ብሔርተኝነት አዳላጭ መንገድና አደገኛ ድጥ ነው – በገነት ዓለሙ

 

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት በሕግ መንግሥት ጉባዔ የፀደቀበት ኅዳር 29 ቀን 2009 ዓ.ም. ዘንድሮም የተከበረው ሕገ መንግሥቱ ከፀደቀበትም (ኅዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም.)፣ ‹‹ሙሉ በሙሉ በሥራ ላይ ውሏል›› ከተባለበትም ከነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም ‹‹ተገንጥሎ›› አሥራ አንደኛው የብሔር ብሔረሰቦች ክብረ በዓል ተብሎ ነው፡፡ ቁጥሩም ሆነ ስያሜው ያስገርማል፡፡ ልክ የዛሬ 22 ዓመት የተመዘገበን ድል ይኼን ያህል ዓመት ሆነው ብሎ ሥሌት ሳይሆን ተራ ቁጥር ለመናገር፣ ዘግይቶ መከበር መጀመሩም ሆነ ከጊዜ በኋላ አዲስ ስያሜ የተሰጠው መሆኑ በጭራሽ ምክንያት አይሆንም፡፡

በኢትዮጵያ የብሔር/ብሔረሰቦች መብት መከበርም አማራጭ የሌለው ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የአንድነት መነሻና መሠረትም ነው፡፡ የብሔር/ብሔረሰቦች ጥያቄም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አጠቃላይ የዴሞክራሲ ጥያቄ አካል እንጂ በተገላቢጦሽ የሁሉ ነገር መፍቻ አይደለም፡፡ ሕገ መንግሥቱ የፀደቀበትን ቀን የብሔር/ብሔረሰቦች ቀን ተብሎ የሚከበረው፣ ዛሬም ከሃያ ሁለት ዓመታት በኋላ ከዚያ በፊት አሥራ ሰባት ዓመት ሙሉ በበረሃ ትግል ውስጥ ሲባል እንደነበረው በኢትዮጵያ ዋናው ቅራኔ ወይም ጥያቄ የብሔር ብሔረሰቦች ነው ተብሎ ከሆነ አሁንም ገና አልገባንም፣ ‹‹መከራ›› አልመከረንም ማለት ነው፡፡

ከዚህ ቀደም የዛሬዎቹ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶቸ ገና ተራ በተራ እንደተመሠረቱ በተለይም ሕወሓት ዋናው ቅራኔ (ጥያቄ) የብሔር ነው አሉ፡፡ ከዚህ ያልተስተካከለ አተያይ ወጥተው የሁሉም ብሔረሰቦች የትግል አስኳል ዴሞክራሲያዊ ነፃነት፣ ፍትሕና ከድህነት መውጣት መሆኑን ለማየትና በእነዚሁ የጋራ ጥቅሞች ላይ ትኩረቱን ለማደላደል የበቃ ድርጅት ሳይፈጠር ቀረ፡፡ የኢሕአዴግ ዋናው አባልና መሥራች ድርጅት የቀድሞው ወይም የመጀመርያው ክልል ገብ ዕይታውና አደረጃጀቱ፣ በኋላ ከመጣው ባለ ብዙ ብሔረሰቧን ኢትዮጵያን ‹‹ነፃ ከማውጣት›› ፍላጎትና አጋጣሚ ጋር ግጭት በፈጠረ ጊዜም፣ አገራዊ የአተያይና የጥንቅር ለውጥ (ትራንስፎርሜሽን) በማድረግ (ለምሳሌ ከዴሞክራሲያዊ ቡድኖች ጋር ኅብረት በመፍጠር በየአካባቢው ነፃ የሕዝብ እንቅስቃሴዎችን በማነሳሳትና ከእነዚሁ ጋር በመሸራረብ) ችግሩን ለማቃለል አልጣረም፡፡ ይልቁንም ጥበታቸውንና ባይተዋርነታቸውን መጋረድ ብቻ ሞከረ፡፡

ሕወሓት በተለይ የኢትዮጵያን ሌሎች ብሔረሰቦች ያቀረበው ያንኑ የትግራይ ነጠላ መንግሥት ለማቆም ይሆነኛል ብሎ የያዘውን የብሔር ጥያቄ ቁንጮነት ተሸክሞ ነበር፡፡ ዋናው ጩኸቱና መፈክሩም ‹‹የአማራው የበላይነት፣ የብሔረሰቦች እስረኝነትና ሙሉ ለሙሉ መብት እስከ መገንጠል›› ሆነ፡፡ በዚህ ጩኸቱና መፈክሩም በኢትዮጵያ ሕዝብ በዋናው የዴሞክራሲ ጥያቄ ላይ ጥላ አጥልቶ፣ በፀረ ዴሞክራሲያዊ ውዥንብር የሕዝብን ፀረ ደርግ ትግል ሊያስጠቃና በገዛ ራሱ ላይም ‹‹አገር የማፍረስ›› ክስ ሲጎትት ኖረ፡፡ ክሱ እየበረታ ሲወጥረው ‹‹የብሔሮች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት መረጋገጥ አንድነትን እንጂ መነጣጠልን አያመጣም፣ በመፈቃቀድ…›› ወዘተ የሚል ትንተና አምጥቶ፣ አብሮ መኖርንና መለየትን ነባራዊ አስገዳጅነት የሌለበት የቢሻኝ ውሳኔ ብቻ እያስመሰለ የበለጠ ግራ አጋባ፡፡

የብሔሮች መብት የዴሞክራሲ መብቶች አንድ ጣት እንጂ ሁለመናው አይደለም፡፡ ብቻውን ስለሰቀሉትና ‹‹እስከ መገንጠል!›› እያሉ ስለለፈፉትም የአንድነት ዋስትና አይሆንም፡፡ አስተማማኝ አንድነት በዴሞክራሲያዊ ትስስር የሚዘማመድና ዕድገትን በመመገብ የሚጠና ነው፡፡ ለፀረ አንድነት ውንጀላም ማርከሻውስ ነጋ ጠባ መማልና መገዘት ሳይሆን ግንዱን ዘንግቶ ብቃይ ላይ ከማተኮር መላቀቅ፣ ከብሔርና ከጎጥ ጎጆ ወጥቶ የሕዝቦችን መሠረታዊ የጋራ ጥቅሞች ፊት ለፊት ደቅኖ የማሳየትና ሰፊ የትግል ትስስር እንዲፈጠር መሥራት ነው፡፡

የኢሕአዴግ መሥራች አባል ድርጅት የሆነው ሕወሓት ይኼንን ተግባር (በኅብረ ብሔር ፓርቲም ሆነ በግንባር አቅጣጫ) ሊወጣ ይቅርና በአቋም ሙሉ አምሳያው ከሆነው ኢሕዲን ጋር እንኳን ሊዋሀድ አልሞከረም፡፡ ኋላ ላይ እንደታየውና ዛሬም አደባባይ በወጣ ሹክሹክታና ሚሥጥር እንደሚወገዘው ‹‹የሚሰግርባቸው በቅሎ ድርጅቶች›› ከመፍጠር ያለፈ እንቅስቃሴ ማምጣት አልቻለም፡፡

ኢሕአዴግ ሥልጣን ከያዘ በኋላም የኢትዮጵያ የችግሮች ሁሉ የበላይና የዴሞክራሲ ሁለመና የብሔሮች ጥያቄ ሆኖ አረፈው፡፡ የብሔር ብሔረሰብ ትንንሽ ፓርቲዎች ረቡ የብሔር ብሔረሰብ ውክልና ገና ከመነሻው በሕዝብ ድጋፍ የማይመዘን የራስ በራስ ሹመት ሆነ፡፡ የአማራ ሕዝብ ጥቅም ውክልና የኢሕዲን/ብአዴን፣ የትግራይ ሕዝብ የሕወሓት፣ የኦሮሞ የኦሕዲድ፣ የደቡብ ሕዝቦች የደሕዴግ፣ ወዘተ እያለ ቀጠለ ኢሕአዴጋዊ ያልሆነ ሌላ አለሁ ባይ ሕዝብን የማይወክል የጥቂቶች ጥርቅም ተባለ፡፡

ከፖለቲካ እስከ ትዳር ትክክል የሚባለው አተያይና አቦዳደን ብሔረሰባዊ ሆነ፡፡ ከተወራረሰ ገጽታ ይልቅ ልዩ ወይም የብቻ የሆኑ መለያዎችን መፈለግና ማጉላት ሚዛን ደፋ፡፡ የብሔር/ብሔረሰብ ማንነት በሆነ ማኅበረሰብ ባህልና ቋንቋ በመቀረፅ የሚገለጽ ከመሆን አልፎ የትውልድ ጀርባን መርመሮ የጠራና ያልጠራ እስከ መለየት ደረስ ፈር ለቀቀ፡፡ በተለያየ ደረጃ የሚታይ የማኅበራዊ ቅልቅሎች ገጽታን እንደ በጎና ተፈጥሮአዊ እውነት የመቀበልና የማክበር ችግር በረከተ፡፡ በተዋሳኝ ብሔረሰቦች ዘንድ ያለ ጉራማይሌ ማኅበራዊ ጥንቅር በተለይ በከተሞች ዘንድ ያለ ከአማርኛ ተናጋሪነት ጋር የተሳሰረ ውጥንቅጥ ስብስብ፣ በብሔርተኞች ዘንድ እንዳልተፈለገ ዕድገትና ችግር ተቆጠረ፡፡ ብሔረሰባዊ መካለስ ወይም መሰባጠር የሚታይባቸውና በአዲሱ አከላለል የተቆረጡ ማኅበረሰቦች፣ በብሔርተኞች ጥንቅር የማጥራት ወይም እውነተኛ ብሔራዊ ባህልና ቋንቋን የማስፋፋት እንቅስቃሴ መረበሽ ግድ ሆነባቸው፡፡ ጉራማይሌ ባህልና አነጋገር፣ ከሌላ ብሔር ጋር መጋባትና መዋለድ ‹‹የሚያስንቅ›› ሲሆን ታየ፡፡ እንዲህ ያለውን ‹‹የማይፈለግ ገጽታ›› የሚያደክም የባህል ‹ዘመቻ›› ተከፈተ፡፡ ብሔርተኛ ንቃቱ ተዛመተ፡፡ በመኖሪያም በሥራ ቦታም ብሔራዊ ማንነትን መለየትና መምረጥ ግድ ሆነ፡፡ የራስንና የልጆችን መጠሪያ መቀየርና የሌላ ብሔር የትዳርን ጓደኛን መፍታት ድረስ ሄዷል የተባለ ቀውስ ተከሰተ፡፡ ‹ብሔር የለኝም ኢትዮጵያዊ ነኝ› ያለ (ከተለያየ ብሔር በመወለዱ ምክንያት የተቸገረው፣ የብሔር ፖለቲካን መቃወም የፈለገውና የብዙ ብሔሮችን እውነትነት በ‹‹አንድ ሕዝብ›› ምኞት የተካው ሁሉ ተደምሮ) ‹‹የብሔሮችን መብት የሚፃረር ትምክህተኛ›› ተደርጎ ተመደበ፡፡ በአንዱ ወይም በሌላው ብሔር ውስጥ ራስን አለመመደብም ሆነ ብሔርተኛ አለመሆን መብት መሆኑም ተዘነጋ፡፡

በብሔር ቡድን ውስጥ መግባት ያልፈቀደና የብሔር ጉዳይን እንደ ሃይማኖት ያላጠበቀ፣ በብሔር ማንነቱ የሚያፍር ተደርጎ ተወሰደ፡፡ ብሔሩን ሲጠየቅ ይቆጣ የነበረውን ለማለዘብ አማራውንና ከአማራና ከሌላ ብሔር የተወለደውን ‹‹ውህድ›› በአማራ ብሔርተኝነት ሠልፍ ውስጥ ለማስገባት ያለመ (አንዳርጋቸው ጽጌ 1985 ዓ.ም.) መጽሐፍም ተጻፈ፡፡ ከውስን ታሪካዊ መረጃ ጋር አፈታሪኩን እያዛመደና እያሳደደ አኩሪ የብሔር ታሪክ የማሰናዳት ጥድፊያም ተያዘ፡፡ የከዚህ ቀደሙ ያለ የሌለ ግፍ ተቆጠረ፡፡ ተራ ፌዝና ብሽሽቁም እየተለቃቀመ የበደል ማስረጃና የሕዝብ ስሜት ማደፍረሻ ሆነ፡፡

የብሔርተኛነት እንቅስቃሴ አመጣጥ ከከበርቴው መደብ ጋር የተያያዘ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ይህ ዕድገት በመጓደሉ ብሔርተኛ ንቅናቄው የታየው ዘግይቶ ከፀረ ቅኝ አገዛዝ ንቅናቄዎችና ከሶሻሊስት እንቅስቃሴ መስፋፋት ጋር ተያይዞ መሆኑን መገንዘብ ችግር ሆነና አፄ ቴድሮስም የአማራ ብሔራዊ መንግሥትና ክልል ባለመፍጠር (ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፍ ገጽ 35-7) ተተቹ፡፡

ሁሉንም ብሔርተኛ ማድረግ አጠቃላይ ሥልት ሆነ፡፡ የብሔር ጭቆና የሌለበት አማራውም ሳይቀር በግድ ብሔርተኛ ካልሆንክ፣ ‹‹ብሔር ብሔር›› ካላልክ ኢትዮጵያዊነትህን እስካጠበቅህ ድረስ ለሌላው አደጋ ነህ ተብሎ ተወጠረ፡፡ ብሔርተኛ አለመሆን ከ‹‹ምርጥ ኢትዮጵያዊነት›› ጋር ተምታታ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔሮች የሚያያይዛቸው መፈቃቀድ መሆኑ ሲሰበክ፣ የዚህ የመፈቃቀድ አንድ ትልቅ ጉዳይ ከእርስ በእርስ ትርምስ አምልጦ የማደግ ጥቅም መሆኑ ነጥሮ ሳይወጣ ቀረ፡፡ መፈቃቀዱ የዘፈቀደ ምርጫ እስኪመስል ድረስ አንዱ ለማኝ፣ ሌላው ተለማኝና እወጣለሁ እያለ አስፈራሪ ወይም ለሌላው ሲል የሚቆይ እስኪመስል ድረስ የመፈቃቀድ አመለካከት ተምታታ፡፡ በመነጠልም ሆነ በአንድነት ጥቅምና ጉዳት ላይ ሕዝብ ያለው በግልጽ የመወያየት መብት ነውር ይመስል ታፍኖ ታለፈ፡፡

ከሕገ መንግሥቱ በፊት (በጥር 1984 ዓ.ም.) የክልሎችን ዳር ድንበር የሚወስን መስተዳድሮችን የሚያቋቁም አዋጅ ወጣ፡፡ አከላለሉ ላይ መለስተኛ ለውጥ ያደረገው ሕገ መንግሥት ፀደቀና የኢሕአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶችም ‹‹በዴሞክራሲያዊ አግባብ›› ተመርተው ‹‹በየርስታቸው› መንግሥታት ሆኑ፡፡ በቋንቋ መተዳደር፣ መዳኘት፣ መማርና መጻፍ ይብዛም ይነስ ተቻለ፡፡ ኢሕአዴግ አለኝ የሚለው አኩሪ ለውጥ ይኼው ብቻ ሆነ፡፡

