እባክህን ወንድሜ አሊዩ ይህንን በሳይታችሁ ለጥፉልኝ [ዳንኤል ሺበሺ ]

ለክቡር ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡፦ ሠይፎትን ወደ አፎቱ እንዲመልሱ የሚጠይቅ የግል ደብዳቤ፤
***********************************
ክቡር ሆይ፣ ሺህ ዓመት ይንገሱ፡፡
D595876A-ACA1-40C5-817B-4AE23A49E31C_cx29_cy4_cw43_w987_r1_s_r1የዛሬ አያረገውና እርሶዎን ያነ በምንጠራዎት በቤተሰባዊ አጠራር <ጋሽ ኃይሌ> ብዬ ጉዳዬን ልጀምር፡፡
ጋሽ ኃይሌ፦ ሁሌም ቢሆን ስለ እርሶዎ የገዘፈው ግላዊ ስብዕናዎትን በተለያዩ ትላልቅ ሚድያዎችም ጭምር ከመመስከሬ ቦዝኜ አላውቅም፡፡ ነገር ግን የኅወሓትን ትብታብ ውስጥ የታመቀውን የሀገሪቱን ውስብስብና ጥልቀት ያላቸው ችግሮችን በጣጥሰው ይወጣሉ ብዬ  እያሰብኩ ጊዜ እንደማላጠፋም ግን አልሸሸገዎትም፡፡
ይህን ደብዳቤ ሳዘጋጅ ምን ሊፈይዱ? በምል ሀሳብ ከራሴ ጋር ሙግት የገጠምኩ ሲሆን፤ ምንም ይሁን ምን አሁን ፊለ ፊታችን የምናውቀው እርስዎን ስለሆነ በእርስዎ በኩል ለዋናዎቹ እንዲደርስ ማድረግ ተገቢ በመሆኑ ነው በቀጥታ ለእርስዎ የጻፍኩሎትና እባክዎትን በጽሞና እንዲያነቡና አንብበውም እንዲያሰላሰሉ በትህትና እጠይቅዎታለሁ፡፡

በአንድ በኩል ከጊዜ መንጎድ ጋር የፖለቲካ አቋማችን መራራቅ፤ በሌላ በኩል እርስዎ ያለ ሕዝብ ድጋፍ በፖለቲካ ሥልጣን ከፍከፍ ሲሉ እኔ ደግሞ በተቃራኒዮ በመንግስትዎ እየተደቆሰ ካለው ህዝብ ጋር መከራን በመምረጤ በሥልጣንም ሆነ በኢኮኖሚ ዝቅዝቅ ማለት እና እርስዎ በሥራ ጫና፤ እኔ ደግሞ በተቃራኒው ያለሁበት ሁኔታ ተዳምሮበት ምናልባትም መረሳሳትን አስከትሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ቅሉ አንዳንድ ትዝታዎችን ብጠቁም ለማስታወስ አይከብድዎትምና … ፡፡
ያነ በደጉ ዘመን ወደ ደርባባው ሱፎዎት ውስጠኛው ኪስዎ የገዛ እጄን በእምነት እየሰደድኩ ለኔ የምበቃኝን ያህል ገንዘብ በመውሰድ በእርስዎ ገንዘብ እርስዎን መጋበዘን፤ ሲቀላ (በአርባ ምንጭ ከተማ) በአሁኑ የኤርትራዉያኖቹ ዳህላክ ጫማ ቤት ለእግርዎ ተስማም ጫማ ስንመርጥ… ለኔም ሲገዙልኝ፤ ሼቻ አሻም ሬስቶራንት አስቀድሜ ምሣ አዝዤ ስጠብቅዎት፤ የወጋጎዳን መመስረትን ተከትሎ በአከባቢዬ የተቀሰቀሰውን ቀውስ ለማብረድ ስንመካከር አቤት የነበረን ፍቅርና መቀራረብ!

