የማለዳ ወግ …አባቱ ፖለቲከኛና እውቁ ባለሙያ ኢንጅነር ሃይሉ ሻዎል!

ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዎል
ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዎል

* ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዎል ህልማቸው የተሳካ ፖለቲከኛ አይባሉም
* ለዲሞክራሲ፣ መእኩልነትና ፍትህ መስፈን የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል
* በኢትዮጵያ ትንሳኤ የትጉሁ አባቱ ፖለቲከኛ ድካም በክብር ይወሳል
* ዛሬ ህዝብ ፍትህ ነጻነትን በአደባባይ ጠይቋል፣ ይህም የሃይሉም ትጋት ውጤት ነው

ኢንጅነር ሃይሉ ሻዎልን በወጣትነት የጋዜጠኝነት ህይዎቴ ደጋግሞ የማግኘት እድል አጋጥሞኛል … ኢትዮጵያን በነፍስ ይወዷታል ፣ ግማሽ ክፍለ ዘመን ለሚጠጋ የጎልማሳ እድሜ አስተምራ ለወግ ማዕረግ አብቅታቸዋለችና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዋታል ! ሃይሉ ቁጡና ኃይለኛ ናቸው ቢባክም ካልነኳቸው አይነኩም … ላመኑነት ወደ ኋላ ማለት አያውቁም … በተለይ በሀገራቸውና በህዝባቸው ቀልድ የለም ! ደፋር ናቸው ፣ ያመኑበትን በግላጭ ከመናገር አያፈገፍጉም ምነዋ ግትር ፖለቲከኛ መሆንዎ ሲባሉ ” በሀገሬና በህዝቤ ለመጣብኝ ግትር ነኝ !” በማለት እንቅጯን ይነግሩዋችኋል !

ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዎል ፖለቲከኛ ያደረጋቸው የሀገራቸው ነገር አሳስቧቸው የአቅማቸውን ለማድረግ ነበር ወደ ፖለቲካው የገቡት … ፖለቲካው ደግሞ የእኛ ሀገር ፖለቲካ ፣ መሪዎች ደግሞ ለሃገር የማይበጅ ራዕይ አራማጅ ናቸውና ከሃይሉ ሻዎል ጋር አይጣጣሙ ም … በፖለቲካው ምህዳር ሰፍቶ ባይሰፋም ኢንጅነር ሃይሉ ሻወል የፖለቲካ ምህዳሩ ሰፍቶ ዲሞክራሲ፣ እኩልነትና ፍትህ ሰፍኖ ለውጥ ይመጣ ዘንድ የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል ፣ ፍርሃታችን ካስወገዱት ፖለቲከኞ አንዱም ናቸው … ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዎል እንደ እኩዮቻቸው ምሁራን የሩቅ ተመልካች ሳይሆኑ ግንባራቸውን ለጦር ሰጥተው እድሜያቸውን እስኪገፋ ጥረው ግረዋል !

ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዎል ህልማቸው የተሳካ ፖለቲከኛ አይባሉም ፣ በህልፈታቸው ዋዜማ እርሳቸው ይጮሁ ይታገሉለት የነበረው ኢትዮጵያዊ ፍትህ ነጻነትን በአደባባይ እየጠየቀ መገኘቱ የሃይሉም ትጋት ውጤት ነው ባይ ነኝ ፣ በህልፈታቸው ዋዜማ ህብረቷ የማይናጋ ኢትዮጵያን የማየት እድል ባያገኙም ከጫፍ እስከ ጫፍ መብቱን እየጠየቀ ያለው ሃገሬ ድምጽና ጸሎት ምህላው ከተሳካ እሰየው ነው ፣ ተከፋፍላ ማየት የማይፈልጓት ኢትዮጵያ ትንሳኤ ሲበሰር የትጉሁ አባቱ ፖለቲከኛ ልፋት ድካም በክብር ይወሳል !

በእስከዛሬው የህይዎት ጉዞ ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዎልም ስለሚወዷት ኢትዮጵያ እንደ ቀሩት የሀገር ባለውለታዎች አቀበት ፣ ቁልቁለት ወጥተው ወርደው ፣ ለፍተው ደክመው ተለይተውናል ፣ ስለ ኢትዮጵያ ለከፈሉት መስዋዕትነት ክብር ለሚገባው ከብር በመስጠት ኢንጅኔር ሃይሉ ሻዎል ክበር ሰጥተን እናመሰግናቸዋለን 🙁

ነፍስ ይማር አባት አለም !

ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 27 ቀን 2009 ዓም

– See more at: http://www.satenaw.com/amharic/archives/22771#sthash.eMlUXeTR.dpuf

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s