ብልጥ የሚባሉበት ጊዜ ያበቃል:: ቢችሉ ከብልጥነት ወጥተው ብልህ ለመሆን ቢሞክሩ በዋናነት ለራሳቸው ይጠቅማቸዋል::

አማራ ማንንም በክፉ የሚያይ ሕዝብ አይደለም:: ሌላውም እንደራሱ የሚያስብ መስሎት ለረጅም ጊዜ ለመከራ ተጋልጦ ቆይቷል:: “ሞኝ የዕለቱን ብልህ ያመቱን” እንዲሉ አማሮች የዘላለም ህይወት ለመታደል ለህሊና የማይቆረቁር በፈጣሪ ዘንድ የተወደደ ተግባር በመፈጸም ታጋሽነታቸውን ሲያሳዩ የትግሬ ወያኔወች ግን የአፍታ ህይወት አጓጉቷቸው: ትዕቢት ልቦናቸውን ሰውሮት ከህዝብ ቀምተው ህዝብን እያዋረዱ ጥለውት የሚሄዱት ሀብት ያከማቻሉ:: ከእንግዲህ በኋላ ግን ሁኔታወች መስተካከል ይኖርባቸዋል:: ከቀን ቀን ይማራል የማይባልን አጥፊ ሰው አዝሎ እሹሩሩ ማለት ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም:: አማሮች አሁንም ቢሆን ባለጌወችን ፈርተው ሳይሆን አምላክን ስለሚያስቡ መሰረታዊ ባህሪያቸውን ቀይረው ማንንም ለማጥፋት ወይም ለመበቀል የሚነሱ አይሆንም:: ነገር ግን ከእንግዲህ በኋላ የትግሬ ወያኔወች ከመሀላቸው ዘና ብለው ተቀምጠው መረጃ እያቀበሉ ትግሉን እንዲያከሽፉ: ጭቆናን እንዲያስቀጥሉ  ሊፈቀድላቸው አይገባም:: ” የሰው ሞኝ የለውም ብልሀቱ ይለያያል እንጅ!” አይደል የሚባለው? እኛም እንዳቅማችን ብልሀት አናጣም:: ሰላማዊ ኗሪ መስለውም ሆነ በግላጭ የጦር መሳሪያ ታጥቀው የወያኔ የመረጃና የአፋኝ ኃይል ሆነው የሚሰሩ በክልሉ የሚኖሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ባስቸኳይ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ ይደረግ:: ይህን የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት የተሰገሰገን የጥፋት ኃይል በጉያ ታቅፎ ይዞ ታግለን እናሸንፋለን ማለት ከየዋህነት የዘለለ ሞኝነት ነው:: ይህ የዘረኝነት ጉዳይ አይደለም: መተኪያ የሌለው የትግል ስትራቴጅ እንጅ::

አማሮች አሁንም ኢትዮጵያን ይወዳሉ:: አሁንም የህዝብን በሰላም አብሮ መኖር ይፈልጋሉ:: አይደለም በአንድ ሀገርና በአንድ ሰንደቅ አላማ ስር ክፉና ደጉን ተጋርተው አብረውት ለኖሩ ሕዝቦች ይቅርና ከሌላ ሀገር ለመጣ ሰላማዊ ሰውም ቢሆን ፍቅርና ክብር የሚሰጥ ትሁትና ፈሪሀ-እግዚአብሔር ያደረበት ሕዝብ ነው: አማራ:: ሰላም የሚነሱት ወያኔወች በያዙት መንገድ እስከቀጠሉ ድረስ ግን “ለሰላም ስትሉ ሁሉንም ነገር ተውት” ማለት “በወያኔ የሚደርስባችሁን ግፍ ችላችሁ አንገታችሁን ደፍታችሁ ተቀመጡ” ማለት ነው:: ከእንግዲህ በኋላ በሀገር ልጅነት ስም ነጻነታቸውን ተገፈው በባርነት ለመኖር አይፈቅዱም:: በዚህ ምክንያት የሚደፈርስ ሰላም ካለ መደፍረሱ የግድ ይሆናል:: ሰላም በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ የሚመጣ አይደለም::

ካድሬወቹን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እያቀረበ “ጥያቄ ካለ በሰላማዊ መንገድ መጠየቅ ሲቻል ለአመጽ መነሳሳት አግባብ አይደለም” የሚል የማጭበርበሪያ አስተያየት የሚያሰጠው ወያኔ ከስህተቱ ቢማር ይበጀዋል:: ለሕዝብ ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ የሕዝቡን ፍላጎት ተከትሎ የሚሰራ ቢሆን ኖሮ አሁን እየታየ ያለው አመጽና ውድመት ባልተከሰተም ነበር:: በየአካባቢው የሚደረጉት እንቅስቃሴወች በሙሉ የሕዝብን ጥያቄ አዳምጦ ትክክለኛ ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት ባለመኖሩ የተፈጠሩ መሆኑን ማንም አይስተውም:: ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሕዝብን ጥያቄ ያቀረቡ የሕዝብ ወኪሎች በእብሪት ስለታፈኑ ነው ተቃውሞው የተቀሰቀሰው::

የትግራይ ሕዝብ “ጥሩውን ጥሩ: መጥፎውን መጥፎ” ማለት ማወቅ አለበት:: ከዚያም አልፎ ጥሩውን በመደገፍ መጥፎውን ደግሞ በማውገዝ ከሌሎች ሕዝቦች ጎን ተሰልፎ አጋርነቱን መግለጽና መስዋእትነት መክፈል ይኖርበታል:: ያ ሲሆን ነው መተሳሰብ አለ ማለት የሚቻለው::

 

ኢትዮጵያውያን ክፉውንና ደጉን ተጋርተን አብረን ኖረናል:: ዛሬም ያንኑ ልማዳችንን ሳንቀይር እንደወቅታዊ ሁኔታው ወይ አብረን እንስቃለን ወይም አብረን እናለቅሳለን:: አንዳችን እየሳቅን ሌላችን የምናለቅስበት አግባብ ግን ሊኖር አይችልም::

ትንሳኤ ለኢትዮጵያ!

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20177#sthash.MPmj3qxT.dpuf

እጅግ በጣም አስቸኳይ መልእክት [ብሥራት ደረሰ]

Ethiopia - Satenawበአሁኒቷ ቅጽበት በዐማራው አካባቢ ሕዝቡ ከወያኔ ታጣቂዎች ጋር በባዶ እጁ እየተፋለመ ይገኛል፡፡ ይህ ለዓመታት ታፍኖ የነበረ የነፃነት ጥያቄ ወቅቱን ጠብቆ አሁን በቅርብ ከሞላ ጎደል በሁሉም የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች ፈንድቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው ጭቆናና ምሬት በኃይል ታፍኖ ሊቀር የማይችል መሆኑን ነው፡፡

ይሁንና ነፃነት የጠማው የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሣና በሃይማኖት ተወስኖ የአንዱ ንቅናቄ ለሌላኛው ባይተዋር ሊሆን እንደማይገባ ሁላችንም ማሰብ ይኖርብናል፡፡ እርግጥ ነው እስካሁን ስህተቶች አልነበሩም አንልም፡፡ ንስሃ ልንገባባቸውና ይቅርታ ልንባባልባቸው የሚገቡ ስህተቶችን ሁላችንም ስንሠራ ለመቆየታችን ትልቁ ማስረጃ የወያኔ ሥልጣን ላይ ለ25 ዓመታት ተገሽሮ ሁላችንንም ሲቀጠቅጥ መቆየቱ ነው፡፡ ብንተባበር ኖሮ 25 ዓመታትን ቀርቶ 25 ቀናትንም አራት ኪሎ ምንሊክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ወያኔ አይቆይም ነበር – ታሪካዊ ፀፀት፡፡

ስህተት አንድ – ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የመብት ጥያቄ አንስቶ ብቻውን ሲታገል ሌላው በአብዛኛው በታዛቢ ወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ያ ትልቅ ስህተት ነበር፡፡ እርግጥ ነው የሙስሊሙን ጥያቄ ከሃይማኖት አውጥቶ ወደ አጠቃላይና ሁሉንም ሊያቅፍ ወደሚችል የመታገያ መስመር ማስገባት ይቻል እንደነበር ብንጠቁም አግባብ ነው፡፡ ጥያቄዎችን ከማጥበብ ይልቅ ማስፋትና ሁሉንም አሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባል፤ ይቻላልም፡፡ ጠባብ ጥያቄዎችን መጠየቅ ለወያኔዎች የተናጠል ብትር ይዳርጋል፤ ማንም ደግሞ በተናጠል ጥያቄዎች ድልን ሊቀዳጅ አይችልም፡፡ በትልቅ ጥያቄ ፍቺ ውስጥ ብዙ ትንንሽ ጥያቄዎች ሊፈቱ እንደሚችሉ ባለመረዳት ወይም ለመረዳት ባለመፈለግ ብዙ ዘመን ተሞኝተናል – በዚህም ሰበብ ለወያኔ ምቹ ፈረስና መጋጃ ሆነን ለብዙ ዘመን ባጅተናል፡፡ ይህን ሞኝነታችንን ተረድተን ባፋጣኝ ካልተስተካከልን የሰሞኑ እንቅስቃሴም ከጊዜያዊ ጫጫታነት አያልፍም፡፡

ስህተት ሁለት – ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን በተለይ ከዚህ ዓመት(2008) መባቻ ጀምሮ በየአካባቢያቸው ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያደርጉና በወያኔ ቅልብ የአጋዚ ጦር እንደዐይጥ ሲጨፈጨፉ ሌላው ዳር ቆሞ ይታዘብ ነበር – የወንድሞቹ ቁስል አልተሰማውም ማለት ግን አይደለም፡፡ ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ሥልት ተንበርክከን ራሳችንን በየግል ቋጠሮ በማስቀመጣችን ግን አልተባበርንም፤ በዚያም ምክንያት ወያኔ ተመቸውና በተናጠል መደቆሱን ቀጠለ፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – የኦሮሞዎችን ጥያቄ ከኦሮሞ ግዛት መጥበብና መስፋት ጋር ብቻ ከማያያዝ ይልቅ እሱን በእርሾነት ይዞ ለትልቁ ሀገራዊ ነፃነት ሁሉም በአንድነት እንዲነሣ ቢደረግ ኖሮ ይሄኔ ይሄ በየአካባቢው የሚደረግ የቁጥ ቁጥ ትግል ባላስፈለገ ነበር፡፡ ይህችን ሒሣባዊ ቀመር እንዴት ማወቅ እንዳልቻልን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ ጥቂት ወያኔዎች በአእምሮ ማለትም በተንኮል በተካነ አእምሮ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ይህን ያህል እንዴት ሊበልጡ እንደቻሉ ሳስበውም እንደዚሁ ይደንቀኛል፡፡ በምን አፈዘዙን?

ስህተት ሦስት – ሰሞኑን የዐማራው ሕዝብ ፀረ ወያኔ እንቅስቀሴውን ጀምሯል፡፡ የዘገዬ ቢሆንም ጅምሩ መልካም ነው፡፡ ሆኖም በተለይ በመነሻው አካባቢ ጥያቄው ልክ እንደላይኞቹ ሁሉ ጠበበና ወይም የሚጠበቀውን ያህል ሌሎችን አሳታፊ ሆኖ የተገኘ አልሆነምና ከክልሉ ውጪ ያሉትን ለመሳብ አቅም ያነሰው መሰለ፡፡ ጎንደር ላይ “የኦሮሞ ወንድሞቻችን ደም የኛም ደም ነው” በሚል ሕዝቡ በራሱ ተነሳሽነት የኦሮሞ ወንድምና እህቶቹን ሰማዕትነት ማስታወሱ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ ሁለቱን የወያኔ መጫወቻ ታላላቅ ብሔሮች (በእስካሁኑ ሁኔታ ማለቴ ነው) ቢያቀራርብም አሁንም ብዙ የሚቀረው ነገር እንዳለ መገንዘብ ይገባል፡፡ ወያኔዎችና ተባባሪዎቻቸው ለዘመናት የሠሩት ዕኩይ ተግባር በአንድና በሁለት የተቃውሞ ሰልፎች የሚናድ እንዳልሆነ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ሁለትም ይሁኑ ከዚያ በላይ ትልልቅ ግንዶችን የሚያሸንፍ ቅርንጫፍ – ቅርንጫፉ ምንም ያህል ቀጭንና ላንቁሶም ይሁን – የግንዶቹን ሥሮች እንደምሥጥ እምሽክ አድርጎ በመብላት ግንዶቹን ከናካቴው ሊያጠፋቸው እንደሚችል እስካሁን ማንም አልተረዳም፡፡ ታላላቆችን ለማጥፋት ደግሞ አካላዊ ግዝፈት የግድ አይደለም – ብልጠትና መሠሪነት ብቻቸውን ብዙ ሚና ይጫወታሉ – በዚያ ላይ መካሪና ሁለገብ ረድኤት የሚሰጥ አጋዥ ኃይል ካለ አናሳዎች የጥፋት መንገዳቸው ቀኝ በቀኝ ነው የሚሆንላቸው፡፡ በዓለም 14.2 ሚሊዮን አካባቢ የሕዝብ ቁጥር ያላት እስራኤል የዓለምን ፖለቲካና ኢኮኖሚ በተቆጣጠሩ ምርጥ የኅቡኣን ድርጅቶች አባላት ልጆቿ አማካይነት የሰባት ቢሊዮኑን የዓለም ሕዝብ የዕለት ተለት ሕይወትና እስትንፋስ እንደምትቆጣጠርና እንደምትወስንም ለሚረዳ ዜጋ ከስድስት ሚሊዮን የፈለቁ ጥቂት አሰለጦች ከውጪ ረዳቶቻቸው ጋር ተዓምር አይሠሩም ብሎ መገመት ሞኝነት ነው፡፡ ብዛት ብቻውን አይጠቅምም – በራሱ ዋጋቢስ ነው፤ እንዲያውም ብዛት ያጃጅላል ይመስለኛል፡፡ የሌለህን እንዳለህ፣ ያልሆንከውን እንደሆንክ በሥነ ልቦና ጥጋብ እያሰከረ ተጠቂ ያደርግሃል – ብዛት፡፡ ስታንስ ግን ጠርጣራና ፈሪ ያደርግህና ከቢጤዎችህ ጋር እያቆራኘ – እንደሙጫ እያጣበቀ – ብዙ ትንግርት እንድትሠራ ያደርግሃል – ጥቂትነት፡፡ ዕድሜ ደጉ… ማንበብም ደጉ… ከብዙው ጥቂቱን አየን፡፡

