ፀጉረ ልውጦች በፍራንክፈርት | በልጅግ ዓሊ

 

frankfurt
እህ ዛዲያማ
በአንድ ጎጆ
እህ!
አንድ ቁርንጮ ይነጠፍና
እህ!
አዋጅ በይፋ ይታወጅና
እህ !
ሀይል ያደራጃል ደግሞ እንደገና
እህ ዛዲየማ !
እህ ዛዲያማ! ምን ትለኛለህ ?
ከየመንገዱ ሰብሰቦ ሲያስርህ
አይደለም እንዴ ገድሎ ሊጥልህ ።
. . .
ወለላዬ

እነሆ ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ አለወትሮዋ በጸጉረ ልውጦች ከተሞላች ሰንበትበት አለች ። ሃገራችን ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴ ያስፈራቸው የወያኔ ጀሌዎችና ደጋፊዎች የተነሳውን እሳት ለመሸሽ በመዘየድ ወደ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ በተራቸው መፍለስ መጀመራቸው መሆኑ ነው። ይህ ትዕይንት የወያኔ ዘመን ሊያከትም መዳረሱን ጠቋሚ ክስተት ነው። ዛሬ በመካከላችን የምንሰማው ዱካ፣ በዓይናችን የምንቃኘው ወዛም ገጽታ፣ በየሱቁ የምናስተውለው ግርግር፣ የባለስልጣን፣ የቱጃር ሚስቶችና ልጆች፣ እንዲሁም ዘመዶችና ቁባቶች መሆናቸውን አንዳች የሚያሳብቅ ነገር አለው ። እንደው በጥቅል አነጋገር በከተማው ውስጥ በሰፊው የሚታዩት እነሱ ስለመሆናቸው ብዙ ዋቢ ማቅረብ የሚያስፈልግ ከቶ አይመስለኝም ።

እነዚህ በፍራንክፈርት ከተማ ውስጥ የሚዘዋወሩትን የቱጃር ሚስቶችና ቁባቶች አተኩሮ ለተመለከተ ሰው ከቆየነው ስደተኞች በቀላሉ ይለያቸዋል። የገዥው መደብ ቅምጥሎች! ከታች እንደ አፋር ወተት በባላና ባላቸው መካካል ሲናጡ ፣ ከላይ አካላቸው የብቸና ምት እስክስታ ሲያረገርግ፣ መሬቱን ሊረግጡ ሲጠየፉት ይስተዋላሉ ። እዚህ ካሉት ሰደተኛ ሴቶች የሚለያቸው አንዱ ነገር ቢኖር ይህ አካሄዳቸው ነው ። የእኛዎቹ ሰደተኛ ሴቶች “ በሞላ ጎደለ “ አዕምሯቸው ተወጥረው፣የባቡር ሰዓት ደረሰ አልደረስ በሚል መቻኮል፣ ስፋ ሰፋ ባለ እርምጃ መንገዱን ቆረጥ ቆረጥ እያደረጉ ሲጓዙ ላየ ለካ አካሄድም ትምህርትና ቄንጥ አለው? አይ ያለው ማማሩ ፣ አረማመዱ ኩሩ ማለቱ አይቀርም።

ዘበናዮቹ ሴቶች የዛሬውን አያድርገውና ግቢያቸው በሰለጠነና በታጠቀ አሽከር፣ እልፍኛቸው በሦስትና አራት ደንገጡር፣ እግራቸው ወዲህ በሃር ስጋጃ ውዲያ በጀርመንና በጃፓን መኪናዎች ሲቀማጠሉ የኖሩ ለመሆናቸው ብዙ ባዕሪያቸው ያስረዳል።እንደው ባጋጣሚ ካገኛችኋቸው ስንት ዜጋ የሚጋፋለትንና የጀርመን ሲያጥላሉት ትታዘባላችሁ።ባቡር ላይ ተጋፍቶ፣ ለአውቶብስ ተንቀዋሎ፣ ወይ ጉድ ! ይህን ኑሮ ብላችሁ !…እንዴት ቻላችሁት? ብለው መልስው ልባችሁን ያወልቁታል። ጀርመን በሦስተኛ አለም ስትመዘን! ስትበሻቀጥ ! ይህ ብዙ የሃገራችን ሰው የሚመኘውን የጀርመን ኑሮ “ለውድ የተከበሩ” ሙሰኛ ባሎቻቸው እየደወሉ ማማረራቸው እየታማ ነው።

ለነገሩ እንዴት አያማርሩ ለዜጎቿ ገሐነም በሆነች ሃገርና አገዛዝ ውስጥ የበረሐ ገነት ኑሯቸውን ሲቀጩ ለኖሩ የሙስና ቱጃሮች አውሮፓ እንዴት ሊመጥናቸው ይችላል? ያም ሆነ ይህ ለክፉም ለደጉም መቸም መሰንበታቸው እንደማይቀር እንገምታለን። እንዲያ ከሆነ ደግሞ፣ ያውሮፓ ሕይወት ሲመራቸው ለባሎቻቸው እየደወሉ “ እነዚህን ጸረ ሰላም ሃይሎች ደምስሳችሁ መቼ ነው ወደ ሃገራችን የምንመለሰው። እኛ እዚህ ባቡር ጥበቃው ሰልችቶኛል ፣ ” ብለው ማስጨነቃቸው አይቀርም ? ለዚህ ይመስላል የጨነቃችው ባሎች ፣ የወደፊት የእነርሱም ዕጣ ፈንታ ስደት መሆኑ እየታሰባቸው፣ ትግሉን ያከሸፉ መስሏቸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እስከማወጅ የደረሱት። መቸም የመንጥር ዘመቻ ለደርግ እንደረዳው ለኛም ይጠቅመናል ብለው ይሆናል።

ከነዚህ የሙስና ቱጃሮች ጋር ጀርመን ወለድ የሆኑ “ ልማታዊ ኢንቬስተሮች “ ተመልሰው ከእኛው ጋር መጋፋት መጀመራቸውን ሌላው አዲስ ክስተት ነው። የእነዚህን “ ልማታዊ የዴያስፖራ ኢንቨስተሮች በተመለከተ ባህሪይቸውና የስብእና ልካቸው ቀደም ብሎ ብዙ ሰለተፈተሸ፣ ዛሬ በቀላሉ እነሱን እንደሌሎቹ ብረት ለበሶች ለመለየት አልተቸገርንበትም። አዲስ አበባ ውስጥ የተሰሩትን ፎቆችና ሆቴሎች ስም በመደርደር የአገሪቷን እድገት ፣ የወያኔን ዴሞክራሲያዊነት ሲሰብኩን የሰነበቱ የሚሌንየሙ ሆደ-ፈጆች፣ ዛሬ ደግሞ እንደ ልማዳቸው ተገልብጠው ተቃዋሚ ሆኖው ( “ወያኔን መክረን ፣ መክረን አልለወጥ አለን ። እነዚህ ሰዎች በፍጹም አይለወጡም”) በሚል ለሆዳቸው እንዳልሮጡ ዛሬ ተቃዋሚ ሆነው ለመታየት ደፋ ቀና ሲሉ ማየታችን የሚያስተዛዝበን እንጅ የሚያስገርመን አይደለም። ጥያቄው ግን እውነት ከልባቸው ነው ? የሚለው ይሆናል። ለነገሩ የ97 ምርጫ ጊዜም እንዲሁ አጨናንቀውን ስለነበር እናውቃቸዋለን።

ዓይን አውጥተው የተቃዋሚነት መድረክ ላይ ካፈጠጡት ሌላ ብዙዎቹ የኛዎቹ “ልማታዊ ኢንቬስተሮች” ደፍረው ከተማ ውስጥ ሲዘዋወሩ አይታዩም ። ነገሩማ ልክ ናቸው ። በየቦንዱ ሽያጭ ስብሰባ ላይ ሲፎክሩ የነበሩ አሁን ተመልስው የሕዝብን ዓይን ማየት እንዴት ይቻሉት። ለነገሩ በሃፍረት ቆፈን ተጨምድደው ከቤት እንደማይወጡ ብዙዎቻችን ታዝበናል ። እዩኝ እዩን እንዳላሉ ደብቁኝ ደብቁኝ ማለትን ይዘዋል ። እነርሱ ይደግፉት፣ ይጨፍሩለት የነበረው ወያኔ በሕዝብ ተጠልቶ ሕዝብ ወግድልኝ ማለቱን ተገንዝበው ቤታቸው ሃዘን ተቀምጠው አንዴ ኢሳትን ፣ አንዴ የአሜሪካንን ሌላ ጊዜ የጀርመንን ሬዲዮ ፣ በማክተሚያው ፋናን ዓይጋ ፎረም ድረ ገጽን ጎብኝተው የዜና ጎረድ ጎረድ እየተመገቡ፣ (እውነተኛው ጎረድ ጎረድ ሸገር ቀርቷል) ወያኔን እንዲከርምላቸው የከበረ ጾሎትና ምህላ ላይ ናቸው። ለሚወዱትና ለሚያፈቅሩት መንግስታቸው ይህም ሲያንስ ነው። ስለ ሕዝብ ስቃይማ እነርሱን አይመለከታቸውም።

ብልጣ ብልጦቹ “ ልማታዊ ኢንቬስተሮች “ ደግሞ የተቃዋሚውን መፈክር ነጥቀው በየሰልፉ ላይ ከፍ አድርጎ በመያዝ፣ የድሃውን ጩኸት ቀምተው ሲጮሁ ይታያሉ። የሚቀጥለው መንግስት ንብረታቸውን እንዳይወስድባቸው የተሳትፎ መረጃ የሚሆን ፎቶግራፍ ከወዲሁ በመሰብስብ ሳያዋጣ እንደማይቀር ሳይማሩ አልቀረም። በእውነት ከልብ ንስሀ ገብተው ተቀይረው ከሆነ በጣም ጥሩ ነው ። እንደውም አብዮት ጥፋታቸውን አውቀው ቀድመው ለሚመለሱ ልቧ ሩህሩህ ነው ። ችግሩ ገብቷቸው አስቀድመው በዘመኑ ቋንቋ ነቄ ብለው ከተመለሱ ፣ ራሳቸውን እንዳጋለጡ ተቆጥሮ ይቅር መባላቸው አይቀርም ። የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሁ ይቅር ማለት አያልቅበት። ግን ሕሊና ወቃሽ ነውና ሃገራቸው ላይ የሰሩት ግፍ ከሕሊና ወቀሳ ከቶ አያድናቸውም። ዛሬ በየቦታው በአንድ ጽምጽ የተነሳው ሕዝብ ትላንት ከየደሃው እየተነጠቀ (ግራውንድ ፓላስ ቱ ቪላ) ለመስራት የተሰጣቸው መሬት ላይ በግፍ የተፈናቀለ መሆኑን ሊረዱት ይገባል።

እነዚህ ሆዳሞች ዛሬም ቢሆን አደገኛም ናቸው። የተቃዋሚውን ክፍል በተገኘው አጋጣሚ ለመከፈፈል ሲጥሩ ይገኛሉ። አንድ እኔን የገጠመኝ ጉዳይ አለ። በፍራንክፈርት ከተማ የተገነዘብኩትና በብዙ ቦታ የሚታይ ነው ። ምንአልባት እናንተም ደርሶባችሁ ይሆናል። እዚሁ ፍራንክፈርት አካባቢ የጎንደር ልጆች ተሰብስበው ትንሽ ዝግጅት አዘጋጅተው ነበር ። ይህንን ዝግጅት በሚመለከት ብዙዎቻችን ስላልሰማን አልተገኘንም ። ብዙም ገቢ የተገኘበት አይመስለኝም ። ለነገሩ እነዚህ የጎንደር ልጆች ብዙዎቻንን ወያኔ ከገባ ጀምሮ በደንብ እናውቃቸዋል። ቆራጥነታቸውን፣ ሃቀኝነታቸው እንመሰክራለን ። በአጋጣሚ እዚህ ፍራንክፈርት በተዘጋጀ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ አንድ ልማታዊ ኢንቬስተር እንደሆነ የሚታማ አሁን “ተለወጥኩ” የሚል ለሃገር ያስበ ፣ ለሐቅ የቆመ በመምሰል “ባለፈው ለጎንደር ሕዝብ ገንዘብ ተሰብስቦ ነበር ። ለመሆኑ የተሰበሰበው ገንዘብ የት ደረሰ?” እያለ ይጠይቃል ። የሆነ ምስጢር የሚውቅ በማስመሰል ዓይኑን ካንዳችን ወደ አንዳችን እያንከባለለ እኛን ይመለከተናል። ብዙዎቻንን ነገሩ ስለገባን ዝም አልን ።(ለነገሩ የተቃውሞ ሰልፉ ላይ መገኘቱም ግራ ገንብቶን ቀደም ብለን ትንሽ አምተን ነበር ) አንድ የዋህ የሆነች እህታችን በዚህ በተጠቀሰው ስብሰባ ላይ ተገኝታ ኖሮ (ምንአልባትም እሱን በዝግጅቱ ላይ አላየችው ይሆናል) አንድ ቁልፍ ጥያቄ ጠየቀችው ። ለመሆኑ አንተ ዝግጅቱ ላይ ሄደሃል ? አይ አልሰማሁምና አልሄድኩም አላት ። ደግማም ታዲያ አንተ ያላዋጠኸውን ገንዘብ እንዴት ትጠይቃለህ ? ስትለው ሁላችንም ሳቅን። ሳቃችን አንድ ላይ ስለነበረ ማንነቱን ማማታችንን ተረዳው ። ዓላማው ሁላችንም ወያኔን መቃወማችንን ትተን የጎንደር ልጆች ጋር ጦርነት እንድንገጥም ነበር ማለት ነው ። እንደዚህ ዓይነት ነገር ወያኔ በሚያሰማራቸው ሆዳሞች በሰፊው መሞከሩ የማይቀር ነው ። በተለይ የድርጅቶችን ልዩነት በማራገብ፣ የዘር ጉዳይን በማክረር ፣ የትውልድ ልዩነትን በማጉላት ፣ ቀድሞ የተሰሩ ስህተቶችንን በማጎን ክፍፍሉን ሊፈጥሩ ይሞክራሉ።

ለማንኛውም እኛ ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባይ ነንና ክብርትና ክቡራን “እንግዶቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ” ። የማይለመድ ነገር የለምና ቻል አርጉት። ቀስ ብላችሁ ሁሉን ትለምዱታላችሁ። እናንተም አታብዙት፣ እንደኛ ስደትን ከባዶ አትጀምሩም ። እድሜ ለባሎቻችሁ! እነሱ ሃገራችንን ይግዙ እንጂ የውጭ ሃገር ዜጎች ናቸው ። እናንተም ልጆቻችሁን አሜሪካ ስለወለዳችሁ ብዙም ችግርና እንቅፋት አየገጥማችሁም ። ስለ ገንዘብ መቸም አናነሳም እማይጭርሱትን ወግ መጀምር ወግ ማቆርፈድ ይሆንብናል ። የአውሮፓንና፣ የዐረቦችን ባንክ ያስጨነቀው የእናንተ ገንዘብ መሆኑን ካወቅን ይበቃናል ። ገንዘብ ከሌላችሁም ብዙ እንዳታስቡ እደተለመደው ባሎቻችሁ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የሠሩትን ግፍ በመጽሐፍ አሳትመው መሸጣቸው አይቀርም ። እኛም እኛ ነን። በራሳችን ላይ የተደረገን የግፍና መከራን ታሪክ ከበዳዮቻችን የደም ብዕር አንደበት ስንሰማ መቅፈፉ ቀርቶ የሚያስደምመን፣ መጠየፉ ቀርቶ የምንገዛ ተረባርበን፣ ሞታችንን፣ ደማችንንና ሰቆቃችንን መልሰን ለእናንተው ሲሳይ የምናውል የሃያ አንደኛው ማሞ ቂሉዎች እስካለን ድረስ ስጋት አይግባችሁ። እኛ እኛ ነን ። ከአዲስ ግለሰብ፣ ከአዲስ ድርጅት ብዙ የምንጠብቅ፣ ከእኛው ጋር የቆዩትን የምናሽጓጥጥ፣ ብዙዎቻንን ከወያኔ የመጡ ሁሉ አዋቂ፣ የፖለቲካ ተንታኝ፣ የነገ ድል ቀዳጅ መስለው የሚታዩን፣ ለአዲሶቹ የምንሰጠውን ክብር ከኛው ጋር ለቆዩ የፖለቲካ መሪዎች ወይም ድርጅቶች የማንሰጥ፣ ይባስ ብለን ከኛው ጋር የሰነበቱትን ለማዋረድ የምንጥር !። ይህ ሊታረም ያልቻለ ቂልነታችን ነው ። ስም አልጠቅስም እንጂ በዚህ ሃያ አምስት አመት ብዙ ተዛዝበናል።

ለምሳሌ ሰሞኑን ከወያኔ “ ከዳሁ” የሚለው ሰላይ አያሌው መንገሻ የሚባለው መጽሐፍ ቢጽፍ ስንቶችንን ነን ለመግዛት የምንሮጠው፣ በየቦታው እሱን ለመጋበዝ የምንጥረው ? ይህንን ሰው የፖለቲካ መሪ ለማድረግ የምንቸኩለው? ጎበዝ እራሳችንን እንታዘብ ! እምንሰራውን እንወቅ ። ተስፋዬ ገብረ እባብን እላይ ስንሰቅለው ያደረሰብንን እናውቀዋለን ። ምክር እንስማ፣ እንደማመጥ፣ ውል አንሳት ። መረጃ አይናቅም ፤ አይደነቅም ይባላል። የሚሰጠንን መረጃ መቀበል ጥሩ ነው ። ሐቀኝነቱንም ማረጋገጥ በዛው ልክ ያሻ ይሆናል። የተሰጠን መረጃ እኛን እንደገና የሚከፋፍለን ሊሆንም ይችላል። ወይንም ራሱን ከወንጀል ለማንጻት ሌሎችን ሊወነጅል የታቀደ ሊሆን ይችላል። ግፋ ቢል የስደተኛ ጥያቄው እስከሚያልቅ ከእኛው ጋር ሊሰነብት ይችላል። ይህ ሁሉ ሳይረጋገጥ ከወያኔ በመምጣቱ ብቻ ከሰማየ ሰማያት ልንሰቅለው ስንፈልግ ነው ችግሩ የሚመጣው ። የሚወነጅላቸውስ ሰዎች ራሳቸውን ሳይከላከሉ እሱ በሰጠው መረጃ መፈረጅ ከተሳሳተ ድምዳሜ እንዳያደርሰን ማረጋገጥ ይኖርብናል ።

ዘመን አልፎ ወያኔ ሊወድቅ ትንሽ ጊዜ እንደቀረው ብዙ ምልክቶች ይታያሉ ። ወያኔ ከሞተ ሰንብቷል። ጥሩ እድር ጠፍቶ ነው እንጂ መቀበሪያው ጊዜ አልፏል ። የወያኔ ቡድንን አሁን ብዙ የሚክዱት ይግተለተላሉ። በንጹህም ፣ በተንኮልም ሕዝባዊ ትግሉን መቀላቀል ሊፈልጉ ይችላሉ ነገሩ ጥሩ ነው ። ግን እነርሱን ወደ አመራር ፣ የፖለቲካ ተንታኝ እያደረጉ ሁሉንም ምስጢር እንዲውቁ ማድረግ ፣ ከሚገባው በላይ መድረክ መስጠት ፣ መጽሐፎቻቸውን እያተሙ ቱጃር ማድረግ በሃገር ላይ የሚሰራ ሌላው ስውር ደባ ይመስለኛል ። መቼም ለኛ ለዘመኑ ማሞ ቂሎዎቹ አንድ ነገር መጨመር ይቻላል። ወያኔን እያካዱ ወደውም ሆነ ተገደው ሃገር ለቀው የሚመጡት ወያኔን ያዳክማልና የሚደገፍ ሊሆን ይቻላል ። ሆኖም ግን ሕዝብን ሲያስጨፈጭፍ የነበረ ሁሉ ዛሬ አቋሜን ቀይሮ ከሕዝብ ጎን ቆምኩ ስላለ ብቻ ማመንና መሪ ባጣው ትግል ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ማድረግ ትልቅ ስህተት ነው ። በተለይ በአሁኑ ወቅት ወያኔ ትግሉን ከውስጥ ለመከፋፈል በተነሳበት ወቅት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

እነዚህ ወያኔን ከዳን የሚሉ የተናገሩት እውነትነቱ እስኪጣራ ድረስ በዓይነ ቁራኛ፣ በጥርጣሬ ልንመለከታቸው ይገባል። መምጣታቸው ከሚጠቅመው ጉዳቱ ሊበልጥ ይችላል ። በተቃዋሚ ድርጅቶች የፖለቲካ አለመስማማት ውስጥ ገብተው ከመፈትፈታቸው በፊት የሰጡትን መረጃ ሰጥተው ጊዜና ወቅትን እንዲጠብቁ እንጂ መሪ እንዲሆኑ መጣር ከልማቱ ጥፋቱ ይበልጣል ። በሕዝብና በሃገር ላይ ከፍተኛ ደባና ወንጀል የሠሩ ባለስልጣናት ተደላድለው በነጻነት ሲኖሩም እየተመለከትን ነው ። እነሱ በሠሩት ጥፋት ግን እነሆ ህዝብ እያለቀ፣ ተተኪ ትውልድ ዛሬም እየመከን፣ ሃገርም እየፈረሰች ነው ። እነሱም ሲያሻቸው አማካሪ፣ ሲያሻቸው የፖለቲካ ተንታኝ እንዲያም ሲል የፖልቲካ ድርጅቶች መሪዎች ናቸው ። በዚህ ዓይነት እየተመራን ትግሉን ከዳር ለማድረስ የተጓዝንበትን መንገድ መቁጠርና እድገታችንን መመዘን ፣ ከዚያም ለምን ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው ።

ወያኔ ዛሬ እነልደቱን ሳይቀር ከተኙበት ቀስቅሶ ስደቡኝ ብሎ ልኳል ። በየተቃዋሚው ብዙ ወኪሎቹን ይልካል ። የይስሙላ ተቃዋሚም ያዘጋጃል ። ይህንን ተንኮል ተረድተን ከወያኔ የሚመጡትን ሙሉ ልብ ፣ ሙሉ ጆሮ መስጠት አይስፋልግም ። ከዛ በላይማ የማይታሰብ መሆን አለበት። ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ።

ስለ ሃገራችን በጎ የሚያስብ በሰላም ይክረም !
በልጅግ ዓሊ
beljig.ali@gmail.com
ፍራንክፈርት

26.10.2016

ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወዴት?