ከዚህ በተረፈ ‹‹ቅድሚያ ለአካባቢው ብሔር ተወላጅ›› ‹‹የብሔራዊ ተዋጽኦን ማመጣጠን›› ይፋ ፖሊሲ ሲሆን ጎሰኝነትም ቀናው፡፡ ተዛነፉ የአካባቢው ብሔር አባላት ልዩ መብት ባለማግኘታቸው የመጣ ይመስላል፡፡ ተዛነፉም በ‹‹በጎ አድልኦ›› ይወገድ ይመስል ‹‹መጤ›› ወይም አናሳ የማኅበረሰብ አባላት በውስጥና በውጭ የትምህርትና የሥልጠና ውድድር፣ በሥራ ቅጥር፣ በዕድገትና በሹመት ላይ የሚንገዋለሉበት አሠራር መጣ፡፡ ውጤትና ብቃት ዋና መመዘኛ ከመሆን ወጣ፡፡ ‹‹በጎ አድልኦው›› ተዛነፍን በማስተካከል ዓላማ ይጀመር እንጂ፣ ያለፈ በዳይነትንና አድሏዊነትን በዛሬ ተራ የማወራረድ ውስጣዊ ግፊት ነበረው፡፡ ግፊቱ እየተሠራጨ በኢንቨስትመንት ፈቃድ፣ በመሬት አሰጣጥ፣ በግብር አተማመን ውስጥ ሳይቀር ገባ፡፡ በሕግ የተፈቀደ ‹‹ማበረታቻ›› ይመስል አሠራሩ ተስፋፋ፡፡ ሌላው ቀርቶ በዕለታዊ ግጭቶች የወንጀልና የፍትሕ ብሔር ክሶች ቅኝትና አፈታት ከብሔር ተወላጅነት ጋር ይናብብ ገባ፡፡ በአንድ ብሔረሰብ ውስጥ ሳይቀር በጎሳ ደረጃ መፈላለግና መወጋገን አዋቂነት እየሆነ መጣ፡፡

ከአንድ ብሔረሰብ በላይ ባቀፉ የአስተዳደር አካባቢዎች በብሔራዊ መብት/ድርሻ ሽፋን የሥልጣን፣ የበጀት፣ የዕርዳታ እህል፣ የግዛት ድርሻ ሥሌቱና የጥቅም ማስፊያ ዱለታውና ፍትጊያው ከክልል እስከ ወረዳ ተስፋፋ፡፡ በሒደቱ ጥቂት ብልጣ ብልጦች ሲከብሩና የመክበሪያ መንገዳቸውን ሲያመቻቹ ለብዙኃኑ ግን ትርፉ በመጠቀሚያነት መታመስ፣ መሸካከርና በፀብ መደራረስ ሆነ፡፡

ከከብት አርቢው ተነቃናቂነት ጋር ያልተጣጣመው የውኃና የግጦሽ የክልል ይዞታነት የብሔርተኞች ቅስቀሳ ተጨምሮበት ተጎራባች ማኅበረሰቦችን ማጋጨቱ ጨመረ፡፡ እያንዳንዷን ነገር በጎሰኛ ዓይን ማየትና መመዘን ተስፋፋ፡፡ ከእኔ ብሔር፣ ከእኔ ጎሳ ምን ያህል ተሾመ? የተመደበው ወይም የተሾመው ወይም የተመረጠው ወይም የወረደው ብሔሩ ከየት ነው? በሬዲዮና በቴሌቬዥን መግለጫ የሚሰጠው ከየት ብሔር ይመስላል? በፀቡ የተመታው ማነው?  መቺውስ?  ወዘተ እያሉ የግል ግጭቶችን ጭምር በብሔረሰባዊ ጥቃት እስከ መጠርጠር ድረስ አዕምሮ ተጠመደ፡፡ የሌላ ብሔር አባል ወይም ለአካባቢው አዲስ የሆነ ሰው ግንባታ ሲያካሂድ ሲያዩ፣ ሌላው ቀርቶ ካርታ አንሺ የአፈርና የዕፅዋት ተመራማሪ ሲያዩ መሬቴ፣ ማዕድኔ እያሉ በስስት ማለቅ ተበራከተ፡፡ ይኼንን በመሰሉ ለዕድገትም፣ ለሰላምም፣ ለዴሞክራሲም እንቅፋት በሆኑ ችግሮች ተተብትበናል፡፡ የዚህ ሁሉ አድራጊ ፈጣሪ በሁለት ሠፈሮች ከትሞ ተምሬያለሁ፣ ፖለቲከኛ ወይም ታጋይ ነኝ ባዩ ክፍል ነው፡፡

በአንድ በኩል የጎሰኛ አበጣባጭነትና የአስተዳደር ጥፋቶች በሚያስከትሏቸው ብልሽቶች ተጎትተው የገቡ ብዙ የዴሞክራሲ ናፋቂዎች የዘቀጡበት፣ ድፍን ‹‹ኢትዮጵያዊነትን›› ብቻ መስማት የሚፈለግበት ሠፈር አለ፡፡ በዚህ ሠፈር ውስጥ ኢትዮጵያን በአምላክ የተመረጠች አገር አድርጎ የሚያስበው ‹‹ብሔሮች››፣ ‹‹ሕዝቦች›› የሚሉ ቃላት መስማት እንኳን የሚያቅረው፣ በቋንቋ መማርና መተዳደር ከመበታተን አደጋ ጋር የሚምታታበት ሁሉ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል የብሔርተኝነት ሠፈር አለ፡፡ በዚህ ውስጥ ከኢሕአዴግ የብሔር ድርጅቶች አንስቶ አንዱን ወይም ሌላውን አካባቢ ለመቁረስ እስከሚታገሉት ድረስ ተሠልፈዋል፡፡ ባልንጀራነትን የግድ በብሔር ማንነት ሳይሆን በግለሰባዊ ማንነት ለመመዘን የሚጥረውና በጎሰኝነት ጉድጓድ ውስጥ ላለመውደቅ የሚፍጨረጨረው ‹‹በብሔሩ የሚያፍር፣ ብሔሩን የሚክድ›› እየተባለ ይጎነተላል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ፣ ሕዝቦች (አገሮች) ቅኝ የተገዙባት ኢምፓየር ነች›› እየተባለ የሻዕቢያ ዓይነት ሐሰትና ቅጥፈት ይበዛታል፡፡

ሁለቱም ሠፈሮች የኢሕአዴግንና የአጋሮቹን የአገዛዝ ችግሮች (የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይባላል በህዳሴው ቋንቋ) እየተመገቡ እርስ በእርስም እየተመጋገቡ ሲስፋፉ ኖረዋል፡፡ ሁለቱም ለየብቻቸው የምለው ምን ይፈይዳል?  ምን ይጎዳል?  የሚል የኃላፊነት ጥያቄ ሳያሸማቅቃቸው በነፃ ይራመዳሉ፣ ይንቀሳቀሳሉ፡፡

መገንጠልን የትግል ግብ አድርጎና በልዩ ልዩ የፈጠራ ታሪክ ደጋግፎ ለማሳካት መታገል ምን ያህል ትርጉም የለሽ ሊሆን እንደሚችል የኤርትራ ትግል አስተምሮናል፡፡ በኤርትራ ያሉ ሕዝቦች ያ ሁሉ የሰላሳ ዓመት ደም ፈስሶ ዴሞክራሲና ፍትሕ ሊያገኙ ይቅርና ከጦርነት እንኳን የመገላገል ዕድልን ሻዕቢያ አልፈቀደላቸውም፡፡ እርግጥ ነው ዛሬ የኤርትራ ሕዝቦች በ‹‹ፀረ ቅኝ የነፃነት ትግል›› የሚምታቱበትና የሚወናበዱባት ሁኔታ የለም፡፡ ለቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብም የኤርትራ ትግል ማስፈራሪያና የገዢዎች መነገጃ ሲሆን የኖረበት ታሪክ አክትሟል፡፡ በዚህ ረገድ ዛሬ ሁለቱም እውነቱን ለመረዳት ችለዋል፡፡ ሻዕቢያ መንገድ የሳተና በደም የነገደ መሆኑ ወለል ብሎ ታይቷል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ኤርትራን ቅኝ ገዛች›› ባይነቱም ሐሰተኛነቱ ተጋልጧል፡፡ ያውም ‹‹ኢትዮጵያ የኤርትራ ቅኝ ሆነች›› የሚል ተቃራኒውን ፈጥሮ፡፡

የኤርትራ የነፃነት ትግል ማስፈራሪያነት ከኪሳራ ጋር ቢያከትምም ሻዕቢያ ኢትዮጵያን (ኤርትራንም) የማጥፋት ተግባሩን አላቆመም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦችም ከመገንጠልና ድንበር ከማስከበር ጣጣ ጋር ከመጓተት አልተላቀቁም፡፡ በኦሮሞ ብሔርተኛነት ውስጥ የሚታይ የ‹‹ሐበሻ ቅኝ ገዢነትና ኢምፓየር››ን እታገላለሁ ባይነት የሻዕቢያን የድሮ ቦታ ተረክቧል፡፡ የኢሳያስ መንግሥትም ኢትዮጵያን የማፍረስ መሣሪያ አድርጎ እየተገለገለበት ነው፡፡

ከኢትዮጵያ የተላቀቀች ነፃ ኦሮሚያን የሚሹ ብሔርተኞች የሚሉትንስ ያውቁ ይሆን? በመጀመርያ አድልኦንና በደልን በጋራ የመታገል ሥልት ገዢዎች ከሕዝብ የሚነጠሉበት መሆኑን፣ በዚህ ፋንታ መገንጠልን የመምረጥ አካሄድ ደግሞ ‹‹እናት አገር ወይም ሞት›› በሚል ዓይነት መፈክር ሥር ብዙ ደጋፊ አሠልፎ አንዱን በሌላው እያጣፉ ለመኖር የሚመች መሆኑን፣ ወደ ሌላ አገር ሳንሄድ የኤርትራ ትግል ልምድ ደንበኛ ትምህርት ሰጥቶናል፡፡

በሌላ በኩል የኦሮሞ ሕዝብ ጉዳይ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ፣ ከደቡብ እስከ ሰሜን የተዘረጋና ከብዙ ብሔረሰቦች ጋር የተሳሰረ የአጠቃላይ ኢትዮጵያ ጉዳይ እንደመሆኑ፣ የመነጠል ጥያቄ ብዙ ብሔሮችን ያደራረሰ መተላለቅ ሊከተልበት የሚችል፣ ኢትዮጵያን ከኢትዮጵያ ልነጥል ከማለት ብዙም አለማነሱን ለመረዳት ጥልቅ ምርምር አይጠይቅም፡፡ ከየትኛውም የአገሪቱ ብሔር ይበልጥ ሰፊ መልክዓ ምድራዊ ሥርጭትና የቁጥር ብዛት ያለው ሕዝብ፣ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ተባብሮ የብዙኃን ዴሞክራሲን ሊያሰፍን የሚችልበትን የተሻለ የትግል አማራጭ መሸሽስ በምን መከራከሪያ ትክክል ይባላል? የተፈለገው ሥልጣን ከሆነ ከመነጠል መንገድ ይልቅ ለዴሞክራሲ ተጋግዞ መታገሉ የበለጠ ይቀላል፡፡

ሻዕቢያ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ ሥነ ልቦና ባህል ያለው አንድ የኤርትራ ብሔር፣ አንድ ሕዝብ ተፈጥሯል የሚል ሐሰት ሲያመልክ እንደነበር ሁሉ፣ ሐበሻነት ኦሮሞን የማይጠቅስ አድርገው የሚያስቡና በኦሮሞና ‹‹ሐበሾች›› (ትግሬ፣ አማራ፣ አገው) መካከል የባህል የሥነ ልቦና ተዛማጅነት የሌለበት መስመር ሊያበጁ የሚሞክሩ፣ የኦሮሞን ወይም የሌላውን ብሔር ብሔረሰብ ሕዝብ ታሪክ ከአጠቃላይ ኢትዮጵያ ታሪክ ለመነጠል የሚለፉ፣ የየጁ መሳፍንት ኦሮሞነት ለማጥፋት ላጲስ የቸገራቸውና ሌላው ቀርቶ የጥቁር ሕዝብ መኩሪያ የሆነውን የአድዋ ድል ላለመቀበል የሚንፈራፈሩ የኦሮሞ ብሔርተኞች አሉ፡፡

ኢትዮጵያ በመሠረቱ ኦሮሞአዊ ልትባል የምትችል አገር ሆና ሳለ በኦሮሞ ፖለቲከኞች አካባቢ የመነጠል ጠባብ ዕይታ ብዙ ዕድሜ ማግኘቱ፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ትግል እምብርት የመሆንና ረዥሙን ኦሮሞአዊ ሒደት በዘመናዊና በሠለጠነ መንገድ ዳር የማድረስ ኃላፊነትን ለመውሰድ አለመቻሉ አሳዛኝ ትራጀዲ ነው፡፡ የዛሬውን እውነት ትተው የምኒልክን ዘመቻዎች፣ የኦሮሞን ሕዝብ የጭሰኝነትና የክርስቲያንነት ታሪክ እያብሰለሰሉ ደረት ሲመቱና ሲቃጠሉ የሚውሉ፣ ከናካቴውም ከጥንት ከጠዋቱ እንደገና ታሪክ ‹‹ሀ›› ብሎ ለመጀመር የሚቃዡም አሉ፡፡

በሕዝብ ላይ የደረሰን ያለፈም ይሁን የቅርብ ጉዳት እየነካኩ መጨስና ማጫጫስ፣ እንዲያም ሲል የትናንትን ጉዳት በዛሬዎቹ ላይ የማወራረድ ዝንባሌ ሕዝብን ወደ ማፋጀት ከመምራት በስተቀር ለዕድገት አንዲት ጠብታ እንደማያዋጣ ታይቷል፡፡ በደም የጨቀየ ታሪክ ዓለማችን የተገነባችበት ሆኖ እያለ በኢትዮጵያ ልዩ ነገር የተፈጸመ አስመስሎ ማላዘን አጥፊ ነው፡፡ በሚዛናዊ አዕምሮ የኢትዮጵያን ታሪክ ለመገንዘብ የሚሞክር ሰው በደቡብ ሕዝቦች ላይ የደረሱት ቅጣቶች (ቃጠሎዎች፣ ዘረፋዎች፣ ጭፍጨፋዎች፣ በባርነት የመነዳት፣ የሰለባና የፉነና ድርጊቶች . . . ) ለ‹‹ባዕድ›› ሕዝብ ታስበው የተፈጸሙ እንዳልነበሩ በሰሜኑም ሕዝብ ላይ (ያውም ለረዥም ጊዜ) ሲፈጸሙ እንደነበሩ ማስተዋል አይቸግረውም፡፡ በ1770 (እ.ኤ.አ) ጎንደር የደረሰው ጀምስ ብሩስ እንደመሰከረው የጦር ምርኮኛን መስለብ፣ የዓይን መጎልጎል፣ ጆሮን አፍንጫን እጆችን ወይም እግሮችን መቁረጥና የመሳሰሉት ቅጣቶች የማንኛውም ሰው ፍርኃትና የማንኛው ውጊያ ውጤት ነበሩ፡፡