ከቅርብ ቀናት ወዲህ የዐማራው ጥያቄ ለአጠቃላዩ ሀገራዊ ነፃነት የጥሪ ደወል ማሰማት ቢጀምርም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በመነሻው አካባቢ በወልቃይት ዙሪያ ያጠነጥን ስለነበር ያ ጥያቄ ለጋሙጎፋውና ለአፋሩ ሩቅ መስሎ ሊታይ ቢችል አያስወቅስም ባይ ነኝ፤ ጥያቄው ሁሉን ቆንጣጭ ነበር ለማለት አያስደፍርም፡፡ አሁን መስተካከሉና ብሔራዊ አጀንዳ መያዙ ግን ደግ ነው፡፡ መስተካከሉን አምነን ታዲያ እንቀላቀለው፡፡ ምክንያቱም የዋናው ድል መቋጫ በዋናነት አዲስ አበባን ጨምሮ የሁሉም ሕዝብ ንቁ ተሣትፎ ነውና፡፡

ስህተት አራት – የዐማራው ጥያቄ ከጎጥና ከሸጥ አልፎ ሀገራዊ ቅርጽ ከያዘም በኋላ የመላዋ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለጋራ ሀገራዊና ብሔራዊ ነፃነቱ በአንድነት “ሆ!” ብሎ እንዳይነሣ ያደረገው ነገር አለ፡፡ ይህን ነገር ሁነኛ የፖለቲካ ቡድች በአፋጣኝ አጥንተው መፍትሔ ካልተፈለገለት ይሄ አንዴ ወለጋ ሌላ ጊዜ ጎንደር የሚደረግ ሕዝባዊ የእምቢተኝነት ዐመፅና የነፃነት ትግል የትም አይደርስም፡፡ አዎ፣ የትም! ለሕወሓት ግን ሠርግና ምላሽ ነው፡፡ ለዚህ ጎጠኛ የአናሳዎች ቡድን መሠሪ ተንኮል መሸነፍ ይብቃን፡፡

ነፃነት ቆራጥነትንና እልህን ትፈልጋለች፡፡ ነፃነት ሸረኝነትና ተንኮልን ያዘለ ፉክክርን አትሻም – የነፃነት ፍልሚያ ውጤታማ እንዲሆን በቀናነትና በእኔ እብስ አንተ ትብስ የጋራ መግባባትና መተሳሰብ መቃኘት አለበት፡፡ ሁሉም እንደየአቅሙ በስሜትና በከፍተኛ ወኔ ከተሳተፈ የነፃነት ቀን ቅርብ ናት፡፡ ነገር ግን “ቆይ እነእንትና ይለይላቸው፣ እነሱ ሲያዳክሟቸው እኛ እንቀጥልና የመጨረሻ ግብኣተ መሬታቸውን እናሳያቸዋለን…” በሚል የማይረባ ሥልት በተናጠል መጓዝ ካለ መቼም ቢሆን ነፃነት አትገኝም፡፡ ነፃነት በእልህ አስጨራሽ የጋራ ትግል እንጂ በብልጣብልጥነትና ከጋራ ትግል በመሸሽ ልትገኝ አትችልም፡፡ በአንዱ ሞት ሌላው ነፃ እንዲወጣ ተደብቆ ወይ አሸምቆ ቢጠባበቅ ደግሞ ከኅሊናም ከሃይማኖትም አንጻር ወንጀልና ኃጢኣትም ነው፡፡ ሁሉም የድርሻውን ይወጣ፡፡ “ማን ይጠይቀኛል? ማንስ ያየኛል?” የሚሉት ጥያቄዎችም የጅል ፈሊጦች ናቸው፤ በመጀመሪያ ዋናው ጠያቂ ኅሊናችንና የሚሰውት ወገኖቻችን ነፍሳት ናቸው፡፡ ከዚህ ነጥብ አኳያ ሁሉም ዐይን ነውና እንዳንታለል፡፡

ስህተትን ለማስወገድ እንዲህ ቢደረግ ጥሩ ይመስለኛል፡-

ኦሮሞው፣ ዐማራውና ሌላው ጎሣ ሁሉ በተጀመረው መንገድ ለአንድ ዓላማ ይተባበር፡፡ የተናጠል ትግል የትም እንደማያደርስም ከልምድ ይረዳ፡፡ ጠላት አንድ ነው፡፡ የጥቃቱ ሰለባዎችም አንድ ናቸው ወይም ቢያንስ አንድ መሆናቸውን ሊረዱ ይገባቸዋል፡፡ ራሳቸውን እየለያዩ በተለያዬ ጊዜ ከሚጠቁ በአንድነት ተባብረው ከዘላለም ባርነት በአንዲት ጀምበር የዘላለም ነፃነታቸውን መጎናጸፍ ይችላሉ፡፡ እንደእስከዛሬው በመለያየትና የመቃብር ጉድጓድ እየቆፈሩ በዐፅምና ባለፉ ሰዎች የታሪክ ጠባሳ የሚጃጃሉ ከሆነ ግን ልክ  እንደስካሁኑ ለጠላታቸው ምቹ እንደሆኑ አንዱ ምዕተ ዓመት አልፎ ሌላው ይተካል፡፡ በሰው ሠራሽና በጠላት-ጠመድ የልዩነት ቦምቦች ፍንዳታ ጊዜያቸውን በከንቱ ማባከን የለባቸውም፡፡ ከዚህ ሞኝነታቸው ተምረው ብልኅነትን ገንዘባቸው ያድርጉ፡፡

ለምሣሌ የቋንቋና የሰንደቅ ዓላማ ልዩነቶች ወደ ውስጥ ገብተው ካጤኗቸው መሠረታዊ ችግሮች አይደሉም፡፡ ያገሬ ባላገርና ሕጻናት ልጆቹ በሕወሓት አልሞ ተኳሾች ጭንቅላታቸው እየተበተነ በቀያቸው ሥጋቸውን አሞራና ውሻ እየጎተተው ሳለ፣ ሕወሓት ኑሯችንን አመሰቃቅሎና ሰብኣዊ ተፈጥሯችንንም  ከእንስሳነትም በታች አውርዶ በነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ የሰቀቀን ኑሮ እየገፋን ሳለ፣ እትብቴ በተቀበረባት የገዛ ምድሬ እኔን ለመንግሥት ሥራ መቅጠሩ እንደቅንጦትና ብርቅ ይቆጠርና እንደህንድ የካስት ሲስተም ሊጨብጡኝ እንኳን እየተፀየፉኝ በምገኝበት ሁኔታ … ፖለቲከኞች ሚዛን በማይደፉ የአዛኝ ቅቤ አንጓች ዓይነት ጉንጭ አልፋ ክርክሮች ቢጠመዱ ሕዝብና ታሪክ ይቅር የማይሉት ሌላ ስህተት ነው – “ቀድሞ የመቀመጫየን” ብላለች ዝንጀሮ፡፡ ከሌላው እንቶፈንቶ ይልቅ የተበላሸን በማቃናት፣ የተሳሳተን በማረም፣ የተዛነፈን በማስተካከል … ወደ ደገኛው መንገድ እንግባና እንደቀድሟችን በቶሎ አንድ ብንሆን ሁላችን እንጠቀማለን፤ ሌላው ቀስ ብሎ ይደረስበታል፡፡

ሞኝነትንና ብልጣብልጥነትን አርቆ መቅበር ይገባል፡፡ ይህን በሕዝብ ደምና አጥንት ላይ የቆመ ከፋፋይ የወያኔ ብልሹ ሥርዓት ከሥሩ መንግሎ ከነሰንኮፉ ለመጣል ሁሉም “ሆ!” ብሎ በአንድ ወቅት መነሣት አማራጭ የሌለው የጊዜው አንብጋቢ ጉዳይ ነው – ከዳር እዳር ተነጋግሮና በጥሞና ተመካክሮ በአንድ ወቅት መነሣት!! ጎጃም የሚፈሰው ደም የአርሲው ነው፤ ወለጋ የሚፈሰው ደም የጎንደሬው ነው፡፡ የወያኔን ሤራ በጣጥሰው ካልጣሉና ሰሞኑን በተጀመረው የአንድነት መንፈስ ካልታገሉ ማንም ነፃ ሣይወጣ የወያኔ አሽከርና ደንገጡር ሆኖ የመከራ ኑሮን መግፋት ነው – እስከወዲያኛው፡፡ መጥፎ ህልም ስታልም መፍትሔው ከእንቅልፍህ መንቃት ነው – ከወያኔ ሰቆቃ ለመዳንም መፍትሔው በከፋፋይ ሤራው ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ኅብረትን ማጽናት ነው፡፡

ያለፈ አልፏል፡፡ “ላለፈ ክረምት ቤት አይሠራም”፡፡ በእጃችን ያለችዋ ጊዜ ናት ወርቃማ ጊዜያችን፡፡ ወንድሞቻችን በጎጃምና በጎንደር እየተዋደቁ በወሎና በሸዋ እንዲሁም በአዋሣና በጋሙጎፋ የሚገኝ ሕዝብ ተኝቶ እንቅልፉን የሚደቃ ከሆነ የምትጠበቀዋ ነፃነት ቅዠት ናት – አትገኝም፡፡ ጎንደርና ባህር ዳር እየታመሱ አዲስ አበባና ናዝሬት በአሥረሽ ምቺው “ዓለማቸውን የሚቀጩ” ከሆነ የነበረችን አነስተኛ በሕይወት የመቆየት ነፃነት ራሷ ወደለዬለት ባርነት ትለወጥና ትልቁ እሥር ቤታችን – ዞን ዘጠኝ – ወደማዕከላዊ የወያኔ የ”ወንጀል ምርመራ” ዘብጥያነት ይለወጣል፡፡ ለዚህም ነው “የነብርን ጅራት አይዙም…” የሚባለው፡፡ ወያኔና የቆሰለ ነብር አንድ ናቸው፡፡ የወያኔን ተፈጥሯዊ የበቀለኛነት ስሜት አዲስ አበቤዎች በተለይ ጠንቅቀን እናውቀዋለን፡፡ ከ97 ምርጫ በኋላ ምን እንደደረሰብን እንኳንስ እኛ ሌላው ዓለምም ያውቃል፡፡ ወያኔ በየጊዜው በደም ካልዋኘ ያስተበተበው ድግምት አይሠራለትም – ትልቁ የሰይጣን ምስ ወይም ግብር ደግሞ ደም ነው፡፡ ለዚህም ነው በበቀል የሰከሩት ወያኔዎች በተለይ ዐማራውንም ሆነ ሌላውን – ዓላማቸውን የማይደግፍና የሚቃወማቸውን ትግሬም ሳይቀር – አዛዣቸው ዲያብሎስ በሉ ባላቸው ቁጥር ባልተወለደ አንጀታቸው ጭንቅል ጭንቅሉን እያሉ ለአባታቸው የሚገብሩት፡፡ እነሱ ካልጠፉ ሞታችንና አሟሟታችን እየከፋ እንጂ እየቀነሰ አይሄድም፡፡ በሰይጣን የቆረበ ሰው የተጎጂዎች አበቅቴ እስኪብት ድረስ ዘመኑ ከሚፈቅድለት የወንጀል ድርጊት ውጪ ሌላ ደግ ነገር ይሠራል ተብሎ አይጠበቅም – የባሕርዩ መገለጫ ክፋት ብቻ ነውና፡፡

ምርጫው የኛ ነው እንግዲህ፡፡ በሕዝብ መተባበር ወያኔዎች ሰሞኑን ደንግጠዋል፡፡ የድንጋጤያቸው ደረጃም ሱሪያቸው ከፊትም ከኋላም እስኪረጥብ ድረስ መሆኑን ምሥጢሩን የሚያዉቁ እየተናገሩ ነው፡፡ ይህን በጥርጣሬ ደረጃ ያለ የወያኔ መረጣጠብ ማፋጠንና የዚህን ሰው-በላ የአፓርታይድ ሥርዓት ዕድሜ በደቂቃዎች እንዲገመት ማድረግ ይቻላል፡፡ እንደዚያ የሚሆነው ግን የተጨቋኞች ዓላማና ፍላጎት አንድ ሆኖ ሁሉም በያለበት ወያኔን ሲያርበደብድ እንጂ አንዱ ከነሱ ጋር ማኪያቶ እየጠጣና ውስኪ እየጨለጠ፣ ሌላው ደግሞ በአልሞ ተኳሾች ልዩ ጥይት ጭንቅቱ እየፈረሰ አይደለም፡፡ አሁንም እርግጥ ነው – ኢትዮጵያ ኢያሪኮ እንዳልሆነች ልብ ይሏል፡፡ የኢትዮጵያ ነፃነት ካለደም እንደማትገኝ የጎንደርና የጎጃም ዐማሮች እያስመሰከሩ ነው፤ ከወያኔ ተፈጥሮ የምንረዳውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ያልቃታል እንጂ ወያኔዎች ፈረንጆቹ ዴሞክራሲ በሚሉት ቀልድ ወይም በሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ቤተ መንግሥት እንደማይለቁ ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም የነሱን ፈለግ በመከተል ሁሉም በተቻለው መፋለም ይገባዋል እንጂ በጩኸት ብቻ ወያኔ አራት ኪሎን ይለቃል ማለት ዘበት ነው፡፡ የዓለም ገዢ ኃይልም ከነርሱ ጋር ስለሆነ ሰሞነኛው ጩኸታችን ቀርቶ የገፍ ዕልቂታችን እንኳን ተገቢውን ዓለም አቀፍ ትኩረት አላገኘም – ማን እንደሰው ቆጥሮን! ይሄኔ የሮበርት ሙጋቤ የክብር ዘብ የአንድ ነጭ ዚምባብዌያዊ የሣሎን ውሻን በባረቀ ጥይት አቁስሎ ቢሆን ኖሮ የነቢቢሲና ሲኤንኤን እንዲሁም የነስካይኒውስና አልጀዚራ ቲቪዎች የአንድ ሣምንት የመክፈቻ ዜና በሆነ ነበር፤ ዘርንና ምጣኔ ሀብትን መሠረት ባደረገ መልክ ዓለም ይህን ያህል አሽቃባጭ ናትና ወደ አምላካችን ብቻ እንጩህ ይልቁንስ፡፡ ከሰው ምንም አንጠብቅ፡፡ ከራሳችን ውስጥ ብዙ ሥጋዊና መንፈሣዊ ኃይል አለ፡፡ ያን እናውጣውና እንጠቀምበት፡፡ ሕዝባችንንም እናንቃው፡፡ የምንችል እናስተምረው፡፡ ከተኛበትም እንቀስቅሰውና የጥንት የጧት አያት ቅድመ አያቶቹ የሠሩትን የመሰለ ታሪክ እንዲሠራ ለዳግም ልደት እናብቃው፡፡…

ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡

ሕዝቡ ማናቸውንም ዓይነት ፖለቲከኛ በልጦ ሄዷል – ወያኔንም ተቃዋሚንም፡፡ ወያኔ ተጎልቶ ያለው ከ41 ዓመታት በፊት በነበረበት ደደቢት ላይ ነው – ሰውነታቸው በዐማራና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ጥላቻ እንደተሞላና ገድሎ በማይረካ የበቀል ስሜት እንደተምቦገቦገ፡፡ ተቃዋሚዎች ያሉት የዛሬ 160 ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያ የነበረችበት የዘመነ መሣፍንት ወቅት ላይ ነው – በማይጨበጥ ህልማዊ ሥልጣን እርስ በርስ ሲራኮቱ፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉም አእምሮውን የነሣው ነገር አለ፤ ሆድ ይሁን የዝናና የታዋቂነት ልክፍት በውል ለይቼ አላውቅም፡፡ ግን ግን አሁን እኔ እምለው ሁሉም ምናልባትም አብዛኛው ራሱን መፈተሸና ከሕዝብ የነፃነት ፍላጎትና የአርነት ትግል ጎን መሰለፍ የሚችልበትን ብልሃት ባፋጣኝ መቀየስ ይገባዋል ነው – በሕዝብ መበለጡን አውቆ ራሱን “ሳያስፎግር” በቶሎ ይስተካከል – በተቃዋሚነት እያምቧተሩና በሕዝብ ስም እየቀለዱ(እየነገዱም) መኖር ከእንግዲህ የሚታሰብ አይመስለኝም፡፡ አንዳንዱ ተቃዋሚ ይህን ዓይነት ሕዝብ የሚቀድምበትን የአጣብቂኝ ወቅት የጠበቀ አይመስልም – ለዚህም ነው ተደናግጦና ፈዝዞ ጥግ ጥጉን ይዞ እንደማንኛውም ተራ ዜጋ የነገሮችን አነሳስና ጡዘት እየታዘበ የሚገኘው፡፡ በየተወሰነ ወቅት ይሰጥ የነበረው መግለጫና ፉከራ(ፉገራም ቢባል ያስኬዳል) እንግዲህ ለላንቲካው ነበር ማለት ነው፡፡ አዎ፣ ትዝብትንና ምን ይሉኝን ዕንወቅ፡፡ እንደካሮት ወደታች ሣይሆን እንደሸምበቆ ወደላይ እንደግ፡፡ የአእምሮ መካንነትን እንዋጋና ጤናማ ሰው እንሁን፡፡ ያኔ ሀገራችን ትነሣለች፡፡

… ብዙ ማሰብ፣ ብዙ መሥራት፣ መጥፎ ነገሮችን መርሳት፣ ደጋግ ነገሮች ማስታወስ፣ ፍቅርንና አንድነትን መዘከር፣ ቂምንና በቀልን እርግፍ አድርጎ መተው፣ ወንድማማችነትን መስበክ፣ ጎሠኝነትን መጠየፍ፣ ሰውኛነትን ማጉላት፣ ከሕዝብ መማር፣ በሌሎች ወንጀል ንጹሕን ሰው ከመጠየቅና በሌሎች ደግ ሥራና ምሥጉን ትውፊት ምንም ያልሠሩ ሰነፎችን ማወደስን መተው፣ … በቃ … ባጭሩ ጤናማ ኅሊና ያለው ሰው መሆን …. የሁሉንም ችግር እንደራስ ችግር መቁጠር፣ የሁሉንም የነፃነት ትግል እንደራስ ትግል አምኖ በጋራ መታገል፣ ያንደኛው መክሸፍ የሌላኛውም መክሸፍ መሆኑን ከልብ መገንዘብና የጋራ ኃላፊነትን መውሰድ … ከሌሎች ብዙ አለመጠበቅ፣ የራስንም ድርሻ መወጣት … በገንዘብም በጉልበትም በዕውቀትም በጊዜም … አቅም በቻለ ሁሉ ለዚህች የጋራ ሀገራችን መስዋዕትነትን መክፈል፣ ካለመስዋዕትነት ነፃነት እንደማይገኝ መረዳት…ነፃነት እንደቡና ቁርስ ከሙዳይ ተቆንጥራ የምትሰጥ የዳቦ ፍርፋሪ ወይም ጭብጥ ቆሎ ሣትሆን የደምና የአጥንት ግብር የምትጠይቅ መሆኗን አምኖ ለሚፈለገው ግዳጅ ሁሉ ራስን ማዘጋጀት …ገና ለገና ሥልጣን አገኝ ይሆናል በሚል ከመጠን በላይና ለትዝብት በሚዳርግ ሁኔታ በሥልጣን ሱስ/አራራ አለመስገብገብ … ከሁሉም በላይ በሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ማመን … ፡፡ ወቅቱ የክተት ነው፡፡ ዐጤ ምንሊክ ወደ ዐድዋ ሲዘምቱ በዘርና በጎሣ የተከፋፈለ የውጊያ ጥሪ አላደረጉም – ይህን ዓይነት ሸንካላ ወያኔያዊ አካሄድ አያውቁትምም ነበር፡፡ ባጠፋሁ ይቅርታ … በስሜት ስትናገሪ የምታስቀይሚው ሰው ይኖራል መቼም፡፡ … ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር፡፡ ለአሁኑ በቃኝ፡፡

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20172#sthash.DddewpJq.dpuf

አሜሪካ፡ “ህወሃት አብቅቶለታል”   የታቀደ፣ ግን ድንገተኛ የሚባል መፈንቅለ መንግሥት ይጠበቃል

በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

army-in-addis-e1472451071352-620x310በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ እንዲካሄድ የማይፈልጉት የአሜሪካ ባለስልጣናት ህወሃት አገር መምራት የማይችልበት ደረጃ ደርሷል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል። የሚያደርጉትን ቢያውቁም ለመፍትሄ በተናጠል ተቀናቃኝ ፓርቲዎችንና የሲቪክ ማህበራትን “ምክር” እየጠየቁ ነው። አሁን ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ በዚህ ከቀጠለ ኢትዮጵያን ላለማጣት ድንገተኛ የሚመስል ግን የታቀደ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሊደረግ እንደሚችልም ፍንጭ እየተሰጠ ነው።

የጎልጉል ታማኝ መረጃ ሰዎች እንዳሉት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) እንዳበቃለት የገመገሙት የአሜሪካ ባለስልጣናት “ከወዲሁ አንድ ነገር ማድረግ አለብን” የሚል አቋም ከያዙ ሰነባብተዋል። ለዚሁም መነሻቸው ህወሃት መልሶ እንዲያገግም ሊረዱት አለመቻላቸውና ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ የኢትዮጵያን መክሰር አለመፈለጋቸው ነው።

“ህወሃት አገር መምራት ካቃተው፣ ኢትዮጵያን ላለማጣት ምን ማድረግ አለብን” ከሚለው መሰረታዊ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዝንባሌያቸው በመነሳት አሜሪካኖቹ በየእርከኑ አገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪዎችን፣ ነፍጥ አንስተው ከሚታገሉ፣ በውጭ አገር ከሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ከሲቪክ ተቋማት ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው። ውይይቱ “ምን እናድርግ በሚል ምክር የመጠየቅ አይነት ነው” ሲሉ የመረጃው ባለቤቶች ያስረዳሉ። አሜሪካኖች የሚያድርጉትን እያወቁ ምክር የመጠየቃቸውን ጉዳይ የመረጃ ምንጮቹ ባያጣጥሉትም ምክር ተጠያቂዎቹ ተደራጅተውና ህብረት ፈጥረው ተጽዕኖ መፍጠር የሚችሉበትን ሁኔታ ሊያስቡበት እንደሚገባ ይመክራሉ።

(ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ እነ አባይ ጸሃዬ “አማራና ኦሮሞ ተባበሩብን፤ ሰግተናል” በሚል ርዕስ ጎልጉል በዘገበበት ዜና ላይ አሜሪካ ህወሃትን ለማዳን ጥገናዊ ለውጥ እንዲደረግ መፈለጓን፤ ለዚህም በተናጠል የተቃዋሚ ቡድኖችን እያናገረች መሆኗን ጠቅሰን ነበር)

kerry

በደም የተነከረውና ህዝባዊ ቁጣ የናጠውን ህወሃት አቅፋና ደግፋ ወደ ዙፋን ያመጣችው፣ በጀት ቆጥራ ስንዴ ሰፍራ እየደጎመች ዙፋኑን ያጠበቀችለት፣ ሲገድል ከበሮ የደለቀችለት፣ የሕዝብ ድምጽ ዘርፎ ራሱን ሲሾም “ዴሞክራሲያዊ” ያለችው፣ ከህዝባዊ ማዕበልና ከውስጥ መበላላት ያተረፈችው፣ የዛሬውንም ህዝባዊ ማዕበል በጥገና እንዲሻገር ስትደክምለት የኖረችው አሜሪካ አሁን ተስፋዋ እንደተመናመነ ለማወቅ ተችሏል። ይህንኑ ሃሳብ ለማጠናከር ሰሞኑን ኬንያ የተደረገውን የጸጥታ ጉዳይ ስብሰባ ለአብነት ያነሳሉ።

ባለፈው ረቡዕ ኬንያ የተደረገውና የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ኃላፊ ጆን ኬሪ የመሩት የጸጥታ ጉዳይና የጸረአሸባሪነት ስብሰባ ከአራት ወራት በፊት ሲታቀድ ለጉባኤው የተመረጠችው አገር ኢትዮጵያ ነበረች። ስብሰባው ህወሃት በደረሰበት ህዝባዊ አመጽ አማካይነት ወደ ኬንያ መዛወሩ ብቻ ሳይሆን ስለ አልሻባብና ቦኮ ሃራም ውይይት በተደረገበት ስብሰባ ላይ ኬሪ አንድም ጊዜ የኢትዮጵያን ስም አለማንሳታቸው በይፋ ታይቷል፡፡ “በዲፕሎማሲው ቋንቋ ይህ የሚያሳየው አሜሪካ ለህወሃት ጀርባዋን መስጠት መጀመሯን ነው” በማለት የምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ የሚናገሩ ያስረዳሉ። ሲያክሉም ኬሪ ይህ ሁሉ ደም በሚፈስበትና ህዝብ በጅምላ በሚታሰርበት አገር ተገኝተው ስለ ጸጥታ ጉዳይ ስብሰባ ማድረጋቸው አሜሪካንን የሚያሳፍር ከመሆን ባሻገር አለቃቸው ፕሬዚዳንት ኦባማ “ዴሞክራሲያዊት” ብለው ባሞገሷት አገር ላይ ስለ ህወሃት ደምአፍሳሽነት ከዓለምአቀፍ ጋዜጠኞች ጥያቄ ቢቀርብላቸው የአሜሪካንን ኪሣራ አምኖ ላለመቀበል የተቀነባበረ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ስለዚህም ስለ አልሻባብ እና ስለ ደቡብ ሱዳን ደኅንነት በተጠራው ስብሰባ ላይ “የሶማሊያ መሃንዲስ የአልሻባብ ባለገድል” እንዲሁም የደቡብ ሱዳን “አሸማጋይ” የሆነውን ህወሃት እንዳይገባ ተከልክሏል፡፡

መለስ በG-20 ስብሰባ

የምዕራብ ተላላኪ የነበሩት ሟቹ “ባለራዕይ” መለስ በአገር ውስጥ ያለው ግፍ እያሳጣቸው በመጣ ጊዜ ጌቶቻቸው ጀርባ ሰጥተዋቸው የዕራት ግብዣ ጠረጴዛ ላይ ሻማ ያዥ አሽከር መስለው የታዩበት ጊዜ የሚታወስ ነው፡፡

በ1983 የሎንዶን ድርድር ኢትዮጵያን በኸርማን ኮኽን አማካይነት ለህወሃት ያስረከበችው አሜሪካ “ህወሃት አብቅቶለታል” ከሚለው ድምዳሜ ላይ ባለችበት ባሁኑ ሰዓት የተቃዋሚው ኃይል በቶሎ አገር ወደማዳን አጀንዳ በኅብረት ተንቀሳቅሶ አንድ ደረጃ ላይ ካልደረሰ አሜሪካ ድንገተኛ የሚመስል ግን አስቀድሞ የታቀደ ወታደራዊ የመፈንቅለ መንግስት ልታካሂድ ትችላለች የሚል ግምት እንዳለ ለማወቅ ተችሏል። የዜናው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ አሜሪካ ይደረጋል ብላ የምትጠብቀው ኩዴታ “በድንገት የሚደረግና የማይታወቅ አይደለም” ሲሉ በየደረጃው ከተቀመጡት አማራጮች መካከል አንዱ ስለመሆኑ ፍንጭ ይሰጣሉ። ሲያብራሩም የቀድሞውን የህወሃት ታጋይ ጻድቃንን እና ሌሎች የቀድሞ የመከላከያ ኃላፊዎችን ከፊት ለፊት ያመጣሉ።

ሰሞኑን ጻድቃን ገ/ትንሣኤ ያቀረቡት “የመፍትሔ ሃሳብ” ውስጥ የመከላከያውና የደህንነቱ መዋቀር እንዳለ ቆይቶ ህገ መንግስቱን መሰረት ያደረገ የስርዓት ማሻሻያ ከማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሌለ የሚያሳስብ ነው። ዜናውን ያቀበሉት ክፍሎች ሲያከሉም “በዚህ እሳቤ ውስጥ ሆኖ መፈንቅለ መንግስቱን ማስላት አግባብ ነው” ባይ ናቸው። እናም አሜሪካ በግል የምታናግራቸውና የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሁሉ በቶሎ ግንዛቤያቸውን ሊያሰፉና የመፍትሄ ሃሳብ ሊያቀርቡ እንደሚገባቸው ያሳስባሉ።

ላለፉት 25 ዓመታት ታማኝ በሆናት ህወሃት አማካኝነት አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የወታደራዊና የደኅንነት መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሷ ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያን ላለማጣት የምትፈልገው ካላት ወታደራዊ ኢንቨስትመንትና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች አኳያ እንደሆነ በሰፊው ይታመናል፡፡

ከተያዙት የተለያዩ መፍትሔዎች መካከል መፈንቅለ መንግስት አማራጭ ከሆነ “ሥልጣን እስከ ሞት” በሚሉ ህወሃቶችና ተራው የእኛ ነው በሚሉ “ንሰሃ በገቡ የለውጥ አራማጅ” ህወሃቶች መካከል እርስ በእርስ መበላላት ሊኖር እንደሚችል ከግምት በላይ ስጋት አለ። መከላከያውና ደህንነቱ የሚመራው ባንድ አካባቢ ተወላጆች መሆኑ የአቋም ልዩነት ከተነሳና መከዳዳት ከተከሰተ መቀዳደም ሊኖር እንደሚችል የሚገመቱ አሉ። በሌላ በኩል ከስልጣናቸው በላይ ዋስትና አግኝተው ያላቸውን ሃብት ማስተዳደርና መኖር የሚፈልጉ ስለሚበዙ ጉዳዩ እጅግ ቀላል የመሸጋገሪያ መንገድ እንደሆነ የሚያስቡም አሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህዝባዊ ተቃውሞው ስልቱን እየቀያየረ ተጠናከሮ ቀጥሏል። ከየአካባቢው በምስል እየተደገፉ የሚወጡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ህዝብ እምቢተኛነቱን የሚገልጽበት መንገድ ኢኮኖሚውን እያመነዠገው ነው። ይህ በሆንበት ሁኔታ ህዝባዊ እምቢተኛነቱ ትምህርት ቤቶችና ከፍተኛ ተቋማት ሲከፈቱ ዋና ዋና ከተሞችን በሙሉ ያዳርሳል የሚል ፍርሃቻ ነግሷል።

