በዐማራው ሕዝብ ላይ የማያዳግም ጥቃት ለማድረግ የሚደረገው ሴራ ለሽህዎች አመታት አይረሳም [አክሎግ ቢራራ (ዶር)]

 ““““`ወያኔ በቀን ስንት የዐማራ እና የኦሮሞ ሕጻናት/ወጣቶች እስከሚገድል እንጠብቃለን?““““

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ክፍል አንድ

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

ህወሓት በአማራው ሕዝብ ላይ እልቂት የጀመረው ቀደም ሲል ነው። ህወሓት ሲመሰረት ያዘጋጀው የመርህ ሰነድ የአማራን ብሄር ዋና ጠላት ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው። እንዲህ ይላል። “የአማራ ሕዝብ የትግራይ ህዝብ ዋና ወይንም አውራ ጠላት ነው። ይኼ ብቻ አይደለም የአማራ ሕዝብ የትግራይ ሕዝብ ድርብ ጠላት ነው። ስለሆነም፤ እኛ (ህወሓቶች) የአማራውን ሕዝብ መምታት አለብን፤ መጨረስ አለብን። አማራው ካልወደመ፤ አማራው ካልተደበደበ፤ ከመሬት ካልተነቀለ፤ የትግራይ ሕዝብ በነጻነት ሊኖር አይችልም። እኛ የምንመሰርተው ተተኪ መንግሥት ጥንቃቄ ማድረግ ያለበት አማራው ዋና መሰናክል እንደሚሆንብን ነው።” ህወሓት የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ሆኖ ሲታገል አማራውን በጠላትነት ከፈረጀው ስልጣን በሚይዝበት ጊዜ ይኼን “አውራ ጠላት” የፖለቲካ ስልጣኑና የመሳሪያ ኃይሉን መከታ አድርጎ አማራውን፤ ቢቻል “ከምድር መንቀል”) ካልተቻለ ቀስ በቀስ ማድከም፤ መግደል፤ እንዲሰወር፤ እንዲሰደድ፤ እንዲደኸይ፤ በራሱ እንዳይተማመን፤ እንዲዋረድ፤ ሰጥ ለበጥ ብሎ እንዲገዛ የራሱን ተወላጆች የጥቅም ሰላይ፤ ገዳይና አጋር ማድረግ፤ የኦሮሞው እና ሌላው አማራ ያልሆነ ሕዝብ በዐማራው ላይ እምነት እንዳይኖረው፤ ጥላቻ እንዲኖረው፤ እንዲያውም መልሶ ያንሰራራብሃል የሚል የከፋፍለህ ግዛው ስልትና ፕሮፓጋንዳ እያስተጋባ ኦሮሞውና አማራው “ጭድና እሳት” እንዲሆን ማስተጋባት የሚል ስትራተጅ ወዘተርፈ ተጠቅሟል። አሁንም ይጠቀማል።

ይህ የጠባብ ብሄርተኛ የከፋፍለህ ግዛውና ምታው ስልት ሰማእታት በሆኑ አማራዎችና ኦሮሞዎች መስዋእትነት ተለውጧል። በአማራውም ሆነ በኦሮሞው ማህበረሰብ ዙሪያ የሚገኙ ምሁራን እና ልሂቃን አሁንም የህወሓት የበላዮች አማራውን ከኦሮሞው በመለየት፤ በማያዳግም ደረጃ ለመምታት የሚያደርገውን ሽር ጉድ አንቀበልም ማለት ታሪካዊ ግዴታችን ነው። ትላንት ዐማራውን፤ ዛሬ ኦሮሞውን፤ ዛሬ ሌላውን እየለዩ መምታትና ማጥቃት የህወሓቶች ልዩ የበላይነት አገዛዝ ዘዴ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ለኦሮሞ ሕዝብ “አዲስ አበባን” እናስረክባለን፤ “በኦሮምያ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትና ስልጣን እንሰጣለን” የሚለው የፖለቲካ ቁማር ቴያትር ዋናው ምክንያት የህወሓትን እድሜ ለማራዘም እንጅ መሰረታዊ የሆኑንትን የነጻነት፤ የፍትህ፤ የሰብአዊ መብቶች መከበር፤ የእውነተኛ አኩልነትን፤ ሕዝብን መአከል ያደረገ የዲሞክራሲ ስርዓት ጥያቄዎችን በምንም አይመልስም። እንዲያውም አገር አቀፍ በሆነ የመንቀሳቀስ እድልና አቅም ያለውን ሕዝባዊ አመጽ ያበርደዋል።

የሕዝቡ ሰላማዊ ዐመጽ ማንም የቀሰቀሰው አይደለም። የመረረው ሕዝብ በየቀኑ የሚደርስበትን ጥቃት እና ጥፋት ለመመለስና ለመመከት የጀመረው አገር በቀል እና አገር ተከል እንቅስቃሴ ነው። ሕዝቡ በአንድ በኩል ልጆቹን መስዋእት እያደረገ በሌላ በኩል ከአሁን በኋላ የህወሓትን አፈና፤ ግድያ፤ ትእቢት፤ ጠባብ ዘረኝነትና ብሄርተኝነት አልቀበልም እያለ በመታገል ላይ ነው። ለእኔ አስደናቂው እና ተስፋ የሚሰጠኝ አንድ አስኳል ጉዳይ አለ። ይኼውም፤ ሕዝቡ የሚአደርገው ሰላማዊ ትግል ማንም ምሁር፤ ልሂቅ ወይንም የኢህአዴግ የመንግሥት አካል ያላሰበው መሆኑ ነው። ለዚህ ዋና ምሳሌ የራሱን መሪዎች፤ የራሱን የትግል ዘዴዎች፤ የራሱን የመደጋገፍ መንገዶች እየፈጠረ እና እየተጠቀመ የሚታየው ክስተት ነው። መመሪያውን የሚቀይሰው ራሱ ነው፤ መሪው ራሱ ነው፤ ግንኙነቱ የራሱ ፈጠራና ችሎታ ነው። የህሊናው መሪዎች በኦሮምያና በአማራ ክልሎች በገፍ የተጨፈጨፉት ወደፊትም የሚጨፈጨፉት፤ የቆሰሉት፤ የታሰሩት፤ የተሰወሩት እና የተሰደዱት ሰማእታት ልጆቹ ናቸው። የእነሱ ደም የእኛ ደም ነው እያለ ነው። የአማራና የኦሮሞ ወላጆች እያለቀሱ የቀበሯቸው በህወሓቶች የአጋዚ ልዩ ኃይል በግፍና በጭካኔ የሞቱትን፤ በአብዛኛው እድሚያቸው ከ25 ዓመት በታች የሆኑትን ከዚህ ጽሁፍ ጋር አባሪ ያደረግሁትን ሰነድ ማየቱ ይጠቅማል። ይህ ሰነድ የያዘው ስማቸው የተገኘውን ብቻ ያካተተ ሰነድ ነው።

