የማለዳ ወግ …ፈጣሪ በታች እናቴና እናቶች ይመሰገናሉ ![ነቢዩ ሲራክ]

* ቤተሰብ ፤ ጎረቤት ፤ ወዳጅና አዝማዶቸም በእጅጉ ትመሰገናላችሁ !

15107304_10211578255717936_6587443468850424585_nአሜሪካውያን ዛሬን ብሄራዊ የምስጋና ቀንን ዛሬ አድርገው ማክበር ግማሽ ምእተ አመት አገባደዋል ። በገና ዋዜማ በህዳር ወር ሁለተኛ ሳምንት ገደማ የሚከበረውን የምስጋና ቅዱስ ቀን Thanksgiving Day በጎ አስተምሮቱ እየተስፋፋ ከሰሜን አሜሪካ ተሻግሮ ካናዳና አውሮፓው ያጡኑ አልም እየተቀባበለ ቀኑ ማክበር ከያዘም ጊዜው በሀገረ ካናዳየሚከበረዉ ከጀመሩ በአሜሪካ ከገና በዓል የበለጠ የምስጋና Thanksgiving Day ቀን ይከበራል ! በእኛም ሀገር አሜሪካኖች በሚያደርጉት ልክ በዓሉ ባይከበርም ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እየተስፋፉ በመጡበት በዚህ ወቅት ምስጋና የማቅረብ በጎ ልምድ እየተቀሰመና እየተስፋፋ የመጣ ይመስለኛል ! እኔም በህይዎት ዘመኔ በውስጤ ለሚላዎሸው ፍቅር በምስጋናው ቀን ፍቅር አክብሮቴን እገልጽበታለሁና ቀኑን የባህል ውርሱን እዎደዋለሁ !

በዚህ የምስጋና ቀን ከሁሉም አስቀድሜ ሰጥቶ ለማያልቅበት ፤ ሁሉን ማድረግ ለማይሳነው ፤ ለእረኛው አምላክ ፤ ለጠባቂው ንጉስ ፡ምህረትና ቸርነቱ ለማያልቅበት የፍቅር አምላክ ለልኡል እግዚአብሄር አምላክ ምስጋናን አስቀደማለሁ ! ስላደረግክኝ ሁሉ አመሰግንሃለሁ !በህይዎት ዘመኔ ፤ በህይዎቴ ለውጥ ይመጣ ዘንድ በድህነት ጎጇዋ በጥሩ ስነ ምግባርና በሃገር ፍቅር ስሜት ኮትኩቶ ላሳደጉኝ ወላጆቸ ምስጋናዬ ወደር የለውም ! ከፈጣሪ በታች የእናት እንግልት ምስጋና ያንሰዋል ፤ አንባገነን የሀገሬ መንግስት በመጣ በሄደ ቁጥር የልጅ አበባ ፤ የልጅ ጠዋሪ ፤ የልጅ ደጋፊያቸውን በጭካኔ ከጉያቸው የሚነጠቁት የሀገሬ እናቶች ፤ በመጠወሪያ ጊዜያቸው ወህኒ ስንቅ አቀባይ የሆኑ እናቶች ፡ ልጆቻቸው ከነዳፊ አውሬ ሸሽተው በስደት ሲኖሩ ፍቅራቸውን እንዳያዩ የተገደቡት እናቴና እናቶች ይመሰገናሉ !

እናቴ ሆይ ! “ በዚህ የምስጋና ቀን የምታመሰግነውን አንድ ሰው ብቻ ምረጥ ?” ተብዬ ብጠየቅ ምንም ሳላወላውል ለከበደው ምስጋና የምመርጥሽ ክብር ሞገሴን ፣ እናት አድባሬን ፣ እናት ህይዎቴን አንችን ነው … እናት ሁለመናየ ሁነሽ አሳድገሽኛልና የህይዎት ርስቴ ነሽ ፤ ትመሰገኛለሽ ! አንችን እምየን መግለጫ ምስጋና ግን አለኝ አልልም !… ጥልቅ ፍቅርሽን ማሳያ ፣ የገዘፈ ክበርሽን ማመላከቻ ፣ የእናትነት ስስትሽን መለኪያ … አንችን በልክሽ መናገር የሚችል ፣ የሚገልጽ አንደበት አጣሁ … ክበር ለአንች ይገባሻል ከማለት ያለፈ የምለው የለም! በቃ ! አንችን የምገልጽበት ፣ ከዚህ ያለፈ የምስጋና ቃላት አጥቻለሁ !…

እናት አለም ! ምስጋና ዋጋ የሚያስከፍል ሆኖ የከበደው ፍቅርና ምስጋናዬን ገላጭ አግኝቸ ለምስጋናው ዋጋ ክፈል ብባል ጥልቁን ፍቅር አክብሮቴን ለፈታ ፤ የነፍስ ምሰጋና ቃሌን ለወለደ ፤ የከበደውን ውድ ክፍያ ለመክፈል አይኔን አላሽም !ፍቅሬን ገላጭ አግንቸ ባለ እዳ መሆን ምንኛ መታደል ነው ?… ፍቅሬን ገላጭ አግንቸ እድሜ ልኬን የሰራሁትን ላንች ክብር ምስጋና እዳ ስከፍለው ብኖር ምንኛ ነፍሴ በፈቀደች … ?… ከምንም በላይ ስላንች ፍቅር የሚከፈለውን መስዋዕትነት መክፈል እንደሚያረካኝ ሳስበው የፍቅርሽን ጥልቀት ልኩ ይጠፋብኛል !
እንደኔዋ እናት በደሳሳ ጎጆ ፍቅር መግበው ፤ በፍቅርና ሰላም አብሮ መኖርን ፤ ለሰብእና ቅድሚያ ሰጥቶ ፤ መተሳሰብ መደጋገፍ ፤ በህብረት መቆምን ፍቅር ያወረሱን እናቶች እናቴም ዛሬ በክብርና ምስጋና ይታሰባሉ !ከወላጆቸ ባልተናነሰ ለዛሬዋ ቀን እንድንደርስ ፤ ስብእናን ተላብሰን ፤ እኛኑ አላብሳችሁ አሳድጋችሁናልና አናመሰግናችኋለሁ ! በወገን ፍቅር ደምቀን ለምገፋው የማናማርረው ህይዎት ጉዞ ምክንያት ለሆናችሁኝ ቤተሰብ ፤ ጎረቤት ፤ ወዳጅና አዝማዶቸም በእጅጉ ትመሰገናላችሁ !

አመሰግናለሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 16 ቀን 2009 ዓም

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s