በሌላ ዜና በአማራ ክልል የሚካሄደውን ህዝባዊ እምቢተኛነት አስመልከቶ መረጃ የሚሰጡ የፖለቲካ ድርጅቶች የመናበብና የመረጃ አሰጣጥ ስልት ችግር እንዳለባቸው ተሰምቷል። በብዛት አሜሪካ ራዲዮ የሚያናግራቸው እነዚህ ክፍሎች የሚሰጡትን መረጃ የማደራጀትና በየሰአቱ የማጎልበት ችግር ይስተዋልባቸዋል። እንደውም ጉዳዩን ወደ ህዝብ ወኪሎች ቢገፉት የተሻለ እንደሆነ የሚመከሩም አሉ። በቅንጅት ወቅት ሁሉም የተሳከረ መረጃ እየሰጡ የተፈጠረውን ችግር የሚያስታውሱ ክፍሎች መረጃ ተደራጀቶ የሚሰራጭበት አግባብ ሊፈለግ እንደሚገባ አበክረው ይመክራሉ። ሕዝባዊ ተቃውሞ አስቀድሞ ከጀመረው የኦሮሞ ተቃውሞ ጋር ኃይልን ማስተባበር እንደ አማራጭ ሊታይ ይገባዋል ሲሉ ሃሳብ ይሰጣሉ፡፡

ከበላይ አመራሩ በስተቀር አብዛኛው የብአዴን ካድሬ ከድቷል በሚባልበት ባሁኑ ወቅት “መንግሥት ፈርሷል” እየተባለ መነገሩና ሕዝቡ በጎበዝ አለቃ እየተመራ መምጣቱ ህወሃትን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ከቶታል፡፡ ሁሉም ድርጅቶች የተናጠል ስብሰባ አካሂደው በመጨረሻም የኢህአዴግን የሚያደርጉበት የተለመደ አሠራር ቀርቶ ህወሃት ብቻ ባደረገው ስብሰባ የኢህአዴግ ምክርቤት መግለጫ አውጥቷል፡፡ ይህም እንደ ኦህዴድ ብአዴንም የከዳና መተማመን በግምባሩ ውስጥ የመነመነ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን በቀጣይ ህወሃት በኦፊሴል ባያውጅም እንደ ኦሮሚያ የአማራን ክልልም በወታደራዊ አገዛዝ ሥር እንደሚያስተዳደር አመልካች ሆኗል፡፡

ይህ አካሄድ ለህወሃት የኅልውና ጉዳይ ስለሆነ የተከፈለው መስዋዕትነት ተከፍሎ “አገር በማዳን” ስም በበርካታ አካባቢዎች የከረረ ወታደራዊ እርምጃ ሊወስድ ይችላል የሚለው በስፋት የሚታመንበት ሆኗል፡፡ በአሜሪካ ድጋፍ ሲቪል መሰል ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከተከሰተም አገር ማረጋጋት በሚል ተመሳሳይ እርምጃ የማይወሰድበት ምክንያት እንደሌለ አስተያየት ይሰጣል፡፡ በመሆኑም “ህወሃት አብቅቶለታል” በሚባልበት በአሁኑ ሰዓት የተቃዋሚው ኃይል ሁሉን አቀፍ አንድ ወጥ ቻርተር ወይም አጀንዳ መቅረጹ በቶሎ ሊሰራበት የሚገባ እንደሆነ ጉዳዩ የሚያሳስባቸው አበክረው ይናገራሉ፡፡ (ቀዳሚ ፎቶ አጋዚ በአዲስ አበባ ፎቶ ምንጭ AP)


– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20182#sthash.26yRPxsm.dpuf

«AmOr!» «አሞር!» – የአምባገነኑን የህውሀት/ወያኔን ስርአት ውድቀት የሚያፋጥን የህዝብ ድምጽ ይሆን? (Could «AmOr» will be the final nail in the coffin of TPLF?)

ልዑልሰገድ ወልደየስ ሂርጳ

ወደ ዋናው ርዕሴ ከመግባቴ በፊት በቅድሚያ በወያኔ ጥይት በቅርቡ በግፍ ለረገፉት የአገራችን ጀግና ወጣቶች ጥልቅ የሆነ ሀዘኔን እየገለጽኩ፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው ፍትህ፤ ዲሞክራሲና ነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ እግዚአብሔር መጽናናቱን እንዲሰጠው ከልብ እመኛለሁ፡፡

ከዛሬ 18-19 ዓመት በፊት ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን (ነፍሳቸውን ይማረውና) በአንድ የአውሮፓ ዋና ከተማ ላይ በተደረገ ትልቅ ስብሰባ ላይ ተገኝተው የተናገሩትን ምንግዜም አስታውሰዋለሁ፡፡

በዚህ ስብሰባ ላይ ብዙ የኦሮሞ፤ የአማራ፤የትግራይና እንዲሁም የኤርትራ የፖለቲካና የታሪክ ምሁራን ተገኝተው ነበር፡፡ ያውም በዚያ ትልቅ አዳራሽ ውስጥ የመጀመርያውን ረድፍ የያዙት እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸው (በሚያሳዝን ሁኔታ እርስ በእርሳቸው እንኳ የአግዚአብሔር ሰላምታ የማይለዋወጡትን) የታሪክና የፖለቲካ ምሁራን እንደነበሩም አስታውሳለሁ፡፡ ወቅቱም ልክ እንዳሁኑ፤ ወይም ባልሳሳት አሁን ካለው ሁኔታ ባላነሰ «ሰይጣን የፈረደበት፤ ብዙ ዱላ የሚችለው» የብሔር፤ የዘር ጭቅጭቅና የማንነት ጥያቄ ተጋኖ የሚነገርበት፡፡ በተቃራኒው «ኢትዮጵያዊነት» ደግሞ ሳይሞት ተገንዞ የመቀበርያው ጉድጓድ እየተቆፈረ ባለበት ጊዜ ነበር፡፡

የሎሬት ፀጋዬ እንደዋና ተናጋሪነት በመጋበዛቸው፤ ህዝቡም ለእሳቸው ያለው አክብሮትና ፍቅር ከፍተኛ በመሆኑና እንዲሁም እኚህ ታላቅ አገር ወዳድ ምሁር ስለምን ይናገሩ ይሆን ብሎ በማሰብ ይመስለኛል በስብሰባው ላይ ብዙ ታዳሚ ከሩቅም ከቅርብም የተገኘው፡፡ ታድያ እኚህ ታላቅ አገር ወዳድ የስነጽሑፍ የቲያትርና የታሪክ ምሁር በስብሰባው አዳራሽ ውስጥ ገብተው የተመደበላቸውን መድረክ እንደያዙ ንግግራቸውን የጀመሩት እንዲህ በሚል አንድ ጥሩ ጥያቄ ነበር፡፡ «እዚህ አዳራሽ ውስጥ የአፋር ደም በጭራሽ የለብኝም የሚል እስቲ እጁን ያውጣ!»

ሎሬት ፀጋዬ እጁን የሚያወጣ ሰው ካለ ብለው በአዳራሹ ያለውን ታዳሚ ከዳር እስከዳር እየቃኙ ለጥቂት ደቂቃ ቆዩ፡፡ አዳራሹም አንድም ሰው የሌለበት በሚመስል ሁኔታ እርጭ ብሏል፡፡ ሁሉም እርስ በርሱ ይተያያል እንጂ ደፍሮ እጁን የሚያወጣ አልነበረም፡፡(እኔ እንኳን በመጀመርያው ረድፍ ላይ ከተቀመጡት፤ የታሪክና የፖለቲካ ምሁራን መካከል ቢያንስ አንድ ሁለቱ እጃቸውን አውጥተው ሎሬት ፀጋዬን ይሞግቷቸዋል፡ እኛም የተጧጧፈ ክርክርና ትምህርት እንቀስማለን ብዬ ገምቼ ነበር – ግን እንደዚያ አልሆነም፤ ምናልባት መልሱ አጣብቂኝ ውስጥ ስለሚያስገባና ብዙም ጥናትና ውይይት ስለሚያስፈልገውም ይሆናል ምሁራኖቹ ዝምታን የመረጡት! አላውቅም)፡፡

ሎሬት ፀጋዬ በአዳራሹ ከተሰበሰበው ምንም መልስ ሲያጡ፤ ፈገግ በማለት እና በመገረም እይታ «ታድያ እዚህ ያለነው ሁላችንም አፋሮች ነን ማለት ነዋ!» ሲሉ፤ ህዝቡም በአንድ ላይ ጸጥታውን በሳቅ ቀየረው፡፡

ሎሬት ፀጋዬ ከአንድ ሰዓት ላላነስ ጊዜ በኢትዮጵያዊነትና ግንዳችን/መነሻችን ከአንድ ምንጭ እንደሆነ ብዙ ምሳሌዎችን እና የታሪክ ማስረጃዎችን እያጣቀሱ አስተማሩን፡፡ ብዙዎቹ ሀሳቦች አብዛኛዎቻችን በመደበኛው ት/ቤት ያልተማርናቸው እንደነበሩም ትዝ ይለኛል፡፡

ስለ አገራችን የተለያዩ ቋንቋዎች ከአንድ ምንጭ መፍለቅ ሳይቀር ሲያስረዱ፤ በአሁኑ ጊዜ ዝምድና የሌላቸው የሚመስሉ ቋንቋዎች ሳይቀሩ ምንጫቸው አንድ እንደነበሩ በማስረዳት፤ እንደ ምሳሌም የኦሮምኛውንና የትግርኛውን የሰላምታ አሰጣጥ በማንሳት ምን ያህል መቀራረብ እንዳለ ተንትነው እንዳስረዱ ትዝ ይለኛል፡፡ በእሳቸውም አገላለጽ የኦሮምኛው «አካም» እና የትግርኛው «ከመኤላሀ» ምንጩ አንድ እንደሆነ ሲያስረዱ፡ በእነዚህ ሁለት ቃላቶች ውስጥ አንድ የሚያገናኛቸው የጋራ ቃል አለ፡ ይሀውም «ካም» የሚለው ቃል ሲሆን፤ ትርጉሙም በጥንት በፈርዖኖች ጊዜ «ፀሀይ» ማለት እንደነበረና፤ እንግዲህ ከመነሻው ትርጉሙ « መልካም ፀሀይ» «መልካም ቀን» ከዚያም ከጊዜ ብዛት «እንደምን ዋልክ» «እንደምነህ»፤«ሰላም» ወደሚለው እንደተለወጠ በመግለጽ፤ የአገራችንም ግዛት በወቅቱ እስከ ሜደትራንያን ይደርስ እንደነበር አብራርተዋል፡፡

ለማንኛውም የሳቸው ዋና መልዕክት – «መነሻችን አንድ ነው፤ አብረን እየወደቅን፤ አብረን እየተነሳን እዚህ ደርሰናል እና መከፋፈሉን ማንጸባረቅ ትተን የሚያገናኙን ነገሮች እጅግ ብዙ ስለሆኑ፤ በፍቅር በሰላም እየተሳሰብንና እየተከባበርን በአንድነት እንኑር» ነበር፡፡

የሎሬት ፀጋዬን ትምህርትና ምክር እዚህ ላይ ላብቃና፤ ታዲያ መነሻችን አንድ ሆኖ፡ ከምንለያይበት ነገሮች ይልቅ፤ የሚያገናኘንና የሚያስተሳስረን ነገሮች እጅግ በዝቶ እያለ ለምን በተለይ በብሔር ተከፋፍለን እንናቆራለን? ብዙዎቻችን ከሶስትና ከአራት ትውልድ በፊት የነበሩትን የቅድም አያቶቻችንን ስም እንኳን በቅጡ መጥራት የምንችል አይመስለኝም፡፡ በወንድ አያቶቻችንና ቅድመ አያቶቻችንን በኩል ያሉትን ስም መጥራት ብንችል እንኳን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ በእናቶቻችን በኩል ያለውን ስም መጥራት የምንችል ብዙም ያለን አይመስለኝም፡፡ (ባህላችን ያንን አለመደም ትሉኝ ይሆናል – እሺ እቀበለዋለሁ ግን ያ ያልተለመደ እና ያለማወቅ ከጀርባው ስንት ኮተት አንዳለበት ስለማናውቅ፤ የብሔር ጥላቻ እንዳይሰፍን ትልቅ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን)፡፡

ምን ያህሎቻችን ነን በእርግጠኛነት ከአምስትና ከስድስት ትውልድ በፊት በአያቶቻችን ዙሪያ ማን ከማን ጋር እንደተጋባ የምናውቀው? በዚያን ጊዜ የኖሩት ቅድመ አያቶቻችን የትኛዋን ሴት ለማግባት የማንን አጥር እንደዘለሉ ወይም እንዳልዘለሉ፤ የትኛውን ወንዝ እንደተሻገሩ ወይ እንዳልተሻገሩ ዛሬ እንዴት በእርግጠኝነት ማወቅ እንችላለን?

