የኢትዮጵያ ሕዝብ የነጻነት ትግል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አይደናቀፍም!!! [ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው]

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ወያኔ ድፍን 25 ዓመታት ሙሉ የኢትዮጵያን ሕዝብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ደፍቆ ይዞ ሲያሰቃይ መኖሩን እረስቶ በትናንትናው 29,1,2009 ዕለት ለ6 ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የኢትዮጵያ ሕዝብ በብርታት እያደረገ ያለውን ፀረ አንባገነን አገዛዝ የነጻነት ትግልን ለመቋቋምና አሸንፎ እንደገና አስከፊ የአንባገነን አገዛዙን ለማስቀጠል ያለ የሌለ አቅሙን አሟጦ በመጠቀም ሕዝብን ሊፋለም ቆርጦ መነሣቱን አስታውቋል፡፡

ይህ አዋጅ ወያኔ በተለያዩ አዋጆችና ሕግጋት አንዴ “የፀረ ሽብር ሕግ”ሌላ ጊዜ ሌላ አሳሪ ሕግ አሁን ደግሞ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ” በማለት ስም እየቀያየረ በአሸባሪ ድንጋጌዎቹ ሕዝብን በማሸበርና በማስፈራራት እጅ እንዲሰጥ አድርጎ አሜን ወዴት ብሎ እንዲገዛለት ለማድረግ ተደጋጋሚ ጥረት ማድረጉን ከማመልከቱ ውጭ ይህ አዋጅ የሚያመጣው ያልነበረ አዲስ ነገር አይኖርም፡፡ 25 ዓመታት ሙሉ ያለ ሕግ ስንተዳደር ወይም ስንገዛ ኖረናልና፡፡

ዜጎች 25 ዓመታት ሙሉ ያለ ፍርድ ይገደሉ፣ ያለ ፍርድቤት ትዕዛዝ ይታፈኑ፣ በነጻ ሐሳብን የመግለጽ መብታቸውን እንዲያጡ ተደርገው፣ የመደራጀት የመሰብሰብ የመቃወም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ተነጥቀው ይኖሩ እንደነበር፣ ከአሰቃቂ የሰብአዊ መብት አያያዝ ባለፈ በዘር ማጽዳትና ማጥፋት አረመኔያዊ አገዛዝ ስር የቆየን መሆናችን የአደባባይ ምሥጢር ነው፡፡

በመሆኑም ይህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከማሸበር ስልትነት ባለፈ የሚጨምርብን አዲስ ቀንበር አይኖርም፡፡

ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ አዲስ የወያኔ የማሸበሪያ ወሬ ሳንበገር የተያያዝነውን ፀረ የጥፋት ኃይሎች የነጻነት ትግል የጥፋት ኃይሉን የጥፋት እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊቀለብስ በሚያስችል ጥንካሬ በመፋለም የተያያዘውን የሞት ሽረት ትግል በድል ለመወጣት ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ተጠናክረን እንነሣ!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s