የመጨረሻው ምሣ – በዕወቀቱ ስዩም | ሊያደምጡት የሚገባ

 

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር ቤት የሚደርስበት ስቃይ ለሆስፒታል እንዳበቃው ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: ለቀናት በቤተሰቦቹ እንዳይጎበኝ ተሰውሮ የቆየው ተመስገን ከታሰረበት እስር ቤት ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተከታተለ መሆኑን ባሰብን ጊዜ በዕውቀቱ ስዩም ስለዚህ ትንታግ ጋዜጠኛ “የመጨረሻው ምሣ” ሲል ከአሜን ባሻገር መጽሐፉ ላይ የጻፈውን በራሱ አንደበት ሲያነበው እንድናዳምጥ በድጋሚ ወደዚህ አመጣነው:: ለተመስገን ደሳለኝ እግዚአብሄር ምህረቱን እንዲያወርድለት ስቃዩን በቃህ እንዲለው እንጸልያለን::

በቤኒሻንጉል ጭላንቆና ባኩጂ ቀበሌዎች የአማሮች አበሳ ቀጥሏል | እየታሰሩ እየተገረፉ ነው

 

(ዘ-ሐበሻ) ሕዝብን ከሕዝብ ጋር በማናከስ ተወዳዳሪነት የሌለው የሕወሓት መንግስት በቤንሻንጉል ሕዝብ በማስመሰል በአማራው ላይ የሚፈጽመውን ጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል:: በተለይ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በቡለን ወረዳ ስር ባሉት ጭላንቆ እና ባኩጂ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩ አማሮች በስርዓቱ ጠመንጃ ታሸጋግራላችሁ; በአማራው ክልል እየተደረጉ ያሉትን ጦርነቶች ትደግፋላችሁ በሚል ግርፋት እና እስር እየተፈጸመባቸው መሆኑ ተዘግቧል::

በጭላንቆና ባኩጂ ቀበሌዎች ውስጥ የሚኖሩት እነዚሁ አማሮች አርሶ ከመብላትና በሰላም ከመኖር ውጭ ምንም የማያውቁ ሆኖ ሳለ ሆን ተብሎ ከመሬታቸው ለማፈናቀልና ተረጋግተው እንዳይኖሩ ለማድረግ ሆን ተብሎ የሕወሃት መንግስት ባሰማራቸው የቤንሻንጉል ተወላጆች እንዲገረፉ ንብረታቸውም እንዲዘረፍ በማድረግ ላይ ነው::

በትናንትናው ዕለትና በዛሬው ዕለት ብቻ ቁጥራቸው ከ25 የሚበልጥ አማራ ናችሁ የተባሉ ወጣቶች ታስረው ወዴት እንደተወሰዱ አይታወቅም የሚሉት የዜና ምንጫችን ንብረት ዘረፋውም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል::

በዚሁ በቤኒሻንጉል ክልል የሚኖሩ አማሮች ላይ ከዚህ ቀደም እንደሚደረገው ሁሉ ወደ መጣችሁበት ሂዱ በሚል ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ዘ-ሐበሻ ሰሞኑን በተደጋጋሚ መዘገቧ አይዘነጋም::

በሌላ ዜና የአማራው ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በቻግኒ ከቤንሻንጉል ባለስልጣናት ጋር ስብሰባ ላይ እንደዋለና በስብሰባው ውስጥም የሕወሓት ሰዎች ሙሉ በሙሉ ተሳትፎ እንደነበራቸው የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል:: የዚህ ስብሰባ ዓላማ ሰሞኑን በጃዊ ሕዝብ ያነሳውን ሕዝባዊ አመጽ ተከትሎ በክልሉ ይኖራል ተብሎ በተሰጋው የመሳሪያ ዝውውር ዙሪያ እንደሆነ ምንጮች አስታውቀዋል:: በቻግኒ ኢትዮጵያ ሆቴል በተደረገው በዚሁ ስብሰባ ላይ የቤንሻንጉል አስተዳደሮች በክልላቸው የመሳሪያ ዝውውር እንዳይኖር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከሕወሃት ሰዎች ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የሚገልጹት ምንጮቹ በተለይም በክልሉ የሚኖሩ አማሮች ሕዝባዊ ዓመጹን እንዳይቀላቀሉት ጥብቅ ክትትል እንዲደረግባቸው ተመክሮባቸዋል::

