ከአሜሪካኖቹ ምርጫ አንድ ነገር ብቻ መማር በቂ ነዉ

ሸንቁጥ አየለ

አሜሪካኖቹ የተዋጣለት ስርዓአት እና ተቋም በመገንባታቸዉ ብቻ የተለያዩ ዉስብስብ እና አስቸጋሪ አስተሳሰቦችን እና እይታዎችን ይዘዉ የሚመጡ ፖለቲከኞችን ማስተናገድ የሚችል ሁኔታን ብሎም አሜሪካ እንደ ሀገር የምትቀጥልበትን ጥልቅ መሰረት ጥለዋል::ለምርጫ ሲወዳደሩ ያለዉ ሂደት: ምርጫዉ ሲጠናቀቅ የሚያሳዩት የሰለጠነ ባህሪ እና የስልጣን ሽግግሩ አስደማሚ ሂደት ሁሉ የአንድ ነገር ዉጤት ነዉ::ስርዓአት እና ተቋም በመገንባታቸዉ::
hillary_trump7
እናም ከነዚህ ህዝቦች ምርጫ አንድ ነገር ብቻ መማር በቂ ነዉ:: እንደተባለዉም እንዴት የተዋጣለት ስርዓአት እና ተቋም በመገንባት የማይናወጥ ሀገራዊ መሰረት ላይ ማስቀመጥ እንደሚቻል ማንሰላሰል::

ይህችን ጽሁፍ እያዘጋጀሁ ትናንት እና ከአንድ ወዳጄ የሰማኋት የበሰለች ነገር ትዝ አለችኝ:: እናም ከአሜሪካኖቹ ምርጫ ምን መማር እንዳለብን ብዙ ለመጻፍ የተነሳሁት ሰዉዬ ልቤም እጄም ብዙ ለመጻፍ አልታዘዝም አሉኝ::ይሄ ወዳጄ ካንድ ጓደኛዉ ጋር ከአሜሪካ ምርጫ ኢትዮጵያዉያን ምን እንደሚቀስሙ ይወያያሉ::

የወዳጄ ጓደኛም “ኢትዮጵያዉያን ከአሜሪካ ምርጫ ብዙ ሊማሩት የሚገባ ነገር አለ” ብሎ ለወዳጄ ሰፋ አድርጎ ያብራራለት ይጀምራል::ወዳጄም በአጭሩ “ኢትዮጵያዉያን በኢትዮጵያ ህልዉና ላይ ገና ሳይስማሙ ስለምርጫ ምን ሊማሩ ይችላሉ?” የሚል ጥያቄን ለጓደኛዉ ያቀርባል::

እናም ይሄ ወዳጄ ያነሳዉ ጥልቅ ሀሳብ እዉነት ነዉ እና እኛ ኢትዮጵያዉያን ከሜሪካኖቹ የምርጫ ሂደት የምንማረዉ አንድም ነገር ላይኖር ነዉ ማለት ነዉ? ብዬ ሀሳብ ማንሳት እና መጣል ጀመርኩ:: በርካታ ፖለቲከኞች በአሁኑ ወቅት ከግራም ከቀኝም ከፊትም ከኋላም ኢትዮጵያ ስትፈርስ ነዉ ለብሄራችን ምቹ ሁኔታ የሚፈጠረዉ የሚል የደናቁርት ጩህት እየጮሁ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነዉ:: እነዚህ በክፋት: በጥላቻ እና በአላዋቂነት የታነቁ ፖለቲከኞች ነገርን ሳስብ ነገሬን በአጭር ሸከንኳት::

ኢትዮጵያዉያን ፖለቲከኞች በኢትዮጵያ የመኖር ህልዉና ላይ ላለመስማማት እየሄዱበት ያለዉ የተጠናገረ ሀሳብ ስለ ዲሞክራሲ ለመወያዬት ያለዉ እድል ብዙ እሩቅ መሆኑን በከፊል የሚያስረዳ ነዉና ከዲሞክራት ሀገር ዲሞክራሲአዊ ስርዓአት አበጃጀትን እና ተቋማት አፈጣጠርን ቅሰሙ ብሎ መስበክ ከፊል ኮሜዲ ነዉ የሚመስለዉ::ሆኖም እንደሰዉ ልጅ ደግሞ ሰዉ የመማር ሂደት ዉጤት ነዉ እና ሙሉ ለሙሉ ተስፋ መቁረጥ አይገባም::

የሆነ ሆኖ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያዉያን ፖለቲከኞች ትራምፕ ወይም ሂላሪ ስለማሸነፏ ሰፋፊ ትንታኔ ከሚሰጡ ይልቅ ይሄን የአሜሪካዉያንን መሰረት ላይ የቆመ የዲሞክራሲ ስርዓአት እና የተቋም ግንባታ ሂደት እንዴት መቅሰም እንደሚቻል ቢመክሩበት መልካም ነዉ::

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s