የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ፣ ባለ እብነ በረዱ ህንፃ እና ኢትዮጵያን አጥፍቶ መጥፋት (የጉዳያችን አጭር ማስታወሻ)

ጉዳያችን/Gudayachn

ህዳር 19፣2009 ዓም (ኖቬምበር 26፣2016)

==============================
የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ጉዳይ
====================
በ2016 እኤአ  ሰኔ ወር ላይ በተዘጋጀ ሪፖርት ኢትዮጵያ ከጠቅላላ ምርት  52% ለብድር ክፍያ እና ዋስትና የሚውል ሲሆን ከእዚህ ውስጥ 30% ለውጭ ብድር ዕዳ የሚከፈል ነው (ካፒታል ጋዜጣ፣ጥቅምት 17፣2016) የአሁኑ የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ በ2014 =16.59 ቢልዮን ዶላር ሲሆን በአንድ ዓመት ውስጥ በ2015=19.04 ቢልዮን ዶላር (ከ400 ቢልዮን ብር በላይ) ደርሷል (CIA world fact book report)
እኤአ 2016 ሲጠናቀቅ ደግሞ ከ21 ቢልዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን በእዚህ ዓመት የሰማናቸውን የብድር ስምምነቶች  ደምረን ማወቅ እንችላለን።በአንፃሩ የኢትዮጵያ ገንዘብ ንፁህ ወርቅ ሳይቀር (ባለፈው ሳምንት ህንድ ኒው ዴሊ የተያዘውን ወርቅ ጨምሮ) በባለስልጣናት እና ዘመዶቻቸው እየተመዘበረ ነው።
ባለ እብነ በረዱ ህንፃ
===============
ከእዚህ በታች የምታዩት ህንፃ አዲስ አበባ ከንግድ ሥራ ኮሌጅ ዝቅ ብሎ የሚገኘው የፀረ ሙስና ኮሚሽን ህንፃ ነው።አሁን መስርያ ቤቱ ጥርሱ ወልቆ ስለ ሙስና ማስተማር እንጂ መክሰስ አትችልም ተብሎ ተቀምጧል።አቶ ኃይለ ማርያም አንድ ሰሞን ስለ ሙስና ፉከራ ነገር ሲያሰሙ ነበር።ዛሬ አቶ ደብረ ፅዮን ባልተስተካከለ አማርኛ ስለ ጥልቅ ተሃድሶ እያሉ ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ ስትዘረፍ ዜማ እያወጡላት ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ጨምሮ ብዙዎች ባለስልጣናት በውጭ ሃገራት በሚልዮን ዶላር እያጋበሱ ነው።የባለስልጣናት ልጆች ከኢትዮጵያ በሚላክ የውጭ ምንዛሪ በሚል ቅለድ ውጭ ሀገር ይኖራሉ፣ይነግዳሉ።ኢትዮጵያ ግን በዕዳ ተዘፍቃ፣ተቆጣጣሪ የሌለባቸው የዘመኑ ባለስልጣናት ይንደላቀቃሉ ሲፈልጉ ከመኪና መኪና ያማርጣሉ።
 federal-ethics-and-anti-corruption-commission-office

ኢትዮጵያን አጥፍቶ መጥፋት

===================
የኢትዮጵያ ውጭ ዕዳ ለትውልድ በሚተርፍ መልኩ እየጨመረ ነው።አሁን ዝርፍያው በኮማንድ ፖስቱ ደረጃ ተደራጅቶ ወደ እያንዳንዱ ሰው ቤት እየወረደ ነው።የኢትዮጵያውያን ቤት ልክ ደርግ በ1960ዎቹ መጨረሻ እንደሚያደረገው ቤት በማንኛውም ጊዜ ይበረበራል። ፈታሹ ያገኘውን ዕቃ የመውሰድ መብት አለው።ብዙዎች ጥሬ ገንዘብ ሳይቀር ከቤታቸው በኮማንድ ፖስቱ ተዘርፎባቸዋል። የሚጠፋው የሰው ሕይወት እና የታሰረው ወጣት ቁጥር የትዬለሌ ነው።ይህ ሁሉ ሆኖ የኢትዮጵያ ንግድ ሚዛን ተዛብቶ ቀውስ ተባብሷል።ኩባንያዎች ሰራተኞች እያባረሩ ነው። ለስርዓቱ ቅርብ የሆኑት እንደ ተክለ ብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን ሳይቀሩ 400 ሰራተኛ የቀነሱት በቅርቡ ነው። ቱሪዝም በአስደንጋጭ ደረጃ ቀንሷል።
የቡና አቅርቦት ለአንድ ዓመት ያህል በኦሮምያ በተነሳ ሕዝባዊ ማዕበል ቀንሷል።በርካታ ኩባንያዎች ኢትዮጵያን እየለቀቁ እየሄዱ ነው።በሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍል ጦርነት መከፈቱ ከተነገረ ሰነበተ።ይህ ማለት ሕወሓት የመከላከያ እና ደህንነት በጀት የበለጠ ያወጣል ማለት ነው።ይህ በደከመው የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ላይ ድህነቱ እና የዋጋ ንረቱን ያብሰዋል።ለእዚህ ሁሉ ቀውስ መነሻው የሕወሓት የስልጣን ጥማት አለመርካት ነው።ኢትዮጵያን አጥፍቶ መጥፋት የሚለው የሕወሓት መንገድ አደገኛ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በጎሳ እና መንደር መከፋፈል ትቶ ለኢትዮጵያ በአንድ ልብ መነሳት ያለበት ጊዜ አሁን ነው።ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማስቀጠል እና ከአጥፍቶ ጠፊ ለመታደግ የእያንዳንዱ ሰው ኃላፊነት ነው።

ጉዳያችን GUDAYACHN

 www.gudayachn.com

ትዝታና ቀልድ መሰል እውነታወች (ከይገርማል)

 

DOWN DOWN  – – -! የምን ነጋ ጠባ መጨነቅ ነው! እስቲ አንዳንዴ ፈገግ እንበል!

commentትናንት በዛሬ: ዛሬ በነገ እየተተካ ህይወት በማያቋርጥ የጊዜ ቅብብሎሽ ሲፈስ ያለፈው በትዝታ የሚታወስ የወደፊቱ ደግሞ በተስፋ የሚናፈቅ ይሆናል:: ጊዜ ጊዜን ሲተካ: ዕድሜ እየገፋ ሲሄድ: የጥንት የጠዋቱን ነገር ማሰብ: ያሳለፉትን ህይወት በትዝታ መኖር ይመጣል:: የወጣትነት ዘመን ትውስታ የጭንቀት ማስተንፈሻ: የእንቅልፍ ማጣት ችግር መከላከያ ክኒን ሆኖ ያገለግላል::

ፎጋሪ የምባል ባልሆንም ወጣት እያለሁ ሰው አስቀይሜ አውቃለሁ:: ከመልኳ በላይ ቁመናዋ የሚያምር አንድ የትምህርት ቤታችንን ልጅ መቸም አልረሳትም:: ጥሎብኝ ከመልክ በላይ ቁመና ልቤን ተርከክ ያደርገዋል:: የዚች ደግሞ የሚገርም ነው:: መቀመጫም መልክ አለውሳ! “መቀመጫዋ ነፍስ አለው” ነው የሚባለው! ከእለታት በአንዲት ቀን ይህች ውብ ልጃገረድ በፈጣን እርምጃ ወደ ት/ቤት ስትገሰግስ ድምጼን አጥፍቸ ከኋላዋ እየተከተልኋት ነበር:: ሳይረፍድባት ለመድረስ ትጣደፍ ስለነበረ ለማንም ለምንም ትኩረት አልነበራትም:: የመቀመጫዋን እንቅስቃሴ ተከትሎ ልቤ ከፍ ዝቅ እያለ ቢያስቸግረኝ ጉሮሮየን አሟሸሁና ድምጼን ከፍ አድርጌ “ጓሮሽ ይደላል!” አልኋት:: አፌን በቆረጠው ኖሮ! ከዚያ በኋላ ለዐይን እንኳ ተከለከልኩ:: መቀመጫዋን ወደአጥሩ ታዞርና እንደተዋጊ በሬ በግንባሯ አጮልቃ እያየች እስካልፍ ቆማ ትጠብቃለች እንጅ እኔን ከኋላ ማስከተል ቀረ:: ምን ዋጋ አለው! አሁንማ ላልቶ: ሟሙቶ ይሆናል::

ችግሬን የምታውቅ የሰፈሬ ልጅ “ስንት ቆንጆ በሞላበት ሀገር ተቀምጠህ ሌላ ሴት አልታይህ ማለቱ የሚገርም ነው:: አልቆረብህባት! ሴት  እኮ እሷ ብቻ አይደለችም: ዐይንህን ግለጥ” እያለች ደጋግማ መክራኛለች:: ያልገባት ነገር ለልጅቷ ያለኝ ስሜት የተለየ መሆኑን ነው:: ደግሞስ ሴቱ ሁሉ አንድ ነው እንዴ? “እሷም ሴት እኔም ሴት” የሚሉ ሴቶች ይገርሙኛል:: የፈለጋችሁትን በሉ እንጅ ሴትም ሆነ ሴትነት አንድ አይደለም: በፍጹም:: ሴትነት ስል የሙያ ወይም ሴታዊ አካል ለማለት ነው:: የሴት አካል ራሱ እንደ ጣት አሻራ በመልክም በጣዕምም የተለያየ ነው:: እ. . .ህ እውነቴን ነው!

አንድ ጊዜ አንድ የሰፈራችን ግድንግድ ሰው ከርሱ ጋር ስትነጻጸር እንጥል ከምታህል ልጅ ጋር ወደአልጋ ክፍል ገብቶ ሲወጣ አየሁት:: በጣም ገርሞኝ “እንዲያው እንዴት አድርገህ ነው­- – -? ልጅቷ ራሷ እኮ ደህና የወንድ አካል አታክልም” ብየ ተገርሜ ጠየኩት:: የበለጠ የተገረምሁት በሰጠኝ መልስ ነበር:: “ሞኝ ነህ” አለኝ እየሳቀ:: “እንዴት?” አልሁት ግንባሬን ከስክሼ:: “ሴትና ሹራብ እኮ አንድ ነው: ማለት ፍሪ ሳይዝ” ሆ – ሆይ! አያናድድም?

የወንድ አካልም እንዲሁ በቅርጽም: በመጠንም ይሁን ሙቀት በማስተላለፍ ጸጋ ይለያያል:: በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ የማውቃት ሴት የነገረችኝን ታሪክ አስታውሳለሁ:: ሴትዮዋ እንዳለችኝ እንደአባት ሆኖ ያሳደጋት ታላቅ ወንድሟ ለሆነ ሰው ድሯት ነበር:: “ሳላለቅስ ያደርሁበት ቀን አልነበረም” ትላለች:: እንደነገረችኝ ሰውየው ከአቅሟ በላይ ነበር:: ችግሩን ፍርጥርጥ አድርጎ መናገር ባልተለመደበት በገጠሩ ባህል በእንዲህ አይነት ሁኔታ የሚደርሰው ጉዳት ቀላል አይደለም:: በነጋ በጠባ እየሮጠች ከጎረቤት ብትሄድም እጇን ይዘው መልሰው ለዚያው ለምትሸሸው ሰው እያስረከቧት ስለተቸገረች የምታደርገው ብታጣ ጥርሷን ነክሳ እህ ብላ ችላ መኖር ትቀጥላለች:: ችግሯን ማንም አላወቀላትም: እርሷስ ብትሆን ምን ብላ ትናገር! “እንዲያው ምን ሆንሁ ብለሽ ነው?” ሲሏት “ምንም አልሆንሁም” ትላለች:: “መታሽ—አልመታኝም:: ሰደበሽ—አልሰደበኝም” እና ምን ልሁን ነው የምትይው ብለው ወስደው መልሰው ለዚያው ለምትጠላው ሰው ይሰጧታል:: አንድ ቀን ግን ስቃዩ በቃሽ ያላት አምላክ መልካም አጋጣሚ ፈጠረላት:: በደብሩ የአመት በዐል ከነባሏ ትጠራና ወደ ታላቅ ወንድሟ ቤት ትመጣለች:: አመሻሽ ላይ ቤተዘመዱ በምድጃ ዙሪያ ተቀምጠው ጠላ እየጠጡ እየተጫወቱ ነበር:: የያኔዋ ወጣት ባለታሪክ ከወንድሟ ጎን ጉልበቱን አቅፋ ተቀምጣ ከዚህ ሰው የሚገላግላትን መላ ታወጣ ታወርድ: ነገር ታላምጥ ይዛለች:: ባልዮው ደግሞ በማዶ በኩል በትይዩ ተቀምጦ ጠላውን እየከለበሰ: ንፍሮውን እየቃመ: ዘና ብሎ ወሬውን ይሰልቃል:: ጨዋታውና እሳቱ ያሞቀው የወይዘሮዋ ባል ቀስ በቀስ አካሉ እየተፍታታ ሲሄድ የወንድ አካሉ ከቁምጣው ያፈተልክና ልክ እንደቀትር እባብ እየተሳበ ወደታች ወርዶ ከአመዱ ላይ መንከባለል ይይዛል (የውስጥ ሱሪ የሚባል እኮ ገጠር የለም):: ወጣቷ ወይዘሮ ያንን “ባህር አንጀቴ ላይ ተኝቶ እንዳልጮህ ድምጼን ይሰልበዋል” የምትለው የወንድ አካል ከጎሬው ጠቅሎ መውጣቱን እንዳረጋገጠች ዕድሏን ለመሞከር ፈለገች:: የሆነ ነገር ልታዋራው የፈለገች አስመስላ በሹክሹክታ “አያ ጋሸ” ብላ ወንድሟን ጎሰም ታደርግና ትኩረቱን ስታገኝ በአይኗ ወደባሏ ጉያ ታመለክተዋለች:: ወንድሟ ያየውን ማመን ያቅተዋል:: በተደጋጋሚ እየተጣላች ከቤት ትወጣ እንደነበር ቢሰማም በቤተሰብ ናፍቆትና በልጅነት መንፈስ የምታደርገው እንጅ እንዲህ የከፋ ነጋር ያጋጥማታል ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር:: “እግዚኦ ያንተ ያለህ! እህቴን እንዴት ገድያታለሁ!” ብሎ ደጋግሞ አማትቦ “በል በቃህ ሂድ:: የስካሁኑ ይበቃሀል” ብሎ ባሏን ሸኝቶ ተጎጅዋን ሀራ አወጣት::

የዚች ሴት ታሪክ ቀላል የማይባል ትምህርት ሰጥቶኛል:: አንዲት ሴት ከባሏ አልመጥን አለች ተብላ ስትወነጀል ስሰማ አንደኛ ተከራካሪ ሆኘ እቀርባለሁ:: “አትብይ ቢላት ነው እንጅ ያን የመሰለ የሞላ ቤት ትቸ እሄዳለሁ ብላ የምትገለገል መሆን ነበረባት! ከአልጋ ሲሉት ከአመድ ማለት እኮ እንዲህ ነው:: መቸም እንደድሀ ጥጋብ የሚነፋው የለም!” ሲባል ከሰማሁ “ከአቅሟ በላይ ሆኖስ እንደሆነ” ብየ ቱግ እላለሁ::

አንዲት ሌላ የማውቃት ሴት “ጣዕሙን ሳላውቀው የሁለት ልጆች እናት ሆንሁ” ያለችኝንም በሳቅ ብቻ አላለፍሁትም::

ከዚህ የከፋ ታሪክ ደግሞ ከወደደቡብም ሰምቻለሁ:: የሰውየው አካል ከመርዘሙ የተነሳ ልክ እንደዝናር ሁለት ዙር ነው አሉ ይታጠቀው የነበረው:: ወገቡን ባላስተውልም ሰውየውን በአካል አይቸዋለሁ:: ከረንቡላ መጫወቻ ያለው ቡናቤት ነበረው:: ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዷል:: የግብረስጋ ግንኙነት በሚያደርግበት ጊዜ ከልኩ እንዳያልፍ በወንድ አካሉ ላይ የሚያጠልቀው ቀለበት ነበረው ይባላል:: ከሚስቱ ጋር ከተጣላ የሚቀጣት በግብረስጋ ግንኙነት ጊዜ ቀለበቱን በማውለቅ ነበር አሉ:: እንዲያ ባደረገ ቀን ለሁለት ሳምንት ያህል ሽንቷ ጠብ ባለ ቁጥር በስቃይ አገር ይያዝልኝ እያለች ትጮህ እንደነበር ሲወራ ሰምቻለሁ:: ሰውየውም እኮ ባይታደል ነው! ቢቸግረው ሜዳ ወርዶ ከአህያና ከፈረስ ጋር መዋል ይጀምራል:: በኋላ ላይ ግን እነሱም ነቄ አሉ:: እና ገና ከሩቅ ሲያዩት ጆሯቸውን ቀጥ አድርገው ሲያጠኑት ይቆዩና  በኋለኞቻቸውም በፊተኞቻቸውም እግሮቻቸው መሬቱን ደጋግመው ደብድበው ጭራቸውን ነስንሰው እያናፉ ወንዝ ነሽ ገደል ነሽ ሳይሉ እግራቸው ወደአመራቸው ጋልበው ይሰወራሉ እየተባለ እንደቀልድ ሲወራ ሰምቸ ጉድ ብያለሁ:: ይህን የሰማ ጓደኛየ ያንን የደቡብ ሰው መሆን እንዴት  እንደተመኘ አትጠይቁኝ! “አብደሀል እንዴ!” ስለው “ያበድህስ አንተ! በሳቀች: ባነጠሰች እና ባሳላት ቁጥር ፍትልክ እያለች የምትወጣ የዶሮ ዕቃ በመያዜ እንዴት እንደምሳቀቅ ምን ብየ ብነግርህ ይገባሀል!” አለና አፌን አስያዘው:: በሴቶች ዘንድ ያለውን የሴትነት ልዩነት በተመለከተ የበለጠ ለተማረ ለተመራመረ ትቸዋለሁ::

እና እንዳልሁት መሳደብ: መፎገርም ሆነ መሸርደድ ላይ አክቲቭ አይደለሁም:: ጨዋታ ግን እወዳለሁ:: ሚስጥር ጠባቂና ጥንቁቅ ነኝ:: ለዚያም ይመስለኛል ሌላውም እንደኔ አልሆነም በሚል ያመንሁት ሰው ሲከዳኝ ወይም ጎድቶኛል ብየ ካሰብሁ መጥፎ ሰው የምሆነው:: መጥፎ ተሰርቶብኛል ብየ ካሰብሁ ለስላሳው ማንነቴ ይጠፋና ልክ እንደተፈታች ሴት ወትዋች ሆኘ አርፋለሁ:: ስህተቴን ባውቀውም ልታረም ግን አልቻልሁም: አይገርምም! ባለቤቴ በሆነ ጉዳይ ሰው ሲነቀፍ ወይም ሲወነጀል ስትሰማ “አትፍረዱበት ምን ያድርግ! ፈጠረበት!” የምትለው ነገር አላት:: እኔም አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ መሆን: መታገስ እንዳልችል አደረገኝ: ፈጠረብኝ:: ምናልባት የስነልቦና ድጋፍ ያስፈልገኝ ይሆናል::

