“ለአማራ ህዝብ  የአማራ ተጋድሎ ጥሪ” !!!  የተጋድሎው መሪወችም በተግሉ ሜዳ የሚገኙ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆች ናቸው!!!

 

amhara

አማራነትን መስበክ ሀጢያት ወይም ወንጀል አይደለም፣ አማራነትን መስበክ በወያኔ የጎጥ ፓለቲካ ቋት ውስጥ ገብቶ ዘረኝነትን ማቀንቀንም አይደለም፣ ከሁሉም በላይ አማራነት ነፃነትና ኢትዮጵያዊነት የነፃነት እምነት ነው። ። አማራ ኩሩና አትንኩኝ ባይ ህዝብ ነው፣ አማራ አኩሪ በህልና ወግ ያለው፣ይሉኝታና ውለታን የሚያውቅ፣እንግዳ ተቀባይ ፣ሰው አክባሪ ፣ካልነኩት የማይነካ በሀገሩና በድንበሩ ቀልድና ይቅረታ የማያውቅ፣ በፍቅር እንጂ በጥላቻ ሽንፈትን የማይቀበል፣ የራሱን የማይሰጥ የሰው የማይመኝ፣ የማይነካ ለሀገሩና ለሀይማኖቱ ቀናኢ የሆነና ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ህዝብ ነው። አማራ ማስመሰል የማያውቅ ፍቅርና ጠላቱን ፊትለፊት የመግለፅ ድፍረት ያለው ህዝብ ነው።

ለጠላቱ ኮሶ ለወዳጁ፣ቅን የሆነ ቅን ህዝብ ነው። አማራ የለም ሲባል የሚኖር አለቀ ሲሉት የሚበዛ፣ ጥላቻን በፍቅር የሚገዛ፣ ለወዳጆቹ ጋሻና መከታ፣ ለጠላቶቹ ፍም እሳት ረመጥ፣ የጋለ የብረት አሎሎ የሆነ ለጠላቱ የማይጨበጥ ህዝብ ነው። አማራ በአማራነቱ ይሰባሰብ፣ የአማራ ተጋድሎ ይደራጅ ፣ይታጠቅ ስንል በአማራነቱ ብቻ ተለይቶ “ኢትዮጵያ ወይም ሞት! “በሚል ጽኑ ታሪካዊ አ ቋሙ እንደ እብድ ውሻ ተደብድቦ ከሚደርስበት የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ፍጅት እራሱ መከላከል እንዲችል ለማስቻል እንጂ ፣የአማራን ኢትዮጵያዊነት ጥያቄ ላይ ጥሎ የወያኔን የጎሳ ፓለቲካ ለማቀንቀን አይደለም። አበው ” እሾህን በእሾህ ” እንደሚሉት ወያኔን በቆፈረው ጉርጓድ ውስጥ ለመቅበር በመረጠው የትግል ስልት በአማራ ተጋድሎ መጋፈጥ የግድ ይላል። ወያኔ ለዚህ እኩይ ተግባሩ” አማራ ቀንዳምና ጅራታም ተናካሽ አውሬ ነው፣ አማራ ከምድረገፅ መጥፋት ያለበት ታሪካዊ ጠላታችሁ ነው ” እያለ ቀስቅሶ በፀረ አማራ ትግሬውን ከጎኑ እንዲሰለፍ ያደረገው በኢትዮጵያዊነት ሰሜት ሳይሆን በትግሬነቱ በዘረኝነት መንፈስ በመቀስቀስ ነው። አማራ በአማራነቱ ብቻ በእሳት ተቃጥሏል።

በጥይት ተገድሏል፣ ከገደል ተጥሏል፣ የዘር ፍጅት ደርሶበታል፣ተፈናቅሏል ተሰዷል፣ታስሯል፣ ተዋልዶ ዘሩን እንዳይተካ መካን ተደርጓል፣ ተዋረዷል ተንቋል፣ ይሄ ሁሉ ሲሆን አይዞህ አለንልህ ብሎ ሊታደገው የሞከረ ማንም የለም። ሁሉም በየጎጡ ተደራጅቶ የጋራ ጠላቱን በጋራ ሲከላከል፣ አማራ ግን በኢትዮጵታዊነት ፀንቶ በጎሳ ከረጢት ውስጥ ሳይገባ እስካሁን የሚደርስበትን ግፍና ሰቆቃ ችሎ ቆይቷል ፣ አሁን ግን የግፉ ዋንጫ ሞልቶ ስለፈሰሰ አምርሮ እምቢ! ብሎ የአማራ ተጋድሎ ተነስቷል።አማራ በተለያዩ ክልሎች በግፍ የተጨፈጨፈው አማራ በመሆን ወንጀል ነው!ጎጃሜ፣ወሎዬ ፣ሸዌ ጎንደሬ እየተባለ ሳይሆን አማራ ተብሎ ብቻ ስለሆነ የተጀመረው ፀረ ወያኔ እራስንንና ሀገርን የመከላከል ትግል በድል ወደፊት መራመድ ካለበት በየትኛውም የሀገሪቱ ኢትዮጵያ ና በውጭ የሚኖር አማራ ለአማራ ተጋድሎ ጥሪ በአንድላይ መቆም አለበት፣ ሁለትና ሶስት አይነት አማራ የለም የትም ይኑርየትም አማራ ሁሉ አንድ ነው፣”አማራ “!!!