አንድ ታዛቢ እንዳለው፤ ሕዝቡ ራሴን በራሴ እመራለሁ፤ ህወሓቶችን አልፈልግም እያለ “በሚጠይቅበት በአሁኑ ሰዓት፣ ነብሰ ገዳዩ የወያኔ ቡድን በሕዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት ከፍቶ ሕጻናትንና እናቶችን ሳይቀር እየጨፈጨፈ ይገኛል፡፡ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንደሚባለው አሸባሪው ወያኔ በሕዝባችን ላይ ጦርነት የከፈተው ራሱ ሆኖ ሳለ፣ የአማራን ወጣቶች በጸረ ሰላምነትና በሁከት ፈጣሪነት ሲከስ እየታዘብን ነው፡፡ ጸረ ሕዝብም ሽብር ፈጣሪም የሰላም ጠላትም ራሱ ነብሰ ገዳዩ ወያኔ ሆኖ ሳለ፣ እንደለመደበት የሕዝብ ጩኸት ለመቀማት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም::” የአንድ ትውልድ ዐማራ በገፍ እየጨፈጨፉ “እርቅና ሰላም፤ እርጋታና እድገት” እንፈልጋለን የሚል ፕሮፓጋንዳ ማስተጋባት ጊዜ ያለፈበት ስልት ነው። ”በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ንጹሐን የአማራ ልጆችን በየእስር ቤቱ አጉሮ ቶርቸር የሚፈጽመው (እስር ቤቶችን እያቃጥለ የሚፈልጋቸውን የፖለቲካ እስረኞች የሚጨፈጭፈው) ወያኔ መቼም ቢሆን ለሰላም ቦታ ኖሮት አያውቅም፡፡ እንግዲህ በዚህ
ሁኔታ ነው የአማራ ሕዝብ “የሰላም ኮንፈረንስ” በሚባለው ጉግማንጉግ እየተቀጠቀጠ ያለው፡፡ ሰላም እንዲሰፍን ካስፈለገ ልጆቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው፡፡” ግድያው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መቆም አለበት። አጋዚ ከሁሉም የአማራና የኦሮሞ ክልሎች መውጣት አለበት። ህወሓት የዐማራው ወጣት ትውልድ የትምኅርት እድል እንዳይኖረው ሲያደርግ ቆይቷል። ይህ የግፍ ግፍ ነው። “ የሁለተኛ ደረጃና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከእስር ተለቀው ወደትምህርት ገበታቸው መመለስ ሲገባቸው እስካሁን አልተፈቱም፤ ይልቁንም ወያኔ አሁንም እስሩንና ግድያውን ገፍቶበታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰላም
የለም፡፡ አይታሰብም፡፡ ልጆቻችን ታስረው የምን ሰላም ነው?
ወያኔ የችግሩ ዋና መነሻ የሆነውን የወልቃይት ጠገዴን ጉዳይ አስመልክቶ የሚያራምደው አቋምም ጨርሶ ሰላም የሚፈጥር አይደለም፡፡ ወያኔና ተላላኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ለትግራይ ክልል ያመለከተ የወልቃይት ኮሚቴ የለም ብለው ተራ የዱርዬ ክህደት ፈጽመዋል፡፡ አሁን ደግሞ ይህን ርካሽ ንግግር በተናገሩበት አንደበታቸው፣ አንዴ የወልቃይት ኮሚቴ ጥያቄውን ለትግራይ ክልል ካቀረበ ችግሩ ይታያል ይላሉ፤ ሌላ ጊዜ ችግሩን ሁለቱ ክልሎችና ሁለቱ ድርጅቶች ተወያይተው ለመፍታት ተስማምተዋል እያሉ ይቀጥፋሉ፡፡ አንድ አስተዋይ የአማራ አርሶ አደር፣ “ሰውን ማመን ቀብሮ ነው፤ ወያኔን ማመን ግን በላዩ
ላይ ሙጃ ከበቀለበት በኋላ ነው” ሲሉ የተናገሩት ትልቅ እውነት አለው፡፡ እውነትም ወያኔን ማመን በላዩ ላይ ሙጃ ከበቀለበት በኋላ ነው፡፡
ከዚህ የወያኔ ሰይጣናዊ ተፈጥሮ ተነስተን ነው፣ የሚሰበከው የሰላም ኮንፈረንስ ለውጥ አያመጣም፤ እንዲያውም ለበለጠ
እልቂት ይዳርገናል የምንለው፡፡ ከዚህ በኋላ የመቀሌን መሬት የሚረግጥ የወልቃይት አማራ አይኖርም!! በኃይል የተወሰደውን መሬታችን ብንችል በኃይል እናስመልሰዋለን፤ እኛ ካልቻልን ጉዳዩን ለወንድሞቻችንና ለልጆቻችን አውርሰናቸው እናልፋለን፡፡ ከዚህ ውጪ ምንም ምርጫ የለንም፡፡ በወያኔ መንገድ ሰላም አይመጣም፤ ኖሮም አያውቅም፡፡
ሁሉም የአማራ ልጅ ለማይቀረው ትግልና መስዋዕትነት መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ በትግላችንና በመስዋዕትነታችን መሬታችን
ይመለሳል!! ነጻነታችንም ይከበራል!! መፍትሔው ያለው በእጃችን ነው፡፡” ይህ አባባል በአገር ቤት በየቀኑ መስዋእት የሚሆኑት ጎንደሬዎች፤ ወሎየዎች፤ ጎጃሜዎች፤ የሰሜን ሸዋ አማራዎች የሚሉት ነው። እነዚህ ለፍትህ፤ ራስን ከእልቂት ለማዳን የሚታገሉ ዐማራዎች “እኔም ጎጃሜ ነኝ፤ እኔም ወሎየ ነኝ፤ እኔም ጎንደሬ ነኝ፤ እኔም ሃረሬ ነኝ” ወዘተርፈ እያሉ በመፈላለግና በመተባበር ራሳቸውን ከዐእልቂት እና ከውርደት ለማዳን መስዋእት እየሆኑ ነው። የጎጃም ዓለም-አቀፍ ድርጅት ባለፈው እሁድ ሲመሰረት በእንግዳነት ተጋብዤ የሰማሁት የዐማራውን ሕዝብ ራሱን ከእልቂት ለማደን ያደረገውን ውሳኔ እና የትብብር አስፈላጊነት አስምሮልኛል። “ኮሎኔል ደመቀ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ነው!!!! ይህን አስደናቂ ሕዝባዊ የሆነ የሰላም ዓመጽ የጀመረልን እሱ ነው” እያሉ ያስተጋቡት ድምጽ ሁሉንም የዐማራ ወጣት ሕዝብ በተከታታይ የሚቀሰቅስ ነው።

ልክ እንደ ጎጃም ዐማራዎች፤ ቀደም ሲል ጎንደሬው ድምጹን ሲያሰማ፤ ህወሓቶች “በኦሮሞ ወንድሞቻችን ላይ የምትፈጽሙት ግድያ ይቁም፤ ወንድማችን በቀለ ገርባ ይፈታ” ወዘተ እያለ ሲጮህ በአንድ በኩል የራሱን ማንም ሊቀማው የማይችል ማንነት፤ ክብርና የተፈጥሮ ኃብት ባለቤትነት ማስከበር፤ በሌላ በኩል ከኦሮሞው ሰፊ ሕዝብ ጋር ያለውን ጠንካራ ግንኙነት ለማደስ ነው። የአማራውና የኦሮሞው እድል አንድ ነው። የአማራውና የኦሮሞው መተባበር ለኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ሉዐላዊነት፤ ዘላቂ ጥቅምና ክብር ወሳኝ ነው የሚል ድምጽ በሰፊው እየተነገረ ነው። ሰላም ሊፈጠር የሚችለው እነዚህ ሁለት ግዙፍ ሕዝቦች የአገራቸውን እና የሕዝባቸውን እድል በበላይነት ሲመሩት ብቻ ነው። ከተባበሩ ማንም ኃይል አያቆማቸውም። ይህን ለማድረግ የጋራ አጥፊና ገራፊ የሆነውን ህወሓትን መቋቋም መቻል አለባቸው። ሸንጋይ የሆኑ የከፋፋይ ድርድሮችን አንቀበልም ማለት አለባቸው። ጭካኔ እየተካሄደ ከፋፋይ የሆነ የውስጥ ድርድር ማንንም አይረዳም። የሚረዳው ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት የብሄር ጥላቻ መርዝና ካንሠር መሰረት እንዲይዝ ያደረገው እና ወጣቱ ትውልድ በዚህ ካንሰር እንዲመረዝ እና እንዲበከል ያደረገውን ህወትን ነው።

በዐማራው እና በኦሮሞው ላይ የሚካሄደው ጭካኔና ግፍ ተመሣሳይም የሚለያይም ነው። እዚህ ላይ ትኩረት የማደርገው በሚጋሩት የህወሓቶች ሰለባነት ነው። ሃሳቡን ለማጠናከር ምሳሌዎች ላቅርብ። ህወሓቶች በተከታታይ አራት እስር ቤቶች አቃጥለው ሌላው አቃጠለው ብለዋል። እነዚህ እስር ቤቶች የፖለቲካ እስረኞች የታጎሩባቸው ናቸው። በደብረ ታቦር ብዙ ወጣት ዐማራዎች የታሰሩበት እስር ቤት ተቃጠለ። እስረኞቹ ከእሳት አደጋ ለማምለጥ ሲሞክሩ የአጋዚ አልሞ ተኳሾች የጥይት ሰለባ ሆኑ። በተመሳሳይ፤ በአዲስ አበባ የቂሊንጦ እስር ቤት በተመሳሳይ “በማይታወቅ” ምክንያት ተቃጠለ። ይህን እስር ቤት የተለየ የሚያደርገው የህወሓትን አፋኝና ጨፍጫፊ አገዛዝ የሚቃወሙ ጋዜጠኞችን፤ የፖለቲካና የሰብአዊ መብት ታጋዮችን፤ የእስልምና ኃይማኖት አባላትንና መሪዎችን የያዘ መሆኑ ነው። እነዚህ የአማራና የኦሮሞ ወገኖቻችን ከእሳት አደጋ ሊያመልጡ ሲሞክሩ የህወሓት መትረየስና የአልሞ ተኳሽ መሳሪያ የያዙ አጋዚያን እያነጣጠሩ ገልዋቸዋል። እጅግ የሚያሳፍረውን የሚያሳዝነው የሞቱት፤ የቆሰሉት ወይንም በሌላ ሁኔታ ያሉት እስረኞች የትና በምን ሁኔታ እንደሚገአኙ የጠየቁ እናቶች፤ ዘመዶች እና የእስረኞች ሚስቶች ምንም መልስ ሊያገአኙ አለመቻላቸው ነው። አንድም የትግራይ ተወላጅ የሞተ ስለሌለ የትግራይ እናቶችን የምጠይቀው ልጆቻቸው፤ ወንድሞቻቸው፤ እህቶቻቸው፤ ባሎቻቸው ወዘተ የሞቱባቸው ወገኖቻችን ሲያለቅሱ፤ ባለሥልጣናትን ጠይቀው ምንም መልስ ሳያገኙ ስታዩ እናንተስ ምን ይሰማችኋል? የሚል ነው። ህወሓቶች አጋዚያንን እየላኩ ንጹህ ኢትዮጵያዊያንን ሲጨፈጭፉ ወደፊት የሚመጣውን አደጋ ከግምት ውስጥ ታስገቡታላችሁ ወይንስ ህወሓትን “ይበለው” ትላላችሁ? “ጅራፍ ገርፎ ራሱ ይጮሃል” እንደሚባለው ህወሓት ራሱ እስር ቤት አቃጥሎ፤ ራሱ ወገኖቻችን ጨፍጭፎር መልሶ ሌላውን የመክሰስ ብቃት የለውም። ይህ በተደጋጋሚ ሲደረግ የዐማራውና የኦሮሞው ወጣት ትውልድ ያለው ምርጫ አንድ ብቻ ነው፤ ራሱን ከጨፍጫፊዎች መከላከል።

የአማራው ወጣት ትዕግስቱ አልቆ ከመሣሪያ ጋር ትንቅንቅ እየገጠመ የወያኔን ጸረ ሕዝብ አገዛዝ የሚቃወመው “የሰላምን ዋጋ ባለማወቁ ነው” እየተባለ ነው፡፡ “በእርግጥ ወያኔ ከዚህ ውጪ ሊያስብ አይችልም፡፡ ከእውነት ጋር አይተዋወቅምና፡፡ እኛ ግን በሕዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት አውጆ ልጆቻችን የሚፈጀውና ሽብር የሚፈጥረው የሕዝባችን ግንባር ቀደም ጠላት የሆነው ወሮበላው ወያኔ መሆኑን አሳምረን እናውቃለን፡፡ በጎን “በዚህ በሰለጠነ ዘመን ችግሮቻችን በሰላም መፍታት ይገባል” እያለ፣ እዚያው በዚያው በሕዝባችን ላይ ግልጽ ጦርነት ያወጀውና ብዙ ንጹሐን ልጆቻችን የጨፈጨፈው፣ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ንጹሐን የአማራ ልጆችን በየእስር ቤቱ አጉሮ ቶርቸር የሚፈጽመው ወያኔ መቼም ቢሆን ለሰላም ቦታ ኖሮት አያውቅም፡፡” ከታች በማስረጃ እንደማሳየው ህወሓት በዐማራው ሕዝብ ላይ፤ በተለይ በወጣቱ ትውልድ ላይ እልቂት ማካሄድ የጀመረው ስልጣን ከመያዙ በፊት ነው። አሁን የዐማራ ጭፍጨፋ አላማውን በቀጥታና በስውር እያካሄደ ነው። ላሰምርበት የምፈልገው፤ ህወሓት በስውር የሚጨፈጭፈው በግልጽ ከሚጨፈጭፈው የባሰ ነው። ለዚህ ነው፤ የመገናኛ ብዙሃን የከለከለው። ለዚህ ነው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ ባለሞያዎችን ለመላክ ወስኖ ህወሓት ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ የከለከለው። የሚደብቀው ነገር አለ ማለት ነው።

