የመከነው የተሐድሶ ተስፋ!

( ከኦህዴድ ሰማይ ስር ዶፍ ጥሎ እዛው ኦሄዴድ ምድር ላይ ያባራው የኢህአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ)

ኢህአዴግ በዘጠኝ የገዛውን በዘጠኝ የመሸጥ ትርፍ አልባ ወከባ ብርቁ አይደለም በዘጠኝ የገዙትን በዘጠኝ መሸጥ ማለት በዋና ከመውጣጥ ስሌት ጋር ሲነጻጸር ፍጹም የሚለያይ የለየለት ትልቅ ኪሳራ ነው፤ ገንዘብ፣ … ጉልበት፣ጊዜ፣ እምነት፣ሞራል፣ተስፋ፣ጉጉት ወዘተርፈ- ብዙ ነገር ነው በዜሮ የሚባዛው እርግጥ መሪውን አለማመንን ቀለቡ ያደረገ እና፣ በተመሪው አለመታመንም ገንዘቡ የሆነ ህዝብ እና ፓርቲ ያሉበት ሀገር ውስጥ የምንኖር ቢሆንም የአሁኑ ግን ከመገረም በላይ የሆነ የተስፋ ማጣት መገረም ውስጥ እንድገባ ብቻ ሳይሆን በኢህአዴግም ተስፋ እንድቆርጥ አድርጎኛል::“ …በጥልቀት እንታደሳለን !” የሚለው የገዥው ፓርቲ ጮክ ያለ ፉከራ እና ፓርቲውን የመሰረቱት የአራቱም ተዋቃሪ ፓርቲ ፖለቲከኞች በየአቅጣጫው ለጥልቁ ተሀድሶ ጉባኤ ከመዘርጋታቸው ጋር ተያይዞ ተስፋ በራቃት ነፍሳቸው ላይ የተስፋ ጀምበር የፈነጠቀችባቸው ብዙ ናቸው:: እኔም ብሆን ኢህአዴግን ማመን ቀብሮ ብቻ ሳይሆን መቃብሩ ላይም ቆሞ ነው ከሚሉት ወገን ብሆንም በአሁኑ ሰአት ግን ሀገራችን ካለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ አንጻር ቃሉን ሊያከብር ይችላል የምትል ጭላንጭል ተስፋ ሰንቄ ቀን ስቆጥር ከርሚያለሁ እጅግ የሚያሳዝነው ግን ኢህአዴግ ዛሬም እንደወትሮው ቃሉን ብቻ ሳይሆን ተስፋችንንም “ ” በልቶ ታድሰናል ከሚሉ የህወሀት እና የብአዴን ሚኒስትሮቹ ጋር እንደገና ተመልሷል::በርካታ ለውጥ፣ አዲስ ፊት፣ ትርጉማዊ እና ከልብ የሆነ የሚኒስትሮች ሹም ሽረት፣ ሌላ ተስፋ የሚያስታጥቀን ካቢኔ ይመጣልን ዘንድ በጉጉት ስንማትር ብንቆይም ለዚህ አልታደልንም:: የራቀ ተስፋችንን የሚያቀርብልን እና ባለመሆን ጭጋግ ተጋርዳ ከእውን እይታችን ልትሰወር የደበዘዘች የሳቅ ቀናችንን የሚያጠባልን አንዳች ተአምር ይፈጠራል በሚል ተስፋ ስናደርግ ብንሰነብትም ተስፋ ያደረግነው ተስፋ ሁሉ እንደ እንቧይ ካብ ተንዶ ከሌላ መብሰክሰክ ጋር ተጋብተናል ጥልቁ ተሀድሶ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በኦፒዲኦ ቤት እየሆነ ያለውን ነገር ስመለከት እውነትም ይሄ ነገር ሊጠልቅ ነው የሚል ስሜት ተፈጥሮብኝ የነበረ ቢሆንም መቀሌ እና ባህርዳር ላይ ታጉረው ውሀ ሲወቅጡ የሰነበቱት ህወሀት እና ብአዴን ግን ለስንት በጎ መልክ የናፈቅነውን ተስፋ አይይዙት መንፈስ አድርገውት ጉም አስጨብጠውን አዲስ አበባ ተመልሰዋል::