የስነልቦናን ጉዳይ ሳነሳ የሳይኮሎጅ መምህሬ ትዝ ይሉኛል:: መምህራችን የሰውን ዐይን ደፍረው ትኩር ብለው ማየት የሚከብዳቸው ዐይናፋር ሰው ነበሩ:: እንዴት የሳይኮሎጅ መምህር እንደሆኑ ሳስበው ይገርመኛል:: ሳይኮሎጅ ማለት የሰውን ገጽ አይቶ: የአካላዊ እንቅስቃሴን ቃኝቶ የውስጥ ስሜትን ማንበብ የሚያስችል የትምህርት ዘርፍ አይደለም እንዴ! ያም ሆነ ይህ ከትምህርቱ በላይ የመምህሩ አቀራረብና ሁኔታ ትኩረታችንን ይስበው ነበር:: ጊዜው በደርግ ጊዜ ነው:: መምህሩ ባኅል በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ በምሳሌ እያስረዱን ነበር:: ከፊት የተቀመጠችውን አጎጠጎጤ ወደደረታቸው አስጠግተው ይዘው “አሁን ይህችን እህቴን አቀፍኋት:: ተመልከቱ እሷም አፈረች እኔም አፈርሁ” ሲሉ ልጅቱ ከት ከት ከት ብላ ትስቅ ጀመር:: መምህሩ ለእንደዚህ አይነቱ ነገር ትዕግስት አልነበራቸውም:: በንዴት “ግን ይህች እህቴ ለምዳለች መሰል…”ብለው ንግግራቸውን ሳይቋጩ ክፍሉ በሳቅ ተሞላ:: መምህሩ በንዴት ክፍሉን ጥለው እብስ አሉ:: ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ተመልሰው ሲመጡ ምንም እንዳልተሰማን ለመሆን ሞከርን:: ቁምነገር እያስተማሩን እያለ መሳቃችን በጣም አበሳጭቷቸዋል:: እናም ስህተታችንን በምክንያት ሊያስረዱን ፈለጉ:: “አያችሁ ወጣቶች! አሁን ይህን አስከፊ ምላሴን እንዲህ አድርጌ ባወጣው አትስቁም” አሉ ምላሳቸውን በሹፈት መልክ አውጥተው እያሳዩን:: ከዚያም ቀጠሉና እጃቸውን ወደጉያቸው እየላኩ “የወዛደሩን አባት ባወጣው ግን  – – -” ሲሉ ክፍሉ እንደገና በሁካታ ደፈረሰ:: መምህር እንደለመዱት ከክፍሉ በረው ወጡ:: ከዚያ በኋላ ተመልሰው የመጡት ከሁለት ቀን በኋላ በነበረው ክፍለጊዜ ነበር:: ወደክፍል ሲገቡ ከወትሮው በተለየ ኩስትርትር ብለው ነበር:: ያም ሆኖ እዚያም እዚያም እንደፈንድሻ ቱፍ ቱፍ የሚለውን ሳቅ ማስቆም ቀላል አልነበረም:: መምህራችን ግምባራቸውን እንደቋጠሩ “ብዙሀኑ ፈገግ ብሏል: አንዳንዱ ይገለፍጣል!” አሉ:: የሳይኮሎጅ የትምህርት ክፍለጊዜ ከምንም በላይ የምንናፍቀው መዝናኛችን ነበር::

 

አዋዜ ……. ፊደል አረፉ፤አንድ ምዕራፍ የዓለም ታሪክ ተከተተ

ፊደል!በማንኛውም መመዘኛ ፃዲቅ!!!!የድሆች አቅም!!!!የድሆች ውበት!!!!!! በማንኛውም መመዘኛ ከፊትለፊቱ በየተራ ከተሰለፉ ጠላቶች በእጅጉ የላቀ የሞራል ልዕልና የነበረው ተፋላሚ!ተፉልሞም ድል ነሺ!!!!!ምሽቱን አዋዜ የመሳ-የለሹን ፊደል ተሰምቶ የማይጠገብ ታሪክ ይዞ ይቀርባል!!!!ርእሱም “ፊደል ዕውንትም ቃል ነበር!”


mengisturaulcastro

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ስለ ኢህአዴግ ግምገማዎችና ተሃድሶ [አለማየሁ አንበሴ]

negaso-2-satenaw-newsየኢህአዴግ የግምገማና የተሃድሶ ባህል ምን የኢህአዴግ የግምገማና የተሃድሶ ባህል ምን
ይመስላል? በሚለው ላይ በሽግግሩ ወቅትና ከዚያ በኋላ እስከ 1993 የተሃድሶ ንቅናቄ ድረስ የኦህዴድ እና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ይመስላል? በሚለው ላይ በሽግግሩ ወቅትና ከዚያበኋላ እስከ 1993 የተሃድሶ ንቅናቄ ድረስ የኦህዴድእና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ
ጊዳዳ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

እርሶ በመንግስት አመራርነት በነበሩ ጊዜ ግምገማዎች እንዴት ይካሄዱ ነበር?
መስሪያ ቤቶችና ተቋማት፣ መጀመሪያ ስራቸውን ለማሻሻል የስራ እቅድ ያዘጋጃሉ፡፡ ከዚያም በየጊዜው መሰረት አፈፃፀሙ ይገመገማል፡፡ እኔ የነበርኩ ጊዜ፣ የየዞኖች የስራ አፈፃፀም በየወሩ ይገመገም ነበር፡፡ የክልል ደግሞ በ6 ወር ይገመገም ነበር፡፡ በዓመት አንድ ጊዜ ደግሞ፣ የየድርጅቶቹ ስራ አስፈፃሚ፣ በኢህአዴግ ጽ/ቤት ይገናኝና ጠንካራ ግምገማ ይካሄዳል፡፡
በአብዛኛው የስራዎች አፈፃፀም፣ ጥንካሬና ድክመት ነው የሚገመገመው፡፡ ይህ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ይባላል፡፡ የስራ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ፤ የፈፃሚ አካላት ግምገማ ይደረጋል፡፡ የፈፃሚው አካል (የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና የክልል ቢሮዎች ወዘተ …) በስራው ጥንካሬና ድክመቶች ላይ ሚናው እንዴት ነበር? የሚለው ይገመገማል፡፡
ይህ ካለቀ በኋላ ተቋማትን የሚመሩ ኃላፊዎችና አባላት በግለሰብ ደረጃ ይገመገማሉ፡፡ በጥንካሬ ውስጥ አስተዋፅኦቸው ምን ነበረ? በድክመቱ ላይስ? የሚለው ለየብቻ በነጥብ ተለይቶ ይቀመጣል። ይህ ከተደረገ በኋላ ሰውየው (ተገምጋሚው)፣ የራሱን ሃሳብ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ሌሎችም ሃሳብ ይሰጣሉ። የሰውየው ጥንካሬ የሚያመዝን ከሆነ፣ በጥሩ የስራ አፈፃፀም እውቅና ይሰጠዋል፡፡ ደካማ ከነበረ ደግሞ፣ ለምንድን ነው የደከመው? የሚል ጥያቄ ይቀርባል። ግለሰቡ (ተገምጋሚው)፣ በዚህ ላይም አስተያየት ይሰጣል፡፡ ለምን ይሄን መፈፀም አቃተህ ተብሎ ሲጠየቅ፣ ስራ ስለሚበዛብኝ፣ መሳሪያዎች ስላጣሁ፣ መኪኖችን ስላጣሁ፣ ገንዘብ ስላጣሁ እና መሰል ምክንያቶችን ብዙውን ጊዜ ይዘረዝራል፡፡
ገምጋሚው አካል፣ ይሄን ምክንያት አልቀበልም፣ ያንን እቀበላለሁ ይላል፡፡ ለመሆኑ ለስራው ከልብህ እምነት ነበረህ ወይ? በስራው ታምንበት ነበር ወይ? ያ ከሆነ እንዴት መፈፀም አቃተህ? የሚሉ ጥያቄዎች ይሰነዝራሉ፡፡ አንዳንዱ፣ የምትሉትን አልቀበልም ይላል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ አምኖ ይቀበላል፡፡ ግለሰቡ የግምገማውን ነጥቦች ከተቀበለ እንዲያሻሽል ተነግሮት ይታለፋል፡፡ ካልተቀበለ ግን፣ “ይሄ ሰውዬ በስራ አያምንም፤ በስራው የማያምነው ደግሞ በድርጅቱ ስለማያምን ነው” ተብሎ ይደመደማል። ከዚያም እንደጥፋቱ አይነት ወደ ቅጣት ይገባል፡፡
ምን አይነት ቅጣት?
ገንዘብ ሰርቆ ከሆነ፣ ስራ በጣም አባላሽቶ ከሆነ፤ በሰው ላይ ጉዳት አድርሶ ከሆነ፣ እስከመባረር እና እስከ መታሰር የሚደርሱ እርምጃዎች ይወሰዳሉ። ለምሳሌ ኦህዴድ እኔም በነበርኩበት በ1989 ዓ.ም፤ በጠንካራ ግምገማ፣ የአርሶ አድር ካድሬዎችን ጨምሮ፣ ወደ 10ሺህ የሚጠጉ አባላትን አባረናል፡፡ እነዚህን ስናባርር መጨረሻ ላይ የቀረው መሃከለኛ ካድሬ 300 ብቻ ነው፡፡ 180 የሚጠጉት ደግሞ ወደ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ እና እንዲታሰሩ መደረጋቸውን አስታውሳለሁ፡፡ እነዚህ ሰው የገደሉ፣ ገንዘብ የሰረቁ፣ ሙስና የታየባቸው ናቸው፡፡ ከዚያ በኋላ በነበረ ሌላ ግምገማ፣ አቶ ኩማ ደመቅሳ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትነት ወርዶ ነበር፡፡
አቶ ኩማ ተገምግመው ነው እንዲወርዱ የተደረጉት?
አዎ! እነ ነጋሶን አልታገልክም ተብሎ በሚገባ ተገምግሞ ነበር፡፡ በደከሙት አመራሮች ላይ፣ በብርቱ አልታገልክም ተብሎ በ1993 ተገምግሞ ነበር፡፡ በ1989ኙ ግምገማ ከከፍተኛ አመራር እንዲወርዱ ከተደረጉት እነ ጫላ ሆርዶፋ ነበሩበት። በኋላ እንዴት እንደሆነ አላውቅም፤ ያኔ ተባረው የነበሩ ሰዎች ተመልሰው ተመልክተናል፡፡
ግምገማዎቹ ጠንካራ ነበሩ?
አዎ! በጣም ጠንካራ ነበሩ፡፡ በኦህዴድ ውስጥ ጠንካራ ግምገማ ይካሄድ ነበር፡፡ የሌሎች እህት ድርጅቶች ሁኔታ አላውቅም ነበር፡፡ በወቅቱም የግምገማ ውጤታቸው አንሰማም ነበር፡፡ ለምን የእህት ድርጅቶች የግምገማ ውጤት አይነገረንም የሚል ጥያቄ በአንዳንድ የኦህዴድ አባላት ይነሳ ነበር። ግን የኦህዴድ ግምገማ ጠንካራ እንደነበር ጥርጥር የለውም፡፡ ያለ ስስት 300 ካድሬ እስኪቀሩ ከ10 ሺህ በላይ ካድሬዎችንና አባላትን ማሰናበት መቻሉ ማሳያ ነው፡፡
በግምገማዎቹ እያንዳንዱ የግንባሩ አባል ድርጅቶች የኦህዴድ፣ የብአዴን፣ የህውሓት የውስጥ ነፃነት ምን ድረስ ነበር?
አራቱም ድርጅቶች በተናጠል ግምገማ ሲያካሂዱ፣ ከዋናው የኢህአዴግ ጽ/ቤት የሚላኩ ታዛቢዎች ነበሩ፡፡ የስብሰባው አካሄድ እንዴት ነበር የሚለውን ለማየት ነው፡፡ በ1989 በነበረው ጠንካራ ግምገማ፣ እኔ እስከማስታውሰው እነ ተወልደ፣ አለምሰገድ በኦህዴድ ግምገማ ላይ ይገኙ ነበር፡፡ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ደግሞ፣ ሁል ጊዜ እንደ ረዳት ተደርጎ ወደ‘ኛ ስብሰባዎች ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ይላክ ነበር፡፡ ወደ ሌሎቹ እህት ድርጅቶችም በተመሳሳይ ከዋናው ጽ/ቤት ሰዎች ይላኩ ነበር፡፡
ወርሃዊ እና በየ3 ወሩ የሚደረጉ ግምገማዎችን ግን ራሳችን ነበር የምናካሂደው፡፡ ሰው አይላክም ነበር፡፡ በድርጅት ተግባራዊ ግምገማ ውስጥ የሚዲያ ጉዳይም አለ፡፡ የሚዲያውን አመራሮች ግምገማ በየ2 ሳምንቱ እኔ ነበርኩ የምመራው፡፡ አመራሮቻቸውን ወደ ጽ/ቤት እየጠራሁ ጠንከር ያለ ግምገማ እናካሂድ ነበር፡፡ አልማዝ መኮ ደግሞ የኦህዴድ አባላት በፓርላማውና በዩኒቨርሲቲ ያሉትን ትከታተል ነበር። ጠንካራ ግምገማዎች ነበር የሚካሄዱት፡፡
ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ወደየድርጅቶቹ የሚላኩት ግለሰቦች ሚና ምን ነበር?
በኢህአዴግ የጽ/ቤት ኃላፊዎች በረከት፣ አለምሰገድ እና ተወልደ ነበሩ፡፡ ይመስለኛል በረከት የሁሉንም ድርጅቶች የድርጅታዊ ስራ ይከታተል ነበር፡፡ አለም ሰገድ ደግሞ የፕሮፓጋንዳውን ዘርፍ ይከታተል ነበር፡፡ ተወልደ ደግሞ ሁለቱን ይቆጣጠር ነበር፡፡ ከነዚህ ሰዎች ስር፣ የተለያዩ ጠንካራ ካድሬ የሚባሉ ነበሩ፣ በትግሉ ውስጥ የቆዩ ሰዎች ስለነበሩ የድርጅቱ ግምገማ እንዴት እንደሚካሄድ ያውቃሉ፡፡
እነዚህ ወደየድርጅቶቹ የሚላኩት ግለሰቦች መድረክ ይመሩ ነበር? በውሳኔ ውስጥስ ይሳተፉ ነበር? ተፅዕኖአቸው ምን ድረስ ነው?
መድረክ አይመሩም፡፡ ግን ሃሳብ ይሰጡ ነበር። አቅጣጫም ያስይዙ ነበር፡፡ የነዚህ ሰዎች ሚና፣ የታዛቢነት ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በውሳኔዎች አይሳተፉም፡፡ መጨረሻ ላይ በግምገማው ላይ የራሳቸውን አስተያየት ያቀርባሉ፡፡ ለኢህአዴግ ጽ/ቤት ያቀርባሉ፡፡ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ደግሞ ወደ ስራ አስፈፃሚው ያቀርባል፡፡ በወቅቱ የስራ አስፈፃሚው ሊቀ መንበር አቶ መለስ ነበር፤ ፀሐፊው ደግሞ አቶ በረከት ስምዖን ነበር፡፡
በአጠቃላይ፣ ከአራቱም ድርጀቶች የተወከልን አምስት አምስት ሰዎች ነበርን – በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፡፡ በየድርጅቶቻችን የተገመገምን ቢሆንም፣ በዚህ የስራ አስፈጻሚ ግምገማ ላይ በድጋሚ ለግምገማ እንቀመጣለን። 20ዎቻችን እኩል ነበር ድምፃችን የሚሰማው። በወቅቱ በኦህዴድ በኩል እኔን ጨምሮ ኩማ ደመቅሳ፣ አሊ አብዶ፣ ዮናታን ዱቢሳ ነበር፡፡
ድምፃችን የሁላችንም እኩል ነበር፡፡ አጨቃጫቂ ጉዳይ ካለ፣ ውሳኔ ለሌላ ጊዜ እናስተላልፍ ነበር። አንዳንዴ ደግሞ አጨቃጫቂ ቢሆንም በድምፅ ብልጫ እንወስናለን፡፡ ለምሳሌ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ውሳኔ ሲተላለፍ፣ አቶ መለስና ዶ/ር ካሱ ብቻ ነበሩ በልዩነት የወጡት፡፡ ከሁለቱ በስተቀር፣ ሌሎቻችን (18) በአንድ ድምፅ ነበር በጦርነቱ ጉዳይ ውሳኔ ያሳለፍነው። ብዙ ሰው በወቅቱ አቶ መለስ ሁሉንም ነገር የሚወስን ይመስለዋል፡፡ ግን አይደለም። መለስ ራሱ በግምገማ ትችት ይደርስበት ነበር። በድርጅት ጉዳይ በተደጋጋሚ ተተችቷል። በእርግጥ፣ የመንግስት ስራን አቶ መለስ እንዴት ይመራ እንደነበር ግምገማ አይደረግም ነበር፡፡ በወቅቱ ይሄ ጉዳይ አጨቃጫቂ ነበር፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከኤርትራ ጦርነት ጋር ተያይዞ ነው፣ አጠቃላይ የመንግስት ስራ ይገምገም ተብሎ
የተወሰነው፡፡ በዚህ ጊዜ፣ አቶ መለስ ሌላ አጀንዳ ይዘው ብቅ አሉ፡፡ እኛ ግምገማ እናደርጋለን ብለን ስንቀመጥ፣ አቶ መለስ እነሱ የድርጅቱን የወደፊት አቅጣጫ የምታሳይ ናት በማለት “ቦናፓርቲዝም” በሚል ርዕሰ የተፃፈ ሰነድ ይዘው መጡ፡፡ የወደፊት አቅጣጫችን ምን እንደሚሆን ከወሰን በኋላ ግምገማ እናካሂዳለን አሉ፡፡ ይሄ ነበር በወቅቱ አጨቃጫቂ የነበረው፡፡ እኔ ከድርጅቱ ከወጣሁ በኋላ እንዴት እንደሚደረግ መረጃው የለኝም፡፡
አሁን የ15 ዓመት የኢህአዴግ የስራ አፈፃፀም ግምገማ እየተደረገ መሆኑና ድርጅቱና መንግስት በጥልቅ ተሃድሶ ላይ መሆናቸው እየተገለፀ ነው፡፡ ከነበረዎት ልምድ በመነሳት፣ ግምገማው ውጤታማ ይሆናል ብለው ይጠብቁ ይሆን?
ግምገማው ትክክለኛ ከሆነ መልካም ነው። ይመስለኛል የስራ ግምገማ ከተደረገ በኋላ፤ የግለሰቦች አስተዋፅኦ ጥንካሬና ድክመት ይገመገማል። እንደማስታውሰው በስራ ድክመት ከድርጅት የሚባረር አልነበረም፡፡ ለመባረር ዋናው ምክንያት፣ የአመለካከት ግምገማ ነው፡፡ በስራ ግምገማ ደካማ ውጤት ያገኘ ግለሰብና ከስራ ቦታው ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወር፣ ከስልጣን ዝቅ እንዲል ይደረጋል፡፡ ለምሳሌ አቶ ሙክታር ከድር እና ወ/ሮ አስቴር ማሞ ከስልጣን ወርደዋል ተብሏል፡፡ ግን በዞኖች ግምገማ ላይ መድረክ ሲመሩ ታይቷል፡፡ ይሄን ስመለከት፣ እነዚህ ሰዎች በግምገማ የተገኘባቸው ጥፋት፣ የስራ ድክመት ብቻ ነው? የሚል ጥያቄ አጭሮብኛል፡፡ ነገር ግን በስራ ድክመቱ የተነሳ‘ኮ ግጭት ተፈጥሯል ተብሏል፡፡ የሰው ህይወትና ንብረት ጠፍቷል ተብሏል፡፡ ይሄ ጥያቄ አጭሮብኛል፡፡ ግን እንዳልኩት የስራ ድክመት አያስቀጣም፡፡
ከአሁኑ ግምገማ ምን ይጠብቃሉ?
የአሰራርና የአመለካከት ግምገማ ተካሂዶ፣ “የተቃዋሚ አመለካከት አለው፤ በዚህ ነው ስራውን መስራት ያልቻለው” ተብሎ ከተገመገመና ጥፋቱ አስከፊ ከሆነ የሚወሰዱት እርምጀዎች፣ ከማሰር፣ ከማባረር እና ከቦታ ቦታ ማዘዋወር የትኛው እንደሚሆን፣ በቀጣይ የምናየው ይሆናል፡፡ እርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡ ቀድሞ በነበረው አሰራር ግን፣ እርምጃ ሳይወሰድ ቀድሞ አይነገርም ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ግምገማው ምናልባት ስራቸውን ለማሻሻል ይጠቅማቸው ይሆናል፡፡
ህዝቡ ያቀርባቸው ብዙ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጥያቄዎች እንዳሉ ሁሉ፣ የፖለቲካና የዲሞክራሲ ጥያቄዎችም አሉ፡፡ እኔ የምፈራው የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳዮችን ብቻ ለማሻሻል ጥረት አድርገው፤ በሚዲያና በዲሞክራሲ ረገድ፣ በተለይ ሰፊው ህዝብ የሚሳተፍበት መድረክ ሳይከፍቱ እንዳያልፉት ጥርጣሬ አለኝ፡፡ በነዚህ ጉዳዮች ላይ፤ ብዙ ሲናገሩ አይደመጡም፡፡ የሰብአዊ መብት አያያዝና የዲሞክራሲ ጉዳይ ካልተሳሻሻለ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መስኩን ማስተካከል፣ ብቻውን ውጤት ላያመጣ ይችላልና ቢያስቡበት ጥሩ ነው፡፡
እኔ ትንሽ የተስፋ ፍንጭ ያየሁት፣ የምርጫ ስርአቱ ላይ ማሻሻያ ይደረጋል የተባለው ላይ ነው። ይሄ ደግሞ ህገ መንግስት ማሻሻልን ይጠይቃል። ያንን ያደርጋሉ አያደርጉም የሚለው ለወደፊት የሚታይ ነው፡፡ በሚዲያ በኩል ደግሞ፣ ሬዲዮ ፋና ውይይት ማዘጋጀቱ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን በመንግስት ሚዲያ ላይ አንቀፅ 29 እየተሰራበት ነው ወይ የሚለውን ማየት አለብን፡፡

