ኢትዮጲያ፤ የሚያድንሽ የልጆችሽ አንድነትና ትብብር ብቻ ነው (ከሙሉቀን ገበየው)

ከሙሉቀን ገበየው

በሓሳብ ምናብ ከሩቅ ከሚፍላቀለቁ ከዋክብት መሃል  በፍጥነት ተጉዘን ወደኛይቱ ሶላር ሲስትም እንክነፍና ወደ ውቧ ሰማያዊ ፈርጥ ፕላኔታችን  መሬት እንዝለቅና  የሰው ልጆች  እናት ወድሆነችው የድንቅንሽ (ሉሲ) ምድር እንውርድ።

በውብ ግርማ ሞገስ በተለባሱ የሰሜን ተራሮች  ተከባ፣ በደንከል ትኩስ አስተ-ጎምራ ተሸልማ፣ በኦጋዴን በርሃ ዘና ብላ፣ በአባይ ሽለቆ  ፈታ ብላ ወዳለቸው  ምድር ኢትዮጲያ። ከ3000 አመታት በላይ በባእዳን ያለተገዛች፣ ነጻ የሆነ ህዝብ የኖረባት አገር፣ ኮሎኒያንዝምን ድል ያደረገ ታላቅ  ህዝብ የኖርባት ምድር።

ጥንታዊ ግብጻውያን በታሪክ ድርሳናት የዘገብዋት፤ የጥንት ግሪኮች፣ ሮምውያን፣ የፋርስ ታሪክ አዋቂውች የጻፉላት ሃገርና ህዝብ። የመጀመሪያዊቹ ክርስቲያን ፣እስላምና አይሁዳያን የኖሩባት የታላልቅ ነግስታት ምድር። የአክሱም፣ላሊበላ፣ የሃ፣ ጎንደር ፍሲለድስ፣ የሓረር ግንብና ሌሎችንም የታሪክ አሽራና የታላቅ ስልጣኔ ምስክር ምድርና ህዝብ። በታላላቆቹ ቅዱሳን መጻሃፍት (መጽሃፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁራን) የተወሳች ሀገርና ህዝብ። በባርነት ብዝበዛና በቀኝ አገዛዝ  ስር ለማቀቁ ህዝቦች  የነጻነት ተስፋና ቀንዲል የነበርች አገርና ህዝብ። ስንቱ የአልም ህዝብ፡ በታሪኳ፣በስልጣኔዋ፣ በባህሏ፣ በደግነቷና በህዝብዋ ሃገር ፍቅርና አርበኝነት የሚቅኑባት አገርና ህዝብ።

ይህቺ ወብ አገርና ድንቅ ህዝብ፡ በሚያሳዝን ሁኔታ  ባለፉት ቅርብ አመታት ግን የስልጣኔና የታሪክን ቁልቁልት እየውርዱ ይግኛሉ። እንሆ አለም፡ ሁሉ በሚያሳፈር ሁኔታ  በረሃብና እርዛት፣ በድርቅና ቸነፈር፣ በርስ በርስ ጦርነትና አምባገነንት እንዲሁም የአልም ከፋት ሁሉ የነገሰባት አገር አድርጎ  ያያታል። አሁንም ድርስ ከውጭ ወረራ ነጻ ምድር ብትሆንም ከራሷ በፈለቁ ጥቂት ልጆቿዋ ፡ ታርኳን፤ ስላጣኔውዋን፣ ሀይማኖትዋን፤ ባህልዋን  ታላቅነትዋን ክደው  እላይዋ ላይ ተፈናጠዋል። እነዚ ልጆቿ ስግብግብ ፣ ለራስ ብቻ አሳቢ፣ በወንድምና እህቶቻቸው ላይ  ክፉና ጠላት  ሆነውባቸዋል። ምድሪቷም የለቅሶ፣ የዋይታና የሞት ምድርም እይሆነች ነው። ወጣቶች የሚገደሉባት፤ እናቶች አምርረው የሚያለቅሱባት ምድር ሆናለች።

ልጆቿ ታሪካቸውንና አሁን ያሉበትን ሁኔታ ላለማየትና ላለመስማት  አይንና ጆሮቻቸውን አወቀው ዘግተወታል። በ ራስ በመውደድና በጠባብ ሃስብ ተይዘዋል። እርስ በራስም ሊጠፋፉም ተዘጋጅተዋል። በመካከላቸው ያለውን ፍቅር አርቀዋል። በብልጣብልጥ ራስ መወደድ አባዜቸውና በታሪካዊ ጠላቶቻቸው ሴራ ታውርዋል።

ይህቺ ታላቅ አገር መስቀልኛ መንግድ ላይ ናት። ኢትዮጲውያን የራሳቸውን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሱንበት ታርካዊ ወቅት ላይ ናቸው።  አንድነትና ተባብሮ መስራት ብቻ ነው አገራቸውንም እራሳቸውንም  የሚያድንና ወደ ታላቅነት የሚወስዳቸው መንገድ።  የተደገሰላቸው እጣ ፈንታ ትልቅ ነው። ይህን ከሳቱት ግን የሚጠብቃቸው የነበራቸውንና ያላቸውን ሁሉ ማጣት ነው። መንግስት አልባ፣ቤት አልባ፣ምድር አልባና ስደትኞች መሆናቸው ነው።

ኢትዮጲያውያን ወገኖች፣ ጎሳዎችና፣ ቤሄርሰቦች ሆይ፤  አይኖቻችሁና ጆርውቻችሁን ክፈቱ። እንደ ቅን ሰውና መልካም ኢትዮጲያዊ አስቡ።ጠባብ ቤሄርተኝነትና  ትምክህተኝነት ፈጽሞ አይጠቅምም። ከአፋፈ ላይ ቁልቁል ለመውርድ እየተዘጋጃችሁ ነው። አገራችሁናና እራስችሁን የሚያድነው ህብረትና ተባብሮ መስራት ብቻ ነው።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s