ከምኒሊክ ዘመቻዎች ጋር ተያይዞ በደቡብ የታየው የመሬት ንጥቂያም በሥረ መሠረቱ የጦርነት ውጤት፣ የቅጣትና የምርኮ አንድ መገለጫ ነበር፡፡ ምኒልክን የተዋጉት (እምቢ ያሉት) አርሲ፣ ሐረር፣ ወላይታ ከሌሎች ቅጣቶች ሌላ የመሬት መነጠቅ ሲደርስባቸው ‹‹በሰላም›› እጅ የሰጡት ግዣቶች ግን ከዝርፊያ ድነው ዓመታዊ ግብር እየከፈሉ እንደ ቀድሟቸው እንዲተዳደሩት ትተው የነበሩት ለዚሁ ነበር፡፡

በአጠቃላይ የገባርነት ሥርዓት ከሰሜን ወደ ደቡብ የመሻጋገር ሒደት ውስጥ በሰሜን ያልነበረ የጭሰኝነት ሥርዓት በደቡብ መምጣትም፣ በዘመቻዎች አሸናፊ የነበሩት የነፍጠኛ ኃይሎች በራሳቸው ሊሠሩበት ከሚችሉት እጅግ የበዛ የመሬት ምርኮ የመገኘት ዕድል ሁኔታ የጎተተው ነው፡፡ ይህ አዲስ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን መለስ ካለ በኋላ ግን መቆሚያ አልነበረውም፡፡ የደቡብ ሕዝቦች በልዩ ልዩ መልክ መሬታቸውን እየተነጠቁ አጠቃላይ ምርኮ መውደቅ እስኪመስል ድረስ ለጭሰኝነት ሰቆቃ ተዳርገዋል፡፡

ይኼንን እውነት አጠንክሮ ለማሳየት የደቡብ ሕዝቦች ባርነት ገቡ፣ ሁለተኛ ዜጋ ሆኑ ብሎ ማለት አያስከፋም፡፡ ከዚህ ርቆ ወጥቶ በሰሜኑ ሕዝብና በደቡብ መሀል የነፃ (ምርጥ) ሕዝብና የምርኮኛ (ገባር) ሕዝብ የመሆን ልዩነት ለመሥራት መሞከር ስህተት ላይ ይጥላል፡፡

ሁሉንም ሕዝቦች አንቆ የነበረውን አጠቃላይ የሥርዓቱን የአስገባሪነት የጋራ ባህርይ ከማየት ያደናቅፋል፡፡ በደቡብ ተደራጅቶ የነበረው የከፋ ምዝበራና ጭቆና ይነስም ይብዛ፣ ነባርና አዲስ የተፈለቀቁ የደቡብ ገዢዎችን ያካተት እንደበረ ከማየትም ይከለክላል፡፡ ለማንኛውም ግን በየትኛውም በቂም ሆነ በቂ ባልሆነ፣ ስም ያለውም ይሁን የሌለው ምክንያት ተነሳ ብሔርተኛነት አዳላጭ መንገድና አደገኛ ድጥ ነው፡፡ ላስረዳ፡፡

በኢትዮጵያችን ውስጥ ብሔርተኝነት በ‹‹ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት›› ስም ተሹሞ በስፋት የሚገኝ እንደመሆኑ አዳላጭነቱን ጠጋ ብሎ ማየት ጠቃሚ ነው

በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካው ዕቅዶች የብዙ ሰዎችን ጥቅም አቀራርቦ መያዝና ብዙዎችን ለመሳብ መብቃት ከባድ ሥራ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ሲተያይ በብሔርተኝነት ተቧድኖ ድጋፍ መፈለግ ከሁሉም የቀለለ ነው፡፡ የፖለቲካ ትግል ልምምድ ትንሽም የሌላቸው፣ ይኼ ይቅርና የፖለቲካ ንድፈ ሐሳባዊ አስተሳሰብ ያላበጁ ሰዎች ፕሮግራም ልትባል የማትችል ወረቀት አዘጋጅተው፣ ብሔርተኛ ብሶትን እያንጎራጎሩ የብሔር ድርጅት ነኝ ሲሉ አጋጥሞኛል፡፡ የብሔርተኛ መንገድ የሚጋጩ አስተሳሰቦች ያላቸውን ሰዎች፣ ዴሞክራቶችንና ፀረ ዴሞክራቶችን፣ ፋሽስታዊ ዝንባሌ ያላቸውን ጭምር በብሔር ተቆርቋሪነታቸው ብቻ አብረው መንጋፈፍ እንዲችሉ የተመቸ ነው፡፡ ብሔርተኛ አስተሳሰብና አደረጃጀት በተዘረጋበት ሥርዓት ውስጥ ምርጫ ቢካሄድም፣ መራጩ ሕዝብ ፓርቲዎችን ባላቸው ፕሮግራም ከማማረጥ ፈንታ ባመዛኙ ብሔር ብሔረሰቡን ‹‹ይወክላል›› ለተባለ ቡድን ዕጩዎች ድምፁን የመስጠት ሁኔታ ውስጥ ይወድቃል፡፡

አመለካከቱ ሙሉ ለሙሉ በብሔርተኝነት ገደብ ውስጥ የገባ ሰው፣ ብሔሩን ከሌላ ብሔር ጋር በእኩል ዓይን ለማየትና ለመመዘን ይሳነዋል፡፡ የብሔሩን ወግና ባህል በሒስ ዓይን ከማየት ይልቅ እንደወረደ መካብ ያጠቃዋል፡፡ የብሔሩን ባለታሪኮች ጥሩ ሥራቸውን የማብዛትና ድክመታቸውን የመከለል (የማሳነስ) ፍላጎት ይስበዋል፡፡ የበላይ ከነበረ ብሔር ወይም ገዢ መደብ ጋር ብሔሩ የነበረውንና ያለውን ታሪክ በመረዳት ረገድም፣ በደልና ጥቃትን የማነፍነፍና ከዚያ አኳያ አዛብቶና አጡዞ የመተርጎም ፍላጎት የምልከታና የማሰብ ሚዛኑን እየታገለ ያስቸግረዋል፡፡ ብሔራችን ተበድሏል፣ እነዚህና እነዚህ አልተሟሉለትም የሚባለው ነገር ብዙ አየር እየተሞላ አንዳንዴም የትግሉ ሁለንተና ሆኖ፣ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር የሚያገናኙ ዓበይት ጥቅሞች እንዳይጤኑ ሊሸፍን የሚችለው ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ ከሌሎች ጋር ያለው የአብሮነት፣ የእኩልነትና የልማት ትግል ምልከታ ውስጥ ሳይገባ የሚካሄድ የድሮና የዘንደሮ የበደል ድርደራ ወደ ቅያሜ የሚያንሸራትት ድጥ አለው፡፡ ከትምክህት ወገኖች ጋር መተራረብ ታክሎበት በፈላ ስሜት መታወር ሊከተል ይችላል፡፡ በአገራችን ተሞክሮ መሰል ችግር እንግዳ አይደለም፡፡

የብሔር ብሔረሰብ ካባ መጎናፀፍ የብሔር ወገንተኝነትን ያጠበቀ ስሜታዊ ድጋፍ የሚገኝበት ጥሩ መደበቂያ መሆን ስለሚችል ሥልጣን ፈላጊዎችና ሙሰኞች ሽፋን አድርገው ይነግዱበታል፡፡ እነሱ የፈጠሩት ድርጅት የያዘውን አቋም የብሔር ብሔረሰቡ አቋም ያደርጉታል፡፡ ድክመታቸው ሲተችና በእነሱ ላይ የተወረወረውን ትችት ብሔር ብሔረሰባቸው ላይ እንደተወረወረ አድርገው ለማምታታት ይመቻቸዋል፡ ‹‹ድሮም… እየተባልክ ትዘለፍና ትናቅ ነበር ዛሬም ይኼው . . . ›› እያሉ ስሜት ውስጥ መክተት የተለመደ ዘዴያቸው ነው፡፡ ለማምታታትም ጠቅሟቸዋል፡፡ ምክንያቱም ብሔረተኛ ተቧድኖና እንቅስቃሴ የቡድን ማንነትና ፍላጎትን ከብሔር ብሔረሰብ ማንነትና ፍላጎት ነጥሎ በማየትና በመረዳት በኩል የበኩሉን አሳሳችነት ይፈጥራል፡፡ ብሔር ብሔረሰብን በደፈናው ሥራዬ ብሎ የሚያወግዝና የሚሳደብ የከተማ እብድ በኢትዮጵያ ሊታይ የቻለው (ከደርግ ውድቀት በኋላ) ከዚህ አሳሳችነት የተነሳ ነው፡፡

ለቅስቀሳ የሚውለው በደል ወይም ፖለቲካዊ ጉዳይ ሁሉንም ብሔር ብሔረሰብ የሚመለከት ሲሆን፣ እንኳን የሁላችንም ችግርና ጥቅም ነው ከማለት ይልቅ የብሔርተኛ ትግል የራሱን ብሔር ብቻ የሚመለከት አስመስሎ በተናጠል የመጮህ ፀባይ ያጠቃዋል፡፡ የፖለቲካ ጥያቄ የተናጠል ብሔርተኛ ጩኸት ሲሆን፣ ሌላው ወገን የራሱ ብሔርተኛ ንቅናቄ ወይም ሌላ የትግል አማራጭ ከሌለው በስተቀር ድርሻው ተመልካችነት ይሆናል፡፡ የብሔርተኛ ንቅናቄ በተፈጠረበት አካባቢ ያለ ውሁድ ኅብረተሰብ፣ በተለይ ገዢ የሚባለው ብሔር አባላት ምንም በደል ባይደርስባቸውም የብሔርተኛ እንቅስቃሴ መፈጠሩ ብቻውን ሥጋታቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ብሔረተኛ እንቅስቃሴው ክልላዊ ሥልጣን ሲይዝም ሥጋታቸው ይቀጥላል፡፡ ትምክህትም ሰለባውን ያበዛል፡፡ የብሔርተኛ ትግሉ ተገንጥሎ የመውጣትን ጥያቄ የጨመረ ከሆነ ደግሞ፣ መገንጠልን ከማይደግፍ ወገን ጋር በሞላ መቃረን ይፈጠራል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦች የትግል ኃይል ይከፋፈላል፡፡

የትኛውም ዓይነት የብሔር ብሔረሰብ ብሔረተኛነት በውስጤ ያለ ሀብትና ጥቅም ቅድሚያ ለብሔር ወገኔ ይሁን የማለት ቁልቁለት አብሮት ይኖራል፡፡ በዚህ ቁልቁለት ከተንደረደሩ ማረፊያው አድሎአዊነት ነው፡፡ እዚህ ውስጥ ከተወደቀ ከሌላው በበለጠ ለብሔር ብሔረሰብ ወገን መታመንና ከሌላው አብልጦ የብሔር ብሔረሰብ ወገንን ማቅረብና መጥቀም ይመጣል፡፡ ጥቅቅሞሹ በግልጽና በድብቅ መንገድ ወደ ልዩ ልዩ የሥራ መስክ፣ ወደ ትምህርት ምዘና፣ ወደ ኢንቨስትመንትና የመሬት ምሪት ሊሻገር፣ የፖሊስና የዳኝነት ሥራን ሊበክል ይችላል፡፡ ሲበክልም ታይቷል፡፡ የአድሎአዊነት ችግር መኖር ከ‹‹ሚዳላለት›› ብሔር ውጪ ያሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ቅሬታ ላይ ይጥላል፡፡ የእኩል ዜጋነት ዕምነታቸውን ይሰብራል፡፡ ትምክህተኛና ተቃራኒ የሆኑ የፖለቲካ መስመሮችን ያነሳሳል፡፡ አድልኦ ባልተፈጸመበት ሥፍራና ጊዜም በይሆን ይሆናል መጠራጠርና ሐሜት እንዲራባ ያደርጋል፡፡ ሐሜቱ ደግሞ በፋንታው የብሔርተኛ ሹምን እልህ እያጋባ ማናለብኝነትና አድሏዊነትን ያባብሳል፡፡ ይኼ ሁሉ የአካባቢውን ሰላማዊ ኑሮና ልማት የሚበድል ነው፡፡

በደሉ በዚህ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ‹‹የሚዳላለት›› ብሔር የተጠቃሚነት ስም ይትረፈው እንጂ ተበዳይነቱ በእሱ ይብሳል፡፡ አድልኦን ፈቅዶ እስከተቀበለው ወይም እስካልተቃወመው ድረስ የነፃነትንና የአኩልነትን ጣፋጭነት ማጣጣም አይችልም፡፡ በራሱም ላይ አድልኦ ይጠራል፡፡ በብሔር የተጀመረው ማዳላት የዘመድ፣ የትውውቅና የሽርክና ድር እየሠራ ይስፋፋልና ‹‹የብሔር ወገኖች››ም የአድልኦ ተጠቂነት አይቀርላቸውም፡፡ እንዲያውም ‹‹የብሔር ወገኔ››፣ ‹‹ለብሔሬ የቆመ›› ባይነት ሚዛናዊ አስተውሎቱን እያደበዘዘበት የጥቅመኞች መነገጃ መሆኑን ለማጤን ከሌላው የበለጠ ጊዜ  ሊወስድበትና ብዙ ሊጠቃ ይችላል፡፡

