“የተሰናሰነው፤ የተቀናጀው፤ ኢትዮጵያዊነት እንዲቀጥል ሞረሽ ይሠራል።” – አቶ ተክሌ የሻው

 

አቶ ተክሌ የሻው፤ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ሊቀመንበር፤ ስለ አውስትራሊያ፣ የአውሮፓና ኒውዚላንድ ጉብኝታቸው ዓላማ፣ ስለ ድርጅቱ ሚናና የወደፊት ትልም፤ እንዲሁም ድርጅቱ ለህትመት ስላበቃው  “ምጽአተ ዐማራ” መጽሐፍ ይዘት ይናገራሉ። SBS Amharic.

የማለዳ ወግ …ፈጣሪ በታች እናቴና እናቶች ይመሰገናሉ ![ነቢዩ ሲራክ]

* ቤተሰብ ፤ ጎረቤት ፤ ወዳጅና አዝማዶቸም በእጅጉ ትመሰገናላችሁ !

15107304_10211578255717936_6587443468850424585_nአሜሪካውያን ዛሬን ብሄራዊ የምስጋና ቀንን ዛሬ አድርገው ማክበር ግማሽ ምእተ አመት አገባደዋል ። በገና ዋዜማ በህዳር ወር ሁለተኛ ሳምንት ገደማ የሚከበረውን የምስጋና ቅዱስ ቀን Thanksgiving Day በጎ አስተምሮቱ እየተስፋፋ ከሰሜን አሜሪካ ተሻግሮ ካናዳና አውሮፓው ያጡኑ አልም እየተቀባበለ ቀኑ ማክበር ከያዘም ጊዜው በሀገረ ካናዳየሚከበረዉ ከጀመሩ በአሜሪካ ከገና በዓል የበለጠ የምስጋና Thanksgiving Day ቀን ይከበራል ! በእኛም ሀገር አሜሪካኖች በሚያደርጉት ልክ በዓሉ ባይከበርም ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እየተስፋፉ በመጡበት በዚህ ወቅት ምስጋና የማቅረብ በጎ ልምድ እየተቀሰመና እየተስፋፋ የመጣ ይመስለኛል ! እኔም በህይዎት ዘመኔ በውስጤ ለሚላዎሸው ፍቅር በምስጋናው ቀን ፍቅር አክብሮቴን እገልጽበታለሁና ቀኑን የባህል ውርሱን እዎደዋለሁ !

በዚህ የምስጋና ቀን ከሁሉም አስቀድሜ ሰጥቶ ለማያልቅበት ፤ ሁሉን ማድረግ ለማይሳነው ፤ ለእረኛው አምላክ ፤ ለጠባቂው ንጉስ ፡ምህረትና ቸርነቱ ለማያልቅበት የፍቅር አምላክ ለልኡል እግዚአብሄር አምላክ ምስጋናን አስቀደማለሁ ! ስላደረግክኝ ሁሉ አመሰግንሃለሁ !በህይዎት ዘመኔ ፤ በህይዎቴ ለውጥ ይመጣ ዘንድ በድህነት ጎጇዋ በጥሩ ስነ ምግባርና በሃገር ፍቅር ስሜት ኮትኩቶ ላሳደጉኝ ወላጆቸ ምስጋናዬ ወደር የለውም ! ከፈጣሪ በታች የእናት እንግልት ምስጋና ያንሰዋል ፤ አንባገነን የሀገሬ መንግስት በመጣ በሄደ ቁጥር የልጅ አበባ ፤ የልጅ ጠዋሪ ፤ የልጅ ደጋፊያቸውን በጭካኔ ከጉያቸው የሚነጠቁት የሀገሬ እናቶች ፤ በመጠወሪያ ጊዜያቸው ወህኒ ስንቅ አቀባይ የሆኑ እናቶች ፡ ልጆቻቸው ከነዳፊ አውሬ ሸሽተው በስደት ሲኖሩ ፍቅራቸውን እንዳያዩ የተገደቡት እናቴና እናቶች ይመሰገናሉ !

እናቴ ሆይ ! “ በዚህ የምስጋና ቀን የምታመሰግነውን አንድ ሰው ብቻ ምረጥ ?” ተብዬ ብጠየቅ ምንም ሳላወላውል ለከበደው ምስጋና የምመርጥሽ ክብር ሞገሴን ፣ እናት አድባሬን ፣ እናት ህይዎቴን አንችን ነው … እናት ሁለመናየ ሁነሽ አሳድገሽኛልና የህይዎት ርስቴ ነሽ ፤ ትመሰገኛለሽ ! አንችን እምየን መግለጫ ምስጋና ግን አለኝ አልልም !… ጥልቅ ፍቅርሽን ማሳያ ፣ የገዘፈ ክበርሽን ማመላከቻ ፣ የእናትነት ስስትሽን መለኪያ … አንችን በልክሽ መናገር የሚችል ፣ የሚገልጽ አንደበት አጣሁ … ክበር ለአንች ይገባሻል ከማለት ያለፈ የምለው የለም! በቃ ! አንችን የምገልጽበት ፣ ከዚህ ያለፈ የምስጋና ቃላት አጥቻለሁ !…

እናት አለም ! ምስጋና ዋጋ የሚያስከፍል ሆኖ የከበደው ፍቅርና ምስጋናዬን ገላጭ አግኝቸ ለምስጋናው ዋጋ ክፈል ብባል ጥልቁን ፍቅር አክብሮቴን ለፈታ ፤ የነፍስ ምሰጋና ቃሌን ለወለደ ፤ የከበደውን ውድ ክፍያ ለመክፈል አይኔን አላሽም !ፍቅሬን ገላጭ አግንቸ ባለ እዳ መሆን ምንኛ መታደል ነው ?… ፍቅሬን ገላጭ አግንቸ እድሜ ልኬን የሰራሁትን ላንች ክብር ምስጋና እዳ ስከፍለው ብኖር ምንኛ ነፍሴ በፈቀደች … ?… ከምንም በላይ ስላንች ፍቅር የሚከፈለውን መስዋዕትነት መክፈል እንደሚያረካኝ ሳስበው የፍቅርሽን ጥልቀት ልኩ ይጠፋብኛል !
እንደኔዋ እናት በደሳሳ ጎጆ ፍቅር መግበው ፤ በፍቅርና ሰላም አብሮ መኖርን ፤ ለሰብእና ቅድሚያ ሰጥቶ ፤ መተሳሰብ መደጋገፍ ፤ በህብረት መቆምን ፍቅር ያወረሱን እናቶች እናቴም ዛሬ በክብርና ምስጋና ይታሰባሉ !ከወላጆቸ ባልተናነሰ ለዛሬዋ ቀን እንድንደርስ ፤ ስብእናን ተላብሰን ፤ እኛኑ አላብሳችሁ አሳድጋችሁናልና አናመሰግናችኋለሁ ! በወገን ፍቅር ደምቀን ለምገፋው የማናማርረው ህይዎት ጉዞ ምክንያት ለሆናችሁኝ ቤተሰብ ፤ ጎረቤት ፤ ወዳጅና አዝማዶቸም በእጅጉ ትመሰገናላችሁ !

አመሰግናለሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 16 ቀን 2009 ዓም

የሜዲያ ሕይወትና ፖለቲካ (ከይገርማል)

conflict-dynamics-for-dummiesበሜዲያ ላይ ተሳትፎ ሳደርግ ጥቂት የማይባሉ አመታትን አስቆጥሬአለሁ:: በመጀመሪያ በጽሁፎች ላይ አስተያየት በመስጠት ነበር የጀመርሁት:: በምጽፋቸው ጽሁፎች ማንነቴ የሚታወቅና የምጠየቅ ይመስለኝ ስለነበረ አስተያየቶቸን የማቀርበው ሀላፊነት በተሞላበት መንፈስ ማንንም በማያስቀይም መልኩ በጥንቃቄ ነበር:: ያም ሆኖ በጻፍኋቸው አስተያየቶች ላይ ተንተርሰው የሚሰጡኝ አሳቃቂ ምላሾች መከሰታቸው አልቀረም:: የሚገርም ነው! የፈለገው ቅዱስ ስራ ብንሰራ ነቃፊ አይጠፋም ማለት ነው! ሌላው ችግሬ ደግሞ የምጠቀምበት ኮምፒዩተር የጋራ ስለነበር ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ሀሳቤን ለመግለጽ አለመቻሌ ነበር:: አስተያየት በምጽፍበት ወቅት የሚያልፉ የሚያገድሙ ሰዎች የምጽፈውን ያነቡብኛል የሚለው የመጀመሪያው ስጋቴ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አስተያየቱን ጽፌ ፖስት ካደረኩ በኋላ የተጠቀምሁበት ስም የማይጠፋ በመሆኑ ይታወቅብኛል የሚል ፍርሀት ነበር:: ምን ላድርግ በዚህ ዘመን ማን ምን እንደሆነ መች ይታወቃል! ቀስ በቀስ ግን ሁሉንም እየተላመድሁ ሌሎችንም እያየሁ እየተማርሁ ሄድሁ::

በምሰጣቸው አስተያየቶች ከትንሽ እስከትልቅ ስድብ ተሰድቤአለሁ:: ጉድ እኮ ነው! የመንግሥትን ጥሩ ጎን ብናነሳ ሕዝበ-አዳም ይወርድብናል: ግንቦት 7ን ብንደግፍ የመንግሥት ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ተቃዋሚወችም እንደጉድ ብድግ ብለው ይሰፍሩብናል: ኢሕአፓን ደግፈን ብንጽፍ ‘ትግሉን የገደሉ የ “ያ ትውልድ” የጥላቻና የመጠላለፍ ፖለቲካ አራማጆች ቅሪት’ ተብለን እንወገዛለን: ከፖለቲካ ውጪ ስለሆነ ነገር ብንጽፍ ‘ሀገርና ሕዝብ ችግር ውስጥ ወድቀው ባሉበት ሁኔታ እንዲህ አይነት ጽሁፍ ማቅረብ ሀላፊነት ማጣት ነው’ የሚለን ሞልቷል:: ዝም ማለት ደግሞ አይቻልም:: ይህ ማለት ግን በምጽፋቸው አስተያየቶች የሚደግፉኝ ሰዎች የሉም ማለት አይደለም:: አንዳንድ በግብራቸው ትላልቅ የሆኑ ሰወችም ያልተስማሙባቸውን ነጥቦች አንስተው በማይኮሰኩስ መንገድ ተችተውኝ ያውቃሉ:: አስተማሪነት በሌለው በአፍራሽ መልኩ ማለት በስድብ ወይም በእርግማን የሰውን ቀልብ የሚገፉ ሰዎችን ምን ቢያደርጓቸው ይሻላል? :: አንዳንዴ ሲብስብኝ ሰዳቢየን በሌላ ስም መልሸ አቀምሰዋለሁ:: ምኔ ሞኝ ነው? በአውላላ ሜዳ ላይ ወጥቶ እያቅራሩ መተኮስ ዱሮ ነው የቀረው:: ስለዚህ እንደዘመኑ አካሄድ በምሽግ ውስጥ ሆኘ ጠሽ እያደረኩ እተኩሳለሁ::

ክፉ የምባል ሰው አይደለሁም:: እንዲያውም ሀቀኛ: ግልጽና ቅን ከሚባሉ ሰዎች ውስጥ ልመደብ የሚገባኝ ነኝ:: ነገር ግን ዕድል የሚባል ነገር እንደሌለኝ አውቀዋለሁ:: እኔ ላይ ነገር ይከራል:: የማደርገውም ሆነ የምናገረው ባልጠበኩት መንገድ ይተረጎምብኛል:: ሰው ብወድም ሰው አይወጣልኝም:: ከእኔ እርዳታ የሚያገኝ ሰው ሳይቀር የምሰጠውን እየበላ በሀሜት ያብጠለጥለኛል: ጉድጓዴን ይምስልኛል:: ለምን እንደሆነ አይገባኝም:: ሌላው ቀርቶ በእርጅና ምክንያት መነሳት አቅቶት ከደጅ ተኝቶ የሚውል ውሻ ሳይቀር በማንም ላይ የማያደርገውን የእኔን ኮቴ ከሰማ አንገቱን እንደምንም ቀና አድርጎ “ቡፍ” ይልብኛል:: እንዲህ ብየ ስል ዕውነት ላይመስል ይችላል: ግን የምሬን ነው:: ግምባር ወይም ኮከብ ወይም ዕጣፈንታ የሚባለው ዕውነት ሳይሆን አይቀርም:: ባለቤቴ “ለኔና ለአንተ ገንዘባችን ነው ዘመዳችን:: እጃችንን እንኳ ቆርጠን ብንሰጠው የሚያመሰግነን የለም” ትለኛለች::

ባለቤቴ በአብላጫ ድምጽ ታምናለች:: ማለቴ ብዙሀኑ የደገፈው ሀሳብ ትክክል ነው ብለው ከሚያምኑት ሰዎች ውስጥ አንዷ ናት:: እኔ ደግሞ ከዚህም ከዚያም በግብአትነት ያሰባሰብኋቸውን ጭብጦች ይዠ በመጨረሻ ላይ ትክክል ነው ወይም የተሻለ ነው ብየ የማምንበትን ውሳኔ የማሳልፍ ሰው ነኝ:: ከአናሳው ድምጽ ውስጥም ዕውነት ልትኖር ትችላለች ብየ የማምን ነኝ:: በዚህ ምክንንያት ከብዙሀኑ የማፈነግጥበት አጋጣሚ ብዙ ነው:: ለምሳሌ የአባይን ግድብ ከሚደግፉት ጥቂት ሰዎች ውስጥ አንዱ ነኝ:: የምደግፍበት ምክንያት ጠቃሚ ነው ብየ ስለማምን ነው:: ወያኔ የሕዝብን ገንዘብ ለመዝረፍ የፈጠረው አዲስ ዘዴ ነው ለሚሉት ሰዎች “ምንም ነገር ሳይሰሩ ሲዘርፉ ማን አስቁሟቸው ያውቃል: ሳይሰሩ ከሚበሉ እየሰሩ ቢበሉ አይሻልም ወይ? አዋጡ ብሎ ያስገደዳችሁ የለም:: ካልፈለጋችሁ አታዋጡ:: እነርሱ ግን ከየትም አምጥተው ይስሩት: እኛ እንቅፋት መሆን አይገባንም” ብየ ተከራክሬአለሁ:: ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ነው የአባይ ግድብ የተጀመረው: አይ አይደለም ውጥረት ስለበዛበት እንደማስቀየሻ የተጠቀመበት መንገድ ነው እንጅ ለሀገር ጥቅም ታስቦ ቢሆን ኖሮ ሱዳን ድንበር አጠገብ ባልተገነባ ነበር ላሉት “የወያኔ ወንጀል አስከፊ ነው: የሚሰራው ግፍ ከልክ ያለፈ ነው::  ስለዚህ  በአባይ ግድብ ምክንያት የሕዝቡ ልብ አይሸነፍም ብየ ተሟግቻለሁ:: ቢያንስ በአባይ ላይ ያገባናል የሚሉትን ወገኖችን እና የአለማቀፉን ማህበረሰብ ፖለቲካዊ ተጽእኖ የምንዳስስበት ሆኖ ሊያገለግል ይችላል” ብየ አቋሜን በግልጽ በማቅረቤ ያልተባልሁት ነገር አልነበረም::

የህትመት ሜዲያውን እየተለማመድሁት ስመጣ ከአስተያየት ሰጭነት ወደጽሁፍ አቅራቢነት አደግሁ:: የምጽፈው ማንንም ለማስቀየም ወይም ለማስደሰት ብየ አይደለም:: በቃ ትክክል ነው ብየ የማምነውን ነው የምጽፈው:: ሁሉንም ማስደሰት እንደማይቻል በሚገባ አውቃለሁ:: እና በሚሰማኝ ጉዳይ ላይ እጽፋለሁ: እተቻለሁ:: የምቃወመውም ሆነ የምደግፈው ሰውን ወይም ቡድንን ሳይሆን ሀሳብንና ድርጊትን ነው:: ነገር ግን የሀሳብ አፍላቂወችና የድርጊት ተዋናዮች ሰዎች ስለሆኑ ዞሮ ዞሮ ትክክል ያልሆነ ሀሳብ ተነስቷል ወይም ጎጅ የሆነ ነገር በተግባር ላይ ውሏል በሚል ዋናወቹ አክተሮች ሊወቀሱና ሊወነጀሉ የግድ ይሆናል:: ለዚያም ነው ተቃዋሚወችንም ሆነ ወያኔወችን ማድረግ ያለባቸውን አላደረጉም ወይም ማድረግ ያልነበረባቸውን አድርገዋል እያልሁ እያወገዝሁ ስጽፍ የነበርሁት:: በዚህ የተነሳ ወያኔ ቢያገኘኝ በጉጠት አፍንጫየን ሊነቅለው ይችላል: ተቃዋሚው ደግሞ አንገቴን::

በወያኔም ሆነ በተቃዋሚው ወገን ያሉ ደጋፊወች ለምን ጭፍን ደጋፊና ጭፍን ተቃዋሚ እንደሚሆኑ አይገባኝም:: እንዴት በሎጅክ አያምኑም! እንዴት ጭንቅላታቸውን አይጠቀሙም! መሬት ላይ በሚያዩት ዕውነታ ተመስርተው ለምን ፍርድ አይሰጡም! አመራር ላይ ያሉት እኮ ሰዎች ናቸው:: የሚገርማችሁ ብዙወች ከማናችንም የሚበልጥ ስብዕና: እውቀትም ይሁን ልምድ የላቸውም:: ለጥቂት ጊዜ ጠጋ ብላችሁ ብታይዋቸው ዕውነቱን ትረዱት ነበር:: የሚሰሩት በአብዛኛው በ trial and error ዘዴ ነው:: ለዚያም ነው ሕዝብንና ሀገርን ቤተሙከራ እያደረጉ ነው እየተባሉ የሚወነጀሉት:: ደጋፊው ግን ምን ነካው? ለምን ጥሩውን ጥሩ መጥፎውን መጥፎ ማለት አይለምድም:: በየትኛውም ወገን ያለ ደጋፊ አመራሩ የሚያወርደውን መመሪያ ተቀብሎ የሚያስተጋባ እንጅ የአመራሩን እንከን ነቅሶ በማውጣት ለማስተካከል የሚሰራ አይደለም:: ለምሳሌ የኮማንድ ፖስቱ በልቡ ቂም ሳይይዝ አልቀረም ተብሎ የሚጠረጠርን ሁሉ እያሰረ እንደሆነ ነው የሚታወቀው:: የትኛው የወያኔ ደጋፊ ነው “ኧረ የሚሰራው ስራ ልክ አይደለም” ብሎ ሲቃወም የተሰማው:: ለነገሩ የሀገር ቤት ተቃዋሚወችስ ወያኔ በፈቀደላቸው ጉዳይ ዙሪያ ብቻ ስለሚንቀሳቀሱ ፍቃድ ካላገኙ በስተቀር ያለቀው ቢያልቅ የሰላማዊ ተቃውሞ ሰልፍስ ቢሆን መች ሊጠሩ ይደፍሩና:: ሰላማዊ ተቃውሞ መንግሥትን ማስገደጃ መንገዶች የሉትም? መንግሥት የፈቀደውን ብቻ የሚፈጽም ተቃዋሚ ተቃዋሚነቱ ምኑ ላይ ነው?