 

አገም ጠቀም ሲል ላለፉት አምስት አመታት ሲካሄድ የነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞና ትግል ፣ ብዙ መስዋአትነት አስከፍሎ፣ አንዳንድ የማይናቁ ድሎችን አስገኝቶ፣ ገዢውን ፓርቲ አስደንግጦና፣ በያዘው መንገድ ከቀጠለም ሕልውናው ጥያቄ ውስጥ አንደሚገባ ግልፅ በማድረጉ አስቸኩዋይ ጊዜያዊ ዓዋጅ አንዲያውጅ አስገድዶ አዚህ ደርሰናል። ከአንግዲህ ትግሉ ምን አይነት አቅጣጫ ሊይዝ ይችላል ፣ ምንስ አይነት አቅጣጫ ይዞ ቢሄድ ለሕዝባዊ ትግሉ ስኬትና ብዙዎቻችን ለምንመኘው የሕግ የበላይነት የሰፈነባትና የዜጎች ሁለንተናዊ መብቶች የሚከበሩባት ኢትዮጵያ አውን መሆን ሊያበረክት ይችላል የሚለውን ለማየት ትንሽ ወደሁዋላ ማየት የግድ ይላል።

Police fire tear gas to disperse protesters during Irreecha, the thanks giving festival of the Oromo people in Bishoftu town of Oromia region, Ethiopia

በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የተደረገው ትግል

ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የተለያዩ ተቃውሞዎች አንደነበሩ ባይካድም በ1997ቱ አገር አቀፋዊ ምርጫ የኢህአዴግን የምርጫ ኮሮጆ ግልበጣና ስርቆት አስመልክቶ ከነበረው ተቃውሞ ቀጥሎ በስፋትና በቀጣይነት የተካሄደው ያለፈው አምስት ዓመት ሕዝባዊ ትግል ፣ አንደኛው ከአንደኛው ልምድ በመማር ሚሊዮኖችን ያሳተፈ፣ የህዝብን የትግል ወኔ ያነሳሳ ልምድን ያጋራና ያዳበረ ፣ሕዝባዊ አጋርነትን የፈጠረ ፣ ሕዝባዊ አምቢተኝነትን በጠነከረ መልኩ በማካሄድ በገዥው ክፍል ውስጥ ጥርጣሬንና ክፍፍልን ከመፍጠርም በላይ አስገድዶ የመንግስት ውሳኔዎችን ያስለወጠ ሂደት ነበር።

ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ውስጥ ካላደረገ አንቅልፍ የሚነሳው ኢህአዴግ አዲስአበባ በሚገኘው የአወሊያ ትምህርት ቤት ዉስጣዊ አስተዳደራዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ሿሚና ሻሪ ካልሆንኩ በሚል የወሰደውን አርምጃ ተማሪዎቹ በመቃወማቸው፣ ተቃውሟቸውም በቤተሰቦቻቸውና ጉዳዩን በሰሙ ሰፈርተኞች ድጋፍ በማግኘቱ ሁኔታው አስደንብሮት፣ ይቺ ባቄላ የሚል አሳቤ ውስጥ ገባ ።ይሄም በመሆኑ ፣መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት የለበትም የሚለውን የሕገመንግስት አንቀጽ የተጻረረና ባፍጢሙ የደፋ፣ አህባሽ የተባለውን አስላማዊ አስተምህሮ፣ ማጥመቅ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ ካልጫንኩ ብሎ በመውተርተሩና የመጅሊሱን ምርጫ አስመልክቶ የወሰደው አቋም፣ አብዛኛውን ህዝበ ሙስሊም ያስቆጣ ሀገር አቀፍ አንቅስቃሴ ለመፈጠር ምክንያት ሆነ። መጀመሪያ የተነሳውን ተቃውሞ በተገቢው መንገድ ማስተናገድ ባለመቻሉና ነገሮችን በማባባሱ ለተቃውሞው አዲስ ጉልበት በመስጠት ድርጅታዊ ቅርጽ ይዞ “የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴን ” ወለደ ።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት፣ የወከላቸውን ህዝበ ሙስሊም ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ረጅምና አልህ አስጨራሽ ውይይቶች ከመንግስት አካላት ጋር በማድረግ ቢቀጥሉም፣ ጥያቄዎችን በአግባቡ ከመመለስ ይልቅ ችግሮቹን በማባባሱ ተቃውሞው አየከረረ ሲመጣና ሀገራዊ መልክ መያዝ በመጀመሩ መንግስት የሀሰት ወንጀል ፈብርኮ የኮሚቴው አባላትን ለአስር ዳረጋቸው ።

ይሄ ምናልባት በመንግስት በኩል ተቃውሞውን ያበርደዋል በሚል አሳቤ የተወሰደ አርምጃ ህዝበ ሙስሊሙን የበለጠ አስቆጥቶ ፣ በአንድ ወገን የታሰሩት ወኪሎቻቸው አንዲፈቱ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ጥያቄያቸው በአግባቡ አንዲመለስ መጠነ ሰፊ አገራዊ አንቅስቃሴ ተቀጣጠለ ። ይሄ ባለ በዙ ፈርጅ ሰላማዊ አንቅስቃሴ በየጊዜው ስልቱን አየቀያየረ አዳዲስ የሰላማዊ ትግል አካሄዶችን በመጠቀም፣የመንግስትን አፈና ተቋቁሞ ቀጣይነት አሳየ። የህዝባዊ ትግሉ እየጎለበተ መሄድና ከአጠቃላይ ህብረተሰቡ ድጋፍ ማግኘት (ለምሳሌ ሰምያዊ ፓርቲ ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ)ያስበረገገው ኢሕአዴግ፣ ከዚህ ቀደም በነበሩት ያገዛዝ ስርዓት ያልታየ ቤ ተ መስጊድን ደፍሮ ሰዎችን መደብደብ፣ማሰርና መግደል በአንዋር መስጊድ ጀምሮ በልዩ ልዩ የሀገራችን ከተሞችና ትናንሽ ቀበሌዎች ማካሄዱን ተያያዘው ።

ይህ አፈናና ግድያ ግን ትግሉን ለጊዜው ትንሽ ያለዘበ ቢመስልም ‘ድምጻችን ይሰማ ‘ በሚል የተደራጀው አካል የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ጥያቄ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንዲሁም ለፍትህ ተቆርቋሪዎች በሰፊው በማስተዋወቅ የኢህአዴግን አስከፊ በደል ለማሳወቅና ትግሉም ቀጣይነት አንዲያገኝ አድርጉአል ። ከዚህ ባለፈም በልዩ ልዩ ስልት የተካሄዱት ትግሎች፣ በኋላ የተቀጣጠሉት ሕዝባዊ ትግሎች ጥቅም ላይ ያዋሏቸውና ውጤታማ የሆኑ የትግል ተሞክሮዎች በርካታ ናቸው። በፈይሳ ሌሊሳ አማካኝነት አለም አቀፍ አውቅና ያገኘው ሁለት አጅን አቆላልፎ ወደላይ በማሳየት ተቃውሞን መግለጽ ጅማሮውን ያገኘው በዚሁ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በየመስጊዱ ይካሄድ በነበረው የተቃውሞ አንቅስቃሴ ወቅት ነበር።

በኦሮሚያ የተካሄደውና በመካሄድ ላይ ያለው ትግል

የአዲስ አበባ የተቀናጀ “ማስተር ፕላን” ተብሎ የሚታወቀው በፌደራል መንግስት ተቀርጾ ፣እንደተለመደው ለይስሙላ እንኳን ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ያካባቢ ከተሞች ተጠሪዎችና የህብረተሰብ ክፍል ጋር ምንም አይነት ውይይት ሳይካሄድ የወጣው ሰነድ የዛሬ ሁለት አመት የመጀመሪያ ተቃውሞ የገጠመው አምቦ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኙ ተማሪዎች ነበር። ይህን ከተማሪዎች የተሰነዘረ ተቃውሞ፣ በእንዴት ተደፈርኩኝ በሚል፣ መንግስት ርህራሄ በጎደለው መንገድ የወሰደው የቅጣት እርምጃ በአንዳንዶች ግምት ወደ ሰባ የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈና መቶዎችን ያቆሰለ፣ ከዚህ ያለፈ ቁጥር ሰዎችን ወደ እስር የሰደደ በመሆን ተጠናቅቆ ነበር።

መንግስት በወሰደው አረመኔያዊ እርምጃ “ማስተር ፕላኑን “ አስመልክቶ የነበረው ተቃውሞ ለጊዜው ረገብ ያለ የነበረ ቢመስልም፣ ከአመት በኋላ ጊንጪ ከተማ የሚገኝ ትምህርት ቤት ቦታን፣ ለአልሚ ለመስጠት በሚል በተንቀሳቀሱ የመንግስት ህይሎች ላይ ተማሪዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ያስነሱት ተቃውሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ሰደድ እሳት ወደ አብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ተዛመተ። ይሄ ባብዛኛው በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆችን ማእከል አድርጎ መቀጣጠል የጀመረው ተቃውሞ፣ የሁለተኛ ደረጃና ከዛም በታች ያሉ ተማሪዎችን ማካተት ሲጀምርና በተለይም የተማሪዎቹን ቤተሰቦችና የየአካባቢውን አርሶ አደር ወደ ተቃውሞው ጎራ መሳብና ጥንካሬ መያዝ፣የኢህአዴግን መንግስት ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከተተው።

የተቃውሞው ስፋትና ጥልቀት ያስደነገጠው መንግስት ፣ ተቃውሞውን ይገታልኛል ብሎ ያሰብውና ተግባራዊ ያደረገው የህዝብን ድምፅ ማዳመጥ ሳይሆን፣ የተለመደውን የሀይል እርምጃ በጅምላ ተቃውሞ ታይቷል በተባሉት ስፍራዎች ላይ በማካሄድ ነበር። ይሄ የጅምላ የሀይል እርምጃ ወንድ ከሴት፣ ልጅ ከአዋቂ፣ ሽማግሌና አሮጊት ሳይለይ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈ በርካቶችን ደግሞ የአካል ጉዳተኛ ያደረገ ነበር። መንግስት የወሰደው አስከፊ እርምጃ ግን፣ መንግስት ያሰበውን ውጤት ሳይሆን በተቃራኒው የህዝብ ቁጣ የበለጠ ገንፍሎ እንዲወጣ በማድረግ፣ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ተቃውሞ በየከተሞችና እንዲሁም በአብዛኛው የኦሮሚያ ገጠር ቀበሌውች ተስፋፋ።

የተቃውሞው ጥልቀት፣ ስፋትና፣ ቀጣይነት ያሳሰበው ኢህአዴግ አድርጎት የማያውቀውን “እኛ ድሮም ያለ ህዝብ ይሁንታ ምንም ነገር አድርገን አናውቅም”በሚል ቅጥፈት “ማስተር ፕላኑ” መታጠፉንና ከእንግዲህም ማናቸውም ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ህዝብን አወያይቶና አሳምኖ ተግባራዊ እንደሚሆን በይፋ አወጀ። በኢህአዴግ ታሪክ የማይታወቀውን በጠቅላይ ምኒስትሩ በኩል የህዝቡን ጥያቄዎች ትክክለኛነት ከመቀበልም በላይ ለሰዎች ህይወት መጥፋት ይቅርታን ጠየቀ። (በጎን እነ አባይ ፀሀዬ ልክ እናስገባዋለን -የኦሮሞን ማስተር ፕላን ላይ ያለ እምቢተኝነትን መሆኑ ነው-ብለው ሲደነፉ ሾልኮ በወጣ የድምፅ ቅጂ የተገኘ ቢሆንም የትግሉ ግለት፣ ይሄንንም እንኳን በአደባባይ ወጥተው እንዲክዱ አስገድዷቸዋል)
ችግሩ ግን ኢህአዴግ ዘገምተኛ በሆነ መንገድ ተጉዞ ውሳኔውችን ወደ መቀልበስና ይቅርታ ወደ መጠየቅ በገባበት ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደው ትግል በታላቅ ፍጥነት በመጓዝ አንዳንድ ውሳኔውችን ከማስለወጥ ባሻገር ፣ ለረጅም ጊዜ ህብረተሰቡን አፍኖ መሬቱን በልማት ስም ዘርፎ አናቱ ላይ የተፈናጠጠውን የኢህአዴግ ስርዓት ከነአካቴው መለወጥ አለበት ወደሚል ድምዳሜ ተሻግሮ ተግባራዊ ትግል የሚያካሂድበት ወቅት ነበር።

በ አማራው ክልል የተነሳው ትግል

በኦሮሚያ የሚካሄደው ትግል ፋታ አልሰጥ ብሎ በቀጠለበት ወቅት ለኢህአዴግ እንደ ዱብ እዳ የመጣበት በጎንደር የተቀሰቀሰው ትግል ነው። መነሻው የወልቃይት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ኮሎኔል ደመቀን ለማፈን በፌዴራል ፖሊሶች የተሞከረውን ከማክሸፍ ጋር የተያያዘ ነው።

የህወሃት ቱባ ባለስልጣናትና ደጋፊዎች የወልቃይት ጥያቄ ትናንት የተነሳ ለማስመሰል ቢሞክሩም ጥያቄው ህወሃት አዲስ አበባ ላይ ስልጣን ይዞ፣ ሀገሪቱን በቋንቋ ፌዴራሊዝም እናዋቅራለን በሚል ማካለል ሲጀመር የአካባቢው ሰዎች በተቃውሞ ድምፃቸውን እንዳሰሙ የትናንት ትዝታ ነው። ከዚህ በተጨማሪ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጅ የሆኑ ህለት አዛውንት ለወቅቱ የሽግግር ፕሬዘዳንት ለመለስ ዜናዊ እርምጃው ወንድማማች ህዝብ ለዘመናት የሚያጣላና ደም የሚያፋስስ ሊሆን ስለሚችል እንዲታጠፍ የማሳሰቢያና የምልጃ ደብዳቤ ፅፈው እንደነበር ይታወቃል።

በጸረ-ደርግ የትግል ወቅት ለአጠቃላይ ስትራቴጂ ጠቀሜታ ይሰጠኛል በሚል የተቆናጠጠውን ወላቃይት ላለመልቀቅ ወስኖ የነበረው ህወሃት፣ የኛን ይዞታ ሊቃወሙ ይችላሉ የሚሉአቸውን ከቀዬው በጦርነቱ ተፈናቅለው ወደ ሱዳን ገብተው የነበሩ ወልቂቴዎች ወደ ቀድሞ ይዞታቸው እንድይመለሱ ትልቅ ዘመቻ በማካሄድ እንዳከላከሉ ገህድ የሆነ ሀቅ ነው። ከዚህም በላይ አዲስ አበባ በገቡበት አመት ከህወሃት በቅነሳ የተሽኙ ሰላሳ ሺ ወታደሮች ከነመቋቋሚያ ገንዘብ ሰፈራ እንዲያካሂዱ የተወሰነውም ወልቃይት ውስጥ ነበር። ሀገሬውም በክፉ አይን ሳያይ እንደወንድሞቹ አስተናግዶ የነበረ ቢሆንም የባለቤትነት ጉዳይ በተነሳ ጊዜ ግን እጅግ በጣም አዝኖ እንደነበር የሚካድ አይደለም። ለዚህ ነው አሁን አንዳንድ የህወሃት ጮሌዎች ምናለ ችግር ካለና የይገባኛል ጉዳይ ከተነሳ በህዝበ ውሳኔ ማለቅ ይችላል የሚለው ስላቃቸው አሳዛኝ የሚሆነው። ይሄ የሚይስታወሰኝ የእስራኤል ሰፋሪዎች በግዥም ሆነ በማፈናቀል የፍልስጤሞችን ስፍራ ወስደው ሲያበቁ፣ በመሬት ላይ ያለው ነባራዊ እውነታ ፍልስጤሞች የኛ መሬት ነው የሚለውን አያንፀባርቅምና ጥያቄያቸው ውድቅ መሆን አለበት የሚል የጉልበተኛ ክርክር የሚያሰሙትን ነው።

የወልቃይት ጉዳይ ጫሪ ምክንያት በመሆን፣ እንቅስቃሴው ቢነሳም፣ ለሃያ አምስት ዓመት በብአዴን አጋፋሪነት ህወሃት በአማራው ክልል የሚያካሂደው በደልና፣ በተለያዩ ጊዜያትና በበርካታ ስፍራዎች፣ ከበደኖ እስከ አርባጉጉና ጉራ ፈርዳ በአማራው ህዝብ ላይ የሚደርሰው ሞት እንግልትና ግፍ ሞልቶ በመፍሰሱ የተፈጠረ ተቃውሞ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ህወሃት ከተቋቋመበት ጅምሮ የአማራውን ህዝብ እንደዋና ጠላት አድርጎ ሲቀሰቅስበት እንደነበረና ስልጣንም ከያዘ በኋላ እስካሁንም ድረስ ትምክህተኛ የሚል ተለዋጭ ስም በህዝቡ ላይ ለጥፎ መከራውን የሚያበላው በመሆኑ፣ አዲሱ ትውልድ በአዲስ ብሄርተኝነትና በቆራጥ ተነሳሽነት በቃኝ ብሎ የተነሳበት አጋጣሚ ነው።

በኢሬቻ በዓል 2009 የብዙ መቶ ዜጎች ሀይወት መቀጠፍና የህዝብ ቁጣ

ዘንድሮ ቢሾፍቱ ላይ ይካሄድ በነበረው የኢሬቻ በዓል ማሳረጊያ ቀን በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በተሰበሰበበት ዙሪያው በውሃና በገደል ፣ቀሪው መውጫና መግቢያ ደግሞ በታጠቁ ወታደሮች የታጠረ መስክ ላይ ወጣቶችሰላማዊ ተቃውሞ በማሰማታቸው፣ በእንዴት ተደፈርን በሚል በስፍራው በነበሩ አለቆች ትዕዛዝ የኢህአዴግ ወታደሮች፣ በአጠቃላይ የተሰበሰበው ህዝብ ላይ አስለቃሽ ጢስና የጎማ ጥይት (ባለቀለህ ጥይት ነው የሚልም ዘገባ አለ)በብዛት አፈንድቶ ሽብር በመፍጠር የተሰበሰበው ህዝብ ነፍሱን ለማትረፍና ከስፍራው ለማምለጥ ሲል በብዙ መቶ ለሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።
የሀያ አምስት አመታት ግፍ ሳያንስ ባለፈው አመት በኦሮሚያ ውስጥ በሚገኙ ልዩ ልዩ ቀበሌዎችና የገጠር ከተሞች ከአምስት መቶ በላይ ንፁሃንን ህይወት ማጥፋት አልበቃ ብሎ፣ በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል ላይ በማንአለብኝነት ኢህአዴግ በወሰደው እርምጃ በህዝብ ላይ በደረሰው አሰቃቂና መጠነ ሰፊ ሞት በቁጣ የገነፈለው ህዝብ፣ ለቀናት የዘለቀ ከመንገድ መዝጋት እስከ ንብረት ማቃጠልና የመሳሪያ ፍልሚያ ያካተተ ተቃውሞውን በመንግስት ላይ አደረገ።
ኢህአዴግ ይሄ ህዝባዊ ቁጣ ያስነሳውን ተቃውሞ በመደበኛ የፖሊስ ሃይል መቋቋም ስለማልችል ሁኔታው አስገድዶኝ ለስድስት ወር የሚቆይ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጄአለሁ ማለቱን በጠቅላይ ምኒስትሩ አማካይነት፣ ተግባራዊ በሆነ ማግስት ለህዝብ አሳውቋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ የህዝቡ ቁጣና የደረሰውም ጉዳት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በምንም መለኪያ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያሳውጅ ህኔታ እንዳልነበር በርግጠኝነት እየታወቀ፣ መንግስት ለምን ይሄን እርምጃ ወሰደ የሚል ጥያቄ ለማንሳት እንገደዳለን።
በአገራችን ባለፉት አመታት በተለይም ደግሞ ባለፉት አስራ አንድ ወራት በኦሮሚያና በአማራው ክልል እንዲሁም በኮንሶና ሌሎች ስፍራዎች በመካሄድ ላይ ያሉት ትግሎች የስልጣን መሰረቱን እንዳናጉበት የተረዳው ኢህአዴግን በበላይነት የሚመራው የህወሃት ቡድን፣ ትግሉን ቢቻል ለመግታት ካልተቻለም ለማዳከም የወሰዳቸው ማስፈራሪያ እስር፣ ድብደባና ግድያን ያካተቱ ዘርፈ ብዙ እርምጃዎች የታሰበውን ግብ ሊመቱ አልቻሉም።
ከላይ እንደጠቀስኩት በጎንደር የተነሳው ተቃውሞ ለህወሃት ዱብዕዳ የሆነበት በኦሮሚያ ያለው ተቃውሞ ሳይረግብ በመቀስቀሱ ብቻ ሳይሆን፣ ለሃያ አምስት ዓመታት ሲስራበት የነበረው ሁለቱን አንጋፋና የሀገሪቱን ሁለት ሶስተኛ የሚወክል ህዝብ እርስ በርስ የማናከስ ፕሮጀክት “ በኦሮሚያ የሚደረገው የወንድሞቻችን ግድያ ይቁም”“ በኦሮሚያ የሚፈሰው የኦሮሞ ደም ደማችን ነው”… በሚሉ መፈክሮች እንደ ነጎድጓድና መብረቅ በመላው ሀገር መሰማቱ ነው።ጎንደር ላይ በተካሄደው መሬት አንቀጥቅጥ ሰላማዊ ሰልፍ የተስተጋቡት መፈክሮች ለሁለቱ ታላቅ ህዝብ የትግል አጋርነት መልካም ጅማሮነትን ባበሰረበት ቅጽበት፣ የህወሃት መራሹን መቃብር ቁፋሮ መጀመርን ያበሰረ ነበር። የዚህ የትግል አጋርነት ጅማሮ ለስልጣናቸው የሚያመጣውን ዘለቄታዊ ችግር ወዲይውኑ የተገነዘቡት የህወሃት ቁንጮዎቹ ሳይውሉ ሳያድሩ ዋልጌ የ”ኮምዩኒኬሽን” ሚንስትራቸውን አሰማርተው ፣ በየቴሌቪዥንና ራዲዮ ጣቢያ እየተወዛወዘ የአጋርነት ጅማሮውን ለማጠልሸትና ተጨማሪ መርዝ ለመርጨት ሲውተረተር ከርሟል።
ዘመቻው በዚህ ብቻ ሳይገታ፣ የጥፋት መልክተኛ የሆኑቱን አባይ ፀሃዬና ስዩም መስፍንን በቴሌቪዥን አቅርቦ፣ የኛን የበላይነት ተቀብላ የማትኖርን ኢትዮጵያ፣ የጦርነት አውድማ አድርገን ህዝቡን እርስ በርሱ በማናከስ እንደ ሀገር የማትኖርበትን ሁኔታ እንፈጥራለን የሚል እንድምታ ያለው አሰልቺና ባዶ ማስፈራራት ለማካሄድ ሞክረው ነበር። ይሄ እናባላችኋለን የሚል ሰይጣናዊ የማስፈራሪያ ፕሮፓጋንዳ ህዝብን ከማስበርገግ ይልቅ በበለጠ እልህ ትግሉን እንዲያቀጣጥል ተጨማሪ ነዳጅ ሆነ፣
የዛሬ አስራ አምስት አመት ከላይ እስከታች መበስበሱን ያወጀ ድርጅት እስካሁን ድረስ በስልጣን ኮርቻ ላይ ተፈናጦ ለመቆየቱ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም፣ ላለፉት አስራአንድ ወራት የተካሄዱት ህዝባዊ ትግሎች ግልፅ እንዳደረጉት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከእንግዲህ ፣በራሱ አንደበት በሙስና የተጨማለቀ፣ ራሱ ያፀደቀውን ህገ መንግስት በየጊዜው የሚደፈጥጥና በውስጡ የማፊያ ቡድኖችን አቅፎ የሚጓዝን የገዢ ስብስብ የመሸከም ትከሻ የለውም።
ይሄን የተገነዘበው የህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ያወጀው፣ በኢትዮጵያ የተቀጣጠለው ህዝባዊው ተቃዎሞ በያዘው ፍጥነትና ስፋት እየቀጠለ ከሄደ መፍረከረከ የጀመረው ድርጅቱ አጠቃላይ ውድቀት ሊደርስበት ይችላል ብሎ በመፍራት ድርጅቱን ለማዳንና በአገሪቷ ላይ ያለውን የበላይነት ለማስቀጠል የወሰደው እርምጃ ነው ለማለት ይቻላል።