እንዴት ከረምሽ! አዲስ አበባ? – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

መንፈቅ ላለፈ ጊዜ ያህል ተለይቻት ነበርና ነው ናፍቆት በተሞላ ሰላምታ ሞቅ አድረጌ ሰላምታዬን ያቀረብኩላት፡፡
ታዲያ ትናፍቀኝ እንጅ አኩርፌያታለሁ፡፡ ሰላማዊ ወገኖቿ በሀገሪቱ በየቦታው በወያኔ ነብሰ በላ ወታደሮች ደማቸው
በግፍ ሲፈስ እሪ! ብላ ኡኡታዋን ማቅለጥና ከጉያዋ የተወሸቀውን ግፈኛ አገዛዝ አንቃ ለፍርድ ማቅረብ ሲገባት
ዓይታ እንዳላየች ሰምታ እንዳልሰማች ሆና ጸጥ በማለቷ የምር አኩርፌያታለሁ፡፡
ለነገሩ እሷ ምን ታድርግ? እኛ “አዲስ አበባ! እናት ሀገርሽንና ሕዝብሽን እረሳሽ እንዴ? ኧረ ተነሽ!” ብለን
ላቀረብንላት ጥሪ ቆራጥ ምላሽ ልትሰጥ ስትሰናዳ ሌላው ደሞ ይነሣና “ፊንፊኔ…… !” በማለት ተቃራኒ
መልእክት ባዘለ ይዘት ጥሪውን ያቀርብላታል፡፡ ግራ ገባት! የማንን ትስማ? ጭራሽ የህልውና ሥጋት አደረባትና
አንጀቷ እያረረ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ እርፍ ብላ ለመቀመጥ ተገደደች፡፡
በነገራችን ላይ ነገርን ነገር ያነሣዋልና አዲስ አበባ ከወያኔ ትዕዛዝ በተሰጣቸው ወገኖች ፊንፊኔ እያሉ በይፋ
የመጥራታቸውን ነገር አግባብነት አለው ትላላቹህ? ምን አዲስ አበባ ብቻ ናዝሬትና ደብረዘይትንም አዳማና ቢሾፍቱ
እያሉ ነው የሚጠሩት፡፡ በምን አግባብ ነው እንዲህ ለማለት የቻሉት? እንዲህ ባዮቹ እነኝህንና ሌሎች የሀገራችንን
ክፍሎች ከ16ኛው መቶ ክ/ዘ በኋላ በወረራና በመስፋፋት እንደያዙት እነሱም ይሁኑ የተቀረነው ጠንቅቀን የምናውቀው
ጉዳይ ነው፡፡ ታዲያ እውነቱ ይህ ከሆነ የሀገራችንን ሥፍራዎች የነበራቸውን ስም አጥፍተው አዲስ የራሳቸውን ስም
የመስጠቱን መብት እንዴት አገኙት? ማንስ ይሄንን የመስጠት መብት ኖሮት ሰጣቸው? ምናልባት እነኝህ ከተሞች ወይም
ስፍራዎች በወረራ ከመያዛቸው በፊት የነበረው የቀድሞ አማርኛ ስሞቻቸው አዲስ አበባ፣ ናዝሬት፣ ደብረ ዘይት
ወዘተረፈ ላይሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጅ ከእነዚህ ሥያሜዎች ያልተለየ አማርኛ ሥያሜ እንደነበራቸው ለመገመት
ተመራማሪነትን የሚጠይቅ ጉዳይ አይመስለኝም፡፡ በዚህም ምክንያት የነበራቸውን አማርኛ ወይም ግእዝ ሥያሜዎችን
ትተው ሌላ ሥያሜዎችን መስጠት መጠቀም በፍጹም አግባብነት የለውም ከዚህ ድርጊትም ሊታቀቡ ይገባል!
አዲስ አበባ እኮ ከ229ዓ.ም. እስከ 461ዓ.ም. ድረስ ከአክሱም በተጨማሪ ለ232 ዓመታት ያህል የረር በመባል
በሚታወቀው ምሥራቃዊ ክፍሏ ላይ የአክሱማውያን ነገሥታት ዋና መቀመጫ የነበረች ታሪካዊት ከተማችን ነች፡፡ ይሄም
ወሬ ሳይሆን በስፍራው፣ በአቅራቢያውና በአካባቢው እንዲሁም ወያኔ ኦሮሚያ እያለ በሚጠራው የሀገራችን ክፍል ሁሉ
በግራኝ አሕመድ ወረራ በፈራረሱ በርካታ ጥንታዊ አብያተክርስቲያናትና አብያተመንግሥታት አሻራዎችና ፍርስራሾች
ማረጋገጥ የሚቻለው ጉዳይ ነው፡፡
እና ታዲያ እውነታው እንዲህ በሆነበት ሁኔታ ወያኔ/ኦሕዴድና ኦነግ ምን ዓይነት ኅሊና ቢኖራቸው ነው እንዲህ
ዓይነቱን ነውረኛ ተግባር ሊፈጽሙ የሚችሉት? ለነገሩ ኅሊና የሚባል ነገርስ የት አላቸውና! ወይ በግልጽ የጨዋታው
ሕግ ውንብድናና ዝርፊያ ነው በሉንና አንድ ፊቱን በእሱ እንዳኝ! ነገር ግን በውንብድና የተገኘን ውጤት ሕጋዊ
ለማድረግ እየተጣጣራቹህ ስለ ፍትሕና እኩልነት የማውራት የሞራል (የቅስም) ብቃት እንዴት ሊኖራቹህ ይችላል?
አዳማ የሚለው ሥያሜ እንኳን አማርኛ ወይም ግእዝ ከዕብራይስጥ ወይም ከሌላ የመካከለኛው ምሥራቅ ቋንቋ ከተዋሷቸው
ቃላቶች አንዱ መሆኑ ስላልታወቀና ግእዝ ወይም አማርኛ ስላልሆነ ኦሮምኛ ሊመስል ቻለና ያንኑ ሥያሜ ሊጠቀሙ ቻሉ
እንጅ ቃሉ ኦሮምኛ አይደለም፡፡
አዳማ ኖኅ ለልጆቹ ርሥት ወይም ግዛትን ሲያከፋፍል ለካም የደረሰች የነበረች በኋላም ለልጁ ለከነአን ከተሰጡት
ግዛቶች ውስጥ አንዷ ሥፍራ ናት ዘፍ. 10፥19
ጎጃምም ውስጥ ዣንበራ ወረዳ ጨጎዴ ሐና በሚባል ሥፍራ ደጉ ንጉሥ (በቤተክርስቲያን የትንቢትና በማቴ. 24
ወንጌል ትርጓሜ ላይ ወደፊት ይመጣል ተብሎ የተተነበየለት ቴዎድሮስ በመባል የሚታወቀው ንጉሥ) ይወጣበታል ተብሎ
የሚነገርለት አዳማ በመባል የሚጠራ  ገመገም ተራራ አለ፡፡ አገሩ ያማራ ሀገር ነው፡፡ በዚህ ሥፍራና አካባቢው
የሚኖሩ አማሮች እራሳቸውን እንደ ንጥር (ኦሪጅናል) አማሮች አድርገው የሚቆጥሩ አማሮች ናቸው፡፡ ሕፃናት በዚህ
ተራራ ላይ ከብት ሲያለቅሙ “አንዳንድ ጊዜ ከከብቶች ጋር ሳር ሲለቅም እናየውና የት እንደሚገባ ስንከታተለው
ሳይታየን የሚሠወረን ነጭ ፈረስ አለ!” ይላሉ አረጋውያኑ “የቴዎድሮስ ፈረስ ነው!” ይላሉ፡፡ ይህ ሥፍራ
ቴዎድሮስ ይወጣበታል ተብሎ ከሚነገርላቸው ቦታዎች ሁለተኛው መሆኑ ነው፡፡ ሌላኛው የረር መሆኑ ይታወቃል፡፡
አይይይ! የኔ ነገር! ነገርን ነገር አንሥቶት ነው እንጂ እኔ እንኳን ዛሬ ላወራላቹህ ያሰብኩት ይሄንን
አልነበረም፡፡ መግቢያዬ ላይ እንዳልኳቹህ ለወራት  አዲስ አበባ አልነበርኩም፡፡ ዛሬ መግባቴ ነው፡፡  ዛሬን
ጨምሮ ሰሞኑን ማዕከላዊ ወይም የፌዴራል ፖሊስ (የራስ ገዛዊ ጸጥታ አስከባሪ) በመባል የሚታወቀው የፀጥታ ክፍል
መሥሪያ ቤቱ ድረስ ተገኝቸ የመጥሪያ ወረቀት እንድወስድ በስልክ (በመናግር) ደውለው እያስታወቁኝ ነበር፡፡ አሁን
ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ ነኝ ከ12 ሰዓት በፊት እንደማንገባ ከአሽከርካሪው ተነግሮኛል ይህም ማለት ከሥራ
ሰዓት ውጪ በመሆኑ ፌዴራል ፖሊስ ተገኝቸ መጥሪያውን ሳልወስድ ልቀር ነው ማለት ነው፡፡
እንደምታውቁት መጋቢት ወር ላይ 2006ዓ.ም. ላይ የአኖሌ የጥፋት ሐውልት በጥፋት ኃይሎች ተገንብቶ ሊመረቅ
አካባቢ ዕንቁ መጽሔት ላይ “የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ
የቅሱፋን?” በሚል ርእስ በዋናነት ስለዚህ የጥፋት ሐውልትና ተያይዞ ስላለው ስለወያኔ/ኦሕዴድና ኦነግ  የጥፋት
ኃይሎች ዕኩይ ሰይጣናዊ ዓላማ በሰፊው አትቸ ነበር፡፡ ያ ጽሑፉ ለዛሬው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ጅማሮ የሆነውን
የኦነግ ደጋፊ የሆኑትን የዩኒቨርሲቲ (የመካነ ትምህርት) ተማሪዎችን ቁጣ ቀሰቀሰና መጀመሪያ በጅማ ከዛ በሌሎቹ
ወያኔ ኦሮሚያ ሲል በሚጠራው የሀገራችን ክፍል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች (መካናተ ትምህርት) ዐመፅ ተቀሰቀሰና ንብረት
ወደመ፣ የመማር ማስተማር ሒደቱ ለቀናት ተስተጓጎለ፣ ተማሪዎች ተቀጠቀጡ የተገደሉም አሉ፣ በርካቶች ታሰሩ፡፡
ጥያቄያቸው የነበረው እኔና ጽሑፉን ያስተናገደው የዕንቁ መጽሔት አርታኢ የነበረው ኤልያስ ገብሩ (ኤልያስ ትግሬ
እንዳይመስላቹህ ከኦሮሞና ጉራጌ የተገኘ ነው) “ለፍርድ ይቅረቡ!” የሚል ነበር፡፡ ብዙ ሳይቆይ የተረጋጋ
የመሰለው ዐመፅ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ጨመረና የአዲስ አበባን የማስፋፊያ ዐቢይ አቅድ ወደ መቃወም
ተቀየረ፡፡
በተማሪዎቹ ጥያቄ መሠረትም ጽሑፉ ከተጻፈ ከወራት በኋላ ከሳሽ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ
“መገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ የማሰናዳት የወንጀል ተግባር” የሚል አንቀጽ ተጠቅሶብን ተከሰስን፡፡ በዋስ እስክንፈታ
ድረስም በተለያየ ጊዜ ማዕከላዊና ቅሊንጦ ታስረን ነበር፡፡ ይሄው ክሱ ሁለት ዓመታት አለፈው በከ20 በላይ
ቀጠሮዎች ፍርድ ቤት በመመላለስ ተንገላተናል፡፡ አብዛኛው ቀጠሮ የተቀጠረው ወኅኒ ቤቶቹ የመከላከያ ምስክሮቻችን
ጋዜጠኞችን እስክንድር ነጋን፣ ተመስገን ደሳለኝንና ውብሸት ታዬን ሊያቀርቧቸው ባለመቻላቸው ነው፡፡ በባለፈው
ቀጠሮ ባጋጠመኝ እክል ምክንያት አዲስ አበባ መምጣት ስላልቻልኩ አልቀረብኩም ነበረ፡፡ በዚህ ምክንያት ፍርድ ቤቱ
ፖሊስ (ፀጥታ አስከባሪ) አስሮ እንዲያቀርበኝ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡
በባለፈው ቀጠሮ ወኅኒ ቤቶቹ ምስክሮቻችንን አላቀረቡም ነበር፡፡ ምክንያት ሲጠየቁ እስክንድርን “መንገድ ላይ
ዐመፅ ያነሣሣብናል!” በሚል ሲሆን ተመስገንንና ውብሸትን ደግሞ “በመጓጓዣ ችግር” እንደሆነ ሲገልጹ
ምክንያቶቻቸው አሳማኝ እንዳልሆነ ተነግሯቸው ለነገው ታኅሣሥ 20 ቀጠሮ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ተብሏል፡፡
አሁን ላይ ተመስገንና ውብሸት በከባድ ሕመም ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷልና ነገ አለመቅረባቸው እርግጥ ነው
ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ነገ በግላጭ ፍርድቤት ቀራቢ ነኝ፡፡ እና! ካላቹህ እናማ ምናልባት አልመለስ ይሆናል
ካልተመለስኩ ደኅና ቆዩ ወይም ደኅና ሁኑ ማለቴ ነዋ!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
amsalugkidan@gmail.com