በታችና ምዕራብ አርማጭሆ ከባድ ጦርነት ተቀስቅሷል – ሙሉቀን ተስፋው

amara-mili-456-satenaw-newsከፋኝ የዐማራ ንቅናቄ ሥር የሚንቀሳቀሱ ታጋዮች ከወያኔ ሠራዊት ጋር ትንቅንቅ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ዛሬ ኅዳር 18 ቀን 2009 ዓ.ም. የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዐማራ ታጋዮች በወያኔ ሠራዊት ላይ ድል እየተቀዳጁ ነው፤ በሳምንቱ በነበሩ ከፍተኛ የጦር ሜዳ ውሎዎች ከአገዛዙ በኩል የተገደሉ ወታደሮች ወደ መቶ የሚጠጉ ሲሆን እስካሁን ባለው መረጃ አራት የዐማራ ወጣቶች ሰማዕት ሆነዋል፡፡ የዐማራ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው የከፋኝ እንቅስቃሴን እየተቀላቀሉ እንደሆንም ሰምተናል፡፡ በአካባቢው የመገናኛ ዘዴዎች በመዘጋታቸው ምክንያት የዛሬውን ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡

የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

 

 28 ክላሽ እና አንድ ብሬን በመማረክ እንዲሁም 75 የህወሃት ወታደሮችን የደመሰሰው #የአማራ #ከፋኝ ቡድን ሶስት ጀግኖች ተሰውተውበታል።
15178996_1185887718163018_7505170249682926770_n

15192706_1185887688163021_705426244836801395_n1.ሞላ አጃው
2.ሲሳይ
3.ማህቤ ይባላሉ።ሁሉም ታሪካቸው ገራሚ ነው።

የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄን በተገቢው መንገድ አለመመለስና ይልቁንም በህዝብ ላይ ግድያ እና እስራትን መከፈት ተከትሎ እጅጉን የተከፉት የአማራ ገበሬዎች፣ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞች በየ አካባቢው ጫካ እየገቡ ነው።ከፋኝ ደግሞ ጠንካራ እና አይገበሬ ናቸው።

በሁሉም አካባቢ ያሉ የአማራ ገበሬዎች የትግሉ ተሳታፊ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።ህወሃት እንጅ እኛ ጦርነትን አልመረጥነውም ነበር ሲሉም ተናግረዋል።እንግዲህ ምን ጭንቅ…..

 

አቶ ልደቱ አያሌው …..መንግሥት ሕዝቡ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዳይነሳ

lidetu-000-satenaw-news-s–  ኢዴፓ አንድ ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር ማንኛውንም ዕርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ ነኝ አለ

በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የተፈጠረውን ቀውስ ባለው የሕግ አግባብ መፍታት እንደማይቻል አምኖ መንግሥት ከመስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ፣ ተገቢና የሚስማማበት ዕርምጃ መሆኑን የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ገለጸ፡፡ ነገር ግን በአገሪቱ ዘላቂ መፍትሔ የሚመጣው፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ፣ በወታደራዊ ጣልቃ ገብነት፣ በጥልቅ መታደስና ካቢኔ በመቀየር ሳይሆን ሕዝቡ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ በመስጠት በመሆኑ፣ ይኼንን ተግባራዊ ሳያደርግ አዋጁ እንዳይነሳ ኢዴፓ አሳስቧል፡፡

የኢዴፓ መሥራችና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ልደቱ አያሌው ኅዳር 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በቅሎ ቤት በሚገኘው የፓርቲው ጽሕፈት ቤት ከፓርቲው አመራሮች በጋራ በመሆን በሰጡት መግለጫ እንዳስረዱት፣ መንግሥት ሕዝቡ ያቀረበውን የዴሞክራሲ፣ የሰብዓዊና ኢኮኖሚያዊ፣ በእኩልነት የመልማትና ፍትሕ የማግኘት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እንዳለበት መንግሥት በተደጋጋሚ መናገሩን፣ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔርም በ2009 ዓ.ም. የፓርላማ መክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ማረጋገጣቸውን አስታውሰዋል፡፡ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር፣ ሕዝቡን በስፋት ለማወያየትና ፖሊሲዎችንም እስከማሻሻል የሚደርሱ ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ጭምር ቃል የተገባ ቢሆንም፣ እስካሁን ምንም አለመደረጉን አቶ ልደቱ አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም በተለይ ሕዝቡ ያነሳቸውን የመብት ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳ፣ አገሪቱን ሊገታ ወደማይችል ችግር ውስጥ ሊያስገባ እንደሚችል ሥጋታቸውን ተናግረዋል፡፡

የሕዝቡ ፍላጎት ኢሕአዴግ ታድሶና ካቢኔውን እንደገና አዋቅሮ አቅሙን በማጠናከር እንዲመራው ሳይሆን፣ ላቀረባቸው ጥያቄዎች በዓይን የሚታይ ተግባራዊ ዕርምጃ በመውሰድ ለውጥ እንዲያመጣለት መሆኑንም አክለዋል፡፡ ኢሕአዴግ አሁን የያዘውን የመታደስና ካቢኔውን የማስተካከል ለውጥም ጎን ለጎን ማስኬድ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስገኘውን ጊዜያዊ መረጋጋት ተጠቅሞ ወደ ትክክለኛ የፖለቲካ መፍትሔ መግባት የመጨረሻው አማራጭ መሆኑን የተናገሩት አቶ ልደቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለዳያስፖራውና በዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ እንዳስረዱት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በቅርቡ የሚነሳ ከሆነ፣ አገሪቱን ሌሎች የጎረቤት አገሮች ወደገቡበት ቀውስ ሊያስገባ ስለሚችል ትኩረት ሰጥቶ ማሰብ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ኢዴፓ ሰባተኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ማካሄድ የነበረበት መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም. ቢሆንም፣ አባላቱን ለመጥራትም ሆነ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ባለመቻሉ፣ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ለስድስት ወራት እንዲራዘም ማድረጉን ገልጿል፡፡

የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴና የጉባዔው አዘጋጅ ኮሚቴ አባል አቶ ግዛቸው አንማው እንዳስረዱት፣ ጠቅላላ ጉባዔውን ማራዘም የተፈለገው ፓርቲውን ወደ አንድ የላቀ የጥንካሬ ደረጃ ለማሸጋገር ነው፡፡

የጉዳዩ ዋና ባለቤት የሆነው ሕዝብ፣ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ያለ ድርጅታዊ አመራር የሚያካሂደው ትግል የትም እንደማያደርሰው ተገንዝቦ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዙሪያ በመሰባሰብና አስፈላጊውን ተሳትፎ በማድረግ፣ የሕዝቡን ትግል በአግባቡ የሚያስተባብርና የሚመራ ጠንካራ ተቃዋሚ ፓርቲ የመፍጠር ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ኃላፊነቱ የመንግሥትም ጭምር መሆኑን አቶ ግዛቸው ጠቁመዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ውስጣዊ ድክመታቸውን በመገምገም፣ ጥራት ባለው ሐሳብና ድርጅታዊ መዋቅር ራሳቸውን በማጠናከርና እርስ በርስ መጠላለፍና መናቆርን ትተው ኅብረትና ውኅደት መፍጠር እንዳለባቸውም አክለዋል፡፡

ፓርቲዎቹ አሁን ባሉበት ደካማ ድርጅታዊ አቅም (ኢዴፓን ጨምሮ) በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ላይ ትርጉም ያለው ተፅዕኖ መፍጠርም ሆነ የሕዝብን ትግል በአግባቡ መምራት እንደማይችሉ የገለጹት አቶ ግዛቸው፣ ለራሳቸው መጠናከር ቅድሚያ በመስጠት ተግተው መሥራት እንዳለባቸውም አስረድተዋል፡፡ አጀንዳው ዕውን እንዲሆን ኢዴፓ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ የተናገሩት አቶ ግዛቸው፣ ‹‹አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የፓርቲው ፕሮግራምና መተዳደርያ ደንብን ከማሻሻል ጀምሮ የፓርቲውን ስያሜ እስከመቀየርና የተናጠል ህልውናውን እስከማክሰም የሚደርስ ዕርምጃ በመውሰድ፣ አንድ ጠንካራ ፓርቲ በአገሪቱ የሚፈጠርበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ዝግጁ ነው፤›› ብለዋል፡፡

አቶ ልደቱ በበኩላቸው ጨምረው እንደተናገሩት የአገሪቱ ምሁራን ዳር ላይ ቆመው ከመታዘብና ከመተቸት ይልቅ፣ በሚያምኑባቸው ፓርቲዎች ዙሪያ ተሰባስበው ትግሉን በዕውቀታቸውና በገንዘባቸው የማጠናከር ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡ ባለሀብቶችም ያለፖለቲካ መረጋጋት ያፈሩት ሀብትና ንብረት ዋስትና እንደሌለውና በአገር ላይ ሠርቶ መኖር እንደማይቻል በመረዳት፣ ሕጋዊና ሰላማዊ ትግሉን በሚችሉት ሁሉ በመርዳትና በማጠናከር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ረግቦ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት የሚሆንበት እውነተኛ የብዙኃን ፓርቲ ሥርዓት አገር ለማድረግ፣ ኢዴፓ ተስፋ እንዳለው አቶ ልደቱ ተናግረዋል፡፡

የአገሪቱ የፖለቲካ ባህል ጽንፈኝነት የተጠናወተው በመሆኑ ከጽንፈኝነት ውጪ አማራጮችን ማየት እንደማይፈልግ የገለጹት አቶ ልደቱ፣ በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ የመጣው በግራና በቀኝ ያለው የፖለቲካ ኃይል ጽንፈኛ በመሆኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ በአንድ ፓርቲ እንደማይፈታ የተናገሩት አቶ ልደቱ፣ በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው አካባቢያዊ ምርጫና ከሦስት ዓመታት በኋላ በሚደረገው አገራዊ ምርጫ፣ ፓርቲዎች ከወዲሁ ጠንክረው በመሥራትና ብቁ ተወዳዳሪ በመሆን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱን ማጠናከር ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የፖለቲካ ምኅዳሩ እጅግ በሚገርም ሁኔታ እየጠበበ መሆኑን ገዥው ፓርቲ ተገንዝቦ ካላስተካከለና ሁኔታዎችን ካላመቻቸ መጪው ጊዜ አስፈሪና ወደማያስፈልግ ሁኔታ ሊያመራ ስለሚችል መንግሥት ሁኔታዎችን በመመርመር፣ በማጥናትና በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮችን አውቆ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር እንዳለበትም አቶ ልደቱ አሳስበዋል፡፡ ለነፃ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ምርጫ አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ ማመቻቸት እንዳለበትም አክለዋል፡፡ ‹‹የችግሩ ፈጣሪ እኔ ነኝ፣ የመፍትሔውም ሰጪ እኔ ነኝ፤›› ማለት ለኢሕአዴግ አያዛልቅም ብለዋል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

 

ርዕዮተ ዓለም የተጫነው ፌደራሊዝማችን [ደረጀ ይመር]

ethnic-federalism-in-ethiopiaየ1987 ሕገ መንግሥት ይዞት ከመጣው ሥር-ነቀል ለውጥ አንዱ በአሃዳዊ አገዛዝ ሥር ስትባትት ለኖረችው ሃገራችን፣ ፀጉረ ልውጥ አስተዳደራዊ መዋቅርን ማስተዋወቅ ነበር፡፡ ይህ ዘርን ማዕከል ያደረገ ፌደራላዊ አወቃቀር /Ethnic federalism/ የታነጸበት ሕገ-መንግስት፣ ከምዕራባውያን ባለ ብዝሃ ባህል ዲሞክራሲያዊ ፌደራሊዝም ይልቅ ለቀድሞው ሶቭየት ኅብረት የሶሻሊስት ሕገ-መንግሥት በእጅጉ የቀረበ ነው፡፡ ለዚህም ዋቢ ማጣቀሻ ይሆን ዘንድ ሕገ-መንግሥቱ በተደላደለባቸው አንጓ ጭብጦች ላይ የትኩረት አቅጣጫን ማሳረፍ በቂ ይሆናል፡፡