መንግሥት የመሬት ይዞታን በሚመለከት የያዘው አቋም በብዙወች ዘንድ እንደሚወገዝ ይታወቃል:: ሕዝቡ ስለዘላቂ ጥቅሙ ብዙም የማያውቅ በመሆኑ መሬቱን ሊሸጥ ስለሚችል መሬት እንዲሸጥ እንዲለወጥ መፍቀድ አደጋ አለው ይላል:: ‘መሬት ይሸጥ ይለወጥ ቢባል መሬት በጥቂት ባለሀብቶች እጅ እንዲሰባሰብ ምክንያት ይሆናል: ስለዚህ መሬት ሳይሸጥ ሳይለወጥ የሕዝብና የመንግሥት ሆኖ መቀጠል አለበት:: ከሕዝቡ ከራሱ በላይ እኔ ስለማስብለት ነው ይህን የማደርገው:: በጮሌወች የማታለያ ዘዴ ተሸንፎ መሬቱን ሸጦ ለጭሰኝነት እንዳይዳረግ ሲባል መሬት የሚሸጥ የሚለወጠው በኢሕአዴግ ከርሰመቃብር ላይ ነው’: ይልና ራሱ ግን ሕዝቡን እንደፈለገ እያፈናቀለ በካሬሜትር በዶላር ይቸረችራል:: ተቃዋሚው ደግሞ የመሬት በመንግሥት እጅ መዋል ጉዳት አለው:- ሙስናን ያበረታታል: ምርታማነትን ይቀንሳል: ፍርሀትና ጥርጣሬን ይፈጥራል: የዜጎች የንብረት ባለቤትነትን መብት ይገስሳል: – – – ሲሉ ይከራከራሉ (ብዙወች የጎሣ ኃይሎች በመሬት ጉዳይ ያላቸው አቋም ከኢሕአዴግ ጋር ይመሳሰላል) :: ደጋፊውም የየፓርቲወችን አቋም ይዞ አመራሩ የሚለውን ተቀብሎ እንደበቀቀን ይደግማል:: ነገር ግን አሁን ኢሕአዴግ ድንገት ብድግ ብሎ አቋሙን ቀይሮ መሬት እንዲሸጥ እንዲለወጥ ፈቅጃለሁ ቢል የኢሕአዴግ ደጋፊወች ስለመሬት የመሸጥ የመለወጥ ጥቅም ቀድሞ በተቃዋሚው ይባል የነበረውን አስተያየት የራሳቸው አድርገው እንደሚከራከሩ: የተቃዋሚው አመራርና ደጋፊወች ደግሞ በአሁኑ ወቅት ገንዘብ የተሰባሰበው በገዥው ፓርቲ እጅ ስለሆነ የሕዝቡን መሬት በገንዘብ ኃይል አታለው በመውሰድ ሕዝቡን ወደከፋ ጭሰኝነት ሊያወርዱት አስበው ነው ብለው እንደሚቀሰቅሱ መጠራጠር አያስፈልግም:: ጥሩውን ከመጥፎው ሳይለዩ መደገፍና መቃወም የጤና አይደለም:: በዚህ ጉዳይ ላይ ወያኔና ተቃዋሚወች በጣም ይመሳሰላሉ:: የሚያመሳስላቸው የራሳቸው ጉድፍ የማይታወቃቸውና የሌላው ጥሩ ጎን የማይታያቸው መሆኑም ነው:: አመራሩ የሚደግፈውን ሁሉ መደገፍ: የሚቃወመውን ሁሉ መቃወም: ካለ አሳማኝ ምክንያት ሀሳቡን እንደፈለገ ሲቀያይር አብሮ ሀሳብን መቀያየር የሰውነት መለኪያ አይደለም እያልሁ ነው ያለሁት::  የሌላ መንፈስ ተሸካሚ ከመሆን ወጥተን ክፉውን ከደጉ ለመለየት ጭንቅላታችንን እንጠቀም የሚል መልዕክት ነው ለማስተላለፍ የፈለኩት::

ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ኃይል ምን ለማድረግ እንደሚፈልግ የማያውቅ ፍጹም ግራ የገባው ነው ማለት ይቻላል:: የምንታገለው የስርአት ለውጥ እንዲመጣ ነው የሚለው ተቃዋሚ ትንሽ ቆይቶ መንግስት አንዳንድ መሻሻሎችን (ጥገናዊ ለውጥ) እንዲያደርግ ተማጽዕኖ ሲያሰማ ይደመጣል:: ለውጥ እንፈልጋለን ይላል: ግን ለለውጥ አይተባበርም:: አሊያም ሊተባበር የሚነሳው በምንም አይነት መልኩ ሊያቀራርብ የሚያስችል የጋራ አጀንዳ ከሌላቸው ቡድኖች ጋር ነው:: እንዲያውም ይግረማችሁ ብለው አንዱን ድርጅት ለሁለት ለሦስት ሲከፍሉትም አይተናል:: አንዱ ተቃዋሚ ነኝ ባይ የስደት መንግሥት እንመስርት ሲል ያወጣውን መግለጫ ሲያጣጥል የነበረው ሌላው ተቃዋሚ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ትንሽ ስሙን ቀይሮ ወይም አሻሽሎ የሽግግር መንግስት እንመስርት ብሎ ጥሪ ሲያደርግ ሀፍረት የሚባል አይሰማውም:: ይኸ ሁሉ ግን ለምን ይሆናል? ተብሎ ቢጠየቅ አርኪ መልስ የሚሰጥ አይገኝም;; እኛ ግን መልሱን በሚገባ እናውቀዋለን:: ሁሉም አለቃ እንጅ ምንዝር መሆን እንደማይፈልግ: ሁሉም መሪ እንጅ ተመሪ ለመሆን እንደማይሻ:: ሁሉም ከፊት እንጅ ከኋላ ለመሆን እንደማይፈቅድ እንረዳለን:: ችግሩ የሚመነጨውም ከዚህ የተዛባ እይታ እንደሆነ እንገነዘባለን::

በፌስቡክም ሆነ በዌብሳይቶች ላይ የሚሰጡ ብዙወች አስተያየቶች አስተማሪ ወይም አዝናኝ ያልሆኑ ተራ ስድቦች ናቸው:: በርግጥ አስተማሪ ባይሆኑም ከልብ የሚያስቁ አንዳንድ በፎቶ ተደግፈው የሚቀርቡ ኮሜንቶች አሉ:: በዕውነት ደስ ይሉኛል: ማሳቅም እኮ ትልቅ ጥበብ ነው:: መጻፍ እንደጀመርሁ በአርቲክሎቼ ያልተደሰተ ወገን  በስድብ ጥርግርግ ሲያደርገኝ እደነግጥ ነበር:: አንዳንዱን ስድብማ ውይ ውይ ውይ እንኳን ደግመው ሊሉት ሊያስቡትም ይከብዳል:: ስንት አይነት ሰው አለ!

ጽሁፍ የሚጻፈው ለጨዋታ አይደለም:: የሆነ መልዕክት ለማስተላለፍ: ቁምነገር ለማስጨብጥ: ወይም አማራጭ የመፍትሔ ሀሳብ ለማቅረብ ነው ጽሁፍ የሚጻፈው:: የምናውቀውን ለማሳወቅ: ስህተት ነው ያልነውን ስህተቱን ለማሳየት ነው:: እንድንማማር ነው:: አስተያየቶችስ በዚህ መልኩ ተቃኝተው በበጐ መልኩ ቢቀርቡ ምን አለበት?

የ”ሀ” ን ዘር የ”ከ” ዘር እያጠፋው ነው በሚለው ጽሁፌ ከጥቂቶች በስተቀር ብዙወች በጎደለ ሞልተው ሀሳቤን ደግፈው አስተያየት ሰጥተውኛል:: ይሁንና ችግሩ የሚቀረፍ ሳይሆን ጭራሽ እየባሰበት ነው የሄደው:: እንዲያውም አሁንማ እንደምን ናቹ: እኔ የምልክ: በልቻለው: ከሚለው አልፎ ተርፎ ከአንድ ርእሰጉዳይ ወደሌላ ርእሰጉዳይ ለመሸጋገር ሲፈለግ “”ይህንን በዚህ ቋጭተን ወደሚቀጥለው አለፍን” ሲሉ ስሰማ በቃ አማረኛ የሜዲያ ሰዎች ሳይቀሩ በዘፈቀደ የሚናገሩት ቋንቋ ሆነ አይደል! ማለቴ አልቀረም:: ይህን በዚህ ቋጭተን ወደሚቀጥለው አለፍን ሲባል ያለፈውን ነገር ለመተረክ ታስቦ ሳይሆን ወደሚቀጥለው ዝግጅት ለመሸጋገር መዘጋጀትን ለመግለጽ እንደሆነ የገባኝ ቆይቶ ነው:: ሀላፊ ግስ(past tense) እና ስለወደፊቱ ገላጭ ግስ (future tense) እንዴት እንደምንጠቀም የማናውቅ ሰዎች በእንደዚያ አይነት መድረክ ምን እንሰራለን:: ይህን በዚህ ቋጭተን ወደሚቀጥለው እናልፋለን በማለት ፈንታ ይህን በዚህ ቋጭተን ወደሚቀጥለው አለፍን ሲባል ስሰማ የመደበኛ ቋንቋ አጠቃቀምን እያዛባን የቋንቋ ስርአተአልበኝነትን እያስፋፋን እንደሆነ አምንና ከልብ አዝናለሁ::

በዚህ ርዕስ ላይ ባለሙያወች አስተያየት ቢሰጡበት ደስ ይለኛል:: ስህተት ለማረም መጀመሪያ ስህተቱ መታወቅ አለበት:: እኔም ተሳስቸ ከሆነ እንድታረም ሊነገረኝ ይገባል::

ተጨማሪ ማብራሪያ ኤርትራ በሚለው ሥያሜ ላይ! [ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው]

eritriaባለፈው ሳምንት “ኤርትራ የሚለው ስም ከመቸ ጀምሮ፣ ከየት፣ በማንና በምንስ ምክንያት መጣ?” የሚል ርእስ ያለው ጽሑፍ ማስነበቤ ይታወሳል፡፡ በርካታ ሰዎች በተለይም የባሕረ ምድር ተወላጆች (ኤርትራውያኑ) ጽሑፉ የገባቸው አልመሰለኝም፡፡ የጻፍኩት ሌላ የተረዱት ሌላ መሆኑን በኢሜይል (በነመልእክት) ከላኩልኝ አስተያየቶች ተረድቻለሁ፡፡

እኔ ጣሊያን ባሕረ ምድርን ኤርትራ ብሎ ከመሠየሙ በፊት ኤርትራ የሚል ስም የባሕረ ምድርም ሆነ የሌላ ሀገር ሥያሜ ሆኖ አያውቅም! አልኩ እንጅ ኤርትራ የሚባል ቃል ወይም ኤርትራ የሚል የሆነ ነገር ወይም ቁስ ስም የለም አላልኩም! ቃሉ አስቀድሞ በቋንቋው ውስጥ ሳይኖር ጣሊያን ታዲያ ከየት አምጥቶ ለሥያሜነት ሊጠቀምበት ቻለ? ከቋንቋው ውስጥ የነበረ ቃል በመሆኑም አይደለም ወይ ሊጠቀምበት የቻለው?

ሌላው ደግሞ እኔ ከአማርኛው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በኋላም በግእዝ መጻሕፍት ላይ የኤርትራ ባሕር በማለት የተጠቀሰው ቃል በሸፍጥ እንዲገባ የተደረገ ቃል ነው እንጅ ከጣሊያን ወረራ በፊት የነበረ ቃል አይደለም! ለዚህም ማስረጃው በሌሎች ቋንቋዎች የተጻፉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ብትመለከቱ ቀይ ባሕር ይላል እንጅ የኤርትራ ባሕር፤ ልብ በሉ ኤርትራ ባሕር ሳይሆን ያልኩት የኤርትራ ባሕር ነው ያልኩት፤ እናም እንዲህ የሚል ቃል በተለያዩ ቋንቋዎች በተጻፉ የመጽሐፍ  ቅዱስ ትርጉሞች አለመገኘቱ ነው፡፡ ጣሊያኖች የእኛን ሰዎች በመግዛትና በመደለል የኤርትራ ባሕር የሚልን ቃል በቅዱሳት መጻሕፍቶቻችን ውስጥ እንዲሠፍር ያደረጉበት ምክንያት ከጥንት ጀምሮ ባሕረ ምድር የኢትዮጵያ አካል ያልነበረች ለማስመሰልና ከፋፍሎ ኢትዮጵያን ለማዳከም ባላቸው ሸፍጥ ምክንያት ነው አልኩ እንጅ ቀይ ባሕር ጣሊያኖች በሚጠቀሙበት ቋንቋ በላቲን ኤሪትራ ታላሳ, Erythra thalassa (ቀይ ባሕር) አይባልም አላልኩም! አልወጣኝም!