ዘ-ሐበሻ ለጠቅላላ ዕውቀት: የሚያስደነግጥ ዕዳ ያለባቸው 10 የአፍሪካ ሃገራት

 

(ዘ-ሐበሻ) በዛሬው የዘ-ሐበሻ የጠቅላላ ዕውቀት ዝግጅታችን ከአፍሪካ ሃገራት የሚያስደነግጥ ዕዳ ያለባቸውን አስር ሃገራትን ከነ ዕዳቸው መጠን ይዘናል:: አንሰርስ አፍሪካ የተሰኘው አጥኚ ቡድን ባወጣው መረጃ መሰረት ሃገራችን ኢትዮጵያም ከአስሩ ውስጥ ተካታለች:: በ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዕዳ 9 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን ከ2015 ወዲህ ግን ዕዳው በሚያስደነግጥ መሉ ከፍ ብሏል:: ዘገባውን ከቭዲዮው ይመልከቱ::

 

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በጠና ታሟል

የእስር ቤቱ ወታደሮች ተመስገንን ወደ ሆስፒታል ይዘውት ከመግባታቸው ቀደም ብለው በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎችን ከቦታው ዞር እንዲሉ ስላደረጉ የተመስገንን የህምም ደረጅ ቀረብ ብሎ ማየት አልተቻለም፡፡ ተመሰገን በእስትሬቸር እየገፉ ወደ ሆስፒታል ውስጥ አንደስገቡት ለማወቅ ችለናል፡፡ አሁን ከቀኑ 8፡10 ሆናል እስካሁን ተመስገን በዝዋይ ባቱ ሆስፒታል ይገኛል::

የዛሬን ቀን በተመለከተ የዝዋይ እስር ቤት አስተዳዳሬዎችና የዛሬው የሽፍት መሪ ሻለቃ ንጉሴ እንዲሁም እስከ ዛሬ በተመሰገን ላይ ለደረሰው እና ለሚደርሰው ነገር ሁሉ መንግስት ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡

ታህሳስ 18/09 ዓ.ም

ታሪኩ ደሳለኝ (የተመስገን ደሳለኝ ወንድም)

 

ሕወሃት በአማራ ክልል የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች ተሰብሰበው ወደ ትግራይ እንዲላኩ አዘዘ

ሕወሃት ሰሞኑን በውክልና የአማራውን ክልል ለሚያስተዳድሩለት የብአዴን ተላላኪዎቹ በላከው ደብዳቤ በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች በሙሉ ተሰብስብሰው ወደ ትግራይ እንዲላኩለት አዟል።

ሕወሃት ስልጣን ከተቆናጠጠ ጊዜ አንስቶ በመላው ሃገሪቱ የሚገኙ ቅርሶችና ጠቃሚ ቁሳቁሶችን ወደ ትግራይ ሲያጓጉዝ እንደኖረ ይታመናል።

ይህ ሰሞኑን ሕወሃት ለብአዴን ታማኞቹ የላከው ማዘዣ ደብዳቤ ምናልባትም በአማራው ክልል እየተቀጣጠለ የሚገኘው ሕዝባዊ አመጽ ከቁጥጥሩ ውጭ እንደሚሆን በመተንበይ የሚችለውን ያህል ታሪካዊ ቅርሳ ቅርሶችን ለመዝረፍና የአማራውን ብሄር ታሪክ አልባ ለማድረግ የሕወሃት ሹማምንት የጠነሰሱት መሰሪ ሴራ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

ጉዳዩ ያሳሰባቸውና ያስቆጫቸው በርካታ ኢትዮጵያውያን በማኅበራዊ ድረገጾች ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

TPLF letter to ANDM

Antique Ethiopian Coptic Christian Manuscriptስ

Ethnic tensions in Gondar reflect the toxic nature of Ethiopian politics

From uneven development to authoritarian government, the morass of issues facing the city of Gondar offer a snapshot of Ethiopia’s wider problems

A coach torched by protesters during anti-government unrest in Gondar, Ethiopia
A coach torched by anti-government protesters in Gondar, Ethiopia. All photographs by William Davison

In Gondar, a city in Ethiopia’s northern highlands, a lone tourist pauses to take a photo of a fortress built more than two centuries ago. Nearby, past a row of gift shops, lies the wreck of a coach torched during unrest in August.

Gondar, known as “Africa’s Camelot”, was once the centre of the Ethiopian empire – at a time when that empire was defined mainly by Amhara traditions.
Today, the city is facing new tensions that have a complex history. A territorial dispute between elites here in the Amhara region and those in neighbouring Tigray has been simmering for at least 25 years.

Tigrayans have been accused by opponents of wielding undue influence over Ethiopia’s government and security agencies since 1991. In recent months, these and other grievances have led to protests, strikes, vandalism and killings in Gondar, causing a drastic reduction in foreign visitors to the tourism-dependent city and an exodus of fearful Tigrayans.

Shops and schools have reopened in Gondar, after the authorities reasserted control in urban areas by declaring a state of emergency on 8 October. But sporadic clashes with the military continue in the countryside.
“We don’t feel like it is our country. We feel like it is the time when the Italians invaded. We are like second-class citizens,” says a prosperous local businessman. Like all interviewees, he requested anonymity due to fear of reprisals from the authorities. Europeans never colonised Ethiopia, but Mussolini’s army occupied the country from 1936 to 1941.

Gondar’s predicament is a microcosm of Ethiopia’s: a toxic brew of uneven development, polarised debate amid a virtual media vacuum, contested history, ethnic tensions, a fragmented opposition and an authoritarian government. Ethiopia’s rulers show few signs of being able to solve the morass of problems, which many believe the government itself caused.

Trouble began in Gondar in July 2015, when word went around that the authorities intended to arrest Col Demeke Zewdu, a former rebel and retired military officer.When security forces tried to arrest Zewdu, who is a member of a committee campaigning over the contested Wolkait territory, armed Amharas protected him and several people, including security officers, were killed.

Wolkait is an administrative district in Tigray that borders Amhara. The committee says Wolkait and others areas were taken out of Gondar’s control by the Tigrayan People’s Liberation Front in 1992, when Ethiopia was divided into a federation along ethno-linguistic lines. Allied rebels led by the TPLF, who unseated a military regime in 1991, introduced the system and still monopolise power.

Critics of the committee point out that a 1994 census found more than 96% of the people of Wolkait were Tigrayan , and that the complaints of annexation stem from the town of Gondar, not the district itself. The activists say the TPLF moved Tigrayans into the area during the rebellion.

The issue struck a chord in Gondar. After Demeke’s arrest, rural militiamen paraded through the city on 31 July, firing bullets into the air during a large, peaceful demonstration. It is thought that the demonstration was facilitated by the Amhara wing of the TPLF-founded Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) – a four-party coalition that, along with allied organisations, controls all the country’s legislative seats.