ምን ይደረግ?
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መከታ በማድረግ ከአሁኑ በርካታ ሺህ ዜጎችን በእስር እንዳጎረና አንጻራዊ ሰላምም እያሰፈነ እንደሆነ የሚፎክረው የህወሃት መንግስት፣ በዚህ መጠነ ሰፊ እስር ፣ግድያና አጠቃላይ የሆነ መንግስታዊ ሽብር፣ጊዜያዊ እፎይታ ያገኝ እንደሆን እንጂ፣ የህዝቡ አልገዛም ባይነትና ትግሉ አሁን በደረሰበት ደረጃ ለረጅም ጊዜ ግፊቱን ተቋቁሞ በስልጣን ይቆያል ለማለት አዳጋች ነው።
እርግጥ ነው ግፍና ጭቆና አንገፍግፎት ያለ ተቀናጀና፣ በትግል ሂደት የዳበረ ልምድ ያለው ድርጅት አመራር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ ወጥቶ በቃኝ! በማለቱ ብቻ ፍትህና ርትዕ የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ይቻላል ማለት እጅግ አስቸጋሪ ነው።

ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ኢህአዴግ በየጊዜው የሚያካሂድባቸው አፈናና፣ አላፈናፍን ባይነት ከራሳቸው ከድርጅቶቹ ድክመት ጋር ተዳምሮ፣ ዛሬ በኢትዮጵያ ምድር ያሉትም ሆነ ውጭ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅቶች ህዝብን መርቶ ለድል ማብቃት ይቅርና አመርቂ በሆነ መንገድ ለማታገልም በቂ አቅም የላቸውም። የተጠራቀመው የህዝብ ብሶት በእንዲህ ያለ ስፋት ተቀጣጥሎ አገር አቀፍ መልክ ሲይዝና መንግስትን ሲያርበደብድ፣ ሱሬውን ሳይታጠቅ የተያዘ መንግስት ብቻ ሳይሆን ተቃዋሚዎችም ጭምር ናቸው።

በዚህ በተዳከመ ሁኔታ ቢሆንም ፣ባሁኑ ወቅት የድርጅቶች ዋና ሃላፊነት አባሎቻቸው በሙሉ ልብ በህዝባዊው ትግል እንዲሳተፉ ማድረግ፣ በተሳትፎአቸውም አዳዲስ የትግል አጋሮችን ማፍራት፣ ትግሉ አሰባሳቢ የሆኑ እገራዊ አጀንዳዎችን እንዲይዝ ያለሰለሰ ጥረት ማድረግ፣ ያላቸውንም ሃይል በበለጠ ማሰባሰብ፣ መቀናጀት ከሚችሉት ጋር መቀናጀትና ድርጅታዊ ጥንካሬአቸውን ማጎልበት መሆን ይኖርበታል።

አታግሎና ሁነኛ አመራር በመስጠት ህዝባዊ ትግሉን ስኬታማ ሊያደርግ የሚችል ድርጅት ባይኖርም፣የህዝብ ምሬት አሁን በደረሰበት ደረጃ፣ ምንም እስሩና ግድያው ቢበረታ እንቢተኝነቱ የሚቀጥል በመሆኑ አገሪቷን ወደ ጦር ቀጠናነት ሊለውጥ፣ የሀገሪቱንም ህልውና ሊፈታተን የሚችል አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠር እነደሚችል ግልጽ እየሆነ ሄዷል።

የህወሃት ቁንጮዎች አገሪቷ ላይ ያላቸውን ሁለንተናዊ የበላይነት ለማስቀጠል በሚል ያወጁት ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ሊሆን የሚችለው በአገሪቱ የመከላከያና የደህንነት እንዲሁም የልዩ ልዩ የፖሊስ ሃይል እንደሆነ ይታወቃል። እነዚህ ተቋማት ሃገራዊ ተቋማት እንደመሆናቸውና አገሪቱም አሁን በምትተዳደርበት ህገ መንግስት ሃላፊነታቸው በዋናነት የሀገሪቷን ህልውና ማስጠበቅና ህገ መንግስቱን ማስከበር እንጂ ስልጣን ላይ ያለውን ፣ ህዝብ በቃኝ መረረኝ ብሎ፣ እንዲወርድ የሚጠይቀውን ቡድን ህይወት ማራዘም እንዳልሆነ ይታወቃል።

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ አሁን በያዘው ጎዳና ከቀጠለና የሀገሪቷ መከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ ሃይሎች የሃገሪቱን ህልውና የማስጠበቅ መሰረታዊ ተግባር ወደ ጎን ትተው፣ የአንድ ጠባብ ቡድንን ዓላማና ፍላጎት ተግባራዊ የማድረግ እንቅስቃሴያቸውን ከቀጠሉና የተደገሰውን የጥፋት ድግስ በህዝቡ ላይ ካደረሱ፣ የሰራዊቱን መፍረክረክ ብቻ ሳይሆን፣ አገራችንን በፍጥነት ወደ መበታተን እንደሚይስኬዷትና ፣በዚህም ታሪክ በፍጹም ይቅር የማይለው ሀገራዊ ክህደት እንደሚፈጽሙ ሊያምኑ ይገባል።
በአሁኑ ወቅት ታሪክ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ታላቅ ፈተና ከፊቱ ደቅኗል። የኢህአዴግ ቁንጮ ሰዎች የፖለቲካ ስልጣኑን በመቆጣጠር ዛሬ እነሱ፣ የስልጣን ማማውን ሙሉ ለሙሉ ካልተቆጣጠሩ፣ የህዝብ ብሶትና በደል፣ ብሎም የሀገር መበታተን ደንታ የማይሰጣቸው መሆናቸውን በግልጽ እያሳዩ ያሉበት ወቅት ነው። በመሆኑም፣ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ልትወጣው ወደ ማትችለው አዘቅት ሊከቱ የሚፈልጉ እኒህ እኩይ አካላት መሳሪያ መሆንን አሁኑኑ ገትታችሁ፣ የሀገርን ህልውናና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታችሁን የመወጣት ታሪካዊ ሃላፊነት ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

ኢትዮጵያ ላይ ያንዣበበውን አደጋና የገባንበትን አሳሳቢ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የመከላከያ ሰራዊቱና የፀጥታ ሃይሎች ብቸኛ አማራጭ የሚሆነው፣ መቶ በመቶ ምርጫውን አሸንፈን የህዝብ ይሁንታ አግኝተን ነው መንግስት የመሰረትነው ነው የሚለው የፖለቲካ ስልጣኑን የተቆጣጠረው ቡድን በፍፁም ተአማኒነት የሌለው መሆኑን፣ ህዝብ ወክለን ነው ፓርላም የተቀመጥነው የሚሉትም አንዳችም ውክልና እንደሌላቸው ያለፉት አስራ አንድ ወራት የህዝብ እንቢተኝነት በማያወላዳ መንገድ በማረጋገጡ፣ ቡድኑ ፓርላማውን አሁኑኑ በትኖ አዲስ ሀገራዊ ምርጫ እንዲያደርግ ጠንከር ያለ ጫና ማድረግ ነው የሚል እምነት አለኝ።

በመንግስት አካባቢ የተሰባሰበው ይሄ አጥፊ ቡድን ጫናውን አልቀበልም ብሎ እንቢተኝነትን የሚመርጥ ከሆነ ፣ ለሀገር ህልውናና ለህዝብ ደህንነት ሲባል ቡድኑን ሙሉ ለሙሉ ከስልጣን አግዶ ብሄራዊ መግባባትና ድርድር የሚካሄድበት የጊዜ ገድብ አበጅቶ ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ሁኔታውን እስከ ማመቻቸት የሚሄድ እርምጃ ሊወስድ እነድሚችልም የመከላከያ ሰራዊቱና የፀጥታ ሃይሉ ማሳወቅ ይኖርበታል። ይሄንን በማድረግም የተቋቋመበትን መሰረታዊ ዓላማ ማለትም የሀገርን ህልውናና ህዝብን ከክፉ መጠበቅን ተግባራዊ ያደርጋል ።

ፓርላማው ይበተን! ሃገራዊ ምርጫ አሁኑኑ ይካሄድ! የህዝብ እንቢተኝነት ወቅታዊ ያደረጓቸው ጥያቄዎች ናቸው።

የብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ድርጅቶች ዋና ዋና ስህተቶች

 

ከደረሰ ለማ

1. ሌሎች ሰዎች/ድርጅቶች እንዴት መደራጀት እንዳለባቸው ምን አላማ ማራመድ እንዳለባቸው የሚፈልጉትን ለማግኘት በምን አይነት የትግል ስልት መታገል እንዳለባቸው ገደብ ሲጥሉና እነርሱ በፈለጉት መንገድ ብቻ እንዲመሩ መፈለጋቸው አንዱና ዋነኛው ችግር ወይንም ስህተት ነው። ምክንያቱም አንዱ ፈቃጅና ከልካይ ሌላው ደግሞ ተቀባይ ሊሆን አይችልምና ነው። ሁሉም ድርጅት ወይንም ሰው እኩል መብት ያለውና የፈለገውን የማሰብ እና በፈለገው መንገድ አላማውን ማስፈጸም መብትና ምርጫ ስላለው።
minnesota
2. ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የአማራጭ ሃሳብ ወይንም ጥናት አቅራቢዎች እነርሱ ያሰቡትን ያቀዱትን እና የፈለጉትን ነገር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ወይንም እነርሱ የተገኙበት ብሔር ወይንም ጎሳ የፈለገው እንደሆነ አድርገው መናገር መግለጫ መስጠት መወሰን እና ሕግ/ቻርተር ማውጣት ሌላው ፈጽሞ የተሳሳተ አሰራር ነው።
ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ አስተሳሰብ እና አካሄድ አሁን ያሉትን ብዙዎቹን ድርጅቶች ከነገሥታቱ ሥርአት ከደርግ እና ከወያኔ አካሄድና ድርጊት ምንም የሚለያቸው አይደለም።
ኢትዮጵያ ውስጥ ትክክለኛ ፍትሐዊ እና ዲሞክራሲያዊ ሥርዐት ተፈጥሮ ህዝቡ በነጻና ትክክለኛ የምርጫ ሂደት የፈለጋቸውን ድርጅቶች እና ግለሰቦች ካልመረጠ በስተቀር ማንም በየትኛውም ህዝብ ስም መናገር ሕግ ማውጣት እና መወሰን አይችልም።

ስለሆነም ሕዝብ በነጻነት የፈለገውን መምረጥ እስኪችል ድረስ ማንኛውም ድርጅት ሊያደርግ የሚገባው ከሁሉ በፊት በሃገሪቱ ላይ ፍትሐዊ ሥርዐት ለመፍጠር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ብቻ ማተኮር ያንን እውን ለማድረግ በጋራና በትብብር መስራት ብቻ ነው። ለሃገርም ሆነ ሊወክለው ለፈለገው ህዝብ ይበጃል የሚለውን የራሱን የሃሳብ አማራጭ ወይንም እቅድ ደግሞ ፍትሐዊው ሥርዐት ከተመሠረተ በኋላ ለህዝብ ማቅረብ ነው። ያኔ ሕዝቡ የፈለገውን ይመርጣል።

ስለሆነም ማንም ሳይወክላቸው በየትኛውም ሕዝብ ስም ሊሆን የሚገባው ይህ ነው ያ ነው ይሚሉ ሁሉ ተሳስተዋል ሊታረሙ ይገባል።
አለበለዚያ ነገሩ ሁሉ ወያኔ የሚፈልገውን ሕዝብ ላይ ጭኖ ያንን እርሱ የፈለገውን አስተሳሰብ እቅድና አካሄድ የተቃወመን ሁሉ እንደሚገድለው እንደሚያስረው እና እንደሚያሳድደው ያለ ወንጀል መፈጸም ይሆናል መጨረሻው።

3. ምንም እንኳን የተለያዩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ያበረከቱት አስተዋጾ ባይናቅም ወደፊትም የሚኖራቸው ድርሻ ቀላል ባይሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረውና የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ወሳኙ ክፍል ህዝቡ እንደሆነ አለመረዳት ይህን የህዝቡን ተጋድሎና ወሳኝነት እነርሱ እንዳደረጉት ወይንም በእነርሱ አመራር ሰጪነት እንደተደረገና ወደፊትም እነርሱ ከሌሉበት ትግሉ እንደማይሳካ መቁጠር ሌላው ከእውነታው የራቀ ነገር ነው።

4. ብዙዎቹ ድርጅቶች እነርሱ ተቀራርበው ቢሰሩ ሊያመጡት ከሚችሉት ውጤት ይልቅ በኢትዮጵያ ላይ/ውስጥ ላለው ችግር የችግሩ ጠንሳሽ ለሆኑት እና እንዳላየ እንደማያውቅ ለሆኑት የውጪ መንግሥታት በከንቱ መጮህ አቤቱታ ማቅረብ ሌላው የብዙ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች ችግር ነው።

ከዚህ ይልቅ እርስ በእርስ ተቀራርበው ልዩነቶቻቸውን በልዩነት ይዘው በሚያስሟሟቸው ነገሮች ላይ ግን በጋራ ቢሰሩ የተሻለ ውጤት ያገኛሉ ባይ ነኝ። ማን እንዳገር ልጅ የሚለው ቢሂል በከንቱ አልተነገረምና። እስኪ ከዚህ በኋላ በዚህኛው መንገድ እንሞክረው። ውጤቱ ያማረ እንደሚሆን ይታመናል።

“የትግራዩ መንግስት አማራውን እየገደለ ያለው በጥይት ብቻ አይደለም” – የአማራ ተጋድሎ አክቲቪስት ቤተልሄም ዓለምሰገድ | ሊያዩት የሚገባ ቪዲዮ

 

(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ ከሁሉም የኢትዮጵያ ማህበረሰቦች የተወከሉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያላቸው ወገኖች የተገኙበት ሕዝባዊ የውውይት መድረክ ባለፈው ቅዳሜ ኦክቶበር 22, 2016 ተካሂዶ ነበር:: በዚህ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ተናጋሪዎች ነበሩ:: የሁሉንም ንግግሮች ተራ በተራ እንለቅላችኋለን:: በቅድሚያ የአማራውን ተጋድሎ ወክላ የቀረበችው አክቲቪስት ቤተልሄም ዓለምሰገድ ያደረገችውን ንግግር እንዲመለከቱ ጋብዘናል:: ቤተልሄም በዚህ ታሪካዊ ንግግሯ የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በአማራው ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ ; በእስራኤል ሃገር በቤተእስራኤላውያን ላይ ከሚፈጸምባቸው ግፎች የባሰ መሆኑን ታሪክ እየጠቀሰች ታስረዳለች:: ወደ ንግግሯ:: ቢያደምጡት አይቆጩም::

 

የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ከስልጣን መውረድ እንዳለበት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የተካሄደው የምሁራን ጉባዔ ጠየቀ

ኢሳት (ጥቅምት 14 ፥ 2009)

a12
በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ በመቀበል ከስልጣን መውረድ እንዳለበትና በሃገሪቱ የሽግግር ስርዓትና የህገ-መንግስት ረቂቅ እንደሚያስፈልግ በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የተካሄደው የምሁራን ጉባዔ አስገነዘበ።

a11የቪዥን ኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው የጉባዔውን መጠናቀቅ አስመልክተው ለኢሳት እንደገለጹት “ህወሃት የሚመራው መንግስት ህዝብን እየገደለና ሰብዓዊ መብት እየረገጠ በመሆኑ ስልጣኑን ሊለቅ ይገባል።
በቪዥን ኢትዮጵያና በኢሳት ትብብር በሳምንቱ መገባደጃ ቅዳሜና እሁድ የተዘጋጀው ኮንፈረንስ ሲጠናቀቅ እንደተገለጸው አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ የሽግግርና አዲስ ህገመንግስት ያስፈልጋል።
በኮንፈረንሱ ማጠቃለያ ላይ በኢትዮጵያ አዲስ ስርዓት ለማበጀት የሽግግር ካውንስል ማቋቋም እንደሚያስፈልግ መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

የቪዥን ኢትዮጵያ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር አሸናፊ ጎሳዬ ለኢሳት እንደገለጹት፣ የሰላም ሚና ያለውና ሃገሪቱን ወደ ሽግግር ሂደት የሚወስደው ካውንስል የተለያዩ አካላት እንዲወስኑበት ማድረግ ያስፈልጋል።
አሁን ያለው ገዢ ፓርት ህወሃት/ኢህአዴግ ግድያውን እንዲያቆምና ለሰላም በሩን በመክፈት ለድርድር ፈቃደኛ እንዲሆን ጥሪ መተላለፍን ገልጸዋል።

ዶ/ር አሸናፊ እንዳሉት በኢትዮጵያ በተካሄደው ግድያና የሰብዓዊ መብት ረገጣ እጃቸው ያለበት ባለስልጣናት ማንኛውም የገዢው ፓርቲ አባላት በህግ መጠየቅ ይኖርባቸዋል።

በቪዥን ኢትዮጵያ የተካሄደውን ስብሰባ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በፌስቡክና በኢሳት ድረገጽ ቀጥታ ስርጭት መከታተላቸው ታውቋል። የአጠቃላይ የስብሰባውን መግለጫና የተደረሰበትን ድምዳሜ ቪዥን ኢትዮጵያ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በተለይ ለኦሮሞ ልሂቃን የተላከ ማስታወሻ (ከነፃነት ዘለቀ)

ከነፃነት ዘለቀ (nzeleke35@gmail.com)

መድሓኒት ከምን እንደሚሠራ አለማወቃችን በጄ እንጂ ብዙ ፈዋሽ መድሓኒቶች የሚቀመሙት ከመርዝና ብዙም ከማንወዳቸው ነገሮች ነው፡፡ ግን መዳን ስላለብን ሃኪምና ዐዋቂ እንድንወስዳቸው የሚመክሩንን የሚቀቡም ሆኑ የሚዋጡ መድሓኒቶች አለማመንታት እንወስዳቸዋለን፡፡ በቤታችንስ ስንቶቻችን ነን የገዛ ሽንታችንን የምንጠጣ? አዎ፣ መድሓኒት ነው ከተባለ የጅብ ጉበትም ይበላል፤ የአህያ ወተትም ይጠጣል፡፡ ዋናው ከሚያሰቃየን ደዌ መፈወሱ ነው፡፡ “ምንም ቢያስቀዝን ጮማ” ብሎ ነገር በጭንቅ ወቅት አይሠራም፡፡ አሁን ያለንበት ሀገራዊ ድባብም እንዲሁ በጣም አስጨናቂና አሳሳቢ ነው፡፡