ፌደራላዊ አወቃቀር በአንዲት ሉአላዊ ሀገር ላይ ሲዘረጋ፣ ሁለት ተጻራሪ ጽንፎችን ከቁጥር ጥፎ ነው፡፡ አንደኛው የሕዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነትን የበለጠ የተሳለጠ ለማድረግ በሚል እሳቤ /coming together/ ቅቡልነትን የሚያገኝ ሲሆን ሌላኛው ሀገርን ከመበታተን ለማትረፍና የሕዝቦችን የእርስ በእርስ ትስስር በአዲስ አተያይ ለመቀየድ ታሳቢ ተደርጎ የሚተገበር /holding together/ ፌደራላዊ አወቃቀር ነው፡፡ ቀዳሚው ለምዕራባውያን፣ የኋለኛው ደግሞ የሀገራችንን ፌደራላዊ አወቃቀር በግብር እንደሚመስል በዘርፉ የተሰማሩ ልሂቃን ያስረዳሉ፡፡
የፌደራል ስርዓቱ መሬት ወርዶ በተግባር ላይ ከዋለበት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ብሥራትም ሆነ ፈተናን ይዞ መምጣቱ አልቀረም፡፡ በታሪክ ሂደት ውስጥ ማንነታቸው በፈጠረባቸው ልዩነት የተነሳ ወደ ዳር ተገፍተው የኖሩ ሕዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት የቋንቋ ነፃነት/lingustic Autonomy/ ማጎናጸፉ እንደ ብሥራት የሚቆጠር ቢሆንም፣ ከዚሁ ጎን ለጎን ፌደራላዊ አወቃቀሩ ላይ ታሳቢ መደረግ የሚገባቸው ነባራዊ ኹነቶች ቸል በመባላቸው የተነሳ ህልውናችንን አደጋ ላይ ከሚጥሉ ተግዳሮቶች ጋር ፊት ለፊት እየተላተምን እንገኛለን፡፡
በፌደራላዊው ሥርዓት ዝርጋታ ወቅት መልከአ ምድራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስነልቦናዊ ዝምድናዎች ፊት ተነስተው ቋንቋ  ብቻ ነው እንደ ዋንኛ አማራጭ የተወሰደው፡፡ በእዚህም የተነሳ  በሀገራዊ ብሔርተኝነት ኪሳራ ክልላዊ ማንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎመራ ሊሄድ ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራሊዝም መለያ ጠባዮች
አወዛጋቢው የብሔር ብሔረሰብ ጉዳይ
በስታሊን አፍላቂነት ለፍሬ በቅቶ የነበረው የቀድሞ ሶቪየት ኅብረት ሕገ-መንግሥት የታነጸበት ስነልቦናዊ ቅኝት የእኛው ሕገ-መንግሥት ተጋርቶታል ከሚያስብለው አንዱ የብሔር ብሔረሰቦችን የአርስ በእርስ ግንኙት የሚመረምርበት የታሪክ መነጽር በአንድነት መግጠሙ ነው፡፡ ሕገ-መንግስታችን እንደ ስታሊኑ የሶቪዬት ኅብረት ሕገ-መንግስት የሚንደረደርበት ታሪካዊ ዳራ ሀገራችን ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት እንደነበረች በማብሰር ነው፡፡ ይህም መንደርደሪያ ሉዓላዊ ስልጣንን ለብሔረሰቦች ጠቅልሎ  በማሸከም ይደመደማል፡፡ አንቀጽ ስምንት፣ ንኡስ አንቀጽ አንድ ላይ፣ ይህንን ስልጣን በግልጽ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡-
“የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች  የኢትዮጵያ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው፡፡”
ከግል መብት ይልቅ ለቡድን መብት የይለፍ ፍቃድ የሚሰጡ አንቀጾች በሕገ-መንግስቱ ውስጥ መመልከት ብርቅ አይደለም፡፡ የቡድን መብት በግል መብት መቃብር ላይ አበባ ያኖራል፡፡ “እንኳን የበቀልኩበት ዘር ጦቢያም ትጠበኛለች” ለሚል ተሟጓች ዜጋ፣ ሕገ-መንግስቱ ፊት አይሰጥም፡፡ ከእዚህም በተጨማሪ በሜትሮፖሊቲያን ከተሞች ውስጥ ለሚኖሩ ሁለትና ሶስት ብሔር ላላቸው ዜጎች የሚተወው ኩርማን ሥፍራ ማግኘት የሚታሰብ አይሆንም፡፡ የብሔር ማንነት ከሁሉም ማንነት ልቆ ሕገ-መንግሥቱን ተዋርሶታል፡፡
ለመሆኑ ብሔር ማለት ምን ማለት ነው?
በሀገራችን የብሔረሰብ ነፃነት ጥያቄ ገዥ ሆኖ ብቅ ያለው በ 1960ዎች የተማሪዎች እንቅስቃሴ እንደነበር ከታሪክ ድርሳናት እንረዳለን፡፡ የተማሪዎች እንቅስቃሴ የፈጠረው መነቃቃት ብረት አንስተው ወደሚታገሉ ሽምቅ ተዋጊዎች ተጋብቶ፣ በሒደት አጠቃላይ ፖለቲካዊ ቁመናቸው በእዚሁ ረግረግ ውስጥ ተውጦ ሊቀር ችሏል፡፡ ገዢውን የፖለቲካ ፓርቲ ጨምሮ በተቃዋሚነት የሚሰለፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀድመው የሚያነሱት አጀንዳ ከብሔር ማንነት ጋር የተቆራኙ ርዕሰ ጉዳዮችን እንደሆነ ከአደባባይ የተሰወረ ሀቅ አይደለም፡፡
ብሔርን የማርክሲዝም ሌኒንዝም መዝገበ ቃላት በእንዲህ መልኩ ነው የሚያብራራው፡
በታሪክ ሂደት ውስጥ የተከሰተ የሰዎች ማኅበረሰብ ነው፡፡ አንድ ብሔር በመጀመሪያ ደረጃ የሚለየው ባሉት የወል ቁሳዊ የኑሮ ሁኔታዎች ነው፡፡ በአንድ መልክ አምድራዊ ክልል ውስጥ መኖር፣ በኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶች መተሳሰር፣ በአንድ ቋንቋ መጠቀም፣ በጋራ ታሪካዊ ሒደት ውስጥ የወል ሥነ-ልቦናዊ ገጽታዎችና ባህላዊ አመለካከቶች መከሰት የብሔር መሠረቶች ናቸው፡፡
በአሁኗ ኢትዮጵያ በአንድ ክልል ውስጥ የተሰባሰቡትን ሕዝቦች በታሪክ፣ በስነ-ልቦና፣ በመልከአ ምድራዊ ኩታ-ገጠምነትና በኢኮኖሚያዊ ትስስር መለኪያ ከገመገምናቸው ከላይ ከሰፈረው የብሔር መለኪያ ምንአልባትም አንዱን ብቻ ነው ሊያሟሉልን የሚችሉት፡፡ ለአብነት ያህል በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪነቱ፣ በአማራ ክልል ሥር የተቀነበበው ሕዝብን እንመልከት፡- ታሪክ እንደሚነግረን ከሆነ የሸዋ አማራ ከወሎ አማራ ወይም ከጎንደር አማራ  ይልቅ ከሸዋ ኦሮሞ ጋር የተሳሰረ ስነ-ልቦና ነበረው፡፡ አጤ ምኒሊክ ሀገር ለማቅናት ወደ ደቡብ ሲዘምቱ፣ የጎንደርና የወሎ ባላባቶች አጤው እንደወጡ እንዲቀሩ የሚመኙትን ያህል፣ ሀገር በማቅናቱ ሂደት ላይ ከአጤው ጎን በመሰለፍ ግምባር ቀደም ተሳታፊዎቹ የሸዋ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡
የሸዋ አማራና የሸዋ ኦሮሞ በስነ-ልቦና፣ በታሪክ፣ በመልክአ ምድራዊ ኩታ-ገጠምነትና በኢኮኖሚዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ሲመዘኑ እጅግ የተዋሀዱ ሕዝቦች ናቸው፡፡ የሸዋ አማርኛ ተናጋሪ ከጎንደር አማርኛ ተናጋሪ ጋር በአንድ ክልል ውስጥ ሊካተት የቻለው ከመለኪያዎቹ መካከል በቋንቋ ማንነት ብቻ ነው፡፡ የቋንቋ ማንነት ደግሞ መገለጫው ዘውግ /ethnicity/ አንጂ ብሔር እንዳልሆነ የስነ-ማኅበረሰብና ፖለቲካ ልሂቃን ያብራራሉ፡፡
አብዮታዊ ዲሞክራሲ
የሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም የእኛ የእትዮጵያዊያን መገለጫ ከሆነ ግማሽ ክፍል ዘመን ደፈነ፡፡ ከ1960 መባቻ እስከ ቆምንበት ዘመን የርዕዮተ ዓለሙ ተጽእኖው በተለያየ ቅርጽ ሲደባብሰን ኖሯል። አምባገነናዊው የደርግ አገዛዝ አፈር ከለበሰበት 1983 ዓም አንስቶ የርዕዮተ ዓለሙ ቅርጽና ይዘት መልኩን እየቀያየረ፣ የፖለቲካ አገዛዙን እንደተጣባው ቀጥሏል። ለእዚህም ማሳያ  አንዱ ገዢው ፓርቲ የሚመራበት  ከማርክሲዝም ሌኒንዝም የተዋሰው አብዮታዊ ዲሞክራሲ መርህ ዋቢ ምስክር ይሆናል፡፡
አብዮታዊ ዲሞክራሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ሕዝብ የተበሰረው በ1917 በራሺያ ቦልሺቪክ አብዮት ወቅት  ኢቪስቲያ በሚባል ተነባቢ ጋዜጣ  ላይ ነበር። ይህ ርዕዮተ ዓለማዊ ቅኝት ከካፒታሊዝም ወደ እውነተኛ ሶሻሊዝማዊ ስርዓት ለመሸጋገር በእነ ሌኒን አታጋይ ፓርቲ /ቫንጋርድ ፓርቲ/ አማካኝነት እንደ ብቸኛ አማራጭ የተወሰደ  መርህ ነበር። ርዕዮተ ዓለማዊው ቅኝቱ፣ ከ1983 መንግሥት ለውጥ በኋላ በሀገራችን ፖለቲካዊ ምህዳር ላይ የፊት አውራሪነት ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
ከ1983 የመንግሥት ለውጥ ማግስት ዋንኛ ጥያቄ ሆኖ ብቅ ያለው፣ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ምን አይነት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይመጥናታል የሚል አጀንዳ ነበር፡፡ ከ 80% በላይ በግብርና በሚተዳደር ሕዝብ ላይ የምዕራባውያንን የሊብራል ዲሞክራሲ የሚሸከም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ንጣፍ ማግኘት የሚታሰብ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። ስለዚህ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ያካተተ፣ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲ ይዘርጋ የሚል ውይይት  ለሥርዓቱ ቅርበት ካላቸው ምሁራን ጋር ይደረግ ጀመረ፡፡
ይህም ውይይት ውሎ አድሮ በሶስተኛው ሞገድ /ሰርድ ዌቭ/ መጽሐፍ የሚታወቁት ጉምቱ ልሂቅ ፕሮፌሰር ሀንቲንገተን አማካሪነት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ከኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊተከል ችሏል። የኢትዮጵያ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ከራሽያው አብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚለይበት ዋንኛ ጠባይ አንዱ መድብለ ፓርቲን በሕገ-መንግሥት ላይ በይፋ መፍቀዱ ነው፡፡ ይህ አይነት አንቀጽ በቀድሞ ሶቪየት ኅብረት ሕገ-መንግሥት ላይ አልተካተተም ፡፡
የአብዮታዊ ዲሞክራሲው ዋንኛ አስኳል መርህ የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ነው። በመርሁ መሠረት የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት የሚያወጣው ማንኛውም ውሳኔ እስከ ታች ቀበሌ አመራር ድረስ ተፈጻሚ ሊሆን ይገባል። እዚህ ጋ ነው የክልሎች ሥልጣንና የፓርቲ ስልጣን መደበላለቅ የሚመጣው።
ሕገ-መንግሥቱ የሰጣቸውን ሥልጣን ለሚሻማ ፖለቲካዊ አሰራር ተገዢ እንዲሆኑ የዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህ ግድ ይላል። በእዚህም ምክንያት የፓርቲ ርዕዮት ዓለምና ሕገ-መንግሥታዊ አሠራር የሚለይበት ቀጭን ድንበር ውሉ እየጠፋ፣ የክልሎችን ራስን በራስ የማስተዳደር ሥልጣን ከፈተና ላይ ሲጥለው በተለያዩ አጋጣሚዎች ይስተዋላል፡፡
የፌደሬሽን ምክር ቤት ሚና
የ1987 ሕገ መንግሥት የወለዳቸው የተወካዮች  እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች ሕግ የማውጣት ሥልጣን ለየቅል ነው፡፡ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት፣ የሕግ አውጪነት ሥልጣንን በበላይነት ጠቅልሎ የያዘው የተወካዮች ምክር ቤት ብቻ ሲሆን የፌደሬሽን ምክር ቤት በሕግ አውጪነት ሥራ ውስጥ የሚሳተፍበት አሠራር የለም፡፡ ይህ አሰራር ፌደራላዊ ሥርዓትን በሚከተሉ ምዕራባውያን ሀገራት ላይ ልዩ ገጽታ ነው ያለው፡፡ ለአብነት ያህል የአሜሪካን ሕገ-መንግሥት ብንወስድ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤቱ /ሴኔቱ/ ከተወካዮች ምክር ቤት/ኮንግረስ/ ጋር በሕግ አውጪነት ረገድ ያለው ሚና እኩል ነው።  የፕሬዝዳንቱን ቪቶ ፓወር/ውሳኔን የማጠፍ ስልጣን/ እንዳይጠቀም ሁለቱም ምክር ቤቶች ከ 2/3 ድምጽ በላይ ወስነው ካሳለፉት ፕሬዝዳንቱ ውሳኔውን የመሻር ስልጣኑ ያከትማል። ስለዚህ ሴኔቱ የአግድሞሽ የቁጥጥር ሥልጣን/checks and balance/ ላይ ያለው ተሳትፎ ልክ እንደ ኮንግረሱ መሳ ለመሳ በሆነ ረድፍ ነው የሚቀመጠው፡፡
የእኛ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ግን ሕገ-መንግስትን ከመተርጎምና በክልሎች መካከል የሚፈጠር ግጭትን ከመፍታት በዘለለ ልክ እንደ አሜሪካው ሴኔት የቁጥጥር  ሥልጣን ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አይችልም፡፡ አንቀጽ 48 እንዲህ ይላል፡-
The constitution provides that where the concerned states fail to reach an agreement on border related issues, the House of Federations shall decide such disputess on the basis of settlement patterns and the wishes of the peoples concerned
በአጠቃላይ ፌደራላዊው ሥርዓት በመርህ ደረጃ ሊከልሳቸው የሚገቡ በርካታ ኹነቶች እንዳሉት እሙን ነው፡፡ በተለይ የርእዮተ ዓለምን ጣልቃ ገብነት የሚሸብቡ አንቀጾችን በሕገ-መንግስቱ ላይ በሪፈረንደም ወይም ከዜሮ ድምር የፖለቲካ ስሌት ነጻ በሆነ ውይይት አማካኝነት በማካተት፣ ራስን በራስ የማስተዳደሩ ሥልጣን የበለጠ ጥርስ እንዲኖረው ማድረግ ከገዢው ሥርዓት የሚጠበቅ ቁርጠኝነት ይሆናል፡፡

ምንጭ   _   አዲስ አድማስ

የዐማራ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የቤት ሥራ!

ከሙሉቀን ተስፋው

በየቀኑ በርካታ መልዕክቶችን ከተለያዩ ሰዎች እቀበላለሁ፤ በቅርብ የደረሱኝን ሁለት መልዕክቶች ግን መቼም የምረሳቸው አይመስለኝም፡፡ የዐማራ ሕዝብ ነጻነቱን እስኪጎናጸፍ አርፌ እንዳልቀመጥ ያስገድዱኛል፡፡ የዐማራን ሕዝብ ትግል በምችለው አቅም ሁልጊዜም እንድደግፍ የምጠቀምበት ዘዴ የተለያየ ነው፡፡

debremarkos-university-satenaw-news

ለምሳሌ አንደኛውን ልንገራችሁ፤ በ2008 ዓ.ም. በዓመያ የዐማሮች አገር እንዳለ ወድሞ በዐይኔ በብሌኑ ያየሁት ዕለት የተሰማኝ ስሜት እስከመቃብር አብሮኝ እንደሚዘልቅ ጥርጥር የለውም፡፡ ቤቶችና የእህል ማስቀመጫ ጎተራዎች በእሳት ወድመው ቦሎቄው ተደፍቶ አየሁት፡፡ ከተደፋው ቦሎቄ ዘገንኩና በቦርሳየ ውስጥ ከተትኩት፡፡ ያን ቦሎቄ ከልብስ ሻንጣየ ጋር አደረግኩት፡፡ የትም አገር ስሄድ ከልብሴ በስር ከዓመያ ያመጣሁት ቦሎቄ አለ፡፡ አውሮፓ ያላችሁ ሰዎች ብትጠይቁኝ በማንኛውም ሰዐት ያን ቦሎቄ አሳያችኋለሁ፡፡ ሁልጊዜ ልብስ ስለብስ ሻንጣየን ስከፍት ያን ቦሎቄ አገኛለሁ፤ ወዲያውኑ እነኚያ ሀብት ንብረታቸው የወደመባቸው የዓመያ ዐማሮች ከፊቴ ላይ ይሳላሉ፡፡ ስለዚህ የዓመያ ዐማሮችን ሁናቴ ልርሳ ብል እንኳ አልችልም፤ ያለኝ አማራጭ የዐማራ ሕዝብ ስቃይ የማያስደስታት አገር እስክትገነባ በምችለው ሁሉ ተግቼ መታገል ነው፡፡

ወደ ቀደመው ነገር ልመልሳችሁ፡፡ አንዲት ልጅ ከሳውድ አረቢያ ደወለችልኝ፡፡ ከማውራቷ በፊት ታለቅሳች፡፡ አታውቀኝ አላውቃት፤ እንዳላረጋጋት የምታለቅስበትን ጉዳይ ማወቅ አልቻልኩም፡፡ እንደምንም በእንባ እየተናነቀች ‹‹ዐማራ ግን ምንድን ነው ወንጀሉ? ለምንድን ነው እንዲህ በየቦታው እንድንገደል የተፈረደው? ዕውነት ፈጣሪ አለ?›› ከምትናገረው ይልቅ ልቅሦዋ የበለጠ ልብ ይሰብራል፡፡ የማደርገው ነገር ቢኖር ማድመጥ ብቻ ነበር፡፡

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ አንድ ጦማር ደረሰኝ፤ መልዕክቱ ባጭሩ ‹‹ተመራቂ ተማሪ ነኝ፡፡ በነሐሴ በነበረው የዐማራ ተጋድሎ ከፊቴ ብዙ እንቡጥ ሕጻናት ሲቀጠፉ አይቻለሁ፤ ጓደኞቼ እና አብሮ አደጎቼ ተገድለውብኛል፤ በዚህ ዓመት የሚመረቁ የዲፓርትመንት ጓደኞቼ በወያኔ ጥይት ተገድለው ከእኔ ጋር ክፍል አልገቡም፡፡ የኔ ቤተሰቦች በወታደር ተከበው በየቀኑ በመታገል ላይ ናቸው፤ በርካታ ወጣቶች በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው፡፡ መመረቄን የሚጠብቁ ድሃ ቤተሰቦች እንዳሉኝ አውቃለሁ፤ ግን የታሠሩ፣ የተገደሉና እየተሰቃዩ ያሉ ወንድሞቼን ሳስብ የመማር ፍላጎቴ ተዘጋ፤ ምን እንደማደርግ ብቻ ነው ቀንና ሌሊት የማስበው…›› የሚል ነው፡፡

 

የዚህ ወንድማችን ጥያቄ የሁሉም የዐማራ ተማሪዎች ጥያቄ ነው፡፡ የዐማራ ተማሪዎች ጥያቄ እንደ 66ቱ ‹‹መሬት ላራሹ›› የሚል እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ በሕግ፣ በፖለቲካል ሳይንስ፣ በአስተዳደርና በመሳሰሉት ትምህርቶች ‹‹ሁሉም ሰዎች ከሕግ ፊት እኩል ናቸው›› እያለ መምህሩ ሲያስተምር ‹‹ዐማራው ግን በትግሬ መረገጡን›› አይታችኋል፡፡ በሕይወት መኖር የተፈጥሮ መብት መሆኑን ለሚነግራችሁ መምህር ‹‹በአጋዚ ወታደር የተገደለውን ወንድምህን ሕልሟ በአጪር ስለተቀጨችው እህትህ›› ማሰብ አለብህ፤ ቡሬ በአንድ የትግሬ ሆቴል ውስጥ አስከሬናቸው ተጠራቅሞ ስለተገኙት ወጣቶች፣ በድፍን ጎንደርና ጎጃም የአጋዚ ጥይት ግንባራቸውን የተባሉ ዐማሮች በዐይነ ኅሊናህ ይምጣ፡፡ ‹‹ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማንም ሰው አይታሰርም›› ሲልህ እናቷን መቅበር ያልተፈቀደላት ልጇን የትም የጣሉባትን ቀለብ ስዩም፣ ስለእነ ንግሥት ይርጋ፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ አታላይ ዛፌ፣ ጌታቸው አደመ፣ አንዷለም አራጌ፣ አንገው ሰጠኝ፣ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጌታቸው ሽፈራው… በብር ሸለቆ ስለታጎሩት የዐማራ ወጣቶች አስብ፡፡ ስለ ሰብዐዊ መብትህ ሲነገርህ ዲሑማናይዝ የሆነውን አባትህን አስታውስ፡፡ በበርሃ እየተዋደቁ ያሉት ወንድሞቻችን ለምን እንደሆነ ሊገባን ይገባል፡፡

ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት አለ ሲሉህ ከመቶ ሺህ በላይ በየአገሩ የተፈናቀሉ ዐማሮችን ጉዳይ አንሳ፡፡ ማንነት የሚወሰነው በራስ መሆኑን በቀቀኑ መምህር ሲያነብ በወልቃይትና በራያ ‹‹ትግሬነት በግዴታ የተለጠፈባቸውን›› ዐማሮች ሥቃይ ትዝ ይበልህ፡፡

ስለፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ስትነገር በሕወሓት የተሸጠችው አገርህን እስብ፡፡ ያኔ ዐማራነት ያለበትን ትክክለኛ ምስል ታያለህ፡፡ የእኔ የቤት ሥራ ምንድን ነው? ብለህ ራስህን ጠይቅ፡፡ ያኔ መማር ለዐማራ ወጣቶች ምንም እንደማይፈይድ ትገነዘባለች፡፡