የሰው ልጅ ታሪክ የሚነግረን፤ ህዝቦች በተለያየ ምክንያቶች ሁልግዜ በእንቅስቃሴ ወይም በዝውውር ላይ መሆናቸውን ነው፡፡ የሰው ልጅ እኮ ከጥንስሱ ጀምሮ «የእንቅስቃሴ» ውጤት ነው፡፡ «እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል » እንዲሉ ህዝቦችም አንድ ቦታ ካልተመቻቸው ወደሚመቻቸው ሌላ ቦታ በመሄድ ይሰፍራሉ፤ አዲስ ከሰፈሩበትም ቦታ ካለው ህዝብ ጋር በመጋባት ይዋለዳሉ፤ የአገሩም/የአካባቢውም ሰዎች ሆነው ይቀራሉ፡፡ እንደዚህማ ባይሆን ኖሮ ዛሬ አሜሪካን የምትባል አገር ዛሬ እንደምናውቃት ባልኖረችም ነበር፡፡

ስለዚህ እኛም ስለ አገራችን ኢትዮጵያ እና በውስጧ ስለሚኖሩት የተለያዩ ብሔሮች ስናስብ፤ በሰላም፤ በፍቅርና፤ በመከባበር መኖር እንዳለብን ወይም እንደሌለብን፤ ለክርክር እንኳን መቅረብ ያለበት ጉዳይ አይመስለኝም፡፡

እኛ አሁን ያለነው በአንድ «ኢትዮጵያ» በምትባል መርከብ ላይ ተሳፍረን ካለ ምንም ካፕቴንና መሪ በአንድ ትልቅ ባህር ላይ እየተጓዝን ነው፡፡ መርከቧ ወዴት አቅጣጫ እየተጓዘች እንደሆነ አይታወቅም፤ ካፕቴንም የላትም ግን ትጓዛለች እና በመርከቧ ላይ ያለነው ተሳፋሪዎች በተለያየ ምክንያት ግሩፕ እየፈጠርን እርስ በርስ መጣላት ብንጀምር፤ ሳንወድ በግድ ከመርከቧ ላይ ወደ ባህሩ መወራወር እንጀምራለን ወይም ነገሮች በጣም ከባሱ ሁላችንም እንሰጥማለን፡፡ ስለዚህ ሁላችንም እንድንድንና መርከቧም አንድ ወደ አልታውቀ ወደብ እስክትደርስ ድረስ የግድ ተፋቅረን፤ በመከባበር መጓዝ ይኖርብናል፡፡

ጤነኛ ሀሳብ የሚያስብ ማንም ግለሰብ አብሮ በጋራ በመተሳሰብ መኖር እንዳለበት ያምናል፡፤ ይፈልጋልም፡፡ ሌላ የውጭ ግፊት ተቃራኒውን እንዲያደርግ ወይም እንዲያስብ ቢገፋፋው እንኳን የውስጥ ልቦናው ምንጊዜም የሚነግረው አብሮ ተፋቅሮ መኖር የተቀደስ፤ ጥሩና ተገቢም እንደሆነ ነው፡፡ እንደዚህማ ባይሆን ኖሮ ዛሬ የዓለም ህዝብ ቁጥር አሁን ካለው እጅግ በጣም ያንስ ነበር፡፡

በእርግጥ የሰው ልጅ በመሳሳት እና በገዢዎቹ በመታለል በግሩፕ/በብሔር ተለያይቶ ቢኖር ከሌላው ግሩፕ/ብሔር የሚያድግ፤ የሚከብርና የተሻለም ኑሮ የሚኖር ሊመስለው ይችላል፡፡ እንደዚያ ዓይነት ሁኔታ ቢፈጠር እንኳን ውጤቱ ዘለቄታ የለውም፤ በጣም ግዜያዊ ነው፡፡ (ብዙ ብሔሮች ባሉበት አገር አንድን ብሔር ወይም ክልል ብቻ ለይቶ ማልማት ቢቻልም ከሌላው ብሔር ጋር ሰላም እና ስምምነት ከሌለ የለማው ሁሉ በጥቂት ቀናት ሊፈርስ ይችላል)፡፡

ልቦናችን፤ ስብእናችን፤ ደማችን፤ ታሪካችን፤ ባህላችን፤ እምነታችን በብሔሮች እና በህዝቦች መካከል አብሮ በመከባበርና በመተሳሰብ መኖርን እየመረጠ፤ ታዲያ መናቆርን፤ ጥላቻንና ንቀትን ከሁሉም በላይ በህዝቦች መካከል የመፈራራት መንፈስ በአንድ አገር ውስጥ እንዲሰፍን የሚያደርገው ምንድን ነው? ማን ነው?

መልሱ አጭር ነው፡ ምንድን ነው ለሚለው «ከፋፍለህ ግዛ» የተባለ የገዢዎቻችን ፖሊሲ ሲሆን፤ ማን ነው ለሚለው ደግሞ መልሱ «አምባገነን ገዢዎች» ናቸው ነው፡፡

በዲሞክራሲ በሚተዳደሩ አገሮች፤ የስልጣን መሰረታቸው የህዝብ ድምጽ ስለሆነ በህዝቦች መካከል «እየከፋፈልን እንግዛ» የሚል ፖሊሲ የላቸውም፤ ሊኖራቸውም አይችልም፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ አገሮች ህዝባቸውን ከብዙሀኑ አደራን ተቀብለው በግልጽ ያስተዳድራሉ እንጂ «አይገዙም»፡፡

በጉልበት በሚገዙ አምባገነኖች ስር ያለች አገር ግን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ከጦር ኃይላቸው ባላነሰ ሁኔታ የሚተማመኑበት ስርአታቸውን ይዞ ካቆመው አንዱ ምሰሶ ነው ማለት ይቻላል፡፡

የወያኔንም ስርአት እና ስልጣን ከተሸከሙት ከአምስት ያልበለጡ ምሰሶዎች (the supporting/bearing wall)ውስጥ ይሄ የከፋፍለህ ግዛ ምሰሶ አንዱ ነው፡፡

ሌሎቹ ምሰሶዎች በአጭሩ፦

1)የጦር ኃይሉ፤ ደህንነቱና ካድሬዎቹ

2)ኤኮኖሚው-ያከማቸው የተዘረፈ ገንዘብ፤ ሀብት ንብረት የኢትዮጵያ መሬት በሙሉ

3)ድርጅቱን ከመነሻው የደገፉትና፤ አሁንም በመደገፍ ላይ ያሉ፡፡ ህልውናውን በማወቅ ወይም በመሳሳት ወይም በጥቅም ከራሳቸው ህልውና ጋር ያያያዙ ግለሰቦች፤ ህዝቦች እና የህብረተሰብ ክፍሎች፤ እንዲሁም ሆድ አደሩ

4)የአፍሪካ ቀንድ ሰላም መጥፋት እና እንደ አልሻባብ አይነት አሸባሪ መፈጠሩ በውጭ በተለይም በምዕራባውያን ዓይን የወያኔ እንደ «ዋስትና» መቆጠርም ስርአቱ በከፊልም ቢሆን የሚተማመንበት ሌላው ምሰሶ ይመስለኛል፡፡

አንድን ቤት ወይም ህንጻን ለማፍረስ የተሸከመውን ምሰሶ በግድ ማፍረስ እንደሚያስፈልገው ሁሉ፤ ስርአትንም ለማፍረስ የግድ ስርአቱን የተሸከሙትን ምሰሶዎች ማፍረስ ያስፈልጋል፡፡ የወያኔንም ምሰሶዎች ማፍረስ ካልተቻለ፤ የወያኔን ዕድሜ፤ ህዝብና ተቃዋሚዎች እንደሚመኙት ለማሳጠር አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

አንድን ነገር ለማፍረስ በቅድሚያ በቀላሉ መፍረስ ያለበትን ነገር ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከላይ የተገለጹትን ምሰሶዎች በአንዴ ማፍረስ ያስቸግራል፡፡ ግን አንዱን ምሰሶ ብቻ በማፍረስ ስርአቱን ማናጋት ይቻላል፡፡ የአንድ ምሰሶ መፍረስ ስርአቱን በግድ ወደ አንድ አቅጣጫ እንዲያዘነብል (ባላንሱን እንዲያጣ)ያስደርገዋል፡፡ የአንዱ ምሰሶ መፍረስ አጠገቡ ያለውን፤ በተለያየ መዋቅር የተሳሰረውን ምሰሶ ጫና ያሳድርበትና እሱም መናድ ይጀምራል፡፡ ከዚያ በኃላ የተቀሩት ምሰሶዎች መፍረስ ለተፈጥሮ ህግ ብቻ መተው ነው፡፡

ታድያ ዛሬ ህዝባችን በከፍተኛ የወያኔ ወከባና ግድያ ላይ እያለ በቀላሉ ሊያፈርሰው የሚችለው የትኛውን ምሰሶ ነው ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ ይሄ «የከፋፍለህ ግዛ» ምሰሶ ነው፡፡ ይሄ «የከፋፍለ ግዛ» ምሰሶ ልብ ብሎ ላጠናው ሰው፤ ከሌሎቹ ምሰሶዎች በተቃራኒ የወያኔ ስርአት ደካማ ጎን የሚጋለጥበት ነው፡፡ (the weakest link in the system) ይሄን ምሰሶ ከሌሎቹ ምሰሶዎች ጋር ስናወዳድረው፡

1)ምሰሶውን ያቆመው የውሸት ፕሮፖጋንዳና፤ ህዝቡ ዓይኑን ያለመክፈቱ መሆኑ፡

2)በቁሳዊ ንጥረ ነገር ያልታሰረ መሆኑ-ገዢዎች ከፋፍለው ለሚገዙት ህዝብ ሁሉ በገንዘብ መደለል አይቻልም፡፡ ለድለላውም የሚበቃ በቂ ገንዘብ አይኖርም፡፡

3)ምሰሶው ሙሉ በሙሉ በገዢዎቹ በወያኔ ቁጥጥር (ግቢ)ውስጥ አለመሆኑ፡

ይህና ሌሎችም ሁኔታዎች ተደማምረውና ህዝቡም ጥሩ አንቀሳቃሽ እና አስተባባሪ ከተገኘ፤ ምሰሶዎን ለማፍረስ በሚቀየሰው ስትራተጂ ላይ ጥሩ የተለያየ ታክቲክ የሚነድፍ ግብር ኃይል በመፍጠር ከታሰበው ግብ ለመድረስ የሚቻል ይመስለኛል፡፡

ሁሉም አገር ወዳድ! የኢትዮጵያን ወደ ጨለማ ጉዞ እና ወደ እርስ በርስ ግጭት ለማስቆም የሚያስብ ሁሉ የበሰለ ሀሳቡን በጨዋነት የሚለግስበትና እና ገዢዎችን በቃችሁ የሚልበት የርብርቦሽ ጊዜው እሁንና አሁን ብቻ ነው፡፡

ዋናው ትግል በሰላም እና ለሰላም መሆን እንዳለበት እንደ መሰረታዊ ሀሳብ መወሰድ ያለበት ይመስለኛል፡፡ ግቡም የገዢውን ክፍል፤ ወያኔን ካለምንም ቅድመ ሁኔታ በክብ ጠረጴዛ ዙርያ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ ማስደረግ መሆን አለበት፡፡ ህዝብ ጠላቱን ካላወቀ ወዳጁንም አያውቅም፡፡ የኢትዮጵያ ጠላቶች ገዢዎቹ ወያኔዎች እናወያኔዎች ብቻ ናቸው አራት ነጥብ፡፡

እነሱ የመጡበት ብሔር እነሱ ላመጡት ጣጣ ሰለባ መሆኑ እጅግ በጣም ስለሚያሳዝን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ጊዜም ወያኔንና የመጡበትን ብሔር ለይቶ ማየት አለበት፡፡ በሁለት በኩል አጣብቂኝ ውስጥ የገባውን ብሔር የሞራልና የትብብር ድጋፍ ከምንጊዜውም በበለጠ ሁኔታ በመለገስ የኢትዮጵያን ትልቅ ጨዋነት፤ ባህል፤ ታሪክ እና እምነት ምን ያህል ስር የሰደደና ከዘር ዘር ተላልፎ የመጣ መሆኑን ለዓለም ህዝብ ሁሉ ማስመስከር ያስፈልጋል፡፡

ሰዎች! ዛሬ የሚፃፈውን ብቻ ሳይሆን ነገም ምን ተብሎ ሊፃፍ ነው ብላችሁ አስቡ፡፡ ነገን የሚጽፉት ልጆቻችን ናቸው ግን ምን ብለው መጻፍ እንዳለባቸው የምንወስነው እኛ ነን፡፡

እንግዲህ በእኔ በኩል ያሰብኩትን እና በርዕሴ ላይ የገለጽኩትን፤ ለድል ሊያደርስ ይችል ይሆናል ያልኩትን «የህዝብ ድምጽ» ላካፍላችሁ፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው አንድን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ግቡን እንዲመታ ወይም ቢያንስ እንዲያፋጥነው ከሚያስፈልጉት ዋና ዋና ነገሮች አንዱ በአንድ ድምጽ የሚጮህ «slogan» ወይም «የህዝብ ድምጽ» ነው፡፡

ድምጹ ጠንካራ መልዕክት ያዘለና ገዢው ክፍል በጭራሽ መስማት የማይፈልገው፤ ቃሉን ለመያዝ ቀለል ያለ፤ በወረቀትም ለመበተንም ሆነ በግድግዳ ለመጻፍ የቀለለ፤ በሶሻል ሜዲያ በቀላሉ የሚሰራጭ፤ የውስጥም ሆነ የውጭ (ጉዳዩ የማያገባው እንኳን ቢሆን -ለምሳሌ የውጭ ጋዜጠኛ በቀላሉ ሊረዳው እና ለአዳማጮቹ በቀላሉ ማስረዳት የሚችለው)፤ መልዕክቱ ሰምና ወርቅ የያዘ እና በብዙ መንገድ የሚተረጎም፤ ሰላማዊ እና የስምምነትን መልዕክት ያዘለና ብዙሀኑን ህዝብ ያካተተ ቢሆን ይመረጣል፡፡

የሶቭዬት ህብረትንና የምስራቅ አውሮፓን የኮሚንስት ጨቋኝ ስርአት ከነ ስሩ ነቅሎ የጣለው በ80 ዎቹ ላይ በፖላንድ የተነሳው «ሶሊዳርኖሽች» የሚል የህዝብ ድምጽ ነበር፡፡

«ሶሊዳርኖሽች» ማለት «ትብብር» ወይም « solidarity» ማለት ሲሆን፤ በእርግጥ «ሶሊዳርኖሽች» ክመነሻው እዚህ ግባ የማይባል በህቡዕ የተደራጀ፤ በአንድ እስክ ስምንተኛ ክፍል ደረጃ ድረስ የተማረ ኢሌክትሪሽያን የሚመራው፤ የነጻ የሰራተኛ ማህበር ነበረ፡፡ በኋላ ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች፡ ከሰራተኛው፤ከገበሬው፤ ወጣት፤ሽማግሌው፤ወንዱ ሴቱ ሁሉም በአንድ ድምጽ ወጥቶ «ሶሊዳርኖሽች» እያለ እየጮሀ «ነፃነቱን»፤«የዲሞክራሲ መብቱን» «በነጻ የመምረጥና የመደራጀት መብቱን» መጠየቅ ጀመረ፡፡ በዚህ ይህን ከባድ መልዕክት በያዘ «አንድ ቃል»፡ አገዛዙ ተሽመድምዶ ወደቀ፡፡ህዝቡም አሸነፈ!

እንዲህ አይነት ኃይለኛ መልዕክት ያለው ቃል በታሪክ ብዙ ቦታ ተስተውሏል፡፡ የፕሬዚዳንት ኦባማም «Yes we can» ን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል፡፡ የሚገርመው ነገር ቢኖር አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ቃላቶች ህዝቡን ለማሰባስብና በአንድ ድምጽ ለመጮህ የሚረዱትን ያህል ከስሜት ባለፈ ትክክልኛ ትርጉማቸውን እንኳን ሁሉም ህዝብ በቅጡ አለማወቁ ነው፡፡ (አንድ የሪፓብሊካን ፓርቲ ደጋፊ የነበረ የአሜሪካን አምባሳደር፤ ፕሬዚዳንት ኦባማ ከመመረጣቸው በፊት ማን እንደሚመረጥ፤ በአንድ ለአውሮፓ ለሚገኝ ጋዜጠኛ ቃለ መጠይቅ ሲሰጥ «አይ አሁንማ ሁሉም ነገር yes we can ሆኗል፤ ባይገርምህ አሜሪካን የምትኖረውን ፤የአምስት ዓመት ዕድሜ ያላትን ልጄን ከስራ ከተመደብኩበት አገር ሆኜ ሁልጊዜ ስልክ እየደወልኩ አናግራት ነበር፡፡ አሁን በመጨረሻው የስልክ ንግግራችን ላይ፤ ስልኩን ከመዝጋቷ በፊት ፡ Daddy! Yes we can! ብላ ስልኩን ዘጋችው» «ይታይህ Yes we can እና «የፕሬዚዳንት Obama መመረጥ እኔን ከስራ እንደሚያሰናብተኝ እንኳን አልተረዳችውም ነበር» ብሎ ሲናገር ሰምቼ ነበር)፡፡

ለእኛ ኢትዮጵያውያኖችስ፤ አሁን ተቀጣጥሎ ያለውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ እና የአንድነት ፍቅር ለመርዳት ምን አይነት «ሶሊዳርኖሽች» ወይም «Yes we can» ያስፈልግናል?