ልዩነትን ስናሽኳልለው “ልዩነት ጌጥ ነው” እንላለን፡፡ ግን ልዩነት የብልቃጥ መርዝ ነው፡፡ የብልቃጥ መርዝ ደግሞ እንደያዥው ነው፡፡ ከተፈለገ በመርዝነቱ ሰውን መጨረስ ራስንም ማጥፋት ይቻላል፡፡ ካስፈለገም ወደመድሓኒትነት ለውጦ ትክክለኛ መጠኑንና የአቀማመም ቀመሩን በጠበቀ ሁኔታ ወደ ፈዋሽ መድሓኒትነት መለወጥ ይቻላል፡፡ ምርጫው ሁለት ነው፡፡ አንድም ልዩነትን በጌጥነት ለመጠቀም ቀመሩን ማወቅና ውበትን መላበስ አንድም በመርዝነት መጠቀምና መተላለቅ፡፡

አስተሳሰብ ወደፊት እየመጠቀ እንጂ ወደኋላ እየተጎተተ ሊሄድ አይገባም፡፡”በምኒልክ የደነቆረ ዕድሜ ልኩን በምኒልክ ይምላል” እንዲሉ ሆኖብን እንጂ የሀገራችን ልሂቃንና ተማርን የምንል ወገኖች ሁሉ አስተሳሰባችን ዘመንንና ወቅትን የዋጀ ቢሆን ኖሮ በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን ቢያንስ ቢያንስ ከነሲንጋፖርና ከነማሌዥያ ተርታ በተሰለፈች ነበር፡፡ ነገር ግን በማይማዊ እልህ እግር ከወርች ታስረን ያልተገባ ፉክክርና የማያሸንፉት ጦርነት ውስጥ ገብተን እኛንም ሕዝባችንንም አገራችንንም የኋሊት ሽምጥ ስናስጋልብ እንገኛለን፡፡ ዛሬ አደጉ በሚባሉ ሀገሮች ውስጥ የሰው መሠረታዊ ፍላጎቶች ተሟልተው አንድም የሚራብና የሚጠማ የሚታረዝም ሆነ ካለመጠለያ የሚኖር ዜጋ የለም፡፡ ካላፈርክ በነፃ ብፌ በሚበላባቸው ምግብ ቤቶች፣ በነፃ በሚታደርባቸው አዳራሾችና በነፃ በሚለበስባቸው ቤተ-አልባሳት በመሄድ ራስህን አንደላቅቀህ ማኖር ትችላለህ፡፡ ድህነት ሲባል በእኛና በነሱ መሥፈርት የተለያዬ ነው፡፡ ይህን ግን መንግሥታችንን ጨምሮ ብዙዎቻችን አናውቅም፡፡ እኛና ሀገራችን ሊናገሩት የሚዘገንን የድህነት አረንቋ ውስጥ ልንገኝ የቻልነው እንግዲህ በቅድሚያ የአስተሳሰብ ድሆች በመሆናችንና ያንንም ተከትሎ በየጊዜው በሚከሰት የርስ በርስ ግጭት በምናጠፋው የሰው ሕይወትና የሀገር ሀብት ውድመት ሳቢያ ቁልቁል ስለምንጓዝ ነው፡፡

አሁንስ? እያሳለፍነው የምንገኘው መከራና ስቃይ አስተምሮናል? በውጪ ሀገራት በስደትም ይሁን በትምህርት ምክንያት ስንሄድ ከምናየው የሕዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማኅበረሰብኣዊ ሕይወት ምን ትምህርት ቀሰምን? እነዚህ ሕዝቦች ርሀብንና የርስ በርስ ቅራኔን እንዴት ፈትተው አሁን ወደሚገኙበት የዕድገት ደረጃ ደረሱ? ለመሆኑ በነሱ ሀገር አሁን በቀን ስንት ጥይት ይጮሃል? ስንትስ ሰው በገዛ መንግሥታቸው ጥይት እንደቅጠል ይረግፋል? እንደሰው ከማያያቸው ባዕድ-መሰል መንግሥት ከተላቀቁ ስንት ዘመን አለፋቸው? የልዩነታችን መሠረትና መንስኤው ምን ይሆን?

ባላምባራስ ጓንጉል ድፋባቸውና ቀኛዝማች አዝብጤ መሸሻ የዛሬ መቶ ዓመት አንዳች ጥፋት አጥፍተው ሊሆን ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሤ ጠንክር ጉዲሣና የደርጉ ሊቀ መንበር ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ፈይሣ  ያዘዟቸው ወታደሮች ደግሞ እነስንሻው መኳንንትን፣ እነለጥይበሉ ማንደፍሮህን፣ እነአበጋዝ ይማምን፣ እነሐጎስ ገመቹን፣ እነሸንቁጥ ለሊሣን… ገድለዋል፡፡ መበደልና መበዳደል ማኅበራዊ ክስተት እንጂ ለአንድ ዘውግና ለአንድ ሀገር ብቻ የሚተው ብርቅዬ ነገር አይደለም፡፡ ባለፉ ዘመናት ማን ማንን በጣም በደለ በሚል አላስፈላጊ እንካስላንትያ ውስጥ መግባት ካላስፈለገ በስተቀር ሁሉም ተበዳድሏል፤ ሁሉም ተሰዳድቧል፤ ሁሉም ይቅር ለእግዜር ተባብሏል፡፡ በጊዜ ሂደት ሁሉም ተቀያይጧል፤ ሁሉም አንድ፣ አንዱም ሁሉም ሆኗል፡፡ ያለፈን ታሪክ እያሞሰኩ ባለፈ ሕይወት አሁን መኖር ምን ዓይነት ውድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ከእኛ በላይ የሚያውቅ ከቶ ሊኖር አይችልም፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ዘመን የለዬለትን መገደልንና መሞትን ለ‹ዕድለኛ› ሟች እንደመልካም አጋጣሚ እንቁጠረውና በርሀብና በዕርዛት በቁም መሞትን የመሰለ በዓለማችን ፊት የሚያሰቅቅ ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ለዚህ የበቃነው ደግሞ የቤት ውስጥ ቀጋው ወያኔ ሳይረሳ በተባባሪነት በቆሙ በውጪ ሀገራት በተለመደው አገላለጽ በርገር እየቆረጡ በሞቀ ቤታቸው ውስጥ በሰላም በሚኖሩ ወገኖቻችን ነው፡፡

ይህ አካሄዳችን መለወጥ አለበት፡፡ መለወጥ ያለበትም አሁን ነው፡፡ መድሓኒት መዋጥ አለብን፡፡ መድሓኒት ሲዋጥ መረረኝ ጣፈጠኝ የለም፡፡ መድሓኒት በተፈጥሮ መራራ መሆኑን እናውቃለን  – ጣፋጭ እንኳን ቢሆን በሥነ ልቦናችን መራራ እንደሆነ ስለምናስብ ጥፍጥናው በምሬት ይተካና እየጎመዘዘን እንውጠዋለን፡፡ ስለዚህ ስለኛ ብቻ ብለን ሳይሆን ስለልጆቻችንና ስለመጪው ትውልድ ብለን ቢመረንም በፈዋሽነቱ ወደር የማይገኝለትን ፍቱን መድሓኒት መርጠን አሁኑኑ እንዋጥ፡፡ ጊዜ የለም!

“እግዜር ሲቆጣ ሽመል አይቆርጥም፤

ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም፡፡” እንዲሉ ሆኖብን እስካሁን ድረስ ጥቃቅን ነገሮችን በምክንያትነት እየደረደርን ላለመግባባት ስንግባባ ቆይተናል፡፡ ይህ ሂደት ግን እኛን አልጠቀመንም ብቻ ሣይሆን ሕዝባችንን ከመኖር ወዳለመኖር እየለወጠው ነው – እስካሁን ኖረ ከተባለ ሊያውም፡፡…

ልክ እንደዐማራው ሁሉ ኦሮሞም በጣም ሰፊና ታላቅ ሕዝብ  ነው፡፡ ሰፊነትና ታላቅነት የሚገለጽባቸው ባሕርያት አሉ፡፡ ከነዚህም ጥቂቶቹ በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸው የሚሸፍኑት የቦታ ስፋት፣ በሕዝብ ቁጥር ያላቸው አብላጫነት፣ በብሔራዊም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው የተማረ የሰው ኃይል ብዛት፣ ጎላ ብለው የሚታዩት ባህላዊና ሥነ ልሣናዊ የዘዬ ልዩነቶች ወዘተ. ለሰፊነታቸው በዋቢነት ሊጠቀሱ ሲችሉ ለታላቅታቸው ደግሞ ኢዮባዊ ትግስታቸው፣ ተቻችሎ የመኖር ችሎታና ብቃታቸው፣ በተራ ወፍ ዘራሽ ስብከት ያለመወሰድ ዝንባሌያቸው፤ በቋንቋ፣በባህል፣ በሃይማኖት፣ በጋብቻና በመሳሰሉት ማኅበራዊ ክሮች በፍቅርና በውዴታ መተሳሰራቸው ወዘተ. ከብዙው በጥቂቱ ሊወሱ የሚችሉ ናቸው፡፡

ኦሮሞ ያልገባበት የኢትዮጵያ ግዛት የለም – አለ ከተባለም ጥቂት የኤርትራና የትግራይ ሥፍራዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ሲወራ እሰማለሁ፡፡ የኦሮሞ ዘር ያልገባበት ኢትዮጵያዊ የዘር ሐረግ በፍጹም የለም፡፡ እያንዳንዳችን ከአባታችን ተነስተን ወደኋላ ብንቆጥር አብዛኞቻችን የኦሮሞ ስም ለማግኘት እስከ ሰባት ትውልድም መሄድ ላያስፈልገን ይችላል – የዐማራ ወይ የሌላ ስም ለኦሮሞ እንደሚሰጥ ግን ልብ አድርጉ! እናም በለየለት ሁኔታ “ገመቹ” ወይም “ረጋሣ” ዓይነት ስም በትውልድ ሐረጋችሁ ፈልጉ ማለቴ እንጂ በሌሎች ስሞችማ ኦሮሞ በሽበሽ ነው – ጋዲሣ የሚባል አማራም ስለማውቅ ይህ አሰያየም ለሁሉም የሚሠራ እንጂ ለኦሮሞው ብቻ እንዳልሆነ ይያዝልኝ (በብዙ ምዕተ ዓመታት የረጂም ጊዜ ተራክቦ ኦሮሞው በአማራው ውስጥ፣ አማራውም በኦሮሞው ውስጥ ቀልጠዋል)፡፡ “ኦሮሞ ከኢትዮጵያ ይገነጠላል” ለሚለው የመነቸከ ቀልድ ኦሮሞዎችን ራሳቸውን ጨምሮ ብዙ ዜጎች “ቅርንጫፍ እንጂ ግንድ ሊገነጠል ይችላል ወይ?” የሚል ትክክለኛ መልስ የሚሰጡበት አንደኛው ምክንያት ይሄው የኦሮሞዎች ሁሉንም የመሆን ተፈጥሯዊ ጠባይ ነው፡፡ በአዲሱ የወያኔ ዘፈን ካልጨፈርን በስተቀር የኢትዮጵያ ትልቁ መለያም የሕዝቧ የደም ትስስር ነው – ለዚህም እኮ ነው እንደወያኔና ደቀ መዛሙርቱ ሤረኛ አጠራር “የኢትዮጵያ ሕዝቦች” ሣይሆን “የኢትዮጵያ ሕዝብ” ሲባል ከውስጠ-ውሳጤያችን ጀምሮ አንዳንዶቻችንን ደስ የሚለን!

ኦሮሞ እንደትግሬ ወይም እንደጽዮናውያን በጣም የተቀራረበ ጎሣዊ አስተሳሰብና ዘውጋዊ ትስስር የለውም ፤ ዐማራም እንዲሁ ነው ወይም ቢያንስ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ እንዲሁ ነበር፡፡ ብዙኃት ተጋሩን ወደዚህ እጅግ አስቀያሚ የጎሠኝነት ስሜት ለማድረስ ሕወሓት የወሰዳቸውን እርምጃዎችና በዚያም ሳቢያ ያደረሰውን ዕልቂት፣ በተጋሩና በተለይም በዐማሮች መካከል የነዛውን የጥላቻ መርዝና የዘመናት ፕሮፓጋንዳ ስናስብ ጥፋትን ዘርቶ ዕልቂትና ውድመትን ለማዝመር ከባድ አለመሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ግን በተለይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እነዚህን ሁለት ሕዝቦች – ኦሮሞንና አማራን – እየገፉ ወደ ደምና አጥንት ጅረት ሊከቷቸው ሌት ተቀን በመትጋት ላይ የሚገኙ ይመስላል – እንደኔ ደግሞ ጨለማው ሊነጋ የተቃረበ ይመስለኛልና ከዚህ በኋላ ይህ እንደውሻ አጥንትና ዘር እያነፈነፉ መጠራራትና ለጥፋት መሰማራት ሊያከትም ጫፍ ላይ ደርሷል እላለሁ፡፡ እዚህ ላይ ልብ ማለት የሚገባን ጉዳይ ግን አንድን ማኅበረሰብ ጊዜ ይፍጅ እንጂ ሸረኞችና ተንኮለኞች በቀደዱት የጥፋት ቦይ መክተት የሚቻል መሆኑን ነው፡፡

ውድ ወገኖቼ! አሁን ጊዜ የለንም፤ ዐማራና ኦሮሞ ወደ ዐማራነትና ኦሮሞነት ለይቶላቸው ከመዝቀጣቸው በፊት እንድረስላቸው፡፡ ልድገመው – ኦሮሞና ዐማራ ወደ ኦሮሞነትና ወደ ዐማራነት በአራዶቹ አገላለጽ ከመሸብለላቸው በፊት ቀድመን ካልደረስንላቸው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከታሪክ መዝገብም ተፍቃ ትጠፋለች፤ ይህ ሰይጣናዊ ትንቢቴ እውን እንደማይሆን በአንድዬ ብተማመንም “ጠርጥር ገንፎም አለው ስንጥር” ይባላልና የሆነው ይሁን በሚል እጃችንን አጣጥፈን መቀመጡ ከእስካሁኑ የከፋ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ትላልቅ ምሠሦዎች ሦስት ናቸው፤ አንደኛው ሳይወድ በግዱ አዝምሟል – የጊዜ ጉዳይ ነው እንዳዘመመም አይቀርም፤ ሁለቱ ግን እስካሁን ደህና ነበሩ – በብዙ የንፋስ ንፅውፅውታ እየተመቱም ቢሆን በጽናት እንደቆሙ እስከቅርብ ዓመታት ዘልቀው ነበር፤ ከአሁን በኋላ ግን አስጊ ነው፤ የጽናታቸውም ምክንያት ሳይደግስ አይጣላምና (a blessing in disguise) በአካባቢና በሕዝብ ብዛት የበላይ እንደመሆናቸው ሁሉንም ወደ አንድ ለማሰባሰብና በአንድ ጠባብ ሥነ ልቦናዊ ቦይ እንዲፈሱ ለማደረግ ባለመቻሉ ነው – እነዚህን ዘውጎች በትናንሽ ነገዶች ሣይቀር ለመበጣጠቅ ሳይሞከር ቀርቶ ሣይሆን ለመሠሪዎች ተንኮል ምቹ አልነበሩም፡፡ ቀስ በቀስና በጊዜ ሂደት ግን የማይቻል ነገር የለምና እነዚህ ሕዝቦች ወደተዘጋጀላቸው የጥበት መንገድ ሊገቡ ይችላሉ፤ አዝማሚያዎችም በግልጽ እየታዩ ነው፡፡ ለዚህም ነው የኢትዮጵያ አምላክ በቅርብ ጣልቃ የሚገባው፡፡ ደስ ይበለን – ጣልቃ ይገባል!…(እውነቴን ነው የምላችሁ ማን እንዲህ በል እንደሚለኝ አላውቅም፤ግን እውነቱ ይሄውና ይው ነው – በቅርብም ኢትዮጵያን የሚያድን ተዓምር እናያለን፡፡ ታሪክም ለዚህ ምሥክሬ ው፡፡)

ኦሮሞ ሰፊ ነው፡፡ የሸዋ ኦሮሞ አለ፡፡ የወለጋ ኦሮሞ አለ፡፡ የአርሲ ኦሮሞ አለ፡፡ የባሌ ኦሮሞ አለ፡፡ የወሎ ኦሮሞ አለ፡፡ ባጭሩ የሌለ ኦሮሞ የለም፡፡ “ኦሮሞ ታዲያ ከየት ነው የሚገነጠለው?” ብለን ስንጠይቅ ችግሩ ከሕዝብ ሣይሆን ከሌላ ሆኖ እናገኘዋን፡፡ ያ “ሌላ” ነገር ደግሞ በዋናነትም ባይሆን በመለስተኛ አጫፋሪነትና በዕቅድ አስፈጻሚነት ልሂቅ ተብዬውን ሀገር አጥፊና ሀገር አልሚ ይይዛል፡፡ የተማረ ሰው ለልማት ቅርብ የመሆኑን ያህል ለጥፋትም በጣም የቀረበ ስለመሆኑ በተለይ ያሳለፍናቸው 42 የመከራና የስቃይ ዓመታት በግልጽ ይናገራሉ፡፡ ልሂቅ ሀገር አጥፊና አልሚ አልሁኝ? ራሳችንን እንመርምር፡፡

ኦሮሞን እገነጥላለሁ ብሎ የተነሣ ወገን ካለ ዕብድ ነው፡፡ እርግጥ ነው አማራጭ ሚዲያ ባለመኖሩ ምክንያት በተወሰኑ በሞኖፖል በተያዙ የሚዲያ አውታሮች የተወሰነ ግርግርና ጊዜያዊ የልብ መሸፈት መፍጠር ይቻላል፡፡ እውነቱ ሲገለጥ ግን ሁሉም አቅል ይገዛል፡፡ እስከዚያውና እንደ እውነቱም ከሆነ ግና “mob” የምንለው ነገር በጣም መጥፎ ነው፡፡ ክርስቶስን ያሰቀለው ሞብ ነው፡፡ ብሩተስን ያሰቀለው ሞብ ነው፡፡ በሞብ ምክንያት ብዙ ሀገሮች ፈርሰዋል፤ ተፈጥረዋልም፡፡ በሞብ ምክንያት እጅግ ብዙ ንጹሓን የዓለም ዜጎች ለሰይጣን ጭዳነት ተዳርገዋል፤ አሁንም ድረስ፡፡ በሞባዊ እንቅስቀሴ ወቅት ምክንያትና ሎጂክ እሥር ቤት ይገባሉ፤ ይገረፋሉ፤ በጭካኔም ይታረዳሉ፡፡ ስለሆነም “ሞብ አያስፈራም፤ ሞብ አገር አይበትንም፤ ሞብ አገር አያስገነጥልም ….” አልልም፡፡ ብዙ መጥፎ ውሳኔዎችና መጥፎ ድርጊቶች በሞብ ጊዜ – በስሜት ግልቢያ ወቅት – ይከናወናሉ፡፡ በነዚህን መሰል መጥፎ ድርጊቶች ወቅት የሚከሰቱ የክፋትና የውድመት ተግባራት ለከፍተኛ ጸጸት የሚዳርጉና ብዙዎቹም የማይቀለበስ አሉታዊ ጠባሳ የሚያኖሩ ናቸው፡፡ በተለይ ወጣቱ – የነብር ጣቱ – ትኩስ ኃይል እንደመሆኑ አዲስ ነገርን የማየት ጉጉት አለው፡፡ መሠሪዎች ይህን ኃይል ተጠቅመው ታሪክን ቢያንሻፍፉና ቢያጣምሙ በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ – ይህን እስኪበቃን አይተናል፤ እያየንም ነውና ለኛ አዲስ አይደለም፡፡ ስለሆነም ምራቅ የዋጡ የማኅበረሰቦቻችን አባላት ብዙ ይጠበቅባቸዋል – ከየጎሣው ያሉ አባቶችና እናቶች ዝም አይበሉ፡፡

ኢትዮጵያዊነትን በተመለከተ በኦሮሞ ሕዝብ ውስጥ የተለያዩ አስተሳሰቦች እንዳሉ ማንም ይገነዘባል፡፡ ጥቂት የማይባሉ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት አቋም ያላቸው የኦሮሞ ልሂቃን መኖራቸውም የማይታወቅ አይመስለኝም፡፡ ጥሪየ እነዚህ ወንድሞቼና እህቶቼ እንዲሁም ልጆቼ ወደኅናሊቸው እንዲመለሱና የጋራ ሀገር እንዲኖረን በጋራ ትግል እንዲሠለፉ ነው፡፡ ከስሜት የወጣ የሰከነ ትግል እስካልተደረገ ድረስ የጠላት መሣሪያ እንደሆኑ ዕለተ ምፅዓትን እየተሰቃዩ መጠበቅ ነው – ተነጣጥሎ ደግሞ ነፃነት ዕርም ናት፤ አትገኝም፡፡ ከእልህ ወጥተን ወደ አመክንዮ እንግባ፡፡ ሥልጣን እንደሆነች ወንበሯ አንዲት ናት፡፡ ያቺን ወንበር ደግሞ ማንም ይያዛት ግን አንዲት እንደሆነች ዓለም ታልፋለች እንጂ እንኳንስ ሺህና ሚሊዮን ሁለትም አትሆንም፡፡ ለሚራኮትባት ሁሉ ብትሆን ደስታውን ባልቻለችው – ስገምት፡፡ ግን ካንድ በላይ ቢቀመጡባት ትሰባበራለችና አትችልም፡፡ ታዲያ ለዚህች አንዲት ምሥኪን ወንበር ይህን ያህል ሕዝብ በውጪና በሀገር ውስጥ በጎሣና በዘር፣ በሃይማኖትና በወንዝ ልጅነት ጎራ ለይቶ አበሳውን ማየቱ ለጤና ነው ትላላችሁ? አቅል እንግዛ እንጂ! “ሀበሻ ዱሮውንም…” ከሚል ትችት መውጣት አለብን – ሀበሻነትና ሀበሻዊ ማንነት በራሱ አጠያያቂ ቢሆንም፡፡