በአድሏዊነትና በጥበት ስሙ የጎደፈ የአስተዳደር አካባቢ ወደ ሥፍራው ሊመጣ የሚችለውን ተወላጅ ያልሆነ አልሚ የማስቀረት ጉዳትም ያስከትላል፡፡ የክልል ልማት በክልል ተወላጅ፣ የአገርም ልማት በአገር ተወላጅ የሚያልቅ አይደለም፡፡ በዛሬው የግሎባላይዜሽን ዘመን ልማት እንዲሳካ ከተፈለገ ባለሀብትንና ባለቴክኖሎጂን ከየትም ይሁን ከየት እየሳቡ ልማትን እንዲያስፋፋ አደርጎ የመንከባከብ ብልህነት ነው፡፡ አገርነት ይቅርና አኅጉርነት ጠብቦ የብሔር፣ የአገርና የአኅጉር ድንበር ሳይገድባቸው በተያያዙ ጥቂት ግዙፍ ኩባንያዎች ሥር በምትመራ ዓለም ውስጥ ሆነን፣ የብሔር ብሔረሰብ ዕድልንና ልማትን በትንሽ ክልል ደረጃ ከማሰብና ‹‹የብሔር አባሎቻችን ክልላችሁን አልሙ›› ከሚል ጠባብ ማዕቀፍ መውጣት አይበዛብንም፡፡ በዚህ አቅጣጫ ከታሰበ ሐዋሳ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ዋና ከተማ ስትሆን፣ ከሁሉም በለጠ የልማት ማዕከል መሆናቸውን በማስተዋል ሲዳማዎች መደሰት ይገባቸዋል፡፡ ሁሉም ዜጋ መልካም ውኃ እንዲጠጣ፣ የትኞቹም አካባቢዎችና ወንዞች ከብክለት እንዲፀዱ፣ ሁሉም ከተሞች ቆሻሻና ፍሳሻቸውን ለገጠሩም ሆነ ለከተማው ጤና ችግር በማይሆን ዘዴ እንዲያስወግዱ ከማሰብና ከመታገል ፈንታ፣ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ውስጥ በመሆኗና የመጠጥ ውኃና የፍሳሽ አገልግሎቷ በኦሮሚያ ላይ የተደገፈ ስለሆነ ክፍያ ልትፈጽም ይገባል የሚል አስተሳሰብ ዘንድሮም ያላቸው ካሉ ወደ ኋላ ቀርተዋል፡፡ ‹‹በክልሎች ውስጥ ፌዴራላዊ መንግሥት ለኢንቨስትመንት መሬት ሲወስድ ኪራይ ይከፍላል ወይ?›› የሚል ጥያቄ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ መነሳቱም አስገራሚና የማይጠበቅ ይሆናል፡፡ በፌዴራል መንግሥት የድጎማ ገንዘብ ድርሻ ሥሌት ላይ ከመብሰልሰልም፣ በአጠቃላይ የልማት ሥርጭት ሚዛናዊነትና ዕድገትን የማጠጋጋት ጥረት ረገድ እየተሠራ ያለውን መመርመር ይበልጣል፡፡

የድርሻ ጉዳይ ሌላ ዓይነት መንፀባረቂያም አለው፡፡ በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ሀብት ክፍፍል ከብሔር ብሔረሰብ አኳያ የሚያሰሉና የአማራ፣ የጉራጌ፣ የትግሬ፣ የኦሮሞ፣ የሐረሪ ወዘተ ምን ያህል ሀብታም አለ? ምን ያህል ካፒታልስ ደርሶታል? እያሉ ለሕዝብ ብዛት ጋር የሚያነፃፅሩ ተፈጥረዋል፡፡ የዚህ ዓይነት ሥሌት ኅብረተሰቡን ለማቃቃር የሚውል መበላለጥን እየፈለጉ ከማቅረብ በስተቀር የሚሰጠው ጥቅም የለም፡፡ ሰንጠረዥና ቀመር ሠርቶ የዚህ ወገን ድረሻ በዝቷልና ከዚህ ወዲህ ይቀነስ፣ ወይም የዚህኛው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ቆሞ የዚህኛው ይስፋ ሊባል አይችልም፡፡ ያልተመጣጠነ ዕድገት አጠቃላይ የሰው ልጅ ታሪክ ባህርይ ነው፡፡ ማድረግ የሚቻለው አድሏዊነት መወገዱንና አቀራራቢ የልማት ፖሊሲ መኖሩን በትግል ማረጋገጥና በዚያ ውስጥ መጣር ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ፖሊሲ ተይዞ ሲጣርም እንኳን፣ ከአድልኦ ውጪ በሆኑ ሌሎች ምክንያቶች መበላለጥ መከሰቱ አይቀርም፡፡

የብሔርተኛ የድርሻ ሥሌት በፖለቲካ ሥልጣንም ውስጥ ይገባል፡፡ በኦሮሞ ድርጅቶች አካባቢ ኦሮሞዎችና ኦሮሚያ በኢትዮጵያ አኮኖሚ ቁልፍ ሚና እንዳላቸው ሁሉ፣ በፖለቲካውም ቁልፍ ሚና ሊይዙ ይገባል የሚል አመለካከት አለ፡፡ የሕወሓቶችን ገዢነት ተገቢ አለመሆን ለማመልከት ሲባል የትግራይ ሕዝብ ቁጥር ተደጋግሞ ሲጠቀስ ይሰማል፡፡ እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ባለው አስተዋፅኦና በቁጥሩ ብዛት ልክ የሥልጣን ድርሻው ይመጠን የሚባል ከሆነ የሚወራው ስለዴሞክራሲ አይሆንም፡፡

በዴሞክራሲና በኢኮኖሚ ግንባታ ትግሉ ውስጥ ኦሮሞዎች የአሰባሳቢነቱንና የአንቀሳቃሽነቱን ቁልፍ ሚና መጫወት አለባቸው ማለት ተፈልጎ ከሆነ፣ የኦሮሞ ፖለቲካ ምሁራን በደንብ ያላስተዋሉትን ኃላፊነት የሚያስገነዝብ ትልቅ እውነት ነው፡፡ ዋና ታጋይና አታጋይ መሆን በሥልጣን ወደ መምራትም ይወስዳል፡፡ በአራቱም ማዕዘን ከመሀል እስከ ዳር በሰፊ መልክዓ ምድር ተሠራጭቶና አብላጫውን የብሔር ቁጥር ይዞ መገኘትም በርካታ የሥልጣን ወንበር ለማግኘት የሚመች ነው፡፡ የምንነጋገረው ስለዴሞክራሲያዊ የመንግሥት ሥልጣን ከሆነ የድርሻ ሥርጭቱን በስተመጨረሻው የሚወስነው የሕዝቦች ድምፅ ነው፡፡ ራሱን በራሱ እያረመና እያጎለበተ የሚራመድ ዴሞክራሲ እስካለና ምርጫና የምርጫ ውጤት እስከተግባቡ ድረስ የትኛውም ብሔር ብሔረሰብ አባላት የሥልጣን ወንበር መበርከት/ማነስ ወይም ርዕሰ ብሔርነትን መያዝ ችግር አይሆንም፡፡ ችግር የሚመጣው የትንሹም ይሁን የትልቅ ብሔር የበላይነትን እንደ መብት/እንደ ሥርዓት ለመዘርጋትና ለማቆየት ሲፈለግ ነው፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

የእስረኞች ወንድም ዳንኤል ሺበሺ ‹‹ወንድም›› ይፈልጋል? – ወንደሰን ክንፌ

የቀድሞው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዳንኤል ሺበሺ ከሚታወቅባቸውና ባህሪያቱ መካከል ሁሉም ሊናገርለት የሚደፍረው ‹‹የህሊና እስረኞች ወንድም››መሆኑን ነው፡፡

የቀድሞው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ዳንኤል ሺበሺ

በሞያው ኢንጂነር የሆነው ዳንኤል በፖለቲካ አመለካከታቸው ወይም በሞያቸው ምክንያት በስርዓቱ እየተቀፈደዱ ወህኒ ሲወረወሩ ለቆዩ ወገኖች በቻለው መንገድ ሁሉ የትግል መንፈሳቸው እንዳይሰበርና በፋይናንስ እጦት ምክንያት ልጆቻቸው ከትምህርት ገበታ እንዳይነጥፉ የብዙዎችን ጎጆ ለመደገፍ ታትሯል፡፡
የቁጫ ሰዎች በብዛት እየታፈሱ ለወህኒ ሲወረወሩ የድረስልን ጥሪ የሚደረገው ለዳንኤል ነበር፡፡ዳንኤል ለጋዜጠኞች አበል ጭምር እየከፈለ የቁጫ ሰዎችን ችግር አገር እንድትሰማው አድርጓል፡፡ብዙዎች አካባቢያቸውን ለቀው ለአቤቱታ አዲስ አበባ በከተሙበት ወቅትም ማረፊያቸው የዳንኤል ቤት ነበር፡፡
ስርዓቱ ዳንኤልን በቁጫ ምክንያት ወህኒ ወርውሮት በሽብርተኝነት እስከመክሰስ መድረሱ አይዘነጋም፡፡ዳንኤልን ለሁለት ዓመታት አስረው ባለመርካታቸው በፍርድ ቤት እንዲለቀቅ ከተወሰነ በኋላ ወደስራው እንዳይመለስ አድርገውታል፡፡
የሁለት ልጆች አባት የሆነው ዳንኤል ስራውን እንዳይሰራ በመደረጉና በድጋሚ ወህኒ በመጣሉ ወንድሞችን ይፈልጋል፡፡ቤተሰቦቹ አባታቸው ቅን እንደነበር ቢያውቁም የእርሱ ቅንነት ባዶ ሜዳ አለመቅረቱን ለማሳየትና ኢህአዴግ እንደ ዳንኤል ያሉትን በኢኮኖሚ እየደቆሰ ለችግር ሲዳርጋቸው ለማየት የማንፈቅድ ወንድሞች መኖራችንን ለማሳየት ይህንን መልካም አጋጣሚ እንጠቀም፡፡
50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለ50 ሰው ግን ጌጥ ነው በሚለው ስሌት ተመርተን ለአንድ ሰው 20 ዶላር ለ400 ሰው 8000 ዶላር ጌጥ ነው እንበል ፡፡እርግጥ ነው ዳንኤል ወንድሞች አሉት፡፡
ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጫንም አጋርነታችንን እንግለጽ፡፡ሌሎች ይሳተፉ ዘንድም እንጋብዛቸው፡፡

ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ [ቢሊሱማ ቢሊሱማ]

ዶር ፍቅሩ ማሩ ሆርዶፋ ይባላሉ። የስዊድን ዜግነት ያላቸው የታወቁ የልብ ሐኪም ናቸው።

ዶር ፍቅሩ ማሩ ሆርዶፋ

በስውድን አገር ተምረውና ከዚያም ሥራ ሰርተው በቂ ልምድና ሀብት ካከበቱ በኋላ አገሬ ገብቼ ሳይማር ያስተማረኝን ሕዝቤን በሙያዬ ላገልግል፣ ለሕዝቤ ውለታ ልክፈል (give back)፣ የዜግነት ግዴታዬንም ልወጣ ብለው ወደ አገር ቤት ተመለሱ።

አገር ቤት ተመልሰው ለመጀመሪያ ጊዜ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የልብ ሕመም መታከሚያ ማዕከል አቋቋሙ። ይህም ማዕከል Addis Cardiac Hospital ተብሎ ተሰየመ።

ዶክተሩ ከጠበቁትም በላይ ተሳክቶላቸው ደንበኞች ከኢትዮጵያም አልፈው ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ሁሉ መጉረፍ ጀመሩ። ስማቸውም እየገነነ በመምጣቱ ክሊኒኩን ለማሳደግና እየጨመሩ ያሉትን ደንበኞች ፍላጎት በአግባቡ ለማስተናገድም ሆስፒታሉን ለማስፋፋት አስፈላጊ ዕቃዎችን ከውጭ ለማስገባት ይወስናሉ። በዚህን ጊዜ ነው የወያኔ የጉምሩክ ኃላፊዎች ጉቦ ካላመጣህ ዕቃው አይገባልህም፤ እንቢ ካልክ ደግሞ የገባልህንም ራሱ ችግር ያጋጥመዋል ብለው ያስፈራሩኣቸው። ዶሩ ግራ ገብቶኣቸው ምንድነው ይህ ነገር ብለው ሲያማክሩ፤ “ጉቦ ካላበለሃቸው እነዚህ ሰዎች አይለቁህም፤ እኛም እንደዚህ እየገበርን ነው የምንኖረው” አሉኣቸው ሰዎች።

በዚህ አኩሃን የወያኔ ባለሥልጣናቱ ዶሩንም አስፈራርተው ጉቦ ከበሉ በኋላ እርስ በርስ ተጣልተው ወህኒ ቤት ወረዱ። ወያኔዎች ዶክተሩንም በዚሁ አሳባው ወንጀል ፈጥረው ወህኒ ቤት ላኩኣቸው። ነገሩ ቀድሞውኑ ወያኔ ዶሩን ለማጥመድ ያደረገ ዲራማም ሳይሆን አይቀርም እየተባለ ነው።

የቂሊንጦ ወህኒ ቤት የተቃጠለ ጊዜ ወያኔዎች እኚህን ወገናቸውን ለመርዳት ከስውድን የድሎት ሕይወታቸውን ጥለው አገራቸው ገብተው እንደ ሕወሐት እየዘረፉና እየገደሉ ለመኖር ሳይሆን በሙያቸው ሕዝብ ሊያገለግሉ ወደ አገራቸው የተመለሱትን ዶር “እስር ቤት አቃጥለህ ሰው ጨርሰሃል” ብለው በመወንጀል በድብደባ ብዙ ብዙ ጉዳት አድርሰውባቸዋል።

ዶሩ ባሁኑ ጊዜ ወያኔ ቶርች አድርጎኣቸው ከፍተኛ ጉዳት ስላደረሰባቸው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ነው። በዚህም መሰረት Cardio thorasic surgery ሕክምና የተደረገላቸው ሲሆን ታዲያ ምን ያደርጋል ቤተሰባቸውና ሐኪሞችም እንደ ልባቸው እንዳይረዱኣቸው የወያኔ ወታደሮች ክፍላቸውን ወደ እስርቤት የመለወጥ ያህል ሆስፒታሉን አጥለቅልቀውታል።

ወያኔ ይሀውና በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በዚህ ዓይነት ዘር የማጥፋት እርምጃዎችን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። ነጋዴውን ከንግዱ፣ ተማሪውን ከትምህርቱ፣ መምህሩን ከማስተማሩ፣ ሐኪሙን ከሙያው፣ ገበሬውን ከእርሻው እያፈናቀለ መለስ ያወጣለትን ፖሊሲ ማለትም የበዛውን ኦሮሞ ቀንሶ ያነሳውን ትግሬ ለማብዛት በ21ኛው ክፍለዘመን ይህን አደገኛ ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ነው። እኚህም የተቀደሰ ዓላማው ይዘው ወደ አገራቸው ከሚሰጡት አገልግሎት ላይ ተይዘው በቶርች የሚሰቃዩት ዶክተርም ለዚህ ሁሉ መከራ የተዳረጉት ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ ነው።

ስለዚህም ኦሮሞ ያለው አማራጭ ወይ ተከላክሎ ጠላትን አስወጥቶ ራስን ማዳን ወይ እንደ ሕዝብ መጥፋት ነው።Umar OmarLenjiso

የዶ/ር መረራ መታሰር ሰላማዊው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተደረገ ጥሪ ነው!!! – መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)

መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)