እኛ መጠቀም ያለብን «AmOr» የሚለውን የፍቅርና የኃይል ቃል መሆን አለበት እላለሁ፡፡ «AmOr» -አሞር ምን ማለት ነው? AmOr በጣም የቆየ የጥንት ቃል ሲሆን፤ ትርጉሙም «ፍቅር» ማለት ነው፡፡ (ቃሉ የመጣው ከግሪክ እንዲሁም ከላቲን የፍቅር አማልክት ከሚለው ሲሆን)፤ሀይማኖታዊ ትርጉሙ ደግሞ «መተላለፊያ» «ኮሪዶር» «Passage» እንደ ማለትም ይሆናል፡፡

ወደ እኛው አገር ደግሞ ስንመጣ የእንግሊዘኛ ቃላቱን ልብ ካላችሁት፤ «Amhara» አማራ ከሚለው የመጀመሪያውን ሁለት ፊደላት «Am» የሚለውን ወስዶ «Oromo» ከሚለውም እንዲሁ ሁለት ፊደላትን «Or» የሚለውን በመውሰድ አምላክ ሳይታሰብ ለአገራችን የገነባው ቃል ነው፡፡

«AmOr»! – አሞር በዚህ አተረጓጎም፤የአማራውና የኦሮሞው ፍቅር ማለት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔው «ከፋፍለህ ግዛ» በሽታ የሚድንበት መድሀኒት እና ለወያኔ ደግሞ የመሞቻው «መርዝ» ነው፡፡

«AmOr» – አሞር በሀይማኖት መጽሀፍ ደግሞ «መተላለፊያ» ነው ብዬአለሁ፤ ያም ማለት ለአገራችን ከጭቆና እና ከአምባገነን የጉልበተኛ አገዛዝ ወደ ዲሞክራሲ እና የግለስብ ነጻነት ወደሚረጋገጥበት የህዝብ አስተዳደር የምንሸጋገርበት የመተላለፊያ ኮሪዶር ማለት ነው፡፡

ቃሉ ኦሮሞና አማራን ብቻ ነው የሚወክለው ልትሉ ትችላላችህ፡፡ ግን ዋናው ትርጉሙ «ፍቅር» ማለት መሆኑን አትዘንጉ – ፍቅር በሁሉም ብሔሮችና ህዝቦች መካክል፡፡ ሌላው ደግሞ ሁለቱን ትልልቅ የኢትዮጵያ ብሔሮች መወከሉ፤ በእነሱ መካክል ያለው ፍቅር በአገሪቷ ውስጥ ለዘላቂው ለምንመኘውም ባላንሱን የጠበቀ ሰላም ይረዳል፡፡ (በአሜሪካና በረሽያ መካከል ፍቅር ከሰፈነ በመላው ዓለም ሰላም ይሰፍናል እንደማለት እንደሆነው)

የኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው በእነዚህ ሁለት ትልልቅ ብሔሮች መካከል ፍቅር፤ መተማመን፤ መረዳዳት እና የኃላፊነት ስሜት ሲሰፍን ነው፡፡

የኢትዮጵያ ጠላቶችና ጨቋኝ ገዢዎች ይህንን ጉዳይ ከህዝቡ የበለጠ ስለሚያውቁት በተለይ በእነዚህ ብሔሮች መካከል አለመስማማት እንዲሰፍን ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ፤ እያደረጉም ነው ያሉት፤ ይሄ ደግሞ ያደባባይ ሚስጥር ነው(በኦሮሞና በአማራ ህዝቦች መካከል በቅርቡ የተፈጠረው የትግል ህብረትን አስመልክቶ «ይሄ የኛን ድክመትና የቤት ሥራችንን አለመስራታችንን ነው የሚያሳየው» በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ቃል አቀባይ በንዴትና በቁጭት ሲዘባርቅ ተደምጧል)፡፡

እንግዲህ ሁሉም አገር ወዳድ AmOr! AmOr! AmOr! የሚለውን ቃል በየአደባባዩ ማሰማት ሲጀምር፤ የወያኔ ጠንካራ ምሰሶ የሚመስለው ቀስ በቀስ መፍረስ ይጀምራል! ያኔውኑ ሌላኛው ምሰሶ (ከአሜሪካንና ከአውሮፓ የሚመጣው የገንዘብም ሆነ የዲፕሎማሲያዊው እርዳታ)መንገዳገድና መፍረስ ይጀምራል፡፡

በመጨረሻም ለመግለጽ የምፈልገው፤ ይህ AmOr «አሞር» የሚለው ቃል የማንንም የፖለቲካ ድርጅት እንደማይወክልና፤ እኔም እንደ አንድ አገር ወዳድ፤ የወንድሞቼና የእህቶቼ ያላግባብ ደም መፍሰስ ካንገበገቡኝ አንዱ በመሆኔ፤ ቃሉን በቅርቡ በግፍ፤ ለመብትና ለነፃነታቸው ሲሉ በወያኔ ጥይት ለረገፉት ጀግና የኦሮሞና የአማራ ወጣቶች መታሰቢያ ይሁናቸው፡፡

ለሁሉም ጊዜ አለው [ማስተዋል በለጠ]

sunset-senggigiበመላዋ ሀገራችን ለነፃነታችን እየተዋደቁ የሚገኙ ዜጎች ውድ ሕይወታቸውን እየሰው የነፃነት ቀንዲሉን በማብራት ላይ ናቸው፡፡ ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ታላቅ መስዋዕትነት እየከፈሉ በመሆናቸው በአልሞ ተኳሽ የወያኔ አጋዚ ጦር አንገታቸው እየተቀላና ጭንቅላታቸው እየተገመሰ ሕይወታቸውን የሚያጡ ውድ ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ፈጣሪ ይማርልን፡፡

በዚያን ሰሞን ካነበብኳቸው መጣጥፎች አንዱ በ16 የትግራይ ተወላጆች የተጻፈው በወያኔ ላይ የተወሰደ አቋም ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ትባርካቸው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን አንድ ወቅት ጥሩ ኢትዮጵያውያን ተጋሩን(ትግሬዎችን) መቁጠር ጀምረው የቀኝ እጅ ጣቶቻቸውን ተጠቅመው (ይመስለኛል) አንድ ሁለት ሦስት ያህል እንደተጓዙ አምስትን እንኳን መዝለል አቃታቸውና “አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ባለኝ” ብለው ተስፋ በመቁረጥ መቁጠሩን እንደተውት አርድተውናል፡፡ አሁን 16 መድረሳቸው ተስፋን የሚያጭር ነው፡፡ እየበዙ እንደሚሄዱ ደግሞ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ዕድሉን ስላላገኙት እንጂ በቁም ነገር ከተጫወትን ኢትዮጵያውያን ተጋሩ ቁጥራቸው ከዚህ እንደሚበልጥ መገመት አይከብድም፡፡ አገዛዙ ከትግሬ አይውጣ እንጂ ወያኔ ሥልጣን ቢለቅ የሚወዱ ትግሬዎች ደግሞ ጥቂት እንደማይሆኑ መገመት ይቻላል፤ ይህን ወያኔ የተከለብንን የዘር መዘዝ ለማጥፋት ማርከሻውን በቶሎ ካላፈላለግንና በ“ሜሪቶክራሲ”(በችሎታና ዕውቀት) መተካት ካልቻልን ገና ወደፊትም ብዙ እንዳክራለን፡፡

በመሠረቱ ከኢትዮጵያዊነት በወረደ ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው ጎሣ እየተባባሉ ማናቸውንም ዓይነት ተቃውሞን መግለጹ ዘመናዊነትን ሊገልጽና የሥልጡን ፖለቲካ መታወቂያ ሊሆን እንደማይገባው አምናለሁ፤ በሃይማኖትና በአካባቢ ልጅነት መደራጀትም እንደዚሁ ተገቢ አለመሆኑ ይገባኛል፡፡ ቢሆንም ቅሉ … ከዐማራ ተወላጆች፣ ከኦሮሞ ተወላጆች፣ ከትግራይ ተወላጆች … የምንለው ነገር ለጊዜው ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ ማለትም እየወረደብን ያለውን የመከራ ዶፍ ከመመከት አኳያ አንዳች ፋይዳ ካለው ቢያንስ በመርኅ ደረጃ ብደግፈው ብዙም አይከፋኝም፡፡ እናም አብላጫውን ደሜን ያገኘሁት ከሦስቱም ‹በጥባጭ‹ ዘውጎች መሆኑን ከሕይወት ተሞክሮ የተረዳሁት ማስተዋል በለጠ በዚህ መጣጥፍ ውስጥ ያለውን አስተያየት በቀናነት የምሰነዝረው አድማጭ አገኛለሁ ከሚል ትልቅ ተስፋ ነው፡፡

ታሪኬን ብዙዎች ይጋሩት ይናል ብዬ ስለማምን ስለራሴ ትንሽ ብናገር ደስ ይለኛል፡፡ መነሻየ ግምት እንጂ ጥናት አይደለም፡፡ የብዙ ጥናቶች መሠረት ለእውነት የቀረቡ ግምቶች መሆናቸውንም አንዘንጋ፡፡ እናም የእኔ ዘውጋዊ ቀመር እንደሚመስለኝ 30% ዐማራ፣ 30% ኦሮሞ፣ 30% ትግሬ እና 10% ከሌሎች ነው፤ እንዲህ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ እንደዚህ ስል ደግሞ የሚያምነኝ እንደማላገኝ ብቻ ሣይሆን ጥቂት የማይባሉ ሰዎች እንደሚያላግጡብኝም ይገባኛል፡፡ የእኔ እውነት መነሻ ግን ይሄውላችሁ፡፡

መልኬን አሁን ላሳያችሁ ባለመቻሌ አዝናለሁ፡፡ ትግሬ ጋ ስሆን ፊቴን ያዩና “ደምህ ወደደቡብና ወደ ኦሮሞ ይሄዳል” ይሉኛል፡፡ ኦሮሞ ጋ ስሆን “መልክህ የዐማራና የትግሬ ይመስላል” ይሉኛል፡፡ ዐማሮች ጋ ስሆን “አባትህ ከደቡብ የተቀጠሩ ወታደር ሳይኑ አይቀሩም” እያሉ ይቀልዱብኛል፡፡ እኔ ራሴን በመስተዋት ስመለከት አንዱንም የማልመስል ከሁሉም ግን ጥቂት ጥቂት እንደወሰድኩ ያህል ይሰማኛል፡፡ ትልቁ ማስረጃየ ግን ሦስቱም ዘውጎች ከየተነሱበት መጥተው የሚያልቁበት ቦታ ላይ መወለዴ ነው፡፡ አዎ፣ የአማራ፣ የትግሬና የኦሮሞ ጠቅላይ ግዛቶች የሚጫፈሩበት(overlap የሚያደርጉበት) ሥፍራ ላይ ነው የትውልድ መንደሬ፡፡ ለዚህም ነው ቁርጥ ባለ ሁኔታ ይህን ወይ ያን ልመስል ያልቻልኩት፡፡

ስለዚህ አንዱ በዐማራነቴ አህያ ቢለኝ ወይም ዛሬ ጧት በፕሮፌሰር አልማርያም መጣጥፍ ላይ እንዳነበብኩት “የአእምሮ ዘገምተኛ” ቢለኝ ወይም በኦሮሞነቴ “ሽብርተኛ”ና “ወንጀለኛ” ብባል ወይም በትግሬነቴ ዘረኛና ጎጠኛ ብባል ብዙም የሚሰማኝ አልሆንም፡፡ ሁሉን መሆን አንዳንዴ ዕዳ አንዳንዴ ደግሞ በረከትም ነው፡፡ የሆንኩትን እንድሆን የመምረጥ ዕድል ያልተሰጠኝ መሆኔ ግን በከንቱዎች ከንቱ አባባል እንዳልቆጣ ትልቅ የትግስት ጋሻ አስጨብጦኛል፡፡ ለመሆንና ላለመሆን ምርጫ ባልተሰጠኝ ሁኔታ በሆንኩት ነገር መበሳጨትም ሆነ ከሰው ጋር ትርፍ ንግግር ውስጥ መግባት ትልቅ ሞኝነት ነው፡፡

ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ ሰሞኑን በጻፈው መጽሐፍ የትውልድ አካባቢየና ተፈጥሮ ቀድመው ያቆራኙትን ዐማራነቴንና ኦሮሞነቴን በተመለከተ ብዙ ነገር አትቷል፡፡ የፕሮፌሰሩ ልፋትና ድካም ይገባኛል፤ በሕዝቡና በሀገሩ ሰላምንና ፍቅርን፣ ወንድማማችነትንና እትማማችነትን ለማስፈን በመፈለጉ ብዙ ርቀቶችን ተጉዞ በእምቅድመ ዘመነ ታሪክ በአዳምና ሔዋን አንድ የሆንነውን ግን የዘነጋነውን እኛን አንድ አድርጓል፡፡

በመሠረቱ ታዲያ ጥቁሮች ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሣይሆን የሰውን ዘር በሞላ በሥነ ፍጥረት አንድ ያደረገ ፈጣሪ ከአዳምና ከሔዋን አንስቶ አሁን የምንገኝበትን የሰባት ቢሊዮን የሕዝብ ቁጥር ለበረከትም ይሁን ለእርግማን እንደሰጠን ለምናምን ሰዎች የሰውን ልጅ አንድነትና የዘር ሐረግ ወጥነት ለመረዳት አንዳችም ምርምር ባላስፈለገን ነበር፡፡ ይሄ አንድ የመሆን ወይም ያለመሆን ችግር አይደለምና ዋናው እየበጠበጠን የሚገኝ ችግራችን፡፡