በአሁኑ ወቅት የዓለም መንግሥታት፤ በተለይ የአሜሪካ፤ የእንግሊዝ፤ የጀርመን፤ የሆላንድ፤ የካናዳና ሌሎች፤ የተባበሩት መንግሥታት፤ የአፍሪካ አንድነት ማህበር እና የአውሮፓ የአንድነት ማህበር ባለሥልጣናት ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ መሆኑን ገምግመዋል። በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ዶር ሳማንታ ፓወር ጁባ፤ ደቡብ ሱዳን ሆነው፤ የአሜሪካን አቋም በማንጸባረቅ የሰጡት መግለጫ የሁኔታውን “ከፍተኛ አሳሳቢነት” ያሳያል። “የአሜሪካ መንግሥት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለ አግባብ ገደብ የሌለው የመሳሪያ ኃይል እየተጠቀመ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የሚያካሂደው እልቂት እጅግ አሳሳቢ ነው” ያሉት። እኒህ የተባበሩት መንግሥታት የደህንነት ካውንስል አባል የሆኑት አምባሳደር ጉዳዩ በዚህ አካል መነሳቱን ፍንጭ ሰጥተው “በኢትዮጵያ መንግሥት የሚካሄደው እልቂት (violence) በጣም አደገኛና ተቀባይነት እንደሌለው” አሳስበዋል። “የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብታቸው እንዲከበር” ያሳሰበ መሆኑን ገልጸው፤ “ነጻና ግልጽነት ያለው” ጥናትና ምርምር እንዲካሄድ አቋም ወስደዋል። እሳቸው የተናግሩት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ለሴክሬተሪ ጆን ኬሪ፤ ለእንግሊዝ ጠቅላይ ሚንስትር፤ ለጀርመን ቻንስለር፤ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ፤ ለተበባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መቦቶች ከፍተኛ ኮሚሽነርና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሊቀ-መንበር የተጻፈውን አስቸኳ አቤቱታ መሰረተ ሃሳቦች ያንጸባርቃል። ***
***ጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

እንግዲህ በዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ነው የአማራ ሕዝብ “የሰላም ኮንፈረንስ” በሚባለው ጉግማንጉግ እየተቀጠቀጠ ያለው፡፡ ሰላም እንዲሰፍን ካስፈለገ ልጆቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መፈታት አለባቸው፡፡ ሆኖም የሁለተኛ ደረጃና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከእስር ተለቀው ወደትምህርት ገበታቸው መመለስ ሲገባቸው እስካሁን አልተፈቱም፤ ይልቁንም ወያኔ አሁንም እስሩንና ግድያውን ገፍቶበታል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰላም የለም፡፡ አይታሰብም፡፡ ልጆቻችን ታስረው የምን ሰላም ነው? ወያኔ የችግሩ ዋና መነሻ የሆነውን የወልቃይት ጠገዴን ጉዳይ አስመልክቶ የሚያራምደው አቋምም ጨርሶ ሰላም የሚፈጥር አይደለም፡፡ ወያኔና ተላላኪው ጠቅላይ ሚኒስትር ለትግራይ ክልል ያመለከተ የወልቃይት ኮሚቴ የለም ብለው ተራ የዱርዬ ክህደት ፈጽመዋል፡፡ አሁን ደግሞ ይህን ርካሽ ንግግር በተናገሩበት አንደበታቸው፣ አንዴ የወልቃይት ኮሚቴ ጥያቄውን ለትግራይ ክልል ካቀረበ ችግሩ ይታያል ይላሉ፤ ሌላ ጊዜ ችግሩን ሁለቱ ክልሎችና ሁለቱ ድርጅቶች ተወያይተው ለመፍታት ተስማምተዋል እያሉ ይቀጥፋሉ፡፡ አንድ አስተዋይ የአማራ አርሶ አደር፣ “ሰውን ማመን ቀብሮ ነው፤ ወያኔን ማመን ግን በላዩ ላይ ሙጃ ከበቀለበት በኋላ ነው” ሲሉ የተናገሩት ትልቅ እውነት አለው፡፡ እውነትም ወያኔን ማመን በላዩ ላይ ሙጃ ከበቀለበት በኋላ ነው፡፡

ከዚህ የወያኔ ሰይጣናዊ ተፈጥሮ ተነስተን ነው፣ የሚሰበከው የሰላም ኮንፈረንስ ለውጥ አያመጣም፤ እንዲያውም ለበለጠ
እልቂት ይዳርገናል የምንለው፡፡ ከዚህ በኋላ የመቀሌን መሬት የሚረግጥ የወልቃይት አማራ አይኖርም!! በኃይል የተወሰደውን መሬታችን ብንችል በኃይል እናስመልሰዋለን፤ እኛ ካልቻልን ጉዳዩን ለወንድሞቻችንና ለልጆቻችን አውርሰናቸው እናልፋለን፡፡ ከዚህ ውጪ ምንም ምርጫ የለንም፡፡ በወያኔ መንገድ ሰላም አይመጣም፤ ኖሮም አያውቅም፡፡ ሁሉም የአማራ ልጅ ለማይቀረው ትግልና መስዋዕትነት መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ በትግላችንና በመስዋዕትነታችን መሬታችን ይመለሳል!!
ነጻነታችንም ይከበራል!! መፍትሔው ያለው በእጃችን ነው።” ይህ ዘገባ በመሬት ላይ የሚስተጋባውን ሃቅ ያንጸባርቃል። ህወሓቶች ሁሉን ነገር በሌላ ከማከኛት ውጭ ዘላቂነትና ተቀባይነት ያለው መፍትሄ ለማቅረብ ፈቃደኛ ሆነው አያውቁም፤ አሁንም ፍላጎት አያሳዩም። ሕዝቡ ለምን እንደ ጠላቸውም ሲወያዩ አይታዩም። የዝግ ችሎት ግን በየቀኑ ያካሂዳሉ!!!

“ሕዝቡ ለምን ጠላን?”
የህወሓት የበላዮች፤ አባላት፤ ደጋፊዎችና አዲስ ተጠቃሚዎች “የኢትዮጵያ ሕዝብ ለምን ጠላን?” የሚል ጥያቄ ማንሳት ጀምረዋል። ሕዝብ ከእንቅልፉ ተነስቶ ወገኑን ወይንም ሌላውን አይጠላም። ብዙ ታዛቢዎች በመረጃ ተደግፈው የሚተቹት ህወሓቶች በግልጽ የሚያደርጉት ጠባብ ብሄርተኝነት፤ በቋንቋ የተመሰረተ አድልዎ፤ ስግብግብነት፤ ራስ ወዳድነት፤ አፋኝነት፤ ገዳይነት፤ መሬት ነጣቂነት፤ ጭፍን የሆነ አድሏዊነት፤ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት፤ ዘራፊነትና ቀማኛነት፤ ብሄርን ከብሄር፤ ኃይማኖትን ከኃይማኖት ከፋፋይነትና ጠብ ጫሪነት ወዘተርፈ ከህወሓት ተላልፎ ለትግራይ ሕዝብ ጥላቻን ሸምቶለታል የሚል ነው። ይህ በህወሓት ላይ ያለው ጥላቻ የድርጅቱ የበላዮች ቢቀበሉትም/ባይቀበሉትም ለብዙ ዓመታት በዐማራው፤ በኦሮሞው፤ በጋምቤላው፤ በኦጋዴኑ፤ በአፋሩ፤ በደቡቡ ወዘተርፈ ተቋማትና ህወሓት በበላይነት በሚቆጣጠረው ወታደር ውስጥም ስር እንደሰደደ ብዙ የውስጥ ታዛቢዎች ይናገራሉ። በመከላከያው ኃይል ሲደረግ የቆየው አይን ያወጣ የደሞዝ፤ የአበል፤ የድጎማ፤ የስራ አመዳደብ፤ የማእረግና ሌላ ልዩነት ከሲቪሉ አይለይም። አብዛኛው ተራ ወታደር፤ አብዛኛው ፊት ለፊት የሚዋጋው፤ የሚሞተው፤ የራስክን ወገን ግደል ተብሎ የሚታዘዘው አማራው፤ ኦሮሞው፤ ደቡቡ ወዘተ ሲሆን በበላይነት የሚያዘው የትግራይ ተወላጅ ነው። ከፍተኛ መኮንኖችና ጀኔራሎች ትግሬዎች ከመሆናቸው በተጨማሪ ኃብታሞች ናቸው። ጠባብ ብሄርተኛ፤ ትእቢተኛ፤ ቂመኛ፤ በሚዘገንን ደረጃ ጉረኛ ናቸው ሲባል ቆይቷል።
ይህ ጥላቻ እንዳለ ሆኖ አሁን በዐማራው ክልል ህወሓቶች የሚጠቀሙበት ዘዴ ለየት ያለ ነው። ድሃ ገበሬዎችን በማባበል፤ የወር ደሞዝ በመክፈል የራሳቸውን ወገን በዘበኛነት እንዲቆጣጠሩ፤ እንዲያቆስሉ፤ እንዲገሉ እየተደረገ ነው። ይህ አማራጭ ለጊዜው ደብረ ታቦር፤ ጎንደር እና ሌሎች ከተሞች እየሰራ ነው የሚሉ የውስጥ ታዛቢዎች አሉ። ሆኖም፤ በምንም አልገዛም ያለው የአማራ ገበሬና ከተሜ ሕዝብ የዐማራ ዘበኞችን እና ሌሎች ተቀጣሪዎችን ስም እየሰበሰበ ነው። እነዚህ ድሃ ተቀጣሪዎች በገጠር ቤት፤ በሬ፤ ላም፤ ፍየል እና ሌላ ንብረት አላቸው። በአንዳንድ ቦታዎች የእነዚህ ተቀጣሪዎች ንብረት እንዲወድም እየትገደረገ ነው። ህወሓት ዐማራው እርስ በርሱ እንዲፋጅ እያደረገው ነው። አሁንም፤ ትግሬዎች አዛዦች፤ አማራዎች ቅጥረኞች እያደረገ፤ በጀርባ ሆኖ “በሉት” እያለ ዐላማውን ያከናውናል። የህወሓት የበላይ ካድሬዎችና መኮንኖች ዐማራውንና ኦሮሞውን የሚቆጣጠሩበትና የሚያጠቁበት መንገድ ብዙ ነው።