በርካታ ሰዎች ግን ሁለቱንም ነጥቦች እንዲህ እንዳልኩ አድርገው አዛብተው በመረዳታቸው ኤሪትራ ባሕር ልብ በሉ የኤርትራ አይደለም ያልኩት ኤሪትራ ነው፤ እናም ቀይ ባሕር በላቲን ኤሪትራ ባሕር ይባል እንደነበር የሚያስረዱ ሊንኮችን (ይዞችን) በመላክ እንደተሳሳትኩ ሊነግሩኝ ሞከሩ፡፡

ከዚያ በፊት እኔ ያልኩትን አንብበው ምን እንዳልኩ ቢረዱ አሳስተው ተረድተው ያላልኩትን እንዳልኩ አድርገው ባልወቀሱኝ ነበር፡፡ ማንም ሊረዳው እንደሚችለው የኤርትራ ማለትና ኤሪትራ ማለት ሰፊ የሆነ የትርጉም ልዩነት አላቸው፡፡ የኤርትራ ማለት ኤርትራ የተባለ አካል ንብረት ማለት ሲሆን ኤሪትራ ማለት ግን ባለቤትነትንም የማያጠያይቅ ነጠላ ቃል ወይም ስም ነው፡፡ ትርጉሙም ቀይ ማለት ነው፡፡ ኤሪትራ ታላሳ ማለት ደግሞ ቀይ ባሕር ማለት ነው፡፡ ይህ ሥያሜ መጣ የሚባለው ደግሞ አንደኛው በጥንት ዘመን ኤሪትራ የሚባል የግሪክ ንጉሥ ነበረ ባሕሩንም በስሙ ስለሠየመው ነው ኤሪትራ የተባለው የሚለው ሲሆን፡፡ ሌላኛው ደግሞ የባሕሩ ወለል ላይ ወቅቱን እየጠበቀ በሚያብብ ቀይ አበባ ምክንያት ባሕሩ ቀይ መልክ ይይዝ ስለነበር ከዚህ የተነሣ ቀይ ባሕር ተባለ ይባላል፡፡ ቀይ ባሕር ውስጥ ባለ ቀይ ትል ምክንያት ነው ባሕሩ ቀይ ባሕር የተባለው የሚሉ የባዕዳን መላምትም አለ፡፡ ለማንኛውም የቀይ ባሕር ሥያሜና ምንጩ ይሄው ነው፡፡ አሁንስ ግልጽ ነው ወገኖቻችን? በመሆኑም “ባሕረ ምድርን ኤርትራ በማለት በፋሺስት ጣሊያን የተሰጠው ሥያሜ የባርነት ስም ነው!” ማለቴ ትክክል ነበር፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

 

የ“ዓለም አቀፍ አማራ ተራድኦ ድርጅት” ምሥረታ አስፈላጊነትን በሚመለከት ለውይይት የቀረበ (ዮፍታሔ)

young-amharaባለፈው 40 ዓመት፣ ይልቁንም ባለፉት 26 ዓመታት አማራውን ያጋጠሙትና አሁንም እንደቀጠሉ ያሉት ችግሮች ከፍ ያሉና ዘርፈ ብዙ ናቸው። ከፍ ያለ ችግር ከፍ ያለ መፍትሔ ያስፈልገዋል።

አማራው በአገር ቤት የደረሰበትና እየደረሰበት ያለው ዘርፈ ብዙ ጥቃት፣ ችግርና መከራ የታወቀ፣ እየታወቀ ያለ፤ በአብዛኛው የተመዘገበና እየተመዘገበም ያለ ነው። ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ይህን ዘርፈ ብዙ ጥቃትና ችግር በማያዳግም መንገድ ለመፍታት የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶችን ማቋቋም እየተከናወነ ቢሆንም እነዚህ ድርጅቶች የሚንቀሳቀሱበትንና ሥራቸውን በአጥጋቢ ሁኔታ ለማከናወን የሚያስችላቸውን የገንዘብ አቅም ለማግኘት በየራሳቸው ብቻ የሚያደርጉት ጥረት በቂ አይሆንም። የሕዝቡ ይልቁንም በውጭ የሚኖረው አማራ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ከድርጅቶቹ ቁጥር መብዛት ጋር ለረጂዎቻቸው አንድ ወጥ መንገድ ማመቻቸትም ተገቢ ነው። ይህ አንዱ ነው።

አማራው ከአገሩ ውጭ እየደረሰበት ያለውም ቀላል አይደለም።  በ Human trafficking ከአገራቸው እየወጡ ሴቶች ከባርነት በሚስተካከል ግርድና ወንዶች በእረኝነት ኑሮአቸውን የሚገፉና  አካላቸው በቀዶ ጥገና እየወጣ የሚገደሉም አብዛኞቹ የአማራው ልጆች መሆናቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። የመረረውን ሕይወትና የሕወሐትን አፈና በመሸሽ በባሕር ሲጓዙ ውኃ ከሚበላቸው መካከል በርካታ የአማራ ተወላጆችም ይገኙበታል። በየዓመቱ በማደጎ ከኢትዮጵያ ከሚወጡ በብዙ ሺ ሕፃናት መካከል የአማራ ሕፃናት መኖራቸውን ከምንኖርባቸው የውጭ ከተሞችና ከማኅበራዊ ሚዲያ ፍንጮች ለመገንዘብ ይቻላል። ኢትዮጵያዊ ሕፃናት በማደጎ የሚወጡት በአብዛኛው ወደአሜሪካ፣ አውሮፓና አውስትራሊያ ቢሆንም በነዚህ አገራት እስከሞት የሚያደርስ ብዙ በደል እንደሚፈጸምባቸው በየጊዜው በዓለም አቀፍ መገናኛ ከሚወጡ ዘገባዎች መረዳት ይቻላል። በነዚህ የውጭ አገራት በአንጻራዊ ሰላም የሚኖሩት ሕፃናት ደግሞ ከአገራቸውና ከማንነታቸው ተነቅለው በባዕድ አገርና የነርሱ ባልሆነ ባሕል፣ ማንነትና አኗኗር ውስጥ ያልፋሉ። ይህ ለአሁኑና ለቀጣዩ የአማራ ትውልድና ሕዝብ ጉዳት አለው። በሳውዲ አረቢያ፣ በሊባኖስ፣ በሊቢያና ባልተረጋጋው መካከለኛው ምሥራቅ ውስጥ ከሞቱትና ከሚሞቱት ኢትዮጵያውያን መካከል አማሮች መኖራቸው የሚታወቅ ነው። እነዚህ ከችግሮች በጣም ጥቂቶች ናቸው። ተቆርቋሪ መንግሥትም ሆነ ማንም ረዳት በሌለበት እነዚህንና መሰል ችግሮች ከሥራቸው ማድረቅና ዘለቄታዊ መፍትሔ መስጠት በአማራው ትከሻ ላይ የወደቀ ነው። ይልቁንም በውጭ አገር ከምንኖር አማሮች ብዙ ይጠበቃል። ሁለተኛው ይህ ነው።

በውጭ የምንኖር አማሮች ቁጥር በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በእስያ፣ በአረብ አገራትና በእስራኤል በትንሹ ከ 1 – 2 ሚሊዮን ሊሆን እንደሚችል ከወጡ አንዳንድ ጠቋሚ መረጃዎች ግምት መውሰድ ይቻላል።

በዓለማችን 2 ሚሊዮን አካባቢና ከዚያ በታች የሕዝብ ቁጥር የሚኖርባቸው አገሮች እጅግ በርካታ ናቸው። ባህሬን፣ ኳታር፣ ስሎቬንያ፣ ላቲቪያ፣ ጊኒ ቢሳዎ፣ ቦትስዋና፣ ጋቦን፣ ስዋዚላንድ፣ ትሪኒዳድና ቶቤጎ፣ ሞሪሽየስ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋቦን ጥቂቶቹ ናቸው።

ስለዚህ በውጭ የምንኖር አማሮች ቁጥራችን የአንድ ትንሽ አገር ሕዝብ ያህል ሆኗል ማለት ነው።

ይህ ከሆነ እንኳን ይህን ያህል ችግር እያለብን ባይኖርብን እንኳን በውጭ የምንኖር አማሮች እንደ አንድ ሕዝብ የሚያገለግሉን ተቋማት ያስፈልጉናል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ሦስተኛው ነው።

ከነዚህ ተቋማት መካከል “ዓለም አቀፍ የአማራ ተራድዖ ድርጅትን ማቋቋም” አንዱ መንገድ ሊሆን ይችላል በሚል በመላው ዓለም የሚገኙ አማራ ኢትዮጵያውያን ሀሳብ እንዲሰጡበትና እንዲወያዩበት ይህ ሀሳብ ቀርቧል።

ይህን የመሰሉ በአንድ ሕዝብ ላይ የሚያተኩሩ ነገር ግን አደረጃጀታቸው ዓለም አቀፋዊ የሆኑ ድርጅቶች በየጊዜው ነበሩ አሁንም ይኖራሉ።

እሥራኤል እ. ኤ. አ በ 1948 እንደአገር ከመመሥረቱ አስቀድሞ በተለያዩ አገሮች ተበትነው ይኖሩ የነበሩትን እስራኤላውያን የሚመዘግብ፣ የሚያሰባስብና ከራሳቸው ከእሥስራኤላውያንና ከበጎ አድራጊዎች ገንዘብ በመሰብሰብ እስራኤላውያንን በያሉበት ይረዳና በኋላም ወደአገራቸው እንዲመለሱና እሥራኤልን እንዲመሠርቱ ያደረገ ድርጅት ነበራቸው። ይህ ድርጅት በመጀመሪያ Jews Agency በመባል ይታወቅ ነበር። በኋላ ደግሞ World Zionist Organization በሚል ስም እንዲጠራ ሆኗል።

ዓለም አቀፍ የአማራ ተራድኦ ድርጅት ቋሚ ድርጅት ነው። የዓለም አቀፍ የአማራ ተራድኦ ድርጅት በአገር ቤትም ሆነ በውጭ አገር አማራውና ሌሎችም ኢትዮጵያውያን የሚደርስባቸውን ጥቃት፣ በደልና፣ ችግር በማያዳግም ሁኔታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ይሠራል። ለአማራው እንደአንድ ጃንጥላ ድርጅት (Umbrella Organization) ሆኖ ሌሎችንም የአማራውን ድርጅቶችና ተቋማት በጠቅላላ በውጭ አገርና በአገር ቤት በገንዘብና በቁሳቁስ የሚደግፍ ይሆናል። ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሌሎችን አስፈላጊ ድርጅቶች ያቋቁማል፣ እንዲቋቋሙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ የተቋቋሙትንና በመቋቋም ላይ ያሉትን ይደግፋል።

ይህ ድርጅት በውጭ ለሚኖሩ አማሮች እንደወኪልና ተሟጋች ሆኖ የሚያገለግል፣ እንደ ቀይ መስቀልና UNHCR ለአማሮችና ለኢትዮጵያውያን ፈጥኖ ደራሽ የሆነ፣ እንደኢንሹራንስና እንደዓለም ዓቀፍ አበዳሪ ባንኮች ለበጎ ሥራና ለአማራው የፖለቲካ፣ የሲቪክ፣ (መረጃ፣ ሚዲያ፣ ባሕል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ዲፕሎማሲ ወዘተ) ተቋማትና ድርጅቶች ረዳትና ዋስትና የሚሆን፣ ለችግሮች መፍትሔ መስጠት የሚችልና የችግሮችን ምንጭ እስከማድረቅ ድረስ የሚሠራ ድርጅት መሆን ይኖርበታል።

Steering committee (tink tank) መጀመሪያ ከተቋቋመ በኋላ ያ ኮሚቴ የድርጅቱን ዓላማዎች፣ ራዕይ፣ ዝርዝር ተግባራት ረቂቅ ያዘጋጃል፣ ድርጅቱ የሚመሠረትበትን ቦታ ይወስናል፣ የሚመለከታቸውን የአማራውና ኢትዮጵያውያን፣ ተቋማት፣ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች ይጋብዛል። በዚያ ስብሰባ ላይ ድርጅቱ ይመሠረታል። እንደሲያትሉ የአማራ ግብረኃይል ዓይነት ማኅበር ይህንን ኃላፊነት ሊወስድ ይችላል።

አደረጃጀት

ዓለም አቀፍ የአማራ ተራድኦ ድርጅት በመላው ዓለም ለሚገኙ አማሮችና ኢትዮጵያውያን የሚሠራ በመሆኑ አደረጃጀቱ ዓለም አቀፋዊ ይሆናል።

ማዕከላዊ የድርጅቱ አስተዳደር (የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ) በአንድ በተመረጠ የውጭ ከተማ ይቋቋማል። ድርጅቱ ቅልብጭ ያለ የቢሮክራሲ ውስብስብነት የሌለው መሆን ይኖርበታል። ይህ እንዲሆን በየአገሩ ኢትዮጵያውያን በጠቅላላ በሚገኙባቸው ከተሞች ንዑስ ኮሚቴዎች (chapters) ይኖሩታል። እነዚህ ኮሚቴዎች ከዋናው ሥራ አስፈጻሚ ጋር በመነጋገር በአካባቢያቸው ስላለው እና መከናዎን ስላለበት ሁሉ የተሰሚነትና የወሳኝነት ቦታ ይኖራቸዋል። በአካባቢያቸው ስለደረሰ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ሁሉ ለድርጅቱ ዋና የመረጃ ምንጭ በመሆንም ያገለግላሉ።

ምንም እንኳን በግንባር ቀደምነት በአማራው ላይ የሚሠራ ድርጅት ቢሆንም እንደሌሎችም ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች በሥራው እውቅና እንዲያገኝ በአንድ አገር መመዝገብ ካለበት የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በሚገኝበት አገር ያለዚያም በዓለም አቀፍ ደረጃ ይህን የሚመዘግብና እንደተባበሩት መንግሥታት እውቅና የሚሰጥ (World Red cross, UNICEF, UNHCR, etc) ድርጅት ካለ በዓለም አቀፍ ደረጃ መመዝገብ ይችላል። ይህን ማጣራትና ለዚህ መንገድ ማግኘት ለዚህ ድርጅት ቀዳሚ ከሆኑት ዓላማዎች አንዱ ነው።

ይህ ድርጅት በየመስኩ የተለያዬ ሥራ ከሚሠሩ እንደ ቀይ መስቀል፣ UNHCR, UNESCO, USAID, World Vision, Medicine san frontier ካሉ፣ የማደጎ ልጆችን ከሚመለምሉና አሳዳጊ ከሚያገናኙ ድርጅቶች፣ ከዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና በየትኛውም መስክ ከተሠማሩ ሕጋዊ ድርጅቶች ጋር በመቀራረብ ይሠራል።

የገንዘብ ምንጭ እና አያያዝ

የድርጅቱ ዋና የገቢ ምንጭ በመላው ዓለም ከሚገኙ አማሮችና ደጋፊዎቻቸው ይሆናል። ይህ ድርጅት በውጭ ለሚገኙ አማሮች በሙሉ እንደ ወኪል፣ እንደድንገተኛ ደራሽ፣ እንደእድር፣ እንደኢንሹራንስ ዋስትና እና እንደ ባንክ ሆኖ ስለሚያገለግላቸው ሁሉም አማራ ሊመዘገብና አባል ሊሆን ይገባል።

ድርጅቱ ድጋፍ በማድረግና ችግሮችን በመፍታት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ከመሆኑ በተጨማሪ በደሎችና ችግሮች እንዳይደርሱ የበደሎችንና የችግሮችን ምንጭ በማድረቅ ላይ ስለሚሠራ በአገር ቤት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ አማራውን ከሚረዱ መንግሥታትና ድርጅቶች ጋራ በመነጋገርና እውቅናውንም ለማጎልበት ከነርሱ ጋር በመቀራረብ ይሠራል። ስለዚህ ኢትዮጵያን በድህነት መቅረፍ፣ በረኃብ፣ በመልሶ ማቋቋም፣ በጤና፣ በሥራ ፈጠራ፣ በመሠረተ ልማት፣ በእርሻ፣ በትምህርት፣ በባህል ወዘተ የሚረዱ መንግሥታትና ድርጅቶች የዓለም አቀፍ የአማራው ተራድዖ ድርጅት ተጨማሪ የገንዘብ ምንጭ ይሆናሉ።

ከዚህ ቀደም ከተገኘው ልምድ በውጭ የሚኖረውን አማራም ሆነ ሌላውን ኢትዮጵያዊ በአንድ ጊዜ ከፍተኛ ገንዘብ (lump sum) እንዲያዋጣ ከማድረግ ይልቅ ትናንሽ ወርኃዊ መዋጮዎች የተሻለ ውጤት ያስገኛሉ።

መዋጮው በአረብ አገራትና በአፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንም የሚያሳትፍ እንዲሆንና በሌሎችም አገሮች የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ደስ እያለው ከወር ወር መዋጮውን መክፈል እንዲችል እጅግ ዝቅተኛ መሆን ይኖርበታል።

እንደማንኛቸውም መሰል ድርጅቶች ገንዘቡ የሚጠራቀምበት (Maturity period) ይኖረዋል።

የገንዘቡ አስተዳዳር ሙሉ በሙሉ ጉዳዩ በቀጥታ በሚመለከታቸው የገንዘብ አስተዳደር ድርጅቶች (Financial Institutions) ይከናወናል። ይህ ለገንዘቡ ሙያዊ አያያዝ ከሚጠቅመው በተጨማሪ በአባላት አማሮች ዘንድ ድርጅቱ ታማኝነት እንዲኖረው ከፍ ያለ አስተዋጾኦ አለው። ይህ ደግሞ ዞሮ ድርጅቱ ዘላቂ እንዲሆን ያደርገዋል።

ይህ የገንዘብ አስተዳደር ድርጅት ከዓለም አቀፍ የአማራው ተራድዖ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ጋራ በመመካከር በመላው ዓለም ተበትነው ከሚገኙ አባላቱ ሳይቋረጥ ገንዘቡ የሚሰበሰብበትን አሠራር ይዘረጋል፣ ገንዘቡን በሥራ ላይ በማዋል የሚያድግበትን መንገድ ይነድፋል፣ ለእያንዳንዱ አባል እንደባንክ አካውንት በመስጠት አባላት አካውንታቸው ውስጥ በሚገቡ ጊዜ ስለሚያዋጡት ገንዘብ ኢንፎርሜሽን እንዲያገኙ ያመቻቻል፣ በየስድስት ወሩ ደግሞ አጠቃላይ ሪፓርት በቀጥታ ለአባላትና ለድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ያቀርባል።