ትናንት በኦኤምኤን – በዐዋጅ ብከለከልም በድብቅ – አንድ ልዩ ዝግጅት ተከታትያለሁ – ባማርኛ፡፡ በዚህ ዝግጅት አወያዩ ደጀኔ ጉተማ ለጠየቀው አንድ ጥያቄ ጃዋር መሀመድ የሰጠው መልስ እንዲህ ነበር – “የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ከሩዋንዳ ጋር የሚመሳሰል አይመስለኝም፡፡ እንደኔ የዚህች አገር መፃዒ ዕጣ-ፋንታ ከዩጎዝላቪያና ከሶቭየት ኅብረት ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡” የመልሱ ጥቅል ይዘት እንዲህ ነበር፡፡

በጣም ገረመኝ፡፡ ከዚህ አባባል ብዙ ነገር መገንዘብ ይቻላል – “የዘፈን ዳር ዳሩ እስክስታ ነው”፤ ጃዋር ምን ማለት እንደፈለገ ብቻ ሣይሆን ምን እንዲሆንለት እንደሚፈልግ ሣይቀር ወደየትም የጥንቆላ ቤት መሄድ ሳያስፈልገን በቀላሉ መረዳት አይከብድም – ከዚያ ይሰውር እንጂ፡፡ በነገራችን ላይ ከሁለትና ከዚያ በላይ ዘውጎች የምትወለዱ ወገኖቻችን ልዩነቶቻችንን ለማጦዝና የሆነ ዓላማ ለማሣካት ከምትሞክሩ ይልቅ የሁለት ቤት አባልነታችሁን የማይገሠስ ወርቃማ ዕድል በመጠቀም ሕዝቦችን ለማስማማትና ለማዋሃድ ብትጥሩ በታሪክም በትውልድም ትከበራላችሁ፡፡ ሰዎች ክፉ ከሆኑ ፣ በሀብትና በሥልጣን ሱስ ከተለከፉ፣ በእርኩስ መንፈስ ከተነዱና ጤናማ ኅሊናቸውን በሆነ ኃይል ከተነጠቁ … ልዩነትን ለክፉ ዓላማ መጠቀም ይችላሉ – እንደ አብነት ጎጃሜዎቹን መለስ ዜናዊንና ገብሩ አሥራትን(የአሁን እሱነቱን አይደለም!)፣ ኦሮሞውን አዲሳለም ባሌማንና ወሎየውን ሼህ አላሙዲንን መጥቀሱ በቂ ነው፡፡ ልዩነትን በተለይም በራስ ውስጥ የሚገኝን የሁለትነት ልዩነት በጎ ላልሆነ ዓላማ መጠቀም ከኩነኔዎችና ከክፋቶች ሁሉ የበለጠ መጥፎ ተግባር ነው፡፡ በኔ ውስጥ ያለውን አንዱን ማንነት በኔ ውስጥ በሚገኝ ሌላ ማንነት ብደበድበው፣ ደብዳቢውም ተደብዳበውም እኔ ራሴው ነኝና በየትኛውም መለኪያ ልክ አልሆንም ብቻ ሣይሆን ትልቁን የወንጀል ፍርድ ያስበይንብኛል – ራስን መግደል ከወንጀሎች ሁሉ የከፋ ነውና! እነጀዋርም የዚህ ሾተላይ ሰለባዎች ናቸው፡፡ ሙሉ በሙሉ “እኔ ‹ንጹሕ‹ አማራ ነኝ” የሚልና ሙሉ በሙሉ “እኔ ‹ንጹሕ› ኦሮሞ ነኝ” የሚል ሰው (ደግነቱ በየዋህነት እንዲህ የሚል ቢኖርም ከእውነት ግን ሊኖር አይችልም እንጂ) ይህን ዓይነት ስህተት ቢሠራ ንስሃ አለው – አለማወቁና አለኝ የሚለው “ንጹሕ” የኦሮሞ ወይም የአማራ ደም መጠነኛ አዘኔታና አመክሮ ሊያስገኝለት ይችል ይሆናል፤ እነጀዋር ግን ሕዝብን አንድ ለማድረግ ማድረግ ከሚጠበቅባቸው መልካም እንቅስቃሴ ውጪ ለመለያየትና ክፍፍል ለመፍጠር ጥረት ቢያደርጉ አይደለም እግዚአብሔር ሰይጣን ራሱ ይታዘባቸዋል – መሬቱ የተደላደለላቸው ኅብረትንና ስምምነትን ለመፍጠር ብቻ ነውና ሁለቱንም ሆነህ ወደ አንዱ ብታዳላ ማዳላትህን ማንኛውም ወገን በፀጋ ሊቀበለው አይገባም – ነግ በኔም እኮ አለ! ለምሣሌ እኔ የጉራጌ ደም እያለብኝ በጉራጌ ላይ ከዘመትኩ ጤናየ ተቃውሷል ማለት ነውና የሀኪም ክትትል በእጅጉ ያስፈልገኛል፡፡ ምን ማለት እንደፈልግሁ በተለይ የሁለት ዘውጎች ውጤት የሆናችሁ ዜጎች በደንብ የገባችሁ ይመስለኛል፡፡

ለማንኛውም የዚህ ንግግር አንድምታ (implication) ኦሮምያ የሚባል በታሪክ የሚታወቅ አንድ ሀገር ኖሮ፣ አማሪያ የሚባል ራሱን የቻለ ግዛት ኖሮ፣ ከፊቾ የሚባል፣ ሃዲያ የሚባል፣ ጠምባሮ የሚባል፣ ጌዲዮ የሚባል፣ ከምባታ የሚባል፣አፋር የሚባል…. ራሳቸውን የቻሉና በተባበሩት መንግሥታት መዝገብ ውስጥ እንደነፃ ሀገር ተመዝግበው የሚኖሩ “የምሥራቅ አፍሪቃ ሀገራት” ኖረው በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በሕወሓት የአፓርታይድ አገዛዝ ሥር ያሉትን “ነጻና ፌዴራል መንግሥታት” በቅጡ የማያስማማ ሁኔታ ከተፈጠረ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሩዋንዳ ዓይነት የዘር ፍጅት ሣይሆን እንደቀድሞዋ ሶቭየት ኅብረትና ዩጎዝላቪያ “ኢምፓየሪቱ” ትበታተናለች የሚል አስተያየትና ቅድመ ትንበያ ነው ጆሃር የሰጠው – “ህልም እልም” ብያለሁ ጆሃር፡፡ ይቺ የፈረደባት ኢምፓየር ደግሞ ስንቶች የኦሮሞ ነገሥታትና መሣፍንት ወያኔ ወደ ሥልጣን እስከመጣበት እስከ 1983ዓ.ም ድረስ ሲገዟትና ሲነዷት እንደነበሩ መጻሕፍት ይናገራሉ፡፡ ዕንቆቅልሽ ምን አውቅልህ፡፡ (ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ ምነው ሰሞኑን ፀጥ አልክ? ኧረ ብቅ በል!)

እንደኔ እንደኔ ኢትዮጵያ መጥፎ ዕድል ከገጠማት የምታመራው ወደ ራሺያና ወደ ዩጎዝላቪያ ሣይሆን ወደ ሶማሊያና ሦርያ እንዲሁም ወያኔዎች በጭካኔያቸው ቀጥለው የትግራይን ሕዝብ መከታና ደጀን በማድረግ ሌሎችን መጨፍጨፋቸውን አባብሰው ከገፉበት ጉዟችን በቀጥታ የሚያመራው ወደ ሩዋንዳ ነው – ማንም ሲያምረው ይቅር እንጂ ኢትዮጵያ ወደ ራሺያ ሊያስኬዳት የሚያስችል ታሪካዊ መደላድልም ሆነ ማኅበረሰብኣዊ ዝግጅት የላትም፤ እውነትና ትንቢት ይለያያሉ ወንድሞቼ፡፡ ይህን መጠራጠር ቂልነት ነው፡፡ በመሠረቱ እኔ የፖለቲካ ሣይንስ ተማሪ አይደለሁም፡፡ ነገር ግን “የኢትዮጵያ ሁኔታ እየከፋ ከመጣ የምንሄደው ወደ ዩጎዝላቪያ ነው ወይንስ ወደ ሩዋንዳ?” ተብዬ ብጠየቅ መልሱ እጅግ በጣም ቀላልና እርሱም ወደ ሩዋንዳ መሆኑን ማስረዳት አይቸግረኝም፡፡ ይልቁንስ “አይመጣምን ትተሸ ይመጣልን ባሰብሽ” ነውና ነገሩ ጤነኛ ነኝ የሚል ዜጋ ሁሉ ይህን ነገር አሁኑኑ ይጨነቅበት፡፡

ብዙ ስናገር መዋል እንደሌለብኝ አውቃለሁ፡ አንዳንድ የኦሮሞ ልሂቃን ከገባችሁበት ወረተኛና ከፋፋይ የባዕዳን አስተሳሰብ ባፋጣኝ ውጡ፡፡ ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ከሞላ ጎደል በእኩል ደረጃ ተረግጠው የሚኖሩባት የምስኪኖች ሀገር ናት፡፡ መበታተን የሚባል ቃል ያለው በልሂቃን ምናብ ውስጥ እንጂ በእውን ምድር ላይ የለም፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ታች ወርዶ ማየትና ኑሮውን እየኖሩ የሚፈልገውንና የማይፈልገውን ማጥናት ይገባል፡፡ የሚሻው አምባነኖችን በአምባገነኖች መተካት ወይም እንደዶሮ ተገነጣጥሎ ለየብቻው መኖርን ሳይሆን እፎይ ብሎ በአንድነትና በነፃነት የሚኖርባትንና ሰብኣዊ መብቶች የሚከበሩባትን የጋራ ሀገር መፍጠር ነው፡፡ በጥቃቅን ታሪካዊ ቁርሾ ምክንያት ትልቅ ሀገር አትፈርስም፡፡ ብትፈርስ ደግሞ ማንም ከማንም በልጦ የማይጠቀምባት ወይም የማይጎዳባት የጃርት መፈንጫ ትሆናለች እንጂ በላም አለኝ በሰማይ በሚገነቡ ትናንሽ መንግሥታት ውስጥ ማንም አፄ በጉልበቱ ከኮልኮሌዎቹ ጋር የሚዘባነንባቸው ብጭቅጫቂ ሀገራት አይመሠረቱም፡፡ ይህ አስተሳሰብ ህልም ነው፡፡

ባንዴራን በሚመለከት ሕዝብን ባናወናብድ መልካም ነው፡፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንደነበረችና እንደነገሩም ቢሆን አሁንም እንዳለች የማንቀበል ከሆነ እንደእስካሁኑ ሁሉ ስምምነቶችና ድርድሮች ሳይጀመሩ እያለቁ ዕዳችን ይቀጥላል፡፡ ይህም ሁኔታ ለጋራ ጠላቶቻችን ምቾትንና እፎይታን እየፈጠረ የግፍ አገዛዙ – እንደሰውኛ አስተያየትና ግምት – ማብቂያ የሌለው ይሆናል፡፡ አዲስ ነገር እየፈጠርን ሕዝብን በተለይም ወጣቱን ውዥንብር ውስጥ አንክተት፡፡ ችግራችን የእራፊ ጨርቆች ቁጥር ማነስ ወይም መብዛት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን ለዘመናት የገዙ የኦሮሞ ነገሥታት ያውለበልቡት የነበሩት የትኛውን ባንዴራ እንደነበረ ታሪክና የታሪክ ሰዎች ቀርተው መሬቱም ያውቃል፡፡ ከዚህ ከኢትዮጵያዊነት አኩሪ ነጥብ አንጻር ራስ አሊ ሚራህ ድንቅ ኢትዮጵያዊ አባት ነበሩ – “የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን የአፋር ሰው ግመሎቻችንም ያውቃሉ” ብለው የተናገሩት ዘመናትን ተሻጋሪ በሳል ንግግር አሁንም ትኩስ እንደሆነ አለ፡፡ ከርሳቸው እንማርና ከታሪክ ተወቃሽነት እንዳን፡፡ የወረት ፍቅር ወረት ነውና ያልፋል፡፡ ስካርም ምን ጊዜም ስካር ነውና በስካር ወቅት የምናደርጋቸው አንዳንድ አልባሌ ነገሮች ለትዝብት እንዳይዳርጉን መጠንቀቅ አለብን፡፡ ወረትም ስካርም ቢያልፉም ጠባሳ ትተው እንጂ እንዲሁ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከብዥታ እንውጣና ወደ እውነቱ እንቅረብ፡፡ እውነት እንደፀሐይ ጨረር በቀጥታ ሲያዩት ቢያጥበረብርም አማራጭ የለንምና ትውልዳችንን ማዳን ከፈለግን ከልቦለድ ዓለም ባፋጣኝ እንውጣ፡፡ ወያኔ ሕዝባዊ እምቢተኝነቱን በቀላሉ እየጨፈለቀ ለጊዜውም ቢሆን ትንሽ ፋታ ያገኘ የመሰለው በኦሮሞና በአማራ ልሂቃን ዕርዳታ ነው – በተለይም በኦሮሞዎቹ፡፡ ችግሩን ቀን ይፈታዋል፡፡ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን እነሱ ምቹ ቦታ ተቀምጠው ሕዝብን የሚከፋፍሉና ልብ ለልብ እንዳይገናኝ ለማድረግ ልዩነትን የሚዘሩ ክፉ ሰዎች አሉ፡፡ ከናዝሬት አዲስ አበባ በደቂቃዎች ውስጥ በኅብረት ጉዞ መድረስ እየተቻለ በኬኒያና በደቡብ ሱዳን ዞረው በሊማሊሞና በግራካሱ በኩል ወደ ፊንፊኔ ለመግባት የሚቋምጡ ኃይሎች እንዳሉ በበኩሌ አውቃለሁ፡፡ ማንም ግን ብቻውን ተጉዞ አራት ኪሎ ይቅርና ቃሊቲም ይሁን ሰንዳፋ አይደርስም፡፡ የዐዋቂ አጥፊ አንሁን፡፡

ቋንቋና ባህልን በተመለከተ ማንኛውም ዜጋ የራሴ ነው የሚለውን ቋንቋና ባህል ማሳደግና ለትውልድ ማስተላለፍ መብቱ ብቻ ሣይሆን ግዴታውም ነው፡፡ ስለሆነም የዚህን ሰፊ ሕዝብ ቋንቋና ባህል ማክበርና ጥቅም ላይ ማዋል የኦሮሞ ብቻ ሣይሆን የሌሎቻችንም ሁሉ የውዴታ ግዴታ ነው፤ የኦሮሞው ብቻም ሣይሆን – የጋራችን ሀብታችንን አማርኛን ሳንዘነጋ – የሁሉም ዘውግና ነገድ ቋንቋ ማደግና መበልጸግ አለበት፡፡ ይህ ሲባል ደግሞ በተለይ ቋንቋ የመግባቢያ መሣሪያ እንጂ አለልክ የሚኮፈሱበት ወይም ሌሎችን ለመናቅና ለማናናቅ የሚጠቀሙበት የግል ዕቃ እንዳልሆነ መረዳት ተገቢ ነው – አንተ ቶሎሣ ባጋጣሚ ኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋህ ሆነ፤ ማነህ አንተ ወንድሜ አቻምየለህ ደግሞ ዐማርኛ ሊሆንብህ ተገደድህ ልበል፡፡ እናሳ? ወደንና ፈቅደን ባልሆንነው ነገር ዝንታለሙን የቋንቋ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቀን መኖር አለብን? እንደግ እንጂ! ሰው የሆነ ፍጡር ሁሉ ኦሮምኛን/አማርኛን መናገር ባይችል እንኳን የኦሮሞነትን/የአማራነትን ማንነት መላበስ ይከብደው እንደሆነ እንጂ የኦሮምኛን/የአማርኛን የባለቤትነት ይዞታ የመጋራት ያልተሸራረፈ መብት አለው – ሁሉም ቋንቋ የሁሉም ነው – ቋንቋ የሰው ነው፤ ባለቤት አልባ የሆኑ ነገሮች ውስጥ ቋንቋ የመጀመሪያው ነው – ባለማወቅና በሞኝነት ግን ሰዎች በቋንቋ ምክንያት ብዙ ሲነታረኩ ይስተዋላል፡፡ ለምሣሌ እንግሊዝኛ አሁን ባለቤት የለውም፡፡ አማርኛም በኢትዮጵያ የዚያኑ ያህል ነው፡፡ በሂደት ደግሞ ሁሉም ቋንቋዎች ወደዚህ ደረጃ ሊደርሱ ይገባል ወይም መድረስ አለባቸው፤ ይህ የኔ ምኞት ነው – ምናልባትም በተግባር ሳይታይ ዓለማችን ቅርጽዋን የምትቀይርበት ከንቱ ምኞት፡፡ ለማንኛውም አንዱ የሌላውን ልሣን ሲያውቅና ሁሉም የሁሉንም ቋንቋ ተናጋሪ ሲሆን ማንም እየተነሣ “የኛ ቋንቋ የናንተ ቋንቋ” የማለት ሥልጣን የለውም፡፡ የኔ ያንተ፣ ያንተም የኔ ይሆኑና አንደኛው የግጭት መንስኤ ይወገዳል፡፡ መሆን ያለበት እንደዚያ ነው፡፡

በቋንቋ አርበኝነት የሀገርም ሆነ የግለሰብ ዕድገት አይመጣም፡፡ የሥነ ልሣንን ህገ ተፈጥሮ እንወቅ፡፡ በሥነ ልሣን ልደትና ሞት የሚጠቀሱ መሠረታዊ አላባውያን አሉ – በጉልበትና በዐዋጅ፣ በዕብሪትና በጥላቻ ግን አንድ ቋንቋ አያድግም፤ አይጠፋምም፡፡ ስለዚህ ትልቁ መፍትሔ ወደ ኅሊና መመለስ ነውና ከጥላቻ መንፈስ መውጣትም ነውና በፍቅር ማዕበል ውስጥ እየዋኙ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ዜጋን በዜግነቱ ብቻ መቀበልና ተፈቃቅዶ አብሮ መኖርም ነው በነዚህ ነጥቦች ዙሪያ እናተኩር፡፡ ኦሮሞና አማራ ትግሬና ጊሚራ የመጣው የዛሬ ስንት ዓመት ገደማ ነው፤ ሰው ግን ሲፈጠር አንድ ብቻ ነበር – ከዚያ ሔዋን ተጨመረችና ሁለት ሆኑ፤ ቀስ ብሎ ደግሞ እኛ ተጨመርንና ሰባት ቢሊዮንን አለፍን፤ ሰው በዛ ነገር በዛ፡፡ እናም ግዴላችም “ፍቅር ካለ ዘጠኝ ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል” ይባላልና ፍቅር ይኑረን፡፡ ፍቅር ካለን የሚጎድለን ነገር አይኖርም፡፡ ፍቅር ከሌለን ግን አለን የምንለው ብዙ ነገር ሁሉ የኛ አይደለም – በዪና ቀማኛ ይታዘዝበታልና፡፡ መደማመጥንና መግባባትን ያድለን፤ ሰላም፡፡

ከተንኮለኛ ሰው ስንቅ አይቀላቅሉም ( አሰገደች ቶሎሳ )

ከተንኮለኛ ሰው ስንቅ አይቀላቅሉም ( አሰገደች ቶሎሳ )

የንብን ቀፎ ተንተርሰው የሚያደምጡትን የህዝብ ድምፅ እንደ እንቅልፍ ክኒን የሆነላቸው የወያኔ እብሪተኞች መሬትን ሽጠው የበሉት ስብና ጮማ ጆሮአቸውን ደፍኗቸው መልሰው ለራሳችን የህዝብ ተቆርቋሪ የድሆችን እምባ ጠባቂ ነን እያሉ ዛሬም በውድቀታቸው ዋዜማ የሀገር ብቸኛ አማራጭ እኛው ነን እያሉ ይቀልዱብናል:: ከጥንትም ይህ መሰሪ ዓላማው ብሄራዊ የሀገር ፍቅርና ህዝብን ያማከለ አልነበረምና በድቡሽት ላይ እንደተዋቀረ ቤት የውጭውን አሳምሮ የአልባ ኒያን ሶሾሊዝምን ፕሮግራም የገለበጠውን የትግራይን ሪፕብሊክ ሊመሰርት ነበር የመከረው:: ሆኖም በዚህ ጠባብና ጨለምተኛ አላማው የመጀመሪያ ተጠያቂው የራሱን የትግራይን ህዝብ ነበር በዚህ በተዛባ አላማው አባቱን ያላጣ፣ ልጇን ያላጣች እናት፣ ወንደሟን ያላጣች እህት የትግራይ ልጅ አልነበረም ምንም እንኳን ይህ ሁሉ ግፍ በራሱ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ቢሆንም ዛሬ ያለውን የትግራይን ህዝብና የወያኔን ግንኙነት ስንመለከት የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን:: በተለይም የትግራይ ምሁራን ክፍል ከወያኔ በፈሰሰላቸው መና በኢትዬጵያ ህዝብ ሀብት ናውዘው እየደረስ ያለው የጐሳ አስተዳደር ጥፋት አልታያቸው ብሏል:: በትግራይ ህዝብ ስም መነገዱ ይቁም ከማለት ይልቅ የሚካሄደውን የግፍ ጭካኔ የሚገባ ነው እያሉ ነው መደገፍ ተያይዘውታል::