ባለፈው ዓመት የተመረቁ የዐማራ ወጣቶች የትኛው ፋብሪካ ተቀጠሩ? ሰንቶች ሥራ ያዙ? ትምህርት ቤት የተመረቁ ዐማሮች ምንድን ነው ተስፋቸው? የትኛው የሥራ እድል ተመቻችቷል? ስንቶች ዩንቨርሲቲ ተመርቀው በአርብ አገር የማዕድ ቤት ሠራተኛና የግመል ጠበቂ ሆኑ? ስንቶቹ ሲሰደዱ በግብጽና በሊቪያ በርሃዎች ቀሩ? ስንቶቹ በሜድትራኒያንና ቀይ ባሕሮች የዓሣ ነባሪ ቀለቭ ሆኑ? ስንቶች ዐማራ በመሆናቸው ምክንያት በወያኔ ተገደሉ? የዐማራ ሕዝብ ስቃይ ምን ያክል ነው? መጨረሻውስ መቼ ነው? ይህን ይስቃይ ማን ያስወግደዋል?
እነዚህ ጥያቄዎች ደጋግመን ማሰብ አለብን፤ የቤት ሥራችን ይህ ነው፡፡ በወረቀት የሚሠራ አይደለም፡፡ በብዕር ሳይሆን በደም የሚጻፍ ነው የእኛ የቤት ሥራ፡፡ ጀግና ይወለዳል፤ ጀግና ይፈጠራል፡፡ የዐማራን ሕዝብ ነጻነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማረጋገጥ የዚህ ትውልድ የቤት ሥራ ነው፡፡ ሁሉም የዐማራ ወጣት፣ በዩንቨርሲቲም በኮሌጅም፣ በመሰናዶም፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ያሉ ተማሪዎች የቤት ሥራ ይህ ነው፡፡ የቤት ሥራ በአንድ ሳምንት አያልቅም፡፡ የጊዜው እርዝመት በትውልዱ ቁርጠኛነት ይወሰናል፡፡ 42 ኪሎ ሜትርን የፈጠነ በ2፡00 ሲጨርሰው የዘገየ ደግሞ ሳምንት ሊፈጅነት ይችላል፡፡ እጣ ፈንታችን በጠላቶቻችን የሚወሰንና እነሱ ሲፈልጉ የሚያስሩን፣ ሲፈልጉ የሚገድሉን፣ ሲፈልጉ የሚያሳድዱንና በሉ ያሉንን የሚያናግሩን ከሆነ እንዳለን አንቆጠርም፡፡ አሁን ያለንበት ሁኔታ ይህ ነው፡፡ ከዚህ የሰው በታች (ዲሂውማናይዚንግ) ከሚያደርግ አስከፊ ሕይወት ነጻ መውጣት አለብን፤ ሌላ ምርጫ የለንም፡፡

የእኛ አባቶች ማንን ወለዱ? እሳት እሳትን ወይም አመድን ይወልዳል፡፡ እኛስ? የእሳት ልጅ እሳት ወይስ አመድ? የዐማራ ነበልባል ወጣት እንደብረት ቀልጦም የሚጠነክር ወይስ እንደ እንጨት ነዶ የሚያምድ? የቤት ሥራ ነው፡፡ በግል ከተሠራ ሁሉም ተማሪ እኩል ማርክ አያገኝም፡፡ እኩል ማርክ የምናገኘው በቡድን የቤት ሥራውን ስንሠራ ብቻ ነው፡፡ የቤት ሥራው የቡድን ነው፡፡ ቡድኑ ደግሞ ለሁለት ወይም ለሦስት ሰዎች አይደለም፤ 40 ሚሊዮኑ የዐማራ ሕዝብ የጋራ የቤት ሥራ ነው፡፡

ማለዳ ወግ …በአረብ ሀገራት ያሉ ኢንባሲና ቆንስሎች ድክመት ! [ነቢዩ ሲራክ]

* የጎዳን የመብት አስከባሪ ማጣት እንጅ አረቦች ከፍተው አይደለም
*  አረብ አሰሪዎች ግፍ ፈጽመው የህግ የበላይ አይሆኑም
* ሶስት አመት ያለ ደመወዝ አሰሯት፣የመብት አስከባሪ ተገኘና ተከፈላትNebiyu-Sirakይህች የምትመለከቷት እህት ከሶስት አመት በፊት ያኔ ” ህጋዊ” በተባለው የኮንትራት ሰራተኞች ወደ ሳውዲ ከጡት እድሜያቸው ለስራ ካልደረሱት መካከል አንዷ ናት ። ለስራ በተሰማራችበት የምስራቅ ሳውዲ አንድ ትንሽ መንደር ከሳውዲ አሰሪዎቿ ጋር ለሶስት አመታት ከሰራች በኋላ አሰሪዎቿ ደመዎዝ ሳይሰጡ ወደ ሀገር ለመላክ ወደ ጊዜያዊ መጠለያ እስር ቤት ያስገቧታል ። ደማም ውስጥ ባረፈችበት ማቆያ እስር ቤት በተመሳሳይ ሁኔታ በኮንትራት መጥተው ወደ ሀገር ለመግባት የቆረጡ እህቶችን ታገኝና እያነባች የደረሰባትን ድካምና ለአመታት የሰራችበትን ደመወዝዋን አለመቀበሏን ላገኘቻቸው ሀበሻ እሀቶቿ ታጫውታቸዋለች ። ይህን አሳዛኝ ታሪኳን የሰሙት እህቶች መረጃውን ተቀባብለው “በዜጎች ጉዳይ ያገባኛል ” ለሚሉ ወገኖች የደረሰባትን በደል ያደርሱታል …

መረጃው በምስራቅ ሳውዲ በደመማም ለሚገኘው አዲስ ተቋቋሚ የኮሚኒቲ አባላት ደርሶ ክትትሉ ተጀመረ ። ብርቱዎቹ አዳዲስ ተመራጭ የኮሚኒቲ አመራሮች ጉዳዩን ይዘው ወደ ሳውዲ መንግስት በማቅረባቸ ው አሰሪው በፖሊስ ተጠርቶ ያልተከፈላትን ደመዟን ሙሉ በሙሉ እንድ ትረከብ ተደረገ …እነሆ በልጅነት ጉልበቷ በላቧ የሰራችው ገንዘቧን  ተቀብላለች ፣ የለፋችበት የሶስት አመት ደመወዝ ገንዘቧን መረከቧልን እነሆ በደስታ እየተፍለቀለቀች ትናገራለች   ! …ደስ ሲል  🙂

አዎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እህቶች በተመሳሳይ ሁኔታ የሰሩበትን ደመወዛቸውን መነጠቁ ሳያንስ ግፍ እየተፈጸመባቸው ተሸፋፍኖ ወደ ሀገር ለመሸኘታቸው ምስክሮች አለን  !  ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት የሳውዲ አሰሪዎች ከህግ በላይ ሆነው ፣ ለዝርፊያ ህጉ የሚፈቅድላ ቸው ሆኖ ሳይሆን የዜጎችን ጉዳት ወደ ሚመለከተው የሳውዲ አካላት አድርሶ መብታቸውን የሚያስከብርልን የመንግስትና የማህበረሰብ ተወካይ በማጣታችን ብቻ ነው  ! ይህን የምለው እንደ እድል ሆኖ ጉዳያቸው ተይዞና ክትትል ተደርጎላቸው የለፉ የደከሙበትን ፣ የተጎዱ የተበደሉበትን ጉዳይ ፍትህ አግኝተው የጉልበት ፣ የላብ ድካም ውጤት ደመወዝና የበደላቸውን ዋጋ ተከፍሏቸው ወደ ሀገር የተሸኙትን ጥቂቶች አውቃለሁና ነው  !

የመብት ጥበቃ ጉድለት በሁሉም አረብ ሀገራት በሚባል ደረጃ ይስተዋላል። ጉዳዩ በአብዛኛው የመብት ረገጣ በመሆኑ ተመሳሳይ ነው።  ከግማሽ ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች ” በኮንትራት ስራ” ስም በተሰደዱባት ሳውዲ አረቢያ ከሌሎች ሀገራት የበለጠና የከፋ መጠነ ሰፊ ችግር መኖሩ ደግሞ እውነት ነው ። ችግሩን በሳውዲና በቀሩት አረብ ሀገራት ያሉ ኢንባሲና ቆንሰላ መ/ቤቶች አብጠርጥረው ያውቁታል ። ዳሩ ግን እየሰሩ ያለው መሆን ያለበትንና የሚጠበቀውን ያህል አይደለም ፣ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ የሚሞግተኝ ካለ ከጥላቻ ለጸዳው ውይይት ሁሌም ዝግጁ ነኝ  ! መረጃ ማስረጃ እያቀረብን መነጋገር እንችላለን  …

ወደ መብት ማስጠበቁ መክሸፍ ስናመራ በእርግጥ ለክሽፈቱ አስተዋጽኦ ወደ ሳውዲም ሆነ ወደ ቀሩት ሀገራት የሚላኩት ዲፕሎ ማቶች ዲፕሎማሲያዊ ልምድ አለያም ጉዳይን የማስፈጸምና የመም ራት አቅሙ ያላቸው አለመሆኑ እንደሆነ በርካታ ማሳያዎችን ማሳዬት ይቸላል ።  ሌላው ሁሉ ቀርቶ እነሱ አቅምና ባጀቱ  ቢያንሳቸው በመብት ማስከበሩ ክሽፈት የተጎዳው ፣  በሚሰራው ልቡ የሚደማውን ዜጋ ማስ ተባበር ቢችሉ ነዋሪው ገንዘብ አዋጥቶ ጠበቃ እስከመቅጠር ቀናኢነት ለመሆኑ ከጥያቄ አይገባም ። ከነዋሪው ባለፈ ሰፋ ባለና በተደራጀ መን ገድ ችግሩን ለመቅረፍ  በየሀገሩ ያሉትን ኮሚኒቲ ማህበራት በማደራጀ ትና በማቀናጀት ጠቃሚ ስራ መስራት ይችሉ ነበር ። እያወቁ አጥፊዎ ች ናቸውና ይህን ግን አያደትጉትም ።

ከተባበሩት ኢምሬት እስከ ኩዌት ፣ ከኳታር እስከ ባህሬን ከሳውዲና ሊባኖስ ኢንባሲና ቆንስሎች የሚከተሉት የፖለቲካ ድርጅትን በውስጠ ታዋቂነት ያማከለ አዲስ የኮሚኒቲ አወቃቀር ደግሞ እንደ መፍትሔ ቢጀመርም ወደ ለየለት አዘቀት ከመወርወር አላዳነንም ።  ነባርና መጠነኛ እርዳታ ያደርጉ የነበሩ ማህበራትን በማፈራረስ በአዲስ መልክ የሚመሰርቷቸው ማህበራት ለነዋሪው የሚፈይዱት ነገር የለም ። የማህበራቱ አደረጃጀት ለሰብአዊ እርዳታ ሳይሆን ለፖለቲካ ፍጆታ እና ለገንዘብ መሰብሰቢያ በመሆኑ ሰው ወደ ተቋማቱ መቅረብ አይሻም ፣ በዚህ ምክንያት ከድጡ ወደ ማጡ እያደርን ለመዘፈቃችን ሁነኛ ምክንያት ነው  !

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በሚኖሩበት በዋና ከተማዋ ሪያድ ኢንባሲው በፈለገው መንገድ ማደራጀት ያልቻለው ኮሚኒቲ  ከፈራረሰና ድብዛው ከጠፋ አመታት ተቆጥሯል። በጅዳም ኮሚኒቲው በተፈለገው ድርጅት ቀመስ አወቃቀር በጣም ጥቂት ነጻ የተባሉ ተመራጮች ቢገ ቡበትም ድምጽ የላቸውምና ኮሚኒቱው የሚተነፍሰው በቆንስሉ ፖለቲ ከኞችና በተሰገሰጉት የድርጅት ጉዳይ ፈጻሚዎች ሳንባ ሆኗል ። ኮሚኒ ቲው ከቆንስሉ መሳ ለመሳ የዜጎችን መብት ማስከበሩ ቀርቶ ከ3000 በላይ ታዳጊዎች የሚማሩበት በሀገር ወዳድ ዜጎች የተመሰረተው የትምህርት ማዕከል እያደር አደጋ የሚሰማበት  ተስፋ አስቆራጭ ማዕከል ሆኖብናል ።  ወደ ኩዌት ብንዘልቅ የምናገኘው እውነት ተመሳሳይ ነው  ! ኢንባሲው ኮሚኒቲውን አደራጅቶ የዜጎችን መብት ለማስከበር ተስኖት ዜጎች ለመብት ረገጣ ተጋልጠዋል   🙁

ከሁሉም የሚያሳዝነው በተጠቀሱት ሀገራት የሚገኙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ” የዜጎች መብት ይከበር ፣ ለተገፋው ዜጋ ዋስ ጠበቃ ሁኑለት! ” ብለን ስንጠይቅ እንደ ተቃዋሚ ያዩናል ። የተበዳይ ዜጎችን ሮሮ ስናሰማ ” ድብቅ አላማ አላቸው!” እያሉ የዜጎችን ድምጽ ለማፈን ያሻቸውን ተቃዋሚ ስም እየለጠፉ  ያሸማቅቁናል ። ይህ ግን መፍትሔ አይደለምና ችግሩ እያደር ተባብሷል  ! የአረብ ሀገራት ያሉ ኢንባሲና ቆንስሎች ድክመት መጠነ ሰፊ ነው ፣ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትና ማዕከላዊው መንግስት ምድር ላይ ያለ እውነቱን አምኖ በመቀበል  ማሻሻል አልቻለም!  የሳውዲም ሆነ የአረብ ሀገር ስደተኞችን የጎዳን  የመብት አስከባሪ ማጣት እንጅ የአረቦች ከፍተው አይደለም ፣ አረቦች ግፍ ፈጽመው ለህግ የበላይ ሆነው አይደለም ፣ ድክመቱ የእኛ ተቆርቋ ሪና መብት አስከባሪ ማጣት ነው ፣ ደረቅ እውነቱ ይህ ነው  !

በየትኛውም የአረብ ሀገር የመብት አስከባሪ ማጣት እንጅ የጎዳን አረቦች ከፍተው ፣ ግፍ ፈጽመው ለህግ የበላይ ሆነው አይደለም  ለሚለው የምታዩት የተገፊዋ እህት የተቀማችውን የአመታት ደመወዝ መቀበሏ እንደ ትኩስ ማስረጃ ውሰዱት  ። ይህ ቅንጫቢ መረጃ በምስራቅ ሳውዲ በደማም ከሳምንታት በፊት የሆነ ነው ፣ ለስኬት የበቃውም በዜጎች ጠቋሚነትና በኮሚኒቲ መብት ማስከበር ትጋት የታከለበት ክትትል ነበር፣ እናም ይህች አንድ ፍሬ እህት የሰራችበትን ደመወዝ መቀበሏ ለአባባሌ ሁነኛ ምስክር ነው  ! በዚህ አጋጣሚ ጉዳዩን ተከታትለው ጥቆማውን ላቀረቡት ወገኖችና ላስፈጸሙ ለደማ ም ኮሚኒቲ አመራሮች የላቀ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ  !

ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 17 ቀን 2009 ዓም

የህልውና ልዕልና በእንቢተኝነት ልቅና የሥህናዊ – ታሪክ ገናና [ሥርጉተ ሥላሴ]

„ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም።“

( ወደ ቆረንቶስ ፩ኛቱ ምዕራፍ ፲ ከቁጥር  ፳፫ እስከ ፳፬)

ከሥርጉተ ሥላሴ  26.11.2016  (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

sirgute
ከሥርጉተ ሥላሴ

ስታቀርበው ያቀርብኃል። ስታርቀው ያርቅኃል። ስታከብረው ያከብርኃል። ስታቃለው – ይነፍግኃል። መርህ ኑሮን ሲያስተዳድር፤ መኖርን ልብን  ይመራል። ህሊናን ደግሞ ሚዛን። ጤነኛ መንፈስን ደግሞ የመኖር ሉዑል – ፍቅራዊነት። በመኖር ውስጥ ሰብዕናን ማክበር የመሰለ ምራቁን የዋጠ የርትህ አመክንዮ የለም።

ጠራጠሮ

ያ …“ባዶ“ … ሳይመክን ዳግም መጣብኝ።ስለሆነም አጥንቴን ርህራሄ ባልሰራለት ፋስተርትሮት በምልሰት በቁስለት ሰቀቀን –በመጎዳትትህትና ልቃኘው ወደድኩኝ። ባይደገም ምንኛመልካም በሆነ ነበር። ግንስ ሆነ። እይተናነቀኝልሂድበት …

እንዲህም ሆነ …

ቀኑ ዕለተ ቅዳሜ ነበር ኢትዮዽውያን በወገናቸው የሰብዕዊ መብት አያያዝ ጉዳይ የሚመክሩበት ብሩክ ማዕልት። እኔም ወገኖቼ ስለ እኛነታችን በወልዮሽ ወደ እምንታደምበት ስብሰባ ለመገኘት ወስኜ ስለነበር ቀደም ብዬ ተገኘሁ። ከ 100  እስከ 120 የምንሆን ታዳሚዎች ነበርን። በአጋጣሚ ወንድሜ ስላልተመቸው እንጂ አብዛኛውን ጊዜ ከወንድሜ ጋር ነበር ዘና እያልን ረጅሙን መንገድ መጪ የምንለው። ወይንም ከቤተሰብ ከአንዱ ጋር። እንደ ዛሬው ውርጭ ሳይደቃኝ። ያን ቀን ግን ጉዞው በተማላ ነበር። ሁሎችም አልቻሉም ነበር። የሆነ ሆኖ ክቡር እንግዳችን መጡ። ከመቀመጫችን ተነስተን በአክብሮት ተቀበልናቸው። ለእኔ በግሌ አጋይሥት- ዓለሙ ሥላሴ በአካል የተገኙ ነበር የመሰለኝ። ሳያቸው እጅግ ደስ አለኝ። የለበስኩት በነጭና በቡኒ የተሠራ የወላይታ ብሄረሰብ ባህላዊ ልብስ ሥለ-ነበር የሳቸውም ልብ እንዳአቀረበኝ አስተውዬበታለሁ። የነበርነው ሴቶች ጥቂቶች ከመሆናችን በላይ ኢትዮጵያዊነት ጠረን ያለው ባህላዊ ልብስ የለበስኩ እኔ ብቻ ነበርኩኝ።

የክብር እንግዳችን የተከበሩ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ነበሩ። ያን ጊዜ የኢሰመጉ ሊቀመንበር ነበሩ። የምናውቅ ቀደም ብለን ብናውቅም፤ እንደ አሁኑ የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት ገመናው አደባባይ ያልወጣ ስለነበር፤ በኢትዮጵያ የደረሰውን የሰባዕዊ መብት ረገጣ ሲገልጡ ታዳሚው በተመስጦ ያዳምጥ ነበር ። የነበረው ጸጥታ ወፍ ለቅማ ትወጣ ነበር። በዚህ ማህል ነው ደፍረስ የሚያደርግ ነገር ፕሮፌሰሩ የቀላቀሉት። አይቼ ሳልጠግባቸው፤ አዳምጬም ሳልጠግባቸው፤ ከአንድ ታላቅ ሙህርና የሀገር ሃብት፤ ለዛውም ሰውን ማዕከሉ አድርጎ መከራን ለመቀበል ከወሰነ፤ እኔ በግሌ እንደ ቅዱስ ሐዋርያ ከቆጠርኩት ዕውቀት – ጠገብ፤ ልምድ – ጠገብ የድርጊት አባወራ፤ ዱብ ዕዳ ነበር የሆነብኝ። እንዴት እንዳገናኙት አላውቅም። በኋላ ላይ ስንሰማ ሌላ ቦታ ሃሳቡን አንስተው የመይሳው ልጅ መልስ እንደሰጠችበት ሰማን። ከሰነዘሩት በትንሹ „አንድ ጠብራራ ጎንደሬ ተማሪ ነበረኝ። ጎንደሬዎችን ታውቋቸው ዬለ፤ ጉረኞች በሌላቸው ላይ የሚኮፈሱ … ባዶዎች፤ ቀጠሉ … ቀጠሉ … ትምህርቱን ለመቀጠል ከእኔ የሚፈልገው የምስክርነት መረጃ ነበር። መረጃውን ሰጠሁት። ካሰበው የትምህርት እርከንም ተሳክቶለት ደረሰ።“ ወዘተ … ዞር ብዬ ተመለከትኩ። አድማጬ ከስሜታቸው ጋር ምን ያህል እንደተጋባ ማረጋገጥ ነበረብኝ። የተናጋሪው የደም ትርታን አድማጩ አልሸመተውም ነበር። በተቀራኒው ከእኔ በባሰ ሁኔታ ገጻቸው ደምኗል። ያው ከስብሰባ ስንወጣ ዝም ብለን አንወጣም። በወገን ህዝባዊ ስብሰባ አይዋ ባይታዋርነት ስላልነበረ፤ የምርጥ ዜግነት ባለ ልዩ ባልድርሻነት ጭምምታውም ስላልነበር ቤተኝነታችን እኩል ነበርና የተለመደውን አድርሰን በፍቅር ተለያዬን።