A Tigrayan lecturer at Gondar University said he abhors Ethiopia’s ethnicised politics and believes jostling between the Amhara and Tigrayan EPRDF wings lay behind the Gondar violence. The TPLF is the predominant party in the EPRDF, and Amhara National Democratic Movement politicians are seeking greater power, he said. “I don’t believe in parties which are organised on ethnicity. I prefer it to be based on the individual.” An end to ethnic politics would make a resolution of the Wolkait issue possible, he believes.

Among activists from Amhara, disavowal of the ethnicity-based system is at the crux of disagreements over how to oppose the EPRDF. Because federalism formally protects the rights of communities marginalised during previous eras, when Ethiopia was a unitary state, promoting national unity at the expense of ethnic autonomy is often cast as regressive.

Groups promoting Amhara identity within a democratised federation are therefore at odds with those focused on national cohesion, according to Wondwesen Tafesse, a commentator on Amhara issues. “Since most diaspora Amharas support Ethiopianist political parties, they seem to have this fear in the back of their mind that a resurgent Amhara nationalism, and the possible emergence of a strong Amhara political organisation, might undermine their political designs,” said Wondwesen.

In the weeks after Demeke’s detainment, there was more unrest, amid allegations that Tigrayan businesses were being targeted and Tigrayans attacked. People in Gondar say the companies were targeted because of their connections with the regime, rather than the owners’ ethnicity.

Amba Giorgis town in the North Gondar district of Ethiopia’s Amhara region
Pinterest
Amba Giorgis town in the North Gondar district of Ethiopia’s Amhara region. A territorial dispute has recently caused clashes between farmers and the military

Unrest in Amhara was preceded by protests by the Oromo, Ethiopia’s largest ethnic group, who also complain of marginalisation and repression. In response, the government has reshuffled officials – and intensified repression. During the state of emergency, the government has sent at least 24,000 people to camps for indoctrination under rules that allow the suspension of due process. According to the Association for Human Rights in Ethiopia, security forces killed some 600 demonstrators over the past year.

Since the beginning of November, a new federal cabinet has been announced and similar changes made in the Amhara government. But while maladministration and corruption were tagged as the pre-eminent problems, there is little evidence of officials being punished, or of policy reforms. An Amhara government spokesman said systemic changes were not required.

In August, on the outskirts of Gondar near Demeke’s neighbourhood, a crowd looted Baher Selam hotel. It was targeted following a rumour that the Tigrayan security officers allegedly involved in the operation to arrest the colonel were staying there.

Near the wrecked hotel, an elderly lady was roasting coffee beans. On the morning of the incident she was coming home from church when she heard gunshots.Business has since declined and large numbers of unemployed young people have been mobilised against the government, she said.

People here believe Wolkait was part of Gondar throughout history. “If they take that place, where else are they going to take?” the woman asked. “The situation is not going to go back to normal. If you light a match, it’s small – but it can burn a whole area.”

አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች ፈተናቸው ብዙ ነው – ቢሆንም ድጋፌ አይለያቸውም #ግርማ_ካሳ

አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች በአሁኑ ጊዜ እየተንቀሳቀሱ ነው ማለት አይቻልም። የአመራር አባላቶቻቸው አብዛኞቹ ታስረዋል። የሰማያዊ ፓርቲን ብንመለከት እንኳን የምክር ቤት ሰብሳቢው ይድነቃቸው ከበደ፣ በቅርቡ የተደረገዉን ጠቅላላ ጉብዬ ሲመርይ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ እንዲሁም ሌሎች ብዙዎች ታስረዋል።

በአገዛዙ የሚደረሰው አፈናና እንግልት እንደተጠበቀ፣ ሌሎች እየታሰሩና ዋጋ እየከፈሉ ታጋይ ነን ባዮች ትግሉ የወያኔ መሳቂያ እያደረጉትም ነው። ወያኔዎች ካደረሱት ጉዳት የበለጠ ደግሞ የሚያመዉና የሚጎዳው ይሄ በፓርቲዎች ዉስጥ የሚታይ የፖለቲካ እንጭጭነት ነው።

አንድ አሳዛኝ ዜና ሪፖርተር ላይ አነበብኩኝ። ጥቂት የኢንጂነር ይልቃል ደጋፊዎች ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሄደው የረበሹበት ሁኔታ ነው ያለው። ቆይ ረብሻ የሚፈጥሩት እነዚህ የኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ደጋፊዎች ፣ ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተገኝቶ መረበሻቸው ለትግሉ ምን ፋይዳ ነው የሚሰጠው ? ይሄንን ቢመልሱልኝ ደስ ይለኛል።

የ2007 ምርጫ ከተደረገ በኋላ በኢንጂነር ይልቃል እና አቶ ይድነቃቸው ከበደን፣ የፓርቲው የምክር ቤት ሰብሳቢን (አሁን በወያኔዎች የታሰረ) ጨመሮ በሌሎች አመራር አባላቶች መካከል አለመግባባቶች ተከስተው ነበር። ከአንድ አመት በላይ ችግሮችን መፍታት ስላልቻሉ ጠቅላላ ጉብዬ ተጠራ። እነ ኢንጂነር ይልቃል ጠቅላላ ጉብዬው የተጠራው በትክክለኛ መንገድ አይደለም ብሎ ለምርጫ ቦርድ አመለከቱ። ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባዬው በድርጅቱ ደንብ መሰረት ስለመጠራቱ እስካጣራ ጉብዬው እንዳይደረግ ብሎ አዘዘ። ነገሮች ካጣራ በኋላ ተወካዮች ልኮ፣ ጉብዬው ተደረገ። በጉብዬው ኢንጂነር ይልቃል አልተገኙም ነበር። ሆኖም ጉባዬው በምትካቸው ለሁለት አመት ከነሃብታሙ አያሌው ጋር በወህኒ ሲሰቃይ የነበረውን የሺዋስ አሰፋን ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ።ኢንጂነር ይልቃል ያንን አልቀበልም ብለው አቤቱታ ለምርጫ ቦርድ አቀረቡ። በአሁኑ ወቅት ምርጫ ቢርድ ጉዳዩን እንደገና እየተመለከተው ነው። (መጀመሪያ ደረጃ ምርጫ ቦርድ ድረስ መካሰስ አሳፋሪ ነው።)

የተደረገው ጠቅላላ ጉብዬ በምርጫ ቦርድ ተወካይ ታዛቢነት ቢደረግም፣ ምርጫ ቦርድ የጉባዬውን ሪፖርት መርምሮ፣ ኮረም መሙላቱን አረጋግጦ፣ በደንቡ መሰረት ጉብዬው መደረጉ አይቶ፣ ለአዲሱ አመራር እውቅና ይሰጣል፤ ወይም እንደገና ሌላ ጠቅላላ ጉብዬ እንዲጠራ ያደርጋል። ያ ወደፊት የምናየው ይሆናል።

ነገሩ በዚህ ሁኔታ እንዳለ የኢንጂነር ይልቃል ደጋፊዎች በዚህ መልኩ ስብሰባዎችን እንደ ዱርዬ መረበሻቸው ግን አሳፋሪ ነው። አንደኛ ምርጫ ቦርድ እነርሱ የፈለጉትን ቢወስንና ኢንጂነር ይልቃል የሰማያዊ ፓርቲ መሪ እንደሆነ ቢገለጽም፣ ይህ አይነቱ ድርጉት ፓርቲው ክፉኛ የሚጎዳ ነው። ለምን አርቀው እንደማያስቡ አይገባኝም።

