የፋሺስት ወያኔ የከፋ ወራዳ ማንነቱና የሚጠብቀው ደሞዙ! [ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው]

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

እንደምን ሰነበታቹህ ወገኖቸ ኢትዮጵያውያን? ወያኔ የደረሰባትን ታላቅ ሽንፈት ውርደትና የፈጸመችውን ኢሰብአዊ ግፍ ለመደበቅ በጎንደርና በባሕርዳር በሌላም የሕዝብ ቁጣ በተቀሰቀሰባቸው የሀገራችን ክፍሎች በተለይም ድረ ገጾችን (Websites) የመጎብኛውን፣ የመልዕክት መላኪያ መቀበያውን የዐውደ መረብ (Internet) አገልግሎት ይሄው እስከዛሬም ሙሉ ለሙሉ በማጥፋቷ ፍጹም ተራርቀን ቆየን፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ ጽሑፍ ወደናንተ መድረስ በነበረበት ጊዜ ሳይደርስ ቀርቷል፡፡  አዲስ አበባ አይደለሁም ያለሁት፡፡ ደኅንነቴ አሳስቧቹህ “ምን ሆኖ ይሆን የጠፋው?” ብላቹህ ለተጨነቃቹህልኝ ወገኖቸ ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋናየን አቀርባለሁ እግዚአብሔር ያስባቹህ እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!

በዚህ ጽሑፍ ላይ ያነሣኋቸውን ነጥቦች በጥሞና እንድትመለከቷቸውና እንድታስተጋቧቸውም እሻለሁ፡፡ ጽሑፉን የጻፍኩት በኮምፒውተር (በመቀምር) ሳይሆን በተንቀሳቃሽ ስልኬ (መናግሬ) ነውና ምናልባት አንዳንድ ችግር ካጋጠመ ይቅርታ! መልካም ንባብ፦

የወያኔ አንድ የሚጠቀስለት ልዩ ብቃቱ ምን እንደሆነ ታውቃላቹህ? አቅሙ ሸንበቆ እንደሆነና በራስ መተማመን የሚባል ነገር ጨርሶ የሌለው መሆኑን ጠንቅቆ ማወቁ ነው፡፡

ይሄንን በማወቁም ከበረሃ ጀምሮ ለአንዲት ቀንም እንኳ ብትሆን በወንድ ደንብ፣ በጀግና ደንብ፣ በአርበኛ ደንብ የሀገርንና የሕዝቧን ጥቅም ታሳቢ በማድረግ ታግሎ፣ ተዋግቶ፣ አጥቅቶ ወይም ተከላክሎ አያውቅም፡፡ እንኳን ሊሞክረው ይቅርና ከናካቴውም አስቦት አያውቅ፡፡

በዚህ ምክንያት ይሄንን ያለበትን የደካማነት ክፍተት ለመሙላት፣ ነውረኛ ጥቅሙን ለማስጠበቅ፣ ዕኩይ የጥፋት ዓላማውን ለማሳካት የሀገራችንና የሕዝባችን ጠላት የሆኑ ሀገራትን ድጋፉ አድርጓል፣ ፈጽሞ ለድርድር የማይቀርቡ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በመሸቃቀጥና አሳልፎ በመስጠት ወራዳ ጥቅሙን ማስከበሪያ አድርጓል፣ የሀገሪቱንና የዜጎችን ብሔራዊ ክብርን ኩራትን ማንነትንና ሉዓላዊነትን አስደፍሯል አዋርዷል ወዘተርፈ.

ወያኔ “እንዲህማ ካደረኩ የሀገር ክህደት ፈጸምክ፣ ፈሪ! ቅዘናም! ጥጥ ልብ! ወራዳ! ባንዳ! እባላለሁ” የሚል የሞራል (የቅስም) ጥያቄ ስሜትና ሥጋት ቅንጣትም ታክልም እንኳ ብትሆን አይሰማውም፡፡

ወያኔ በዚህ ወራዳና ነውረኛ፣ በእኛ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተጠላና እጅግ የተናቀ ማንነቱ የተነሣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ፈጽሞ ተቀባይነት እንደማያገኝና እንደማይታገሰውም ስለሚያውቅ እሱ ከሱዳንና ከልሎች ሀገራት ያገኝ የነበረውን ጥቅምና ሁለንተናዊ ድጋፍ የኢትዮጵያ ሕዝብም “ከፋኝ!” ብሎ መብቱን ለማስከበር ለመታገል በሚያስብበት ጊዜ ይሄንን ዕድል ፈጽሞ እንዳያገኝ ለማድረግ ስር በሰደደ በእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የአህያ አስተሳሰቡ በመገፋት የሀገሪቱን ሰፋፊ መሬት ጨምሮ ሌሎች ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን አሳልፎ በመስጠትና በመደለያነት በማቅረብ ጎረቤት ሀገራት በሙሉ ለመታገያ ተገን እንዳይሰጡን፣ መሸሻ መሸፈቻ እንዳናገኝ፣ ሕዝባችንንም በዘር በሃይማኖት በመከፋፈል አንድነት ፈጥሮ እንዳይነሣ አድርጎን ቆይቷል፡፡

ምክንያቱም ከላይ እንዳልኳቹህ ወያኔ በጀግና ደንብ፣ በአርበኛ ደንብ፣ በወንዶች ደንብ፣ በኢትዮጵያዊያን ደንብ፣ በጨዋነት ክብርንና ኩራትን ጠብቆ የመፋለም አቅም ልብ ወኔና ቁርጠኝነት የላትማ! ማንነቱ ባሕሉ ወጉ ሥርዓቱ የላትማ! ሱሪይቱን አልታጠቀቻትማ! አቅሟ ሸንበቆ ነዋ! ማንም ቢሆን ግድ የላትም ብቻ ግን የምትደገፈው ከሌላት ትወድቃለቻ!