ይህ መነሻ ሀሳብ ሲሆን ውይይት ከተደረገበት በኋላ የሚለወጥ፣ የሚሻሻልና የሚዳብር ስለሚሆን መላው የአማራ ማኅበረሰብ አባላት ሀሳብ እንድትሰጡበት ትለመናላችሁ።

አዲስ አበባ እንደገና የፅንፈኛው ጎራ አጀንዳ ሆናለች። ( ቬሮኒካ መላኩ)

ቬሮኒካ መላኩ
ኅዳር 12 ፣2009 ዓ ም

እኤአ ከ1936 እስከ 1941 ኢጣሊያ በኢትዮጵያ የመሰረተችው አስተዳደር። ምንጭ : "Ethiopia Under Mussolini and the Colonial Experience" By Alberto Sabacci.  via Veronica Melaku
እኤአ ከ1936 እስከ 1941 ኢጣሊያ በኢትዮጵያ የመሰረተችው አስተዳደር።
ምንጭ : “Ethiopia Under Mussolini and the Colonial Experience” By Alberto Sabacci.
via Veronica Melaku

አዲስ አበባ እንደገና የፅንፈኛው ጎራ አጀንዳ ሆናለች። የእነ ኤርምያስ ለገሰ ትንታኔ ተከትሎ ይመስላል ። እንኳን በከተማዋ ብዙ የሰራበት ኤርሚያስ ይቅርና እኔም በፅንፈኞች የሚመራውና ሰበታ የደረሰው የኦሮሞ አመጽ አዲስ አበባ ውስጥ እንደማይገባ 100% እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ምክንያቱም ራሱን በራሱ ማጥፋት የሚፈልግ ማህበረሰብ ስለሌለ፡፡
ለንደን ላይ “ትበታተናለች ” እያለ የፎከረና አትላንታ ላይ “ኮንቬንሽን ” የሚል የዳቦ ስም የተሰጠው የመገነጣጠልን አጀንዳ እያራገበ እንኳን የአዲስ አበባ ሊቀበል ይቅርና ሙሉ ኢትዮፕያ ፉርሽ አድርጎታል።

ከዚህም በተጨማሪ ” አዲስአበባ የማን ናት? ” የሚለው ጥያቄ መልስ አላገኘም ። አማራም የእኛ ናት ይላል ። ኦሮሞውም የእኔ ናት ይላል። በማእከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን መረጃ መሰረት ከ55 % በላይ የከተማው ነዋሪም አማራ መሆኑንም ማወቁ ለብዙ ጥያቄወች መልስ እና ፍንጭ ይሰጣል።


ወያኔ በመጀመሪያ ስልጣን ሲይዝ የተጠቀመው ካርታ እና የፌደራል አወቃቀር ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮፕያን ሲይዝ የተገበረውን ካርታ ነበር ። በብሔር የተከፋፈለች ኢትዮጵያን ካርታ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራው የፋሽስት ጣሊያን ወራሪ በ1936 እ.ኤ.አ ሲሆን፤ አላማውም የጎሳና የብሔር ግጭትንበማነሳሳት ሰላም አልባ ኢትዮጵያን መፍጠር ነበር፡፡ ጣሊያኖች ለገዛ አገራቸው ለእነ ሮማ እና ቬነስ ያላደረጉትን የብሔር ክፍፍል ካርታ ለእኛ ለመስጠት ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነበር፡፡

ከ50 ዓመት በኋላ ግን በአቶ መለስ ዜናዊ አማካኝነት የጣሊያኖች ምኞት ሊሳካ ችሏል፡፡ ልዩነቱ የጣሊያን ካርታ በዚህ ሰሞን ግራና ቀኛቸውን መለየት የተሳናቸው
የኦሮሞ ፅንፈኞች የሚሟገቱበትን የአዲስ አበባንና አካባቢዋን የኦሮሞ ሳይሆን የአማራ ግዛት አካል ማድረጉ ነበር፡፡ጣሊያን አማራን የሚባለውን ብሄር አምርሮ ቢጠላም አዲስአበባ እና ሸዋ የዚህ ብሄር ታሪካዊ ግዛት መሆኑን ተቀብሎ ነበር ። መለስ ዜናዊና ኦነግ የአማራን ብሄር ከጣሊያን የበለጠ ይጠሉ ስለነበር አዲስአበባን ከአማራ ክልል ካርታ ላይ ሊፍቁት ችለዋል።


በሌላ ወገን የወያኔ-ትግሬ ፍርሃት በሰሜናዊና ምስራቃዊ አዲስ አበባ ላይ አለ፡፡ በክልሎች ክፍፍል ጊዜ ኦነግና ወያኔ ሃገር ሲከፋፈሉ አማራ ክልል መግባት የሚገባቸው ነገር ግን ሆን ተብለው ያለአግባብ ወደትግራይ፣ ኦሮሚያና አዲስ አበባ ክልል የገቡ ብዙ ቦታዎች አሉ፡፡ ኦነግም በጊዜው የትክፍፍሉ አካል ስለነበር ሁኔታውን ከሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች የተሻለ ይረዳል፡፡ በጊዜው ተነስተው ከነበሩት ጥያቄዎች መካከል የፍቼ አማራነት ጥያቄ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ወያኔ ምስራቃዊ አዲስ አበባ የአማራ ክልል ግዛት አድርጎ ስለሚያስበው ፋብሪካዎችና መሰረተ ልማቶች ባጠቃላይ ማለት በሚቻል መልኩ ከምስራቃዊና ሰሜን ምስራቃዊ አዲስ አበባ በራቁ ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲገነቡ ያደርጋል፡፡

አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ ቁጥር የሌላቸው ፋብሪካዎችና ኢንቨስትመንቶች የተሰሩትና የታቀዱት በናዝሬት መስመር፣ በሰበታ አካባቢ ነው፡፡ በደብረ ብርሃን መስመር በስህተት ከተሰሩ ጥቂት ፋብሪካዎች በስተቀር ምንም የለም፡፡ ወያኔ ይህንን ያደረገው በአማራ ጥላቻ ነው፡፡ ኦነግ ደግሞ ይህንን የሚያየው በተቃራኒው በመሬት ነጠቃ ነው፡፡

———
ቬሮኒካ መላኩ (የብዕር ስም ይመስላል) በፌስ ቡክ ላይ ትችት አዘል አስተያየት በመጻፍ ትታወቃለች።

ጽሁፉን ማጋራት አይርሱ።

የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር 31 ሚሊዮን፣ 7 ሚሊዮን ወይስ 50 ሚሊዮን ! – ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

ህዳር 22 ፣ 2016 ዓ.ም

መግቢያ

Oromoያለፉትን 40 ዓመታት ፖለቲካችንን ለመረመረ አገርን በሚመለከት የሚሰነዘሩት አስተያየቶች ወይም የሚሰጡት ትንተናዎች ሁሉ ሳንይሳዊ ይዘት ይኑራቸው አይኑራቸው የሚጠይቅ የለም። በተለይም ፖለቲካ ፍልስፍናዊ መሰረት ያለው ታላቅ ፅንሰ-ሃሳብ መሆኑ ግንዛቤ በሌለበት አገርና፣ ማንኛውም ህብረተሰብንና የአገርን አጠቃላይ ሁኔታ በሚመለከት ረገድ የግዴታ ሳይንሳዊ ትንተና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ቀርቶ ስሜት ዋናው መመሪያ በሆነበት አገር የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ትክክል መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ቁጭ ብሎ በሰከነ መንፈስ ለመመርመር የሚቃጣ ሰው በፍጹም የለም።

እንደሚታወቀው በተለይም በአብዮቱ ወቅት ሳይንስና ፍልስፍና መመሪያ መሆናቸው ቀርቶ ስሜት የፖለቲካውን መድረክ በመያዙ እንደተከታተልነው ለብዙ መቶ ሺህ ህዝብ መሞትና ለአገር ውድመት የራሱን አስተዋፅዖ አበርክቶ አልፏል። ዛሬ አገራችን ለምትገኝበት እጅግ አስቸጋሪና አደገኛ ሁኔታ በአብዮቱ ወቅት የተከሰተውና የተካሄደው ስሜት አዘል ፖለቲካ በተለይም የፖለቲካ ተዋናይ ነን የሚሉትን ጭንቅላት በመያዙ ከሳይንሳዊ ትንተናና ውይይት እንዲሁም ክርክር ይልቅ ስሜት በመቅደሙ ሁሉም የሚፈራራና የሚገዳደል ወደ መሆን አበቃ። ይህ ቁስል ዛሬም ያለና ከአብዮቱ የተረፈው የተወሰነ ኃይል ዛሬም ከቂም-በቀል ፖለቲካውና ሰውን ከማስፈራራት ለመላቀቅ  ያልቻለ ሆኖ እናገኘዋለን።  አብዮቱ ከሸፈና ወደመ ከተባለ ከአርባ ዓመት በኋላም የጭንቅላት ተሃድሶ ባለመካሄዱ የድሮው ዐይነት በተለይም በተንኮልና በቂም በቀል ላይ የተመሰረተው ፖለቲካ የሚሉት ፈሊጥ አሁንም እንዳሰፈሰፈ እንመለከታለን።

ባለፉት 25 ዓመታት በአገራችን ምድር የተንሰራፋውን እጅግ አሳዛኝና አገር አፍራሽ ሁኔታ በምንመረምርበት ጊዜ ዋናው ምክንያት በተለይም በፖለቲካ መድረክ ውስጥ የሚሳተፉት ሰዎች ወይም ድርጅቶች አዕምሮ የቱን ያህል ያልበሰለና መንፈሰ-አልባ መሆኑን ነው የምንገነዘበው።  በክርክርና በውይይት ያልታነፀ ጭንቅላት፣ በተለይም ደግሞ ፍልስፍናና ሳይንስን መመሪያው ያላደረገና፣ በየጊዜው አስተሳሰቡንና ድርጊቱን ለመመርመር የማይችል ኃይል የመጨረሻ መጨረሻ የታሪክ ወንጀል ሰርቶ እንደሚሄድ መገንዘብ እንችላለን። ከዚህ ስንነሳ የምንገነዘበው ዋና ሀቅ ለአገራችን መዘበራረቅና ውድመት ተጠያቂው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን የፖለቲካ ኤሊት የሚባለው እንደሆነ መረዳቱ ከባድ አይሆንም።

ስለሆነም በእልክና በአወቅሁኝ ባይነት፣ እንዲሁም ለከፋፍለህ ግዛ እንዲያመች፣ ይሁንና ደግሞ የመጨረሻ መጨረሻ ራሳቸው የተንኮሉ ጠንሳሽ የሆኑ ሰዎችንም ብዙም የማያራምዳቸው በቋንቋ ላይ የተመሰረተ የብሔረ-ሰብ ክልላዊ አስተዳደር የሚሉት ፈሊጥ አዳዲስና ጭንቅላታቸው ያልበሰለ ወጣቶችን በመፈልፈሉ የፖለቲካውን መድረክ አጣበውታል። አገዛዙና የውጭ ኃይሎች አገራችንን ለማዳከምና ለመበታተን በፈጠሩት የታሪክንና የህብረተሰብን ህግ ያላካተተ ፌዴራላዊ የክልል ፖለቲካ ተግባራዊ በመሆኑ፣ በተለይም በዛሬው ወቅት የወያኔ አገዛዝ በህዝባችን ላይ በሁሉም አቅጣጫ የከፈተውን ጦርነትና በህዝባችን ላይ የሚፈጽመውን ፋሺሽታዊ ድርጊት ለመዋጋት ኃይላችንን መሰብሰብና በጋራ መታገል ሲገባን የብሔረሰብ-አጀንዳ ሜዳውን በማጣባብ የብዙዎቻችንን አመለካከትና የትግል ስትራቴጂ እየቀየረው መጥቷል ማለት ይቻላል። አገዛዙ የሚያካሂደውን አገር አውዳሚ ድርጊትና በህዝባችን ላይ የሚፈጽመውን ፋሺሽታዊ ጭፍጨፋ ለማቆምና በአገራችን ምድር ሰላም እንዲመጣ ከመታገል ይልቅ የሁላችንም ፍርሃት ይህች አገር ልትበታተን ነው፤ እንዴት አድርገን ነው ይህ ሁኔታ እንዳይከሰት መታገል ያለብን“  በሚለው ላይ እንድናተኩር  ተገደናል።

የዛሬውን የተተረማመሰ ፖለቲካ ለራሳቸው ስልጣን መወጣጫና ከውጭ ኃይሎች ጋር በመመሰጣጠር አገራችንን ወደ ልዩ አቅጣጫ ለመውሰድ የሚፈልጉ ኃይሎችና፣ በዚያውም መጠን የድህነቱን፣ የተበዝባዥነቱንና የኋላ-ቀርነቱን ዘመን  ለማራዘም የሚፈልጉ ኃይሎች የፖለቲካ ሜዳውን ወጥረው በመያዝ የአብዛኛዎቻችን አመለካከት ሊቀይሩት በቅተዋል። በተለይም ለንደን የተካሄደውና ከአንድ ሳምንት በፊት ደግሞ አትላንታ የተካሄደው የኦርሞ መሬዎች ስብሰባ„          (Oromo Leadership Convention) የሚባለው ስብስብ ላይ የተሰጠውን ፓለቲካዊና ሳይንሳዊ ትንተና ሳይሆን ከምሁራን የማይጠበቅ  ሀተታ-መሳፍንት አብዛኞቻችንን እንድንጯጯህ ሲያደርግ፣ አንዳንዶቻችንን ደግሞ አስደንግጦናል። ይህንን ዐይነቱን ህብረተሰብን አፍራሽና ኋላ-ቀርትነትን እዚያው ፈርጥሞ እንዲቀር ከሚያደርገው ስብሰባ ላይ የሚሰነዘረውን አስተያየትና በየቴሌቪዥኑም የሚስተጋባውንና፣ የወጣቱን መንፈስ የሚበርዘውን በታሪክና በሳይንስ ያልተደገፈና ሊረጋገጥ የማይችል አመለካከት ካለምንም ርህራሄ መዋጋት የሚያስፈልግ ይመስለኛል። እንደምከታተለው ከሆነ መሪ ነን የሚሉት ሰዎች ጭንቅላት የደነደነ ስለሆነና፣ ለጊዜውም ቢሆን የልብ ልብ ስለተሰማቸው ከእነዚህ ሰዎች ጋር በቲዎሪና በሳይንስ ላይ የተመሰረተ ውይይትና ክርክር ማድረግ በፍጹም የሚቻል አይመስለኝም። ስይንሳዊና የቲዎሪ ክርክርና ውይይት የሚገባቸው አይመስለኝም። ስለዚህም ያለው አማራጭ መንገድ እየመላለሱ ሌላው እንዲረዳው እነሱን በሳይንሱ መንገድ መዋጋቱ ፍቱንና ሊታለፍ የማይችል መሳሪያ ነው ብዬ አምናለሁ።

ችግሩ የዘመናዊነትና የተሃድሶ እጦት ወይም የብሔረ-ሰብ ጥያቄ !

