(ሰበር ዜና) ዛሬ ሌሊት የአማራ ታጋዮች በሳንጃ የወያኔ ካምፕን ገንጥለው በመግባት እርምጃ ወሰዱ – በርካቶች ወታደሮችን ገድለው የጦር መሳሪያ ወስደው ተሰወሩ


(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር የአማራ ተጋድሎ ታጋዮች ከትግራዩ ነጻ አውጪ ወታደሮች ጋር የሚያደርጉትን ትንቅንቅ አሁንም እንደቀጠሉ ባሉበት በዚህ ሰዓት ዛሬ ለሊት ለእሁድ አጥቢያ (ሕዳር 4, 2016) የአማራ ተጋድሎ ታጋዮች ሰሜን ጎንደር ሳንጃ የሚገኘው የወያኔ ካምፕ ላይ ጥቃት አድርሰው በርካታ የወያኔ ወታደሮች መግደላቸው ተሰማ::

ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ (ሕዳር 4, 2016) ሌሊት ታጋዮቹ ሳንጃ የሚገኘውን የትግራይ ነጻ አውጪ ካምፕ ወረው በወታደሮች ላይ እርምጃ የወሰዱ ሲሆን በዚሁ ካምፕ ውስጥ የነበሩ የጦር መሳሪያዎችን ወስደው መስወራቸው ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጠቁሟል::

በዚህ ጥቃት የሞቱ የትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ቁጥር ለጊዜው ባይታወቅም በርካታ እንደሆኑ ምንጮቻችን ተናግረዋል::

በሳንጃ የአማራ ተጋድሎ ታጋይዮች መሳሪያዎችን ይዘው መሰወራቸው ያስደነገጠው መንግስት በአሁኑ ወቅት ከነርሱ ጋር ተፋጦ ይገኛል:: እንደ ምንጮች ገለጻ የአማራው ሕዝብ ተከዜ የሚገኘው የአማራ ድንበር ድረስ እስካልደረስንና ማንነታችንን ካልስከበርን አንመለስም በሚል ቆርጦ ለትግል ተነስቷል::
(ሰበር ዜና) ዛሬ ሌሊት የአማራ ታጋዮች በሳንጃ የወያኔ ካምፕን ገንጥለው በመግባት እርምጃ ወሰዱ – በርካቶች ወታደሮችን ገድለው የጦር መሳሪያ ወስደው ተሰወሩ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s