አንድነት ሀይል ነው፣ ማንም ወደደ ጠላ በአማራነቱ ይሰባሰባል፣የአማራ ተጋድሎ ይደራጃል፣ ይታጠቃል ፣ ሊየጠፉት የተነሱበትን ጠላቶቹን እንደ አማራ ተደራጅቶ ፊትለፊት ይጋፈጣቸዋል። ስለዚህ በዚህ ትግል ” በመረጠው ዳኛ የሚረታና በቆረጠው ዱላ የሚመታ” ማን ሊሆን እንደሚችል እየቆየን እናያለን። እስካሁን ባለው ሁኔታ በመላው ኢትዮጵያ አማራውን ጨርሶ ለማጥፋት እየተደረገ ያለው የዘር ፍጅት አማራ በመሆኑ ብቻ እንጂ ወሎዬ ፣ጎጃሜ፣ ጎንደሬ ሸዌ በመሆኑ አይደለም። ሰለዚህ የትም ይወለድ የትም ይኑር አማራ አማራ ስለሆነ ጎንደሬ ፣ጎጃሜ፣ ወሎዬ፣ሸዌ እየተባለ በጎጥና በመንደር የሚደረገው መሰባሰብ የተባበረውን የአማራ ህዝብ ትግል የሚያኮሰምን ከመሆኑም በላይ ለተናጠል ጥቃት የሚያጋልጥ ነው። የዚህ አይነቱ የአማራ ልጆች መከፋፈል ደግሞ የሚጠቅመው ወያኔን ብቻ ነው።

ይህ የገባንበት የአማራ ተጋድሎ የአልሞት ባይ ተጋዳይነት ትግል ወያኔን ለመከላከልና መልሶም ለማጥቃት የመረጥነው የአማራ ተጋድሎ ታክቲክና አስትራቴጂ ወደንና ፈልገን የገባንበት የትግል ስልት ” እሾክን ነእሾክ” በሚባለው አማራዊ ስልት ነው።ስለሆነም የተጀመረው ፀረ ወያኔ እራስንንና ሀገርን የመከላከል ትግል በድል ወደፊት መራመድ ካለበት በየትኛውም የአ ለም ክፋ ል የሚኖር አማራ በአንድላይ መቆም አለበት፣ወያኔ ያለርህራሄ እየገደለ እያሰረና እያሰቃየ ሥልጣኑን ለማቆየት በሚያደርገው ጥረት እስካሁን ከሆነው የወደፊቱ ሊከፋ እንደሚችል በጉልህ እየታየ ባለበት በዚህ ወቅት በተቃውሞው ጎራ ወቅቱን የሚመጥን -ራሱን በራሱ አደራጅቶ የአማራ ተጋድሎ ነጻነት ወይንም ሞት ብሎ በጀመረው ትግል መስዋእትነት እየከፈለ ባለበት፣ስለ ነገ መታሰብ ስለ ነገም ተጨንቆ መስራት መነታረኩን ትተን ፤አደጋን በቀነሰ ሁኔታ ወያኔን ማስወገድእያደረሰ ያለውን አደጋ በመከላከልና ትግሉን በማጠናከር ለድል የሚበቃበትን ስራ ለመስራት ሁለትና ሶስት አይነት አማራ የለም የትም ይኑር አማራ ሁሉ አንድ ነው፣ አንድነት ሀይል ነው፣ ወያኔ የሚንበረከከውና ቅስሙ የሚሰበረውም አንድ ሁነን በአማራ ተጋድሎ ሲያየን ነው፣ ሂዩመን ራይት አክቲቪስቶችና ሶሻል ሚዲያዎችም መፃፍና መናገር ካለባቸው አንድና አንድ ስለሆነው የአማራ ተጋድሎ ብቻ ነው። እንደዚያ ሲሆን የኛ ጡንቻ ሲፈረጥም የወያኔ ይላላል፣ የኛ ምሽግ ሲገነባ የወያኔ የውሸት ካብ ይፈርሳል፣ መተባበሩ ግድ ነው።

ይህ የአማራ ተጋድሎ ትግል የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ትግል ነው። ይህ ትግል የዛሬ ነው።ይህ ትግል በሀገራዊ ራዕይና ተልዕኮ በመሳተፍ ከያንዳንዳችን የሚጠብቀው አስተዋፅዖ አለ። በርግጥ የሀገራችን የኢትዮጵያ ታጋዮች ያሉት በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ዛሬ ከፍተኛውን መስዋዕትነት በመክፈል፤ከስህተት ወደ ጥፋት ከተሸጋገረው የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት /ከህወሃት ወያኔ ሰዎችና የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሌት ተቀን በኑሯቸው እየተገደዱ፣ እየተሰቃዩ፣ በእስር ቤት እየተንገላቱ፣ እየተቀሙ፣ ግፍና የበደል በደል ለማስቆም የተጋድሎው መሪወችም በተግሉ ሜዳ የሚገኙ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆ ች ናቸው !!! በኢትዮጵያዊነት ትውፊት ለኢትዮጵያ ያሉት የአማራ ተጋድሎ ታጋይ ልጆች ናቸው የሕዝብ ጠላቶች መወገድ መሠረታዊ ስለሆነ፤ መተባበሩ ግድ ነው።የኢትዮጵያ ጉዳይ፤ ከንብረት፣ ከኑሮ የበለጠ ክብር የምንሠጠው ሰ ን ደ ቅ ነው :: “ለአማራ ተጋድሎ እንተባበር”ሁሉም ዘብ ይቁም በቦታው !!!
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!
ሰልፍ የጀግና ድል የእግዚአብሄር ነው።
ገብርኤል ብዙነህ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s