የሰማያዊ ፓርቲን ደንብ አንብቤዋለሁ። ማንም ከፈለገ ደንቡን ተመርኩዞ ልከራከር ካለ መከራከር እችላለሁ። በደንቡ መሰረት የኦዲት ኮሚሽኑ ጉብዬ መጥራት ይችላል። በመሆኑም አሁን ላለው አዲሱ አመራር በግሌ እውቅና እሰጣለሁ። በአቶ የሺዋስ አሰፋ የሚመራውም ይህ አዲስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር፣ በሁኔታው ሳይደናገጥ መስራትና ማድረግ የሚችለው ፣ በጣም ዉስን በመሆኑ ( የአገዛዙ አፈና በመብዛቱ) ትንሿን ማድረጉን እንዲቀጥል አበረታታለሁ። ለዱርዬ ፖለቲካ ብዙ ቦታ መስጠት የለባቸውም። አለመስማማቶች፣ ልዩነቶች ይኖራሉ። ግን ልዩነቶች ደንብና ሕብ በሚፈቅደው መሰረት መፍታት ሲገባ መረበሽ ዘመናዊ ፖለቲካ አይደለምና፣ ብዙ ሊያስጨነቃቸው አይገባም።

ለኢንጂነር ይልቃል ደግሞ አጭር መልእክት አለኝ። ትግሉ ከርስዎም ሆነ ከማናችንም የበለጠ ነው። በመሆኑም እርስዎ ለችግር ምክንያት መሆን የለብዎትም። የእርስዎን ስም እየጠሩ የሚረብሹትን አደብ እንዲገዙ ያደርጉ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ። በአዲሱ አመራር አካሄድ አለመስማማትዎት መብትዎት ነው። በዚያ ችግር ሊኖር አይችልም። ሆኖም ግን የድርጅቱን ደንብ አክብረው፣ እንደዉም በድርጅቱ ዉስጣዊ መድረክ የአሁኑ አመራር ቻልንጅ እንዲያደርጉ አበረታታዎታለሁ። እርስዎና አቶ የሺዋስአንድ ወቅት አንድነት ፓርቲ የነበራችሁ ጊዜ ጓደኛሞች ነበራችሁ። ታዲያ ምን ችግር አለው አሁን ለሰማያዊ ፓርቲ ዋጋ የከፈሉት አንገት ከሚደፉ ከቀድሞ ጓደኛዎ፣ ለትግሉ ዋጋ ከከፈለው፣ ከአሁኑ ሊቀመንበር ጋር ቁጭ ብለው ቢነጋገሩ ? ምን ችግር አለው ሊቀመንበርስ ባይሆኑ ? ለመታገል የግል መሪ መሆን ያስፈለጋል እንዴ ?

ለተቀረነው ደግሞ ይሄን እላለሁ። አገር ቤት ያሉ ደርጅቶች ብዙ ችግር አለባቸው። አዎን ደካሞች ናቸው። ዉጭ ካሉ ደርጅቶች የደከሙት እነርሱ ይሻላሉ። አዎን ፈተናቸው ብዙ ነው። ግን እነርሱን የበለጠ እንዲጠናከሩ ማድረጉን ነው የምመርጠው።

ኦህዴድ በተሃድሶ እና በአመራሮች ሹም ሽር ኦፌኮ በአመራሮች እስር የተጠመዱበት የኦሮሚያ ፖለቲካ

 

በይርጋ አበበ 

ከ80 በላይ ብሔረሰቦች እና ብሔሮችን የያዘው የኢትዮጵያ ግዛት ላለፉት 25 ዓመታት በኢህአዴግ እየተመራ ሲሆን 547 መቀመጫዎች ያሉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ደግሞ ላለፉት 14 ወራት በኢህአዴግ አባሎች ብቻ ተይዟል። በአገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት በህግ ደረጃ የጸደቀ እና እውቅና የተሰጠው ቢሆንም ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የአገሪቱን ሁሉንም ክፍሎች በትጥቅ ትግል የደርግን መንግስት አስወግዶ ስልጣን ከያዘው ከኢህአዴግ እና አጋር እያለ ከሚጠራቸው የአምስቱ ታዳጊ ክልሎች (ሶማሊያ፣ ሀረሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ አፋር እና ጋምቤላ) ገዥ ፓርቲዎች ውጭ የፖለቲካ ስልጣን የተረከበ ሀይል አልታየም። ይህ ክስተትም ኢህአዴግን “ስልጣኑን ለማካፈል የማይሻ እና የፖለቲካ አመለካከት ብዝሃነትን መቀበል የሚከብደው” እየተባለ እንዲተች አድርጎታል። የመድረክ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉ አቶ ጥሩነህ ገምታ “የፓርቲ ፖለቲካ በኢትዮጵያ” በሚለው መጽሃፋቸው “ህወሓት/ኢህአዴግ የሚከተለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ አውራ ፓርቲነት የተለያየ አመለካከት ያላቸውን የኢትዮጵያ ህዝቦች በአገር ስሜት ማስተባበርና ማሳተፍ የማይችል ከቻይናው አዲሱ ዴሞክራሲ የተቋጬ ዲቃላ ርዕዮተ ዓለም የሚከተል ድርጅት ነው” ሲሉ ይገልጹታል። አቶ ጥሩነህ አያይዘውም “ኢህአዴግ በባህሪው የመድብለ ፓርቲ ስርዓትን (የፖለቲካ አመለካከት ብዝሃነትን) ለመቀበል የሚከብደው ነው” ይላሉ።

በ2008 ዓ.ም ኅዳር ወር ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ቁጣ እና በኋላም በአማራ ክልል ከተፈጠረው ተመሳሳይ ሁነት በኋላ ገዥው ፓርቲ ወደ ውስጡ ተመልክቶ ችግሮቹን ለይቶ በማውጣት ከህዝብ ጋር በመወያየት በጥልቀት ተሃድሶ እንደሚያደርግ ቃል መገባቱ የሚታወቅ ነው። እንደተባለውም በአቶ ኃይለማሪያመ ደሳለኝ አማካኝነት በ2008 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ የተሾሙት የገዥው ፓርቲ ጎምቱ ካቢኔዎች (የፌዴራል መንግስቱ ባለስልጣናት) ለአንድ ዓመት ስልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ በሌላ ጓዶቻቸው ተተክተው እነሱ ደግሞ ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋውረው እንዲሰሩ ሹመት ተሰጥቷቸዋል። ይህ የፌዴራል መንግስቱ ተሞክሮም የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች በሚያሰተዳድሯቸው ክልሎች ተፈጻሚ በመሆን በርካታ የክልል፣ የከተማ አስተዳደር፣ የዞን፣ የክፍለ ከተሞች እና የወረዳዎች ካቢኔ ሹም ሽሮች ተካሂደዋል። በዚህ ዝግጅታችን በአገራችን ሰፊ የቆዳ ሰፋት እና ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የያዘውን የኦሮሚያን ክልል ፖለቲካዊ ብዝሃነት (Political Diversity) ሁኔታ ለመመልከት እንሞክራለን።

 

የኦሮሞ ፖለቲካ በ25 ዓመታት ውስጥ

በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ተሳተፎ እያደረጉ ከሚገኙ ዘውጌ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሚያን ክልል የሚያስተዳድረው የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) እና በክልሉ የኦህዴድ ተቀናቃኝ የሆነው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ይገኙበታል። እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች በተለያዩ የፖለቲካ ግለቶች እና ውዝግቦች ታጅበው በክልሉ እየተንቀሳቀሱ ሲሆን በተለይ የአራት ኪሎውን ቤተ መንግስትም ሆነ የፍላሚንጎውን የኦሮሚያን ጬፌ (የኦሮሚያ ክልል መንግስት) ወንበር መጨበጥ ያልቻለው ኦፌኮ ከሚያቀርባቸው ፖለቲካዊ አቤቱታዎች መካከል ኦህዴድ እንዳልንቀሳቀስ ቀፍድዶ ይዞኛል የሚለው ክሱ ቀዳሚው ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በክልሉም ሆነ በብሄረሰቡ ተመራጭ “እኔ ነኝ” ሲል በድፍረት ይናገራል። ለዚህም አንዱ ማሳያው አድርጎ ኦፌኮ የሚያቀርበው “ላለፉት 25 ዓመታት በኦሮሚያ ክልል የተረጋጋ ሁኔታ አለመኖሩን በተለይም በተደጋጋሚ ጊዜ በክልሉ የሚነሳው ህዝባዊ አመጽ እና ባለፈው አንድ ዓመት ሙሉ በክልሉ የነገሰው ውጥረት ምክንያቱ ኦህአዴድ በክልሉ ህዝብ ያለመፈለጉ ምክንያት የፈጠረው ነው። ለዚህ ደግሞ ኦህዴድ ለክልሉ ህዝብ መስራት ከሚገባው በታች መስራቱ ነው” ኦፌኮ አያይዞም ኦሀዴድን በሙስና እና በኪራይ ሰብሳቢነት ይከሰዋል።

