ሰበር ዜና . . .  የህወሃት ሰራዊት ባለ ቀይ መስመር የአርማጭሆ ወረዳዎችን ተቀማ!

50454082በጎንደር ሰሜን ምእራብ ኢትዮጵያ በሱዳን ጠረፍ አዋሳኝ በደቡብ ተከዜ አቅጣጫ ሰሜን ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ የላይኛዉ አርማጭሆን ጨምሮ ተሰማርቶ የነበረዉ የህወሃት ጦር በደረሰበት ተደጋጋሚ ጥቃት ምክንያት የጥቃት ወረዳዎቹን ባጠቃላይ እየተነጠቀ ይገኛል ።

ጀግናዉን የአማራ ገበሬን ትጥቅ ለማስፈታት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ያደረገዉ ህወሃት በ14/02/2009 ማምሻዉን የተጠናከረ ሐይሉን ቢያሰማራም በለሱ አልቀናዉም! ወደፊት ለማጥቃት የማይመቸዉ የአማራዉ የነጻነት ምድር አርማጭሆ! ጀግናዉ ህዝብ ከነጻነት ሀይሎች ጋር በመተባበር ዙሪያ ገጠም እሳት በህወሃት ሰራዊት ላይ አርከፍክፏል

ሄሊኮፍተሮች ቢያንባርቁ! ዝቅ ብለዉ ለመብረር እንዳይችሉ የነጻነት ሐይሎች ዙ23 እና ሞርተሮች ከተራራዎች ስርቻ እየተስፈነጠሩ የህወሃትን አየር ሐይል መድረሻ ያሳጡት ሲሆን። የጦር መሳሪያ ድምጽ የሰሙ የአካባቢዉ ገበሬዎች ከየአቅጣጫዉ በማጥቃታቸዉ ምክንያት ወደ ሗላ ማፈግፈግ ያልቻለዉን የወያኔ ሐይል አኮላሽተዉታል።

ከፍተኛ መሰዋትነውት በመክፈል ትጥቅ በማቀበልና በመተባበር ድል የቀናቸዉ የነጻነት ሐይሎች ቆላ ድባትን ጨምሮ ዙሪያ ቁልፍ የጥቃት ወረዳዎችን በቁጥጥራቸዉ ስር ማድረጋቸዉን የህወሃት ወታደራዊ አስተዳደር መርዶዉን ዛሬ የተረዳ ሲሆን መልሶ ጥቃት ለመፈጸም የ 25ተኛ እና ሌሎች ተጨማሪ ክፍለ ጦሮች ተዉጣጪ ወታደሮችን እንዲያሰማሩ መመሪያ ወጥቷል።

ህወሃት ወያኔ በአካባቢዉ ላይ በቀሰቀሰዉ ጦርነት የቆሰሉ ወታደሮችን በሄሊኮፍተር በማመላለስ ከመጠመዱ ባሻገር ቁጥራቸዉ 200 የሚጠጉ የጦር አባላቱ የነጻነቱን ትግል ከነሙሉ ትጥቃቸዉ ተቀላቅለዋል።

እጁን ለነጻነት ሐይሎች በፍቃዱ የሰጠ በቅጽል ወዲ ሳንጃ የተባለ አንድ የ24ተኛ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራር እንድተናገረዉ

” የምንዋጋዉ አርሶ ካበላን ካሳደገንና ካጎለበተን አባት ገበሬ ጋር ነዉ ጸጉሩ ሸበት ያለ ፊቱን ቅጭም አድርጎ በብርቱ አይኖቹ አሻግሮ የሚመለከት አዛዉንት አባት ላይ ከመተኮስ እጅ መስጠቱና ወደ ህወሃት መዞሩ አዋጪ ሆኖ አግኝቼዋለዉ ” በማለት የገበሬዉን ብቃት አረጋግጧል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

 

ልዑል አለሜ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s