በአንድ ወቅት የቀድሞው መሪያቸው መለስ ዜናዊ በራሱ አንደበት የህወሀት የመኖር ህልውናው የተመሰረተው የሌሎች ብሄሮች በተለይም አማራና ኦሮሞ ተስማምቶ የማይኖሩ ለታ ነውና ሁለቱ ብሔሮች ዘወትር እሳትና ጭድ ሆነው መቀጠል እንዳለባቸው የድርጅታችን እምነት ነው:: በዚህ ዙሪያ ድርጅቶታችን ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ሲል ተድምጧል:: በውጤቱም ህዝብን በመከፋፈል ልዩነት የጠፋ የዘር፣ የጐሳ ፣ የኃይማኖት፣ የአውራጃ የቀበሌና የመንደር ግጭቶችን በመፍጠር እርስ በርሳቸው እያፋጁ ሰላምና ኢትዮጵያዊንትን አራርቀው እነርሱ የሀገሪቱን ሀብት ያጋብሳሉ ወያኔዎች ከሱዳን ጋር የትግራይ ድንበር ለመፍጠር በያዙት እቅድ መሠረት በአካባቢ የሚኖሩትን የጎንደር አስተዳደር ወረዳዎች በተለይ የወልቃይት፣ ጠገዴና ሑመራ አካባቢ ኢትዮጵያውያንን በግፍ አስለቅቀው ለም የእርሻ መሬት በወረራ ይዘዋል። በሕዝቡ ላይ የሚፈጸመው ሁሉን አቀፍ ግፍ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፣ በይዘቱ ከኢጣሊያ ፋሽስት ያላነሰ ግፍ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ ሳይለይ ቀጥሏል። ለዚህም ይመስላል የአካባቢው ህብረተሰብ፡- በሆድም ያላችሁ በጫንቃም ያላችሁየወያኔን ነገር ትረሱታላችሁ በማለት የተቀኙት።

እንደሚታወቀው  ወያኔዎች የወረራ አድማስን በማስፋት በከፋ መልኩ በጠገዴ ሠሮቋና በታች አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ ተጨማሪ ሰፊ የእርሻ መሬት ፍለጋ ዘመቻው ላይ ተገተው እየሰሩበት ነው።. በትግራይ መንግሥት የሰለጠኑ ሚሊሻዎችና በረከት ስምዖን የሚመራውና የአማራን ሕዝብ እወክላለሁ በሚለው ሆድ-አደር ብአዴን አስፈጻሚነት የመስፋፋት ዘመቻውን እውን ለማድረግ በከፋ መልኩ ከፍ ዝቅ እየተባለም ነው። ወረራውን በመቃወም መብታችን ይከበር ያሉትን የሀገሬው ሰዎች ትግራይ አሰልጥነው ባስታጠቋቸው ልዩ ሚሊሻዎች መግደልና እስርን ተያይዘውታል:: በዚህ ግጭት ብዙ ሰዎች ሞተዋል ተጎድተዋል፣ ውዝግቡም አልበረደም ይቀጥላል። ወያኔዎች በነደፉት ትግራይን የማስፋፋት አዲስ እና ቀጣይ ዓላማ ካሁን ቀደም በኃይል ይዘው የትግራይ ክልል ነው ብለው ከወረሩት ዳንሻ ከተማ ወደ ደቡብ ምዕራብ 103 ኪሎ ሜትር በረሃውን አቋርጦ ከአብደራፊ ጋር ለማገናኘት ብሎም ሰፋፊ የእርሻና የትግራይ ሠፈራ ለማካሄድ ታስቦ ሱር በተባለው የወያኔ የመንገድ ሥራ ተሰርቷል። ለዚህ መንገድ ሥራ የሚወጣውን $300 ሚሊዮን ብር ወጪ የኢትዮጵያ መንግሥት መድቧል። በዚህ ሳያቆም ከሰሜን ወደ ደቡብ የሱዳንን ጠረፍ እያዋሰነ ማለትም ከሑመራ ጫፍ ከልጉዲ ተነስቶ ወደ አብደራፊ የሚያገናኘው መንገድ በአስፋልት እየተሠራ ነው። የዚህ ወረራ ቅርጽ ሦስት ማዕዘን ቅርጽ የያዘ ሲሆን፣በዚህ አካሄድ የትግራይ ምድራዊ አቀማመጥ ተቀይሮ በእስራኤልና አረቦች ያለው ካርታ ዓይነት እየሆነ መጥቷል። ይህም ብቻ ሳይሆን መተማን አልፎ እስከ አባይ ግድብ ድረስ እንሄዳለን የሚል ህልም አላቸው። ይህ አዲስ ወረራ ለምን አስፈለገ ቢባል፣ ለም የሆነውንና ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን መሬት ወያኔዎች ይዘው ባለቤት የሆነው የአካባቢው ኑዋሪው ሕዝብ ከውጪ የንግድም ሆነ ሌላ ግንኙነት እንዳይኖረው በብቸኝነት ለመቆጣጠር መሆኑ ግልፅ ነው።

ከዚህ ባሻገር በስብሀት ነጋ በሚንቀሳቀው በሦስት አቅጣጫ ትግራይን የማስፋት እቅድ የመቀሌን፣ የአዲግራትና የአክሱም ዩንቨርስቲዎች ይዞ ስራውን በዕቅዱ መሠረት በማካሄድ ይገኛል በዕቅዱ መሰረት የኬሚካል ኢንጅነሪግን ከአዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር በማስተሳሰር ደጀና ኬሚካል ኢንዱስትሪ በሚል መቋቋሙን፣ የማእድን ዘርፍ በሽሬ እንዳስላሴና ዓዲዳዕሮን ማዕከል ያደረገ፣ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ማዕከልን ደግሞ ዓድዋ በማድረግ ከአክሱም ዩኒቨርስቲ ጋር በማስተሣሰር፣የብረታብረት ኢንጂነሪንግን እንዲሁ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ጋር በማስተሳሰር የትኩረት አቅጣጫ ሆነው እንዲሠሩ እየተንቀሳቀሱ ነው ወያኔና ተባባሪዎች ግዛትን ለማስፋፋትና ሕዝብን በኃይል ለማፈናቀል ባላቸው ዕቅድ መሠረት በጎንደር ሰሜን-ምዕራብ ግዛት ጦር ማሥፈር ጀምረዋል። ወያኔዎችና ምሑሮቻቸው ሊገነዘቡት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ አለ፣ የሌሎችን መሬትና ሰላም በወረራ አደፍርሶ የታሰበው የትግራይ ልማት እውን ሊሆን ከቶ አይችልም። ትርፉ ውርደትና አጉል የጀብደኝነት ሥራ ሲሆን ውጤቱም አስከፊ ነው። አብሮ ተከባብሮ የሚኖርን እና የሚመሩትን ሕዝብ ሰላምና አንድነት ኃላፊነት በጎደለው የጀብደኝነት ተግባር ሊያደፈርሱ አይገባም። ከሁሉም በላይ የትግራይ ታላቅነት እና ልማት በሌሎች ኪሣራ ላይ የተቀመረ ሊሆን አይገባም። በእኛ አመለካከት የትግራይ ሕዝብ እራሱን ከዘረኛው የወያኔ መንግሥት መለየት አለበት። ይህም ማለት ወያኔ በትግራይ ስም የሚያካሂደውን ተስፋፊነትና ወረራ መቃወም፣ የጎሣ ፖለቲካን ሚዛናዊ ያልሆነ ዕድገትን እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን በአደባባይ ወጥቶ መቃወም የግድ ይላል። በኢትዩጰያዊነቱ የሚታመን ማንኛውም ዜጋ በፈለገውና በመረጠው ቦታ የመኖር መብቱም ሊጠበቅለት እንደሚገባ ሁሉ ነዋሪውም ብሄረስብም እንደሌሎቹ ጐሳዎችን መኖር እንድሚችል ሊቀበሉት እንድሚገባ ግልፅ ነው ኢትዩጵያዊነቱ ከብሄር ማንነቱ ይቀድማል በመሆኑም የትግራይ ህዝብ እንደ ማንኛውም ዜጋ በመረጠው አካባቢ መኖር ይችላል ነገር ግን የሰፈርኩት ቦታ ሁሉ የትግራይ ግዛት የሚያደርግ ሥራና ዓላማ ከኢትዩጵያዊነት ውጭ ነው::

መሬቱ የእኔ ነው ከማለቱ ባሻገር በደራ የመሬት ገበያ ሽያጭ ከአፍሪካ ልቆ መገኘቱ አሳፋሪም አስገራሚም ነው ሽጦም የራሱን አቀንቃኞች ካዝና ሲያደልብ ተው የሚለው ስላጣ ከልካይ እንዳጣ በሬ ፋኗል:: ወያኔዎች ኢትዬጵያ የምትባል ሀገር እንደ አገር መኖር እስካላቆመች ድረስ የጥፋት ዘመናቸውን አያቆምም የዛሬው የኦሮሞ ህዝብ ንቅናቄና የ አዲስ አበባ መሬት ሽያጭ ተቃውሞ ሳይነሳ ቀደም ብሎ ከሁመራ ጀምሮ ርዝመቱ 1600 ኪ ሜ እና እስክ 50   ኪ ሜ ስፋት ያለውን የጠረፍ መሬት ለሱዳን በስጦታ መልክ አስረክቧል:ከተንኩለኛ ሰው ስንቅ አይቀላቅሉም እንዲሎ የዛሬዎቹ ባለ ግዜዎች የአረፍንበትን እንብላ ማለታቸው ሌላውን ብሔረሰብ ቢያስቆጣም አዲስ ነገር አይደልም: ዛሬ ዛሬ የወያኔ መሬት ሽያጭ ባለፈ ጭቆናና ግድያው ወደር እያጣ መቷል በመሆኑም ጭቆናው ፣ ትግሉን ወልዷል ትግሉ አንድነትን፣ አንድነቱ ደግሞ አመፅን ፣ አመፅ ደግሞ የወያኔን መቃብርን እያቀረበው ነውና ትግላችንን መቀጠል ብቻኛ አማራጭ ነው::

ኢትዩጵያ ለዘላለም ትኖር!

አንድ ኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ የተግባር እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲሳተፉ ሃገራዊ ጥሪ ያቀርባል።

አንድ ኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ

መግቢያ

እኛ ኢትዮጰያዉያን በመከባበር፤ በፍቅር፤ በመቻቻልና በአንድነት ፍጹም የሚያኮራ ባህል መስርተን የምንኖር ህዝቦች ነን። እጅግ የሚያኮራ ታሪክ ያላት ሃገር ክቀደምት አያቶቻችን ተረክበንም በጨዋነት፤ በታጋሽነትና፤ በፍጹም ኢትዮጵያዊ ባህል ችግሮቻችንን እየፈታን እስካሁን ኖረናል።

ይህ በእንዲህ እያለ ለዘመናት በላያችን ላይ እየተማቹ ያሉ ችግሮች ከመብዛታቸዉ የተነሳ ህዝቡ ትዕግስቱ ተሟጦ ችግሮቹን ሊሸከማቸዉ የማይችልበት አሳሳቢ ደረጃ ደርሶ የሃገራችንና የህዝባችንን ህልዉና አደጋ ዉስጥ ከቷል። ህዝቡም ብሶቱን ለመግለዕ በሚያደርጋቸዉ ትግሎች ዉስጥ እጅግ ልብን በሚሰብር ሁኔታ ክቡር የሰዉ ህይወት እየጠፋ ይገኛል። በዚህም ምክንያት የሃገራችን ህልዉናና የህዝባችን እጣ ፈንታ ሁሉንም ለሃገሩ ቀና የሚያስብ ወገን ጭንቀት ውስጥ ከቶት ይገኛል። የችግሩም ውስብስብነትና አደገኝነት ጊዜ የማይሰጥ ሲሆን ጉዳዩ በአፋጣኝ ካልተፈታ የመጨረሻ ዉጤቱ የሀገራችንና የህዝባችንን ህልዉና ሊታሰብ የማይቻል አደጋ ውስጥ መክተቱ አይቀሬ ነዉ።

እየተከሰተ ባለዉ ሁኔታም ልቡ ያልተሰበረ፤ ህሊናዉ ያልቆሰለ፤ በየቤቱ እያለቀሰ፤ አምላክን እየተማጸነ፤ ሌት ተቀን ተስፋንና አፋጣኝ መፍትሄን እየተመኘ የማይገኝ ኢትዮጵያዊ የለም። ህዝቡም ከዳር እስከዳር የመፍትሄ ያለ እያለ እየጮኸ ይገኛል። ለህዝቡም ጥሪ ምላሽ ለመስጠት እያንዳንዳችን ኢትዮጵያዉያን የሃገሬ ጉዳይ ያገባኛል በማለት እጅ ለእጅ ተያይዘን በቆራጥነት ከተነሳን ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት አያቅተንም።

ትብብሩ ለችግሮቻችን አፋጣኝ መፍትሄ ለማግኘት ቁልፍ ሚና ይኖረዋል ብለን የምናምን ኢትዮጵያዉያን በመፍትሄዎች ዙርያ ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚንቀሳቀስ ህዝበ ዉሳኔ 2009 (referendum 2009) የሚባል ሁሉን አሳታፊ የሆነ በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የትብብር መድረክ በመመስረት ሁሉንም ኢትዮጵያዉያን ትብብሩ በሚያቀርባቸዉ የመፍትሄ የተግባር እንቅስቃሴዎች ላይ እንዲሳተፉ ሃገራዊ ጥሪ ያቀርባል።

ዓላማ

የህዝብን ድምጽ ማስማትና የመፍትሄ ሃሳቦችን በማመንጨት ህዝቡን በማስተባበር ተግባራዊ ማድረግ

አካሄድ

ህዝብንና ድርጀቶችን በማስተባበርና በማቀናጀት የመፍትሄ ሃሳቦችን ተፈጻሚ ማድረግ

ግብ

ኢትዮጵያዉያን በሀገራቸዉ ጉዳዮች ድምጻቸዉ እንዲሰማና ቀጥተኛ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ማስቻል።

እሴቶች

1. ፍትህ
2. እኩልነት
3. ነጻነት
4. ዲሞክራሲ
5. ትብብር
6. ግልጽነት
7. ተጠያቂነት

የትብብሩ መለያ

1. ህዝባዊ – ኢትዮጵያዉያንን ያሳትፋል
2. አዳዲሰ – ታላላቅ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸዉን ሀሳቦች ያፈልቃል
3. ተግባራዊ – በተጨባጭ የሚታዩ ተግባራትን ያከናዉናል
4. ግልጽነት – ተግባራትን በፍጹም ግልጽነትና ተጠያቂነት ያከናዉናል
5. ሁሉን አቀፍ – በዓላማዉ የሚያምንን ሁሉ ያለገደብ ያሳትፋል
6. ገለልተኛ – የማንንም የዘር፤ የሃይማኖትና፤ የፖለቲካ ዓላማ አያራምድም

የትብብሩ መፈክር

እንድ ኢትዮጰያ – አንድ ሀዝብ – አንድ ጥያቄ!!! (Ethiopia First)

የትብብሩ ዓርማ

ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚያስተሳስርዉ ቀይ፤ ቢጫ፤ አረንጓዴ ባንዲራችን ላይ እንድ ኢትዮጰያ – አንድ ሀዝብ – አንድ
ጥያቄ የሚለዉን መሪ መፈከርና የዲሞክራሲ መገለጫ የሆነዉን የምርጫ ምልክት የሆነዉን ጠቋሚ ጣትን ወደ ላይ ያወጣ
የተጨበጠ እጅ

አቋም

ትብብሩ ተግባራቱን በፍጹም ገለልትኝነት ያክናዉናል።
ተቋማዊ ምድብ
ለፍትህ፤ ለህዝቦች ነጻነት፤ ለእኩልነት፤ ለዲሞክራሲ፤ ለሰላም፤ የሚታገል የህዘብ ንቅናቄ ነዉ።

የትብብሩ አባላት

ማንም በትብብሩ ዓላማዎች የሚያምን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የትብብሩ አባል ነዉ።

የአባልነት መብት

1. በትብብሩ ማናችዉም እንቅሰቃሴዎች ያለገደብ መሳተፍ
2. አዳዲስ ሀሳቦችን ማፍለቅና በትብብሩ ፕሮጄከቶቸ መሳተፍ
3. ድምጽ የመስጠት፤ ሰለትበበሩ እንቅስቃሴ መረጃ የማግኘት
4. ትብብሩ በሚያቀርባቸዉ ጥሪዎች መሳተፍ

የአባልነት ግዴታዎች

አባልነት ነጻ ሲሆን በትብብሩ የሚሳተፉ ሁሉ የትብብሩን ዓላማና የአባላቱን መብት ማክብር ይጠበቅባቸዋል።
በጎ ፈቃደኝነት
የትብብሩ ተግባራት ሁሉ በበጎ ፈቃድኛ አገልጋዮች ይከናወናሉ።

ድርጅታዊ መዋቅር

1. ትብብሩ አድጎ የትብብሩ ሃሳብ ፈጣሪዎች ያለሙለት ደረጃ እስኪደርስ ድረስ በሀሳቡ አፍላቂዎች አስተባባሪ ቡድን ይመራል
2. ቀጣይ ድርጅታዊ መዋቅሩ በጊዜዉ ተጨባጭ ሁኔታዎችና በአባላት ምክክር ይወሰናል
3. አስተባባሪ ቡድኑ እንዳስፈላጊነቱ የተለያዩ ግብረ ሃይሎች፤ ምክር ቤቶች፤ ኮሚቴዎች፤ የስራ ሃላፊዎችና አስተባባሪዎችን ይመድባል

የገቢ ምንጭ

1. ትብብሩ ለዘመቻዎች፤ ለስራ ማስኬጃዎች፤ ለፕሮጄክቶች፤ ፕሮግራሞችና፤ ለሌሎችም ተጨማሪ ያልታቀዱ አጋጣሚዎች ገልጽ የሆኑ የተግባር ፕሮጄክቶች በመንደፍ ክአባላትና ሌሎች ለጋሽ ደርጅቶች ድጋፍ በማሰባሰብ ስራዎቹን ያንቀሳቅሳል።
2. በትብብሩ ስም የባንክ አካዉንት ተከፍቶ ማናችዉም የትብብሩ የሂሳብ እንቅስቃሴዎች በሂሳብ ባለሙያ ይንቀሳቀሳሉ
3. የሂሳቡ እንቅስቃሴም ለህዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ በድረ ገጽ እንዲታይ ይደረጋል

ኢዲት

የትብብሩ ሂሳብ በተረጋገጠለት ኦዲተር አየተመረመረ በየጊዜዉ በኦዲተሩ ለህዘብ ይፋ ይደረጋል

ፕሮጄክቶች

ትብብሩ ሀገራዊ ፋይዳ የሚኖራቸዉን ተጨባጭና ተግባራዊ ሃሳቦች በማመንጨት ለህዝብ ይፋ ዉይይት በማቀርብና የህዝቡን ድጋፍ በማንቀሳቀስ ተግባራቱን ያክናዉናል።

የትብብሩ እድሜ

ትብብሩ የተመሰረተዉ ላልተወሰነ ጊዜ ነዉ። ትብብሩ በማናቸዉመ ምክንያት ቢፈርስ የትብብሩ እሴቶቸ በአሜሪካን መንግስት ህግ መሰረት ይክናወናሉ።

No automatic alt text available.

የኢህአዴግ መሰነጣጠቅ ወደ አደባባይ ይወጣ ይሆን? * ከአዜብ ቀሚስ ስር ያመለጠው ኦህዴድና የህወሓት ቀጣይ ሴራ * ለገዱ የተደገሰውና ዉዝግቡ

 

የኢህአዴግ መሰነጣጠቅ ወደ አደባባይ ይወጣ ይሆን? 