የክልሉ ገዥ ፓርቲ ኦህዴድ በበኩሉ “ኦፌኮ ለኦሮሞ ህዝብ ሰላምና ልማት የሚያበረክተው አንዳች ረብ ያለው ፓርቲ እንዳልሆነ ደጋግሞ ይገልጻል። የራሱን ፕሮግራም ተመልክቶ ለክልሉ ህዝብ የሚበጀውን አጀንዳ ከመቅረጽ ይልቅ የተሰሩ ልማቶችን በመንቀፍ ጊዜውን ያጦፋል” በማለት ይተቸዋል። በኪራይ ሰብሳቢነትና በሙስና ላይ ያለውን አቋም በተመለከተም የቀድሞው የፓርቲው ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር ከድር የኦህዴድን 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አስመልክቶ ለመንግስታዊ አዲስ ዘመን ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ “በፓርቲያችን ውስጥ ሙስና እና ኪራይ ሰብሳቢነት መኖሩን በግምገማችን ለማወቅ ችለናል። በዚህ ላይ በወሰድናቸው ተከታታይ እርምጃዎችም ኪራይ ሰብሳቢነትን በገጠሩ ክፍል ሙሉ ለሙሉ በሚያስችል መልኩ ማጥፋት ብንችልም በከተማዎች ግን ችግሩ ስር የሰደደ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ገና ብዙ ይቀረናል።” ሲሉ ተናግረው ነበር።

የኦህዴድ ተሃድሶ

ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ኦህዴድ በተደጋጋሚ ጊዜ የአመራር እና አባላት ግምገማ በማካሄድ ተስተካካይ የለውም። የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶከተር ነጋሶ ጊዳዳ “ዳንዲ የነጋሶ መንገድ” በሚለው መጽሃፋቸው በአንድ ወቅት “3000 የፓርቲው አባላት መባረራቸውን” አስታውቀዋል። ከዚያ ጊዜ በኋላም ቢሆን ኦህዴድ ከቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት ጁነዲን ሳዶ እና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አልማዝ መኮ ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ አመራሮቹ በግምገማ ከመሰናበታቸውም በላይ በፖለቲካ አመለካከታቸው ልዩነት ምክንያት ከአገር ሲኮበልሉ እና አገር ውስጥ ሆነው ሲቃወሙ ይታያሉ።

ካለፈው ዓመት ጀምሮ አሁንም በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ያደረገው በገዥው ፓርቲ ላይ የተነሳው ህዝባዊ ቁጣ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው በኦሮሚያ ክልል ያለው ተቃውሞ መሆኑን ተከትሎ ኦህዴድም ራሱን ገምግሞ የመፍትሔ እርምጃዎችን ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ቀደም ባሉት ሳምንታት አስታውቋል። ከዚህ የፓርቲው እርምጃዎች መካከል ደግሞ አንዱ የሆነው ከፓርቲ አመራሮቹ እና ከክልሉ የመንግስት ኃላፊዎች ላይ የካቢኔ ሹም ሽር ማድረጉ ይገኝበታል። በዚህ የካቢኔ ሹም ሽሩ መሰረትም የክልሉን ፕሬዝዳንት ሙክታር ከድርን በቀድሞው የክልሉ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ለማ መገርሳ የተካ ሲሆን የፓርቲውን ምክትል ሊቀመንበር ወይዘሮ አስቴር ማሞን ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተክቷል።

በወቅቱም አዲሱ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ “በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚታየውን የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት በህዝብ አገልጋይነት ለመተካት ልዩ ትኩረት እንሰጠዋለን። ወጣቱን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ማድረግ፣ የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ማረጋጋት እና ከህዝቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይኖርብናል” ሲሉ ተናግረው ነበር።

የክልሉ መንግስት የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ፈቃዱ ተሰማ በበኩላቸው ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “በክልላችን ለሚገኙ ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ከኢኮኖሚው ተጠቃሚ ማደረግ፣ ለህዝብ የሚቀርቡ አገልግሎቶችን ማሻሻል፣ ህዝቡ ሲያነሳቸው የነበሩ ጥያቄዎችን መመለስ፣ ከድንበሮች ጋር ተያይዞ የሚነሱ ግጭቶችን መፍታት፣ በኢንቨስትመንት ስም የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ማቋቋም እና ተገቢውን የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት እና የክልሉን ሰላምና ጸጥታ ማረጋጋት” ሲሉ የአዲሱን ካቢኔ የመጀመሪያ የቤት ስራዎች መናገራቸው ይታወሳል።

ኦህዴድ ከክልሉ የመንግስት መዋቅር እና ከከፍተኛ የፓርቲ አመራሮች ሹም ሽር ማግስት ደግሞ ሰሞኑን (ባሳለፍነው ሰኞ) በምዕራብ አርሲ እና በጅማ ዞኖች እንዲሁም በጅማ እና ሻሸመኔ ከተሞች የካቢኔ ሹም ሽር አካሂዷል። ይህ እርምጃም ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ ለመስጠትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እንደሚረዳ ኦህዴድ ገልጿል። በሌላ በኩል ደግሞ የካቢኔ ሹም ሽሮችና የፓርቲው የተሃድሶ ስራ በክልሉ ለሚነሱ የህዝብ ጥያዎችና አለፍ ሲልም ህዝባዊ ተቃውሞዎች የሚሰጡት ምላሽ ሊኖር አይችልም ሲሉ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ተናግረዋል።

 

 

የኦፌኮ አቤቱታ

ኦፌኮ ሊቀመንበሩ ዶከተር መረራ ጉዲና “ከሽብርተኛ ድርጅት አመራር (የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ)” ጋር ተገናኝቶ በመወያየት የጸረ ሽብርተኝነት አዋጁን ተላልፈዋል ተብለው ታስረው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የውጭ ቋንቋዎች አስተማሪ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ወደ አሜሪካ ሂደው “ከአሸባሪው” ኦነግ ጋር በመገናኘት የሽብር ተልዕኮ ለመፈጸም ተነጋግረው መጥተዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው እስር ቤት ከገቡ ዓመት አልፏቸዋል። የፓርቲው ዋና ጸሃፊ አቶ በቀለ ነጋ ደግሞ ከማንኛውም የፖለቲካ ተሳትፎ እና ማንኛውንም ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ በቤታቸው በቁም እስር ከዋሉ ዓመት አልፏቸዋል፤ የእሳቸው ምክትል አቶ ደጀኔ ጣፋም እስር ላይ ናቸው። ከዚህ በተረፈ ደግሞ ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ለእስር መዳረጋቸውን ፓርቲው ይናገራል።

የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ “ፓርቲያችን ኦፌኮም ሆነ ሊቀመንበራችን ዶክተር መረራ እንደሚታወቀው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን የምንመኝ ነን። በጠብመንጃ ስልጣን ይዞ የአገሩን ዜጋ ከሚጠራጠር የአገዛዝ ስርዓት ተላቀን የምንፈልገው ሰላምና ዴሞክራሲ የሁላችንም በሆነችዋ አገራችን ላይ እንዲሰፍን የምንታገል ሰዎች ነን” ብለዋል። በቅርቡ የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) በአመራሮቹ ላይ ሹም ሽር አካሂዷል ተሃድሶ እያደረገም ይገኛል። ይህ የክልሉ ገዥ ፓርቲ እንቅስቃሴ በእናንተ እና በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚኖረው ጠቀሜታ አይኖርም ወይ? ለሚለው የሰንደቅ ጋዜጣ ጥያቄ መልስ የሰጡት አቶ ሙላቱ “አዲሶቹ አመራሮች እኮ የሚሰሩት የቀድሞዎቹን እንጂ የስርዓት ለውጥ ወይም የሲስተም ለውጥ የሚያመጡ አይደሉም። የህዝቡ ጥያቄ እኮ እርቅ ይውረድ፣ ከአለአግባብ የታሰሩ ሰዎች ይፈቱ፣ የስርዓት ለውጥ ይምጣ እንጂ እናንተ እርስ በራሳችሁ እየተለዋወጣችሁ ታድሰናል አትበሉን አላልንም ነው። ስለዚህ የዚህ ፓርቲ ተሃድሶም አልኮው መለዋወጥ ይበልጥ አፈናውን እና እስሩን ያባብሰዋል እንጂ የተሻለ ዴሞክራሲ እና መረጋጋትን ሊያመጣ አይችልም” ሲሉ ገልጸዋል።