(እንደኔ አስተሳሰብ) የሰው ልጅ ዋና ችግር የዘር ሐረጉ መለያየት አይደለም፡፡ ትልቁ ችግር የተፈጥሮ ሀብትን በአግባቡ ከመከፋፈል አንጻር የሚታየው ኢ-ፍትሃዊነት ነው፡፡ ምክንያቶቹ የፈለገውን ያህል በቅርጽ ቢለያዩም ዋናው ችግራችን የሀብት ክፍፍል ላይ የሚፈጠር የ“ያንተ በዛ፣ የኔ አነሰ” ዓይነት መፎካከርና ያን ተከትሎ የሚፈጠር ቀውስ ነው፡፡ አንዱ በጉልበቱ ወይም በብልጠቱ ቢሊዮን ሲወስድ ሌላው መቶም አያገኝም፡፡ አንዱ ያለ የሌለ ዘዴና ብልኃቱን ተጠቅሞ ወደሀብትና ሥልጣን ማማ በአቋራጭ በመውጣት እንደካሙዙ ባንዳ ዕድሜ ልኩን ሲጎለት ይህን ቅጥፈት የታዘበ ሌላው ባለወር ተራ ደግሞ ወደዚያ ሥፍራ ለመጓዝ የንጹሓንን ደም እየገበረ ሌት ከቀን በእውኑም በህልሙም ይባዝናል፡፡ እንጂ የመለስ ዜናዊ የ17 ዓመታት ጉዞና የቢሊዮን ዶላሮች ክምችት ለእንደርታው ገበሬ ለአቶ ሐጎስ ፀጋዝኣብ የፈየደለት አንድም ነገር እንደሌለ ቢያንስ ኅሊናችን ይረዳዋል – ይህን የምለው ታዲያ አጠቃላዩን እውነታ ለመግለጽ እንጂ የመለስ ሸፋፋና ወልጋዳ አስተሳሰብና አመራር ጥቂት የማይባሉ ተጋሩ ወንድምና እህቶቼን አልጠቀመም እያልኩ አይደለም፡፡ የተጠቀመ ተጠቅሟል፤ የተጎዳም እንዲሁ፡፡

ሁላችን እናውቀዋለን፤ የሰው ልጅ ዘር አንድ ነው፡፡ ነጭና ጥቁር የመጣው ከጊዜ በኋላ እንደሆነ መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ የመልክና የቁመት ልዩነት እንደሆነ በማኅበረሰብ ደረጃ ይቅርና በኔ ቤትም ጎልቶ የሚታይ ግን ተዓምራዊ ያልሆነ ተራ ክስተት ነው፡፡ በኔ ቤት ለምሣሌ እኔ ወደጥቁርነት የማደላ ፉንጋ የቀይ ዳማ ስሆን አንዱ ልጄ ቆንጆ ቀይ፣ አንዱ ደግሞ ከኔ የባሰ አሻሮ ናቸው፤ ሌሎቹም እንዲሁ የተለያዬ መልክ፣ ቁመትና ጠባይ አላቸው – “ቤቴ መንገድ ዳር አለመሆኑን”ና ታማኝ የትዳር አጋር ያለኝ መሆኔን አስቡልኝ ታዲያ! (በነገራችን ላይ አንዳንድ ሸረኛ አንባቢ ምን ሊለኝ እንደሚችል እያሰብኩ ነው ከመንገድ እየወጣሁ ደረጃውን ባልጠበቀ የመነቸከ ቀልድ ላስፈግጋችሁ የምሞክረው)፡፡ እነዚህን ልዩነቶች እኔና እናታቸው አልሰጠናቸውም – ባልሰጠናቸው ልዩነት ደግሞ አይጣሉም፡፡ ስለዚህ ልዩነትን ለጠብ ማዋል የከይሲዎች ተግባር እንጂ የደግ ሰው ጠባይ አይደለምና መጠንቀቁ ጠቃሚ ነው፡፡

ይህን የልዩነት ሰበዝ በኦሮሞነትና በዐማራነት ካየነው እርግጥ ነው “ይህ ሰው ኦሮሞ ነው”፣ “ይህ ሰው ጉራጌ ነው” የምንልባቸው ልማዳዊ የሰውነት ቅርፆች ሊኖሩ እንደሚችሉ በበኩሌ እረዳለሁ፡፡ ለዚህም ነው ከፍ ሲል የኔ የሰውነት ቅርጽና የመልክ ይዘት የዚህ ወይ የዚያ ሣይሆን ድብልቅ ነው ለማለት የደፈርኩት – ለፖለቲካ ፍጆታ አይደለም፡፡ To my belief, there are some typically subtle features of ethnics if they are not mixed up and diluted through intermarriage. And, in most cases, the Ethiopian societies are said to be interwoven to the extent of not being able to be clearly and unmistakably identified as this or that ethnic group, excepting some incidents especially in remotest rural areas where there is less chance of intermingling through intermarriage.

እውነት እንነጋገር ካልን ታዲያ ከሥነ ልሣናዊ ተቀራራቢነትም ይሁን ከአካላዊ ቅርጽ አኳያ አንድ ትግሬና አንድ ዐማራ የሚለዩበትን ገጽታ(feature) ለመለየት በበኩሌ እቸገራለሁ – ተፈጥሯዊ ዝምድናቸው በጣም ያቀራርባቸዋል፡፡ ይህንን ስል ፕሮፌሰር ፍቅሬ ያለውን የኦሮሞና የአማራ ጎሣዎች የመባቀያ ተመሳሳይነት ጨብጬ ይህን እኔ የምለውንም በተጨማሪነት ለማስገንዘብ ፈልጌ እንደሆነ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ዐማራና ኦሮሞ አንድ መሆናቸው የሚያስደስተኝን ያህል ትግሬና ዐማራም አንድ ብቻ ሣይሆኑ እንደኔ እንዲያውም ሁለቱ ጎሣዎች ወያኔን ተመስሎ ከፋፋይ ሰይጣን በመካከላቸው ገብቶባቸው እንጂ በልይት ዘውግነት መለያየት ራሱ ይበዛባቸዋል ባይ ነኝ – በአንድ ዘውግ ሥር መመደብ ነበረባቸው እያልኩ ነው በግልጽ ዐማርኛ፡፡ የአሁኑን ባላውቅም በኔ የወጣትነት ዘመን አንድን ትግሬ ከአንድ ዐማራ ለመለየት ምናልባት በትግሬው ግምባር ላይ ይቺ 11 ቁጥር የምንላት ታርጋ ኖራ በሷ ካልለየነው በስተቀር በምንም መንገድ አይለዩም ነበር – በነገራችን ላይ የሌላቸውም አሉ (ባይገርማችሁ ባለ 11 ቁጥር ዐማራ አለ፤ 11 ቁጥር የሌለው ትግሬም አለ)፡፡ ወያኔ እንደጣዖት የሚያመልክባትን የብሶተኞች የምትመስል 11 ቁጥርን በድንበር አካባቢ ያለን ሰዎችም አለችን፡፡ ለዐይን ህመም ተብሎ ብዙዎቻችን እንቀነደብ እንደነበር የኔም ግምባር ኅያው ምሥክር ነው፡፡ በኔ አካባቢ የባህሎች መዋሃድ ስላለ የብዙ ማኅበረሰቦች አሻራ በሁሉም ሰው ላይ ይታያል፡፡

በተረፈ ግን ዱሮ ትግሬን ከዐማራ ለመለየት የሚቻልበት ዘዴ አልነበረም፡፡ መልክና ቁመናቸው፣ ሥነ ልቦናዊ ቀመራቸው፣ ሥነ ልሣናዊ ዳራቸው፣ ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸው፣ አመጋገባቸውና አለባበሳቸው፣ እንግዳ አቀባበላቸው፣ ሰውን አክባሪነታቸው፣ ባህላቸውና ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸው ሲታይ አንዳቸውን ከሌላኛቸው መለየት የማይቻልበት ሁኔታና ወቅት ነበር – የዛሬውን ዘመነ ጥልሚያኮስ አያድርገውና፡፡ ለምሣሌ ሁለት ኦሮሞዎች እዚህ አጠገቤ እያወሩ ነው ልበል፡፡ በዚህኛው ሌላኛው አጠገቤ ደግሞ ሁለት ትግሬዎች እያወሩ ነው ልበል፡፡ አንድ ኦሮምኛም ትግርኛም የማይችል በዐማራነት የሚታወቅ ሰው ቢያዳምጥና ከየትኛዎቹ ምን እንደተረዳ/እንደሰማ ይህ ቢጠየቅ በርግጠኝነት ከትግርኛ ተናጋሪዎቹ በአነስተኛ ግምት ወደ 25 በመቶ የሚጠጋውን ሊረዳ ሲችል ከኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግን 5 በመቶውን እንኳን ስለመረዳቱ እጠራጠራለሁ፡፡ ታዲያ ይህን የትግሬ-ወያኔዎችን በዐማሮች ላይ መጨከን ምን አመጣው? ይህ ይመስኛለል ትልቁ የዘመናችን ዕንቆቅልሽ፡፡ ፍቺ ያጣንለት ሚሌኒየማዊ ጥያቄ ነው፡፡ ምን ዓይነት ሰይጣን በወንድማማቾች መካከል ገባ? በውነቱ በተለይ በተጋሩ ወንድሞቼ አካባቢ ይህን የምለውን እውነት የሚያስታውስ ጠፍቶ ነው ወይንስ ማስታወስ አስፈላጊ ሣይሆን ቀርቶ ይሆን? ለምን? ማንን ለመጥቀም? እነዚህን ወንድማማች ማኅበረሰቦች በማፋጀት የሚገኘው ጥቅም ምንድን ነው? ጥላቻን ዘርቶ ዐመፃን ማጨድ ማንን ነው የሚጠቅመው? ተጋድመው የተፉት ምራቅ ተመልሶ ወደራስ እንደሚመጣስ መገንዘብ እንዴት ያቅታል? አሁን በዐማሮች ላይ እየተደረገ ያለው ሊታመን የማይችል ሲዖላዊ ተዓምር ወደሰማዩ ጌታ መጮኹና መልስ ማግኘቱ ይቀራል? ያኔ ምን ይውጠናል?

የሰዎች ትክክለኛ የኅሊና ፍርድ ተዛብቶ ወደ ከፋና ከረፋ ዝቅተኛ የአስተሳሰብና የአመለካከት ደረጃ ለምን እንደሚወርድና አንዱ በአንዱ ለምን እንደሚጨክን ብዙ ጊዜ ይጠየቃል፡፡ መልሱ ደግሞ ቀላል ነው – እሱም ጥቅም ነው፡፡ ጥቅም አይደለም ጎሣና ነገድን ወንድምና እህትን ያገዳድላል፡፡ አባትና ልጅን ያባላል፡፡ ቤተ ዘመድን ያጨራርሳል፡፡ ጥቅምና ሥልጣን በጣም አደገኛ መርዝ ናቸው፡፡ “የአቦይ ስብሃት ሀብት ከሚነካ የትግራይ ሕዝብ ጥንቅር ይበል፤ የአባይ ፀሐዬ ሥልጣን ከሚሸረሸር የትግራይና ዐማራ ሕዝብ ሚና ለይቶ ይጨራረስ፡፡ መንግሥቱ ኃ/ማርያም ሥልጣኑን ከሚያጣ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ባፍ ጢሟ ትደፋ፡፡…” ይህ ነው የግለሰቦች የሥልጣንና የሀብት አምልኮ፡፡ እንጂ ሕዝብና ሕዝብ በየትም ሀገር ለጠብና ለፍጅት ተፈላልጎ አያውቅም፡፡ የዕልቂት ከበሮ የሚጎስሙ ወገኖች በሀብትና በሥልጣን ሱስ ናላቸው የዞረ ጥቂት ግለሰቦችና በሥራቸው የሚኮለኩሏቸው አጥፊ ጀሌዎች ናቸው፡፡ ይህ ዓይነቱ የትያትር መድረክ ደግሞ መጋረጃው ሲዘጋ አብሮ የሚዘጋና በሌላ የተሻለ ወይም እንደኛ እንደስካሁኑ ከሆነ የጥንቱን በሚያስመሰግን መጥፎ ታሪክ የሚተካ ነው – እስካሁን እንዲህ ነበር ወደፊትም እንዲሁ ነው፤ ክፉም ሆነ ደግ መንግሥት ወይም ሥርዓት ባለበት ለዘላለም አይኖርም፡፡ ሕዝብ ግን ዘላለማዊ ነው፡፡ እናም ውድ ኢትዮጵያውን አይዞን ይህ ወያኔዊ የጥፋት ዘመን አልፎ የፍቅርና የመተሳሰብ ዘመን በቅርብ ይመጣል፡፡ ጸሎታችን መሆን ያለበት መስዋዕትነቱ እንዲቀንስልን “ጌታ ሆይ ዕርዳን” ነው – እኛም ከክፋትና ከአጥፊነት ርቀን ታዲያ፡፡ ደግሞም በመካከላችን ጥላቻን አናባብስ፡፡ የሚተርፈን ትዝብቱ ነው፡፡ ኢትዮጵያ እንደሆነች ጠፍታ የማትጠፋ የፈጣሪ ቃል ኪዳን የሚጠብቃት ሀገር ናት – በወረት የዘረኝነትም እንበለው የትምክህተኝነት ንፋስ አንወሰድ፡፡ ከሁሉም ከሁሉም ምንም ዓይነት ጥጋብ አይፈታተነን፡፡ ብናገኝ አንኩራ፣ ብናጣም አንፍራ፡፡ “ሁሉም በርሱ ሆነ – ያለርሱ በሰማይም በምድርም ምንም አልሆነም፡፡” ስለዚህ ለምኑ እንጨነቃለን? የተወሰደ እንደሚመጣ፣ የመጣም እንደሚወሰድ አናውቅምን? ማን ነው እንደኮራ እንደደራ የኖረ? ማን ነው እንዳነሰ እንደኮሰመነ ኖሮ ከምድር የተሰናበተ? ጠቢቡ አስቀድሞ “ለሁሉም ጊዜ አለው” ብሏል፡፡

ከአዳም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ይህ የጥቅምና የሆድ ጉዳይ የዓለም ሕዝቦችን እያፋጀ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን ከገነት የተባረሩት፣ አቤል በወንድሙ በቃየል የተገደለው፣ ያቆብ ጭብጥ በማትሞላ ምሥር ብኩርናውን የለወጠው፣ ይሁዳ ጌታውን በሠላሣ ዲናር የሸጠው፣… በዘመናችንም ሲአይኤና ሞሳድ በዲሞክራሲ ጭምብላቸው ዓለምን እንዲህ የሚያሽቃንጡባትና እንደፈለጉ የሚፈነጥዙባት በጥቅምና ለጥቅም ሲባል ነው(ህእ! ሳውዲ ዐረቢያ ውስጥ የዴሞክራሲ ጭላንጭል የለም … በአውራ መንገዶችና በሠፈር ውስጥ ብቻዋን መሄድ የማይፈቀድላት ሴት መኪና እንኳን አትነዳም፤ ስለዴሞክራሲ ጭንቅ ጥብብ የምትለውና በዴሞክራሲ በሚመጣባት ሀገር ላይ ከማዕቀብ እስከ ጦር ማዝመት የምትደርሰው አሜሪካ የዚህች ሀገር የበላይ ጠባቂና ዘበኛ ናት – ለጥቅም ሲባል… ዕንቆቅልሽ፡፡)

