ባልሽን አያርገኝ – መታሰቢያነቱ እሬቻ በዓል ላይ ለተገደለችው ወጣት

balshin
ከአያሌው መንበር

በእርግጥ ሁሉ አልቃሽ ነው ሀገር አዘንተኛ
ትውልድም ከንቱ ነው እንደወጣ ቀሪ የሌለው እረኛ
ግና ግና ግና እኔ እርሱን አያርገኝ የትዳር አጋርሽን
በህልሙም በውኑም የሚዳብስሽን
ውጥንሽ ሳይሰምር ህልሙም በአጭር ቀርቶ
እንዴት ይገፋዋል የቃል ኪዳን ሰነድ አብሮነቱን ትቶ???
በክንዱ ሊያንተርስ፣
በሎጋ ጣቶቹ ገላሽን ሊዳብስ
ከንፈርሽን ሳም አርጎ ፍቅሩን ለማጣጣም
አይኑን እያሻሸ ከእንቅልፉ ሲነቃ አንቺ ግን የለሽም
በውድቅት ሌሊት ገላሽን ሲዳብስ፤ ህልሙን ሊያጫውትሽ
ዳቢሎሱን መንግስት ባንቺ ቦታ አገኘው ከእቅፉ ሲነጥቅሽ

(መታሰቢያነቱ እሬቻ በዓል ላይ ለተገደለችው ወጣት

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s