ጉዞዬን በሙሉ ሲገልጡ የነበራቸው የሰውነታቸው እንቅስቃሴ፤ የድምጽ ምቱ፤ እዬተመላለሰ አወከኝ። የዕውነት ውስጤ ተቆርጦ እንደ ሰነበተ ጎመን ጥውልግ ነበር። በሳቸው ጻዕዳ መንፈስ ውስጥ እኔ ባይታዋር ነኝና። እንዳይደረስ የለም ቤት ስደርስ ወንድሜ ቡናው አፍልቶ እንዳስቀመጠው በረንዳ ላይ ለሽ ብሏል። የእንቅልፍ ዲታ ነው። የደላህ ብዬ ቀስቅሼ ትንሽ ከተጫወትን በኋላ እሱ ወደ ቤቱ በሰላም ሄደ። ድፍርስ ስሜት ይዞ ቢሾፍር ዕዳ ነበረው። የጎንደር ነገር አይሆንለትም። ጎንደር ለእሱ ሊቀ – ንግሥቱ ናትና። መልስ አለመስጠቴን ካወቀ ፍጥጫውን ማን ችሎት። ብቻ ዋጥ አደረኳት እንደ ካፌኖል። ምኔ ሞኝ …

በማግስቱ ስብሰባ ያልተገኙ ጎንደሬዎች በስልክ አጣደፋኝ። „ለምን ከዚያው ላይ መልስ አልሰጠሻቸውም ነበር?“ „ሪፖርቱን ልትሰሪው ነው?“ አዎን። „ምን ብለሽ?“ የአዳመጥኩትን ሳይሆን ያዬሁትን። ልንግባባ አልቻልነም። ምክንያቱም የተሳታፊዎችን ተሳትፎ መግለፁ ነፃነት ለራበው ምልዐት የወገን ተስፋ ነው፤ ሌላው ደግሞ የድርጅቴን ክብር መጠበቅ ነበረብኝ። ስለ እኔ ምሥክርነት የሰጡት አለቆቼንም በምንም ነገርና ሁኔታ አለማሳዘን፤ ከልጅነት እስከ እውቀት ስለ እኔ ምስክርነት ለሰጠ አካል አለማሰፈር እጅግ የማከብረው መርሄ ነው። ከሁሉ በላይ ጎንደር ለግራጫ ጸጉር ልዩ አክብሮት ስላለው „መንገድ ስታቋርጡ ታላቆችን አስቀድሙ“ እዬተባልን ነው ያደግነው፤ በተጨማሪም ልቤን የሸለምኩት ሙያዬ፤ ያደኩበትን ማህበረሰብ ጨዋ ሥነ – ምግባርና የኢትዮጵን ተስፋ መተላለፍን አልፈቀድኩትም ነበር። እንጂ የሳቸው ንግግር እዛው አዳራሽ የሚቀር፤ የእኔ ግን ዓለም የሚያዳምጠው ነበር። ዘገባዎቼ ደግሞ ጉልበታም ናቸው። መንፈስን የመግዛት አቅሙም እንዲሁ። አዬር ላይ ሞገዱ ስብርብር የማድረግ አቅም ነበረው። ግን እኔ ህመሜን ተጋፍቼ፤ ትእግስትን ከእዮብ ሸምቼ፤ የኢሰመጉን ዓላማ ያከበረ ዘገባ አቀረብኩ። ክቡርነታቸውንም የቀደሰ። እግዚአብሄር ይመስገን፤ እንዲሁም „በመርህ ይከበር“ የአንድነት ፓርቲ ችግር ውስጥ የፊት ለፊት ተሟጋች ነበርኩ። ከቂመኞች ማህበር ያልዘነቀኝ አምላክ አሁንም ይመስገን።

አሁን ወደ ቀደመው እንደ አቨው … አንድ ሰውን ማዕከሉ ያደረገ የሰብዕዊ መብት ተቋም መሥራችና ተሟጋች ከሀገሩ ልጆች ውስጥ በልቦናው የተፋቀ ማህበረሰብ መኖሩን ለሚያገናዝብ ማንኛውም ፍጡር፤ ይህን ወጣገብ ዕይታ ቢያደምጥ፤ ህዝበ ውሳኔው ከባድ ይሆን ነበር። ይህ የሃቅ ማህደር ጎንደሬ መሆን ሳይሆን እንደ ሰው ማሰብን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። የተከበሩት ፕሮፌሰር መስፍን  በደንበሩ ጉዳይ ላይ ያላቸው ዬተባደግ ዕይታም ጎንደርን በመንፈስ ከማግለል የመጣ ነው። ሚስጢሩ ይሄነው፤ የፋሲል ፈረሱ ስናር ሱዳን ላይ ይታሰር እንደነበር ሊቀ – ሊቃውንቱ ዝክረ ታሪካችን አስተምረውናል። አሁን ሰሞኑን በጻፋት ጹሑፍ ብስጭታቸውም የተፋቀው ዕውነት በድርጊት ከብሮ አደባባይ በመዋሉ ነው። በአጋጣሚ እዬጠበቀ የጎንደር ጥላቻ ዕምቅ ገመናን እንዲህ ይዘረግፋል። የእሚወራጬ መንፈሶች ፉጭትም ይሄው ነው።

ሆድ።

መረጃ አጉል ቦታና ጊዜ መፍሰስ ስላልነበረበት ጠብቄው ቆዬሁ። አሁን ግን የህልውና ህይወታዊ ታሪክ ስለሆነ ይገለጥ መዝገቡ – ይነበብ ተብሎ ተፈቀደለት። „ባዶ“ እራሱን አባዛቱ ክራሞትሽን ላግኘው ብሎ እንዲህ ከች ሲል፤ ከምሸከመው በላይ ነው።  የሆነ ሆኖ በሁለት ነገር መንፈሴ እረክቷል። የመጀመሪያው ለተከበሩ ፕ / መስፍን ወልደማርያም ወርኃ መስከረም ሲያብት በ2015 አሜሪካ አቀባበል ያደረገላቸው ጎንደሬ በመሆኑ፤ „የጎንደሬን ባዶነት፤ በባዶው መንጠባረሩን፤ በሌው መኮፈሱን“ ዕድሉን አግኝተው ማጣጣም ይችሉ ዘንድ እግዚአብሄር ስለፈቀደ ሁለተኛው ደግሞ በህይወት እያሉ ያ በያጋጣሚው ምክንያት እዬቆፈሩ ሥሙን እያነሱ ከሚያጣጥሉት፤ ከሚያብጠለጥሉት፤ መንፈሳቸው አብዝቶ ከሚጸዬፈው ቀዬ የአማራ ተጋድሎ ገኖና ደምቆ በብሌናቸው ማዬት እንዲችሉ መገደዳቸው። ከዚህ በላይ ለእኔ የመዳህኒተዓለም ታምር የለም። ልዑሌ ተመስገን።

„የእንግሊዝ ቪዛ የተከለከሉት ፕሮፌስር መስፍን ወ/ማርያም አሜሪካ ገቡ“

https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2015/09/03/gtf-6/

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ በቅንፍ ጎንደርን ያገለለ፤ ጎንደሬነትን የተጸዬፈ፤ ጎንደሬነትን ያጣጣለ። ከዓናቱ በተበላሸ ምናብ ውስጥ ጎንደር ላይ ይፈጸም የነበረው የሰባዕዊ መብት ረገጣ ሁነኛ መንፈስ አልነበረውም። „ዬኢትዮጵያ“ በሚለውም አስኳል ውስጥም ጎንደር ያልነበረበት ነበር። ይህ አግላይነት የተጠናወተው መንፈስ ውክልና በሚያገኝበት ቦታ ላይ ሁሉ፤ የእሳቸው መንፈስ ባረፈበት አዳዲስ ተቋማት፤ ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ጎንደር ስርዝ ነው። መንፈሳቸው በምንም ሁኔታ ከጎንደር ቅዱስ መንፈስ ጋር አይታረቅም። መቸውንም። ጎንደርን ሲያነሱ እንደምን እንዳገፈገፋቸው ላይ እኒህ ሰው መድፍ ከእጃቸው ቢገባ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ … ብቻ ከመራራ ያለፈ ጎምዛዛ ነው።

በኢትዮዽያ ሥም ለመሳተፍ መፍቅዴን ሳልመርምር ከሆነ ጎንደሬነቴን በሰረዘ መንፈስ ውስጥ መሆኑን ልብ ልለው ይገባል። ይህን ከተላለፍኩ እንኳንስ ለሌላው ለውስጤ የማልሆን ከንቱ ነኝ ማለት ነው፤ በውሸት መኖር ውስጥ ለመንፈሴ ግዞት የወሰንኩበት ግዑዝ። ከአማራ ማህበረሰብ ተውልጄ „አማራ የሚባል ማህበረሰብ የለም“ ስባል፤ አንቺ ኢትዮጵያ አይደለሽም መባሌ መሆኑን ሳይጎረብጠኝ ከቀረ ህይወቴን እንዲመራው የፈቀድኩለት ደመነፍሳዊ ዕሳቤ ነው ማለት ነው። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በሳሏት ኢትዮዽያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ጎንደሬ ብቻ ነኝ ብልም፤ ወይንም ኢትዮዽያዊ አማራ ብልም በሁለቱም አማራጮች እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ስሩዝ ነኝ። አውራውን የማንነቴን መግለጫ ኢትዮዽያዊ ዜግነቴን አልተቀበሉትም። ስለምን? ጎንደሬ ነኛ። „አማራነቴም የለም“ ከተባል የዜግነቴ ደግ መንፈስ በሳቸው መንፈስ የተፋቀ ወይንም የተፈገፈገ ነው። እና እኔ ዬት ነኝ? ምንድንስ ነኝ? ቅጠል ወይንስ ምን?  አዲሱ „የአደራ መንግስት“ የሚሉት ንድፈ ሃሳብ እኔን እንደ ጎንደሬነቴ ሆነ እኔን እንደ አማራነቴ የማያስተናግድ ነው። ነገር ግን ለመቆስቆሻነት ሆነ ለማገዶነት አሁንም ቅድምም ጎንደር ይታጫል። ቁስለት። የቅንጅት ጊዜ በአኃታዊ ዕድምታ „አሁን እንዲህ ትሉናላችሁ ነገ ባላችሁን መስመር አናገኛችሁም“ በማለት ገጥ – ለገጥ ልዑካኑን አፋጥጧል – መከረኛው። „ቃል የዕምነት ዕዳ“ ነውና በቃላችሁ ስለመገኘታችሁ ውል እሰሩ በማለት ሞግቷል – አሳረኛው። የእኔ መንፈስ መርኽ ይህ የቆሰለው የተገላይነት የወገኔ መንፈስ ነው።

ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ በክቡርነታቸው መንፈስ ውስጥ ጎንደሬነቴም ሆነ አማራነቴ በቁርሾ የተጠቀለለ መርዝ ነው። „በስማ በለው“ ሳይሆን ጠረናቸው እንዳይርቀኝ ከቅርባቸው ሆኜ „ባዶ“ ሲሉኝ አዳምጪ በተከበረው የሲያትሉ የአማራ ሆነ በአትላንታው የኦሮሞ ማህበረሰብ ህዝባዊ ስብሰባዎች የድጋፍ እንቅስቃሴዎች „ባዶን“ በብዕራቸው ደገሙት „ጎሠኛነት በባዶሜዳ“  ሲሉ። ለሁለተኛ ጊዜ ያን መንፈሴ ክፋኛ የተፀየፈውን የአንድ ክ/ሀገርን ህዝብ „ባዶ“ ባሉ በስንት አመቱ ሁለቱንም ታላላቅ ህዝቦች „ባዶ“ ሲሉ የአንድነት ኃይሉም ሊያመው፤ ሊጎዳው ይገባል። የፖለቲካ ወይንም የሲቢክስ ድርጅቶች ማኒፌስቶን ሳይሆን ሰውን ማዕከሉ ያደረገ ሚዲያም ቢሆን ቁስለቱ ሊሰማውና ሊያርመጠምጠው ይገባል።

እንደ ታቦት ክብካቡ ለሰው ልጅ ክብርና ልዕልና እንጂ ለተራጋጭ መንፈስ ሊሆን አይገባም። ማኒፌስቶ ወረቀት ነው። የሚቀደድ። የሰው ልጅ ግን ልዑል እግዚአብሄር በአምሳሉ የፈጠረው፤ ስለ ሰው ልጅ በደል መስቀል ላይ የተሰቀለበት፤ በችንካር የተቸነከረበት፤ መራራ ሃሞትና ከርቤ የጠጣበት፤ የሞተበት፤ ሞትን በሞቱ ድል ያደረገበት የቃሉ፤ የፍቅሩ ሚስጢር ትርጉሙ ሰው። ስለሆነም የርምጃችን አህዱ የሰው ልጅን ልዕልና፤ ልቅና መሆን ይገባዋል። „እግዚአብሄርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌያችን እንፍጠር።“ (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ“ ፩ ቁጥር ፳፮)። ክቡር ፕ/ መስፍን ወልደማርያም በተለይ አሁን በዚህ ጉልበታም ዬጎንደር አብዮት የህልውና የአማራ ተጋድሎ ያሸተ ምዕራፍ ሊናደዱ ይገባል። በአንድ ፋሽስታዊ የጥቂቶች የጎሳ አንባገነን ግዛት „ለአማራ ማህበረሰብ የምን ውክልና?“ በማለት የፈለሰሙት „አማራ የለም ግዑዝ ዶክተሪን“ ግባዕተ መሬቱ የሚፈጸምበት ወቅት ነው። „የአማራ የለም ዶክተሪን“ ቀባሪ አልባ፤ ምሾ ወራጅም አልባ በደመ ነፍስ ኖሮ፤ እንዲህ ትቢያ ለብሶ፤ የፈለገውን ሳያገኝ እንደሻቀለ ላሽቆ ብን፣ ትን፣ ቅብር ሲል መበሳጨት የግድ ይሆናል። የአሳቻው ሽምቅ ተዋጊ „የአማራ ብሄር የለም ጠቀራ ዶክተሪን“ እንሆ ሁነኛ ጊዜ አግኝቶ ግባዕተ መሬቱ ተፈጸመ። በማን? በህልውና ልዕልና በእንቢተኝነት ልቅና በሥህናዊነት የታሪክ ገናና።

ስለምን „የአደራ መንግስት“ ፍልስፍና በስጋት ተናጠ?

የሁለቱ ማህበረሰብ ጉባኤዎችም „የአደራ መንግስት“ ፍልስፍን በእጅጉ የሚያሰገው ነው። እንደ በፊቱ በሚገለባበጡ ተለዋዋውጭ የፖለቲካ ምሥረታዊ ሥም ዛሬ መርፈስ የለምና። ወጣቱ ፍሬ ነገሩ ገብቶታል። መከራውንም – ኑሮበታል። እንደ ሀገር ተረካቢነቱም የወደፊቱ ዕጣ ፈንታው እሱን የበይ ተመልካች እንዳያደርገው የጠራውን መንገድ ጀምሮታል። የወረቀት ማንፊስቶ ሳይሆን ህልውናው ብቻ ሆኗል ማኒፊስቶ። ኑሮውን የሚወስነው በማኒፌስቶ በመቁንን በሚታደል ሽርፍራፊ ጥገኛ የመብት ልመና ሳይሆን፤ እሱ በፈቀደው፤ በቀዬሰው፤ የእኩልነት ፍትኃዊነት መሆን እንዲችል ወስኗል። በቃኝ ሲል ሁሉንምትብትብ በቃኝ ማለቱ ነው። አሻም ያለው ባለቤትነት በተነፈገው መኖር ውስጥ እንደማይቀጥል መቁረጡን ለወዳጅምለጠላትም ማሳወቁ ነበር። የመገፋት ክርፋትን ማስወገድ የሚቻለው ትግሉ የገማውን በድን ዕሳቤ ከአናቱ መናድ ሲችል ብቻ ነው። ለዚህ የደም ዋጋ እዬከፈለ ነው። በአዋጣው የደም ልክ ማንነቱን ያስከብራል። ወጣትነት ሁለመናነት ነው። ወጣቱ የራበው ፍትኃዊነት ብቻ ነው።

ወጣቱ ሁሉም ነገር አለው። ስለዚህ የፍላጎቱ የስኬት ቁልፍ በእጁ ነው። ደጅ ጥናት አያስፈልገውም። „የአደራ መንግስት“ ፍልስፍና (ለዛ ከተበቃ) ጤነኛ መንፈሱ በሃኪም ካልተረጋገጠ፤ ተገላብጦ ካልተመረመረ በስተቀር እንደ በፊቱ በዝንቅ ገጠመኝየወጣቶችን ሥነ – ህሊና መግዛት አይቻልም። ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ እንዳለ ዬተቀበልናቸው መንፈሶች ጦሶች ጊዚያቸውን ጠብቀው እያዬናቸው ነው። የግጭት ዓውድ። በአንድም በሌላም እዬተገለጡ ነው። ዕድሉን የተሰጣቸው መንፈሶች የአማራ ተጋድሎ ላይ ሲደረስ ወገቤን እያሉ ነው። ሽሽት እንጂ ድፍረት አላዬሁም እኔ። እኔ ነኝ ባሉ በሁሉም ዓይነት ሙያ በተሰማሩት ሊቀ – ሊቃውንታት በሁሉም ማለት እስከሚያስችል ድረስ። „ትዝብት ነው“ አሉ ፍሰኃ ለምለም። ቢያንስ ዕውነት ለሆኑ ጭብጦች አቅም አልተገኘም፤ አንዱ „ከፋኝ“ ይላል በታከተው ሥያሜ፤ ሌላው „የነፃነት ኃይሉ“ ይላል ባልጠራ አቋም፤ ሌላው ደግሞ „እራሳቸውን ያስታጠቁ“ ይላል በተቀረቀር ዕይታ። ወያኔ ደግሞ „ጥቂት ሰላም አዋኪዎች ምንትሶ ቅብጥርሶ“ ይላል። ዕውነት እንዲህ በግራ ቀኝ ተዘምቶባት ሱባኤ ገብታለች። ብሩህ ዳኛ ካልተገኜ ነገም ተንጠልጥሎ የሚታዬን ሰዎች አለን።

የሆነ ሆኖ ክቡር ፕ / መስፍን ወልደማርያ በህይወት እያሉ አማራ የአቅም ዓውራነቱ በበቃ ዕውቅና እና ውክልና የኢትዮጵያ ወሳኝ አካል ሆነው ከሚወጡት ጋር የደሙን ዋጋ በሥማ በለው፤ በተወካይ፤ በጥገኝነት፤ በፍርፋሪ ተጠማኝነት ሳይሆን እራሱን ሆኖ የተስፋ አካልነቱ ሲያረጋግጥ እንዲዩ አምላኬን አብዝቼ እለምነዋለሁ።

የአማራ ጉዳይ መወያያ አጀንዳ መሆኑ የግድ ነው። በሁለገብ ጠላትነት የተፈረጀበት፤ በሥሙ የተነገደበት ዘመን ማክተሚያ ዋዜማ ላይ ስለሚገኝ። በተረፈ „የፈሩት ይደርሳል“ ብሎ ማሰቡ፤ እራስን ለውጦ ተሰናድቶ መጠበቅ ይገባል። ወቅት ብልህ ነውና የራድ ቁራኛ ላለመሆን ውስጥን ማሰናዳት ይገባል። ይህ ገድለኛ ሞገድ አይመለስም። ዬቆረጡ ጀግኖች አሉበት።

ዕውን የሁለቱ ታላላቅ የማህበረሰብ ልጆች የዕንባ አለኝታነት ትጋት „ከባዶ“ የተነሳ ነውን?