… እንጂ ዐማራ ከማንም የበለጠ “አህያና ደደብ” ወይም “የአእምሮ ዘገምተኛ” ሆኖ አይደለም – ሰፊው ኦሮሞ ከትግሬ በልጦ ጠባብ ሆኖ አይደለም፡፡ ትግሬ ከማንም በልጦ ጀግናና አልሞ ተኳሽ ሆኖ አይደለም፡፡ ማዕከላዊው የግጭት መንስኤ ጥቅም ነው፡፡ በጥቅም የታወሩ ወንድሞቻችን አቅል አጡና ከምድረ ገጽ ሊያጠፉን ቆርጠው ተነሱ፡፡ ባጭሩ ይህን ሁሉ ዕልቂትና ፍጅት እያስከተለ ያለው ከፀሐይ በታች ያለ የሸርና የተንኮል ጉንጉን የተላበሰ የወያኔዎች የሀብትና የሥልጣን ጉጉትና የዓለም አቀፉ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሤራ ድምር ውጤት ነው፡፡ ከወያኔዎች ጋር ተሰልፎ ጃዝ ሲሉት እየገደለና እየዘረፈ የሚተመው የጥፋት ሠራዊት ደግሞ ከዕውቀትም ከባህልም ከሃይማኖትም የወጣ ወፍ ዘራሽ ጀሌ ነው – አብዛኛው ከእረኝነት በቀጥታ የመጣና ማኅበራዊ እንስሳነቱ የተጓደለበት ከመሆኑም ባሻገር ዐማራን እንዲጠላና ከጥላቻውም ብዛት የተነሣ በጭካኔ እንዲፈጀው ሥነ ልቦናዊ ጫና የተደረገበት አሳዛኝ ፍጡር ነው፡፡ ሳይፈልግ በተደረገበት ተፅዕኖ ምክንያት ስለሆነ ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈጽመው ሙሉ በሙሉ በርሱ ለመፍረድም ይከብዳል፤ በዚያ ላይ የውጭ ጠላቶቻችን ለውስጥ ምንደኞች ያሸከሙት ታሪካዊ የጥፋት ተልእኮም ቀላል አይደለም – የየትኛውንም ሀገር ባለሥልጣናት ብሔራዊ ስሜት በማጥፋት የነርሱ አሽከሮች የሆኑ መሪዎችን በማፍራት የሚታወቁት የዐውሬው ልጆች ምዕራባውያንና አውሮፓውያን ካልጠፉ ወይም ሰይጣናዊ ተፈጥሯቸውን ካልቀየሩ (ይህ የማይሆን አማራጭ ነው) አለዚያም እኛ ይህን መርዝነታቸውን ነቅተንባቸው በኅብረት ካልታገልናቸውና ድል ካልነሳናቸው ደግሞ ዕረፍት እንደሌለን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ የዘመቻቸው ጅማሮ ጥንታዊ ነው፤ ድላቸው ግን ጊዜያዊ ነው፡፡

ጥቂት ታገሱኝ – አንዲት ነገር ብቻ ትቀረኛለች፡፡ የትግራይ የወቅቱ መሣፍንትና መኳንንት ትግራይን ይዘን እንሄዳለን ቢሉ ጥርሳችንን ተነቅሰን እንስቅባቸዋለን፡፡ በርግጥም ጤነኛ ነኝ የሚል የዚህች ዓለም ዜጋ ይስቅባቸዋል፡፡ “እውነት እውነት እላችኋለሁ” ብሎ ይጀምር ነበር ክርስቶስ የመረረ እውነት ሲናገር፡፡ እኔም ልዋሰውና – እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ትግራይን መገንጠል ቢያስፈልግ ኖሮ ይቻል የነበረው የዛሬ 25 ዓመት ገደማ በ1983ዓ.ም ወርኃ ግንቦት ላይ ነበር፡፡ አሁን እጅግ መሽቷል፤ “ቢያዩኝ እስቅ፣ ባያዩኝ እሰርቅ“ የሚለው ብሂል የማይሠራበት የመጨረሻው ሰዓት ላይ ስላሉ ያን ቅዠታቸውን ዘመን ሽሮታል፡፡ “ዕድላችንን እንሞክር” የሚባልበት ጠባብ የተስፋ ጭላንጭል እንኳን የለም፡፡ አንድ የትግርኛ ብሂል ላስታውስ – ወዳማርኛ ልመልሰው ፡- “የሚበቃትን ያህል ጥሬ ከፈጨች በኋላ የማርያም በዓል ነው ትላለች” ይላል፡፡ ግሩም ብኂል ነው፡፡ በልጆች ጨዋታ ጊዜ “ጨዋታው ፈረሰ፣ ዳቦው ተቆረሰ” ሊባል ይችል የነበረው ዛሬ ሣይሆን ከዛሬ 25 ዓመታት ገደማ በፊት ነው፡፡

ወልቃይትንና አካባቢዋን ከጎንደር፣ ራያዎችን ከወሎ፣ የአባይ ግድብን ከቤንሻጉል፣ እንትናን ከአፋር … ከዘረፉና ወደ “ታላቋ የትግራይ ሪፐብሊክ” ካካለሉ በኋላ፣ ሰፊ የዐማራ ግዛትን ለሱዳን ከሸጡ በኋላ፣ የኢትዮጵያን ሀብትና ንብረት ለ40 እና 25 ዓመታት በተከታታይ ካለተቆጣጣሪ እንደልብ ከመዘበሩና ወደሚፈለጉት ቦታ ካዘዋወሩ በኋላ፣ በሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በልዩ ልዩ ዘዴ ከምድረ ገፅ ካጠፉና እንዲሰደድም እንዲፈናቀልም እንዲራብና እንዲታረዝም ካደረጉ በኋላ፣ የኢትዮጵያን አስተዳደር በአንድ ጎሣ ቁጥጥር ሥር አውለው የሀገሪቷን አንጡራ ሀብት እንዳሻቸው ከቦጠቦጡና መዋቅሮቿን ሁሉ ካፈራረሱ በኋላ፣ የሚንቀሳቀስንም ሀብትና ንብረት ወደ አሳቻ ቦታ ካሻገሩ በኋላ… ለዚህ ሁሉ ዘመን በአንዲት ሉዓላዊት ሀገርና በአንድ ሕዝብ ላይ እንደልብ ከፈነጩ በኋላ አሁን ሲመሽ “የያዝኩትን ይዤ የራሴን ግዛት እመሠርታለሁ” የሚለው ብልጣብልጥነት ከማሣቅም ያልፋል – ወያኔ ከኢትዮጵያ የአንበሣና ዝኆኑን ድርሻ ዝቆ ወደራሱ ጎተራ ካስገባ በኋላ ለመሆኑ ለሌላው ሕዝብ ምን የቀረለት ነገር አለና ብቻውን መንግሥት መሥርቶ ከነሱ ጋር በአቻ ጉርብትና የሚኖረው? የመረጃ ቋቱ ሳይቀር ተጉዞ መቀሌ ገባ ከተባለ በኋላ ሌሎቹን እንደፍጥርጥራችሁ ብሎ “ትግራይ ሪፐብሊክ” የምትመሠረተው በየትኛው ሥሌት ነው? የዋህነት ወይንስ ድምበርን የማያውቅ ብልጠት? ሀገርን ማስተዳደርና ሀገርን መመሥረት የልጆች የቃቃ ጨዋታ አይደለም፡፡ አንድን ሀገር አፍርሶም ሌላ ሀገር መገንባት የሚታሰብ አይሆንም፡፡ ቂልነት ነው፡፡ ወይም የለዬለት ዕብደት፡፡

የወያኔዎች አጀማመር ሁሉ እንዳይሆን ነው፤ ሲጀምር ትልቅ ሀገርን እየገዙ የ”ገዛ ሀገር”ን መሬት ለባዕድ መሸጥና በነሱው አጠራር ካንዱ ‹ክልል‹ ወደሌላው ‹ክልል‹ ቁርጥራጭ መሬት እየቀደዱ መስፋት ጥንቱንም አላስፈላጊ ነበር – ሌላ ታሳቢ ተንኮል እስከሌላቸው ድረስ፡፡ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀገር እስከሆነች ድረስ በግዛት መካለልና ያንንም ተከትሎ በመጣ ዕልቂት የሰውና የንብረት ውድመት መከሰት አልነበረበትም፡፡ ማንም ዜጋ የትም ሄዶ መሥራትና ሀብት ንብረት ማፍራት ስለሚችል አዲስ አከላለል ወይም ኬሌላ ግዛት የመሬት ዝርፊያ ባላስፈለገም ነበር፡፡

ወያኔ ግን የነገን ሣይሆን የዛሬን ብቻ ስለሚያስብ የሆነው ሁሉ ሳንወድ በግዳችን ሆነ፡፡ ግዴለም – “በዚሁ ይለፍ፡፡” ዋናው ነገር ግና ከዚህ ሁሉ የሰው ዕልቂትና የንብረት ውድመት በኋላ የ“ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ” ለመመሥረት ማሰብ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ዕብደት እንጂ ሌላ ሊሆን አለመቻሉን መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ወያኔዎች እንደዚህ ያለ ጅል አስተሳሰብ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ ከፍ ሲል በዐማርኛ የጠቀስነውን የትግርኛ ብሂል ደግመን በማስታወስ ”ዝአኽለን ጥሂነን በዓል ማርያም ትብላ” ብለን እንተርትባቸዋለን፤ ወቅቱ የሀዘን ቢሆንም በለበጣ የአግራሞት ሣቅ እንፈግባቸዋለን፡፡ ይህን ቅዠት ማንም ወያኔም ይሁን የትግራይ ክፍለ ሀገር ሰው ሊያስበው አይገባም፤ አይችልምም፡፡ ሁለት ተቃራኒ ነገሮች ኅብረት የላቸውም፡፡ ብርሃንና ጨለማ በአንድ ጊዜ አይገኙም፡፡ ኢትዮጵያዊነትና ትግራዊነትም እንዲሁ፡፡ ጤናማ ተጋሩ ከዚህ ወያኔያዊ ቅዠት ባፋጣኝ ውጡና የሚሻለውን ለማድረግ ተመካከሩ፡፡ ይህ “ወርቃማ” ዕድል የዛሬ 25 ዓመት አለፈ፡፡ የፈሰሰን ውኃ ማፈስ ደግሞ አይቻልም፡፡

ይልቁንስ ለትግራይና ለተጋሩ የሚያዋጣው ብቸኛ መንገድ የሆነች መፈንቅለ መንግሥት ማድረግና ያችን ተከትሎ ጤናማ ትግሬዎች የያዙት “የክልሉ መንግሥት” ከሌሎች ጤናማ ወገኖች ጋር አዲስ ድርድር ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም የጤናማ ትግሬዎች ሚና በጣም ወሳኝ ነው – በተለይ ወጣቱ፡፡ ይህ ሣይሆን ቀርቶ ወያኔ የትግራይን መፃዒ ዕድል እንደእስከዛሬው ሁሉ እንዲወስን ከተደረገ በርግጥም የትንቢቱ ፍጻሜ ይሆንና  ሊያስወግዱት በሚቻል ችግር ሀገራችን የማትወጣው አደጋ ውስጥ ትገባለች፡፡ ይህን እውነት አሁን ሳይመሽ በጊዜ እንዲህ ባልተለመደ ድፍረት የምናገረው ሌላውን ተውትና ከነባራዊው ዓለም ተጨባጭ ወይም ገሃድ እውነት በመነሳት የተበደለ ሲነሳ የሚያቆመው ነገር እንደሌለ በመረዳት ነው፡፡

እዚህች ላይ አንዲት ጠቃሚ ነጥብ ላንሳ፡፡ … ደጋግ ሰዎች ለፈጣሪ ከጮኹና የፈጣሪን ልብ ካራሩ ትንቢት ሊለወጥ ወይም የሚከሰት ውድመት ሊቀንስ እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነውና ለፈጣሪ የቀረባችሁ ዜጎች የእንቅልፍ ሰዓታችሁን በመቀነስ ሌት ተቀን ወደፈጣሪ ጩኹ፤ እየመጣ ያለው የመከራ ዶፍ ሰው ቀርቶ ምድር አትችለውም – በዓለም ታሪክ ወደር የሌለው የወያኔዎች ዐረመኔነት የሚያስከትለው ጦስ እንዲህ በቀላሉ የሚገመት ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ስለወንጀል ዕዳ አከፋፈል ምንም የማያውቅ የዋህ ሰው መሆን አለበት፡፡ ይህን የማይም ማስጠንቀቂያ እየተናገርኩ ያለሁት በዱባ ጥጋብ ለታበዩትና በዕብሪት ጉሽ ጠላ ለሰከሩት ወያኔዎችና መሰሎቻቸው አይደለም፤ ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውምና እነሱ መቼም ሊለወጡ አይችሉም – እንዲለወጡ የሚጠብቅም ሰው ካለ የአእምሮ ህክምና የሚያስፈልገው የለዬለት ሞኝ ነው፤  እነሱና ጋዳፊ ሊለወጡ እንደማይችሉ በበኩሌ በደንብ አውቃለሁ – ጋዳፊ ስምንት ቀን ተሸሽጎበት ከነበረው የቆሻሻ ቱቦ ወጥቶ “ምን ሆናችሁ? ሊቢያ ውስጥ ምን ተፈጠረ?” እያለ መሪው እርሱ የሆነ ያህል ቆጥሮ በባትሪ እየፈለጉት የነበሩትን ተቃዋሚዎች ለማዘዝ ቃጥቶት ነበር አሉ – ግን ወዲያው ያዙትና በመቀመጫው በኩል ሣንጃቸውን ወድውደው አንጀቱን በጣጥሰው ገደሉት – የአምባገነኖች መጨረሻ እንዲህ ነው፡፡ እኚህን መሰል ደናቁርት ከአህያ የማይሻል የማየት ችሎታ ነው ያላቸው፤ የጅልነታቸው መጠን የጨካኝነታቸውን ያህል ነው፡፡ …

እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ከተጋረጠባት የጥፋት ዳመና ያውጣልን፤ ፍቅርና አንድነትን ይስጠን፡፡ ለሳዖል የሰጠውን ማስተዋል ለሕወሓትም ሰጥቶ ሕዝብንና አገርን እያረዱበት የሚገኙትን ጎራዴ/ሠይፍ ወደ አፎቱ እንዲያስገቡና ዕርቅና ሰላም በሀገራችን እንዲሰፍን እግዜር ይርዳን፤ ምርጫ አጥተን የምንገባበት መብታችንን የማስከበር ትግል ሁሉ ብዙ የሕይወትና የንብረት መስዋዕትነትን ይጠይቃልና የእስካሁኑ መከራችን በቃችሁ ብሎ ባፋጣኝ ምሕረቱን ይላክልን፤ አሜን፡፡

ማስተዋል በለጠ

mz23602@gmail.com

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20115#sthash.JgjXDo1h.dpuf