የብዙ አገሮችን ታሪክና የህብረተሰብ አገነባብን ታሪክ ለተመለከተ ብዙ ውጣ ውረድ እንደሚያስፈልገው መረዳት ይቻላል። በመጀመሪያ ደረጃ ማንኛውም ነገር ከአንድ ሁኔታ በመነሳት እንደየሁኔታው ኑሮን ለማሸነፍ በሚደረገው ሂደት ውስጥ እየተሰበጣጠረና ከሌሎች ጋር እየተቀላቀለ፣ በዚያው መጠንም የመጀመሪያው አስተሳሰቡ እየከሰመና አድማሱ እየሰፋ ይመጣል። የማደግ፣ የመበሰጣጠርና፣ እንዲሁም ከሌላው ጋር በመቀላቀልና በመጋባት፣ የአስተሳሰብ አድማስን ማስፋት የሚቻለውና እያንዳንዱ ግለሰብም ከተተበተበበት ዕድገትን ከሚያደናቅፍ ወይም ትራዲሺናል ቫልዩ(Traditional Values) በመላቀቅ ራሱን በራሱ ማግኘት የሚችለው በዚያ ህብረተሰብ ውስጥ በአንዳች ተዓምር ብቅ የሚሉ ግለሰቦች ጥያቄ መጠየቅ ሲችሉና ስርዓቱን መጋፈጥ የቻሉ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብን ማዳባር በተለያዩ ህብረተሰቦች ልዩ ልዩ ዐይነት መልክ የያዘ ቢሆንም፣ የበለጠ መዳበር የቻለው በጥንታዊቱ ግሪክና፣ በአውሮፓ ምድር ደግሞ ከአስራአራተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ ነው ማለት ይቻላል።

ይህ ዐይነቱ ተሃድሶና መሻሻል የበለጠ እየተስፋፋ ሲመጣ በአንድ አካባቢ የሚኖር ህዝብ በዚያው ባለበት ረግቶ እንዳይኖር ተገደደ። በቴክኖሎጂና በሳይንስ እንዲሁም በከተማዎች ማደግ ምክንያት የተነሳ ከተለያየ ቦታ ፈልሰው የሚመጡ ሰዎች በመኖርና የመፍጠር ችሎታቸውንም በማሳደግ  መቋቋም ሲችሉ ከዚያ በፊት የነበራቸውን ውስን አስተሳሰብ አሽቀንጥረው በመጣል ከአዲሱ ሁኔታ ጋር የበለጠ እየተላመዱና ከሌላ ክልል ከመጣው ጋር በመጋባት ራሳቸውን የዚህ ወይም የዚያ ብሔረ-ሰብ አካል ነኝ ብለው ሳይጠሩ የሚኖሩበት አካባቢ አካል መሆናቸውን እየተገነዘቡ መምጣት ቻሉ። የማደግና በህብረተሰብ ውስጥም ተቀባይነትን የማግኘት ኃይል ሊወሰን የሚችለው እያንዳንዱ ግለሰብና ኩሙኒቲ በታታሪነትና በሰለጠነበት ሙያ ለህብረተሰቡ በሚያደርገው አስተዋፅዖ ብቻ እንጂ ከዚህ ወይም ከዚያ ብሔረ-ሰብ በመምጣቱ እንዳይደለ ግንዛቤ ውስጥ ተገባ። ከዚህም በመነሳት እያንዳንዱ ግለሰብ የራሱን ዕድል ራሱ ወሳኝ መሆኑን ሲገነዘብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አንዱ ከሌላው የተሻለ ሆኖ ለመገኘት ሲል የፈጠራ ችሎታውን በማሻሻል ራሱን ማሳደግ የኑሮው ፍልስፍና ድርጎ ለመውሰድ በቃ። በዚህ መልክ ሁሉም በየችሎታው በመሰመራት ሰፋ ላለ የአመራረት ዘዴ ሁኔታዎችን አመቻቸ። የበለጠ ሊያመርት የሚችልበትን የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በመፍጠር ራሱን ማሳደጉ ብቻ ሳይሆን፣ ለህበረተሰብአዊ ዕድገትም ከፍተኛ አስተዋፅዖ  ማበርከት ቻለ።

በዚህ መልክ የዳበረው የስራ-ክፍፍልና እያንዳንዱ ግለሰብ ራሱን በራሱ አግኝቶ ማደግና ራሱን መግለጽ መቻል ቀሰ በቀስ ከዳበረው የፖለቲካ ፍልስፍና አስተሳሰብና ተግባራዊ እየሆነ ከመጣው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር በመጣመር የኋላ ኋላ ህብረ-ብሔር ወይም ኔሽን(Nation) ለሚለው አስተሳሰብ መሰረት በመጣል ለካፒታሊዝም ዕድገት በር መክፈት ቻለ። በሌላ አነጋገር፣ የብሔርና የብሔራዊ ስሜት አስተሳሰብ (Nation and Nation-hood) ቀስ በቀስ ሊዳብሩና መሰረታቸውን ማረጋገጥ እየቻሉ መምጣት ከአስተሳሰብ መዳበር፣ በስራ-ክፍፍል(Division of Labour) ማደግና መስፋፋት ጋር የተያያዙ እንደሆን ብቻ ነው። ለምሳሌ በዘመነ ፊዩዳሊዝም ወይም በከብት እርባታ ላይ ብቻ ተሰማርቶ የሚገኝ ህዝብም ሆነ ብሔረ-ሰብ እንደ አንድ ብሔር ሊታይ በፍጹም አይችልም። አንድ ህዝብ ብሔር ሆኖ እንዲጠራ ከተባለ ለስራ-ክፍፍል መዳበርና ለቴክኖሎጂ ግኝትና ምጥቀት አስፈላጊውን መሰረት በመጣል በዚያው መጠንም የአስተሳሰብ መጎልመስን መቀዳጀት መቻል አለበት።

የእኛንና ዛሬ በጎሳና በሃማኖት የሚተራመሱ አገሮችን ሁኔታ ስንመለከት ያለው ችግር በየጊዜው የአስተሳሰብ ለውጥ ለማድረግ ያለመቻልና ጥያቄ ለመጠየቅ ዝግጁ ያለመሆን ነው። እንደሚታወቀው አንድ ሰውም ሆነ አንድ ህዝብ ጥያቄ ሲጠይቅ ብቻ ነው መልስ ለማግኘት የሚችለው። እንደሚታወቀው ራስን እየመላለሱ መጠየቅ የሎጂካዊ አስተሳሰብና የሳይንሳዊ ግኝት ዋናው መክፈቻ መንገድ ነው። በተለይም ከሬናሳንስ ጀምሮ ያለውን የአውሮፓውን የህብረተተሰብ ዕድገት ሁኔታ በምንመረምርበት ጊዜ ጥያቄ መጠየቅና ለአንድ ለተዘጋ ነገር መልስ ማግኘት መጣጣር ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ ዕድገት ዋናው ቁልፍ ነገር መሆኑን መገንዘብ እንችላለን። ጥያቄዎችን መጠይቅና ራስን ማስጨነቅ፣ እንዲሁም ደግሞ የመከራከር ልምድ በሌለበት አገር ዕውቀትን ከማዳበር ይልቅ ጭቅጭቅና መነዛነዝን ማስቀደም ይቀድማል። ሰለሆነም እያንዳንዱ ግለሰብ ሎጂካዊ በሆነ መልክ በማሰብና ከመከራከር ይልቅ ወደ ንትርክና እንዲያም ሲል ወደ ድብድብ ያመራል። ብዱናዊና ክልላዊ ስሜት ባየለበት እንደኛ ባለበት አገር ደግሞ የባሰውኑ ወደ ጦርነት በማምራት ታሪክን ማፈራረስና ህዝብን ማፈናቀል እንደሙያ ተደርጎ ይወሰዳል። በዚህም ምክንያት የተነሳ የብሔረ-ሰብ ፖለቲካንም ሆነ ወይም ብሔራዊ ፖለቲካን እናራምዳለን የሚሉትን ሁሉ በምንም ዐይነት በክርክርና በጥሞና ውይይት ማስተማር፣ መማር፣ ማሳመንና ማመን በፍጹም አይቻልም። ጭንቅላታቸው በተወሰነ አስተሳሰብ ስለተቀረጸና ህይወታቸውም ከመጠርጠር ጋር የተያያዘ በመሆኑ የነገሮችን ሂደት በሎጂካዊ መንገድ ለማሳመን በፍጹም አይቻልም። በደነደነው አስተሳሰባቸው በመግፋት የአገር አፍራሽ ተግባራቸውን በተለያየ መንገድ ያፋጥኑታል። ስለሆነም እየተጯጯሁና እየተደናበሩ መኖር ትግል የሚሉት ፈሊጥ ዋናው ስልት ከመሆን አዳዲስ አስተሳሰቦችን በማዳበር ወደ ፊት መጓዝ በፍጹም አይቻልም። በዚህ ዐይነቱ ትግል በሚሉት ፈሊጥ የኋሊት ጉዞ የሚሄዱ ነው የሚመስለው እንጂ እንደሰለጠነ ሰው በሳይንሱ መንገድ ለመወያየትና ለመከራከር በፍጹም አይችሉም።

ወደ መነሻዬ ልምጣና፣ በአገራችን ምድር ውስጥ የጭንቅላት ተሃድሶና ከዚህ ጋር የተያያዘ ቴክኖሎጂያዊ ለውጥ(Technological Revolution) ባለመካሄዱ አሁንም  ስለብሔረ-ሰብ ጭቆናና በቁጥር ስለመብለጥና አለመብለጥ፣ እንዲሁም ከቁጥር መብለጥ ጋር የሚመጣጠን ፖለቲካዊ ድርሻ ስለማግኘት ጉዳይ እያነሳን ችግርን ወደ ማይፈታ  ጭቅጭቅና ንትርክ ውስጥ በመግባት ተፈጥሮ የሰጠንን የማሰብ ኃይል ብቻ ሳይሆን፣ እንዲሁም የማቴርያል ሀብትም እናወድማለን። ዋናው ችግራችንም የብሔረ-ሰብን ጥያቄ አድርገን በመወሰድና በማመን መሰረታዊና ለሰው ልጅ ከሚያስፈልገውና የሰውን ልጅ ችግር ከሚፈታው ሳይንሳዊ ምርምር እንሸሻለን።

    በቁጥር ብልጫ ላይ የተመሰረተ አስተዳደር የአንድን ህዝብ ችግር ሊፈታ አይችልም !!

የታሪክንና የህብረተሰብን ሂደት ማህደር በደንብ ሳያገላብጡና ሳይመረምሩ የኦሮሞ ኤሊት ነን ባዮች ቀድሞሞ ሆነ ዛሬ እየመላለሱ የሚነግሩን የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ከቆዳው ስፋትና ከቁመቱ ጋር የሚመጣጠን የፖለቲካ ስልጣን አልተሰጠውም„ እያሉን ነው። ይህንን ዐይነቱን አስተሳሰብ ሲያስተጋቡና ሲያስፋፉ ምን ለማለት እንደፈለጉ ለማብራራት ባይችሉም፣ ውስጣዊ ይዘቱን ስንመረምረው ግን ሊሉን የሚፈልጉት በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ውስጥ አንድ ብሔር ብቻ ለብዙ መቶ ዓመታት የፖለቲካ ስልጣንን በመጨበጥ ሀብታችንን(Resources) በመበዝበዝና ዕድላችንን በመወሰን ወደ ኋላ እንድንቀር አድርጓል ይሉናል። ብዙም ሳይራመዱ ደግሞ እዚያው በዚያው ከብዙ መቶ ዐመታት በፊት ተግባራዊ እናደርግ የነበረውን ለዲሞክራሲ ማበብ፣ ለነፃነት መስፋፋትና ለቴክኖሎጂ ፈጠራ የማያመቸውን የጋዳ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ እንፈልጋለን ይላሉ። ይሁንና ግን በዚህ ዐይነቱ ስርዓት እንዴት አድርገው ቴክኖሎጂን በማሳደግ ብሔራዊ ሀብት አዳብረው ህዝባቸውን ከድህነት እንደሚያላቅቁት በፍጹም አይነግሩንም። በአጠቃላይ ሲታይም ምን ዐይነት ህብረተሰብ ለመመስረት እንደሚፈልጉም አያስረዱም ወይም አያብራሩም። በአስተሳሰቡ አንድ ወጥ የሆነ፣ አንድ ሃይማኖት ያለው፣ በስራ-ክፍፍል ያልዳበረ፣ ወይንስ ደግሞ የተሰበጣጠረና በስራ-ክፍፍል ላይ በመሰማራት የራሱን ዕድል ራሱ በመወሰን ራሱን በራሱ አግኝቶ ህብረተሰቡንም የሚጠቅም ስርዓት ለመገንባት ፟? ከዚያም በመነሳት የገበያ ኢኮኖሚና ካፒታሊስታዊ ስርዓት ለመገንባት ወይስ ዝም ብሎ ብቻ በከብት እርባታና በሳይንስ ላይ ባልተመሰረተ የእርሻ ክንዋኔ ላይ ብቻ  በመሰማራት የሚኖር ብሔረ-ሰብ ነው ? ለመመስረት የሚፈልጉት። ይህንን ጉዳይ ግልጽ ካላደረጉ ደግሞ ዝም ብለው ነው የሚደናበሩት ማለት ነው። አዲሶቹ የኦሮሞ ኤሊት ነን ባዮች እየደጋገሙ ስለብሔረ-ሰባቸው መጨቆን ሲነግሩን ጠቅላላው ኦሮሞ እያሉ የሚጠሩት የህብረተሰብ ክፍል ምንም ዐይነት የዲያሌክት ቋንቋ ልዩነት እንደሌለውና፣ የሚያልመው ህልምና ፍላጎቱ አንድ ዐይነት እንደሆነ፣ ሲነሳም ሲተኛም በአንድ ጊዜ እንደሆነና፣ ሃይማኖቱም አንድ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን፣ በስራ-ክፍፍልና በመደብም ሆነ በገቢ እንዲሁም ደግሞ በህሊና አወቃቀር(Pyscholigical makeup) ያልተከፋፈለ ወይም ያልተለያየ(undifferenciated) እንደሆነ ነው ለማሳመን የሚሞክሩት። ይህ ዐይነቱ አካሄድ ደግሞ ኢ-ሳይንሳዊ አቀራረብ ነው። ለዕቅድና ለዕድገት የሚያመች አቀራረብ አይደለም።

ያም ሆነ ይህ አንድን ወጣት ትውልድ ለማደናበርና ጭንቅላቱን አጨልሞ በጥላቻ መንፈስ እንዲወጠር ከማድረግ በስተቀር በብዙ መንገድ እንደተረጋገጠው በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ዕድገትና የአገዛዝ ታሪክ ውስጥ፣ በተለይም ከ14ኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ አንድ ብሔረ-ሰብ ብቻ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነትን በመቀዳጀት የሌሎችን ብሔረ-ሰቦች ዕድል ያጨለመበትና ለኋላ-ቀርነታቸውም ምክንያት የሆነበት ሁኔታ የለም። የኢትዮጵያን የፖለቲካ አወቃቀር ስንመለከት በስልጣን ላይ የተቆናጠጡት ኃይሎች ሁሉ በተለያየ ሁኔታ ከዚህኛውም ሆነ ከዚያኛው ብሔረ-ሰብ ጋር በደም የተሳሰሩ እንደነበር ታሪክ ያረጋግጣል። በተለይም ኦሮሞዎች በተለያዩ አቅጣጫዎች መስፋፋት ከጀመሩ ከ16ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ የፖለቲካ ማትሪክሱን በመጋባትና በመዋለድ የህብረተሰቡን አወቃቀር እንደለወጡት መገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም ስምንት መቶ ዓመት ያህል አንድ ብሔረ-ሰብ ብቻ ነው ሲገዛን የነበረው፣ ከህዝባችን ስፋት ጋር የሚመጣጠን የፖለቲካ ስልጣንና ሀብታችንን ወይም ሬሶርሳችንን የመቆጣጠር ዕድል አላገኘንም የሚለው የተረት ተረት ወሬ ብቻ  እንጂ በታሪክም ሆነ በሳይንስም የሚረጋገጥ ጉዳይ አይደለም። ስለ አገሪቱ ኋላ-ቀርነት ሲወራ ደግሞ ፖለቲካዊ፣ ባህላዊና ከውጭው ዓለም ከነበረን እጅግ ከላላ ግኑኝነት ጋር የሚያያዝ እንጂ የአንድ ብሔረ-ሰብ የበላይነቱን በመቀዳጀቱ የተከሰተ ችግር እንዳልሆነ መገንዘብ ይቻላል፟።

ስለሆነም በኢኮኖሚና በማህበረሰብ ያለማደግን ጉዳይ ስንመለከት አንድን ብሔረ-ሰብ የሚመለከት ብቻ ሳይሆን፣ ጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለስልጣኔና ለዕድገት የሚያመች ዕድል በታሪኩ ውስጥ እንዳላጋጠሙት እንመለከታለን። በተለይም በ20ኛው ክፍለ-ዘመን በውስን መልክ በዘመናዊነት(Modernization) ስም የገባው የኢንዱስትሪ ፖለቲካው የነበረውን ስርዓት የባሰውኑ ድህነትን ከመፈልፈል በስተቀር አጠቃላይ የሆነ ብሔራዊ ሀብት(National Wealth) እንዳላዳበረና፣ ጠቅላላውን ህዝብ እንዳልጠቀመ በምድር ላይ የሚታየው ሀቅ ራሱ በቂ ማስረጃ ነው። ስለዚህም ስለ ዕድገትና ስለ ኋላ-ቀርነት በሚነሳበት ጊዜ ነገሩን፣ 1ኛ) ከምሁራዊ ብስለትና ሰፋ ያለ ክርክር ካለመኖር ጋር ማያያዝ ያስፈልጋል። 2ኛ) በዚህም ምክንያት የተነሳ በራሱ የማሰብ ኃይል ሊዳብርና ሊንቀሳቀስ የሚችል የተገለጸለት የህብረተሰብ ኃይል(Middle Class) መፈጠር ባለመቻሉ ስርዓቱን መጋፈጥ አልተቻለም። በመሆኑም የፊዩዳሉ ስርዓት ዘመናዊ ከሚባለው ጋር በመቆላለፍ የአስተሳሰብ ግድፈት እንዲስፋፋና ድህነት መለዮአችን እንዲሆን ተደረገ። 3ኛ) አገዛዙ ራሱ የተከተለው ለፈጠራ የማያመች  የኢንዱስትሪ ፖለቲካ ሰፋ ያለ በስራ-ክፍፍል ላይ የዳበረ የውስጥ ገበያ እንዳይዳብር አገደ። ይህም ማለት ስለአንድ ብሔረ-ሰብ መበደል ወይም መጨቆን በምናውራበት ጊዜ ከጠቅላላው የአገሪቱ ፖሊሲና፣ ከአገዛዙ ውስን አስተሳሰብ ነጥሎ ማየት ከባድ ስህተት ነው። በተጨማሪም ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረው አዲሱ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሚሊታሪ ሁኔታ ለእኛ ዕድገት አመቺ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን የዚህን ውስብስበ አዲስ ሁኔታ የመረዳትና ስትራቴጂ የመቀየስ ምሁራዊ ኃይል አልነበረነም። ስለሆነም በተለየያ የዕውቀት ዘርፎች ላይ በመሰማራትና አድማሳችንን ለማስፋት ዕድል ባለማግኘታችን ከውስጥ ያለውን ኋላ-ቀርነትን ከሚያራምደው ፖለቲካና ከውጭ የሚመጣውን ግፊት ደግሞ መጋፈጥ አልተቻለም። ዛሬም ያለን ዋናው ችግር እንደዚህ ያለውን ምህራዊ ዝግጅት ያለማድረጉ ነው። ማንኛውንም ነገር ለመቆጣጠር የሚቻለው ሰፋ ያለ የበሰለ የሳይንስና የምሁራዊ ኩሞኒቲ ሲኖር ብቻ ነው። አገር ወዳድነትና ዕድገትም መዳበር የሚችሉት በዚህ አማካይነት ብቻ ነው።