 

ethiopia_cabinet-810x540
ኦህዴድ ተሀድሶውን በጀመረበት አፍታ የድርጅቱን ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀ መንበር በማስወገድ በተስፋ፣ በጉጉት እና ሌሎችስ ዘንድ ምን ይፈጠር ይሆን በሚል ናፍቆት አስጀምሮን ስድስት ሚኒስትሮቹን ሳይቀር በሌሎች እንዲተኩ በማድረግ ተሀድሶውን ሲያጠናቅቅ በሌሎቹ ቤት ግን ከህዝብ ጋር ሲደረግ የኖረው የድብብቆሽ እና የማስመሰሉ አኩኩሉ አሁንም ቀጥሎ የብአዴን እና የህወሀት በዘጠኝ ገዝቶ በዘጠኝ የመሸጥ ትርፍ አልባ አባዜ ከአዲስ ነገር እንዳፋታን ለስንት የተጠበቀው ተሀድሶ በተለባብሶ ተጠናቋል ይህ የአለባብሶ ማረስ የሰነፍ ፍልስፍናቸው በአረም መልሷቸው እንደገና ሱሪ ባንገትን ሲያስተርታቸው ለማየት ግን ቀጠሮውን ለጊዜ መተው ሳይኖርብን አይቀርም ኦህዴድ ካሉት ዘጠኝ ሚኒስትሮች ውስጥ ስድስቱ ተነስተው የቀሩትም ቢሆኑ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ተዘዋውረው እንዲሰሩ ሲያደርግ፤ ሌሎች እህቶቹ ግን ሁሉንም ሊያስብል በሚችል መልኩ የቀድሞ ሚኒስትሮቻቸውን ሰብስበው ሴቶቹን ሌላ ሹሩባ አሰርተው፣ ወንዶቹንም ጺም ጸጉራቸውን አስተካክለው “ እና ላጭተው አይናቸውን በጨው በማጠብ ሌላ እኮ ነን!” ሊሉን ተመልሰው መጥተዋል:: በኦህዴድ ቤት የታየው ተሀድሶ የሚኒስትሮቹ ለውጥ ወይም የውጤታማ ፖለቲከኞቹ ወደ ክልል መሄድ ብቻ ሳይሆን በአካዳሚክ ዳራቸውም አንቱ የተሰኙ እና ከስማቸው ጫፍ ላይ ዶክተር እና ፕሮፌሰር የሚሉ ማእረጎችን ያስቀደሙ ምሁራንንም አሳይቶን የህወሀት አፈ ቀላጤ እንደሆነ የሚታማው ሪፖርተር ሳይቀር እንዳለው “በከፊልም ቢሆን ሹመት በብቃትን እንድናስተዛዝል ያደረገን ኦህዴድ ብቻ ሆኖ ተሀድሶው!” አልቋል22 ለስንት ነገር የጠበቅነው የኢህአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ ግን በህወሀት እና በብአዴን ልፍስፍስ አካሄዶች ሳብያ የኦህዴድ ብርቱ ጥረት ላይም ጥቁር ጥላውን በማጥላት የነገረ ስራውን አጠቃላይ ሂደት ግማሽ ልጮ ግማሽ ቁንጮ አድርጎት ሌላ ስጋት ላይ ጥሎናል22 ለመታደስ ቃል ገብቶ ከነ ጭራሹ መከርከስ እያሳቀ የሚያስለቅስ አጉል ፌዝ ቢሆንም እነ እገሌ ኮከብ ሚኒስትሮች እንደነበሩ ቢረጋገጥም በሚኒስትርነት አላካተትናቸውም አይነት ቧልታይ ጫወታ ለመተወን መሞከር ግን ትርፉ ትዝብት ነው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን የመሩት አቶ አብይ አህመድ፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር የነበሩት ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱን ከነዚህ ውስጥ ስማቸው ተነስቷል ኮከቦችን ያጨለመው የኢህአዴግ ጥልቅ ተሀድሶ የሞሸርናትን ተስፋ አደብዝዞ ከሌላ ቀቢጸ ተስፋ ጋር አፋጦን አልፏል::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s