እናም እንዲህ እንዲህ እያደረገች አንድ ጀንበር ሊቆይ አይችል የነበረውን ዕድሜዋን ሩብ ክ/ዘ ያህል ማራዘም ቻለች፡፡ ነገር ግን ይህ ወያኔ “እስከፈለኩበት ዘመን ድረስ ያዘልቀኛል” ያለችው ነውረኛና ወራዳ የፈሪ ዘዴዋ የአገልግሎት ዘመኑን በመጨረሱ በወያኔ ሸፍጥ መሸሻ መሸፈቻ እንደሌለው ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የትም ሔዶ መሸፈት ሳያስፈልገው በያለበት ገንፍሎ በመውጣት ከዚህ በኋላ ወያኔን መሸከም እንደማይፈልግ እየገለጸ ይገኛል፡፡

እንደሚታወቀው የዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ መነሻ በኦሮሞ ወገኖቻችን በኩል፦ ሕገመንግሥታዊ መብት ጉዳይ ሲሆን በአማራ በኩል ደግሞ፦ የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ሕገመንግሥታዊ ጥያቄ ነው፡፡ እያደር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ የደረሰበት ግፍና በደል ልክ የለውምና ሕዝባዊ ተቃውሞው ሀገር አቀፍ ሆኖ ፀረ ወያኔ መልክና አቋም ያዘ፡፡

ከዚህ ቀደም በሁለቱም ርእሰ ጉዳዮች በሰፊው ብየበታለሁ፡፡ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን በተመለከተ አንድ ግርም የሚለኝ ነገር ቢኖር ግን፦ ወያኔ እንደሚለው “ወልቃይትን ወደ ትግራይ እንዲከለል ያደረኩት ሕገመንግሥቴ ቋንቋንና ብሔረሰብን መሠረት ያደረገ የራስ ገዝ (የፌዴራል) የአሥተዳደር አከላለልን ሥርዓትን መሠረት ያደረገ ስለሆነ ነው” ይላል፡፡ ይሄም የሚሆነው በሕዝብ ፍላጎት ፈቃድና ይሁንታ መሆኑን አስምሩልኝ፡፡ ወያኔ ወልቃይትን ወደ ትግራይ ሲከልል ግን የወልቃይትን ሕዝብ ፈቃድ ፍላጎትና ይሁንታ ጠይቆና አግኝቶ አልነበረም ወልቃይትን ወደ ትግራይ የከለለው፡፡ ይሄ አንዱ ውንብድና ነው፡፡ ሌላውና የሚገርመው ግን ከወልቃይቴዎች ሁሉም ባይሆኑም ትግርኛ ተናጋሪ የሆኑ እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ትግርኛ ተናጋሪዎቹ “ትግርኛን እንናገር እንጅ ማንነታችን ግን አማራ ነው!”  እያሉ ወያኔ ወልቃይትን የትግራይ ለማድረግ የሚረዳው ታሪካዊ መረጃ እንደሌለው ጠንቅቆ ያውቃልና ትግርኛ መናገራቸውን ምቹ ምክንያት አድርጎ መሬቱን ለመውሰድ ስለፈለገ ወደ ትግራይ ሊከልላቸው ቻለ፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ችግሩ፤ ምክንያቱም ቋንቋ በመናገር ከሆነማ የሌላ ብሔረሰብ ተወላጅ ሆኖ ግን አማርኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋው የሆነ ምናልባትም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ከፊል የሚሆን አለና እነዚህ ዜጎችም “አማራ ናቸው!” ይባሏ!!!

ዋና መሥፈርቱ ቋንቋ ከሆነ ታዲያ ቅማንቶች ቋንቋቸው አማርኛ ሆኖ እያለ እንዴት የራስ ገዝ አሥተዳደር ሊፈቀድላቸው ቻለ? ወልቃይቶች አማርኛ ተናጋሪ ቢሆኑም ትግርኛ ይናገራሉና “ትግሬ ናቸው!” ተብለው ወደ ትግራይ እንዲከለሉ ከተደረገ ምነዋ ታዲያ ቅማንቶች ቋንቋቸው አማርኛ በመሆኑ “አማራ ናቸው!” ተብለው በአማራ እንደተከለሉ እንዲቀሩ አልተደረገ???

ቅማንቶች አሁን ላይ ቢጠፋም በታሪክ ግን የራሳቸው ቋንቋ እንደነበራቸው ይነገራል፡፡ ነበራቸውም አልነበራቸው “ቅማንት ነን!” የሚሉ ወገኖች አሁን ላይ አማርኛ ተናጋሪ ቢሆኑም አማርኛ ተናጋሪነታቸው ከአማራ ተለይተው የራሳቸውን ክልል እንዲመሠርቱ ከመደረግ አልተገቱም፡፡ አሠራሩ እንዲህ ከሆነ ታዲያ የኛ የብሔር ብሔረሰቦች ሕልውናና መብት ተቆርቋሪው ወያኔ ይልቁንም ትግራይ ውስጥ ላሉት የራሳቸው ቋንቋ ላላቸው ኢሮብና ኩናማ ምነዋ የራስገዝ አሥተዳደር ሳትፈቀጅላቸው ቀረሽ? ነው ወይስ አደይ ትግራይ ላይ ሲሆን ይሄ መብት አይሠራም??? ቁጥራቸው እንደሆነ ጠባቧን የሐረር ከተማን አንድ ክልል አድርጋቹህ ያቋቋማቹሀቸውን አንድ የኳስ መጫወቻ ሜዳን እንኳ የማይሞሉትን ሐረሪዎች ይበልጣሉ እንጅ አያንሱ!!