በቁጥር መብለጥና ይህንን ተመርኩዞ ተወካይነትን ከዚያው ብሔረ-ሰብ ለወጣ የፖለቲካ ኤሊት ኃላፊነትን ስለመስጠቱ ጉዳይ ስንመለከትና በኢምፔሪካልም ለማረጋገጥ እንደሚቻለው ይህ ዐይነቱ የፖለቲካ ስሌት አካሄድ በፍጹም ሊስራ የሚችልና ለዕድገትም የሚያመች አይደለም። እንደሚታወቀው ከአንድ ብሔረ-ሰብ የተውጣጣ ብቻ ሳይሆን፣ ከተለያዩ ብሔረ-ሰቦች የተውጣጣ የፖለቲካ ኤሊትም ሆነ የገዢ መደብ ራሳቸው ባዳበሩት ቲዎሪና ሳይንስ ስለማይመሩ የባሰውኑ ከዕድገት ይልቅ ፀረ-ዕድገትን ነው የሚያስፋፉት። ሀብትን ከመቆጣጠር ይልቅ ሀብት በውጭ ኩባንያዎች እንዲመዘበርና አካባቢ ወድሞ ህብረተሰብ እንዲመሰቃቀል ከማድረግ በስተቀር ሀብትን በስርዓት የመቆጣጠርና ቴክኖሎጂዎችን የማዳበር ዕድል በፍጹም አይኖርም።  የዓለም አቀፍ ኮሙኒቲውን የሚወክሉት ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች(IMF & World Bank) የማይሆን ምክር በመምከርና ተፅዕኖም በማድረግ የባሰውኑ ድህነት እንዲስፋፋና ነፃነትም እንዲገፈፍ ያደርጋሉ። ይህንን ጉዳይ በብዙ አገሮች የምንመለከተው ሃቅ ስለሆነ የኦሮሞ ኤሊት ነኝ ባዩ ከዚህ ዐይነቱ አጋር አፍራሽ ዕድል ሊያመልጥ አይችልም።

ይህ ዐይነቱ አካሄድ በተለይም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተሞክሮ በፍጹም አልሰራም። የደቡብ አፍሪካ ጥቁሩ ህዝብ ወይም የህብረተሰብ አካል ከአፓርታይድ ለመላቀቅ ያደረገው ትግልና ለጊዜውም የተጎናጸፈው ዕድል የሚደገፍ ቢሆንም፣ ከ25 ዓመት በኋላ ጥቁርን እንወክላለን ከሚል አገዛዝ ስፊው ጥቁር የህብረተሰብ ክፍል የዕድገት ተጠቃሚ ሊሆን በፍጹም አልቻለም። የኤኒሴ(ANC) አገዛዝ ተግባራዊ እንዲያደርግ በተገደደው የኢኮኖሚ ፖሊሲ(Neo-Liberal Economic Policy) አማካይነት፣ ጥቂት የፓርቲው ካድሬዎች ተጠቃሚ ከመሆንና ሀብት ከማካበት በስተቀር የሰፊው ጥቁር አፍሪካዊ ህይወት ሊሻሻል በፍጹም አልቻለም።  የዚህ ዐይነቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲና ሀብትን ማካበት ውጤት ማህበራዊ ቀውስና(Social Crisis) ከዚህ ጋር የተያያዘ ወንጀለኝነት መስፋፋታና በኤድስ በሽታ መለከፍ ነው። እንደምንሰማው የአገዛዙ አባሎች ከውስጥም ሆነ ከውጭ የንግድ ሰዎች ጋር በመመሰጣጠር ሀብት የሚያሸሹና የተቀረውንም በማከማቸት ራሳቸው ተንደላቀው እንዲኖሩ ሆነዋል። ስለሆነም በጥቁር ይበልጣል የሚባለው የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ በራሱ ኤሊት ቢወከል ከመቆርቆዝና ሀብቱ ከመበዝበዙ በስተቀር የስልጣኔን ዕድል በፍጹም ሊጎናጸፍ አይችልም ማለት ነው። በሌላ አነጋገር፣ ጥያቄው በቁጥር በልጦ የመገኘቱ ጉዳይ ሳይሆን በሳይንስ ጭንቅላቱ የዳበረ ሰፋ ያለ ምሁራዊ ኃይልና ህብረተሰቡንም ለመለወጥ ዝግጁ የሆነ፣ እንዲሁም ህዝቡንና አገሩን ወዳጅ ኃይል ለዕድገት እጅግ ወሳኝ መሆኑን የህብረተሰብን ዕድገት ታሪክ ላገላበጠ መገንዘብ ይቻላል። አገር ወዳድነትና ህዝብን መውደድ ደግሞ ከብሔራዊ ባህርይ ጋር የሚጣመሩ ሲሆን የብሔረ-ሰብን አርማ ለሚያራግብ አገር ወዳድነትና ህዝብ ማለት ምን እንደሆኑ አይገባውም።

                    በሳይንስና በሎጂክ ሊደገፍ የማይችል የቁጥር ብዛት !!

የኦሮሞ ኤሊቶች እየደጋገሙ የሚሉን ጠቅላላው ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ ውስጥ በቁጥር በልጠን የምንገኘው እኛ ስለሆን ስልጣኑም ለኛ የሚገባ ነው፣ ካለበለዚያ ተገንጥለን የራሳችንን ግዛት እንመሰርታለን እያሉ ነው የሚያስፈራሩት። ለብዙ ዓመታት ይህንን ያህልም ሳይረጋገጥ በአብዛኛዎቻችን ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው የኦሮሞ ብሔረሰብ ቁጥር 31 ሚሊዮን ያክላል እየተባለ ነበር። ከሁለት ሳምንት በፊት አውስታራሊያ ለሚገኘው የአማርኛ ራዲዮ አዘጋጅ ለሆነው ለአቶ ካሳሁን ዶ/ር ሃይሌ ላሪቦ በሰጡት ሰፊና ትምህርታዊ ትንተና የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር  ከ7 ሚሊዮን እንደማይበልጥ እቅጩን ነግረውናል። አሁን ደግም የኦሮሞ የአመራር ኮንቬንሽን ላይ ከተሳተፈ ግለሰብ በቃለ-መጠይቅ ምልልስ የሰጠው መልስ የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ከ50 ሚሊዮን በላይ እንደሚቆጠር ነው።  እነዚህን የተምታቱ ቁጥሮች ስሰማ፣ ብዙ ካሰላሰልኩ በኋላ የደረስኩበት መደምደሚያ የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ከማንኛውም ደም ጋር ሳይቀላቀል  በንጹህ መልክ ይህንን ያህል ቁጥር ሊኖረው አይችልም የሚለው ሳይንሳዊ መረጋገጫ ላይ ነው ለመድረስ የቻልኩት። በሌላ አነጋገር የኦሮሞን ብሔረስ-ሰብ ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ከተፈለገ በታሪክና በህብረተሰብ ውህደት ውስጥ ያደረገውን መቀላቀሎች በልዩ መሳሪያ በማውጣት የነሱ ደምና ጂን ልዩ መሆኑን ከተረዳን የተቀረውን መጠን ካወጣን በኋላ በእርግጥም የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር ይህንን ያህል ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል። ይህንን ዘዴ ከተጠቀምን ደግሞ የግዴታ የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር በጣም አነስተኛ ይሆናል ማለት ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ የአንድ አገር ህዝብ በቤተሰብ(Households) አማካይነት በተደራጀ መልክ ሲቆጠር ዝም ብሎ ለመቁጠር ያህል ሳይሆን ለኢኮኖሚና ለማህበራዊ ዕቅድ ወይም ፕላን እንዲያመችና፣ ከዚያ በመነሳት እንደየደረጃው ከቤት አንስቶ እስከ ትምህርትቤት፣ ህክምና መስጫ፣ ክሊኒኮችና ሌሎች ለአንድ ህብረተሰብ ያስፈልጋሉ የሚባሉ የንጹህ ውሃንና የኃይልን አቅርቦት ለማደራጀትና ለማምረት ነው። በዚህ መልክ በአንድ አገር ውስጥ የሚኖር ህዝብ በቤተሰብ ደረጃ(Households) ቆጠራ ሲካሄድ የተለያየ ክፍል ያላቸው ቤቶችና ልዩ ልዩ ነገሮች በመታቀድ ይሰራሉ። ከዚህ በተጨማሪ የወሊድ ቁጥር አስቸጋሪ እየሆነ በመጣበት በኢንዱስትሪ አገሮች ውስጥ የህዝብ ቆጠራ አዲስ በሚወለዱና በታዳጊው እንዲሁም እድሜው በጠና መሀከል የሚደረግ የህዝብ ቆጠራ(Demography) ይካሄዳል። በዚህ መልክ የሚወለደው የህዝብ ቁጥር እያነሰ የሚሄድ ከሆነ አዲስ የሰራተኛ ኃይል እጥረት ስለሚኖርና ቀረጥና የጡረታ አበል የሚከፍል ኃይል ስለሚያጥር አይ ህዝቡ እንዲወልድ ልዩ ድጎማ ይሰጣል ወይም ደግሞ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ይካሄዳል። በዚህ መልክ የዲሞግራፊን ችግር መቅረፍ ይቻላል። በተጨማሪም በህዝብ ቆጠራ ውስጥ በአንድ አገር ውስጥ የሚኖርን የሴቶችና የወንዶች መጠን ለማወቅ ተያይዘ ቆጠራ ይካሄዳል። ሌላው የህዝብ አቆጣጠር ዘዴ ደግሞ በገቢና በሀብት ክፍፍል ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን፣ ይህ ዐይነቱ አካሄድ የሀብትንና የገቢን አከፋፈል ዘዴ ለማወቅና የተዛባ ሁኔታ ካለ ማስተካከያ ዘዴ ለመፈለግ ነው። ከዚህም በላይ በተለያየ ሙያ የተሰማሩ ሰዎችን ለማወቅ ሲባል የሚካሄድ አቆጣጠር ሲሆን፣ ይህም የሚያገለግለው በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠነ ሰው እጥረት በሚኖርበት ጊዜ የተማረ ኃይል እጥረት እንዳይኖር ሲባል ዝግጅት ለማድረግና አስፈላጊውንም እርምጃዎች ለመውሰድ ሲባል ነው። በዚህ መልክ የሚካሄድ የህዝብ አቆጣጠር ዘዴ ለኢኮኖሚና ለማህበራዊ ዕቅድ ያመቻል። ይሁንና ግን በጀርመንም ሆነ በሌሎች የኢንዱስትሪ አገሮች የተለያዩ የውጭ አገር ስዎች ቢኖሩም በተናጠል እየወሰዱ አንተ ከዚህ በሔረ-ሰብ ወይም ከዚህ አገር የመጣህ ነው እየተባለ ለየት ያለ ቆጠራ አይካሄድም። በሂደት ውስጥም አብዛኛው ከጀርመን ጋር በመጋባቱ የተነሳ፣ ከአንድ አገር የመጣው ከሌላ አገር ጋር ከመጣችው ጋር ስለሚጋቡ የህዝብን ቁጥር በጎሳ ደረጃ እየለያዩ መቁጠር እጅግ አስቸጋሪ ነው። ይህ ዐይነቱ አካሄድም እጅግ አደገኛና ወደ ዘረኝነትም የሚያመራ ስለሆነ በጎሳ ላይ ያተኮረ ቆጠራ ሳይንሳዊ ባህርይ ሊኖረው በፍጹም አይችልም። ስለሆነም የህዝብ መቀላቅል ስላለ ጀርመኑን ከሌላው ለመለየት የሚያስቸግርበት ጊዜ ይኖራል። በተለይም ከላቲንና ከተለያዩ የአውሮፓ አገሮች መጥተው እዚህ እየሰሩ የሚኖሩትንና የተጋቡትንና ልጅ የወለዱትን ከጀርመኑ ለመለየት እጅግ ያስቸግራል።

ወደ አገራችን ስንመጣ በተለይም ዶ/ር ሃይሌ ላሪቦ በሚገባ እንደተነተኑት ኦሮሞዎች ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ሲጓዙ ከተቀረው ብሔረ-ሰብ ጋር በመጋባት ተቀላቅለዋል። በሳቸው አባባል በወለጋ ሆነ በአርሲ ኦሮሞዎች በቁጥር ብዛት ይበልጣሉ ተብሎ ቢገመትም፣ ሀቁ ግን በወለጋ ውስጥ አብዛኛው ከጎጃሙ ጋር የተጋባና የተዋለደ ሲሆን፣ በአርሲ ደግሞ ከጉራጌ ጋር በመጋባት ኦሮሞዎች ጥንታዊ በሆነ መልክ እንደማይገኙና  ከማንኛውም ብሔረሰብ ጋር ሳይቀላቀሉ በንጹህ መልክ ሊኖሩ እንደማይችሉ ነው የሚነግሩን። ስለሆነም ይላሉ ምሁሩ፣ ቋንቋ ብቻውን ስለቁጥር መብለጥ መለኪያ ሊሆን አይችልም ብለው እቅጩን ይነግሩናል።  ወደ ከፋም ስንመጣ ከኩሎኮንታዎችና ከከፋዎች ጋር በመጋባትና በመቀላቀል ተዋልደዋል። ለምሳሌ የድሮው በኢህአዴግ ተመርጠው የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በአያታቸው ከፍቾ እንደሆነ ይታወቃል። እሳቸው ግን ንጽሁ በንጹህ መልክ እሮሞ እንደሆኑና በአፄ ምኒልክ ዘመን ተገደሉ የተባሉ ኦሮሞዎችን መቃበር ሲያስቆፍሩ ነበር። እንደዚሁ የኦሮሞ ነፃ አውጭ ድርጅት(OLF) እያለ ራሱን የሚጠራው ድርጅት መሪዎች አብዛኛዎቹ በአባቶቻቸው የጎንደርና የመንዝ ቄሶች እንደሆኑ ይታወቃል። እነሱ ግን ንጹህ በንጹህ ኦሮሞዎች ነንና ተጨቁነናል በማለት ነው ስንትና ስንት የዋህ ሰዎችን ሲያሳስቱና ሲያስገድሉ የከረሙት። አሁንም በየሜዳው የሚቧርቀው የዘመኑ ተዋናይ ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ጃዋር መሀመድ በአባቱ የመናዊና በእናቱ ደግሞ ወሎ እንደሆነ ይነገራል። ሌላው የሚናፈሰው ደግሞ ጃዋር በአባቱ ኦሮሞ ሲሆን በእናቱ መንዜ ነው እየተባለ ነው። ይህ አንደኛው ሲሆን፣ የኦሮሞ መጨቆንን የሚያነሱት ኤሊት ነን ባዮች ከደሃው የህብረተሰብ ክፍል የወጡ ሳይሆን በሶሻል ስታተሳቸው ሻል ካለ ቤተሰብ ከመጡና የመማር ዕድልም ለማግኘት ከቻሉት እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ቀደም ብለው ከውጭው ዓለም አገር ግኑኝነት ስለሚፈጥሩና የጥላቻ ሰለባ ስለሚሆኑ ፖለቲካ የሚባለውን ትልቅ ፅንሰ-ሃሳብ የራሳቸው ጥቅም ማስጠበቂያ አድርገው በመውሰድ ሰፊውን ህዝብ ወደማሳሳት ያመራሉ።

