ጎንደር የሥራ ማቆም አድማ ተጀመረ | ከተማዋ ጭር ብላለች

 

gonder
(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጃለሁና ካሁን በኋላ መስብሰብም ሆነ አድማ ማድረግ አይቻልም እያለ በተደጋጋሚ በቲቭና ራድዮ እንዲሁም የሚያዛቸው ድረገጾች አማካኝነት እየለፈለፈ ቢሆንም የአማራውና የኦሮሞ ሕዝብ ግን አሁንም አልገዛም ባይነቱ ላይ ቀጥሎበታል::

ትናንት በሜታ ሮቤ የተደረገውን እና ከ100 ሺህ ሕዝብ በላይ የወጣበትን ሰላማዊ ተቃውሞ ዘ-ሐበሻ የዘገበች ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ጎንደር የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ማስፈራሪያ ወደ ኋላ ጥላ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማዋን ጀምራለች::

በጎንደር ከተማ እየተደረገ ባለው የሥራ ማቆም አድማ ትራንስፖርት የቆመ ሲሆን ንግድ ቤቶችም ተዘጋግተዋል:: አንዳንድ የባጃጅ እና የታክሲ ሹፌሮች የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስትን መልካም ገጽታ ለመግንባት ሥራ ወጥተው የነበረ ቢሆንም በሕዝብ ማስጠንቀቂያ ለማቆም ተገደዋል::

በጎንደር ሕዝብ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ የተነሳ ከተማዋ ጭር ያለች ሲሆን በአደባባዩ የሚታዩት የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ብቻ መሆናቸውን ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጠቁሟል::

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s