የህወሓት የበላይ መኮንኖች ልክ እንደ ሲቪሉ የህወሓት ክፍል የኢትዮጵያን የተፈጥሮና ሌላ ኃብት ከነዋሪዎች የመንጠቅ መብት አላቸው፤ ራሳቸውን ከኦሮሞውና ከዐማራው የመለየት ስልጣንና መብት አላቸው። በአጠቃላይ እነዚህ ራሳቸውን
ከሌላው ኢትዮጵያዊ የለዩ የደህንነት፤ የመረጃ፤ የመከላከያና ሌሎች የፖሊሲ አውጭና አስፈጻሚ ድርጅቶች የበላዮች፤ በተለይ የህወሓት መኮንኖች ለህወሓት ህይወትና ዘላቂነት ወሳኝ የሆኑ፤ የሚከተሉትን የሚመስሉ ስራዎችን ይሰራሉ፤
1. ከሕግ በላይ እንቅስቃሴና ማንኛውንም እርምጃ የትም ክልል፤ በማንም ሕዝብ ላይ መውሰድ፤
2. ትግራይ ያልሆነ ዜጋ አባብለውና ቀጥረው የራሱን ሕዝብ እንዲጨፈጭፍ በጀርባ ሆነው ማዘዝ፤ ባያደርግ በራሱ ላይ እርምጃ መውሰድ (ደብረ ታቦር፤ ጎንደር ወዘተ የሚጠቀሙት ዘዴ)፤
3. የትግራይ ተወላጆች “ የህልውና አደጋ ይገጥማቸዋል” በሚል ሰበብ በያሉበት እነሱን መጠባበቅና አስፈላጊ ሲሆን ከአሉበት ቦታ ማውጣት፤ በጎንደር/ባህር ዳር እና ሌሎች ቦታ የሆነው ምሳሌ ነው፤
4. የትግራይ ተወላጆችን ኃብት መጠባበቅ፤ ኃብት ወደ ሌላ ቦታ ለማሸሽ ቢፈልጉ የደህንነት ሽፋን መስጠት፤
5. የህወሓት መኮንኖች በሚመሩት እና በሚቆጣጠሩት ማንኛውም የመረጃ፤ የደህንነት እና የመከላከያ ኃይል የትግራይ ተወላጅ ያልሆኑ “አፈንጋጮችን” ተከታትሎ በቁጥጥር ማዋል፤ ማፈንና መግደል፤
6. የትግራይ ክልልን መስፋፋት ዓላማ ስኬታማ ለማድረግ የሚደረገውን የመሬት ነጠቃና ሌላ የረቀቀ ስራ ተቃዋሚ ዐማራዎችን፤ በተለይ አባውራዎችን እየለቀሙና እየለዩ መግደል፤ እንዲሰወሩ ማድረግ፤ ማባረር፤
7. የህወሓት አመራርን ፈለግ ተከትሎ የዐማራውን ድንበር ቆርሶ ለሱዳን ሲሰጥ ውሳኔውን በኃይል ስኬታማ ማድረግ፤ ነዋሪው ዐማራ ጩኸት ሲያደርግ “አመፅኞች፤ ትምክህተኞች፤ የውጭ ጠላቶች፤ ሽብርተኞች፤ ኢሰፓዎች” የሚሉ ቅጽል ስሞች እየሰጡ ማሳደድ፤ መግደል፤ መሰወር፤ ማቁሰል፤ ማዋረድ፤ ማሰር፤ እንዲሰደዱ ማድረግ፤
8. በሌላው አመካኝቶ የፖለቲካ እስር ቤቶችን ማቃጠል፤ የሚፈለጉ ወይንም ከፍተኛ አደጋ ያስከትላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ እስረኞችን በአልሞ ተኳሾች መረሸን ወዘተርፈ፤
9. በስውር የሚካሄደውን የዐማራ ብሄረሰብ ማጽዳት እና ማጥፋት ስራዎችን በሌሎች፤ ለምሳሌ በኦሮሞ ወገኖቻችን አመካኝቶ ለህወሓት ሽፋን መስጠት፤
10. የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለህወሓት ከፍተኛ እውቅናና ክብር እንዲሰጡ ሶማሊያ፤ ደቡብ ሱዳን ወዘተ ወታደራዊ ድጋፍ መስጠት።
በአጠቃላይ ሲታይ፤ የህወሓት የበላይ መኮንኖች የሚኖሩበት ሁኔታና “ታዛዢና ግደል” ተብሎ የሚገደደው ተራው የአማራ፤ የኦሮሞና ሌላው ድህ ወታደር የሚኖሩበት ሁኔታ የሰማይና የምድር ልዩነት አላቸው። ተራው ወታደር ታዛዥ ከመሆኑ በተጨማሪ የሚኖርበት ሁኔታ ከወላጆቹና ከዘመዶቹ የተለየ አይደለም። ተራውን ወታደር የሚያዙት የህወሓት መኮንኖች በጠባብ ብሄርተኝነት፤ በትእቢተኝነት፤ በአልበገረም ባይነት፤ በይገባኛለነት፤ በሙሠኝነት፤ በዘራፊነት ወዘተርፈ የተበከሉ ስለሆኑ በጦሩም ውስጥ የጥላቻን ባህል ጥልቀትና ስፋት ሰጥተውታል። ይህ ለ25 ዓመታት የህወሓትን የበላይነት አስተማማኝ ሆኖ ሲያገለግል የቆየ ስልት በዐማራውና በኦሮሞው ሕዝብ በሚካሄደው ሰላማዊ ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት በመበጣጠስ ላይ ነው። አንድ ለአምስት የሚለውም የስለላው መረብ እንደ እምቧይ ካብ እየተናደ ነው የሚሉ ብዙ ናቸው። ሆኖም፤ ህወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጠረውና ያመጣው ጥላቻ በቀላሉ የሚወገድ አይመስልም። ለዚህ የሚዘገንን ግፍና በደል መጠየቅ ያለበት በጥላቻ የተገነባውን ስርዓት-ወለድ የክልል አጥር የፈጠረውና ተቋማዊ ያደረገው ህወሓት ነው። ትእግስተኛውና መከራ ችሎ የቆየው፤ ልጆቹ በየቀኑ ልክ እንደ አውሬ በአጋዚ ጥይት የሚፈሱት የኢትዮጵያ ሕዝብ አይደሉም።
ዛሬ ያለንበት ሁኔታ የሚያመለክተው የዐማራው ሕዝብ ሲካሄድበት የቆየውን ጭካኔና ግፍ ሲያጠና፤ ሲመዘግብ፤ ሲያወጣ ሲያወርድ መቆየቱን ነው። ህወሓቶት የዐማራውን አስደናቂ ትእግስት የተረጎሙት “መምታት፤ መጨረስ፤ ማውደም፤ መደብደብ፤ ከያለበት መሬት ነቅሎ ማውጣት” የሚለው መርህ ሰርቷል በሚል የተሳሳተ ዘገባ ነው። የሞተ ሰው አይነሳም፤

የተሰደደ አይመለስም፤ የተሰወረ አይታወቅም ወዘተርፈ የሚል ስሌት ነው። ህወሓቶች “የወደመው፤ የተነቀለው” ዐማራንም በማያንሰራራበት ደረጃ “ደምስሰነዋል”፤ የፈለግነውን መሬት ወደ ትግራይ ለማጠቃለል እንችላለን” ከሚል ድምዳሜ ላይ ደረሱ። ህወሓቶች! የሞተው ሙቶ፤ የቆሰለው ቆስሎ፤ የታሰረው ታስሮ፤ እንዲሰወር የተደረገው ተሰውሮ፤ የተሰደደው ተሰድዶ እና አንገቱን ቀና እንዳያደርግ በህወሓት የስለላ መረብ የታፈነው ዐማራ እድል ይጠብቅ ነበር እንጅ አልጠፋም የሚሉ ብዙ የውስጥ ታዛቢዎች አሉ። በሌላ አነጋገር ህወሓቶች ዐማራውን አልቀበሩትም፤ ሊቀብሩትም አይችሉም፤ አቅም የላቸውም። ሆኖም፤ ወደ ኋላ ዙረን የዛሬ ዓመቱን ሁኔታ ብናንሰላስል፤ አሁን የተከሰተው ስር ነቀል ሰላማዊ ሕዝባዊ አመፅ እንደዚህ በስፋትና በጥልቀት፤ አገር በቀል እና አገር ተከል ሆኖ ይከሰታል የሚል ምሁር ወይንም ልሂቅ አልነበረም። ህወሓት ማንኛውንም መገናኛ ብዙሃን፤ በተለይ የውጩን ባያግብ ኖሮ እና የዓለም መገናኛ ብዙሃን ትኩረት ቢሰጠው ኖሮ እነደዚ ጥበበኛ የሆነ ባለ ብዙ ዘርፍ ሰላማዊ ሕዝባዊ ዐመጽ የትም አገር አልተካሄደም። ለምሳሌ፤ ከቤት ቁጭ ብሎ አልገዛም ማለት፤ አንዱ ሌላውን መደገፍ፤ የኢኮኖሚ እገባ፤ አንዱ ቦታ ዝም ሲል ሌላው መነሳት፤ የጎበዝ አለቃዎች እንዲመሩ መመራረጥ፤ በኮሚቴ መስራት፤ የአካባቢውን አስተዳደር ለመለወጥ መቻል አስደናቂ ነው። የኢኮኖሚው እገባ ዘመቻ አገር አቀፍ ቢሆን ጠቅላላ ኢኮኖሚው ይናዳል።

