በኢንተርኔት ላይ የተጣለው እገዳ ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን ወደማይችሉበት ደረጃ እንደደረሱ መሆኑን የተመድ ወኪሎች ገለጹ

ኢሳት (ኅዳር 9 ፥ 2009)
internetመቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ የተባበሩት መንግስታት ወኪል ድርጅቶች መንግስት በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የጣለው እገዳ ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን ወደማይችሉበት ደረጃ እየወሰዳቸው መሆኑን ገለጡ።
በተለይ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እረዳታ በተጋለጡ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች የእርዳታ አቅርቦትን ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ያሉ ተቋማት አለም አቀፍ ግንኙነት ለማድረግ እና ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳልቻሉ የተመድ የዜና አውታር የሆነው ኢሪን አርብ ዘግቧል።
የኢንተርኔት አገልግሎት በተለይ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መውጣት በኋላ ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱን የሚናገሩት አለም አቀፍ ድርጅቶቹ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመጀመር የተያዙ እቅዶች መዘግየት እንዳጋጠማቸው ለዜና ተቋሙ ገልጸዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የተባበሩት መንግስታት ወኪል ድርጅቶቹ ሃላፊዎች የስልክም ሆነ የኢሜይል መልዕክት ልውውጥ ለማደረግ ባለመቻላቸው ምክንያት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን መቆጣጠርና መከታተል እንዳልቻሉ አስረድተዋል።
ክትትልና ቁጥጥር የማይደረግበት ስራ ደግሞ ግልጽነት የሌለው በመሆኑ አዳዲስ በጀት መመደቡ የማይታሰብ ነው ሲሉ እነዚሁ ሃላፊዎች አክለው ገልጸዋል።
በሃገሪቱ የእርዳታ አቅርቦት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ በርካታ ድርጅቶች ድረገጻቸውን ማስተዳደር ባለመቻላቸው ምክንያት ዘርፉ ብዙ ችግሮችን እያጋጠሟቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
የአሜሪካን ኤምባሲን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ተወካዮች በኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ ማካሄድ እንዳልቻሉ ለመንግስት ቅሬታን ማቅረባቸው ይታወሳል።
ፈቃዳችንን ማደስ የምንፈልግ በመሆኑ ስማችን አይገለጽብን ያሉ አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅት ተወካይ የኢንተርኔት አገልግሎቱ መቋረጥ በተለይ በእርዳታ ማቅረብ ስራ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ በማሳደር ላይ መሆኑን ለኢሪን የዜና አውታር አስረድተዋል።
በርካታ ሰዎች ኢንተርኔት የሰጣቸውን ነጻነትና ዕድል መጠቀም ፍላጎት ቢኖራቸውም መንግስታት ይህንን አማራጭ የመረጃ መንገድ እየዘጉ ይገኛሉ ሲሉ ለቴክኖሎጂው መብት በሚታገለው አክሰስ ናው (Access Now) በተባለ የቴክኖሎጂ ተቋም ተወካይ የሆኑት ደጂ አሉኮቱን ትናግረዋል።
ከቀናት በፊት አመታዊ ሪፖርቱን በዚሁ ጉዳይ ዙርያ ያወጣው ፍሪደም ሃውስ የሰብዓዊ ፣መብት ተሟጋች ድርጅት ኢትዮጵያ በኢንተርኔት አገግሎት ላይ የከፈ አፈናን እና ቁጥጥርን ከሚያካሄዱ ስድስት የአለማችን ሃገራት መካከል መሆኑን ይፋ አድርጓል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s