መረራ ጉዲና ገና ከለጋ ወጣትነት ህይወቱ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ባልተቋረጠ ወኔና ጥራት ለአንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሲታገል የኖረ ዜጋ ነው፡፡ በዚህ ያልተቋረጠ ተጋድሎው በንገሱ ዘመን አምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ በተማሪው ንቅናቄ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ለአጭር ጊዜም ቢሆን እስር ቤት ተወርውሯል፡፡ በደርጉ ዘመን ደግሞ በመኢሶን ታጋይነቱ ለሰባት አመታት በእስር ተንገላቷል፡፡ ለአለፉት 25 አመታት ደግሞ የወያኔ ኢህአዴግን ግፈኛ አገዛዝ በመቃወም በሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልት ተሰማርቶ ከነዚህ የጥፋት ሃይሎች አንጻር እነሱ ከፋፍለህ ግዛን ሲያራመዱ የህዝቦች ወንድማማችነትን እየሰበከ፣ እነሱ ለስልጣናቸው ሲሉ በለየለት የአፋኝና የአመጽ ጎዳና ሲሰማሩ ዴሞክራሲን፣ ሰላምንና ህጋዊነትን እያነገበ ሲሞግታቸውና ሲታገላቸው በህዝባችን ፊት ተአማኒነትንና ተወዳጅነትን ያተረፈ ብርቅየ የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡

Dr. Merera Gudina

መረራ ጉዲና በዚህ ረጅም የታግል ታሪኩ የሚታወቀው በወያኔ ኢህአዴግ ተቃዋሚነት ብቻ አይደለም፡፡ ለተቃዋሚዎች ጎራም ባለፉት 25 አመታት ያለመታከት የሚያስተላልፋቸው መልእክቶች የዚያኑ ያህል ግልጽና ያልተቋረጡ አንዳንዴም ከዚሁ ሰፈር ተቃውሞ የሚሰነዘርባቸው አቋሞች ናቸው፡፡ የኦሮሞን ህዝብ ኢትዮጵያዊነት አብስሮ በህዝቦች ወንድማማችነትና እኩልነት ላይ ለተገነባች ለአንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሲታገል በአንድ ወቅት ‘የዘመኑ ጎበና’ የሚል ቅጽል ተቃውሞ ገጥሞት ነበር፡፡ ሰላማዊና ህጋዊ ትግል በማለቱና ይህን ሰሞን እንኳን በውጭ እያለ በተደጋጋሚ የሃገሪቱን ችግር በሰላማዊ መንገድ ከኢህአዴግም ጋር ተወየይተን እንፍታ እያለ በሚያስተጋባው አቋሙ በአንዳንዶች በ’ታማኝ ተቃዋሚነት’ ተፈርጆ ነበር፡፡ ይህንን ሁሉ ከምንም ሳይቆጥር ሚልዮኖችን የሚያንቀሳቅስ ህዝባዊ ትግል መልክ እንዲይዝ ላለፉት 25 አመታት በግንባር ቀደምነት ታግሏል፡፡

በዚህ አዋጅ ምክንያት ትግሉ አይቆምም፡፡ ላለፉት 25 አመታት በተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች፣ በማስ ሚድያው በነጻ ጋዜጠኞች፣ በፖለቲካ መሪዎች ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል ይካሄድ የነበረው፣ ባለፉት ሁለት አመታትም በተለይ በአማራና በኦሮሞ ክልሎች የተጧጧፈው ህዝባዊ ትግል የሚደረገው ታጋይ ዜጎች በጠራራ ጸሃይ እየተተኮሰባቸው፣ በገፍ እስርቤት እየተወረወሩና በገፍ እየተደበደቡ አንጅ ይህ የጥፋት ሃይል እነዚህን ትግሎች በሰላምና በጸጋ እያስተናገዳቸው አልነበረም፡፡ ዛሬ በዚህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰላማዊው ትግል መከልከሉ እስከዚህም የሚቀይረው ነገር አይኖርም፡፡ ባለፈው ሰሞን በአምስተርዳም ባደረገው ንግግር ዶ/ር መረራ ይህንን እውነታ ሲያስረግጥ ‘’ በይፋ አልተነገረም እንጂ ኮማንድ ፖስቱ ከአዋጁ በፊትም የነበረ የኢህአዴግ አሰራር ነው’’ በማለት በግልጽ አስቀምጦታለል፡፡ የሰላማዊና ህጋዊ ትግል ተምሳሌት የሆነው የዶ/ር መረራ በዚህ አዋጅ ሳቢያ መታሰር ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ይህ ዜጋ የቆመለት ህዝባዊና ሃገራዊ ትግል ሚልዮኖችን በሚያካትት መልኩ ተፋፍሞ እንዲቀጥል በኢህአዴግ የተላለፈን ጥሪ አድርገን መቁጠር ይኖርብናል፡፡

ትግሉ ይቀጥል ሲባል ስለ ፍሬያማነቱም ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዛሬ በዶ/ር መረራ መታሰር የሚቆጩና የሚቆጡ ሚለዮኖቸ ከሁሉም በላይ የዚህን ታጋይና የሌሎች በግፍ በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎቻችን መፈታት እየጠየቁ ይህ ውድ ዜጋችን ‘ተባበሩ ወይ ተሰባበሩ’ ብሎ ያስተላለፈውን መልእክት ተከትለው በአንድነት፣ እንዲሁም ከድሮ ጀምሮና አሁንም በአምስተርዳም ቆይታው ከፋፋይ የሆነውን ‘‘የታሪካ ሂሳብ ማወራረድ አቁሙ’’ ብሎ የሰነዘረውን ምክር አጢነው በብሄር፣ በሃይማኖትና በአካባቢ ሳይከፋፈሉ ወንድማማችነት፣ እርቅና ሰላም ወርዶ ለሁላችንም የሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚደረገውን ትግል ‘በመረራ መንፈስ’ እየተመሩ ማፋፋም ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡ እኛም ዛሬ በዚህ ራእይ እየተመራን ይህንን በጎና አገራዊ ራእይ እውን ለማድረግ ትግላችንን ማቀነባበርና ማፋፋም ይጠበቅብናል ፡፡

መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)
ታህሳስ 2009

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17293/#sthash.5nGFCkoi.dpuf

በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ሽፋን የሽብር ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠሩ ክስ ተመሠረተባቸው

 

–  ከ202 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ተብሏል

የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በሚባል ሽፋን በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መሪነት በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች፣ ታኅሳስ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሠረተባቸው የሰሜን ጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አቶ መብራህቱ ጌታሁን፣ ጌታቸው አደመ፣ አታላይ ዛፌና አለነ ሻማ ናቸው፡፡ ከትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሰቲት ሁመራ ነዋሪ አቶ ነጋ ባንተይሁንም በክሱ ተካተዋል፡፡

ተከሳሾቹ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን የሽብር ተልዕኮ ለማስፈጸም ‹‹የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ›› በማለት ራሳቸውን አባልና አመራር ብለው ከሰየሙ በኋላ፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን የፕሮፓጋንዳ ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው ተከሳሾቹ የማንነት ጥያቄውን ሽፋን በማድረግ፣ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በተለያዩ ተንቀሳቃሽ ስልኮች በቀጥታ ተገናኝተዋል፡፡ በትግራይ ክልላዊ መንግሥትና በወልቃይት አስተዳደሮች ላይ የግድያና የአፈና ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ለወጣቶች የጦር መሣሪያ አስታጥቀዋል፡፡ የታጠቁት ወጣቶች በዳንሻ ከተማ ግለሰቦችን እንዲገድሉ፣ አፍነው እንዲወስዱና በቃፍታ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ላይ የግድያ ሙከራ በማድረግ፣ የዳንሻና ሶሮቃ መንገድ እንዲዘጋ ማድረጋቸውን ክሱ ይዘረዝራል፡፡

በክልሉ በሰሜን ጎንደር ዙሪያ በፀገዴ ወረዳዎች በደባርቅ፣ እንጂባራ፣ ወረታ፣ ደምቢያ፣ መገራ፣ በምዕራብ አርማጭሆ በመተማ ዮሐንስና ዙሪያው ተከሳሾቹ ከመጋቢት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ባስነሱት አመፅ በመንግሥትና ሕዝብ ተቋማት፣ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶችና ተሽከርካሪዎች ላይ ከ95.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ማድረሳቸውን በክሱ ተጠቅሷል፡፡ በጎንደር ከተማ በሚገኙ ቀበሌዎችም በመንግሥትና በሕዝብ ተቋማትና በተሽከርካሪዎች ላይ ከ10.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንም አክሏል፡፡

ከነሐሴ 18 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ደግሞ በምዕራብ ጎጃም በሚገኙ በባህር ዳር ዙሪያ መርዓዊ ከተማ፣ በሜጫ ወረዳ፣ በቡሬ፣ በደጋ ዳሞት አዴት ከተማ፣ በፍኖተ ሰላምና ባህር ዳር ከተማ ከ95.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንና በድምሩ ከ202 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያብራራል፡፡

ተከሳሾቹና ኮሎኔል ደመቀ ሰብሳቢ በመሆን ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ውስጥ በሚገኝ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ግለሰቦችን በመሰብሰብ፣ ‹‹የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ሊሰጠን አልቻለም፡፡ የወልቃይት ፀገዴ የማንነት ጥያቄውን ምክር ቤቱ ወርዶ ሊያየው የሚችለው ደም ሲፈስና ግጭት ሲከሰት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እዚህ ተወክላችሁ የተገኛችሁ በሙሉ ወደ መጣችሁበት ቦታ በመሄድ፣ አመፅ በመፍጠርና መንገዶችን በመዝጋት የሽብር ተግባር መፈጸም አለባችሁ፡፡ ይህንን ስታደርጉ ከእናንተም ሆነ ከመንግሥት አካላት ሰው ሊሞት ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄያችንን ይፈታልናል፤›› በማለት ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

በወረቀትና በብዕር የሚመጣ ፍትሕ እንደሌለና በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ አመፅ እንዲነሳ የሚያደርጉና የሚያስተባብሩ ሰዎችን በመምረጥና በመመልመል፣ የሽብር ተግባሩን እንዲያፋፍሙ ተልዕኮ መስጠታቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡

ተከሳሾቹ በተለያዩ አካባቢዎች ለመለመሏቸው ወጣቶች ገንዘብ በመላክ ከአዲ ረመጽ አካባቢ ጥይት ገዝተው እንዲዘጋጁ ማድረጋቸውን፣ ወጣቶችን እያፈኑ መውሰዳቸውን፣ በተለያዩ ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውንና የግድያ ሙከራ ማድረጋቸውንም ክሱ ያብራራል፡፡

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የማንነት ጥያቄውን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ በውጭ አገር ከሚገኙት ስረበ ጥሩነህ፣ መዓዛው ጌጡና አስማረ ከተባሉት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በስልክ ግንኙነት በማድረግ የገንዘብ ድጋፍ ሲያገኙ እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል፡፡

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች በኤርትራ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በማድረግ፣ የጦር መሣሪያ እንዲገዙና በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ፀገዴ ወረዳዎች በተለያዩ አካባቢዎች መንገድ በመዝጋት እንዲፈጸም ትዕዛዝ መስጠታቸውን ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾቹ ክሱን በንባብ አሰምቷቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ የተገለጸውን የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል የተባለው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀእናለን)፣ 38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001ን ተላልፈው በመሆኑ፣ የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሠረተባቸው የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ የተጠቀሱባቸው የሕግ አንቀጾች ዋስትና ስለሚከለክሉ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የቅድመ ክስ መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡና ከጠበቃ ጋር ተመካክረው ታኅሳስ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር

መሬት ሳትበይኝ ልብላሽ (ከይገርማል)

 

ወያኔወች ከትግራይ ጋር የሚካለሉትን የአፋርና የአማራ ለም አካባቢወችን መቆጣጠራቸው ሳያንስ ረጅም ርቀት ተጉዘው የጋምቤላንና የቤንሻንጉልን ለም መሬት በኢንቨስትመንት ስም ሕዝቡን ሳይቀር እያፈናቀሉ እየሸጡ እንደሆነ ስሰማ በታሪክ የማውቃቸው አንድ አባት ትዝ ይሉኛል:: በርግጥ እኒህ አባት የማንንም ሳይሆን የራሳቸው የነበረውን ሰፊ መሬት ነው እየሸነሸኑ የሸጡት::

ቀኛዝማች ሰውነቴ እልምነህ ይባላሉ፥ አጭር ቀጭን ወደጥቁር ያደላ መልክ ያላቸው። ተወልደው ያደጉት በዱሮው አጠራር በጎጃም ክፍለሀገር በደብረማርቆስ አውራጃ በስናን ወረዳ አሽመን እየሱስ በሚባለው የገጠር ቀበሌ ነው። የአርባው ዘር ወይም የወንበዴው ዘር በሚል ከሚታወቅ የዘር ሐረግ የሚመዘዙት “እኔን እኔን” በሚለው አባባላቸው የሚታወቁት ቀኛዝማች ሰውነቴ በአንደበተ ርቱእነት፥ በጫወታ አዋቂነትና በመብት ተሟጋችነታቸው በጎጃም ውስጥ ከሚጠቀሱ ስመጥር ሰዎች ውስጥ አንዱ ነበሩ። ቀኛዝማች ከሚታወሱባቸው መሀል ጥቂቱን አነሆ!

መሬት ሳትበይኝ ልብላሽ

ቀኛዝማች ጉልበታቸው ሳይዝል፥ ኣይናቸው ሳይፈዝ፥ ነጣቂ ሳይመጣ ነበር ትርፍ የተባለ ቤትና ቦታ ሸጠው ያጠናቀቁት። አብማ ተብሎ በሚጠራው የከተማው አካባቢ የሚገኘውን ትርፍ ቦታና መሬት ሲሸጡ “መሬት ሳትበይኝ ልብላሽ” እያሉ ነበር።ደርግ ወደስልጣን መጥቶ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት በአዋጅ ሲወርስ ሰውነቴ የቀራቸው የሚኖሩበት ቤት ብቻ ነበር። ተበድሮም ተገድሮም ለመጦሪያ ይሆነኛል ብሎ ሰርቪስ ቤት ሰርቶ ያከራየ ሳይቀር በትርፍ ቤት ስም ሲነጠቅ ሰውነቴ ትርፍ የተባለ ቤትና ቦታቸውን ሙልጭ ኣድርገው ሸጠው ባጠራቀሙት ገንዘብ በሰላም እየተጦሩ ነበር። እኒህን አባት እንደነብይ ያያቸውና በአድራጎታቸው የተገረመ ቢኖር የሚፈረድ ኣይሆንም። ወያኔስ እንዲህ አገር ምድሩን እየሸነሸነ እየሸጠ ያለው ምን ቢታየው ይሆን!