የኢኮኖሚው እገባ በጎንደር፤ በደብረ ታቦር፤ በባህር ዳር፤ በደብረ ማርቆስና በሌሎች ከተሞች በተከታታይ ሲካሄድ ቆይቷል። የኦሮሞው ሕዝብ ከSeptember 6-September 12, የጠራው የኢኮኖሚ እገባ ከተሳካ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። የኢኮኖሚውን እገባ ዘመቻ ያዘጋጁት የኦሮሞ ወገኖቻችን የሰጡት ማሳሰቢያ እንዲህ ይላል። “የገበያ ማቆም አድማ በመላው ኦሮሚያ ነገ ጷግሜ 1 እንደሚጀምር አስቀድመን መግለጸችን ይታወቃል።፡ ይህ አድማ እስከ መስከረም ሁለት ይቀጥላል። በዚህ ኣድማ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ክልሎች ለሽያጭ እቃዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ማስገባት ክልክል ነው። እቃዎችን ጭነው በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም አቀናጆች አስታውቀዋል። የመኪና ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎች እና ነጋዴዎች ይህንኑ አውቀው ይህን የአድማ ወቅት በማክበር ለህዝብ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ እና ንብረታቸውንም ከውድመት እንዲያድኑ ደግመን እናሳስባለን።” ይህ ከባድ ማሳሰቢያ ነው። የአማራውና የኦሮሞ የኢኮኖሚ እገባ ዘመቻ የተያያዘዘ እና ተከታታይ መሆኑ ውጤቱን ያጠናክረዋል የሚል ግምት አለኝ።

እርግጥ ለድሃው ሕዝብ እገባ ሲደረግ ቤተሰቦች ሊጎዱ ይችላሉ። ዋጋ ይከፈልበታል ማለት ነው። ዋጋ ያልተከፈለበት ዲሞክራሳዊ ለውጥ ስለሌለ ይህን የቅርብ ጊዜ ጉዳት ከዘላቂው ጥቅም ጋር ማመዛዘን ይቻላል። ለዚህም ተጠያቂ መሆን ያለበት የዐማራው ወይንም የኦሮሞው ሕዝብ አይደለም። አይነ ጭፍኑ፤ የሕዝብን ሰላማዊ አመፅ በመትረየስ፤ በአልሞ ተኳሾች፤ በሄሊኮፕተር አስፈላጊ ከሆነ ልክ እንደ ሊቢያ በጦራ አውሮፕላን እቋቋመዋለሁ ብሎ የዘመተው ህወሓት ነው። በአሁኗ አፍሪካ፤ በራሱ ሕዝብ ላይ ጦርነት የከፈተ ኃይል ህወሓት ብቻ ነው። የተዋሰው ስልት ከሊቢያ፤ ከሶሪያ፤ ከኢራክ (በከርዶች ላይ) ጋር ተመሳሳይ ነው። የእነዚህ አገሮች የመጨረሻ እድል ምን እንደሚሆን አሁን ያለውን አሰቃቂ ሁኔታ ማየቱ ብቻ ይበቃል። የራሱን ሕዝብ የጨረሰ መንግሥት በሰላም የመቆየት ዋስትና የለውም።

“የጦር መስኮች”

ምንም የማይካደው፤ ዛሬ የኦሮሞውና የዐማራው ክልሎች “የጦር መስኮች ሆነዋል (Horn Spiegel, September 4, 2016 and Africa Confidential, August 27, 2016). በቅርቡ የህወሓቱ የመከላከያ ኤታ ማጆር ሹም እና የህወሓት ቀንደኛ አባልና ደጋፊ ጀኔራል ሳሞራ ዩኑስ የጎንደርን ሕዝብ ለማንበርከክ ለሚደረገው ዝግት ቅድመ ሁኔታውን ለማመቻቸት ወደ ጎንደር ሄዶ የፓርቲውን አቋም ገልጿል። በጨዋነቱ የሚታወቀው የጎንደር ሕዝብ ይህን የአጋዚ አለቃ ካዳመጠ በኋላ ከተነሳበት ዓላማ ወደ ኋላ እንደማይል፤ ማለትም እንደማይንበረከክ በማያሻማ ደረጃ ነገረው። መልእክቱ “የፈለጋችሁትን እርምጃ ውሰዱ” የሚል ነው። ጀኔራሉ ከጎንደር ወደ ባህር ዳር መሄዱ ይታወቃል። በባህር ዳር ዐማራ ሕዝብ የሚሰጠው መልስ ተመሳሳይ ይሆናል። በእኔ ግምትና እምነት፤ የህወሓት አጋዚ አልሞ ተኳሾች የዐማራ ዘር የማጥፋት ዘመቻ በጎንደር፤ በደብረ ታቦር፤ በባህር ዳር፤ በደብረ ማርቆስ እና በሌሎች ከተሞችና በገጠር እያካሄደ ሕዝቡን ለማባበል የሚደረገው ጥረት ዋጋ ቢስ ነው። በገፍና በጭካኔ እየገደሉ “ሰላም እንፈልጋለን” ማለት ሰውን እንደ ደንቆሮ ከማየት አይለይም።

ይህን ክፍል ለማጠቃለል፤
ከላይ እንዳቀርብኩት፤ የዚህ ሃተታ መሰረታዊ ሃሳብ ህወሓት የፖለቲካ፤ የሰራዊት፤ የመሳሪያ፤ የገንዘብ፤ የባጀት፤ የስለላ፤ የዲፕሎማሲ፤ የፖለቲካ የበላይነቱን ኃይልና አቅም ተጠቅሞ ስልጣን ከመያዙ በፊት እና ስልጣን ከያዘ በኋላ በዐማራው ሕዝብ ላይ ያካሄደው የዐማራ ብሄር ማጥፋትና ማጽዳት እና አሁንም በዐማራው ሕዝብ ላይ ያወጀው ጦርነት በዓለም ፍርድ ቤት ያስከስሰዋል የሚል ነው።

ለምን ብለን ብንጠይቅ፦
አንድ፤ በዓለም ሕግ ያስከስሰዋል፤ የተካሄደውና አሁንም የሚካሄደው Deliberate and Silent Genocide ነው፤ ሁለት፤ ኢትዮጵያን ሊያፈራርሳት ይችላል፤
ሶስት፤ የእርስ በርስ ጦርነት በስፋት እንዲካሄድ ያደርጋል፤
አራት፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ቂም በቀልና ጥላቻ ስር ይሰዳል፤
አምስት፤ ለውጭ ጠላቶች መግቢያ ቀዳዳ ይፈጥራል።
የህወሓት ሴራና ድርጊቶች ከጥላቻ አልፎ ከዐማራውና ከኦሮሞው ሕዝብ ላይ የደረሰውን ጭካኔ ግድያና ሌላ በሚመሳሰል ወይንም በሚብስ ደረጃ ለትግራይ ሕዝብ አስከፊ ጉዳት ያመጣል የሚል ግምት አለ። የትግራይ ሕዝብ ኃይማኖተኛ፤ መንፈሳዊ፤ አገሩን ኢትዮጵያን አክባሪና ተቀባይ መሆኑን ታሪክ መዝግቧል። ሆኖም በዐማራው ሕዝብ ላይ የተካሄደውንና የሚካሄደውን የዐማራ ዘር የማጥፋት ዘመቻ ምንም ትኩረት አልሰጠውም፤ የሚሰጠውም አይመስልም። ከትኩረት አልፎ በዓለም የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ለመክሰስ የሚያስችል መረጃና ሰነድ መኖሩን አልተቀበለውም።

ጨፍጭ የሚል መብት የት አገር ይታያል፤ ተደርጓል?