 • በጥልቀት መታደስ ወይስ በጥልቀት መበስበስ?
 • ከአዜብ ቀሚስ ስር ያመለጠው ኦህዴድና የህወሓት ቀጣይ ሴራ
 • ለገዱ የተደገሰውና ዉዝግቡ

ከመሃዲ ሂርጳሳ

ለ25 ዓመታት ኢትዮጵያን በኢህአዴግ ስም ቀጥቅጦ የገዛው የአውራው ፓርቲ ዘዋሪ ህወሓት ጭንቅ ጥብብ ያለው ይመስላል፡፡ ጭንቀቱ የፈጠረበት መንቆራጠጥ ደግሞ ከጓዳ ወጥቶ ሳሎን ደርሷል፡፡ በዙሪያቸው ሆኖ በንቃት ላስተዋላቸው ሁሉ በግልጽ የሚታይ ህመም ነው፡፡ አንደአካሄዱ በቅርቡ በረንዳ ላይ ቀጥሎም አደባባይ ይወጣል ወይስ ህወሐት እንደለመደችው በሴራዋ ታኮላሸዋለች የሚለው ግን ተራ ጥያቄ አይመስልም፡፡ ለማነኛውም ኢህአዴግ ከውስጥ መሰነጣጠቅ ስለመጀመሩ የታዘብኩትን፣ ከታማኝ ምንጮቼ ያገኘሁትን ጭምጭምታና መላምት ከሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ጋር እያይዤ ነጥብ በነጥብ እንደሚከተለው ላቅርብ፡፡

screen-shot-2016-10-24-at-5-12-52-am

ኦህዴድን ያልተሻገረው ጥልቅ ተሀድሶ

በታሪክ ከታዩ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቀውሶች ውስጥ ከግንባር ቀደምቶቹ ተርታ የሚሰለፈው የአሁኑ ሀገራዊ ችግር በርካቶችን ስጋት ላይ የጣለና አሳሳቢ ነበር፡፡ ይህን እውነትም መንግስት በተደጋጋሚ በሚሰጣቸው መግለጫዎቹ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ሲገልጻቸው ይደመጣል፡፡ ስርዓቱ የችግሩን ጥልቀት ከማመኑ ጋር ተያይዞም ̎የማስተካከያ እርምጃዎችን እወስዳለው በጥልቅም እታደሳለው̎ ሲል ሙሉ እምነት ባይጣልበትም ሀገሪቱ ላይ ከተከሰተው ችግር አሳሳቢነት አንጻር ግን ተስፋ ያደረጉ ነበሩ፡፡ እውነት ነው ጅማሮው መልካም የሚባልና ፖለቲካውንና ኢህአዴግን በቅርብ ለሚከታተሉ ተስፋ ሰጪ ነበር፡፡ በቀደሙት ጊዜያት ብዙው ሰው ለፖለቲካው ቅርበትም ሆነ መሳብ ስላልነበረው የለውጡን ጅማሮ ሀያልነት መረዳት አይችልም፡፡ ነገር ግን አራቱ ፓርቲዎች በየራሳቸው የጀመሩት ግምገማ ከምንጊዜውም በተሻለ በአንጻራዊነት ከህወሓት ጥርነፋ ነጻ የነበረና ለሚወክሉት ህዝብ በመወገን የተጀመረ ነበር፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደው የኦህዴድ እርምጃ ነው፡፡

ፖለቲካውን የሙጥኝ ብሎ ለሚከታተል ሰው በግልጽ እንደሚታወቀው እስካሁን ድረስ ኦህዴድን ሲዘውሩ የነበሩ ሰዎች በተዘዋዋሪ በህወሓት ስውር እጅ ኦሮሚያን ሲያስተዳድሩ ሳይሆን ሲያስመዘብሩ የቆዩ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜም የኦሮሚያን አመራሮች ለማንሳትም ሆነ ለመሾም በተዘዋዋሪም ቢሆን የህወሓት ውሳኔና ምክር በቀጥታ ይወርዳል፡፡ የአሁኑ አዲስ ሹመትም ሆነ የቀደሙትን የማውረድ ውሳኔ በራሱ በኦህዴድ ነጻ ግምገማ የተከናወነ ሲሆን ውሳኔውን አምኖ መቀበል ያቃተው ግን ኦህዴድን በጥርጣሬ የሚመለከተውና የሚተቸው ህዝብ ብቻ ሳይሆን በይበልጥ ህወሓትንና ሌሎች አጋር ፓርቲዎችንም ጭምር ያስደነገጠ ነበር፡፡ በአንድ በኩል በግልጽ የህወሐት ተላላኪ መሆኑ የሚታወቀው የኦህዴድ አንጃ መመታቱ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎችም ድርጅቶች የኦህዴድ አይነቱን ወይም የበለጠውን ውሳኔ እንዲያሳልፉ ጫና መፍጠሩ ነው፡፡

ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ንኡስ ርዕሶች ስር የማነሳቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለአሁኑ የኢህአዴግ ውስጣዊ መሰነጣጠቅ ጅማሮ አንዱና ዋነኛው መንስኤ የኦህዴድ እርምጃና እሱን ተከትሎ የተፈጠሩት ዉዝግቦች ናቸው፡፡

የኦህዴድን ዉሳኔ የበለጠ ቦታ የምንሰጠው ደግሞ አንዳቸውም ይህንን ዉሳኔ የማስተላለፍ ሞራል ላይ መድረስ ባለመቻላቸው ነው፡፡ የብአዴንና የገዱ አንዳርጋቸው ጉዳይ በተለየ የሚታይና በቀጣይ ርዕሶቼ የማነሳው ይሆናል፡፡ ያም ሆነ ይህ የተጀመረው ̎የተሀድሶ̎ መንገድ አለመቀጠሉ ዛሬም የስርአቱን አለመለወጥ ከመንገር አልፎ ኢህአዴግ በጥልቅ ከመታደስ ይልቅ በጥልቅ ወደመበስበስ ተሸጋግሯል የሚለው አስተሳሰብ ገዢ እየሆነ የመጣ ይመስላል፡፡

ገዱን ከስልጣን የማስወገድ ዱለታ

የኦህዴድ እርምጃ ሁለት ባላ ላይ የተንጠለጠለ ለመሆኑ ከየድርጅቶቹ የሚሰሙት ሹክሹክታዎች ይናገራሉ፡፡ አንዱና ቀደም ብዬ የጠቀስኩት የህወሓት ተናዳጁና የታማኝ ተላላኪዎቹ መመታት ያንገበገበው ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን የኦህዴድን ውሳኔ ፍጹም መቀበል የከበደውና ያልፈለገ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ግን ታማኝ አገልጋዮቹን በኦህዴድ ውስጥ የተነጠቀው ህወሓት በብአዴን ውስጥም ዳግም ላለመነጠቅና የቀድሞ አሰላለፉን መንሻፈፍ ለማስተካከል ሲል የጠላውንና ያስደነገጠውን የኦህዴድ መስመር መከተል የፈለገ ይመስላል፡፡ ነጥብ እስካስቆጠረለት ድረስ ህወሐት የትኛውም አሰላለፍ ውስጥ ለመቆየት የሚቸገር አይመስልም፡፡ እናም ብአዴንም የኦህዴድን መንገድ ተከተለች በሚል እሳቤ የእግር እሳት የሆነባቸውንና ከህዝቡ ጋር የወገኑትን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከስልጣናቸው ዘወር ማድረግ ስለመፈለጋቸው ከሹክሹክታ ከፍ ባለ ድምጽ እየተሰማ ነው፡፡

ሁለቱ የኦህዴድ አንጃዎች 

በኦህዴድ ውስጥ ብዙም ያልተሰወረና የኦሮሞ ፖለቲካን በቅርብ የሚከታተሉና የሚያጠኑት ጭምር ደጋግመው ሲሉ እንደሚደመጠው ሁለት አንጃዎች አሉ፡፡ አንደኛው ቡድን ተላላኪና ከመንገድ ላይ ድርጅቱን ተመልምሎ የተቀላቀለ ኦህዴድን በህወሐት ሰንሰለት ጠፍሮ ያከረመው የነአስቴር ማሞ አንጃ ነው፡፡ ሌላኛው ሁለተኛው ቡድን በኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የሚደርስበትን ስልታዊ ጫና ተቋቁሞ በውስጡ የሰነቀውን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ብዙ መሰናክሎችን ያለፈውና አሁንም ለማለፍ የተዘጋጀው ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን አሁን ባለው ሁኔታ ሰልጣኑን ይዞታል፡፡ በዚህ ቡድን ላይ የኦህዴድ ካድሬዎችም ሆኑ ብዙ ቁጥር ያላቸው ኦሮሞዎች እምነት እንዳላቸው ከሹመቱ ማግስት ጀምሮ የተለያየ አቋም ያላቸው ጸሀፊዎችና የኦህዴድ ተቺዎች ጭምር ያሰፈሩትን ጽሁፍ አንብበናል፡፡

እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በኦሮሚያ ላይ ለተፈጠሩ ማናቸውም ከፍተኛ ችግሮች መንግስትም አምኖ ሽምግልና የሚልካቸው፣ ህዝቡም የክልሉ ፕሬዝዳንቶች እያሉ ከዚህኛው ቡድን ካልሆነ ሌላ ሰው ድርሽ እንዳይልብን ማለታቸው በራሱ አንዳች የሚያስረዳን ሚስጥር አለው፡፡ እርግጥ ነው በዚህ ቡድን ውስጥ ያሉ አመራሮች ለህዝቡ ወገንተኝነት ያለውን አስተያየት በመንግስት መገናኛ ብዙሀንም ሆነ ለስርዓቱ በወገኑ ሚዲያዎች ላይ ጭምር ሲሰነዝሩ አስተውለናል፡፡ ለምሳሌ ከማስተር ፕላኑ ጋር በተያያዘ የመጀመሪያውና ወዲያው ጋብ ብሎ የነበረው ተቃዉሞ ተቀስቅሶ ህዝቡና የጸጥታ ሀይሉ በተጋጨበት ወቅት ይሄኛው ወገን ነበር ብቅ ብሎ ህዝቡ ያነሳው ጥያቄ ተገቢና ተቃዉሞውን ማሰማት መብቱ እንደሆነ አስረግጠው የተናገሩት፡፡

የኢሬቻው ሀዘንና መላምቶቹ

እጅግ ልብ ሰባሪ አሳዛኝ ህልፈት የደረሰበት የመስከረም 22ቱ የኢሬቻ በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ በቦታው የተገኙ የዉጭ መገናኛ ብዙሀንን ጨምሮ መንግስትም የሞቱ መንስኤ መረጋገጥ ነው ሲሉ ሌላኛው ወገን ደግሞ የለም ከወታደሮች በተተኮሰ ጥይት ነው ግፍ የተፈፀመው ሲሉ አምርረው መንግስትን ይወነጅላሉ፡፡  ከዚህ በተለየ ግን እውነታው እስኪረጋገጥ ድረስ በመላምት ደረጃ የሚሰነዘር አንድ ነጥብ አለ፡፡ ይህ መላምት በኦህዴድ ውስጥ ከነበረው የጎራ መለያየት ጋር በተያያዘ የሚሰነዘርና ኦህዴድ እራሱ እስካሁንም የተገለጠለት የማይመስለው ጉዳይ ነው፡፡ ይኽውም  የቢሾፍቱው ሞት በመጨፈላለቅ ብቻ ያልደረሰና ይልቅም  የቀድሞው የኦህዴድ አመራሮች በህወኃት ፊትአውራሪነት አዲሱን አመራር ለማስወገዝ የተዶለተ ነው የሚል ነው፡፡ በዳያስፖራው ላይ ያነጣጠረና ለፖለቲካው ጡዘት ሲባል  ደም እንዲገበር የዳያስፖራው ክንፍ ከጥግ ቆሞና ሆን ብሎ ያራገበው ነው የሚለው የሌሎች ወገኖች መላምትም እንዳለ ሆኖ፡፡

opdo

ከአዜብ ቀሚስ ስር ያመለጠው ኦህዴድ

በኦህዴድ ሁለቱ አንጃዎች ላይ ያለን መረጃና መሬት ላይ ያለው እውነታ ፍጹም የተራራቁ ናቸው፡፡ በነአስቴር ጎራ ስላለው ሙሰኝነትና ዘረፋ ብዙ አንሰማም፡፡ ለፓርቲው አመራሮች ቅርብ ከሆኑ ሰዎች የሚሰማው ተጨባጭ እውነታ ግን ፍጹም ተቃራኒና የሚያስደነግጥ ነው፡፡ የነ አስቴር ጎራ በግሉ ብቻ አይደለም የሚዘርፈው፡፡በቡድንም ጭምር እንጂ የሚያዘርፈው፡፡ በአዜብ መስፍን ፊትአውራሪነት ኦሮሚያ ላይ በህወኃት ቡድኖች ለሚደረገው የሀብት ዝርፊያ ዋነኛዋ ተወካይና አመቻች አስቴር ማሞና ግብረአበሮቻቸው ነበሩ፡፡ በተዘዋዋሪም የመለስ ህወሓት ብቻ ሳይሆን ኦህዴድም እስካሁን ድረስ በአዜብ ቀሚስ ስር ነበር፡፡ አሁን ግን የአዜብና አስቴር ፍቅር መሞጃሞጃው መጨረሻው የደረሰ ይመስላል፡፡ ምንም እንኳን ከውስጥ ሰዎች ሾልኮ እንደሚሰማው አዜብ መስፍን በኦሮሚያ ላይ ለማካሂደው ዝርፊያና ግልቢያ ቀኝ እጄ የሆነችው አስቴር ተቆርጣለችና ቀጥሉልኝ በማለት ዳግም መፍጨርጨር ብትጀምርም፡፡

የሆነው ሆኖ ዋናው ጉዳይ በመግቢያዬ ላይ የነካካኋቸው ሁለት ጉዳዮች መሰረታዊ ናቸው፡፡ አንዱ በይፋ ኢህአዴግ ተሰነጣጥቆ ገመናው አደባባይ ላይ ይወጣል ወይስ በውስጣቸው ተጀምሮ የነበረውን ለውጥ አምነው ይቀበላሉ? ወይስ ደግሞ ህወሐት እንደለመደችው የትግሉን አቅጣጫ አስቀይሳ ለውጡን ታዳፍነዋለች? ይህንን ግን ጊዜው የሚፈቅድላቸው አይመሰልም፡፡ ይህ ከሆነ ምናልባትም የኢህአዴግን መሰነጣጠቅ አደባባይ አስጥቶት የፓርቲውን ግብዓተ መሬት ያፋጥነው ይሆናል፡፡

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

እመኑኝ አይለወጥም

አሁን ዋናው ጥያቄ መሆን ያለበት እዚህም እዛም ያለውን ከፍተኛ ቀውስ እንዲሁም በየድርጅቱ ውስጥ የሚደረገውን ለውጥና ጠንካራ ግምገማ ተከትሎ ኢህአዴግ ይለወጣል ወይ የሚለው ነው፡፡ ከሁነኛ የመረጃ ምንጮች እንደሚሰማው ከሆነ፣ ከኋላ ሆነው ስርዓቱን የሚዘውሩት የህወሕት ጉምቱ ባለስልጣናት በኦህዴድ አዲሱ አመራርና አጋሮቻቸው ላይ ጥርሳቸውን ነክሰዋል፡፡ በክልል ላይ አሽከሮቻቸው ለተወሰደባቸው የበላይነት እነሱ ደግሞ በተቃራኒው በፌዴራል ደረጃ ተጽዕኖ ለመፍጠርና ከሚኒስትርነት ጭምር ለማግለል ተግተው እየሰሩ ነው፡፡ ምናልባትም ከተሳካላቸው ጥቂት የማይባሉ የኦህዴድ ጠንካራ አመራሮችን ከሚኒስትርነት ያስወግዳሉ ማለት ነው፡፡ እርምጃውንም ጠንካራውንና ወጣቱን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በማንሳት ጀምረውታል፡፡

ሌላው ከብአዴን፣ በተለይም ደግሞ ከአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር የተያያዘው ጉዳይ ነው፡፡ ህወሕት በአቶ ገዱ ላይ ተስፋ ከቆረጠች ቆየ፡፡ ነገር ግን እሳቸውን ከስልጣን ቆርጦ መጣሉ ቀላል የሆነላቸው አይመስልም፡፡ በኦህዴድ አመራሮች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ወደመስማማት የመድረሳቸውን ያህል በአቶ ገዱ ጉዳይ ግን ለሁለት ተከፍለዋል፡፡ አንደኛው ወገን አባረን ወይም አነስ ያለ ስልጣን በመስጠት የሚመጣውን እንይ ሲል፣ ሌላኛው ቡድን ግን ትንሽ ጊዜ ሰጥተን ዉሳኔውን በሂደት ብናየው ይሻላል የሚል ነው፡፡

አመጽ የተጨቆኑ ህዝቦች ቋንቋ ነው – ዳዊት ዳባ

 

አርእስቱን ከፌስ ቡኬ ላይ ያገኘሁት ነው።

ዳዊት ዳባ።

Saturday, October 15, 2016

Demonstrators chant slogans while flashing the Oromo protest gesture during Irreecha, the thanksgiving festival of the Oromo people, in Bishoftu town, Oromia region, Ethiopia, October 2, 2016. REUTERS/Tiksa Negeri - RTSQF70

በቀለ ገርባን አይነት  ብዙ ምርጥ የህዝብ ልጆች  የታሰሩበት የቂሊንጦ እስር ቤት ላይ እሳት ተነስቶ ብዙ እስረኞች እንደተቃጠሉ ወያኔዎች ባልተለመደ መንገድ በራሳቸው መገናኛ ነገሩን። ክህዝብ አልገዛም ባይነት ጋር በተያያዘ የታሰሩ የኦሮሞ ህዝብ ታጋዬችና አመራሮች፤ የስልምና እምነት ተካታይ ዜጎች ወኪሎቻቸው በቅሊንጦ እስር ቤት ታሳሪዎች ናቸው።   በቃጠሎው ማን ሞተ  ማን ተረፈ የሚለው ግን አይደለም ለህዝብ የቅርብ ቤተሰብም ሳያውቀው ሳምንት እንዲያልፍ ተደረገ። ጥብቅ የሆነ ሚስጢር ተደረጎ ተይዞ ነበር። ይባስ ብሎ ድህንነታቸውን የጠየቁ ቤተ ዘመዶች እስር ድብደባና ማዋከብ ተፈፀመባቸው። ፍጅቱን ከፈፀሙ በሗላ ከሳምንት በላይ ቢጠብቁም ህዝብ  አልገዛም ባይነቱን በጀመረው ሰላማዊ በሆነው መንገድ አጠንክሮ ቀጠለበት።  ቆያይተው እቅዳቸው ከታሰበበት አላማ ውጪ እንዳይወጣና ህዝባዊ እንቢተኛነቱ አዲስ አባባ ላይ እንዳይፈነዳ በመስጋት ይመስላል ቀድሞ ያላግባብ በቅሊንጦ ታስረው የነበሩ የድምፃችን ይሰማ አመራሮች ድህንነት ቀስ በቀስ  እንድናውቅ ሆነ። ቆያይቶም ተፈቱ። በሗላ ግልፅ እንደሆነው አመራራቹ ደህና ቢሆኑም  እሳት ለኩሰውባቸው የገደሏቸው ብዙዎቹ ኦሮሞዎች መሆናቸውን አውቀናል።

የቅሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ለአንድ አመት ሙሉ የቀጠለው የህዝብ  ሰላማዊ ትግል ጉልበት እያገኘ እየሰፋ አለማቀፋዊ ድጋፍንና ትኩረትን በእጅጉ እያገኘ አገዛዙን እለት በእለት እየገዘገዘው እየሄደ ባለበት ጊዜ ላይ የተፈፀመ አስደንጋጭ ክስተት ነው ። ሌሊሳ ፈይሳ የውጪውንም የአገሩንም ሜዲያ ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረበት ጊዜ ነበር። ለአንድ አመት በዘለቀው ትግል  ቀን በቀን ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ የሚገደሉ ንፁሀን ዜጎች ጉዳይና የናቶች ለቅሶ መላውን ዜጋ ሲቃ ውስጥ የሚከትና  እልህ ውስጥ ያሚያሰገባ አልነበረም ማለት በጭራሽ አይቻልም። በእልህ ምክንያ የትግል ስልት መቀየር አለበት የሚሉ ድምፆች መሰማት  ጀማምረው ነበር። ከቅሊንጦው ፍጅት እና ወያኔ ፍጅቱን የያዘበት ጠቅላላ ሁኔታ ለተከታተለ ወያኔ ህዝብን ሴሜታዊ ለማድረግና ወደ ለየለት አመፅ ውስጥ ለማስገባት  እየሰራ እንደሆነ ግልፅ ነበር። በግሌ ልፅፍበት አስቤ ከሌሎች ጋር ስወያይበት ቆይ ቆይ ወያኔ ስላደረገው ብቻ ለምን መጥፎ ይሆናል?  ትግሉ ላይ ጥቅሙንና ጉዳቱን ስናሰላው  ጠቃሚነቱ የበዛ ስለሆነ ይታለፍ አለን። እርግጠኛ ነኝ ትግሉ ላይ በቅርብ ያሉትም  ይህንን ጉዳይ አይተውታል።  ወያኔዎች በፈለጉት መንገድ እንዲያስኬዱት እንደተዉላቸው እርግጠኛ ነኝ። ይህን ለማለት የሚያስችሉ ምክንያቶችም አሉ።።

ቀጠለ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ አግባብ ያለው ነው። አልፎም ሊመለስ የሚችል ነው። መንግስት መመለስ አለበት። የትግራይ ህዝብ የኦሮሞን ህዝብ ትግል ደግፎ ሊሰለፍ ነው። ከአማራ ተጋድሎ ጋር በማፎካከር መሆኑ ነው። ማዘናጊያ ፕሮፓጋንዳ ጦዘ። ከአርባ አመት በሗላም ይህቺን የውሸት ፕሮፓጋንዳ እንደተሰጣቸው  የዋጧት ነበሩ።  ለወደፊቱ እንንቃ ትግሉ አገራቀፋዊ ሆኗል። ጥያቄው ወደስርአት ለውጥ አድጓል። የትኛውም ጥያቄ ወያኔ ስላጣኑ ላይ ባለበት ሊመለስ የሚችል አይደለም።  የትኛውም የኦሮሞዎች ጥያቄ ወያኔ ሊመልሰው የሚቻላውም አይደለም።  ሲጀመር ጥያቄው አንድ ብቻ አይደለም። ቀለል ተደርጎ የተገለፀው የአዲስ አባባ ማስተር ፕላን ጥያቄ ራሱ ለመመለስ እንደምንለው ቀላል አይደለም።   ከቅሊንጦው ፍጅት በሗላ በቀጣይ ምን ተሳቦ ይህቺ ቀልድ መጣች ብሎ መጠየቅ ለሁላችንም የተገባ ነበር።  ጫወታው ወደዚህ ነበር።

የቅሊንጦው ፍጅት አልሰራላቸውም በቀጣይ ምን ያደርጋሉ የሚለወን ስንወያይ የተለያዩ መላ ምቶችንም አስቀምጠናል። በግሌ ግን በቀጣይ ሊያደርጉት የሰቡትን  ማወቅ እችል ነበር። ከፈፀሙት በሗላ ደደብ ነኝ ነው ለራሴ ያልኩት።  በፈረንጆች አቆጣጠር 1989 እንግሊዝ ውስጥ የሊቨር ፑል የእግር ኳስ በድን ደጋፊዎች እልቂት በተመለከተ በጊዜው ሜዲያዎች በሙሉ ተቀባብለው እንደዘገቡት በደጋፊዎቹ ስርአት አልበኛነት ምክንያት ሳይሆነ የፀጥታ አስከባሪዎች በሰሩት ተራ በሆነ ስህተት የተፈጠረ እልቂት መሆኑን የሚያሳይ አስገራሚ ጥናታዊ ፊልም  ሲኤን-ኤን ላይ የዛኑ ሰሞን ተላልፎ አይቼ ነበር።  ይህቺኑ በቀጥታ ቀድተው ይጠቀማሉ ብዬ ግን እንዴት ይታሰበኝ።

ላለፈው አንድ ኣመት ሙሉ  አገዛዙ የተነሳበትን ህዘባዊ አልገዛም ባይነት ለመቀልበስ ብዙ ጥሯል። መሪ ብሎ ያሰባቸውን ሰብስቦ ማሰር፤ ፍጅት፤ ጀምላ እስር፤ የርስ በርስ ግጭትና በዜጎች ዘንድ መፈራራትን መፍጠር፤ ማስፈራራት፤ እስረኞችን እስከነብሳቸው በእሳት ማቃጠል፤ የመሳርያ ትግላቸውን እርግፍ አድርገው ትተው ህገመንግስቱን አክብረው ለመታገል ስለወሰኑ ድርጅቶች … ብዙ ብዙ። ግብፅ፤ ኤርትራ፤ አክራሪ የሚሉ ማሸማቀቂያዎችን ማጦዝ…።  ይህ ሆሉ ጥረት ግን እንደቀድሞው ህዝባዊ እንቢተኛነቱን ሊያቆመው አይደለም ትግሉን ይጠቅማል ብሎ ሊገፋው ወዳሰበው አመፅና ውድመት ያለበት መንገድ  ሊወስደው አልቻለም። ይባስ ብሎ መላው ዜጋ አገዛዙ  ሟች መሆኑን አውቆ ስለቀጣዩ እጣ ፋንታው ወደማውራት  ተሻገረ። በውጪ  ብቻ እንዳይመስለን በመላ አገሪቷ በይበልጥም አዲስ አበባ ላይ ዋናው መወያያ ቁም ነገር ሆኖ ነበር።