ቢጨንቀኝ ነው

የ፩፱፻፪፰ ዓመተ ምህረቱን የጣሊያን ወረራን ተከትሎ የጣሊያን ጦር ደብረማርቆስ እንደገባ የወሰደው የመጀመሪያ እርምጃ ባላባቶችን እና ታዋቂ ሰዎችን ሰብስቦ መግደል ነበር:: በአንዲት የጭንቅ ዕለት በውሰታ ሜዳ ላይ ተሰብስበው ሞትን ሲጠብቁ ከነበሩት የጎጃም ታላላቅ ሰዎች አንዱ የሆኑት ቀኛዝማች ሰውነቴ አንድ ያልታሰበች ቃል ከሞት ልትታደጋቸው በቃች:: “እኔን” የምትለዋን ቃል ደጋግመው ሲናገሩ የሰማ አንድ የጣሊያን ወታደር “ይኸ ሰው ምንድን ነው የሚለው?” ሲል አንዱን አስተርጓሚ ይጠይቀዋል:: ምንም ቢሆን ታዋቂ ሰው ስለሆኑ አስተርጓሚው በክብር “ጌታየ ምንድን ነው የሚሉት እያለ ነው ነጩ እየጠየቀዎት ያለው” ሲላቸው ፈጠን ብለው መላ አካላታቸውን በአይኖቻቸው እየፈቀዱ  ” እኔን እኔን! አይ እጅ! አይ እግር! አሁን ይኸን ገላ አፈር ሊበላው!” ሲሉ ያጉተመትሙና ቀጥለው በቁጭት “ከሁሉ ሁሉ የሚቆጨኝ ያንን ዳኛቸው የሚባል ሽፍታ ሳላስይዝ መሞቴ ነው” በማለት ይናገራሉ::

ዳኛቸው ማለት በዕድሜ ከርሳቸው የሚያንስ የናታቸው ወንድም የሆነው የስናኑ ፋኖ ፊታውራሪ ዳኛቸው ተሰማ ነበር:: ይህ ሰው ደግሞ በጣሊያኖች ከሚፈለጉት የጎጃም አርበኞች ውስጥ አንዱ ነበር:: ቀኛዝማች የተናገሩትን ከአስተርጓሚው አንደበት የሰማው የጣሊያን ወታደር ብርሀን ይዞ የመጣውን የጣሊያን ጦር በመውጋት ችግር እየፈጠረ ያለው ዳኛቸው እንዲያዝ የሚረዱ ከሆነ እንደሚሾሙ እንደሚሸለሙ ደጋግሞ ቃል በመግባት ወደ ማባበል ይገባል::

ቢያንስ ለአንድ ቀን ነፍሳቸውን ለማቆየት እንዲችሉ የዕድል በር ስለተከፈተላቸው በውስጣቸው የአሽመኑን እየሱስ ሳያመሰግኑ አይቀሩም:: “ምንም ችግር የለም” አሉ ፈጠን: ቆፍጠን ብለው:: “ሰተት አድርጌ ወስጀ እጁን አስጨብጣችኋለሁ:: ከዚያ በኋላ ብሞትም አይቆጨኝ” አሉ በእልህ እየተንቆራጠጡ::

የሰውነቴን ንግግር የሰሙ አብረዋቸው ተቀምጠው ሞታቸውን ይጠብቁ የነበሩት ትላልቅ ሰዎች: አጎታቸውን ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት የቆረጡ ከሀዲ አድርገው ሳይታዘቧቸው: አይንህ ላፈር ሳይሏቸው አይቀርም:: እሳቸው ግን በውሳኔያቸው ጸንተው “በሉ ፍጠኑ እንሂድ!” በማለት ያን የሞት አውድማ ጥለው የጣሊያንን ጦር እየመሩ ወደካብ ጊዮርጊስ ገሰገሱ::

ከገደማላ ጀምሮ እስከመንክርባዶ ድረስ የተዘረጋው በረባዳ ቦታ ላይ የሚገኘው “ገማና” ተብሎ የሚጠራው ጥቅጥቅ ያለው ደን በመሀሉ የሽገዛ ወንዝ የሚፈስበት ሲሆን ለወስፋት መግደያ የሚሆን አጋሙ: ቀጋው: ኮሽሙ: እንጆሩ: አሽቃሞው የተትረፈረፈበት ነበር:: ለነገሩ ወፍ የበላውን ሁሉ ቢበሉትስ ምን ይላል! በዚህ ደን ውስጥ አውሬ ብቻ ሳይሆን በተለያየ ምክንያት የሸፈቱ ሰዎችም ተደብቀው ይኖሩበታል:: ገማና እየኖሩ ጦም ማደር የለም:: ሚዳቋው: ድኩላው: ቡኸሩ ሞልቷል:: ለአደን ተብሎ ሩቅ መሄድ ሳይስፈልግ ከአንድ ቦታ ድምጽን አጥፍቶ በአይን ማማተርና ጆሮ መቀሰር ብቻ በቂ ነው:: አንዳንድ ጊዜም ሁሉም በየራሱ ሀሳብ ሲጥደፈደፍ ሳይታሰብ መጋጨት ሊኖር ወይም ተጠላልፎ መውደቅም ሊያጋጥም ይችላል:: ያሁኑን አያድርገውና ገማና ለመዋያ ብቻ ሳይሆን ቢከርሙበትም ለሆድ የማይታሰብበት ምን እበላ! የማይባልበት ቦታ ነበር::  ዳኛቸው ይገኝበታል ተብሎ የተገመተው ቦታ ይኸው ገማና ነበር::

ጦሩ በቀኛዝማች ሰውነቴ እየተመራ ገማና ሲደርስ የአርበኞች ሰራዊት በአካባቢው አልነበረም:: ሽፍቶቹ ለቀውት ከሄዱት ቦታ ላይ የተለያየ ትዕይንት ይታያል:: በየቦታው ተቆፍሮ ከተሰራው ምድጃ ከሚነደው እሳትና በብረትምጣድ እየበሰለ ካለው ምግብ የሚወጣው ጭስ ይትጎለጎላል:: ተገፈው ያለቁ እና ገና በመገፈፍ ላይ የነበሩ ፍሪዳወች እዚያም እዚያም ይታያሉ:: አካባቢው ዝርክርክ ያለ በመሆኑ የአርበኞች ጦር በድንገት ተነስቶ ከአካባቢው ለመሰወሩ ተጨማሪ ማስረጃ የሚያስፈልግ አልነበረም:: ወደቦታው የተንቀሳቀሰውን የጣሊያን ጦር ያየ የአካባቢው ሰው ለአርበኞች እንደተናገረ በሁሉም ዘንድ የተገመተ ቢሆንም ይህንን ያደረጉት ራሳቸው ቀኛዝማች ሰውነቴ ይሆናሉ ብሎ ያሰበ ግን አልነበረም::

ወደገማና ጉዞ ሊደረግ ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜ ቀኛዝማች ምን ማድረግ እንዳለባቸው እያውጠነጠኑ ነበር:: ነፍሳቸውን ለማዳን ብለው ለሀገሩና ለወገኑ እየተዋደቀ ያለውን የብዙ አመት ታናሻቸው የሆነውን የእናታቸውን ወንድም አንገቱን ለገመድ አሳልፈው ለመስጠት የሚታሰብ ነገር አልነበረም:: በድንገት አንድ የሚያውቁት ሰው ላይ አይናቸው ሲያርፍ ነፍሳቸው በደስታ እፎይ አለች:: ይህችን የጭንቅ ጊዜ አለፍኋት ማለት ነው ሲሉም አሰቡ:: አመች ጊዜ ጠብቀው ያን የሚያውቁትን ሰው በአይናቸው ይጠቅሱና “በፍጥነት ገስግሰህ ዳኛቸው ዘንድ ገማና ሂድና የሆነውን ሁሉ ንገረው:: ነፍሴ የተረፈችው አንተን ለማስያዝ እንደምፈልግ ስለነገርኋቸው ነው:: ወደአንተ ልንመጣ ዝግጅት ላይ ነን:: አብስላችሁ ልትበሉ ስትሉ ድንገት እንደደረስንብህ አድርገህ ጥፋ:: እየመጣ ያለው ጦር ከባድ መሳሪያ የታጠቀ ጦር ነው:: ለእኔ ስትል ምንም ነገር ሳታደርግ ከአካባቢው ተሰወር:: እሱን እንደሆነ ነግ ከነገ ወዲያ ታገኘዋለህ:: ለዛሬው እኔን አትርፈኝ:: ብለህ ንገረው” ብለው ሰውየውን ከላኩ በኋላ ነበር ተረጋግተው ጦሩን እየመሩ ጉዟቸውን በደስታ የጀመሩት::

ይህንን ተልዕኮ ለማስፈጸም ጦሩን በበላይነት የመሩት የጣሊያን ወታደራዊ መኮንኖች ገማና ላይ ባዩት ሁኔታ ቀኛዝማች ሰውነቴ ሀቀኛ ናቸው ብለው በማመናቸው በነጻ ለቀቋቸው::

ከ5 አመቱ የአርበኝነት ውጊያ በኋላ የጣሊያን ጦር በኢትዮጵያ አርበኞችና በእንግሊዝ ሰራዊት ጥምር ኃይል ተመትቶ ሲወጣ አጼ ኃ/ሥላሴ ወደአዲስ አበባ የተጓዙት ደብረማርቆስ ለአንድ ወር ያህል ከቆዩ በኋላ ነበር:: ቀኛዝማች ሰውነቴ ከንጉሱ ጋር ቀደም ሲል ጀምሮ ቀረቤታ ስለነበራቸው ንጉሡ ደ/ማርቆስ በቆዩበት ጊዜ ሁሉ አልተለይዋቸውም::

ጉልት ከልጅ ልጅ የሚተላለፍ በየደብሮች (የገበሬ ቀበሌወች) የባላባቶች የአካባቢ አስተዳደር አካል ነው:: ቀኛዝማችን የጣሊያን የጦር አዛዦች በምህረት ሲለቋቸው የጣሊያን መንግሥት ሽህ አመት ይግዛ ብለው መርቀዋል በሚል በጠላቶቻቸው የተቀናበረ ክስ ስለተመሰረተባቸው የወቅቱ የጠ/ግዛቱ ገዥ ከጉልታቸው ነቀሏቸው:: ይህን ውሳኔ ተቀብሎ እሽ ብሎ መኖር ለቀኛዝማች ፈጽሞ የማይሞከር ነበር:: ከአያት ቅድመአያት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን እርስተጉልት አሳልፎ ሰጥቶ አርፎ መቀመጥ የሚታሰብ አልነበረም:: ሰውነቴ ካላግባብ ተወስዶብኛል ያሉትን እርስትና የተነካባቸውን ክብር ለማስመለስ አዘናግተውና አመች ጊዜ ጠብቀው ለአቤቱታ ወደሸዋ የተሻገሩት በዚህ ምክንያት ነበር::

በማንኛውም ጊዜ ቤተመንግሥት ለመግባት ፈቃድ ያላቸው ሰውነቴ ካላንዳች ችግር ከጃንሆይ ዘንድ ቀርበው እንደደንቡ ለጥ ብለው ሰግደው ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ቁጭ ብለው ጨዋታ ይጀምራሉ:: ንጉሱ ቀኛዝማቹ የመጡበትን ጉዳይ ቢጠረጥሩም የሆዳቸውን በሆዳቸው አድርገው “ልትጠይቀን ነው የመጣህ ወይስ ችግር ገጥሞህ ነው?” ሲሉ ጥያቄ አቀረቡላቸው:: ቀኛዝማች ሲመልሱ “አንድም አይንዎን ልይ ብየ ነው: ሌላም ችግር ገጥሞኝ ነው” አሉ:: ጃንሆይ ምንም እንደማያውቁ መስለው “ምን ችግር ገጠመህ?” ሲሉ  ጠየቋቸው:: “ከአያት ከቅድመአያቶቼ ሲወርድ ሲዋረድ የተረከብሁትን ጉልቴን ብቀማ ነው አቤት ልል የመጣሁት” አሉ ቀኛዝማች አንገታቸውን ሰበር አድርገው:: ይኸኔ ንጉሡ “ጣሊያንን ሽህ አመት ግዛ አላልህም?” ሲሉ  ቆጣ ብለው ጠየቁ:: ሰውነቴ “እኔ አላልሁም” ብለው ክርክር ለመግጠም ፍላጎቱ አልነበራቸውም እና ምንም መረበሽ ሳያሳዩ ረጋ እንዳሉ “አዎ ብያለሁ” አሉ አንገታቸውን ቀና አድርገው ፊት ለፊት እያይዋቸው:: “እኮ ለምን?” አሉ ጃንሆይ ይበልጥ ተቆጥተው:: ቀኛዝማች ትንሽ ፈርጠም ካሉ በኋላ የሆነውን ሁሉ ነግረዋቸው ሲያበቁ “ጣሊያንን ሽህ አመት ግዛ ያልሁት ቢጨንቀኝ ነው:: እርስዎስ ቢጨንቅዎ አይደል ሀገር ጥለው የሄዱ” ሲሉ አከሉ:: ይኸኔ ንጉሡ ደፍረው ቀኛዝማችን የሚቆጡበት አንደበት አልነበራቸውም:: እንዲህ እንዳሁኑ የቅጥፍጥፍ ዘመን ስላልነበር ጃንሆይ የራሳቸውን ድክመት ሸፍነው ሌላውን ተጠያቂ የሚያደርጉበት መሰረታዊ ምክንያት አልነበራቸውም:: ለደቂቃወች ጸጥ ብለው ሲተክዙ ከቆዩ በኋላ ከአንደበታቸው የተደመጠው “እውነት ብለሀል ሰውነቴ:: ምነው ሌላውም እንዳንተ ዋሽቶም ቢሆን ነፍሱን ባቆየልኝ ኖሮ!” የሚለው ነበር::

ሰውነቴ የተወሰደባቸውን ጉልት አስመልሰው ደርግ በአዋጅ እስኪሽረው ድረስ በስራቸው የነበረውን ሕዝብ በሰላምና በፍቅር ሲያስተዳድሩ ኖረዋል::

የሕዝብ ጠበቃነት

ሰውነቴ የአካባቢ ዕድገትና የሕዝብ ሰላም የሚያሳስባቸው ነበሩ:: ጎጃም ተበድሏል ብለው ካሰቡ ግምባር ቀደም ተከራካሪ ሆነው ተሰልፈው ታግለው ለማታገል ወደኋላ ብለው አያውቁም:: ለዚህም እንደምሳሌ የሚጠቀሰው የሚፈለገውን ያህል ሥራ አልሰሩም በሚል ሕዝቡን በማስተባበር ደጃዝማች ጸሀይ ዕንቁሥላሴን ከጎጃም እንዲነሱ ማስደረጋቸው አንዱ ነው:: ተቃውሟቸውን ለመግለጽ የተጠቀሙባቸው ሰላማዊ መንገዶች ደግሞ በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው:: በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በሚዘንብበት አንድ ቀን ብዙ ሕዝብ በሚያይበት ቦታ ላይ ከሜዳ ላይ ቆመው ዝናብ እየወረደባቸው ያሰሙት ተቃውሞ በጎጃሞች ዘንድ ሲታወስ ይኖራል:: “ኧረ እባክዎት ወደዚህ ይምጡና ይጠለሉ?” ብለው የለመኗቸውን ሰዎች “ጸሀዩ ነው እንጅ ዝናቡስ አልጎዳኝም” በማለት በደጃዝማች  ጸሀይ ላይ የነበራቸውን ተቃውሞ በሰላማዊ መንገድ አሰምተዋል:: በአንድ ወቅት ደግሞ ከበጅሮንድ ረታ ጋር በነበራቸው ክርክር በፍ/ቤት በመረታታቸው ተናደው የተናገሩት ነገር ነበር:: በክርክሩ የተረታሁት ደጃዝማች ጸሀዩ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ለበጅሮንድ ረታ ድጋፍ ስላደረጉ ነው በሚል ቀኜ ቂም ቋጥረው ቆይተው ኖሯል:: በጅሮንድ ረታ የቁምጥና በሽታ አለባቸው ተብለው ይታሙ ስለነበር የክርክሩን ውጤት ለማወቅ የጓጓ አንድ ሰው ከርቀት ላይ ሆኖ “እንዴት ሆነ?” ብሎ ሲጠይቃቸው ሌላውም እንዲሰማ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው “ስንሟገት ውለን ከጠዋት እስከማታ: ጸሀዩ በርትቶ ቆማጣው ረታ” ብለው ተባብረው በድለውኛል ያሏቸውን ሰዎች ስም ጠቅሰው ብሶታቸውን በመረሩ ቃላት ገልጸዋል::

የሰጠህን አመስግነህ አትቀበልም! አበድረኸዋል?