የባሰውን ይባስ ብሎ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የወያኔ አጋዚ ጦርና የፌደራል ፖሊስ ልዩ ግብረ ኃይል የጎንደርን ዐማራ ሕዝብ እንዲደመሥስ ሙሉ የጭፍጨፋ መብት ሰጥቶት በምእራብ ጎንደር ተሰራጭቶ በተጠንቀቅ ይገኛል። ይህ ዐማራውን ኢላማ ያደረገ የጨፍጭፍ አዋጅና ትእዛዝ የሚያስከትለው እልቂት ህወሓትን ብቻ ሳይሆን ጠቅላይ ሚንስትሩንም በተባባሪነት (ከታች ቁጥር ሶስት) በሃላፊነት ያስጠይቀዋል።
ለማጠናከር፤ መጀመሪያ ስለ ዘር ማጥፋት እና እልቂት ወንጀል የተባበሩት መንግሥታት ያጸደቀውን ሕግ Convention on the Prevention and Punishment of the Crime of Genocide ላቅርብ፤
አንቀጽ ሁለት ጀኖሳይድን እንዲህ በሚል ይተረጉመዋል። “አንድ መንግስት ወይንም ፓርቲ ወይንም የኃይማኖት ወይንም የብሄር ቡድን ሌላውን ቡድን ወይንም ዘር፤ ወይንም ብሄር፤ ወይንም ኃይማኖት በከፊልም ሆነ በሙሉ ለማጥፋት የሚደረግ ድርጊት ነው ይልና የሚያካትታቸውን ክፍሎች ወይንም ዘርፎች እንደሚከተለው ይዘረዝራቸዋል፤
(a) የአንድን ክፍል ወይንም ቡድን አባላት መግደል፤
(b) በቡድኑ ላይ ከፍተኛ የአካል ወይንም የአእምሮ ጉዳት ማድረስ፤
(c) ሆነ ብሎ ኢላማ በተደረገበት ቡድን ወይንም ሕዝብ ወይንም ብሄር ወይንም የኃይማኖት ተከታዮች ላይ አካላቸውን፤ ሰውነታቸውን እና ሰብእነታቸውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የሚጎዱ ሁኔታዎችን መፍጠር፤ ህይወታቸውን ሲኦል ማድረግ ማለት ነው፤
(d) ኢላማ የተደረገበትን ቡድን ወይንም ዘር ወይንም ብሄር ወይንም ኃይማኖት አባላት በልዩ ልዩ ዘዴዎች እንዳይወልዱ (እንዳይባዙ፤ ተተኪ ትውልድ እንዳይኖራቸው) ማድረግ፤ እና
(e) ኃይልን፤ ጫናን እና ሌላ ዘዴን ተጠቅሞ ኢላማ የተደረገበትን ሕዝብ ልጆች ለሌሎች ማስተላለፍ።
በዚህ ዓለም ባጸደቀው ሕግ መሰረት አንቀጽ ሁለት፤ ንኡስ አንቀጽ ሶስት ወንጀል ናቸው ተብለው የሚታወቁት የሚከተሉት ተግባሮች ናቸው ይላል።
(አንድ) Genocide (ዘር ወይንም ብሄር ወይን ኃይማኖት ማጥፋት)፤ (ሁለት) ከላይ በአንድ የተቀመጠውን ለማካሄድ የሚደረግ ሴራና እቅድ፤
(ሶስት) ቀጥታ በሆነ ደረጃ አንድን ዘር ለማጥፋት ደጋፊ የሆነውን ውይንም ሊሆን የሚችለውን ሕዝብ የመቀስቀስ ሴራና ስኬታማ ለማድረግ የዝግጅት ስራ፤

(አራት) አንድን ብሄር ወይንም ዘር ለማጥፋት የሚደረግ ሙከራ፤ Attempt to commit genocide; እና (አምስት) ኢላማ የሆነውን ዘር ወይንም ብሄር ለማጥፋት የሚደረግ ተባባሪነት።
ህወሓትና ተባባሪዎች በዐማራው ሕዝብ ላይ ያካሄዱትና አሁንም የሚያካሂዱት የዘር ወይንም የብሄር ማጥፋት ስራዎች ከላይ የቀረቡትን መስፈርቶች ሁሉ ያሟላሉ። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ተደርጎ የማያውቅ የአንድ ብሄር ወይንም ዘር የማጥፋት ወንጀል ለተከታታይ ዘመናት ለዓለም የወንጀል ፍርድ ቤት ይቀርባል የሚል ግምት አለኝ። ምክንያቱም የእልቂቱ ብዛትና ስፋት ከቀድሞው ዩጎስላቪያ፤ ቱርኮች በአርመኖች ላይ ካደረጉት ወንጀሎች አያንስም የሚሉ ጥናቶችና መረጃዎች ስላሉ ነው። ይህ ትንተና በከፊልም ቢሆን መረጃዎችን መሰረት አድርጎ አንባቢዎች ፍርዱን እንዲለግሱ ይጠቁማል። የባሰ እልቂት ከመካሄዱ በፊት ዓለም-አቀፍ በሆነ ደረጃ ድምጻቸውን ለመንግሥታት እንዲያሰሙ ያሳስባል።
ይህ እንዳለ ሆኖ፤ ችግሩ የትግራይ ሕዝብ መገንዘብ የሚኖርበት ከራሱ አብራክ ወጣን፤ ለትግራዩ ሕዝብ ተቆርቋሪ ነን የሚሉት ህወሓቶች ለህሊና የማይገዙ፤ የነገውን የማያስቡ፤ ታሪካቸውን የካዱ፤ ጨካኝና ከአውሬ የባሱ፤ ምንም ይሉኝታ የማይሰማቸው ሆነው ይገኛሉ። የንጹህ ሰው ደም እንደ ድኩላ ደም ነው ብለው የሚቀበሉ ህወሓቶች ምን ሊባሉ ይችላሉ? ከትግራይ ክልል ወጥተው በዐማራውና በኦሮሞው ክልሎች ኃብት ሰብስበው ለሌላው ነዋሪ ሕዝብ ኑሮ የማያስቡ ፍጡሮች ናቸው። ዐማራው በሚኖርበትና በሚሰራበት ቦታ ሁሉ የአማራውን ሰብእነት፤ ቀልብ መግፈፍ፤ ማዋረድ መግደል እንደ ጉብዝና የሚቆጥሩ ሆነው ይታያሉ። ጎንደር ሰፍረው እና ኃብት ይዘው፤ ትርፍ እያተረፉ ጎንደሬውን አዋርደውታል። አሁን የጎንደርን አማራ ለመጨፍጨፍ ሙሉ ዝግጅት አድርገው ወደ ተጋባር ሊዞሩ ተዘጋጅተዋል። እስካሁን የጨፈጨፉት ወጣት ትውልድ አልበቃቸውም ማለት ነው።
ህወሓቶች እና ደጋፊዎቻቸው ልክ እንደ ዱሮ ኮሚውኒስቶች ኃይማኖተ-ቢስ ናቸው። ኢትዮጵያ ሶስት ኃይማኖቶች– ክርስትና፤ ሙስልምናና ጁዴይዝም–የሚስተናገድባት አገር ናት። እነዚህ ሶስት ኃይማኖቶች The Golden Rule (ወርቃማውን) የግብረገብነት መመሪያ የተቀበሉ ናቸው። “ሌሎች ሊያደርጉልህ የምትወደውን አንተም አድርግላቸው” የሚለውን ማለቴ ነው። ይህን መንፈሳዊ መርህ ከተቀበልን፤ “ሌሎች ሊያደርጉብህ የማትፈልገውን አንተም አታድርግባቸው” የሚለውን የመቀበል ግዴታ አለብን።
የትግራይን ሕዝብ፤ በተለይ የትግራይን ምሁራን፤ ልሂቃን፤ “ተቃዋሚ ፓርቲዎች” እና መንፈሳዊ መሪዎች የምጠይቀው ይኼን ወርቃማ ስነምግባር የተቀበሉ ከሆኑ የዐማራና የኦሮሞ ሕዝብ፤ በተለይ የዐማራው ሕዝብ ግልጽ የሆነ የዘር ማጥፋት ዘመቻ በወያኔው አጋዢና የፌደራል ፖሊስ ሲካሄድበት እያያችሁ ለምን ዝም አላችሁ? የተቀበላችሁ፤ ያስተናገዳችሁ የዐማራ ሕዝብ ወጣት ልጆች፤ ህጻናትን ጨምሮ ከራሳችሁ አብራክ በወጡ ህወሓቶች ሲጨፈጨፉ ለምን ልጆቻችሁን ተው! ይህ አያዋጣም ! አላላችሁም? ህወሕት የፈጠራ ወሬ መሰረት አድርጎ ከፈጠረው በሬ ወለደ ታሪክ ውጭ፤ አንድም የትግራይ ተወላጅ ሳይደበደብ፤ ሳይቆስል፤ ሳይደማ፤ ሳይሞት ለምን ከጎንደር ወጣችሁ እና ለምን ሃቁን አትናገሩም? ህወሓት እናንተን እንድትጠሉ፤ ሕዝቡ እንዲጠራጠራችሁ ካደረገ እናንተስ ራሳችሁን ከዚህ ጠባብ ብሄርተኛና አፋኝ ቡድን ነጻ ለማውጣት ለምን እንደ ዐማራውና እንደ ኦሮሞው ሕዝባው አመጽ አትጀምሩም?

ከላይ የቀርቡት ጥያቄዎችና ሃሳቦች እንዳሉ ሆነው የዐማራው ሕዝብ ስር ነቀል እና የተሳሰረ ራስን የማዳን እንቅስቃሴ እንዲቀጥል በሁሉም አቅጣጫ ድጋፍ የመስጠቱ ኃላፊነት የእያንዳንዱ የህወሓት ተቃዋሚ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ነው። በዐማራው ሕዝብ ላይ እልቂት እየተካሄደበት ነው። ይህ እልቂት የሁላችንም እልቂት ነው ብለን የምንነሳበት ጊዜ አሁን እንጅ እልቂቱ ከተካሄደ በኋላ አይደለም።
ይቀጥላል

አባሪውን ሰነድ ይመልከቱት

አባሪ፤ የሰማእታት ዝርዝር (የታወቁት ብቻ) List: Oromo and Amhara Martyrs Partial List as of September 1, 2016
Notation
i) Sources (Various)
ii) Agazi refers to a special hit squad established by the TPLF and commandeered by
high level Tigrean officers
iii) More than 90 percent of those murdered are in their 20s.
iv) Oromo and Amhara are losing their future engineers, scientists and leaders at a
fast rate
v) The list is incomplete; some observers believe that the number killed is in the thousands not in the hundreds
vi) 50 young people were murdered in the Amhara region in two days
vii) Agazi is systematic and capable of hauling and burying those killed in mass graves
hidden from public space at locations hard to find immediately

