ጥይት ሳይተኮስ ወያኔዎችን ድባቅ ማድረግ ይቻላል – #ግርማ_ካሳ

ወገኖች ፣

14199649_1832192370345209_3967048599230077349_nየነብርን ጭራ ከያዙ መልቀቅ አያስፈለግም ነው የሚባለው። 2009 የለዉጥ አመት እንዲሆን ሁላችንም በቁርጠኝነት መነሳት አለብን። የተጀመረው ትግል የበለጠ መጠናከር አለበት።

እነርሱ አንድ ትልቁ መሳሪያቸው ራሳቸውን እንደ ግዙፍ አድርገው በአይምሯችን ዉስጥ መሳላቸው ነው። እኛ ምንም ማድረግ እንደማንችል አድርገን እንድናስብ ማድረጋቸው ነው። ጨዋታው የሳይኮሎጂ ነው ..ስለወያኔዎች ዉሸትና ቅራቅንቦ አይምሯችን ውስጥ አጭቀን ራሳችንን በራሳችን በማሰራችን ነው መከራችን የበዛው።

እንግዲህ ለዉጥ በአገራችን እንዲመጣ ከፈለግን መጀመሪያ እኛው ራሳችንን በአይምሯችን እንታደስ። እኛ ከተባበረን እና ከቆረጥን ወያኔዎች እፍ ብንል የሚበተኑ ጉሞች መሆናቸውን አንርሳ። እነርሱ እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው። እኛ ሚሊዮኖች ነን።

ለምሳሌ በቀላሉ ራስን አደጋ በማያጋልጥ መልኩ ከሚከተሉ አንዱን ብቻ ማድረግ ከተቻለ ወያኔዎችን ጥይት ሳንተኩስ አከርካሪያቸው መስበር እንችላለን፡

1. አምስቱን የአዲስ አበባ መንገዶችን መዝጋት
2. ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ የሚወስደዉን መንገድ መዝጋት
3. በጎንደር እና በጎጃም የተነሳዉ እንቅስቃሴ ወደ ወሎና ወደ ሰሜን ሽዋ ማሸጋገር
4. የአዲስ አበባ፣ የአዳማና የቢሾፍቱ ፣ እንዲሁም የደቡብ ክልል ሕዝብ ገንፍሎ እንዲወጣ ሕዝቡን ማደራጀት ( እነዚህ አካባቢዎች በአማራ ወይንም ኦሮሞ ብሄረተኝነት ዙሪያ፣ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሆነ የወልቃይት ጥያቄን አንስተው ሊንቀሳቀሱ አይችሉም። ኢትዮያዉያንን ሁሉ ሊያታግሉ የሚችሉ አጀንዳዎች በመያዝ እንጅ)
5. የብአዴን እና የኦህዴድ የፓርላማ አባላትን ለይቶ በማወጣት፣ በፓርላማ ስብሰባ ሕወሃት ላይ እንዲነሱ ከፍተኛ፡ጫና ማድረግ( እነዚህ ሰዎች በፓርላማ ሕወሃት የወሰነዉን ዉሳኔ አጨብጭበው የሚያጸድቁት ሕወሃትን ስለፈሩ ነው። አሁን ግን ሌላ ሃይለ እንደሚከታተላቸውና ላጨበጨቡበት ዉሳኔ ሁሉ ተጠያቂ እንደሚሆኑ ከተነገራቸው ከሕዝብ ወገን ሊቀላቀሉ ይችሉ ይሆናል)

ይህ ተግል የሕዝብ ትግል ነው። ወያኔዎችን የምንታግለው የጥፋት ሃይል ስለሆኑ ነው። ዘረኛና መርዛማ ፖለቲካ ስለሚያራምዱ ነው። በህዝባችን ላይ የትግራይን ህዝብ ጨመሮ የግፍ አገዛዝ ስለጫኑ ነው። ወያኔዎችን የምንታግለው ለሰብአዊነት እና ለዜጎች መብት ስለመንቆረቆር ነው።

ወያኔዎችን እንታገላለን እያልን እኛም ዘረኛ ከሆንን፣ ለጥላቻ ቦታ የምንከፍት ከሆነ እና የጠላቴ ጠላቴ ወዳጄ ነው በሚል አጉል ፈሊጥ እንደ ወያኔ ካለ ሃይል ጋር የምንሽሞደሞድ ከሆነ ግብዞች ነው የምንሆነው።

ትግላችን ዘርና ሃይማኖት ሳይለይ ሁሉንም ባቀፈና ባላገለለ መልኩ መሆን አለበት። በተለይም በአሁኑ ወቅት “እኛ ከሌለን ሌላው ይነሳባቹሃል። እኛ ነን ያለናችሁ፡ እኛም ከጠፋን እናንተም ትጠፋላችሁ” በሚል የትግራይ ልጆችን ሲስተማሪክ በሆነ መንገድ በማስፈራራት የትግራይ ማህብረሰብን ከጎናቸው ለማድረግ ሕወሃቶች ደፋ ቀና እያሉ ነው። ይሄንን ደባ ማክሸፍ አለብን። ለምን ዉሸት ነውና። የምንካሸፈው ደግሞ አንደኛ ለወያኔዎች ሳናስበው መሳሪያና መጠቀሚያ መሆናችንን ስናቆም እና የትግራይን ህዝብ የትግሉ አጋር ስናደርግ ነው።

ወገኖች ከትግራይ ህዝብ ጋር ሆነን ሕውሃትን ድባቅ እንመታታለን። በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ሕወሃት ታሪክ ትሆናለች።

በ2009 ፖለቲካችን ፍጹም ከዘረኝነትና ከጥላቻ የጸዳ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተ የሰለጠነ ፖለቲካ መሆን አለበት።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s