“ለነጻነታችን መኪናችንን ሸጠን፤ ሃብታችንን ጥለን ነው በርሃ ገብተን እየታገልን ያለነው” – የአማራ ታጋዮች በወልቃይት

amhg

ሰለሞን ቦጋለ ዘአማራ

ወልቃይት ብረሳሽ ቀኘ ትርሣኝ ፣አማራነት ደም ነው! አማራ ክብር ነው! በማለታቸው TPLF/EPRDF እያሣደዳቸው የሚገኙ ገንዘብ ሃብትና ንብረት አንገታቸው ድረስ ያላቸው የሞላቸው የደላቸው ሶስት አራት የትራንስፓርት እና የጭነት መኪና ያላቸው፣ በእግር ሣይሆን በመኪናቸው ጎንደርና ባህርዳር የተንፈላሠሡ፣ ሆቴል የንግድ ድርጅት ያላቸው በእርሻ ስራ የተሠማሩ የእለት ከእለት የንግድ ሥራቸው ሲያንቀሣቅሱ የነበሩ አርሶ አደሮች ናቸው ነገር ግን ከሁሉም በላይ ክብር ማንነት ስለሚበልጥና በህወሓት /ኢህአዴግ የተቃጣውን ጅምላ ግድያ እስራት ቁመን አናይም ቁመን አንሞትም አሁንም ወልቃይት ብረሳሽ ቀኘ ትርሣኝ ! ሞት እንኳን ቢደገስ አንፈራም በማለትና ቆሞ ከመሞት እየገደሉ ለመሞት ራሳቸውን ያደራጁ የቆረጡ የወሠኑ የምናውቃቸው ጓደኞቻችን ወገኖቻችን እንደምትመለከቷቸው ራሳቸውን እንዲህ አደራጅተው ከማንም ሳይለጠፉ በራሳቸው በአርማጭሆ በአገራቸው በርሃ ይገኛሉ ።

እነዚህ የአማራ ወጣት እና ገበሬ ናቸው::  አይታቹህ ከሆነ በፌስቡክና በሌሎች ሶሻል ሚድያዎች ውዥንብር ተፈጥሯል:: ይልቅ ችግር ተፈጥሯል:: ለምን ብትሉ እነዚ ንብረታቸውን ትተው ትግሉ ኤርትራ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ምድር ላይ ነው ብለው እየተዋጉ ነው:: ታዲያ ለነዚ ታጋይ ክብር አይሰጣቸውም? ለምን የአማራ ገበሬ አይባሉም? እነሱም የተናገሩት እኛ የአማራ ገበሬ ነን የነፃ።  “ሀይል የተባለ የለም:: እኝ በራሳችን መኪናችን ንብረታችን ሽጠን ነው በርሀ የወረድን እና የነፃነት ሀይል እዳትሉን” ብለዋል – እነዝህ መሪዎች ናቸው:: በሽ የሚቆጠሩ የአማራ ወጣት እና ገበሬ ተቀላቅለዋል ።አማራ መደራጀቱ የተፈለገው እነዚህን ለመርዳት ነው እጅ ሌላ ታስቦ አይደለም አሁንም እመኑኝ አማራው ተደራጅቶ እነዚህን ጀግና ገበሬ ካልረዳን ወያኔ አይወርድም ።

 

ድል ለአማራ ገበሬዎች ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s