Oromo and Amhara Nationals: names, gender, age, locality, Zone and military/police/security unit involved
A. List of Oromo Martyrs
1 Abbuu Muummee M 17 Arsii Ticho- Agazi
2 Abdallaa Mohammed M – East Harageh Qobo Agazi
3 Abda Jiloo M 24 West Arsii Asasa Agazi
4 Abdaa Hasanoo M 31 West Arsii Asasa Agazi
5 Abdii Daawud M – East Harageh Kombolcha Police
6 Abdii Jamal Suraa M 27 Arsii Heraroo Agazi
7 Abdallaa Kadir M 26 Arsii Baalee Roobee Agazi
8 Abdisaa Gamachu M 23 West Arsii Shashamane Agazi
9 Abdisaa Tolaa M 19 West Arsii Asasa Agazi
10 Abdoo Tolaa Dibaba M 20 Arsii Dheraa Agazi
11 Abdulsalam Milkeessaa M – East Harageh Qarsa Agazi
12 Abdunasir Ture Xulloo M 24 Baalee Waabee Agazi
13 Abdurraa Caabii M 26 West Arsii Asasa Agazi
14 Abduu Rashaad M 19 Baalee Waabee Agazi
15 Abdusalam Ahme/shekko M – East Harageh Haroo Maayaa Police 16 Abdushakuur Dhaqqabaa M – East Harageh Awadayi Agazi
17 Afandii Mohammed M – East Harageh Haroo Maayaa Agazi
18 Ahmed Aman M West Arsii Adaba Agazi
19 Ahmed Girboo M – East Harageh Quubsaa Agazi
20 Ahmed Hakim H.Heddo M West Arsi Adaba Agazi
21 Ahmed Hussein M 25 West Arsii Qore Agazi
22 Ahmed Rahiman Umaro M West Arsii Adaba Agazi
23 Ahmed Rauf Amana M West Arsii Adaba Agazi
24 Aliyyii Jaqon Hasen M 19 Arsii Gobessoo Agazi
25 Aliyyoo Said Aloo M 22 West Arsii Hajee Agazi
26 Alii Simboo M 26 West Arsii Shashamane Agazi
11
27 Amaan Bilbiltu Tolaa M 28 West Arsii Asasa Agazi 28 Amaan Kamal Usman M 57 Arsii Sagure Agazi
29 Amin Aburroo Turee M 30 Arsii Seeruu Agazi http://www.Qeerroo.org qeerroo2011@gmail.com
30 Amir Zeynu Awal M 19 Arsii seeruu Agazi
31 Awwal Tolaa Dibabaa M 20 West Arsii Adaba Agazi
32 A.Ra’uf Sh/Hasen M – West Arsii Adaba Agazi
33 A. Razaq Mahamed M – West Arsii Adaba Agazi
34 Amanu’el Girmaa M – East Wollega Naqamtee Boordii Agazi 35 Awol Haji Bulina M 14 West Arsii Dodola Agazi
36 Awwal Amaan M 32 Baalee Diinshoo Agazi
37 Awwal Kadir Mohammed M 25 Arsii Bayimaa Qeransaa Agazi 38 Awwal Kadir M 18 Arsii Sagure Agazi
39 Awwal Kadir Usman M 45 Arsii Boqoji Agazi
40 Awwaluu Kadir M 12 West Arsii Asasa Agazi
41 Bahaar Abdii M – East Harageh Qobo Agazi
42 Biraanuu Rabbirraa M – East Wollega Giddaa Ayyanaa Police 43 Buxoo Mohammed M – west Hargeh Asbot Police
44 Dassaalee Guddataa M – West Harageh Hirnaa Police
45 Eliyas Teshome M – West Shawa Bakkoo Police
46 Faahmii kadir F – East Harageh Adellee Police
47 Farahan Mohammed M – Harar Harar Police
48 Falmataa Hajii Dibuu M 15 Arsii Agazi
49 Firaol Ogina M – East Wollega Najo Police
50 Gabii Nabii M 25 Arsii Muneessaa Agazi
51 Dr.Gebeyehu Jalata M – East Wollega Nakemet Agazi
52 Hadhaa Shammee F – East Harageh Awadayi Agazi
53 Hasan Dirrii Adam M 29 Arsii Shirka Agazi
54 Heydar Ture M 27 Arsii Habee Agazi
55 Heeydar Umar Aman M 38 Arsii Chobeessaa Agazi
56 Huseen Abdo Hajii M 25 Arsii Hayyoo Agazi
57 Huseen Hajii M 25 West Arsi Asasa Agazi
58 Huseen Tashii M 25 Arsii Ticho qeransaa Agazi
59 Huseen Amaan M 30 West Arsii Kofale Agazi
60 Hora Fajiso M – East Shawa Adami Agazi
61 Ibsaa Ibrahim Muummee M – East Harageh Awadayi Agazi
62 Ibsaa Ibrooshe M – Dire Dhawaa Dire Dahawaa Agazi
63 Ibsaa Jamal M 23 West Arsii Kofalee Agazi
64 Ibrahim Jamal M 22 Arsii Zuway Agazi
65 Idiris Kade M West Arsii Adaba Agazi
66 Jamal Abdallaa M – West Harageh Hirnaa Agazi
67 Jamal Dirmamoo M 18 Hamdoo Agazi
68 Jamal Haruun M – West Harageh Hirnaa Agazi
69 Jamal Hasen M West Arsii Adaba Agazi
70 Jamal Mohammed M – East Harargeh Awadayi Agazi
71 Kadijaa Ahmad F 20 West Arsii Asasa Agazi
72 Kadir Abdurhamaan M – East Harageh Awadayi Agazi 73 Kadir Mohaammed M – East Hargeh Awadayi Agazi 74 Kamal Abdulqadiir M 26 West Arsii Asasa Agazi
75 Kamal Kadir Adam M 18 Hurufaa Agazi http://www.Qeerroo.org qeerroo2011@gmail.com
76 Keeyruu Awwal Said M 20 West Arsii Adaba Agazi
77 Kidane Garoma M – Kake Police
78 Maammee Saala Huseen M 30 Habee Police
79 Mahaadii Usman M – East Harageh Dhangaggoo Police 80 Mahmuush Biraanuu M – Waliso Walisoo Police
81 Melese Teshome M – East Wollega Naqamtee 05 Agazi 82 Misraa Kamal F 18 Arsi Ajee Agazi
83 Mohammed Abdellaa M 30 Baalee Dinshoo Agazi
84 Mohammed Adam M 22 West Arsii Kofale Agazi
85 Mohammed Husen Hebo M West Arsii Adaba Agazi
86 Mohammed Ibroo M – West Harageh Hirnaa Police
87 Mohamed Isma’el M West Arsii Adaba Agazi
88 Mohammed Sanii Siraj M 27 Baalee Roobee Agazi
89 Mohammed Yuyyaa M – East Harageh Awadayi Agazi
90 Muhammed Adam Ali M 22 West Arsii Dodola Agazi
91 Muhamed Hasan Dawano M 31 West Arsii Asasa Agazi
92 Muhamed Kade M West Arsii Adaba Agazi
93 Muhamed Sa’id M West Arsii Adaba Agazi
94 Sh/Muhamed Said M 40 West Arsii Asasa Agazi
95 Muktar Ibrahim M – West Arsii Adaba Agazi
96 Munir Abdoo Nashaa M 20 Arsii Seeruu Agazi
97 Mustafa Yuna M – West Arsii Adaba Agazi
98 Musxafaa Muhamednur M West Wollega Gimbii Police
99 Musxafaa Sadiq M 19 Arsii Diksiisa Agazi
100 Naasiruu Adam M – West Harageh Asaboot Agazi 101 Nasiroo Abdallaa M 25 West Arsii Kofale Agazi 102 Naasir Huseen Aloo M 20 Baalee Dooyyoo Agazi 103 Nuuraddin Nasha Adam M 22 Baalee Baalee Agazi 104 Qaasim Mohammed M 21 Arsii Edoo Agazi
105 Rashid Indris M – East Harageh Awadayi Agazi 106 Saamiyaa Ahmed F – East Harageh Awadayi Agazi 107 Saladhiin Shakiim M – East Harageh Qobo Agazi 108 Sardaa M – West Shewa Mogor Police
109 Seeyfaddiin Aman Kadir M 19 Arsii Shirka Agazi 110 Shamsi Qaadii Tolaa M 28 Arsii Zuway Agazi
111 Sufiyaan Aminoo M 30 West Arsii Nagallee Agazi
14
112 Seyifu Husen M West Arsii Adaba Agazi
113 Seeyfuu Isadiir Aloo M 27 Arsii Sagure Agazi
114 Sisay Birru Tolaa M West Arsii Dodola Agazi
115 Taarikuu Dabalaa M – East Wollega Naqamte Agazi
116 Taganee Mulatu Kennaa M 20 West Arsii Shashamanee Agazi
117 Tajudin Kadiro M West Arsii Adaabbaa Agazi
118 Tamaam Tolaa Biluu M 30 West Arsii Shashamane Agazi
119 Tarii Huseen Mohammed M 32 Arsii Roobee Agazi
120 Tolaa Abdii Kenna M 20 Arsii Dheraa Agazi
121 Tolaa Waariyoo M 28 Arsii Ticho Agazi
122 Tolasaa Girma Argaa M 22 West Arsii Shashamanee Agazi 123 Tolasa Wakjira M – East Wollega Leeqa Dullacha Agazi 124 Tolchaa Nasir Filmo M 25 Arsii Seeruu Agazi
125 Tunaa Mammaa Hamid M 35 West Arsii Asasa Agazi
126 Turaa Argoo M 18 Arsii Ticho Agazi
127 Umar Abdo Adam M 20 Arsii Gobessoo Agazi
128 Usman Xasallaa M 29 West Arsii Asasa Agazi
129 Wakjira Terefa M – East Wollega Leeqa Dullacha Police 130 Yasiin Waliyyii M 16 West Arsi Dodolaa Agazi
131 Zeeytunaa Abdi Jilo F 17 Arsii Seeroftaa Agazi
132 Zeynaba Mohammed F 22 Baalee Dinshoo Agazi
133 Zeyaad Aliyyii Suraa M 22 West Arsii Asasa Agazi
134 Ziidan Mohammed M 18 Arsii Edoo Agazi . Some pictures that shows the brutality of Ethiopia’s armed forces https://qeerroo.files.wordpress.com/…/partial-list-of-oromo…

