
በወረዳው አመኖ በሚባለው ቀበሌ አቶ አድነው መርሀግብር የተባለን የአካባቢ የጎበዝ አለቃ ለመየዝ ሙከራ ያደረገው የወያኔ ጦር ከፍተኛ ዕልቂት ደርሶበታል ተብሏል፡፡ አቶ አድነው በጀግንነት የከበቧቸውን ከዐሥር ያላነሱ ወታደሮች አብዛኛዎቹን ገድለው እንደተሰዉ ሰምተናል፡፡ በዚህ የተናደደው የወያኔ ጦር የአቶ አድነውን ሦስት ሙክቶች አርዶ መብላቱን የታወቀ ሲሆን በጎበዝ አለቆች እርብርብ አንድም ወታደር በሕይወት ሳይወጣ መቅረቱን ለማወቅ ችለናል፡፡
ሪፖርቱን እንዳቀረቡልን የጎበዝ አለቆች ከሆነ በአመኖ እና በሊቦ ቀበሌዎች ያልተነሱ የወያኔ ወታደሮች አስከሬን እስካሁን መኖሩን ነው፡፡ ከገበሬዎች በኩል ሁለት ሰዎች መሰዋታቸውንም ለማወቅ ችለናል፡፡ ተጨማሪ ሁለት ኦራል ጦር ወደ ሊቦ ቀበሌ መውጣቱንም አክለው ገልጸውልናል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በዓለፋና ጣቁሳ ወረዳዎች በተለይም በሻውራና የደልጊ ከተሞች ከ60 በላይ ወጣቶች ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. መታሰራቸው ታውቋል፡፡ የጎበዝ አለቆች በከተማ በመቀመጥ እጃቸውን አጣጥፈው ለወያኔ እስር የሚደረጉ ወጣቶች ወደ ማጥቃት እንቅስቃሴ መግባት እንዳለባቸው መክረዋል፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል//
Muluken Tesfaw