በፍፁም።

  1. ውጪ ሀገር ያለው ወገን መሠረቱ የወገኑ የዕንባ ድምጽ ያሰባሰበው እንጂ፤ ሠርግ ላይ የተቀመጠ ሽሙንሙን፤ ኬክ የተቆረሰለት የቅልጣን ደቮ አይደለም። ይህ የበቃኝ ጉዞ እኮ እውነት ማህደሩ፤ የምልዐቱ ትንፋሸ መሰረቱ፤ መሪውም የጀግና ውሎ፤ ባለቤቱ ህዝብ ነው። ስለሆነም ቅብ ዕሳቤ ክፍሉ አይደለም። ወፊቱ ሹክ ያለችውም ይህንኑ ነው። የወገኔ ኑሮ በወፏ ዜና የተገነባ ነውና።
  2. ልጆቹ የበቃኝ ታሪካዊው ተጋድሎ ዕድምታ ባክኖ እንዳይቀር ሥራ ላይ ናቸው። የበቃኝ ታሪክ በመንፈስ አንድነት ውል ጅምር ነው። መተንፈሻ ያጡ የንፁህ አዬር መተንፈሻ ቯንቯዎች፤ የግዞት ስውር አፈናዎችና ዘመቻዎች፤ ባለቤት ያልነበራቸው የቀደሙ ሥልጡን የሃሳብ ማዕከሎች፤ ባለቤት ኑሯቸውም የትኩረት ስስነት የሚታይባቸው ቁም ነገሮች፤ አቅጣጫ ያልያዙ ተዛነፍ አስተሳሰቦች፤ የእኔ ባይ አግኝተው የፍላጎት ወጥነትን ለመውለድ መንገድ የወጠኑበት፤ ክፍተቱን በባለቤትነት ለመሙላት በስክነት ለመምከር የተሰናዱበት በጎ ጅምር ሲሆን፤ እርግጥ ነው „ዬሦስተኛ መንገድ ጥመኞች“ጥነት መንፈስን ነቅቶ በብቃት መመከት ከተቻለ፤ ለተስፋው አዝመራ ሰብሉን ከወዲሁ ማስላት ይቻላል። ይህም በተለይ ለአማራ የተጋድሎ ድጋፍ አምንጪ ኃይሎች የመወሰን አቅምን ብቻ ሳይሆን፤ የደም ዕንባን በቅጡ የመተርጎም ችሎታን፤ በሳል ተስጥዖን ይጠይቃል።

ተመስጦ

የአህዱ ጅማሬ ቆባ ላይ የሚገኘውን ፍላጎታችነን ብስል የማድረግ፤ የወጥ ፍላጎት ጣዕምን ከህዝብ ናፍቆት ጋር ለማገናኘት ብልህ ዕሳቤዎችን ዕውቅና ለመስጠት፤ የደጋፊ አባላትን የአያያዝ ድክመትን፤ ጤናማ ያልሆነውን መንገድ ሳይቀርም አቅርቦ የመንፈሱ ተጠቃሚም – ጠቃሚ ኃይልም የማድረግ አዲስ ፈር ነው። የለመድነው ከሊቃናት ብቻ ሲሆን፤ ይህ መንገድ ግን የተዘጉ አውራጎዳናዎችን ክፍት ለማድረግ ሞክሯል። በዚህ  ከቀጠለ ልብ ይሸለማል። የልቤ ይባላል፤ ምክንያቱም ዜግነታቸውን የተነፈጉ ምንዱባን መንፈሶች አሉና። በኢትዮዽያ የፖለቲካ አመራር ተፈጥሮ ባለቤት ካላቸው ማህበረሰቦች ይልቅ አቋጣሪ የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ይበልጣሉ። ይህ ግንዛቤ እንደ መልካም ውርስ የተያዘ ነበር፤ አሁን የተጀመረው መንገድ ግን ፊት ተነስተው የነበሩ ወገኖች ጠያቂ እንዲኖራቸው ያነቃል – ያደራጃል። ትጉህ ት/ ቤት የመሆን አቅሙ ለነገ የዬምስራች ፍንጭ ነው። አውንታዊ የሆነ ፋክክር ይጸንሳል። አላችሁን? ይመጣል። ረጋ ብሎ ከተጀመረ የጦሮ ሰለባ አይሆንም። ሞቅ ሲል ሞቅ፤ ቀዝቀዝ ሲል ቀዝቀዝ የለም። የእኛ የፖለቲካ አያያዝ አደብ ያንሰዋል። ስለዚህም የኛ የፖለቲካ ክህሎት አድማጭነትን ጣዕሙ አድርጎ አያውቅም። ለዚህም ነው ህልሞቻችን መዋዋጥ የተሳናቸው። ፋሽስትም እንዳሻው ልዕልት ነፃነትን እንዳሻው ማረድ ዕለታዊ ተግባሩ የሆነው። አሁን የወያኔ መደበኛ ሥራ ህዝብ ማሰር፤ መግደል ብቻ እንጂ ኢትዮዽያን እያስተዳደረ አይደለም። ስለዚህም ባልታዩ ጉዳዮች ላይ መረባረብ ግድ የሚያደርገውም ይሄው ጭብጥ ነው። በእጃችን ላይ በወጥ ፍላጎት ላይ መዋዋጥአልተጀመረም። ቢያንስ ደፍረን እንጀምረው በሚሉት ላይ ጥርጣሬን አስወግዶ ቅንነትን ምራኝ ማለት ይገባል። ድጋፍ ማድረጉም ሆነ ማበረታቱ ቢቀር።

በጎ ዕንቡጥ።

እነኝ ሁለት ጉባኤዎች ማለትም የአትላንታውና የስያትሉ ማለቴ ነው፤ ዝንቅንቅ ፍላጎቶች መልክ ለማስያዝ ፊደል መቁጠር የተጀመረበት፤ የፖለቲካ መሪዎች ከወንበራቸው ወረድ ብለው ካለ ፕሮቶኮልና፤ ካለ ምንም ዓይነት ሲናሪዮ ከህዝብ መሃል ቁጭ ብለው ህዝብን ያደምጡ ዘንድ ፊደል የቆጠሩበት፤ ተማሪ መሆንን እንዲቀበሉ ያስተማረ የነገይቱ ኢትዮዽያ መቅድመ ብጡል ነበር።

ታላቁ የሥልጣን ምንጭ የህዝብ ፍላጎት እንጂ ቀና የሚያስቡ ወገኖች ስብስብ ፍልስፍና ብቻውን መሪ እንዳይሆን፣ ይልቁንም ከህዝብ ውስጥ መነሳትን መሪ አጀንዳና ሃሳብ መሆን እንዳለበት በድርጊቱ የሰበከ መልካም መንገድ ነበር። በሌላ በኩልም የችግር መፍቻው ቁልፍ የፖለቲካ መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ፤ ህዝቡም መሆን እንዲችል መደረጉ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ጫና፤ የሥራ ብዛት የሚቀንስም በጎ ጅምር ነው። ከሁሉ በላይ ሕዝቡ መስመሩ ከተዘረጋለት በፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ያልታዩ፣ ያልተዳሰሱ፣ አዲስና ቀንበጥ ታታሪ ዕሳቤዎች ይፈልቃሉ። ይህ በህዝብ ፍላጎትና በፓለቲካ መሪዎች መካካል ቀጥተኛ የሆነ የጤናማ ፍላጎት ጥምረት መስመርን ይዘረጋል። በማህል አቅምን የሚበሉ የኢጎ ዕዳዎችም መቅኖ ያጣሉ። ጥላቻ ፈጣሪው አዋኪ ሃሳብን በጠራ መስመር ለመምራት ምቹ ይሆናል። የዘበጡ ሃሳቦችን ገርቶ የአቅም አካል በማድረግም እረገድ ይህ አዲስ መንገድ የሁሉንም የቤት ሥራ ያቃልላል። የተጣራ ምርት ለተጠቃሚው ለማቅረብ ገድ መንገድም ነው።

ዬዝግ ስብሰባ – ጠቀሜታው።

የአትላንታው ምልዓታዊ የምክክር መድረክ ዝግ መሆኑ አትራፊ መንገድ ነበር። እንዴት? የጠላት ፕሮፖጋንዳ ማዳበሪያ እንዳይሆን መደረጉ በራሱ አዲስ ቅጽ ነው። የተናጋሪዎችን ነፃነትንም ይጠብቃል። ተሳታፊዎች ነጻነት ከኖራቸው ውስጣቸውን የመግለጥ አቅም ይኖራቸዋል። ከሁሉ በላይ መሸከም የማይቻሉ፤ የውስጥ ሃዘን ፈጣሪ ዕሳቤዎች የአደባባይ ሲሳይ እንዳይሆኑ ክትር መሰራቱ፤ ለኢትዮዽያዊነት መንፈስ ብቁ ጥበቃ ያደረገ ቅዱስ ውሳኔ ነው። ከህሊና ጉስቁልና ሁላችነንም ታድጓል፤ ጤናችን ጠብቋል። የተዘመተበትን የአብሮነታችን ሩህ ብቁ ትንታግ በመሆን ለእያንዳዳችን መንፈስ የደህንነት ዘብ ቆሞለታል። ባላለቁ ዕይታዎች፤ ባልታሹ ጉዳዮች፤ ባልሰከኑ አጀንዳዎች መታመስን ከሥሩ ነቅሏል። ጊዜያችነን አልበላም። ስለሆነም ለዚህ ብልህና የቀደመ እርምጃ ታላቅ አክብሮት አለኝ፤ ዕውቀትም ገብይቸበታለሁ። ምክክሩ ዝግ መሆኑ የፖሮፖጋንዳን ቅንጥብጣቢ ክብር ነክ ምክንያቶች እንዳይጠጋው በእጅጉ ተጸይፎታል። እዩልኝም አላለም። እዩኝ … እዩኝ አላለም። ስለሆነም በሳል ምዕራፍ ነው። ተባረኩ።

ዝግነቱ … ሥልጡን ነው። ውስጥ ካለ ግርዶሽ ታዬ ማለት ነው። (X-ray) ስለዚህም ሸከር ያሉ ዕሳቤዎችን ልጎ ዉስጥን ከውስጥ ጋር ለማዛመድ ቀና መንገድ ነው። በዚህ መንገድ አድብተው የሚጠብቅ የግራ ፖለቲካ ጎታችና ቅንነት የፈለሰበት ሽምቅ ውጊያ ኪሳራ በኪሳራ ይሆናል። ይህ ደግሞ በስለት እንኳን የማይገኝ የመከራችን መፍቻ የሚስጢር ቁልፍ ነው። መጀመሩ በራሱ ነገን ቦግ ብሎ ይመጣልናል የሚል በጎ ምኞትና ተስፋ እንዲያድርብን ያደርጋል። የግብረ ኃይሉ አስተባባሪዎችም ባገኙት የውስጥ መንገድ ጠቃሚና ጠቃሚ ያልሆነውን በመለዬት በአገኙት መረጃ (feedback)፤ በጥበባዊ አስተዳደር ሁሉንም አቅም ቤተኛ ለማድረግ ይረዳቸዋል። የምልዕቱን የአቅም ጥሪት በአግባቡ ለማስተዳደር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። በተጨማሪም እንደ ባህል እዬሆነ የመጣ አዳጊ ያልሆነ መንገድ ነበር። “ኑ ስብሰባ። … ግን ስትመጡ አንደበታችሁን አሽጋችሁ የሚዋጣውን አዋጥታችሁ በወሰንላችሁ ልክ ብቻ መቀጠል ግዴታችሁ ነው“ የሚለው ብልህነት የጎደለው መንገድ ሃዲዱ እንዲሰበር አድርጓል።

ስትመጣ „አፍህ እንደከረቸምክ ሰምተህ ብቻ መመለስ።“ ይህ በዚህ ግሎባላይዜሽን ዘመን፥ ዘመኑን ያላዳመጠ አካሄድ ነው። „ጨዋታን ጨዋታ“ ያነሳዋል ይላል የጎንደር ሰው። ስብሰባ ስሄድ በነበረበት ጊዜ ሁልጊዜ እማስታውሳት ወ/ሮ ነበረች። ወርቅ የሆነች። ብዙ የጎንደር ሰው የጠራ የገጽ ቀለም ነበረው። የዛሬን አያድርገውና። ከእነሱ ጋራ በአጥር ነበር የምንለያዬው። ያቺ ታይታ የማትጠገብ እመቤት ጎንደር ጡረታ ሰፈር በዘመናዊ ቢላ ነው የምትኖረው፤ የሰፈሩ እድር ማህበርተኛም ናት። ሃዘን ሲሆን እንጀራውንና ወጡን የምትልከው በቤት ሠራተኛ ነበር። የዕውነት ነው የምነግራችሁ። እሷ በቀብርም – በማስተዛዘንም ትውር አትልም። አቶ ሞት ከቤቷ ገባ። የአውራ ጎዳና ተወዳጅ ሠራተኛ የነበሩት ባለቤቷ አረፉ። ታዲያንላችሁ ማታ – ማታ ሠፈርተኛው ሰራተኛ ያለው በቤት ሰራተኛው፤ ልጅ ያለውም በልጅ እንጀራና ወጡን እዬላከ በመንፈስ ብቻ አስተዛዘነ። ጎንደር ዋዛ፤ እህ። መከራ በባዶ ድንኳን። እጅግ ከባድ ቅጣት ነበር። የጸደቀ እርምጃ ነበር። ስለዚህ ታሽጎ ውሎ ከመመለስ አቅሙ ያለው ሁሉ ገንዘብ በመላክ ስብሰባ ቢቀር ምን ይባል ይሆን? የሆነ ሁኖ ከዚህ ቅጣት በኋላ የእድሩ መሪ ሆነች። ስለዚህም የኦሮሞና የአማራ ማህበረሰብ ስብሰባዎች የገነገኑ ግትር መንገዶችን ሁሉ በሚገርም ሁኔታ ገርተዋል። በባይታወርነት የተገረፋ መንፈሶች ሁሉ አለንላችሁ ተብለዋል። ማለፊያ። ይሄ ዝንተዓለም ዬተኖረበት „እንዳያማም ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ አቁሳይ ሂደትም በፈንታው ድንኳን ጥሎ እንዲቀመጥ ተገዷል። ለዚህም ነው ዘገባው ሁሉ አስተዛዛኝ የነበረው። ከዘገባ ውጪ የሆነ ታላቅ ማህበረሰብም አለ። አማራው። በውስጥ ለውስጥ መንገድ መሠረዙን አስተውሎበታል። እነዚህ የውስጥ ኃዘኖች ናቸው ለብሄርተኝነት ጥሎሽ የሚጥሉለት – ማጫም የሚያማቱለት። ለጎጆው ድምቀት ድርና ማግ የሚሆኑት። ነፍስ ታለች። ህሊና ታጥጣለች፤ አንደበት ትሞታለች። ብዕርና ብራን ለሌላው ለዕውነት እንዳደሩት ለዚህ ዓይን ላወጣ መገፋትም ዕውቅና ይሰጣሉ። እራስን ሰርዞ መኖር ስለማይቻል።

አውታር።

የፖለቲካ፤ የሲቢክስ፤ መሪዎችና አክቲቢስቶች እንደ ህዝብ – ከህዝብ ጋር ተቀምጠው እንዲያደምጡ መደረጉ የሥልጣን ሹም-ሽር ሲገጥም እንደ አንድ የእኔ ቢጤ ተራ ሰው ከሥር መኖርን እንዲለማመዱትም፤ ሰራዊታቸው ሕዝብን እንዲያደርጉ የልምምድ ት/ ቤት ተከፍቶላቸዋል። ይህ ፈጣሪ የገለጠው ሚስጢር እንጂ በሰው እጅ የተሠራም አይደለም። አመል ሆኖብን ከእኛ ብቻ ባለመሆኑ ለመግፋት ካላሰብን በስተቀር እንዲህ የምናቃልለው፤ የምናጣጥለው፤ ከዚህም አልፈን ተርፈን „በባዶነት“ የምንፈርጀው ሊሆን አይገባም። ለዘመኑ ጥልቅ፤ ምጡቅ ጅማሬ ነው። ክንውኑ ያደጉ መንገዶችን – የቀሩን ስልቶችን የሚሳዩ መስታውቶች ነበሩ። እንደ እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ አሰልቺ ወይንም አትራፊ ያልሆኑ መንገዶችን በቅጡ ገምግመን አቅማችን ለማፅናናት ቀበቷችን ሊሆን ይገባል ባይም ነኝ። በስተቀር በእጃችን ያለው ኃይል ሳይቀር መንፈሱ ይሸፍታል። ይተናልም። ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳልና። አንድ ሰው ምንም አያደርግም ማለት የሚቻል አይመስለኝም። አንድ ሰው መንፈስ ቅዱስ ከቀረበው፤ ቅንነት ጥሪቱ ነውና ልዩ አቅም የመሆን ችሎት አለው።

አንድ የፖለቲካ ድርጅት ወይንም ሚዲያ፣ ወይንም ሙሁር፤ ወይንም የሲቢክስ ድርጅት ብቻውን ይህን የገዘፈ የፈተና ወንዝ መሻገር አይችልም – ዛሬ ባለው የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ። ሁሉም የቤት ሥራውን ለመሥራት በተመቸው መንገድ ተደራጅቶ መሥራት አለበት። መብት ቦንዳ የጣቃ ጨርቅ አይደለም። በሜትር ተለክቶ የሚታደል ወይንም እንደ ሸቀጥ በጀምላና በችርቻሮ በገብያ ሥርአት የሚተዳደር። ክትር ተሰርቶል በተዘጋጀልህ እንደ አሸንዳ ፍሰስ የሚባልም አይደለም – መብት። ወይንም በሰዎች መልካም ፈቃድ ብቻ የሚቸር የቡፌ ግብዣ አይደለም -መብት። መብት በውስጥ ፈቃድ ብቻ ህልውናው የተረጋገጠለት የሥነ – መንፈስ ልዑል ነውየእኔ ብቻ ሊባል የሚችል የነፍስ ጥሪት ነው። መብት የህልውና ገዢ መሬት ነው። ይህ ንፁህ የሰው ልጆች መብት ለዘመናት እግር ከወርች ታስሮ የኖረበት ዘመን የሚከትመው የህልውና ልዕልና በእንቢተኝነት ልቅና የሥህነ – ታሪክ ገናና በሆነው የህዝብ ተጋድሎ ብቻ ይሆናል። መንገዱን ደግሞ ጀግኖቹ ጀምረውታል።