B. List of Amhara Martyrs
የሰማ እታት ስሞች እና የተገደሉበት ቦታ በከፊል ስማቸው ያልታወቀ
1. የደምሰው ወልደማርያም ልጅ (አርማጭሆ)
2. የበሬ ፀጋየ ልጅ (አርማጭሆ)
ስማቸው የታወቀ
1. እድሜአለም ዘዉዱ እድሜ (27) (ባህርዳር) 2. ገረመዉ አበባዉ እድሜ ( 25) (ባህርዳር) 3. ተፈሪ ባዩ እድሜ (16) (ባህርዳር)
4. ሰለሞን አስቻለ እድሜ (25) (ባህርዳር)
5. ሙሉቀን ተፈራ እድሜ (27) (ባህርዳር)
6. አደራጀዉ ሃይሉ እድሜ (19) (ባህርዳር) 7. አስማማዉ በየነ እድሜ (22) (ባህርዳር)
8. ታዘበዉ ጫኔ እድሜ (21) (ባህርዳር)
9. አስራት ካሳሁን እድሜ (24) (ባህርዳር) 10. የሽዋስ ወርቁ እድሜ (20) (ባህርዳር)
11. ብርሃን አቡሃይ እድሜ (29) (ባህርዳር) 12. ሽመልስ ታየ እድሜ (22) (ባህርዳር)
13. አዛናዉ ማሙ እድሜ (20) (ባህርዳር)
14. ሲሳይ አማረ እድሜ (24) (ባህርዳር)
15. ሞላልኝ አታላይ እድሜ (21) (ባህርዳር) 16. መሳፍንት እድሜ (22) (እስቴ)
17. እንግዳዉ ዘሩ እድሜ (20) (ባህርዳር)
18. ዝናዉ ተሰማ እድሜ (19) (ባህርዳር)
19. ሞገስ ሞላ እድሜ (23) (ባህርዳር)
20. ዋለልኝ ታደሰ እድሜ (24) (ባህርዳር) 21. ይታያል ካሴ እድሜ (25) (ባህርዳር)
22. እሸቴ ብርቁ እድሜ (37) (ባህርዳር)
23. ሞገስ እድሜ (40) (ባህርዳር)
24. አደራጀዉ ደሳለኝ እድሜ (30) (ባህርዳር) 25. አበበ ገረመዉ እድሜ (27) (ጭስ አባይ) 26. ማህሌት እድሜ (23) (ባህርዳር)
27. ተስፋየ ብርሃኑ እድሜ (58) (ባህርዳር) 28. ፈንታሁን እድሜ (30) (ባህርዳር)
29. ሰጠኝ ካሴ እድሜ (28) (ባህርዳር)
30. ባበይ ግርማ እድሜ (26) (ባህርዳር)
31. አለበል አይናለም እድሜ (28) (ደብረ ማርቆስ) 32. አብዮት ዘሪሁን እድሜ (20) (ባህርዳር)
33. አበጀ ተዘራ እድሜ (28) (ወረታ)
34. ደሞዜ ዘለቀ እድሜ (22) (ወረታ)
35. አለበል ሃይማኖት እድሜ (24) (ወረታ)
36. ሰለሞን ጥበቡ እድሜ (30) (ቻግኒ)
37. ፍስሃ ጥላሁን እድሜ (25) (አዲስአበባ)
38. ቅዱስ ሃብታሙ እድሜ (16) (አዲስ አበባ) 39. በረከት አለማየሁ እድሜ (28) (ዳንግላ)
40. ያየህ በላቸዉ እድሜ (30) (ዳንግላ)
41. አለማየሁ ይበልጣል እድሜ (27) (ዳንግላ) 42. በለጠ ካሴ እድሜ (32) (ደብረታቦር)
43. ይህነዉ ሽመልሽ እድሜ (30) (ደብረታቦር) 44. ይበልጣል እዉነቱ እድሜ (24) (ጭስአባይ) 45. ሃብታሙ ታምራት እድሜ (27) (ባህርዳር) 46. ታደሰ ዘመኑ እድሜ (26) (አዴት)
47. ሽመልስ ወንድሙ እድሜ (28) (ቡሬ)
48. አይናዲስ ለአለም እድሜ (24) (ደብረወርቅ) 49. እስቲበል አስረሳ እድሜ (19) (አዴት)
50 ዘሪሁን (ሰሎሜ) ገደብየ (ጎንደር)
51 ባየሁ ጎንደር (ጎንደር)
52 በለጡ መሀመድ (አዘዞ
17
53 እንጀራ ባየ (አዘዞ)
54 የቻፖራ ወንድም (ጎንደር)
55 ግርማቸው ከተማ (ላይ አርማጭሆ)
56 ሊሻን ከበደ (አይባ)
57 መሌ አይምባ (አይባ)
58 አዛነው ደሴ ኩርቢ (አርማጭሆ)
59 አራጋው መለሰ ኩርቢ (አርማጭሆ)
60 ሰጠኝ አድማሱ (ደልጊ)
61 ታረቀኝ ተሾመ (ደልጊ)
62 ሔኖክ አታሎ ደልጊ)
63 ደሴ ደረሰ (53) (ሻውራ)
64 ግርማቸው ሞገስ (ሻውራ)
65 ወርቁ ጠቁሳ ገጠር (ሻውራ)
66 ማማየ አንጋው (ዳንሻ)
67 ፈንታ አህመድ (ዳንሻ)
68 ክንፌ ቸኮል (በአከር)
69 ስሙ ያልታወቀ ፡ደካማ እናት አሉት (ደብረ ማርቆስ ቀበሌ 03)
70 ሲሳይ ታከለ (አርማጭሆ)
71 ማእረግ ብርሃን (ደብረ ታቦር)
72 መምር ተስፋየ ብርሃን (ደብረ ታቦር ቀበሌ 01) 73 ይበልጣል ደሴ (ደብረ ታቦር ቀበሌ 01)
ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በጎንደርና በጎጃም በወያኔ አጋዚ የተጨፈጨፉ ዐማራዎች ስም ዝርዝር (ከላይ ከቀረበው ዝርር ጋር መመሳከር አለበት፤ አንዳንድ ስሞች ተደጋጋሚ ሊሆኑ ይችላሉ)
1. ዕድሜዓለም ዘውዱ
2. ገረመው አበባው 25
3. ተፈሪ ባዩ 16
4. ሰሎሞን አስቻለ 25
5. ሙሉቀን ተፈራ 27
6. አደራጀው ኃይሉ 19
7. አስማማው በየነ 22
27 ባሕር ዳር ባሕር ዳር ባሕር ዳር ባሕር ዳር ባሕር ዳር ባሕር ዳር ባሕር ዳር
18
8. ታዘበው ጫኔ
9. አሥራት ካሣሁን
10. የሽዋስ ወርቁ
11. ብርሃን አቡሃይ
12. ሽመልስ ታዬ
13. አዛናው ማሙ
14. ሢሣይ አማረ
15. ሞላልኝ አታላይ
16. እንግዳው ዘሩ
17. ዝናው ተሰማ
18. ዋለልኝ ታደሰ
19. ይታያል ካሤ
20. እሸቴ ብርቁ
21. ሞገስ 40
22. አደራጀው ደሣለኝ 30 ባሕር ዳር
23. ማኅሌት 23
24. ተስፋዬ ብርሃኑ
25. ፈንታሁን
26. ሰጠኝካሤ28ባሕርዳር
27. ባበይ ግርማ 26 ባሕር ዳር
28. አብዮት ዘሪሁን 20 ባሕር ዳር
29. ሀብታሙ ታምራት 27 ባሕር ዳር
30. ሞገስሞላ23ባሕርዳር
31. ታደሰ ዘመኑ 26 አዴት
32. እስቲበል አስረስ
33. አበበ ገረመው
34. ይበልጣል ዕውነቱ
35. ሰሎሞን ጥበቡ
36. በረከት ዓለማየሁ
19 አዴት
27 ጢስ ዐባይ 24 ጢስ ዐባይ 30 ቻግኒ
28 ዳንግላ
21 ባሕር ዳር 24 ባሕር ዳር 20 ባሕር ዳር 29 ባሕር ዳር 22 ባሕር ዳር 20 ባሕር ዳር 24 ባሕር ዳር 21 ባሕር ዳር 20 ባሕር ዳር 19 ባሕር ዳር 24 ባሕር ዳር 25 ባሕር ዳር 37 ባሕር ዳር ባሕር ዳር
ባሕር ዳር
58 ባሕር ዳር 30 ባሕር ዳር
19
37. ያየህ በላቸው 30 ዳንግላ
38. ዓለማየሁ ይበልጣል 27 ዳንግላ
39. ሽመልስ ወንድሙ 28 ቡሬ
40. አለበል ዓይናለም 28 ደብረማርቆስ
41. ስሙ ገና የሚጣራ ደካማ እናት ያሉት ደብረ ማርቆስ ቀበሌ 03
42. ዓይንአዲስ ለዓለም 24 ደብረወርቅ
43. አበጀ ተዘራ 28
44. ደመቀ ዘለቀ 22
45. አለበል ሃይማኖት
46. መሣፍንት አማራ
47. በለጠ ካሤ 32 ደብረታቦር
48. ይህነው ሽመልስ 30 ደብረታቦር
49. ማዕረግ ብርሃን ደብረታቦር ቀበሌ 01
50. መምህር ተስፋዬ ብርሃን ደብረታቦር ቀበሌ 01
51. ባየሁ ጎንደር
52. የቻፖራ ወንድም ጎንደር
53. በለጡ መሐመድ አዘዞ
54. እንጀራ ባዬ አዘዞ
55. ግርማቸው ላይ አርማጭሆ
56. አዛናው ደሴ
57. አራጋው መለሰ
58. ሲሣይ ታከለ
59. ሊሻን ከበደ
60. መሌ አይምባ
61. ሰጠኝ አድማሱ ደልጊ
62. ታረቀኝ ተሾመ ደልጊ
63. ኖኖክ አታሎ ደልጊ
64. ደሴ ደረሰ 53 ሻውራ
65. ግርማቸው ሞገስ ሻውራ
ወረታ ወረታ
24 ወረታ 22 እስቴ
አርማጭሆ አርማጭሆ አርማጭሆ አይምባ
20
66. ወርቁ ሻውራ
67. ማማየ አራጋው ዳንሻ
68. ፈንታ አህመድ ዳንሻ
69. ክንፈ ቸኮል በአከር
70. ፍሥሃ ጥላሁን 25 አዲስ አበባ
71. ቅዱስ ሀብታሙ 16 አዲስ አበባ
72. ይበልጣል ደሴ
September 6, 2016

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s