ያም ሆነ ይህ የኦሮሞ ኤሊት ለማሳመን እንደሚሞክረው የኦሮሞ ብሔረ-ሰብ ቁጥር በምንም ዐይነት 31ና 50 ሚሊዮን ሊሆን አይችልም። አንድንም ብሔረ-ሰብ በጎሳ እየለያዩ ቁጥሮ ይህን ያክላል ማለት ለሳይንሳዊ ትንተናና ለኢኮኖሚ ፕላኒንግ በፍጹም የሚያመች አይደለም። በታሪክ አጋጣሚ የኦሮሞ ብሔረሰብ በመስፋፋቱና በሄደበት ቦታ ሁሉ ከሌላው ጋር በመጋባቱና በመዋለዱ፣ በዚህም የተነሳ የቋንቋ ተፅዕኖ ስላደረገ በቁጥር ይበልጣል የሚያሰኘው አንዳችም ሳይንሳዊ መረጋገጫ ሊኖር አይችልም። ለአንድ ምሁር ወይም የፖለቲካ ታጋይ ነኝ ለሚል ዋናው መለኪያ የአንድ ብሔረ-ሰብ በቁጥር በልጦ መገኘቱ ሳይሆን፣ የምርምር መነሻውና የአተናተን ዘዴው፣ በዚያ ህብረተሰብ ውስጥ የሚገኘው የፖለቲካና የመንግስት አወቃቀር፣ በዚህም የተነሳ የኢኮኖሚና የማህበረሰብ አደረጃጀት፣ ስለሆነም ብሔራዊ ሀብት የመፍጠርና ያለመፍጠር ጉዳይ ናቸው መነሻና ሳይንሳዊ መንገድ መሆን ያለባቸው።  ከዚህም በመነሳት ስልጣንን የጨበጠ የገዢ መደብ ከውጭው ዓለም ጋር ያለው ፓለቲካዊ፣ የሚሊታሪና የኢኮኖሚ ግኑኘነትና፣ ይህ ዐይነቱ ግኑኝነት የዕድገት አጋዥ ነው ወይስ ሀብትን የሚያዘርፍና ወደ ጦርነት እንድናመራ አድርጎ የተደላደለ ህብረተሰብ እንዳንገነባ የሚያግደን ነው ? የሚለው የምርምርና የአተናተን ዘዴ ትክክለኛው ሳይንሳዊ መንገድ ነው።  በዚህ አማካይነት ይህንን መሰረት በማድረግ ነው፣ ስለ ፖለቲካ፣ ስለማህበራዊና ስለኢኮኖሚ እኩለነት ወይም ጀስቲስ(Jusitce)  መታገልና የተደላደለና ጤናማ ህብረተሰብ እንዲፈጠር የሚቻለው። አንድን ህብረተሰብ በብሔረ-ሰብ ደረጃ እየከፋፈሉ መቁጠር የሚያመቸው ዕድገትና ስላምን ለሚቀናቀኑ ኃይሎች ብቻ ነው። ስለሆነም ማትኮር ያለብን ስለጠቅላላው ህዝባችን አኗኗርና፣ አሁን ካለበት አስከፊ ሁኔታ እንዴት አድርገንና በምን ዐይነት ስትራቴጂያዊ ዘዴ ልናወጣው እንችላለን በሚለው መርህ ላይ ብቻ ነው ። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ትግል ድህነትንና ኋላ-ቀርነትን ያራዝማል።  በጦርነት ዓለም ውስጥ እንድንኖር ያስገድደናል።

ፈቃዱ በቀለ

fekadubekele@gmx.de

መካሪ ልቦናስ አለ ! ተመካሪ ሰዉ ግን ከወዴት አለ? [ሸንቁጥ አየለ]

04et214-monks-staying-in-the-caves-near-the-churches-of-lalibela-10051ሸዋ ዉስጥ ደብር ዜና ማርቆስ የሚባል ገዳም አለ::በ1986 ዓም የ12ኛ ክፍል ፈተኛ ስጨርስ ወደ አንድ መለኩሴ አጎቴ ካንድ ጓደኛዬ ጋር ወደ እዚህ ገዳም ሄድን::ይሄን ጓደኛዬን ለማስመከር መሆኑ ነዉ::በወቅቱ ይሄ ጓደኛዬ ነገር ክርስቶስ ላይ ጥርጣሬ ቢያበዛ እስኪ ከኝህ አጎቴ ምክር ስማ ብዬ ነበር ይዤዉ የሄድኩት::እናም መለኩሴዉ አጎቴ ልንጠይቃቸዉ እንደመጣን ሲያዉቁ ደስ አላቸዉ:: ፈገግ ብለዉም ተቀበሉን::

ሆኖም በቤታቸዉ ያለዉንም የሚበላ ነገር አቀራርበዉልን በትንሿ ቤታቸዉ ትተዉን “በሉ ተጨዋቱ:: እኔ ወደ ጸሎት መሄዴ ነዉ” ብለዉን ሄዱ::ቢጠበቁ አልመጡም::እኛም ስለደከመን ቁጭ ባልንበት መደብ ላይ እንቅፍል ይዞን ሄዶ ኗሯል::እሳቸዉ ግን በጣም ከመሸ መጡ::ጥቂት አርፈዉ እንደገና ተነስተዉ ሌሊትም ለጸሎት ብለዉ ሄዱ::ጠዋት ቅዳሴ ቆይተዉ መጡ::አሁንም ያላቸዉን ነገር አዘገጃጅተዉ አቀራርበዉልን የተሰዓት ጸሎት ደርሷል ብለዉ ሊሄዱ ተነሱ::

ነገር ክርስቶስ ላይ ጥርጣሬ የገባዉ ጓደኛዬም የመለኩሴዉ ለጸሎት እያሉ ጥፍት ማለት ገርሞታል እና አንድ ጥያቄ ጠዬቃቸዉ:: “ለመሆኑ ጸሎት የሚበቃዎት መቼ ነዉ? የሚጸልዩትስ ምን እያሉ ነዉ?” ሲል ጠዬቀ::እርሳቸዉም ፈገግ እያሉ ” የምድር ጸሎቱ ስሞት ነዉ የሚበቃኝ::ሆኖም በሰማይም ክርስቶስን ማወደሱና እና ማመስገኑ ይቀጥላል::የምጸልዬዉም “አምላኬ : ጌታዬ : ፈጣሪዬ: ንጉሴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ምስጋና ይገባሃል” እያልኩ ነዉ” ሲሉ መለሱለት::

ልቡ በክርስቶስ ነገር ላይ የሸፈተዉ ወጣትም “ክርስቶስ እኮ ፈጣሪ አይደለም::ለምንድን ነዉ ፈጣሪ የሚሉት?” ሲል ሳያፍር መለኩሴዉ አጎቴን ጠዬቃቸዉ::እኔም አመዴ ቡን አለ::በፍርሃትም ተሸማቀቅሁ:;እንዴት አንድን መለኩሴ እንዲህ በብልግና ይጠይቃል ብዬ መሆኑ ነዉ::እርሳቸዉም ፈገግ አሉ::”ክርስቶስን ፈጣሪ አይደለም ብለህ ታስባለህ? ማለት ነዉ?” ሲሉ::

“አዎን!” አለ ምንም ቅር ሳይለዉ::
“እዴት?” በድጋሚ ጠዬቁ::
“ምክንያቱም መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚያብራራዉ…” ብሎ የሚያዉቃትን ጥቂት ጥቅስ ጠቃቀሰ::ድንገትም የዮሀንስ ወንጌል ምዕራፍ አንድን መናገር ጀመረ::ድምጹን ከፍ አድርጎም እየተናገር የነበረዉ መለኩሴዉን ክርስቶስ ኢየሱስ አምላክ አይደለም ብሎ ለማሳመን ነበር::ድንገት ግን ቀጥ ብሎ ቆመና መናገር አቆመ::”እንዴ ቆይ ? ” ብሎ መንጎራደድ ጀመረ::”እንዴ …ቆይ ይሄ ምዕራፍ እኮ ስለክርስቶስ አምላክነት እና ፈጣሪነት የሚያስረዳ ነዉ::እንዴ?…” እንደገና እራሱን አርሞ ምዕራፉን ደግሞ በቃሉ ለበለበዉ:: እራሱ እየተናገረ እራሱ ደግሞ እያብራራ “እንዴ ? እንዴ? ! …” ማለቱን ቀጠለ::

መለኩሴዉ አጎቴ በዚህ ሁሉ የጓደኛዬ ንግግር መሃከል ጣልቃ አልገቡም::እራሱ ክርስቶስ ፈጣሪ አይደለም ብሎ ጥቅስ ማብራራት ጀምሮ እራሱ ደግሞ መዞ ባመጣዉ ጥቅስ ክርስቶስ ፈጣሪ ነዉ ብሎ እራሱን ማስረዳት ጀመረ:: መለኩሴዉ አጎቴም በመጨረሻ ጓደኛዬን እያስተዋሉ እንዲህ አሉ:: “አንተ ጎበዝ ልጅ ነህ::መካሪ ልብ ያለህ::ተመካሪ ልብም ያለህ:: አሳስተዉ ያስተማሩህን ነገር በየዋህነት ሰምተህ በልብህ ብታስቀምጠዉም ልቦናህ ግን እዉነትን የማድመጥ ጸጋን የተሰጠህ ሰዉ ነህና እዉነት እና ሀሰትን አብላልተህ በራስህ መለዬት ቻልክ::”

መለኩሴዉ አጎቴ ይሄችን ብቻ ከተናገሩ ብኋላ “በሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ” ብለዉን ጥለዉን ወደ ጸሎታቸዉ ሄዱ:: የልጁ ክህደትም ሆነ እራሱን አርሞ ወደ ትክክለኛ ሀሳብ መምጣቱ ድንቅም አላላቸዉ::ሲጀምር እኝህ መለኩሴ ምንም ነገር የሚደንቃቸዉ ነገር ያለ አልመሰለኝም::ከመመልኮሳቸዉ በፊት አላቃቸዉም:: እንዲህ ምንም ነገር የማይደንቀዉ ያደረጋቸዉ ምልኩስናዉ ይሁን ወይም አይሁን ግን አላቅም::

በሶስተኛዉ ቀን ከትንሿ ቤታቸዉ ተሰናብተን እዬሄድን ሳለ ድንገት አንድ ሀሳብ መጣልኝ::ለዘለአለም ስንቅ የሚሆን ምክር ከኝህ ሰዉ ማግኘት:: እናም ዞር ብዬ እያስተዋልኳቸዉ “አባ ! በህይወታችን ሙሉ የምንመራበት ምክር ቢለግሱንስ?” ስል ጠዬቅኋቸዉ::እንደለመዱት ፈገግ አሉ::ከስዉ ልጅ ባህሪ ዉስጥ ፈግግ ማለት ጥልቅ የሰዉነት ህሳቤ ሚስጥር ይመስለኛል::ገና ህጻን ሆኜ::እናም እኝህ አባት ዉስጥ ይሄን ጥልቅ የሰዉነት ሚስጥረ ሀሳብ ያነበብኩት መስለኝ::እናም የሚናገሩትን ለማድመጥ በጥንቃቄ አቆበቆብን:: ሌላዉ ቀርቶ በነገር ክርስቶስ ላይ ልቡ ሲዋዥቅ የነበረዉ ጓደኛዬም በሶስት ቀን ዉስጥ የሆነ የማይታመን የአስተሳሰብ ለዉጥ አምጥቶ አባ የሚናገሩትን በአክብሮት እያደመጠ ነዉ::

አባ ምክር ስጠይቃቸዉ ፈገግ ብለዉ ሲያበቁ እንዳልሰማ ሆነዉ ግን “በሉ ሰላም ግቡ::ቆላማዉን ሀገር እስክትወጡ ቀስ እያላችሁ::” ብለዉን እንድንሄድ ገፋፉን:: እኔም “ምክሩን እኮ አልነገሩንም !” ስል በድጋሜ ጠዬቅሁ::አባ እንደገና ፈገግ አሉ:: እናም “እዉነተኛዉ ምክር እያንዳንዱ ሰዉ ልብ ዉስጥ አለ::ሰዉ የልቡን እዉነተኛ ምክር ለመስማት ከፈቀደ ከልቡ ዉጭ መካሪ አያስፈልገዉም::ለዚህ አባባሌም ምስክር የሚሆነዉ ይሄ ወጣት ነዉ” ብለዉ ወደ ጓደኛዬ በአገጫቸዉ አመለከቱ:: “ተመካሪ ሰዉ ካለ መካሪ ልቦናንስ እግዚአብሄር በየሰዉ ዉስጥ አኑሯል:: ሰዉ ከልቦናዉ ዉጭ መካሪ አያስፈልገዉም” በማለት አባ አብራሩ:: አጭር ግን ቆፍጠን ያለ ማብራሪያ ነበር::

እናም ሰሞኑን የመለኩሴዉ አጎቴ ጥልቅ ምክር ታስቦኝ እንደ እርሳቸዉ ብቻዬን ፈገግ አልኩ:: በኢትዮጵያዉያን ፖለቲከኞች መሃከል እየተከናወነ ያለዉን የእርስ በርስ መጠፋፋት ጉዳይ ሊያስቀር የሚችል አንድ ግሩም ምክር አዘል ጽሁፍ ማዘጋጀት አለብኝ ብዬ ሰሞኑን አስቤ ተነስቼ ነበር::የኢትዮጵያ ነገር ለልቤ ጭንቅ : ለመንፈሴ ህመም: ለህሳቤዬ እሩቅ ሲሆን በኢትዮጵያ ፖለቲከኞች መሃከል እኮ አብሮነት ቢፈጠር “አንዲት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን” በፍጥነት እዉን ማድረግ ይቻል ነበር ብዬ እንደ ሞኝ እፈላሰፋለሁ::

እንደ ሞኝ ያልኩት ያለምክንያት አይደለም:: በጥልቅ ምክንያት ነዉ::እንኳን የማይተዋወቁ : በነገድ የሚለያዩ: በፖለቲካ ህሳቤ እና ርዕዮት አለም የተነጣጠሉ ሀይሎች አንድ ሊሆኑ ይቅር እና በእዉቀት ኮትኩተን እና አጀግነን ለጋራ ትግል ይሆናሉ ብለን የምናዘጋጃቸዉ ሰዎች በጣም በፍጥነት ሲገለባበጡ እና ሲከረባበቱ ብሎም ወደ ሌላ ጎራ ሲሰለፉ በተደጋጋሚ ላስተዋለ ሰዉ የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ለምን አንድ አልሆኑም ብሎ ማሰቡ በራሱ ሞኝነት ነዉ::አንድ ባይሆኑ ግን ለምን ተከባብረዉ አይታገሉም? ብሎ መጠዬቅ ግን ጤናማ ጥያቄ ይመስላል:: ግን ይሄም የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቀርቦ በደንብ ለሚያጠናዉ ሰዉ የሞኝ ጥያቄ ነዉ::

እናም ማዘጋጀት የጀመርኩትን የምክር ጽሁፍ አጥፍቼ ስለ መለኩሴዉ አጎቴ ምክር ማንሰላሰል ጀመርኩ:: “ተመካሪ ሰዉ ካለ መካሪ ልቦናንስ እግዚአብሄር በየሰዉ ዉስጥ አኑሯል:: ሰዉ ከልቦናዉ ዉጭ መካሪ አያስፈልገዉም” የሚገርም እና የተራቀቀ አባባል ነዉ::ኢትዮጵያዉያን ይሄን ያህል ጥልቅ ህዝብ ሆነዉ ሳለ ለምን ጥልቅ መሰረት ላይ የቆመ ሀገር መመስረት አቃታቸዉ?