ወያኔ ሆይ! ወልቃይት ላይ ቋንቋን ዋነኛ መሥፈርት ካደረግሽና ለሕዝቡ የ “ትግሬ አይደለንም!” ጩኸት ወይም ተቃውሞ “መስሚያ የለኝም!” ካልሽ እንዴት ሆኖ ነው ቅማንት ላይ ቋንቋን ጨርሶ ከመሥፈርት ሳታስገቢ ነገሩ በሕዝብ ፍላጎት ብቻ እንዲወሰን ልታደርጊ የቻልሽው??? ለቅማንቶች አማርኛ ተናጋሪ መሆናቸውን ከቁብ ሳትቆጥሪ በፍላጎት ብቻ እንዲወስኑ የሰጠሽውን የፈቀድሽውን መብት ለወልቃይት ሕዝብ ግን ልትነፍጊ ልትከለክይ የቻልሽበት ምክንያት ምንድን ነው??? ሕገመንግሥትሽ ቋንቋን መሠረት ያደረገ አከላለልን የሚከተል ከሆነ የቅማንቶች ቋንቋ አማርኛ ሆኖ እያለ እንዴት አድርገሽ ነው የራስገዝ መብት ልትፈቅጅ የቻልሽው? ይሄ ደግሞ ሌላው ውንብድና ነው፡፡

እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጅ ከዚህ ቀደምም እንዳልኩት ወያኔ ሕገመንግሥቱን ለውንብድናው እንዲመች አድርጎ ስለደነገገው በሕገመንግሥቱ መሠረት የወልቃይት ሕዝብ ወደ ማን መከለል እንደሚፈልግ ወይም በማንነቱ ላይ እንዲወስን ቢፈቅድ እንኳ ሕገመንግሥቱ በሕዝበ ውሣኔው አገሬው ወይም ተወላጁ ብቻ ሳይሆን “በአካባቢው መኖር ከጀመረ አምስት ዓመታትና ከዛ በላይ የሆነው ሁሉ ድምፅ መስጠት ይችላል!” ስለሚል በተለያየ ጊዜ ከትግራይ እየጫነ ወስዶ ወልቃይት ላይ ያሠፈረው ወገኑ ቁጥሩ ከወልቃይት ሕዝብ ስለሚበልጥና በሕዝበ ውሣኔው እነሱንም ድምፅ እንዲሰጡ ስለሚያደርግ ይህ ሕዝበ ውሣኔ የወልቃይትን ሕዝብ ፍላጎት የሚያስጠብቅ ውጤት ሊገኝበት የሚችል አይሆንም፡፡

እንግዲህ ይሄን ይሄን የምለው ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን ወያኔ አስቀድሞ የወልቃይትን መሬት ለራሱ ለማድረግ በረሀ እያለ ጀምሮ ሲፈጽመው የኖረውን የአማራን ዘር ከወልቃይት የማጥፋትና የማጽዳት አረመኔያዊ ግፍ የተሞላበት የውንብድና ተግባር ባለበት ትቸ አከላለሉን ሕጋዊ ለማስመሰል ወያኔ የሚናገራቸው ምክንያቶችም ምን ያህል ብላሽና ሕገወጥ እንደሆኑ ለማሳየት ስል ብቻ የምለው ነው፡፡ እውነታውን ያየን እንደሆነ ግን እንኳንና ወልቃይት ትግራይም ራሱ የትግሬ እንዳልሆነች ዐፄ ካሌብ የመን ውስጥ የናግራን ክርስቲያኖችን ከአይሁዶች መጠነ ሰፊ ጥቃት ለመታደግ ዘምተው ድል አድርገው በሚመለሱ ጊዜ ለባርነት ለአገልጋይነት ከየመን በግዞት ያስገቧቸው መሆናቸውን፣ በዚህም ምክንያት ባሪያ መሆናቸውን ለማመልከት ትግሬ መባላቸውን፣ ሀገሩም በምን ምክንያት በምን የታሪክ አጋጣሚ ከመቸ ጊዜ በኋላ ትግሬ ወይም ትግራይ ሊባል እንደቻለ በግልጽ የሚታዩና ሊስተባበሉ የማይችሉ በርካታ መረጃዎችን ጠቅሸ ታሪካቸውን መጻፌ ይታወሳል፡፡ ባጠቃላይ ግን ተጀምሮ እስኪጨረስ ይህ የወልቃይት ጉዳይ በወያኔ የውንብድና ተግባር  የተሞላ ነው፡፡ ስለሆነም ነው የዚህ ሕዝባዊ ተቃውሞ አንደኛው መነሻ ሊሆን ተቃውሞው አድጎ በመላ ሀገሪቱ በመስፋፋት ፀረ ወያኔ የተቃውሞ ሰልፍ ሊሆን የቻለው፡፡

ምክንያቱም ሕዝብ ይሄንን የማድረግ ሙሉ መብት፣ ሥልጣን፣ ኃላፊነት አለውና፤ ታሪካዊ ግዴታውም ነውና፡፡ “የወያኔ አገዛዝ ጠቅሞኛል ወይስ አልጠቀመኝም?” ብሎ የመገምገምና እንዳልጠቀመው ካወቀ ወይም ካመነም “ይወገድልኝ!” ብሎ የመወሰን መብት ያለው ሕዝብ እንጅ እራሱ ወያኔ ወይም ጌቶቹ የባዕዳን መንግሥታት አይደሉም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰልፎቹ እያረጋገጠ እንዳለው ወያኔን “አልጠቀመኝም!” ብቻ ሳይሆን “ጠላቴ ነው! እጅግ ጎድቶኛል!” ብሎም ያምናል፡፡ ደሙ በግፍ እንዲፈስ በተደረገበት ሰልፎቹ በሚያስተጋባቸው መልዕክቶች ይሄንን ነው እያረጋገጠ ያለው፡፡ ይህ ሕዝብ ድምፁ ጩኸቱ አልተሰማለትም እንጅ በጨዋና ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በወጉ በደንቡ በምርጫ ድምፁ ወያኔን ፈጽሞ እንደማይፈልግና እንደማይፈቅደው አንዴ ብቻ አይደለም በተደጋጋሚ አስታውቋል አረጋግጧል፡፡ ምርጫን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ያሰማው ጩኸቱ ሊሰማለት ስላልቻለና ተስፋ በመቁረጡ ነው ወደ ዐመፅ እንዲያመራ የተገደደው፡፡