በቅርቡ ለእስር የተዳረጉትን የፓርቲውን ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲናን የእስር ቤት ሁኔታ በተመለከተ ደግሞ “ዶክተር መረራ ተጠርጥሮ ቢታሰርም በወዳጆቹ እንዳይጠየቅ ተደርጓል። ይህ ደግሞ የግለሰቡን ሰብአዊና ህገ መንግስታዊ መብት መጣስ ነው። በሌላ በኩል ጠበቆቹ አቶ ወንድሙ ኢብሳ እና ዶክተር ያዕቆብ ኃይለማሪያም እንዲጠይቁት የተደረገውም እጆቹን በካቴና ታስሮ እና በፖሊስ ታጅቦ ሲሆን ለተወሰነ ደቂቃ ብቻ (30 ደቂቃ) ነው እንዲያነጋግሩት የተፈቀደው። ከዚህ በተረፈ ደግሞ ምንም እንኳ ሰውየው የጤና ችግር ቢኖርበትም በአሁኑ ወቅት ግን ጤንነቱ ደህና መሆኑን ጠበቆቹ ነግረውናል” ብለዋል።

ምንጭ፦- ሰንደቅ

በገዢው ፓርቲ ጥልቅ ተሐድሶ ፍኖተ ሐሳብ፣ ተራማጅ ኃይሎች ከወዴት ነው ያሉት?

 

በ2008 ዓ.ም. ህዳር ወር ጀምሮ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የተነሣሣው ሕዝባዊ ቁጣ ለበርካታ ሕይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም ምክንያት መሆኑ የአደባባይ እውነት ነው። ቀውሱን ተከትሎ የተለመደው ህግ የማስከበር ሥርዓት አደጋ ላይ በመውደቁ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ሁኔታዎች አስገድደዋል። ዐዋጁ በሥራ ላይ በሚቆይባቸው ስድስት ወራት ሀገሪቱ በተቋቋመው ኮማንድ ፖስት እንደምትመራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበውም አጸድቀዋል።

በወቅቱ በተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ የተደናገጠው ገዢው ፓርቲ የችግሩ ምንጭ የመልካም አስተዳደር እጦት እንደሆነ መግለጹ የሚታወስ ነው። ይህም በመሆኑ ‘ጥልቅ ተሃድሶ’ ለገዢው ፓርቲ እና ለሥርዓተ-መንግስቱ አስፈላጊ መሆኑ ተነገረ። በይፋም ገዥው ግንባር የተሃድሶ ክተት ዐውጆ የፓርቲ እና የመንግስት መዋቅርን ለማፅዳት እየተፍጨረጨረ ይገኛል።

‘ጥልቅ ተሃድሶ’ እየተባለ በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ መድረኮች እና በመገናኛ ብዙሃን የሚለፈፈው፣ አነጋጋሪ ብቻ ሳይሆን፣ “ለምጣዱ ሲባል፣ አይጧ ትለፍ” እንዲባሉ፤ ልፈፋው የቀድሞውን ሊቀመንበር አገላለጽ የሚያስታውስ ሆኖ ነው ኅብረተሰቡ ያገኘው።

አብዛኞቹ የፓርቲው የፖለቲካ አመራሮች ስለጥልቅ ተሃድሶው መሰረታዊ አስተሳሰቦች ሲያብራሩ፣ “የአስተሳሰብ መታነጽ፣ የተንሸዋረረን አመለካከት መለየትና ማስተካከል፣ የሥርዓተ-መንግስትን ስልጣን እና የፓርቲን ስልጣን መለየትና እንደአግባቡ መጠቀም” የሚሉ ሐረጎች ሲጠቀሙ ይደመጣሉ። የጥልቅ ተሐድሶው አፈፃጸም ጓዶቻቸውን “የግድ መጠየቅ እና ማሰር ላይጨምር ይችላል፤ ዋናው የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ነው፤ ሲሉ ተደምጠዋል።

ሆኖም ግን ከፖለቲካ አመራሮቹ የሚሰማው “የአመለካከት ለውጥ ማምጣት” የሚለው ፍሬ ነገር መነሻው ግልጽ አይደለም፤ ምክንያቱም የሚባለው ኪራይ ሰብሳቢነት ከዝንባሌም አልፎም  በተግባር ከገነገነ በኋላ ሁኔታውን እንደምን በተሐድሶ ለመቀየር እንደሚቻል አመራሮቹ ብቻ ነው የሚያውቁት። ከእነርሱም አንዳንዶቹ በዚሁ የአመለካከት እና የተግባር ንቅዘት ውስጥ የተነከሩ መሆናቸው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው።

ራሳቸውን ያላጸዱ ወይም መፅዳት የማይፈልጉ የፖለቲካ አመራሮች፣ ጓዶቻቸውን እና ሌሎች የሲቨል ሰርቪስ ሠራተኞችን ወደ አመለካከት ጥራት ለማምጣት እንዴት ይቻላቸዋል?

ገዢው ግንባር አሁን በሚገኝበት ፖለቲካዊ ቁመና፣ በነጭ እና በጥቁር የሚመሰሉ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ናቸው ያሉት፤ ብሎ መደምደም ይቻላል። የግራጫውን ማለትም የቀናውንና የሚበጀውን ቦታ የያዙ ተራማጆች እንዳሉ ለማሰብ ያዳግታል፤ አሉ ቢባል እንኳን የበላይነቱን ከተቆጣጠሩቱ ኪራይ ሰብሳቢ የሆኑት የፖለቲካ አመራሮች የሚደርስባቸውን ጫና ለመቋቋም ይሳናቸዋል፡፡ ስለዚህም ምርጫው የበላይነቱን ከያዙት ኪራይ ሰብሳቢ የፖለቲካ አመራሮች ጋር በግልጽ መቀላቀል አልያም ከውስጣዊው የፓርቲ ትግል ራሳቸውን አርቀውና የታዛቢነት ሚና ወስደው የለውጥ ሒደት እስኪጀመር በአማራጭነት መጠበቅ ብቻ ነው።

በሚለፈለፈው “ጥልቅ ተሃድሶ” ምንአልባት ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው እነዚሁ ከውስጣዊ ትግል ራሳቸውን አርቀው የታዛቢነት ሚና ወስደው የሚበጀውን የለውጥ ሒደት በአማራጭነት እየተጠባበቁ ካሉ አመራሮች ነው። የንቅዘት ፈረስ ሲጋልቡ የነበሩቱ ግን ዛሬ ላይ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በደህንነት ኃይሎች ዋጋ በተረጋጋ ሀገር የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚን “ከእኛ” በላይ የሚደፍቀው የለም እያሉ በአደባባይ ቢለፈልፉም፣ በሕዝብ የተተፉ ኃይሎች ናቸው።

ለዚህም ነው፣ የጥልቅ ተሃድሶው ፍኖተ ሐሳብ በቀለም አልባ መስመሮች የተሰመረ ነው የሚባለው። ፍኖተ ሐሳቡ ከውስጣዊ የፓርቲው የፖለቲካ ትግል ወደ ሰፊው ሕዝብ መሰመር አለበት የሚባለው። ይህም ሲባል በ‘ጥልቅ ተሃድሶ’ ይቀጣጠላል የተባለው የፖለቲካ ትግል፤ በፓርቲው እና በሥርዓተ-መንግስቱ ውስጥ የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚ ከዝንባሌም አልፎ በተግባር እንዲንሰፋራ ያደረጉትን አመራሮች ቆርጦ በመጣል መገለጽ አለበት ነው፤ እየተባለ ያለው። ከዚህ ውጪ ከአመለካከት ወደ ተግባር፤ ከተግባር ወደ አመለካከት እንቀይራለን እየተባለ የሚለፈፈው ከቃል ነቢብ በዘለለ ፋይዳ እንደማይኖረው ነው የሚታመነው፡፡