መውደድ ብቻም ሳይሆን ለምናከብራት ባለቤትዎ ለእተጌይቱ ሮማን ተስፋዬ’ም የምለው አለኝ፡፡ እርሳቸውም በትክክል የተሟላ የሴትነትና የእናትነት ፀጋ የተጎናፀፉ በዕውቀትና በጥበብ የተካኑና ለባልዋም ዘውድ ወይዘሮ መሆናቸውን በግሌ እመሰክርላታለሁ፡፡ ያኔ በዩኒቨርሲቲ መኖሪያ ቤታቸው እንጀራ ተቀራምተን ስንበላ በጆግ ውሃ እየቀዱ ስረጩብንና ሲያባረሩን፤ እኛም በውሃው ከመረስረስ ራሳችንን ለመከላከል ሲንል እርሶዎን ተሸክመን ወደ እልፍኞዎት አስገብተን በሩን በላይ ላይ እየዘጋን ስንጫወት፣ ስንስቅ፣ የተዘጋውን በር እንዲከፈትልዎት ሲማጸኑልን የነበረንበትን ጊዜ ዛሬ ላይ ሆኜ በህሊናዬ ሳስብ ያ! ዘመን ተመልሶ እንደማይመጣ አዕምሮዬ እየጠቆመም ቢሆንም ግን ገራገሩ ልቤ አሁንም በምኞቱ ቀጥሎበታል፡፡ ምን እያልክ ነው ያሉኝ እንደሆን እርሶዎን ባያገኙ ኖሮ ጋሼ እዚህ ላይ ስለመድረሳቸው እርግጠኛ አይደለሁም እያልኩ ነው፡፡
ዛሬም አንድ ነገር የማለት ግዴታ አለቦዎት፡፡
የአንድ መንግሥት ከሚጠበቅበት ትላልቅ ኃላፊነቶች ውስጥ ዋነኛው ሥርዓት አልበኝነትን መቆጣጠር፣ የህዝቦችን/የሰዎችን ፀጥታንና ሠላምንና የሀገሪቱን ግዛት አንድነትን ማስጠበቅ እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ምንም እንኳ ያልተሳካልን ቢሆንም፡፡ በአንፃሩ በአሁኑ ወቅት በሀገራችኝ እየተስተዋለ ያለው ግን ሥርዓት አልበኝነት፣ ለህግ ያለመገዛት . . . ነው የሚያሰኝ ምልክት አለ ለማለት ይቸግረኛል፡፡ የተበደለ፣ የተገፋ፣ የተሰደበ፣ ፍርድንና እውነትን ያጣ፣ በዚህም የተማረረና በሀገርቱ ከተንሰራፋው ሙስናና አድልዎ የተነሣ በድህነት እየደቀቀ ያለው ህዝብ የተሰማውንና በውስጡ የታመቀውን ስሜቱን ከመግለጽ ውጭ፡፡

ስለዚህ እርሶዎ በቀን ነሐሴ 24, 2008 ዓም የተናገሩት ለትልቁ ምክር ቤትዎ ባይሆንም “እኔ በበኩሌ ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስዱ አዝዤያለሁ!” ብለው በድፍረት ተናግረዋል፡፡
ክቡር ሆይ፦ ለክብሮነትዎ ሁሌም ሠላምን እመኛለሁ፡፡ ሠላማችንን አያደፍርሱብን፡፡ ያወጁብን ነገር ታላቅ ጥፋት ነው፡፡ በህዝብዎ ላይ የተወጠነ አደገኛ ነገር ፡፡ ይህ ሕዝብኮ የጣሊያን ወራር ኃይል አይደለም፡፡ የአጥንትዎ ክፋይ ነው፡፡ በእርስዎ የሚተዳደር ሕዝብ፡፡ በገዛ ሀገርዎና  በሕዝብዎ ላይ በጠራራ ፀሐይ ጦርነት አውጀዋል፡፡ ተበድያለሁ ብሎ ደመ እንባ በሚያለቅስ ሕዝብ ላይ እንዴት የቡድንና የነፍስ-ወከፍ ጦር መሣሪያ የያዘ ጦር ኃይል በአንድ ጠቅላይ ጦር አዛዥ ይታዘዛል?? ወይስ አማራና ኦሮሞ ከመቼ ጀምሮ ነው የእርሶዎና የኢት/ያ ጠላት የሆኑት? በእውነት  በእርስዎና በአመራርዎ አፍርያለሁ፡፡ ስለዚህ በአስቸኳይ ሠይፍዎትን ወደ አፎቱ ይመልሱ!  የሕዝብዎት እንባ ምን እንደሆነ ለማዳመጥ ጆሮ ይስጡ እንጂ እደመስሳለሁ እያሉ የግዛትዎትን ነዋሪ ማሳደድዎትን ያቁሙ፡፡