ይህ የእስከዛሬ ጩኸቱ ጥያቄው ሊሰማለት ያልቻለ ሕዝብ ድምፁን ጩኸቱን ፈጽሞ ሊሰማው ሊቀበለው ያልቻለውንና ያልፈለገውን አገዛዝ “አልፈልግህም! ሥልጣን ልቀቅ!” ብሎ በአደባባይ ለመጠየቅ በሦስት ዐበይት ምክንያቶች ወያኔ የሚለውን ዕውቅናም ሆነ ኢሕገ መንግሥታዊ ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልገውም፡፡

1ኛ. “ሕዝብ ያለማንም ጣልቃገብነትና አስገዳጅነት ወይም አታላይነት የሀገርንና የሕዝቧን ጥቅም ታሳቢ በማድረግ በራሱ እስከወሰነ ጊዜ ድረስ ምንግዜም ትክክል ነው!” በሚለው መርሕ መሠረት የፈለገውንና የፈቀደውን ነገር በፈለገውና በፈቀደው መንገድና ሁኔታ ያደርጋል እንጅ እንደ የፖለቲካ ፓርቲ (የእምነተ አሥተዳደር ቡድን) ሕጋዊ ሰውነት ተሰጥቶት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ አካል ስላልሆነና እንደ ግለሰብ ወይም እንደ ድርጅት በይዘት የተወሰነ አካል ስላልሆነ ሲሆን፡፡

2ኛ. ሕዝብ በሰልፍ ይሄንን የመጠየቅ መብት ቢኖረውም ወያኔ ግን ይሄንን “የሥልጣን ልቀቅልን!” የሕዝብ ጥያቄ መስማትና በዚሁ የሕዝብ ጥያቄ መሠረትም ሥልጣን መልቀቅ ፈጽሞ አይፈልግምና የሰልፍ ጥያቄውን እንዲለቅ ለተጠየቀው ለራሱ ማቅረብ አግባብ ስለማይሆን፡፡

3ኛ. ሕዝቡ ለወያኔ ቀድሞውንም ቢሆን ያልሰጠውንና ወያኔ በጉልበቱ ያዝኩት የሚለውን ሕጋዊነት ስለሻረ ይህ በጉልበቱ እራሱን የሾመ አሁን ግን በሕዝቡ የተሻረው አካል ዕውቅናም ይሁን ፈቃድ የመስጠት መብትና ሥልጣን ስለሌለው፣ ሕዝቡም ለሚያደርገው ነገር የሻረውን አካል ዕውቅናም ይሁን አገዛዙ የሚለውን ሕጋዊ አግባብነት የሌለውን ፈቃድ የመጠየቅ ግዴታ ስለሌለበት የሚሉት ነጥቦች ናቸው፡፡

የሥልጣን ባለቤትና ሥልጣን ሰጭም ነሽም ሻሪም ሿሚም ሕዝብ ከሆነና ይህ ሕዝብ ደግሞ በሰላማዊ መንገድ ፍላጎቱን የሚያሟላበት የሚያሳካበት መንገድ ዝግ ከሆነ በእነኝህ ሦስት አመክንዮዎች መሠረት የወደደውን የፈለገውን የማድረግ መብት እንዳለው ማንም ሊጠራጠር አይገባም፡፡ ወያኔ ይሄንን የሕዝብ ጥያቄ ፈጽሞ መስማት ባይፈልግም ሕዝብ ብሏልና የግድ ሊቀበል ይገባል፡፡ ወዶ ባይቀበል ተገዶ ይቀበላል፡፡ ሰልፎቹ እንደ ፌስ ቡክ (መጽሐፈ ገጽ) ባሉ ማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛዎች የተጠሩት ሕዝብ መደበኛ (Conventional) የብዙኃን መገናኛዎችን በመጠቀም ስለደኅንነቱ፣ ስለሀገሩ፣ ስለ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መብቶቹ መጠበቅ እንዳይመክር ሐሳቡን በነጻነት እንዳይገልጽ እንዳያንሸራሽር በብዙኃን መገናኛዎቹ የመገልገል ሕገ መንግሥታዊ መብቱን በአገዛዙ ሙሉ ለሙሉ ስለተነጠቀ ስለተከለከለ ፈጽሞ ስላልተፈቀደለት ነው፡፡

አገዛዙ ካለው የከፋ አፋኝና አንባገነናዊ ባሕርዩ የተነሣ ሕዝብ እንኳንና መደበኛ የብዙኃን መገናኛዎችን ሊጠቀም ቀርቶ ማኅበራዊውን እንኳን እንዳይጠቀም ተደርጎ ታፍኗል፡፡ ይሁንና ሕዝባዊ ሰልፎቹ በማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛዎች መጠራታቸው ምንድን ነው ችግሩና ነውሩ? የወያኔ ባለሥልጣናት ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎቹ በዚህ መልኩ መጠራቱን “ጥቂቶች፣ አንዳንድ” እያሉ ለማራከስ ለማጣጣል  መሞከራቸው ገርሞኝ ነው፡፡

ወያኔ ይሄንን በግልጽ በገሀድ የሚታየውን “አላየሁም አልሰማሁም!” ብሎ ሕዝብ ነቅሎ  የወጣባቸውን ሰልፎች “ሕዝብ” ብሎ ላለመጥራትና የሕዝብ ዕውቅና ላለመስጠት “ጥቂቶች፣ አንዳንድ” ካለ ወያኔ በታሪኩ ለእሱ ድጋፍ ለመስጠት ሕዝብ መቸና የትስ በዚህ ደረጃ ወጥቶለትና ድጋፉን በጋለ ስሜት በአደባባይ ሰጥቶት አሳይቶለትስ ነው ሕዝባዊ ድጋፍ እንዳለው የሚያወራው??? ወያኔ ይሄንን ሊመልስ ወይም ሊያረጋግጥ ይችላል? በፍጹም!!! እውነት እንነጋገር ከተባለ ወያኔ ሳያስገድድና በአበል ሳይደልል በሕዝብ ነጻ ፍላጎት ብቻ ሰልፍ ቢጠራ ዐሥር ሰዎች እንኳን ሊወጡበት የሚችሉበትን ሰልፍ ማድረግ ይችላል??? “ለማያውቅሽ ታጠኝ!” አለ ያገሬ ሰው፡፡ በአንጻሩ ግን በፊትም እንዳየነው አሁንም እያየን እንዳለነው ለተቃውሞ ሲሆን ግን ሕዝብ በወያኔ ታጣቂዎች ሩምታ ቶክስ ሊፈጅ እንደሚችል እያወቀም፣ እንዳይወጣ በወያኔ ከባድ ማስጠንቀቂያ እየታወጀበትና ከየበሩ በወታደር እየተዘጋበትም እንኳ እንዲህ ነቅሎ በመውጣት ወያኔን በምሬት እያወገዘ “በቃኸኝ!” ብሏል እያለም ይገኛል፡፡ ይሄ ታዲያ የኢትዮጵያ ሕዝብ ልብና ፍላጎት ምን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ አያሳይም???