በያኔው የአጼ ኃይለሥላሴ ያስተዳደር ስርዐት ጉቦ መብላት የተለመደ ነበር። ጉዳዩን ለማስፈጸም ወይም አቤቱታ ለማቅረብ የፈለገ ሰው ለጉልተገዥው ትንሽም ቢሆን በጉቦ መልክ ሸጎጥ ማድረግ እንደነውር አይታይም ነበር። ቀኛዝማች በህዝቡ አንዲወደዱ ካደረጓቸው ምክንያቶች አንዱ በትንሽ በትልቁ እየተነሱ ሰውን ለመቅጣት የማይፈቅዱ: የሰውን መብት አክባሪና ፍትሀዊ ከመሆናቸው በተጨማሪ የተሰጠኝ ጉቦ አነሰ ብለው ስለማይሉ ነበር። ይህን በተመለከተ የሚነገርላቸው አንድ ነገር አለ። አንድ ባለጉዳይ ቀኛዝማች ዘንድ መቅረብ ይፈልግና ለእልፍኝ አስከልካዩ ሁለት ብር ይሰጣል። የልፍኝ አስከልካዩ በድፍረቱ ተናዶ ሰውየውን አያዳፋ ሲያባርረው ቀኛዝማች ይሰማሉ። ወዲያው የልፍኝ አስከልካያቸውን ያስጠሩና ሰውየውን ለምን አየገፈተረ አንዳባረረው ይጠይቁታል። የልፍኝ አስከልካዩ ንዴቱን መቆጣጠር አንዳቃተው ከላይ ከላይ እየተነፈሰ የሆነውን ይነግራቸዋል። ሁሉንም በጸጥታ ካዳመጡ በኋላ እንዲህ አሉ፥ “የሰጠህን አመስግነህ አትቀበልም! አበድረኸዋል? በል አሁን ባስቸኳይ ሂድና ጥራው” ብለው ሰውየውን አስጠርተው ጉዳዩን ሰሙለት::

ከቂጡ ቆርጨ በአፉ ስላጎረስሁት

ሌላው የሚወደዱበት ምክንያት ደግሞ በጉቦ ያገኙትን ገንዘብ አጠራቅመው ሕዝቡን ሰብስበው ግብር የሚያበሉ በመሆናቸው ነበር። ይህንን በሚመለከትም የሚታወስላቸው ነገር አለ። “እንዲያው ምን ቢያደርጉ ነው ሕዝቡ እንዲህ የሚወድዎ?” ተብለው ሲጠየቁ “ምን ኣደርግለታለሁ ብላችሁ ነው ከቂጡ ቆርጨ በአፉ ስላጎረስሁት ይሆናል እንጅ”።

 

 

በጣም ዘግይተሻል ወያኔ! [ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው]

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

“You are late!” ይላል ፈረንጅ በመዘግየቱ ያለቀለት ነገር ሲያጋጥመው፡፡ አንዳንድ ጓደኞቸ የሰሞኑን የብሔራዊውና ወያኔ ክልል በማለት የሚጠራው የሀገር ክፍል የኅትመትና የኤሌክትሮኒክስ (ነርሃላዊ) የብዙኃን መገናኛዎች የሚያቀርቧቸውን ነገሥታትንና ታሪካችንን አወዳሽ፣ ዘካሪ፣ አክባሪ ዝግጅቶች እያዳመጡ “ዝግጅቶቹን እንዴት አገኘሀቸው?” ሲሉ ጠየቁኝ፡፡ ሲመስለኝ እነኝህ ዝግጅቶች እየቀረቡ ያሉት በአማርኛ በሚቀርበው የብሔራዊው ጣቢያ ዝግጅቶችና ወያኔ የአማራ ክልል በማለት በሚጠራው የሀገሪቱ ክፍል ያሉ የመንግሥት ሬዲዮ (ነጋሪተ ወግ) ጣቢያዎች ላይ ነው፡፡ እንደ ኦሮምኛና ትግርኛ በመሳሰሉ ቋንቋዎች በሚያቀርቡ ጣቢያዎች ተመሳሳይ ዝግጅቶች መቅረባቸውን በእጅጉ እጠራጠራለሁ፡፡

እኔ የመንግሥት (የሕዝብ) የብዙኃን መገናኛዎች ከመገናኛ ብዙኃን መርሖ (Principle) እና ሥነ ምግባር (Ethics) ውጭ ከሚዛናዊነት ጋር ተቆራርጠው የሀገሪቱንና የሕዝቧን ጥቅም እጅግ በሚጎዳ አቅጣጫ አጥብቀው በመንጎድ ከሀገርና ሕዝብ ጥቅም በተፃራሪ የቆመውን የወያኔን ዕኩይና ነውረኛ ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ ለፋፊ ቱልቱላ ሆነው መቅረታቸውን ከተረዳሁ ወዲህ አዳምጨም ተከታትየም አላውቅምና የሆነውን ነገር ለመረዳት እነሱኑ መልሸ መጠየቅ ነበረብኝ፡፡

ለካ ወያኔ ሆየ ሰሞኑን በብዙኃን መገናኛዎች ለ26ዓመታት አርቃ ለመቅበር ጥልቅ ጉድጓድ ስትቆፍርለት የኖረችውን፣ ከትምህርት ሥርዓቱም አሽቀንጥራ የጣለችውን የታሪክን ነገር በጥሩ ጥሩ ዝግጅቶች ስታዜምና ስትተርክ ሰንብታ ኖሯል፤ ሰውም ይሄ መሆኑ ገርሞት ነው መጠያየቁ፡፡ አንዳንድ ተላሎች ወገኖቻችንም በእነኝህ ዝግጅቶች በመደሰት የቀረቡ ዝግጅቶችን በመጽሐፈ ገጽ መዝገባቸው (በፌስቡክ አካውንታቸው) ላይ ተጋርተው ለጥፈውታል፡፡ መቸስ ይገርማል! እንግዲህ ወያኔ በጥልቅ ስለታደሰች በጥልቅ መታደሷ ያመጣው ለውጥ ይሆናላii ኪኪኪኪኪ…

መስሏቹሀል! ከወያኔ ይሄንን የምትጠብቅ ጅልና ተላላ ዜጋ ካለህ ሳትበላ ብትነቃ ይሻልሀል!! በብዙኃን መገናኛዎች የቀረቡት አንዳንዶቹ ዝግጅቶችማ የምር ወያኔ የተፀፀተና ለመታረምም የቆረጠ የሚያስመስል ነው፡፡ ወያኔ ሲናዘዝ “በትውልዱ ላይ ለደረሰው የሞራል (የቅስም) ዝቅጠት፣ የሀገር ፍቅር ስሜት መጥፋት፤ በኢትዮጵያ ሕዝብ (ብሔረሰቦች) መሀከል ለተፈጠረው የእርስበርስ ጥላቻና መለያየት፣ በጠላትነት መፈላለግ መተያየት፣ የኢትዮጵያዊነት ስሜት መጥፋት ወዘተረፈ. ተጠያቂው እኔ ነኝ!፣ ይህ ውጤት እንዲፈጠር አድርጌአያለሁ!፣ ሕዝብን እንዲህ በቁጣ ተቃውሞውን እንዲያሰማ ያደረገው ለዘመናት ሲደርስበት ሲፈጸምበት የቆየው የአሥተዳደር በደል ነውና ተቃውሞውን ማሰማቱ አግባብ ነው!” ወዘተረፈ. እስከማለት መድረሳቸውን ላየ ከልብ መፀፀታቸውንና መመለሳቸውን ለማመን ሳይዳዳው የሚቀር አይመስለኝም፡፡

ቆይ እንጅ እኔ የምለው! የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄንን ማኅበራዊና የማንነት ቀውስ ወያኔ እንዲያስመዘግብ፣ በደል እንደጉድ እንዲፈጽም ነበር በ26 ዓመታት ውስጥ አምስት ጊዜ በተደረጉ እንከን የለሽና ዲሞክራሲያዊ (መስፍነ ሕዝባዊ) ምርጫዎች በተደጋጋሚ ሲመርጠው የኖረው ማለት ነው??? መቸም እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ለዚህ ካልሆነ ደግሞ ወያኔ የኢትዮጵያ ሕዝብ በአምስቱም ምርጫዎች “እኔን መርጧል!” ማለቱ ሐሰት ነበር ማለት ነው፡፡

እኔ የሚገርመኝ ወያኔ ይሄንን ሁሉ ቀውስና ኪሳራ በማስመዝገቡ በሕዝብ እንደተጠላና እንዳልተፈለገ ካወቀው ታዲያ ይሄ ሁሉ ከሆነ በኋላም እንዴት ሆኖ ነው “አሁንም እኔው እቀጥላለሁ እንጅ ለሌላ አላስረክብም!” ሊል የሚችለው? እስከፈለገበት ጊዜ ድረስ ረግጦ ቀጥቅጦ እንዲገዛ ሥልጣንን በዓጽመ ርሥትነት ለወያኔ ማን ነው የሰጠው? የኢትዮጵያ ሕዝብ “በቃኸኝ! አልፈልግህም!” እያለ ባለበትም ሰዓት መንግሥት የመቀየር፣ ሌላ የማየት መብትና ሥልጣን የለውም ማለት ነው? “ሌላ እፈልጋለሁ!” ማለት አይችልም ማለት ነው? ማን ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ይሄንን ሊለው የሚችለው? በምንስ አግባብ? አገዛዙ በስብሻለሁ! እያለም ሕዝቡ እንደበሰበሰ እያወቀ በበሰበሰና በገማ አገዛዝ የመገዛት ግዴታ አለበት ማለት ነው? እኮ በምን አግባብነት ያለው ምክንያት? በበሰበሰና በገማ አሥተዳደር የመገዛት ግዴታን በዚህ ሕዝብ ላይ የጣለበት ማን ነው? ሕዝብስ ይሄንን ጉዳይ በጸጋ መቀበል አለበት?

ተላሎች ሆይ! ይሄ የሰሞኑ የብዙኃን መገናኛዎች አቀራረብ እውነተኛና ዘላቂ እንዳይመስላቹህ! በምንም ተአምር ከወያኔ ይሄንን እንዳትጠብቁ! ወያኔን ከእኩይነት መለየት ማጥራት ማለት ከሰልን አጥቦ ከጥቁረቱ እንደማጥራት እንደመለየት ማለት ነው! ይቻላል እንዴ? ይህች ይህች የሰሞኑ መቅለስለስ ከጭንቀት የመጣች ናት እንጅ በፍጹም በፍጹም ከመፀፀትና ከመታረም የመጣች አይደለችም!

እንደምታስታውሱት ከዓመታት በፊት “ወያኔ አፍጥጦ ከመጣበት ጥፋት ለመዳን የማያደርገው ነገር፣ የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ ነግሬያቹህ ነበረ፡፡ ወያኔ ፍላጎቱን ለማሳካት፣ ጥቅሙን ለማስከበር፣ ህልውናውን ለማስቀጠል ሲችል እንደወንድ ተንቀባሮ ተጀንኖ በማስገደድ፤ ሳይችል ደግሞ እንደውሻ ከእግር ስር ተልከስክሶ ተልሞስሙሶ በመቅለስለስ ህልውናውን ለማስጠበቅ፣ ጥቅሙን ለማስከበር የማያደርገው ነገር የለም! ብያቹህ ነበረ፡፡

የኦባማ አሥተዳደር ከወያኔ ጋር ሲበሻቀጥ ከርሞ በቅርቡ በተደረገው ምርጫ ፈጽሞ ፈጽሞ  ያልጠበቀው ሽንፈት አጋጥሞት በወያኔ እንደረከሰ ነጩን ቤተመንግሥት መልቀቁ ሞት ሆኖበት፣ ለታሪኩ አስቀያሚ ጠባሳ ሆኖበት፣ ይሄም እጅግ አሳስቦት ባለቀ ሰዓት ወያኔን አስጨንቆ ይዞታል፡፡ ወያኔ እንደምንም ብላ ጥር ለመድረስ ጥረት እያደረገች ነው፡፡ “ጥር ላይ ግን የኦባማ አሥተዳደር ለተመራጮቹ ለነ ትራምፕ ሥልጣኑን አስረክቦ ተጠራርጎ ውልቅ ስለሚል ከዚያ በኋላ ምንም ሊያመጣ አይችልምና አሁን አንዳንድ ትዕዛዞቹን እየፈጸምኩና በዚያ እየደለልኩ ጥር ላይ ልድረስ!” በማለት እየዶለተች ትገኛለች፡፡ የኦባማ አሥተዳደር ምን ያህል እንደሚሳካለት እናያለን፡፡

እንግዲህ ወያኔ እያሳየው ያለው መቅለስለስና መለማመጥ እነ ኦባማ ስለጨከኑባት አማራጭ ስላጣች ነው እንጅ የተጠያቂነት ስሜት ወይም ተፈጥሮ ኖሯት “ሕዝቡ እምቢ! ካለ ምን አደርጋለሁ? ጨርሸ አልፈጀው ነገር!” ብላ ለሕዝብ እምቢተኝነት እጅ ሰጥታ እራሷን ስላረመች አይደለም እየተቅለሰለሰችና እየተለማመጠች ያለችው፡፡

እራሷን አዋርዳ እግራቸው ስር እንደ ውሻ እየተልሞሰሞሰች ከጎኗ እንዲቆሙ ያደረገቻቸው መንግሥታት በወራዳና ኢሰብአዊ ግፏ ትልቅ ትዝብት ላይ ስለጣለቻቸው፣ ስላጋለጠቻቸው ለስማቸው፣ ለታሪካቸው ሲሉ ጨከን ስላሉባትና ፊት ስለነሷት ነው አሁን ልትደልልና አፍጥጦ ከመጣባት ጥፋት እራሷን ለማዳን ለከት ባልነበረው ንቀትና ጥላቻ ስትረግጠው፣ ግፍ ስትሰፍርበት ከኖረችው የኢትዮጵያ ሕዝብ እግር ስር እንደውሻ እየተልሞሰሞሰች የምትገኘው፡፡ ገና ከዚህም የከፋ ጭንቅና መጋለጥ ቢያጋጥማት ያለ አንዳች ሐፍረትና መሸማቀቅ ዓይኗን በጨው አጥባ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንጀት ለመብላት “በፍጹም ምሕረት የማይገባኝ ወራዳ ወንበዴ ነኝና ፍረዱብኝ!” እስከማለት ሁሉ ልትደርስ ትችላለች፡፡ በእነሱ ቤት እነሱ ብቻ ናቸው ብልጥ እኮ!

