አገሬ ሃዘንሽ ቅጥ አጣ! | ከያሬድ ኃይለማርያም

 

በኢሬቻ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ወያኔ ቀልብ ይገዛ ይሆን የምትለውን ሙጣጭ ተስፋዮን ገሎታል፡፡ ጥልቅ ሃዘንም ውስጥ ከቶኛል፤ እጅግ ያማል፤ እንቅልፍ ይነሳል፤
ትላንት በቢሸፍቱ በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ወያኔ ከሕዝብ ጋር አብሮ ባይዘልቅም ‘ማምሻም እድሜ ነው’ እንደሚባለው ለአጭር ጊዜም ቢሆን እያምታታም፣ በእድሳት ስም እያጨበረበረም በጡንቻ እንዲከርም የሚያስችለውን የመጨረሻዋን ክር በጣጥሶ የጣለበት ቀን ነው፡፡

ያሬድ ኃይለማርያም ለ7 ዓመታት ያህል ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ካውንስል ጋር አብሮ የሠራና የኖቬምበር 1 እማ 2ቱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከሃገር ብዙ ምስጢሮችን ይዞ በመውጣት ለአውሮፓ ሕብረት ያቀረበ ነው።
ባለፉት አስር ወራት ብቻ በኦሮሚያ፣ በአማራ ክልሎችና በኮንሶ በፈጸማቸው ጭካኔ የተሞላበት የግፍ እርምጃ በትንሹ ከ700 በላይ ወንድምና እህቶቻችንን በጥይት እሩምታ የረፈረፈ አውሬ ሥርዓት ቢሆንም ለአገር ሰላም ሲባል ስርዓቱ ልብ እንዲገዛ ተማጽነናል፡፡

‘ያዲያቆነ ሴጣን ሳያቀስ አይለቅም’ እንደሚባለው ወያኔን የተጠናወተው የተጋዳላይነት ልክፍት እንኩዋን ልብ ሊገዛ የጨካኝነት ደረጃውን ባለበት አልገታውም፡፡ የጭካኔው ደረጃ እያደር እየከረረና እጨመረ መጣ እንጂ፡፡ ከዚህ በኋላ ጥያቄው እንዲህ በግድያ ልክፍት ከተመረዘና አውሬነቱም እየበረታ ከመጣ ስርዓት ጋር አብሮ እስከ መቼ ? ነው፡፡
59cbcc0b93dc457ea0f6f5000f4fef1d_18
ዛሬም በቢሸፈቱ የጭካኔውን ልክ አሳየን፤
ዛሬም ይህ ዕኩይ ስርዓት እንደለመደው በኢሬቻ በግፍ ለጨፈጨፉቸው ወገኖቻችን ኃላፊነቱን ከመውሰድ ይልቅ ጠአቱን በሌሎች ላይ እየጠነቆለ ተሳለቀብን፤
ዛሬም አንድም የወያኔ ባለስልጣን ኃላፊነት ሲወስድና በፈቃዱ ከስልጣን ሲለቅ አናይም፤
ዛሬም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያን በዚህ እኩይ ስርዓት ማቅ ለበስን፤
ዛሬም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ልባችን ተሰበረ፤ ተሸማቀቅን፤

ወያኔ እራሱን ያርቅ ይሆን፤ ልብ ይገዛ ይሆን፣ ከሕዝብ ይታረቅ ይሆን የሚለው ተስፋችን ተሟጧል፡፡ እንደ እኔ እምነት ከዚህ በኋላ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከባዱ ፈተና የሚሆነው ወያኔን ማስወገዱ ሳይሆን ኢትዮጵያ የወያኔ አይነት እኩይ፣ ዘረኛ፣ ከፋፋይና ግፈኛ የሆነ ስርዓት የማይበቅልባት እና የሁሉንም ኢትዮጵያዊ መብትንና ነጻነትን በእኩልነት የምታስተናግድ አገር እንድትሆን ማድረጉ ነው፡፡ ወያኔ በራሱ እጅ ሞቱን እየያፋጠነ ስለሆነ ቀባሪ እንጂ ገዳይ አያስፈልገውም፡፡

ይልቅስ ይህ እኩይ ስርዓትም ሆነ ሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶችና ወዳጅ መሳይ ጠላቶች ወገኖቻችንን እንዳሳጡን ሁሉ አገራችንንም እንዳያሳጡንና ወደ ከፋ እልቂት እንዳይወስዱን የጎንዮሽ ወይም የእርስ በእርስ ትንቅንቁን ወይም መናቆሩን ወደጎን ትተን በአንድ ልብና ሕብረት ኢትዮጵያን ከግፈኞች እጅ ነጻ እናውጣ፡፡
ሀዘኑ የሁላችንም ቢሆንም በቢሸፍቱ የቤተሰብ አባላት ላጡ ወገኖቼ ሁሉ ከልብ መጽናናትን እመኛለሁ፤ እግዝያብሔር የተሰበረ ልባችሁን ይጠግን!
ሃዘናችሁ ሃዘኔ ነው፤ ህመማችሁም ህመሜ ነው፤

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s