በእነዚህ ሕዝባዊ የአደባባይ የተቃውሞ ሰልፎች ወይም ዐመፆች መግቢያው የጨነቃት ፈሪዋ፣ ቅዘናሟ ወያኔ የፈሪ ዱላዋን በመምዘዝ ከመብረቃዊ የብሶት ጩኸቱ በስተቀር ስንጥር እንኳን ባላነሣ የሰላማዊ ሰልፈኛ ሕዝብ ላይ የእሩምታ ቶክስ  በመክፈት በግፍ ፈጅታ መንገዶችን በደሙ ከማጨቅየት ጀምራ እንደቀደመው ልማዷ ሁሉ “”ፈሪ ያሰኘኛል፣ “በራስ መተማመን የሌለው” ያሰኘኛል፣ የሕዝብ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) መብቶችን ገፋፊና ፈላጭ ቆራጭ አንባገነን ያሰኘኛል”” ብላ ሳትጨነቅ ሕዝብ ለሰላማዊና ሕጋዊ ትግሉ እንዳይመክር፣ እርስበእርሱ እንዳይገናኝ፣ ሐሳቡን በነጻ እንዳይገልጽ  የመናግር (የስልክ፤ ስልክ ከዓረብ የተወሰደ ቃል ነው ዓርብኛም ከአውሮፓ) አገለግሎትን ጨምሮ የማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛውን አገልግሎት አቋርጣዋለች፡፡

ሥራዋን ታውቃለችና በራስ መተማመን የላትም፡ ነጻ የመረጃ ልውውጥና ነጻ የብዙኃን መገናኛ የህልውና ሥጋቷ ነውና፡፡

ወያኔ የምትለው ብታጣና ቢጨንቃት ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ጩኸቱን እያሰማ እንደሆነ ዕያየች ባለሥልጣናቷ “ኃላፊነትን የሚወስድ አካል ወይም ባለቤት የሌለው ሰልፍ ነው!” ይላሉ፡፡

አየ ወያኔ! ቢጨንቅሽ እኮነው!

ሰማያዊ ፓርቲ ለበቀደም እሑድ ነሐሴ 1,12,2008ዓ.ም. ባሕርዳር ጠርቶት የነበረውን ሰልፍ “ከአቅም በላይ በሆነ ጫና” በሚል ምክንያት ሰልፉን በሰረዘ ጊዜ ሲጀመርም ቢሆን ሕዝብ በራሱ ተነሣሽነት የተቃውሞ ሰልፎችን እያደረገ ባለበት ወቅት እነሱ ሰልፍ መጥራት እንዳልነበረባቸው፣ ከጠሩ ደግሞ ሊያጋጥሙ እንደሚችሉ አስቀድሞ በሚገመቱ ፈተናዎች ሳይበገሩ እጅ ሳይሰጡ የጠሩትን ሰልፍ ማከናወን እንደነበረባቸው በመንገር ለመውቀስ ለፓርቲው አመራሮች ደውየ በወቀስኳቸው ዕለት ወያኔ እየተደረጉ ያሉ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎችን “ባለቤት የሌላቸው…” እያለ እንደሚጠራቸው ሲያነሡልኝ ለእነሱም እንደተናገርኩትና ከዚያ በኋላም እንደተስተጋባው ሁሉ አዎ እርግጥ ነው ለእነዚህ ሰልፎች ኃላፊነትን የሚወስደው ወይም ባለቤቱ ግለሰብ ወይም ድርጅት አይደለም፡፡ ወያኔ ማሰብ ይችል ከሆነ ግን የጉዳዩ ባለቤት ሕዝብ እንደመሆኑ የሰልፎቹ ባለቤትም እራሱ ሕዝቡ ነው፡፡ ኃላፊነቱንም የሚወስደው እራሱ ሕዝቡ ነው! ሕዝብ የሰልፍ ባለቤትና ኃላፊ ከመሆንም በላይ የሀገርና የሥልጣንም ባለቤትና ኃላፊም ነውና ወያኔዎች “አይደለም!” ካላሉ በስተቀር ይህ አባባላቸው ድንቁርና የተሞላና ለሕዝብ ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው፡፡

እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር በወያኔ አባባል ሕዝቡ “ባለቤትና ኃላፊነት መውሰድ የሚችል አካል በሌላቸው ሕገወጥ ሰልፎች” ደም ለማፍሰስ እንደ ቀትር እባብ የሚክለፈለፍ የወያኔን አፈሙዝ ቅንጣት ታክል ሳይፈራ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ በመሳተፍ ለወያኔ ያለውን ጥላቻ በጋለ ስሜት ማሰማቱ ብሶቱ ምን ያህል ፈጽሞ ሊታገሰው ከማይችልበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ የደረሰ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መሆኑን ነው፡፡