ሌላውና እዚህ ጋ ጠቅሼ ማለፍ የሚፈልገው ነገር ቢኖር፦ እርስዎ ወደ ሥልጣን በመጡ ቁጥር ሁሌ እልቂትና መከራ በህዝብዎ ላይ ይበዛል፡፡ ግን ለምን  ይሆን??
ለምሣሌ፦ ➊ እርስዎ የወጋጎዳ ከፍ/አመራር በነበሩ ጊዜ የአርባምንጭ፣ የሳውላ የዳውሮና የአከባቢው እልቂትና ውድመት ይቅርና በገዛ በትውልድ ከተማዎ በሶዶ ብቻ መተኪያ የሌለው ሕይወታቸውን ያጡ  ምን ያህል እንደነበሩ ሁላችንም የምናውቀው ሲሆን፤ በዚህም እንደ ቅጠል የረገፈው የንጹኃንን ነፍስ፣ የወደመው ንብረትና የባከነው ጊዜ እንርሳው ብንል እንኳ የሚሆን አይደለም፡፡
➋ እርስዎ የደቡብ ክልል ከፍ/ባለሥልጣን በነበሩ ጊዜ በሀዋሳና በአከባቢዉ በከንቱ የፈሰሰው ንጹኃን የሲዳማና የሌላ አከባቢ ተወላጆችን ደም፤ የወደመው ንብረትና የባከነ ጊዜ እንዴት ምንም እንዳልተፈጠረ ልንቆጥር እንችላለን?
➌ አሁን ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ የሀገሪቱን የፖለቲካ ሥልጣን ጠቅልለው መርሄ መንግሥት ከሆኑ ወዲህም እንደ ቀድሞ አለቃዎት ሁሉ ተመሳሳይ አንዳንዴም የከፋ ነገር መፈጸምን ሥራዬ ብለው ተያይዘዋል፡፡ እባክዎትን ጋሽ ኃይሌ!! ልማጽኖዎት፡፡

ስለዚህ መጽሐፉ <ቢሰሙም ባይሰሙም” እንደሚል፤ እኔም ለእርስዎ የሚከተሉትን ምክር ቢጤ ጠቆም ላደርግና እንሰነባበት፡፡
#1ኛ- ለጽሁፌ መነሻ የሆነውን የአሸባሪ ንግግሮዎትን በአስቸኳይ ይሳቡ፡፡ ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ ክብር ነው እንጂ በፍጹም ውርደት ሊሆን አይችልም፡፡
#2ኛ፡ እኛ ተቃዋሚዎች ለሩብ ምዕተ ዓመታት ያህል ስናነባ የነበርነው ለዛሬው መመሰቃቀልና ለከፋ አደጋ ያዳረጉ አፋኝ ህጎች በሙሉ መሰረዝ/መሻሻል ብቻም ሳይሆን ቀደም ሲል በዚህ የተፈፀሙ ኢ-ፍትሐዊ የሆኑ ውሳኔዎች በድጋሚ እንዲታዩ፣ አሳታፊና ሁሉንም ባለድርሻዎችን ያቀፈ የሽግግር ሥርዓት እንዲቋቋም የሚጋበዝ ውጥንዎን ከወዲሁ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርጉ፤
#3ኛ፡  ይህ የማይሆን ከሆነ ሹልክ ብለው ወደ አንድ  ሀገር ተጉዘው ጥገኝነት ይጠይቁ ባልልም (ከሕዝቦዎ ጋር መከራ መጋራትን ትተው መሰደድ ለአንድ ሀገር መሪ ክብር ነው ብዬ ስለማላምን)፤ ሥልጣንዎትን በፍላጎትዎ መልቀቅዎትን ያውጁና እቤትዎ ቁጭ ይበሉና ታሪክ ይሥሩ፡፡  በርግጥ ይህንን በማድረግዎ ዘለግ ያለ ዋጋ ያስከፍሎዎት ይሆናል፡፡ ቢሆንም ከትውልድና ከታሪክ አንፃር ሲመዘን ብድራቱ ታላቅ በመሆኑ፡፡

ደፍረው ይህንን ካደረጉ የግድ ይቅርታ መጠየቅ  አይጠበቅብዎትም፡፡ በቂያችን ነውና፡፡ ይሄንን በማድረግ ለትውልድ የሚተላለፍና ዘመን የማይሽረውን ታሪክ ተክለው ከማለፍዎ ሌላ ሀገሪቷን ማነው የሚመራው? እየተባለ የሚነሣውን ውዥንብር በማጥራት በትክክልም መሪ መሆንዎትን ያረጋገጡልናል፡፡ ቸር ያሰማን!

ከሰላምታ ጋር
ዳንኤል ሺበሺ – አክባሪዎ
ነሐሴ 30ቀን, 2008 ዓ.ም ተፃፈ፡፡

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/20494#sthash.58YLJGD4.dpuf

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s