“መካሪ ልቦናስ አለ ! ተመካሪ ፖለቲከኛ ግን ከወዴት አለ?” የሚል ጥያቄ ሲቀርብም ይሰማኛል::እናም በክፉ መንፈስ የተጠለፈዉን: ዘረኛ እና አንባገነን ስርዓት ለማስወገድ በተጋድሎ ላይ ያለዉ ህዝባችን የተባበረ እርዳታ የሚፈልግበት ወቅት አሁን ነበር::ፖለቲከኞች ግን በመርዛማ የመጠላላት እና የመጠላለፍ ሀሳብ ዉስጥ ወድቀዋል:: ይሄ ዛሬ አልተጀመረም:: ቅንጅት የተበታተነዉ የተንኮል ፖለቲካ ማጥ ዉስጥ ተቀርቅሮ ጭምር ነዉ:: ከቅንጅት በፊት የነበሩትን አቢዮታዊ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ወደ መርዛማ አዘቅት ዉስጥ የጣላቸዉም ይሄዉ በሸፍጥ እና በአሉታዊ እንቅስቃሴ የተሞላዉ የፖለቲካ ህሳቤ ነዉ:: የፖለቲከኞቻችን ልቦና እዉነትን ሳይሆን ሸፍጥን ለማፍልቅ ፈጣን ነዉ::

እናም ምክር ፖለቲካን አቅጣጫ አያሲዘዉም::በተለይም እንደ ኢትዮጵያ አይነት ፖለቲካዊ ምህዳር ዉስጥ የሚተራመስ የፖለቲከኛ ህዝነ ልቦናም እራሱን ለመምከር የሚያስችለዉን እዉነተኛ ምክር ለማፍለቅ ልቦናዉን ጸጥ የሚያደርግበት ሁኔታ ዉስጥ አይደለም::በኢትዮጵያ የፖለቲካ ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት ፖለቲከኛነት በልብ ዉስጥ ትርምስ እና በዉጭም ትርምስ የሰፈነበት ከባቢ ህይወት ዉስጥ መመላለስ ይመስላላል::

እናም “እዉነተኛዉን እና ትክክለኛዉን ሁኔታ ለመለዬት እና ለማወቅ የሚያስችል መካሪ ልቦና በያንዳንዱ ዉስጥ አለ:: ተመካሪ ፖለቲከኛ ግን ከወዴት አለ?” ብሎ ዝም ማለት የቀለለዉ መፍተሄ ባይሆንም አንዱ አማራጭ ግን ይመስላል:: “መካሪ ልቦናስ አለ ! ተመካሪ ሰዉ ግን ከወዴት አለ?”

ለኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥብቅና! [አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ]

ረቡዕ ሐምሌ ፳ ፯ ቀን ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት ( 08/03/2016 )

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግሌ አላውቀውም፤ ነገር ግን እስከሚበቃኝ ድረስ አውቀዋለሁ። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እኔን አያውቀኝም፤ ነገር ግን እኔና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ጠበቆቹ እንዳለን ያውቃል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደር ውስጥ አንገረብ እስር ቤት ባሁኗ ሰዓት – ምሽት፣ ረቡዕ ሐምሌ ፳ ፯ ቀን ፳ ፻ ፰ ዓመተ ምህረት – ለጊዜው አለ። እዚያ እንዲቆይ ያደረገው ወገኑ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው፤ በእስር ቤት ያለ ግለሰብ፤ በትክክል ይሁን በድፍረት በመታሰሩ ብቻ፤ ጠበቃ ያስፈልገዋል። እናም ጠበቃው ነኝ።
የጠበቃ ሀ፣ ሁ ው፤ ሠርተሃል ከተባለበት ወንጀል በፊት፤ ፍርድ ቤቱን መመዘን ነው። እናም ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የሚቀርብበትን ፍርድ ቤት እንመርምር። እንደማንኛውም ፍርድ ቤት ቆጥረን ይሄን ፍርድ ቤት ብንመለከተው፤ ሕግ አለ፣ ፖሊስ አለ፣ ዳኛ አለ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ፤ ፍርድ ቤቱን ያቋቋመው መንግሥት አለ። ፍርድ ቤቱን ስንመረምር፤ ያቋቋመውን መንግሥትም ማጤን አለብን። ከላይ ያነጠብኳቸውን እያንዳንዳቸውን ነጣጥሎ መመልከቱ ችግር ይፈጥራልና፤ እስኪ ጠቅለል አድርጌ በአንድነት ላቅርበው። በርግጥ አንድነት ባሁኑ ዘመን አስቸጋሪ ከመሆኑ በላይ፤ ራሱ አንድነት የሚለው ቃል ወንጀል ሆኗል። ነገር ግን፤ የማያመልጡትን መረብ፤ በተስፋ ቃኝተው፤ መውጪያ በመፈለግ መጣር ያለ ነውና፤ በዚያው ላምራ።

ፍርድ ቤቱን ያቋቋመው መንግሥት፤ የኅብረተሰብን ብሶት አንገብኩ ብሎ፤ ትጥቅ አንስቶ፤ በጉልበቱ ሥልጣን ላይ የወጣ አካል ነው። እናም ከተፈጥሮው ምንነት የተነሳ፤ ማንንም የኅብረተሰብ ብሶት አንስቶ የሚታገልን ግልሰብ ሆነ ቡድን፤ ፍርድ ቤት ሊያቀርብ፤ ሕጋዊ ፈቃድም ሆነ የሞራል ብቃት የለውም። የዚህ አካል መሪዎች፤ የሥልጣን ንጥቂያ ግብግባቸው ባይሳካላቸው ኖሮ፤ ራሳቸው ፀረ-ሕዝብ፣ ፀረ-ሀገር፣ ፀረ-መንግሥት ተብለው በዚሁ ፍርድ ቤት ይቀርቡ ነበርና!

በሌላ በኩል ደግሞ፤ አሁን በሀገራችን ሕግ የለም። አሁን በሀገራችን ደንብ የለም። አሁን በሀገራችን የአስተዳደር መመሪያ የለም። ያለው የጉልበት ግዛት ነው። ያለው፤ ባለጉልበቱ የሚፈልገው፣ በፈለገው መንገድ፣ በፈለገው ጊዜና በፈለገው ቦታ፤ ባሻው መንገድ መፈጸሙ ብቻ ነው። ቋሚ የሆነ ሕግ የለም። እንዲያውም እንደ ዕውነቱ ከሆነ፤ ሕግ ቦታ የለውም። ቦታ ያለው፤ ገዥው የሚፈልገው ጉዳይ ብቻ ነው። ከዚህ ተነስተን፤ ዳኛው፣ ፖሊሱ፣ ሕጉ፣ ጠበቃዎቹ፣ ሁሉ የገዥውን ፍላጎት አስፈጻሚ አካል ለመሆናቸው ጥርጣሬ ሊኖረን አይገባም። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በመከላከል ሊቀርብ የሚፈልግ ጠበቃ ሁሉ፤ ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የበለጠ ወንጀለኛ ሆኖ እስር ቤት ይገባል። ለዚህ ነው፤ አንድ ብቻዬን ሳልሆን፤ በሚሊዮን የምንቆጠር ኢትዮጵያዊያን ለሱ ጥብቅና የቆምነው፤ አንዳችን ስንታሰር ሌላችን በየተራ ለመታሰር ተዘጋጅተን።

ቀረብ ብለን ስንመለከት፤ ፍርድ ቤቱ በተግባር የገዥው ክፍል መሣሪያ ከመሆኑ አልፎ፤ ከላይ እስከታች የተሰገሰጉት፤ የዚሁ ገዥ ፓርቲ አባላት ናቸው። የገዥው ፓርቲ አባላት ሙሉ በሙሉ ትግሬዎችና ትግሬዎች ብቻ ናቸው። በወሳኝነት ያሉት የዚሁ ፍርድ ቤት አባላት ደግሞ፤ ሁሉም በአባልነታቸው ትግሬዎች ናቸው። እና አንድ አማራ ወልቃይቴን፤ ለዚያውም በጥቅማቸው በወልቃይት ላይ ለመጣ ወኪል፤ በደሉን ሆነ ወንጀሉን ያዳምጣሉ ማለት፤ ከሰማይ መና ይወርዳል ብሎ ነጠላ መዘርጋት ይሆናል። ወልቃይት እኮ የታሪክ ወይንም የሕግ ጉዳይ ሳይሆን፤ የትግሬዎች ክልል የጥቅም ጉዳይ ነው! እናም የወልቃይትን ጉዳይ የትግሬዎች መንግሥትና ክልል መዋቅርና ዳኞች ይመልከቱት ማለት፤ ወይንም በዚያ ቀርቦ ትክክለኛ ፍርድ ለማግኘት መሞከር፤ ትርጉም የማይሠጥ ሂደት ነው። በጎንደሩ ሰላማዊ ሰልፍ አንድ መፈክር ከሁሉ ደምቆ ታይቶኛል፤ “ትግሬ እንጂ ትግራይ ተከዜን ተሻግሮ አያውቅም!” የሚለው።

በመጀመሪያ ነገር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የመጀመሪያው ወይንም የመጨረሻው እስረኛ አይደለም። ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ታስረው፤ በዚያው ዕድሜያቸውን ጨርሰዋል። እስክንድር ነጋ፣ አንዱዓለም አራጌ፣ የእስልምና ተከታይ አቤቱታ አቅራቢዎች፣ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች፤ አሁንም በስር ቤቶች እየማቀቁ ይገኛሉ። ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተቋማትና መሪዎቻቸው በሙሉ ተባረዋል፣ ተደምስሰዋል፣ ተገድለዋል፤ – የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበር፣ ወ. ዘ. ተ. ።

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለምንድን ነው ለእስር የተዳረገው? ተመልከቱ፤ በሌሊት ሊያፍኑት የመጡትን የትግራይ መሪ የአባይ ወልዱ ታጣቂዎች፤ “በሕግ የምትፈልጉኝ ከሆነ፤ ሲነጋ፤ መጥታችሁ ልትወስዱኝ ትችላላችሁ። እኔ በሕግ የሰፈረልኝን መብት ጠንቅቄ የማውቅ ግለሰብ ነኝ።” ቢላቸው፤ በግድ ገብተው እጁን ሊይዙት ሞከሩ፡ ራሱን እንደሚከላከል ሲገልጽላቸው፤ ተኩሰው ዘው ብለው ገብተው ሊያፈኑት ጣሩ።  ራሱን ለመከላከል እሱም ሞከረ። በዚህ የተኩስ ልውውጥ አመለጠ። ሕዝቡ ከጎኑ ቆመ። ለሕዝቡና ለሕዝቡ ድምጽ ደንታ የማይሠጠው የትግራይ ክልል ገዥና የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ዋና መሪ ብሎም የኢትዮጵያ መሪ፤ ጉልበት እንጂ ራሱ ያወጣውን ሕግም ስለማያከብር፤ ሕዝቡን ጥሶ ሰዎችን ገደለ። ቀደም ብሎ አፍኖ የያዛቸውን የወልቃይት ሕዝብ አቤቱታ ወኪሊችን ሰወረ። አሁንም የውሸት ውርጅብኝ በማከታተል፤ ሕዝቡን ወንጀለኛ ራሱ ግን ሕግን አክባሪ አድርጎ አስቀመጠ። መቼም ማን ሕግን አክባሪ፤ ማን ሕግን ጣሽ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውቀዋል።

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ወልቃይትን ለዘለዓለም ታድጓታል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደርን በሕይወቱ ጠመንጃውን አንስቶ ታድጓታል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አማራውን በማንነቱ እንዲኮራ ታድጎታል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ኢትዮጵያን ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነፃ እንድትሆን ክንፉን ዘርግቶ ታድጓታል። ነገ ዛሬ የተጫረው እሳት ምን ሊያስከትል እንደሚችልና ምን መሆን እንዳለበት በጃችን ነው። አሁን በዚች ሰዓት ግዴታችን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን መታደግ ነው። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በዚህ ሕገ-ወጥ በሆነ መንግሥት ፍርድ ቤት ትክክለኛ ፍርድ አያገኝም። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ነፃ የሚሆነው በቆመለት ሕዝብ ብቻ ነው። ምንም ያጠፋው ነገር እንደሌለ ሁላችን እናውቃለን። ያደረገው ቢኖር፤ አማራ ነኝ እንጂ ትግሬ አይደለሁም። በጎንደሬነቴ የመጣ ሕይወቴን እሠጣለሁ። ነፃነቴን እፈልጋለሁ፤ ማለቱ ብቻ ነው። ነፃነቱን ለሚሻ አብረን መቆም አለብን። በአንድነት እንሰለፍ።

ከታላቅ አክብሮታ ጋር

አክባሪያችሁ አንዱዓለም ተፈራ

“የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱን አቁሙ!” – ፕ/ር መረራ ጉዲና (ዛሬ በአምስተርዳም ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ የተናገሩት)

 

dr-merera

ለዘ-ሐበሻ ዘገባ – ከክንፉ አሰፋ

“በውይይት የማይፈታ ችግር የለም። ስትወያዩ ግን የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱ ላይ አታተኩሩ። ትኩረታችሁን አሁን የተጋፈጥናቸው ችግሮች ላይ አድርጉ።” ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አስታወቁ።

ፕሮፌሰሩ ይህንን የገለጹት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በኔዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያ ጋር በትላንትናው እለት 20 November 2016 በአምስተርዳም ባደረጉት ውይይት ላይ ነው። በውይይቱ የኦሮሞ አክቲቪስቶችም ተገኝተው ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

ስለ ሃገሪቱ ፈታኝ ሁኔታ እና ስለወደፊቱ እጣ ፈንታ በስፋት ያብራሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ – ፕ/ር መረራ ጉዲና ከተሰብሳቢው ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።

“አዋጁ እና ኮማንድ ፖስቱ ሕዝባዊ አመጹን ያበርደዋል ወይ?” ተብለው ሲጠየቁ፣ ሃገሪቱ አሁን በመስቀለኛ መንገድ ላይ መሆንዋን ገልጸው አሁን ያለው ሁኔታ ላይ እንዲህ ይሆናል ብሎ መናገር እንደማይቻል ገልጸው፣ነገሮች በሁሉም አቅጣጫ ሊሄዱ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ችግሮች እስካልተፈቱና የህዝብ ጥያቄዎች በአግባቡ እስከልተመለሱ ድረስ ሁኔታው ወደ እርስ በርስ እልቂት ሊወስደንም ይችላል። ይላሉ።

በይፋ አልተነገረም እንጂ ኮማንድ ፖስቱ ከአዋጁ በፊትም የነበረ የኢህአዴግ አሰራር እንደሆነ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ምእራባውያን ስላላቸው ሚና ተጠይቀው፣ እኛ የቤት ስራችንን ካልሰራን ምእራቡ አለም ምንም ሊረዳን አይችልም። እኛ ካልሰራን እንኳን ምእራቡ አለም እግዚአብሄርም አይረዳንም። ብለዋል።

በዚህ ወቅታዊ የሀገር ጉዳይ ላይ የተዘጋጀ የውይይት ገለጻ ሲሰጡ በዲፕሎማሲው እና በአለም አቀፍ ህብረተሰብ በአንድ በኩል፣ በሃገር ውስጥ የተጀመሩት በርካታ የ”እርቅ” እንቅስቃሴዎችን በስፋት ቃኝተዋል።

merera-gudina

በአለም አቀፉ ህብረተሰብ እና በምእራባውያን ሃገሮች በኩል አሁን ለተቃዋሚዎች በር ተከፍቷል ይላሉ ፕ/ር መረራ ጉዲና። በጋራ ሆነን በአንድ ቋንቋ የመናገሩ ህብረታችን ግን አሁንም ፈተና ላይ ነው።

በቅርቡ በአውሮፓ ህብረት ጥሪ ተደርጎላቸው ሃገሪቱ ስላለችበት መስቀለኛ መንገድ በስፋት ተናግረዋል። አሜሪካ በነበሩበት ግዜም ከሠማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ጋር “አትላንቲክ ካውንስል” ከተባለው የአሜሪካ ቲንክ ታንክ ቡድን ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ውይይት ሄርማን ኮኽን እና የቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ሺል የተገኙ ሲሆን የተቃዋሚ ፓርቲዎች በህብረት ያለመንቀሳቀስ ትኩረት ስቦ እንደነበር ይናገራሉ።

ገዥውን ፓርቲ ከተቃዋሚዎች ጋር ለማግባባት ሰባት የሚያህሉ የእርቅ እና ሰላም ቡድኖች በኢትዮጵያ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል። አብዛኞቹ የ”እርቅ” ቡድኖች ባህላዊውን የ”አንተም ተው ፣ አንተም ተው” ሚና እንኳን የማይጫወቱ አንድን ወገን ብቻ ለመጫን የተቋቋሙ መሆናቸውንም ይተቻሉ።

ስለ ቀድሞው ተማሪያቸው እና ስለ አሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስለ ወርቅነህ ገበየሁ ተጠይቀው፤ በምርጫ ውድድር ይጠቀምበት የነበረው ስም ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ ሲሆን በትምህርት በት ያለው ፋይል ላይ ደግሞ ወርቅነህ ገበየሁ ወልደ ኪዳን እንደሆነ ገልጸዋል። ይህንን ጉዳይ በሁለተኛው መጽሃፋቸውም ላይ መጥቀሳቸውን ተናግረዋል።

በመጨረሻም በሃገር በት በኦሮሞ እና በአማራው ህብረተሰብ እየተፈጠረ ያለው ትብብር እነ ጌታቸው ረዳን ሳይቀር በአደባባይ ወጥተው እንዲናገሩ ያደረገ ትልቅ የታሪክ አሻራ መሆኑን ገልጸው፣ በውጭ ያለውም ወገን የቀድሞ ሂሳብን ማወራረድ አቁሞ፣ በወደፊቱ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ እንዲወያይ ምክር ሰጥተዋል።

በቪዲዮ የተቀረጸው ሙሉ ውይይት በቅርቡ ይለቀቃል።