የኢሬቻን ፍጅት በተመለከተ። {1989 የሊቨር ፑል ደጋፊዎች እልቂት ፊልም ላይ በዚህም መንገድ ፍጅት መፈፀም እንደሚቻል ወያኔዎች በእርግጠኛነት ግንዛቤ ወስደዋል}። የእሬቻ በዓል።

 1. በትንሹ ከሁለት ሚሊዬን በላይ ህዝብ የሚታደምበት በዓል ነው።
 2. በዓሉ በተከበረባቸው የቀደሙ አመታት ሁሉ ህዝብ በበዓሉ ላይ ላገዛዙ ያለውን ተቃውሞ ያሰማ ነበር። ምን አልባት የትግሉ መነሻ  በየዓመቱ የሚደረገው ይህ ታላቅ በዓል ነው ማለት ይቻላል።
 3. የኦሮሞ ህዝብ ተቃውሞ ከደረሰበት ደረጃ አኳያ በዚህም ዓመት ጠንካራ ተቃውሞ በበዓሉ ላይ እንደሚኖር የሚጠበቅ ነበር።
 4. ከባድ ተቃውሞ እንደሚኖር ስላወቁም ታንክ፤ከባድ መሳርያና ብዙ ወታደር ቦታው ላይ አዘጋጅተው ነበር።
 5. በዓሉ የሚከበርበት ቦታ መልካ ምድርና ከህዘቡ ብዛት አኳያ በቀላሉ እወካን በመፍጠር ህዘብ ሲገፋፋ ገደል ውስጥ እንደሚገባና፤ በጭሱ ሊታፈንና ተረጋግጦ ሊሞት እንደሚችል ይህን ተጠቅሞ እልቂት እንዲደርስ ማድረግ እንደሚችል አስልተዋል።
 6. በእለቱ የነበረው ጠንካራ ተቃውሞ ቢሆንም ፍፅም ሰላማዊ የነበረ መሆኑ በግንዛቤያችን እናስቀምጥ።
 7. በዓሉ ከሚከበርበት ቦታ አኳያ ተቃውሞው ለስልጣን፤ ለሰው ሆነ ለንብረት ውድመት ብቻ በየትኛው ሁኔታ ላገዛዙ አስፈሪ ሊሆን የሚችልበት ሁኔታ ማጣቀስ ለማንም አይቻልም። ታቃውሞው ፍፁም ስላማዊ ስለነበረም  ታላቅ በዓል ከመሆኑ ጋር ደምሮ ፍጅት ለመፈፀም ቀድሞ ለተዘጋጀ አካል ካልሆነ በቀር ለምንም አይነት ሀላፊነት ለሚሰማው ክፍል  አግባብ ያለው ሁኔታውን መቆጣጠርያ መንገድ ተቃውሞው እንዲቀጥል መተው፤  የተቻለውን ያህል ጣልቃ አለመግባትና  ያሰማራቸውን ወታደርና የመገደያ መሳርያዎች ከዛ አካባቢ ማራቅ  ነበር።
 8. በተቃራኒው ያገዛዙ ተንኳሽነትና አስጨናቂ ድባብ መፍጠር ነበረበት። ታነክ በቦታው ነበር፤ ከባድ መሰራያ ነበር። መሰርያ የታተቁ ወታደሮች በመኪና ሆነው በዓሉን ለማክበር በተሰበሰበው ህዝብ ውስጥ ይመላለሱ ነበር። ተደብቀውም በተዘጋጅ የሚጠብቁ ብዙ ወታደሮች ከጀርባ ነበሩ። ከነዚህ በተጨማሪም መሳርያ ያልያዙ ብዙ ወታደሮች ከፊት ተደርድረው ነበር። ህዝቡ  አመቱን ሙሉ ሲገድሉ በየቀኑ ልጆቹን እየቀበር ሲቃወማቸው እንደነበረ እየታወቀ የመንግስት ባለስልጣናት በዓሉ ላይ ንግግር ለማድረግ ማሰባቸው ተንኳሽነት ነው። ይህ ሙከራቸው ለተቃውሞው መጠንከርና ቦታው ላይ ንትርክን ያስነሳ  ነበር። በድርጅታዊ ስራ ብዙ የኦፒዲዬ አባላት በዓሉ ላይ እንዲገኙ ተደርጓል። ተለይተው እንዲታዩ ባንዲራ ይዘው ነበር። ይህ ድርጊት በራሱ የርስ በርስ ግጭት ለማስነሳት ነበር። የእቅድ አነድ አካል ነበር ማለት ይቻላል። አስገራሚውና ሁላችንም መዘንጋት የሌለብን ሀላፊነት ከሚሰማቸው ክፍሎች ቀድምው በዓሉን አገዛዙ ለፖለቲካል ፍጆታ ለመጠቀም መሞከሩ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ በማስረዳት እንዲታቀብ  አስጠንቅቀውት የነበረ መሆኑንም ክግንዛቤ እናስቀምጥ።
 9. ከባድ መሳርያን ጨምሮ ተኩስ ነበር፡ አስለቃሽ ጪስ ተተኳሷል። በቦታው ሂሊኮፕተር ነበር። በቀደሙት አመታት  በእሬቻ በዓል ላይ የመልካም በዓል መልእክት የያዘ ወረቀት  በሂሊኮፕተር ይበተን የነበረ መሆኑ ገና መመርመር ያለበት ነው። እነዚህ ሂሊኮፕተሮች አስለቃሽ  ጪስ ወደህዘብ ተኩሰዋል። ወረቀትም አስለቃሽ ጪስም ሁለቱንም ለምን ቀድምው ተዘጋጁበት ? የሚለውም።
 10. አገዛዙ ከእሬቻው ፍጅት በሗላ እንግዳና ባልተለመደ ሁኔታ ፈጣን መግለጫ አውጥቷል። ከፍጅቱ በፊት የተዘጋጀ መግለጫ ነው የሚመስለው። መግላጫው ላይ የተካተቱት ቁም ነገሮች በሙሉ አንድ በአንድ ሲመረመሩ ቅድመ ዝግጅት እንደነበረ ተጨማሪ አስረጅነት አላቸው። በሗላ ላይ የፅጥታ አስከባሪዎቼ ምንም አይነት ተኩስ አላደረጉም የሚለው የጠቅላይ ሚንስትር ተብዬው ውሸት ሚሊዬኖች በቦተው ሆነው በአይናቸው ያዩትና የሰሙት ሆኖ እያለ ህዝቡን በማናዳድ ስሜታዊ ለማድረግ ሆን ተብሎ እንዲናገረው የተደረገ ነው ።
 11. እልቂቱ ከመፈፀሙ ከትንሽ ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ባካባቢው የነበሩ የሜዲያ ሰዎች ሁሉ ካካባቢው እንዲርቁ በፀጥታ ሀይሎች ተገደዋል።

 

አሁን ላይ በእሬቻ በዓል ላይ ሂወታቸውን ያጡና የተጎዱ ዜጎች ዝም ብለው ተረጋግጠው አለመሞታቸውንና አለመጎዳታቸው ለማንም ግልፅ ሆኗል። ተረጋግጠውም ሆነ ገደል ገብተው ወይ ባስለቃሽ ጪሱ ምክንያት አየር አጥተው ይሙቱ   መንግስት በወሰደው እርምጃ  ምክንያት የተፈጠረ ፍጅት መሆኑ የማያከራክር ሆኗል። እልቂቱ በስህተት ምክንያት የተፈጠረ ነው ወይስ አገዛዙ ቀድሞ አቅዶበት የፈፀመው ነው የሚለው ግን ገና ጎልቶ አልወጣም። ትክክለኛ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የቅሊንጦንና የእሬቻውን እልቂት አጣምሮ ማየት ተገቢ ነው። ከትግሬ ወያኔዎች የሗላ ተመሳሳይነት ያለውና ብዙ ንፁሀንን የመፍጀት ታሪክና መፈጸሚያ መንገዶቹን አካቶ ማየትም አስፈላጊ ነው። አሁን ላይ እያየን እንዳለነው የገጠመውን የህዝብ ተቃውሞ ለመወጣት ያዋጣል ብሎ ያስቀመጠው እቅድና እየወሰደ ያለው እርምጃንም ጨምሮም ማየት ያስፈልጋል። ከላይ አንድ ሁለት ተብለው የተዘረዘሩትን መክንያቶች ከነዚህ ቁም ነገሮች ጋር አብሮ ለጨመቀ  መረጃዎች የሚያስረግጡት ፍጅቱ በአግባቡ የታቀደና አስበውብት ተፈፃሚ ያደረጉት መሆኑን ነው። በተፈጠረ ስህተትና ቀድሞ በታቀደ ሁኔታ የተፈፀመ ፍጅት  የሚለው የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አለው። ይህን የንፁሀን ፍጅት እየመረመሩ ያሉ አካላት ሁሉ ቢፈልጉ ምክንያት ዘርዝረው ቀድሞ በታቀደ መንገድ መንግስት የፈፀመው አይደለም ማለት ይችላሉ። ግኝታቸው ላይ በስህተት ወይስ ቀድሞ ታቅዶ በአገዛዙ የተፈፀመ ነው የሚለው ላይ ልዩነት ባደረገ ጥርት ያለ መደምደሚያ ከሌለው  ግን  ሀላፊነት በተሞላበት አልቀረበም ወይም ሽፍጥ እንደሆነ አሁኑኑ መናገር ይቻላል። ይህ  ቁም ነገር ፍጅቱን መርምሮ ግኝቱን ለህዘብ ይፋ ለማድረግ እየሰራ ላለ የትኛውንም ክፍል ይመለከታል። በዋንኛት የገዳው ስርአት መሪዎች ሀላፊነት አለባቸው። በቦታው ነበሩ የተፈፀመውን ፍጅት በአካል ተገኝተው አይተዋልና።

ሞት እስር መደብደብ እያንዳንዱ የኦሮሞ ቤት ውስጥ ገብቷል። የህዝቡ ቁርጠኛነት ጽናት አስገራሚ መሆኑ እንዳለ  ተጠቂነት እልህና ቁጭት አዝሏል።  ወገኖቹን አስረው እሳት ለኩሰውባቸው ጠብሰው እንደበሏቸው ሰምቷል። ከሰባት መቶ በላይ ንፁሀን አራት ሚሊዬን ህዘብ  እቦታው ኖሮ እማኝ በሆነበት ፈጅተዋቸዋል። በዚህ እውነታ ውስጥ ህዘብ ስሜታዊ ሆኖ በንብረት ላይ ውድመት መፈፀሙ አስገራሚ አይደለም። አመፅ የተጨቆነና የተገፋ ህዝብ ድምፅ ነው። ይህ በሰው ልጆች ታሪካ ውስጥ ሁሌም የነበረና ወደፊትም የሚኖር ነው። የወደመው ለአገዛዙ የመጨቆኛ ጉልበትና የባለስልጣናቱ ንብረት ነው።  ስራችንን ወያኔዎችዩ  ቀሙን እንጂ እነዚህን ንብረቶች ዶጋ አመድ ማድረጉ ትግሉ ላይ አንዱ ስራችን ነበር።

ህዘብ ስሜታዊ እንዲሆን ምን ያህል እንደሰሩበትና ፍጅት መፈፀም ድረስ እንደሄዱ ከለይ  አይተናል።  ንዴት ውስጥ ገብቶ የንብረት ውድመት እንዲፈፀም አጥበቀው ፈልገዋል። ግን ለምን?። ይህ ፍላጎታቸው በእሬቻው እልቂት ምክንያት ተፈፃሚ በይሆን ኖሮ በእርግጠኛነት ሌላ አይነት ደግሞ ፍጅት ፈፅመው መሞከራቸው አይቀርም ነበር። መላ አሮሚያን በሰባት የፀጥታ ዞን ከፍለው በወታደራዊ አስተዳደር ስር ከዋሉት ቆይተዋል። ይህ ሁሉ የፈሰሰ ጦር ሰራዊት የህዝብን ደህንነት ሊጠብቁ አይደለም እዛ ያለው። ውድመቱ ባይፈለግ ኖሮ በደንብ መከላከል ይቻለው ነበር። ንብረቱን መጠበቅ የሚችል እጅግ ቁጥሩ የበዛ ፀጥታ አስከባሪ በቦታው ነበር። ለጊዜው ግልፅ ያልሆነው ቆያይቶ መታወቁ ግን የማይቀረው ወያኔዎች በዚህ ውድመት ላይ ከፍላጎትና የህዘብን ትግል ወደዛ ከመግፋት ባለፈ ቀጥተኛ በሆነ መንገድ በመሬት ላይ ምን አይነት ድርሻ ነበረቻው? የሚለው ነው። ይህን ጥርጣሬ የሚያጠናክረው ሌላ ጉዳይ ደግሞ ጠቅላላ  የአገሪቷ ፖለቲካ ባልተለመደ መንገድ ላሁኑ  አገዛዙን በፈለከው ደረጃ ማሳጣት፤ መውቀስ መስደብ ተፈቅዷል። ተናጋሪው ግን ሳይረሳ  “እንዴት ንብረት ይወድማል” የሚለውን በሆነ አገላለፅ ንግግሩ ውስጥ  እስካስገባ ማለት ነው።

ለማጠቃላያ ወያኔ ትግሬዎች የተነሰባቸውን አልገዘም ባይነት ለመቆጣጠር ተፈፃሚ እያደረጉ ያሉት እቅድ ሁሉም አይሰራም። አያዋጣምም።

 1. የጭንቅ ጊዜ አዋጁ። ዋና አላማው “አስቸኳይ”ና “አዋጅ” የሚለው ነገር ላይ ያለን የህዘቡ ስነልቦናና ያለፈ ተሞክሮ በመጠቀም ማስፈራራት ነው። የሚያስፈራ ግን አልሆነም።  እንደውም የተከለከሉትን ነገሮች በቀላሉ ህዘብ በብዙ ቁጥር በተራ በተራ በማፍረስ ቀላል መታገያ አድርገን ልንጠቀምባቸው የምንችልባቸውን ቁም ነገሮች ሰጥቶናል። ይህ ተጀምሯል ይቀጥላል።
 2. በተጓዳኝ በጠረቤዛ ዙሪያ በሚደረግ ወይይት መፍትሄ ለመስራት ተነሳሽነት ያለ የሚመስል የተጠናና በደንብ የታሰበበት ቲያትር በመስራት ማዘናጋት ነው። ቲያትሩም ተዋናዬቹም ጥሩ ሊከውኑት ግን አልቻሉም። ተሳክቶላቸውም ቢሆን አይገባቸውም እንጂ ህዝብ የዚህ አይነት ቲያትር ሁሌም ለህዝብ ካለ ንቀት የሚመጣ እንደሆነ ስለሚያውቅ የተማረረበትና ስልችት ያለው ነገር ነው። በነገራችን ላይ የመለስ ልጅ ንግግርም የቲያትሩ አካል ነው። በአጠቃላይ ወይይቱ ያንድ ጊዜ ነው። እንደተባለው ወደህዝብም አይወርድም። ምክንያቱም ህዝብ መፍራት አቁሟል። ፍርጥ አድርጎ ይናገራል። በጥልቅ ለመታደስ ማሰባችሁ ጥሩም ችግራችሁም ነው። እኛ ላይ ሆናችሁ ግን አታስቡት ማለቱ አይቀርም። ለፈፀሙት የንፅሀን ፍጅት ምክንያት ህዝብ መድርክ ላይ የሚቀርቡትን ባለስልጣናት ጉሮሮ ለማነቅ መነሳቱ አይቀርም። ልጄን ገድላችሗል ውለድ። ልጄን ያለአግባብ አስራችሗል በአስቸኳይ ፍቱ በሚል የቅርብ ዘመዶቻቸው ሊጋፈጧቸው እንደሚችሉ ያውቃሉ።
 3. የደረሰውን የንብረት መውደምና የኦሮሞ ህዘብ ትግል ላይ ያለን ጥርጣሬና ፍራቻ በማጦዝ የፈፀሙትንና የቀጠሉበትን የንፁሀን ፍጅት በህዝብ ዘንድ ዋና ትኩረት እንዳይሆንና ወንጀላቸውን  ተቀባይነት ያለው ለማድረግ መጣር ነው። ህዝብ እውነተኛውን መረጃ የሚያገኝበትን መንገዶች ሁሉ ዘግተው አጠንክረው እየሰሩበት ያለ ነው። በቀላሉ የዚህ አይነት ወጥመድ ውስጥ የሚወድቁ ፈዛዛ ሙህራኖች ተቃዋሚዎችና ተሰሚነት ያላቸወን ሰዎች መጠቀማቸው አይቀርም። ይህም ቢሆን አካሄዳቸው ከታወቀ መላ የሌለው አይደለም። ሲጀመር አልገዛም ባይነቱ በመላው አገሪቱ በጠቅላላው ህዝብ ዘንድ ስለሆነና የአማረው ተጋድሎ በሰሜን ባየለበትና አገዛዙ በተመሳሳይ  ጊዜ ንጹሀን ዜጎችን እየፈጀ ባለበት ይህቺ እቅዳቸውም እንደወትሮው አትሰራላቸውም።
 4. መላ አገሪቷን የመረጃ ጨለማ ውስጥ መክተት ነው። ይህ ለኛም ለነሱም ሁለት ጎን ስለት ያለው ቢሆንም አሳሳቢ ነው። ለጊዜው አውሪዎች እነሱ ብቻ ናቸው። እዚህ ጉዳይ ላይ ህዝብም የለውጥ አንቀሳቃሾችም የሚቻላቸውን ያህል መላ መፋላለግና ይህን ችግር መገዳደር ወና ስራ መሆን አለብት። በቀጥታ መታገል ባይቻል እንኳ በትላልቅ ህዝባዊ እንቢተኛነት ከበፊቱ በጠነከረ መንገድ አከታትሎ በማድረግ ማፈን እንደማይችል ተስፋ ማስቆረጥ ያስፈልጋል።

 

ምክር ቢጤ።

ህዘብ ግርግዳ አስደግፎ ማንቁርት ይዟል። ውጤት እያመጣ ያለ ትግል በደም ፍላት ስለገደሉ ስላሰሩ ተብሎ አይቀየርም። ከዚህ በፊትም ሁሌም በዚህ አይነት ሁኔታ ተገፍቶ የሚደረግ የትግል መስመር ለወጥ ፍዳችንን ሲያበዛው ነበር። ሊገልህ የመጣን አካል መከላከል አግባብም መገላገያም ሊሆን ይችላል። የማይካደው ግን ጉልበታም የሆነው በመግደላችን ሳይሆን በብዙ ቁጥር ሆነን አንፈልግም ማለት በመቻላችን ነው። ትልቁ ጉልበታችንም በቀላሉም ልናደርገው የሚቻለንም ይህው ነው። ያንኛው መንገድ እየተሰማንን ያለውን ጉልበተኛነትና የደረስንበትን በራስ መተማመን ገድሎ ነፃ አውጪ ጠባቂ ነው የሚያደርገን። ትግል በዋናነት የጭንቅላት ጨዋታ ነው። አዋጩ መንገድ አሁን ደግሞ ቀዝቀዝ አድርጎ ፍፁም ሰላማዊ ወደሆነ እንቢተኛነት መአቀፍ ውስጥ በቶሎ መልሶ ማጫወት ነው።  ይህን ስናደርግ ውስብሰም በቀላሉ  አሸናፊም እንሆናለን። ያዋጣል ካለ ለሁለተኛ ጊዜ ወደሀይልና ውድመት እሱ ይግፋው። ያኔ ለትግሉ የሚጠቅም ወይ የሚጎዳ መሆኑን የምናየው ይሆናል። አንድ ክልል ህዘብ ወይ የአንድ ከተማ ህዘብ ተነጋግሮ ላንድ ሳምንት እቤት መቀመጥ ከቻላ ሊያደርግ የሚችለው ብዙ ነግሮች ይኖራሉ። ፋታ መስጠት ግን ጥሩ አይደለም። እንደውም በአገር አቀፍ ደረጃ አዲስ አበባንም ጨምሮ አገር አቀፋዊ ተቃውሞ ተጣምሮ በቶሎ መጥሪያ ጊዜ ነው። የትግሉን አርማ  በእኩል ሰዓት ለደቂቃዎች በያለበት ቀጥ ብሎና ሁሉን ነገር ቀጥ እደርጎ በማሳየት የጭንቀት አዋጁን አንድ ሁለት እያሉ ከማፈራረስ  መጀመር ነው። ይህን ፅሁፍ ከመላኬ በፊት ከደቂቃዎች በፊት ይህን ጨመርኩ። የኢትዬጵያን ፖለቲካና አንድነት የሚያተረማምስ፤ ይህን ያህል መሰዋትነት የተከፈለበትና ቀና ያለ የህዘብ ትግል በቂጡ የሚያስቀምጥ፤ ሀላፊነት የሚባል ነገር በማይሰማቸው የሆነ ጊዜ ላይ አፍሮ ያበጥሩ የነበሩ አሮሞ አቢዬተኞ አባቶች   እየሰማው ነው። ታግሶ የመጨረሻውን ድምዳሜ መጠበቅ ተገቢ ይሆናል ልባል ላሁኑ እየተሰማኝ ያለው ግን ጥልቅ ሀዘንና ተስፋ ቢስነት ነው። በደም ፍላት ብዙ ላለማለት እዚህ ላይ ላቁመው።