ደርግ በሕዝባዊ ዐመፅ ያልተወገደው ደርግ ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) ስለሆነና ሕዝቡም ይወደው ስለነበር እንዳልነበረ ሁላችንንም የሚያስማማ ይመስለኛል፡፡ ደርግ ላይ የልተነሣ ሕዝባዊ ዐመፅ ወይም እንዲህ ዓይነት የተቃውሞ ሰልፎች ወያኔ ላይ መነሣቱ በወያኔ አገዛዝ ከደርግ በከፋና በሰፋ መልኩ በሀገርና በሕዝብ ላይ የከፋ ጉዳት በመድረሱ ነው እንጅ ወያኔ የተቃውሞ ሰልፎቹ ወይም ሕዝባዊ የአደባባይ ዐመፆቹ እንዲደረጉ ስለፈቃደ እንዳልሆነ ወያኔ በየጊዜው ለተቃውሞ ሰልፍ በወጣው ሰላማዊ ሕዝብ ላይ በወሰደው አረመኔያዊ እርምጃ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

ወያኔ ጥቂት እንኳን ሳያፍር ለዚህ ፋሺስታዊ (አረመኔያዊ) እርምጃው የሰጠው ምክንያት “ሕግን ለማስከበር!” የሚል ነው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን አንባገነኖች የሚፈጽሙትን ጭካኔ የተሞላበት አንባገነናዊ የግፍ እርምጃ ለመሸፈን ምክንያት ከመደርደር አይታቀቡም፡፡

ደርግም “በኢሕአፓ የነጭ ሽብር የጥቃት ዘመቻ ስለተከፈተብኝና በርካታ አባሎቸ ስለተገደሉብኝ እራሴን ለመከላከል ስል ነው የቀይ ሽብር ዘመቻን የከፈትኩት!” አለ እንጅ “ሥልጣንን ላለመልቀቅ ነው!” አላለም፡፡ የወያኔ ይግረም ደግሞ! ከተቃውሞ ድምፁ በስተቀር ስንጥር እንኳን ያላነሣን ሰላማዊ ሕዝብ በሩምታ ቶክስ ፈጅቶና ከሰልፎቹ በኋላም በሕገ ወጥ የአፈሳ እስር አግባብነት በሌላቸው ቦታዎች እያጎረ ከሕይዎት ሕልፈት እስከ አካል መጉደል በሚያደርስ ዓይን ጥርስ ሳይባል በሚፈጸም ጭካኔ የተሞላ የዱላ ቅጥቀጣ ሕግን የሚጻረር ወይም ሕገወጥ አረመኔያዊ ቅጣት እየፈጸመና ሕዝብ እያሰቃየ  “ሕግን ለማስከበር ነው!” ብሎን አረፈው፡፡

ሲጀመር ወያኔ ሕግ የሚባል ነገር ያውቃል እንዴ??? መቸ አክብሮት የሚያውቀውን ሕግስ ነው የሚያስከብረው??? እውን ወያኔ ስለሕግ መከበር የሚናገርበት አፍና የሞራል (የቅስም) ብቃት አለው??? ወያኔ ለአንድ ቀን እንኳ ቢሆን ለሕግ ተገዝቶ ሕግን አክብሮ ያውቃል እንዴ??? የትኛው የወያኔ ጥቅም ነው ሕግን ባከበረና መሠረት ባደረገ መልኩ ተፈጽሞ የሚያውቀው??? ወያኔ ለሕግ ተገዥና ሕግ አክባሪ አስከባሪ ባለመሆኑ እንጅ ሕግ አክባሪና አስከባሪ ቢሆንማ ኖሮ ሕዝብን እንዲህ በቁጣ መሥዋዕትነትን ሳይፈራ ምን ፈንቅሎ ያስወጣው ነበር ታዲያ??? ወንበዴ ሕግ የሚባልን ነገር ያውቃል እንዴ? ባለማወቁም ነው ወያኔ ለአንዲት ቀንም ቢሆን ከሕግ በላይ እንጅ ከሕግ በታች ሆኖ የማያውቀው፡፡

ወያኔ ሰልፍ የሚወጣን ሕዝብ “ሕገወጥ ሰልፍ ነው! ሕግ ለማስከበር!” በሚል “መግደል ተገቢ ነው!” ብሎ ካመነና ካደረገውም እሱ እንዳሻው ሲጥሰው ለኖረውና በየዕለቱም ለሚፈጽመው ከባባድና አደገኛ የሕግ መተላለፎች ሁሉ “ሽህ ጊዜ ሽህ ሞት ይገባኛል!” ብሎ በራሱ ላይ መፍረዱ እንደሆነ ልብ እንዲለው ወያኔን ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ አሁን ፍርድ እየፈረደ ያለው ጊዜ እንጅ ፍትሕና እውነት አይደለምና እውነተኛውን ፍትሐዊ ፍርድ ለጊዜ ሰጥተን እንጠብቃለን፡፡

አደራቹህን ለእነዚያ ጅብ አንጎል ለወያኔ ሞግዚቶች ለምዕራባውያን

“ይህ ቀን አልፎ ልላ ፤ ነገ ይመጣና

ተዉ ያስተዛዝበናል ፤ ይህ ቀን እንደገና”

በሉልኝ እባካቹህ? በግፍ ከተፈጀው ሕዝባችን ደም ይልቅ “የልማት አውታሮች” ያሉት መውደሙ እንዳሳሰባቸው በመግለጽ ሰደቡን እኮ! የእኛ ነፍስ ስለሆነ ነው ዋጋው ከንብረት ያነሰው? ነው ወይስ እየወደመ ካለው ሰላም የመንገደኞች ማጓጓዣ ድርሻ አላቸው? በሀገራቸው የሌለውንስ አማርኛ “ፈቃድ የሌላቸው ሰልፎች!” የሚለውን ቃል ከየት አመጡት? ለምንስ ቢባል? በሀገራቸው በፈቃድ ነው እንዴ ሰልፍ የሚወጣው?