ቢያንስ ባለፉት አዐሥራ አምስት የዕድገት አመታት ውስጥ አንዳንድ ተጠቃሽ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ዝቅጠት፤ ከአመለካከት ወደ ተጨባጭ ተግባር የገነገነውን የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚን፣ “በሶስት ወር “የጥልቅ ተሃድሶ” ወደ ሕዝባዊ መስመር እንመልሰዋለን” መባሉ አመክንዮአዊ ያልሆነና ሕዝባዊነትን ያላስቀደመ ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ብቻ የሚነገር ያስመስለዋል፡፡ የፓርቲውን ባለድርሻ አካላት ሳይቀር ውዥንብር ውስጥ መክተቱ አይቀርም፡፡

“ጥልቅ ተሃድሶ” የአመለካከት ለውጥ በማድረግ የሚመጣ መሆኑ ቢገለጽም በፓርቲ ውስጥ የመወሰን ስልጣንን ባላቸው ኃይሎች የሚወሰን ነው፡፡ የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ አራማጆችን በውስጠ ፓርቲ ትግል ከሥሩ ነቅሎ መጣል እስከአልተቻለ ድረስ፤  የሚካሄድ ማኅበራዊ አብዮት እንደሚኖር ነብይነት አይጠይቅም፡፡

በግልፅ ለመናገር፣ ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት የተረጋጋ የፖለቲካ አየር ያገኘችው፣ ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን የመጠበቅ ኃላፊነት በተጣለባቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በደህንነት ተቋማት እንጂ የፖለቲካ አመራሩ በዘረጋቸው የሲቪል ተቋማት አለመሆኑ ግንዛቤ መውሰዱ ጠቃሚ ነው። ለዚህም ነው፤ ገዢው ፓርቲ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከደህንነት ተቋማት ድጋፍ ውጪ፤ ሕዝባዊ መሰረት ባለው የፖለቲካዊ ቁመና ላይ ፈጥኖ መገኘት አለበት፤ የሚባለው፤ ወይም ግፊት እየተደረገበት ያለው።

ይህ እንዳይሆን ግን፣ በገዢው ግንባር ውስጥ አንዱ ሌላው ላይ ላለመደራረስ የወሰኑ የሚመስሉ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ቁጥር፣ በግልፅ ለመፈታተሽ ፈቃደኛ ከሆኑት ከፍተኛ አመራሮች የበዙና የገዘፉ እንደሆኑ አሳማኝ ምልክቶች አሉ። ይህም በመሆኑ ነው፣ ከሥርነቀል ለውጥ ይልቅ ጥገናዊ ለውጥ ማድረግን በአማራጭነት ይዘው የቀረቡት። ለዚህም ነው፣ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሕዝባዊነትን የዘነጉ የፖለቲካ አመራሮች፣ በሌላ ቦታ እንደገንዘብ ታጥበው ብቅ እንዲሉ በፓርቲው ውስጥ በዘረጉት ኔትዎርክ የሚፈቀድላቸው። ለምን እንደዚህ ይሆናል ተብሎ ሲጠየቅም፣ የአመለካከት ለውጥ እንጂ ሰዎችን በማሰር ወይም በማሳደድ የሚመጣ ውጤት የለም፣ እየተባለ የኔትዎርኮቹን ቁልፍ በያዙ አመራሮች የሚገለጸው፡፡

በኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚ አመለካከትና ተግባር ውስጥ የተዘፈቁና ሕብረተሰቡ በአደባባይ የሚያውቃቸው የፖለቲካ አመራሮች፤ በተለያዩ ትንታኔዎች ሽፋን ሾልከው የሚያልፉበት አሰራር መዘርጋቱ አጠያያቂ ከመሆን አይዘልም፤ በአስቸኳይም መቆም ይኖርበታል፡፡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የደህንነት ተቋማትም፤ ገዢው ፓርቲ፣ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን መሰረት ባደረገ መልኩ ኪራይ ሰብሳቢ የፖለቲካ አመራሮቹን እንዲታገላቸው ጫና ማሳደር ይጠበቅባቸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታወጀው፣ ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ እንጂ፣ ገዢው ፓርቲ ኪራይ ሰብሳቢ የፖለቲካ አመራሮቹን እንደተሸከመ ከመጣበት ፖለቲካዊ ቀውስ እንዲሻገር አይደለም። ገዢው ፓርቲ ለሕዝቡ ፍላጎት እንዲገዛ ማስገደድ ወይም በጎ ተፅዕኖ  ማሳደር ሕገ መንግስታዊ ተልዕኮ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ተግባር ነው፤ ይገባልም።

ገዢው ፓርቲ፣ “በጥልቅ ተሃድሶ የአመለካከት ለውጥ” ትንታኔ ሽፋን፣ ኪራይ ሰብሳቢ የፖለቲካ አመራሮችን ተሸክሞ የተሃድሶ ጉዞውን ደምድሜያለሁ ካለ፤ በቀጣይ ለሚፈጠረው ማኅበራዊ አብዮት ከተጠያቂነት አያመልጥም፤ ለሚደርሰውም ጥፋት ግንባር ቀደም ተጠያቂ እንደሚሆን ሊታወቅ ይገባል፡፡ ማሕበራዊ አብዮቱ መከሰቱ አይቀሬ ከሆነ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የደኅንነት ተቋማት ከሕዝቡ ጋር በመሆኑ ሒደቱን ከግብ ለማድረስ ከወዲሁ ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ሊከሠት የሚችለው ማሕበራዊ አብዮት፣ የኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካ ኢኮኖሚ የተሸከመውን ሥርዓት አራግፎ፣ በተራማጅ ማኅበራዊ ሥርዓት የሚተካ ነው የሚሆነው። በምትኩም አዲስ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ሥርዓት ነው የሚፈጥረው። ይኽውም የማሕበራዊ አብዮት ጥያቄ፣ የመንግስት ሥልጣን ጥያቄ በመሆኑ ነው። ለዚህም ነው፣ ማሕበራዊ አብዮት ከመፈንቅለ መንግስት የሚለየው። አሁን እየተከናወነ ያለው ‘ጥልቅ ተሃድሶው’ በመገለጫው፤ የፓርቲና የመንግስት ሰዎችን በሌላ መተካትና  በብዙሃን ዋጋ የጥቂት ኪራይ ሰብሳቢ ኃይሎችን ፍላጐት ይዞ ከማስቀጠል የዘለለ መሠረታዊ ለውጥ እስካላመጣ ድረስ የማኅበራዊ አብዮቱ መከሰት የጊዜ ጉዳይ ብቻ ነው የሚሆነው።

ከላይ የሰፈሩት ሁኔታዎች ከመከሰታቸው በፊት፣ ገዢው ፓርቲ እራሱን ሊያርም የሚችልበት እድሎች በጣም ሰፊ ናቸው።በመሰረታዊነት ግን፣ በፓርቲው ውስጣዊ ትግል ኪራይ ሰብሳቢው የፖለቲካ አመራር በተራማጅ ኃይሎች ሳይውል ሳያድር መተካት አለበት። ተራማጅ ኃይሎች እነማን ናቸው? ሕዝባዊ ወገንተኝነት ያላቸው፣ ሕዝብን ለማገልገል የተሰጡ፣ የጋራ ብልፅግናን የሚሹ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ፍትህን የሚደግፉ እና ለዚህም መሳካት ቁርጠኛ የሆኑ ናቸው። ከማሕፀን ኪራይ እስከ ሕዝባዊ ቁስ ኪራይ ሰብሳቢነት ኔትዎርክ ውስጥ የሌሉ ኃይሎች ናቸው። እነዚህን ሕዝቡ አጥብቆ ይሻል። “ለምጣዱ ሲባል፣ አይጧ ትለፍ” የሚለው ብሂል፣ ኪራይ ሰብሳቢ አመራሮችን ለመሸከም ከዋለ ምጣዱን መስበር ተገቢነቱ ምትክ አልባ ነው።

ምንጭ፦- ሰንደቅ