የተከበሩ ፕ / መስፍን ወልደማርያም ሆይ!! „ዝም በሉት¡ ምን ያመጣል¡ የት ይደርሳልማ!“ ከስሎ ቀረ። አይጠራጠሩ አማርኛም ሆኖ ኦሮምኛ ብሄራዊ ቋንቋ መሆኑ ብቻ የትውልዱን ጥያቄ አይመልስም ወይንም በመጠጋገን ፕሮፖጋንዳ መላሾ አይወራረድም። ከእንግዲህ አንቅረው የተፋት አማራም እንደወትሮው „የስማ በለው“ ውክልና መጠቃጠቂያ አይሆንም።

ክቡርነተዎት ዬቤተሰቦቼን የዘር ሐረግ አማራነቴን፣ እንዲሁም ናፍቆቴን የፋሲልን ከተማ ባይወዱትም በአመኑበት መሥመር የድርሻዎትን ለማበርከት  ከልጅነት እስከ እውቀት ልፋተዎትና ድካመዎትን፣ ላደረጉት የራስ መንገድ ተጋድሎ አክብራለሁ። እግዚአብሄር ዕድሜ ሰጥቶዎትም የተመኟትን ኢትዮጵያ ያዩ ዘንድ በቅን መንፈስ አልማለሁ። የዛን ግዜ ያን የመሰለ ሪፖርት የሠራችው ጎንደሬዋ ሥርጉተ ሥላሴ ነበረች፤ ለዛን ጊዜዋ ወጣቷ ሥርጉተ የሰጧት ሥጦታም ነበር። ከስጦታው ይልቅ ለቀንበጡ መንፈሴ ተጠንቅቀውለት ቢሆን ጥሩ ነበር። የማልሸሽገዎት  – ጎድተውኛል። እኔ ግን እስከዛሬ ድረስ አከብረዎታለሁ። ለወደፊቱም። እኛ ምን እንደምንፈልግ? ምን እንዳለን? ምን እንደምንችል? ጠንቅቀን እናውቃለን። ክቡርነተዎት እንደሚሉን „በሌለን ላይ የምንኮፈስ አይደለንም።“ „ባዶዎችም – አይደለነም።“ አቅማችን ወደ ተግባር ለማሸጋገር መንገዱ ዝግ ቢሆን እንጂ ያለንማ አለ። ለኢትዮዽያም ማገሮች ነን። ተስፋዎች። እኛን አልባ ኢትዮዽያ አንድ ጋት አትራመድም። „ጎንደር ምን አለ?“ ብሂሉም ይሄው ነው። ዕጣ ፈንታው ከመማገድ በቀር ዕልፈት አግኝቶ ባያውቅም። አሁንም ያሰፈሰፋ አይኖች ከእሱ ራስ ወርደው አያውቅም። ውጪ ያሉ ሊቃውንታት የአብዛኛው የአደራ ቤት ነው ጎንደር። አንድም ባለዕድል ህይወቱ ሲስተካከልለት አንድ የጎንደር ልጅ ወስዶ ለመስተማር ያሰበ የለም። ወጭት ያልሰበረ አላዬነም – አልሰማነም። ጎንደር የመከራ ጊዜየኢትዮጵያን እናቶች አደራ ያወጣ ታላቅ ህዝብ ነው። አማራ ማለት ሰባዕዊነት ማለት ነው

መርህ።

የማከብረዎት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም። ጥሪው የዕንባ ነው። የኃላፊነቱ ማሳ ዘርፈ – ብዙ ነው። ስለሆነም ለጥቂት ፓርቲዎች አቅም ብቻ የሚተው አይደለም። የሁለቱን የማህበረሰብ ልጆች ያሰባሰባቸው ወቅትን ያዳመጠ፤ ልቅናን ያጨው የብዙኃኑ የበቃኝ ገድል እንጂ፤ ውጪ ሀገር የሚኖሩ የሁለቱ ታላላቅ ማህበረሰቦች አምክኖዬ አይደለም። ወቅቱ ከቀደመው በተለዬ ሁኔታ በራሱ የጊዜ መስመር የፈነዳውን ማእበል የሚመጥን አቅም ይጠይቃል። ዬፖለቲካ ድርጅቶች ይህን የበቃኝ ገድል ምንጭ ይሆናል ብለው ስላላሰቡት በማኒፌስቷቸው ውስጥ አላካተቱትም ነበር። የማኒፌስቷቸው መንፈስ በዚህ የህዝብ ረመጥ ዝር አላለም ነበር። የዚህ ገድል ባለቤት ህዝብ ብቻ ነው። ከፖለቲካ መሪዎችና ማኒፌስቶ የዳታ ጉዞ አሻም ብሎ የተነሳው ህዝባዊ የበቃህኝ – የሂድልኝ ጥያቄን ለመምራት እውነትን ስንቁ ያደረገ፤ መነሻውም መድረሻውም ከህዝብ ፍላጎት ዉስጥነት የሚነሳ፤ እራሱን ዝቅ አድርጎ ለህዝብ የበላይነት ታዛዥ የሆነ መሪ ይሻል። የወቅቱ የእንቢተኝነትን ሞገድ ለመምራት ከታሰሩበት የማኒፌስቶ ፍቅር ራስን ማውጣት በእጅጉ ይጠይቃል። ምክንያቱም የወቅቱ የህዝብ „የማንነት ጥያቄና ተያያዥ ጉዳዮች“ በፖለቲካ ድርጅቶች አክብሮት ያልነበራቸው ስለነበሩ ማንፌስቶዎች ይህን የእውነት ጎዳና ለመምራት ከሽሽት በድፍረት የውስጥ ለውጥ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ከተጋድሎ ስያሜዎች ጀምሮ እውቅና መስጠት ብቻ ሳይሆን ሙሉ አክብሮትም መሰጠት ይገባቸዋል። የተሻለ ክህሎትና ጥበብ የተሞላው መንገድ ወቅቱ ይጠይቃል። ስለሆነም አጋዢ ጥረቶችን ማበረታት ይጠይቃል። ነፃነት ከተፈለገ። በተለመደው መንገድ ከሆነ ግን ለወያኔ የገድ መንገዱ ይሆናል። የዕናቶች ዕንባ የወገን ደምም ባክኖ ይቀራል። ትዕግስትን ዋጥ አድርጎ እውነት ብቻ እንዲመራ ቢፈቀድ ኢትዮዽያ አላዛር ናት። እንደ ገና አዎን እንደ ገና ፈተናን አሸናፊው የተፈጥሮ ሚስጢርነቷ ዳግም ይጎመራል። ግን ወቅቱን በተደሞ ማድመጥ የሚችል ምራቃቸውን የዋጡ መሪዎች ጥሪዋን ሰምተው በሃቅ ማሳ አብሮነትን ማፍለቅ ከቻሉ ብቻ። እናት ሀገር ኢትዮዽያ ሁሉም አላት – ለሁሉም ትበቃለች። የምንም ነገር ደኃ አይደለችም። እኛ ታምሰን የምናምሳት እኛው ነን።

ወቅቱ በቢሮክራሲና በማዕከላዊነት ያልታሰረን መንገድ ይጠይቃል። ግልጽነትና አድሮ የሚገኝ ዕውነታዊነትን ብቻ ስንቅ በማድረግ፤ ጥርጣሬና ስጋትን በፍጹም ሁኔታ የሚታደግ ቀጥተኛና ያልተወሳሳበ፤ በፕሮፖጋንዳ ያልበከተ ቅልብጭ ያለ ቀላል መንገድን ይሻል – ባላንባራስ ዛሬ። ማዕበሉ ፈጣን፤ ፈተናዎቹ እጅግ የገዘፋ በመሆናቸው ፈጣን የጥያቄ ምላሽ ሰጪ አካልን መስመር መዘርጋትን ይጠይቃል። በዛሪይቱ ኢትዮዽያ የፋሽስቱ አስተዳደር ገዢ መሬት ላይ ሲሆን የህዝቡ የበቃኝ አብዮት ግን በከፋ ሁኔታ ሙት መሬት ላይ ስለሚገኝ። የነፃነት ትግሉ መሪዎች ሰብዐዊነታቸው ሚዛን የደፋ መሆን አለበት። ትንፋሹ ያጠረው መከረኛ ህዝብ ነው ያለን፤ ቀን በጨለማ የተዋጠበት፤ ፀሐይ የደም ካባ የለበሰችበት። መተንፈስ ፋታ ያጣበት። ስለሆነም የተጋድሎ አርበኛውን ደህንነት ለጠላት ጥቃት የሚያመቻቹ መረጃዎችና የፕሮፖጋንዳ ገብያዎች ባስቸኳይ መታረም ይገባቸዋል። ለእኔ የሚበልጥብኝ የፕሮፖጋንዳ ሰይፍ ሳይሆን የሰው ልጅ ለሚከፍለው መስእዋት በቂ ጥበቃ ሲደረግለት ማዬትን ነው።ለዚህ ነው ኃላፊነትትን መከፋፈል ግድ የሚሆነው። ባለቤትነት ከርህርህና ጋር መዋደድ አለበት። በዚህ ክፋ ጊዜ ያን መከረኛ ህዝብ ለበለኃሰብ እንይሰጥ ጋዜጠኞችም ቢሆኑ ለህሊናቸው ቢያድሩ ይሻላል። ህዝቡ በአውሮፕላን ቢጨፈጨፍ፤ ብርሸለቆ የታገቱት ቀንበጦች ቢረሸኑ የሚጎዳው ነው የሚጎዳው። ስለሆነም ኃላፊነት ከጎደለው የመረጃ ቅብብሎሽ በእጅጉ መቆጠብን በአጽህኖት ወቅቱ ዬጠይቃል። ስክነት የተጠናወታቸው ዕሳቤዎች ሁሉ ጥንቃቄ እርስታቸው ሊሆን ይገባል። ከዛ ማህበረሰብ የተፈጠሩትም ቢሆን ጠብተው ላደጉት ጡት ደጀን መሆን ይገባቸዋል። በግራ – ቀኝ ቋያ ላይ ለሚገኝ ማህረሰብ ተጨማሪ ውጋት መሆን አይገባም። ልብን፣ እትብትን፤ ማህፀን በማስተዋል ማድመጥ ይገባል። በሳት ጨዋታ የለም። የግል ክብርና ዝና አላፊ ነው። ትውልድና ታሪክ ግን ቀጣይ ነው። በዚህ ዙሪያ – ገባው ጨለማ በሆነበት ዘመን „ምሳሩ አልጠበቀም፤ ክፍተት አለበት፤ ደህና አድርገህ ቸንክርልን ብሎ ማወጅ“ ርህርህናን የመወጋት ያህል ነው። የህዝብን ተነቃቂነት በብርድ ምች ያሳቅቃል። የተሳትፎውንም አድማስ መንፈስ ያሸማቅቃል። ጎንደር መሬት ከተሆነ ታላቁን ብሂሉን „ሙያ በልብን“ ልብ ማለትን ይጠይቃል። „የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል“ እንዲሉ።

የብዕር መኸር ክወና።

ክቡር ፕ / መስፍን ወልደ ማርያም … የዋሽንግቱ ጉባኤም እኮ አንድ አውራ ህብረ ብሄራዊ ፖርቲ ከሦስት የዞግ ድርጅቶች ጋር በሚያስማማው ጉዳይ ብቻ አቅሙን በወልዮሽ ለመጠቀም ነበር ስምምነት ያደረገው። ችሎታው ከኖረ ስለምን እንደ አትላንታውና እንደ ሲያትሉ ጉባኤ አላብጠለጠሉትም? ለእርሰው መንፈስ የክትና የዘወትር ኢትዮዽያዊነት አለን ወይንስ ድፍረት እንደኛው ተሰደደ? ለነገሩ በፖለቲካ ወይንም የሲቢክሳ ድርጅቶት ያሉ የአማራ ልጆች በዬተደራጅበት የግል ነፃነታቸውን ማስከበር የቻሉም አይመስለኝም። ቅድመ አትላንታ ጉባኤ ምጥ እንደ ተያዘ ሰው ቃለ ምልልሱ ጥድፊያ ላይ ነበር። ለሲያትሉ ጉባኤ ግን ጭንቅ አልነበረም። ዬትም አይደርስም ነው። በለንደኑ ጉባኤም ሆነ በአትላንታው ጉባኤ ላይ አልተመቸንም ያሉ ወገኖች ብዙ ጽፈዋል። ግን በጸሐፊዎች የብራና ሰሌዳ ላይ የአንድም የኦሮሞ ማህበረሰብ የፖለቲካ ድርጅት አርማ ተለጥፎ አላዬሁም። „አማራ መደራጀት“ የለበትም በሚሉ ጸሐፍት ግን ልጅ – እግሩ የአማራ ድርጅት ቅስም በሚሰብር ሁኔታ የሁሉም አርማዎች ተለጥፈው አይቻለሁ። ዬጸሐፍት አለመሆኑን ግን አረጋግጫለሁ። ምክንዬቱም ሌላ ቦታ ሌጣውን ወይንም ብሄራዊነትን የሚያክበር ነገር ነበር ያዬሁት። እርግጥ በኋላ ላይ ተስተካክሎ አይቻለሁ። ሥህተትን ማረም መልካም ነገር ነው፣ ሊበረታታም ይገባዋል። ሰሞኑን ወያኔ አዲስ ካቢኔ ውስጥ ወደ ዘጠኝ የሚጠጉ የኦሮሞ ወገኖቼን ሲሾም አማራ ግን የለም።ስለምን? ዬት ይደርሳሉ ነው ነገሩ። „ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ።“ በጠላት ወረዳም ይሁን በወገን ወረዳ ያሉ የአማራ ልጆች እራሳቸውን ሸሽተው ስለሚኖሩ ንቀት እንዲነግስ ዕድሉን ሰጥተውታል። የወላጅ እናታቸውን ማህፀን ሆነ የአባታቸውን አብራክ ከሰው ሠራሹ ማንፌስቶ በታቻ አንገቱን እንዲደፈ በይነውበታል። የወላጅ እናታቸውን ጡት እረግጠውታል። የወላጅ እናት ዕንባ ደግሞ እዮርን ያንኳኳል። የኦሮሞ ልጆች ግን በሁሉም ቦታ ቁልፋን ይረከባሉ። እራሳቸውንም የእናታቸውንም ጡት የክብር ተክሊል በዬትኛውም ሁኔታ አሰርተውለታል። ማርከሻ ናቸው። ኩራት። (proud und Stolz) የሆነ ሆኖ እስከ ዛሬ ይታይ፣ ጅምር ነው እያልን እንደቆዬነው ለሁለቱ ታላላቅ ማህበረሰቦች ውጥንም ለሌላው የሰጠነው ዕድል ሊነፈግ አይገባም። ሽበቱ የዕውነት ሽበት ከሆነ።

ሌላው ግን በአብዛኛው ኢትዮዽያዊ የታቦትነት ማዕረግ የተሰጣቸው ታላቅ ሙሁር ያሉበት ህይወትን ከሳቸው በላይ የሚውቀው የለም። የፋሽስት ሥርዓቱ ለአንድ ሰውን ማዕከሉ ያደረገ (ጎንደርም አማራም ዬሌለበት ቢሆንም) ከተመቸዎት እሰዬው ነው። „ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው“ ይባል የለ።

ዬማከብረዎት፦ ዕውነት ቤቷ ህዝብ እንጂ ፕሮፖጋንዳ አይደለም። ዕውነት ዕልፍኟ ህሊና እንጂ ሰው ሠራሽ ማኒፌስቶ አይደለም።ህዝባዊ ማዕበሉ ከሰማይ የጠበቁት መና ሳይሆን መሬት የያዘ የሃቅ ዕንቁ ነው። ከዚህ በላይ አንገብጋቢ ጉዳይ የለም። ሊኖርም አይችልም። ስለዚህም ውስጣቸውን ያገኙት ልጆቹ ለዕንባው ዘብ እንዲቆሙ ግድ ይላቸዋል።

ክቡር ፕ/ መስፍን ወልደማርያም የውጬ የወገን ተቆርቋሪነት መሠረቱ ይህ የምልዐቱ ድምፅ ነው። „በባዶ ሜዳ“ አለመሆኑን  ምን አልባት ሥራ በዝቶቦዎት ካላዳመጡት እንሆ  — በአክብሮት። የዕውነት አሮጌ ሆነ ልዋጭም የለውም። ዕውነት ቅልብጭ ያለ ጉልህ አመክንዮ ነው። የሚታይ፣ የሚጨበጥና የሚዳሰስ። ዕውነት የምናብ ህልም ሰሌዳ ደንገጡር አይደለም። እውነት ብርኃን ነው። የአደባባይ ሚስጢርም።።

ምርኩዝ

የጎንደር አብዮት ዋዜማ – ሩህ። ጉልላት።

https://www.youtube.com/watch?v=DUWkqaWdj2w

„የፈራ ይመለስ ጎንደር ጥምቀት በአል አከበረች Gonder protest YEFERA YEMELES“

https://www.youtube.com/watch?v=tDA2amRLpxY

ገድለኛው የጎንደር አብዮት የአማራ ተጋድሎ የአልገዛም – ፀሐይ።

https://www.youtube.com/watch?v=ERwU7NNu7J4

ልጁን የገበረበት የአማራ ተጋድሎ ብረት ክንድ የበላይ መንፈስ ልዕልና። እጨጌ ።

ፍትህን ያለመ ድንቅ ቅኔ ዘ -ጉባኤ።

https://www.youtube.com/watch?v=5DRf6OBkxE0

„በጎንደሩ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነበበ አስገራሚ ግጥም“

 ገድለኛው የግንጫ አብዮትና ህዝባዊ አዝመራው። ዕንቁ።

https://www.youtube.com/watch?v=NQEbZGps6Cc

“Oromo Students protest – As it happened in various parts of Oromia”

የብሩህ ተስፋ ማህደር። ርትህን —- https://www.youtube.com/watch?v=5DRf6OBkxE0

https://www.youtube.com/watch?v=5DRf6OBkxE0

ዬናፈቀ።

https://www.youtube.com/watch?v=kc1UT9SDoqk

“Oromo Protesters’ funeral processions turn into protest Satenaw Latest Ethiopian News & Br”

የበቃኝ ትንታግቀንዲል።

https://www.youtube.com/watch?v=nZFYlFqZryA

„Oromo Irecha Protest በኢሬቻ በአል ላይ የተገድሉትን ሰዎች ቁጥር መንግስት ለማቅረብ አልፈለገም። Oct 2016 Low, 360p”

….. ምን ያህል እንደተጓዝኩ አላውቀውም።

ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም።

አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ነገረኝ።

ተስፋን እጠብቃለሁ፤ የራዕዬ ሐሤት ነውና። ማዕዶቴ።

አምላኬ ሆይ! እምዬን ኢትዮጵያ ሀገሬን ጠብቅልኝ።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ደህና ሰንብቱ። መሸቢያ ጊዜ።