እኛ በልጠናቸዋል ማለት ነዋ! ሰልፍ ለማድረግ ማሳወቅ እንጅ አስፈቅድ የሚል ሕግ የለንምናiii

ይሄኔ የኛው ወያኔ ጋዳፊን፣ ሶሪያን ወይም ዩጎዝላቪያን ወዘተርፈ. ቢሆን ኖሮ በወያኔ ላይ የፈንጂ ዝናም አዝንመው ወያኔን ለመቅበር ይህ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የተፈጸመው ግፍ ከበቂ በላይ ምክንያት ሆኖ ባገኙት ነበር፡፡ በየጊዜው እንደሚሉንም በምርጫ መንግሥት ለመቀየር የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደጋጋሚ ጥረት አድርጎ በአገዛዙ የማጭበርበር የውንብድና ተግባር ምክንያት በሰላማዊ መንገድ መንግሥት የመቀየር ጥረቱ መና ሆኖ እንደቀረበትና አማራጭ በማጣቱ ሀገሩንና ራሱን ለማዳን ዐመፅ ለማድረግ እንደተገደደ ጠንቅቀው እያወቁ “በሰላማዊ መንገድ ካልሆነ በስተቀር መንግሥትን በኃይል ለማውረድ ለማስወገድ የሚደረግ ማንኛውንም ዓይነት ጥረትና እንቅስቃሴን አንደግፍም! እንቃወማለን!” እያሉም አጉል ባልተመጻደቁብን ባልቀለዱብንም ነበር፡፡

ነገር ግን ወያኔ ገረዳቸው በመሆኑና መለኪያቸው የሰው ልጆች ሊያገኙት የሚገባው ሰብአዊ መብቶችና ዲሞክራሲያዊነት (መስፍነ ሕዝብነት) ሳይሆን የእነሱ ግፍ የተሞላበት ነውረኛ ጥቅማቸው ብቻና ብቻ ነውና ወያኔ ሲፈጽምብን እንደኖረው ሁሉ የፈለገውን ያህል ግፍ አሁንም ሆነ ወደፊት ቢፈጽምብን “ሃይ” የሚል አንደበት እንደሌላቸው ጠንቅቀን እናውቃለንና የሚፈጽሙብንን ግፍ አደባባይ እንዲያውቀው ፀሐይ እንዲሞቀው ታሪክ እንዲመዘግበው ያህል እየወጣን እንጮሀለን እንጅ ይፈርድልን ይመለከትልን ዘንድ የምንጮኸውስ ወደ እግዚአብሔር እንጅ ወደ እነሱ አይደለም፡፡

ምዕራባውያን ሆይ! ችግሩ የተፈጠረው በሕዝብና በአገዛዙ መሀከል እንጅ በአገዛዙና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መሀከል አይደለም፡፡ ይሄንን ሀቅ “ባለቤት የሌላቸው ሰልፎች!” ሲል ከተናገረው የወያኔ መግለጫ ማረጋገጥ ትችላላቹህ፡፡ ነገር ግን ችግሩ በሕዝብና በአገዛዙ መሀከል መሆኑን መቀበል እኛን በተመለከተ ትክክለኛ አቋም ለሌለው ሸፍጠኛ ፖለቲካቹህ (እምነተ አሥተዳደራቹህ) ስለማይመችና ስለሚያሳቅላቹህ ወይም ስለሚያሳጣቹህ ወያኔ እንኳን ያልወጣውን ቃል ፈጥራቹህ ለይስሙላ በመለፈፍ በቁስላችን ላይ እንጨት ትሰዱብናላቹህ፡፡

በሀገራቹህና ቆመንለታል በምትሉት መርሐቹህ እንኳንና ሕዝባቹህ ሕዝባዊ ዐመፅ ለማድረግ የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሮ ይቅርና በተለሳለሰ መንገድም ቢሆን የሚያሰማው ተቃውሞና ቅሬታ “የግድ መደመጥ ተቀባይነትም ማግኘት አለበት እንጅ በምንም ተአምር ቢሆን የኃይል እርምጃ በሕዝብ ላይ አይወሰድም! ተቃውሞው ቅሬታውና ጥያቄውም እንዲቀለበስ አይደረግም! የሥልጣንና የሀገሪቱ ባለቤት እሱ ነውና!!!” ስለምትሉና ይህ የእኛ ጉዳይም በዚሁ መርሐቹህ መሠረት መስተናገድ ስለነበረበት ይህ መሆኑ ግን የገረዳቹህን የባሪያቹህን የቅጥረኛቹህን የወያኔን ህልውና እንዲያበቃ ስለሚያደርገውና ይህ እንዲሆንም ስለማትፈልጉ ነው ችግሩ፣ ግጭቱ፣ አለመግባባቱ በኢትዮጵያ ሕዝብና በአገዛዙ መሀከል መሆኑ በግልጽ እየታየና በሚገባ እያወቃቹህት በአገዛዙና በተቃዋሚ ፓርቲዎች (ቡድኖች) መሀከል እንደሆነ ማስመሰል የፈለጋቹህት፡፡ እውነት እላቹሀለሁ ወራዶች ናቹህ!

እውነት እውነት እላቹሀለሁ ዛሬ በእኛ ላይ እንዲህ እንደቀለዳቹህብን እንዳፌዛቹህብን ትናንት በእኛ ላይ አሲረው ዛሬ አይወድቁ አወዳደቅ እንደወደቁት ሁሉ እንዲሁ ደግሞ ተራቹህ ደርሶ ከባቢሎን በከፋና በፈጠነ አወዳደቅ ተምዘግዝጋቹህ ስትፈጠፈጡ እኛም በእናንተ ላይ የምናፌዝበት ቀን ይመጣል! ቀኑም ሩቅ አይደለም፡፡

ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭድ ዘንድ ግድ ነው ይላልና ቅዱስ ቃሉ፡፡

በዚህ አጋጣሚ ከሀገር ውጭ ላለው ወገኔ አጥብቄ ማሳሰብ የምሻው ነገር ቢኖር እኛ የራሳችንን የቤት ሥራዎች አጠናቀን ከሠራንና ወገባችንን አስረን ትግላችንን ካጠናከርን እኛ ወደእነሱ መሔድና መለመን መለማመጥ ሳያስፈልገን እነሱ እራሳቸው “የት ነው ያሉት?” ብለው ያለንበት ድረስ ፈልገውን ይመጣሉና ሙሉ ትኩረታችንንና ርብርባችንን ትግላችን ላይ እናድርግ፡፡ ይሄንን ካደረግን እመኑኝ እንዲያውም የእነሱ እገዛ ድጋፍም በሉት እርዳታ ላያስፈልገንም ይችላል፡፡ እነሱን ደጅ መጥናቱ እንደወያኔ ሁሉ የእነሱ ቅጥረኛ ሊያደርግ ወደሚችል ወጥመድ ውስጥ ሊከት ይችላልና እነሱን እንርሳቸው፡፡ ያለንን አቅም በመጠቀም ቆርጠን መታገል ከቻልን እግዚአብሔር ይመስገንና አሁን ትግላችን ሰፊና ጠንካራ ሕዝባዊ መሠረት የያዘ በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለድል እንደምንበቃ ላረጋግጥላቹህ እወዳለሁ፡፡

ወደዋናው ጉዳየ ልመለስና ወያኔን ልላት የምፈልገው ነገር ቢኖር እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ይህ ጀግና ሕዝብ እንዲህ በግፍ ለደፋሻቸው ወንድምና እኅቶች ለእያንዳንዳቸው ሽህ ሽህ እራስሽን ሳያስከፍልሽ የቀረ እንደሆን እውነትም እሳት አመድን ወለደ ብለሽ ተርችብን! ብቻ ያንን የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ጠብቂ እንጅ አይቀርልሽም!!!

በየ ዕለቱ እንደምትደሰኩሪብን ለዚህች ሀገርና ለሕዝቧ ልማትን እንጅ አንችን ለማጥፋት የሚያበቃ በሀገርና በሕዝብ ላይ ጥፋት ያመጣሽ የፈጠርሽ ካልሆንሽና ለዚህም በራስ መተማመኑ ያለሽ ከሆነ፣ እንደምትደነፊብንም ወንድ ከሆንሽ፣ ሱሪይቱን ከታጠቅሻት የሕዝብ መብት የሆነውን ሰላማዊ ሕዝባዊ ትግሉን በኃይል ለመጨፍለቅ ጥረት ሳታደርጊ፣ የስልክንና (የመናግርን) የማኅበራዊውንና መደበኛውን የብዙኃን መገናኛዎችን ሳታፍኝ፣ ጥሰትና ሕገወጥ አንባገነናዊ ማዕቀብሽን ሳታደርጊ ሕጋዊና ሰላማዊ ትግሉን ፊት ለፊት አትጋፈጭም ነበር ታዲያ?

እውነትን ከሚያስተጋባው አስገምጋሚ ድምፁ በቀር ባዶ እጅ የሆነን ምስኪን ሕዝብ ይሄንን ያህል ፈርተሽ ቀሚስሽ ላይ የቀዘንሽው እንደ አንቺ ቢታጠቅማ ኖሮ ምን ይውጥሽ የትስ ትገቢ ኖሯል ባክሽ? አየ ቅዘናሞ! ይህችን ጥጥ ልብ ይዘሽ ነው ታዲያ እንደ ጀግኖቹ፣ እንደ አንበሶቹ፣ ሱሪይቱን እንደታጠቋት ስትደነፊብንና ስትፎክሪብን የኖርሽው??? እንዲያው ትንሽም እንኳን አታፍሪ?

ይሄንን ጥጥ ልብ ይዘሽ ለዚህ ስኬት መብቃትሽ ለዚህ ስኬትሽ የድጋፎችሽ ሚና ምን ያህል ከፍተኛ እንደነበረ ያሳያል፡፡

ወያኔ ሆይ! በዚህ አንቺ በመጣሽበት የወራዳ፣ የነውረኛ፣ የፈሪና የከሀዲ መንገድማ ማንስ ቢመጣ እንዴት ሆኖ ነው ሳይሳካለት የሚቀረው??? ይሄ ያንቺ ተጋድሎ ለእኛ ለኢትዮጵያዊያኑ እጅግ የሚያሳፍር፣ የሚያሸማቅቅ፣ ሸሽጉኝ ሸሽጉኝ የሚያሰኝ የወራዶች የፈሪዎች የከሃዲዎች ተግባር ነው እንጅ በጭራሽ እንደ ጀብድ የሚወራ የሚያስፎክርም የኢትዮጵያውያን ሥራ አይደለም፡፡ ምን ይደረግ የሰውነትን ልክ፣ የዜግነትን ክብር፣ የማንነትን ከፍታ፣ የሉዓላዊነትን ማዕረግ ፈጽሞ አታውቂውምና ካንቺ ይሄንን ግንዛቤ አንጠብቅም፡፡

ወያኔ ሆይ! ለሕጋዊና ሰላማዊ ሕዝባዊ ጥያቄ ስንጥር እንኳን ባላነሣ ሕዝባችን ላይ በእሩምታ ቶክስ አንባገነናዊና ጨካኝ የአጸፋ ምላሽ ሰጥተሻልና ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በግፍ እየተኮሰ ከሚገለው አረመኔያዊ አገዛዝ እራሱን የመከላከል በየትኛውም የዓለማችን ክፍል ሁሉ የሚሠራበትን ሕጋዊ መብት በመጠቀም ማንኛውንም እርምጃ በወያኔ ላይ በመውሰድ ጠላቱን ወያኔን ማጥፋት ይችላልና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እራስህን ከጥቃት የመከላከል መብትህን በመጠቀም በቅርብህ በምታገኘው ወያኔና አጫፋሪዎቹ ላይ ሠይፍህን በማንሣት ጠላትህን በመደምሰስ እራስህን ለመታደግ ቆርጠህ ተነሥ!!!

እንግዲህ ወዴት ትገቢ ወያኔ? ደሞዝሽ በሚገባ ተሰልቶ ሊከፈልሽ መጨረሻው ሰዓት ላይ ደርሰሻል፡፡ ሕዝብ በመፍጀት የሚቀርልሽ ይመስልሻል? ማን እንደቀረለት ነው የሚቀርልሽ ባክሽ?

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s