እንጅ በፍጹም በፍጹም ወያኔ የሚማር፣ የሚመከር፣ የሚፀፀት ልብ ኖሮት ተምሮ፣ ተመክሮ፣ ተፀፅቶ አይደለም!!! ይሄ ላለመሆኑ ቅንጣት ታክል ጥርጥር የለኝም! ወያኔ ይታረማል፣ ሰው ይሆናል ብለሽ ተስፋ የምታደርጊ ቂላቂል ካለሽ ቁርጥሽን እወቂ! በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ እንደጻፍኩበት ሁሉ ወያኔ እንዳይታረም ሦስት ነገሮች ያግዱታልና ይሄንን ተስፋ ማድረግ ከንቱ ቅዠት ነው፡፡ የሚያግዱት የሚከለክሉት ነገሮች 1ኛ. የሚከተለው ርዕዮተዓለም 2ኛ. ዕኩይ ተፈጥሮው 3ኛ. ለይቅርታና ምሕረት የማይመቹ በሀገርና በሕዝብ ላይ የፈጸማቸው ግፍ፣ በደልና ክህደት ናቸው፡፡

እናም ወያኔን በተመለከተ የተለወጠና ወደፊትም የሚለወጥ፣ ተስፋ የተጣለበትና ወደፊትም የሚጣልበት ምንም ነገር የለም አይኖርምምና ምንም የሚያስቆም ወይም ወደኋላ የሚያስብል ነገር የለም! ትግልህን አጠንክረህ ግፋ! ነው መልእክቴ ወገኔ!

እስከ አሁን ድረስ “የትም አይደርሱም! ተቀጥቅጠው አጉል የትም ለመቅረት፣ ለማለቅ ነው! በከንቱ ለመጥፋት ነው!” እያልክ ሕዝባዊ ትግሉ የትም እንደማይደርስ እየለፈፍክ ዳር ተመልካች የሆንክ ያልነቃህ ዜጋ ሁሉ እባክህን ልብ ግዛና ጊዜ ሳታባክን ቢረፍድብህም ሳይመሽብህ ሕዝባዊ ትግሉን ተቀላቀል! የሚጠበቅብህንም ታሪካዊና የዜግነት ግዴታህን በብርታት ተወጣ! በየት ሀገር ነው ያለመሥዋዕትነት ድል ተገኝቶ የሚያውቀው? ሌላው ቢቀር ማንነትህ ወንጀል ተደርጎብህ በሚታወቅም በማይታወቅም የዘር ማጥፋት ጥቃቶች ተለቅመህ ማለቅህ ካልቀረ ጠላትን ተበቅሎ ማለፍ ብቻ በራሱ ለድል የሚያቀርብ ተግባርና ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሞት ካልቀረ ተዋርዶ ከመሞት ለክብሩ ለነጻነቱ ታግሎ የክብር ሞት መሞት ትልቅ ጀብድ ነው፡፡ እናም እባካቹህ ዳር ተመልካቾች ሆይ ኧረ ንቁ!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

 

ሕወሓት በወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ላይ አስከ ሞት የሚያስቀጣ ክስ መሰረተባቸው

የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በሚባል ሽፋን በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መሪነት በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች፣ ታኅሳስ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሠረተባቸው የሰሜን ጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አቶ መብራህቱ ጌታሁን፣ ጌታቸው አደመ፣ አታላይ ዛፌና አለነ ሻማ ናቸው፡፡ ከትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሰቲት ሁመራ ነዋሪ አቶ ነጋ ባንተይሁንም በክሱ ተካተዋል፡፡
ተከሳሾቹ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን የሽብር ተልዕኮ ለማስፈጸም ‹‹የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ›› በማለት ራሳቸውን አባልና አመራር ብለው ከሰየሙ በኋላ፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን የፕሮፓጋንዳ ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው ተከሳሾቹ የማንነት ጥያቄውን ሽፋን በማድረግ፣ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በተለያዩ ተንቀሳቃሽ ስልኮች በቀጥታ ተገናኝተዋል፡፡ በትግራይ ክልላዊ መንግሥትና በወልቃይት አስተዳደሮች ላይ የግድያና የአፈና ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ለወጣቶች የጦር መሣሪያ አስታጥቀዋል፡፡ የታጠቁት ወጣቶች በዳንሻ ከተማ ግለሰቦችን እንዲገድሉ፣ አፍነው እንዲወስዱና በቃፍታ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ላይ የግድያ ሙከራ በማድረግ፣ የዳንሻና ሶሮቃ መንገድ እንዲዘጋ ማድረጋቸውን ክሱ ይዘረዝራል፡፡

በክልሉ በሰሜን ጎንደር ዙሪያ በፀገዴ ወረዳዎች በደባርቅ፣ እንጂባራ፣ ወረታ፣ ደምቢያ፣ መገራ፣ በምዕራብ አርማጭሆ በመተማ ዮሐንስና ዙሪያው ተከሳሾቹ ከመጋቢት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ባስነሱት አመፅ በመንግሥትና ሕዝብ ተቋማት፣ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶችና ተሽከርካሪዎች ላይ ከ95.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ማድረሳቸውን በክሱ ተጠቅሷል፡፡ በጎንደር ከተማ በሚገኙ ቀበሌዎችም በመንግሥትና በሕዝብ ተቋማትና በተሽከርካሪዎች ላይ ከ10.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንም አክሏል፡፡

ከነሐሴ 18 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ደግሞ በምዕራብ ጎጃም በሚገኙ በባህር ዳር ዙሪያ መርዓዊ ከተማ፣ በሜጫ ወረዳ፣ በቡሬ፣ በደጋ ዳሞት አዴት ከተማ፣ በፍኖተ ሰላምና ባህር ዳር ከተማ ከ95.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንና በድምሩ ከ202 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያብራራል፡፡

ተከሳሾቹና ኮሎኔል ደመቀ ሰብሳቢ በመሆን ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ውስጥ በሚገኝ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ግለሰቦችን በመሰብሰብ፣ ‹‹የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ሊሰጠን አልቻለም፡፡ የወልቃይት ፀገዴ የማንነት ጥያቄውን ምክር ቤቱ ወርዶ ሊያየው የሚችለው ደም ሲፈስና ግጭት ሲከሰት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እዚህ ተወክላችሁ የተገኛችሁ በሙሉ ወደ መጣችሁበት ቦታ በመሄድ፣ አመፅ በመፍጠርና መንገዶችን በመዝጋት የሽብር ተግባር መፈጸም አለባችሁ፡፡ ይህንን ስታደርጉ ከእናንተም ሆነ ከመንግሥት አካላት ሰው ሊሞት ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄያችንን ይፈታልናል፤›› በማለት ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
በወረቀትና በብዕር የሚመጣ ፍትሕ እንደሌለና በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ አመፅ እንዲነሳ የሚያደርጉና የሚያስተባብሩ ሰዎችን በመምረጥና በመመልመል፣ የሽብር ተግባሩን እንዲያፋፍሙ ተልዕኮ መስጠታቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡

ተከሳሾቹ በተለያዩ አካባቢዎች ለመለመሏቸው ወጣቶች ገንዘብ በመላክ ከአዲ ረመጽ አካባቢ ጥይት ገዝተው እንዲዘጋጁ ማድረጋቸውን፣ ወጣቶችን እያፈኑ መውሰዳቸውን፣ በተለያዩ ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውንና የግድያ ሙከራ ማድረጋቸውንም ክሱ ያብራራል፡፡

በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የማንነት ጥያቄውን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ በውጭ አገር ከሚገኙት ስረበ ጥሩነህ፣ መዓዛው ጌጡና አስማረ ከተባሉት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በስልክ ግንኙነት በማድረግ የገንዘብ ድጋፍ ሲያገኙ እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል፡፡

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች በኤርትራ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በማድረግ፣ የጦር መሣሪያ እንዲገዙና በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ፀገዴ ወረዳዎች በተለያዩ አካባቢዎች መንገድ በመዝጋት እንዲፈጸም ትዕዛዝ መስጠታቸውን ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾቹ ክሱን በንባብ አሰምቷቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ የተገለጸውን የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል የተባለው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀእናለን)፣ 38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001ን ተላልፈው በመሆኑ፣ የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሠረተባቸው የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ የተጠቀሱባቸው የሕግ አንቀጾች ዋስትና ስለሚከለክሉ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የቅድመ ክስ መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡና ከጠበቃ ጋር ተመካክረው ታኅሳስ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

ዜና- ሪፖርተር

የወልቃይት ጉዳይ ለትግራይና ለአማራ – መፍትሄውስ? – ምስጋናው አንዱዓለም

ለትግራይ

ትግራይ አለማቀፍ ድንበር የላትም፡፡ እንደምንገነዘበው የትግራይ እና የኤርትራ ድንበር ያልተፈታ ችግር ያለበት ስለሆነ ለትግራይ የተረጋጋ እና ጠቃሚ አለማቀፍ ድንበር ነው ተብሎ አይወሰድም፡፡ ቢያንስ ለአሁኑ ጊዜ፡፡ ብቸኛው የውጭ መገናኛዋ ሊሆን የሚችለው የሱዳን ድንበር ነው፡፡ በሱዳን እና በትግራይ በኩል ደግሞ አማራ አለ፡፡ ያ የአማራ አገር ደግሞ ከኤርትራ ጋር ይገናኛል፡፡ ያ የአማራ አገር ክፍል ደግሞ ወልቃይት ነው፡፡ ስለዚህ ወልቃይት ለትግራይ ከውጭው አለም ጋር መገናኛ ድልድይ ነው፡፡ ይህም ማለት ወልቃይት ለትግራይ የሕይወት መስመር ናት ማለት ነው፡፡

ወልቃይት ለትግራይ የሀብት ምንጭ ነው፡፡ አማራ ሁልጊዜ ፊቱን ወደአዲስ አበባ አዙሮ ስለሚኖር ከጀርባው ማለትም ወልቃይት ላይ ያለውን የሀብት መጠን ብዙ ጊዜ ልብ አይለውም፡፡ ግን ትልቅ የሀብት ምንጭ ነው፡፡ ስለዚህ ወልቃይትን ከትግራይ መቀነስ ማለት ለትግራይ በጣም ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ያስከትላል፡፡ ስለዚህ ወልቃይት ለትግራይ የምግብ ጥያቄን አጭቃ የያዘች ናት፡፡ ይሄም ማለት ወልቃይት ለትግራይ የህይወት ጥያቄ ናት ማለት ነው፡፡

ወልቃይት ለትግራይ አማራን መቆጣጠሪያ ማማ ናት፡፡ ወልቃይትን መቆጣጠር ወደመሀል ጎንደር ለሚደረገው ዝግመታዊ የትግራይ ተስፋፊነት ቁልፍነት አለው፡፡ ወልቃይትን መቆጣጠር፣ ከዛ እየተሳቡ የመሀል ጎንደርን ምድር መውሰድ፤ የቅማነት ንኡስ ብሄረተኝነትን በመፍጠር አማራውን ለሁለት ከፍሎ ማጫረስ፣ እግረ መንገዱንም አማራን ሙሎ በሙሉ ከውጭ መገናኛው የሱዳን መስመር በመቁረጥ ጎንደርን በትግራይ ተስፋፊነት መቀየር ያስችላቸዋል፡፡ ወልቃይትን እና አጎራባች የመሀል ጎንደር ወረዳዎችን መቆጣጠር በራሱ አማራውን በኢኮኖሚ ለማዳከም አይነተኛ መሳሪያ ነው፡፡

ለአማራ

ወልቃይት ለአማራ ሁሉም ነገር ናት፡፡ ወልቃይት ለአማራ የአማራ የማንነት ጥያቄ ናት፡፡ ወልቃይት የአማራ ምድር፣ የአማራ መኖሪያ ናት፡፡ ወልቃይት ለአማራ የታሪክ ጥያቄ ናት፡፡ በታሪክ አማራ ሆና ዝንተ አለም ኖራለች፡፡ ወልቃይት ለአማራ የመሬት ጥያቄ ናት፡፡ ዝንተ አለም የአማራ ርስት ሆና ቆይታለች፡፡ ወልቃይት ለአማራ የክብር ጥያቄ ናት፡፡ ታሪኩን፣ ማንነቱን፣ መሬቱን፣ ወገኑን አስዘርፎ ቁጭ ብሎ የሚያይ አማራ አይኖርም፣ የለምም፡፡ ከሁሉም በላይ ወልቃይት ለአማራ ከላይ ከትግራይ አንጻር በተጠቀሱት ምክንያቶች የህልውና አምድ ናት፡፡ በህወሀት መዝገበ ቃላት ትግራይ ሰፍታ ተንሰራፍታ እንድትኖር አማራ መጥፋት አለበት፡፡ አማራን የማጥፊያ መሰላሉ ደግሞ ወልቃይት ላይ ነው የሚጀምረው፡፡ ስለዚህ የወልቃይት ጉዳይ ለትግራይ አማራን ማጥፊያ ወጥመድ ከሆነች ለአማራ ሕይወቱን የማስቀጠያ ጥርኝ ውሀ ትሆናለች ማለት ነው፡፡

የወልቃይት ጉዳይ መፍትሄው ቀላል ነውን?

አይደለም፡፡ የወልቃይት ጉዳይ መፍትሄ የሚያገኘው አንድ ወጥ የሆነ ብሄራዊ ጥቅም የሚያስተሳስረው ኢትዮጵያ የተባለ አገር ሲፈጠር ብቻ ነው፡፡ አንድ ወጥ የሆነ ብሄራዊ ጥቅም ያለው አገር ሲመሰረት ብቻ ነው መፍትሄ የሚያገኘው፡፡ አሁን ግን የአንድ አገር ብሄራዊ ጥቅም የሚባል ነገር የለም፡፡ አሁን ያለው በአንድ አገር ብሄራዊ ጥቅሞች ውስጥ ከአገራዊ ብሄራዊ ጥቅሞች ይልቅ የገነኑ የክልላዊ (ለወደፊት አገር የሚሆኑ) ጥቅሞች ናቸው፡፡ ህወሀት የሚሰራው ለትግራይ ክልላዊ (የወደፊት “ብሄራዊ”) ጥቅም መከበር ነው፡፡ የትግራይ ብሄራዊ ጥቅም የሚሳካው የአማራን ክልላዊ (“ብሄራዊ”) ጥቅም ወደትግራይ ብሄራዊ ጥቅም በመቀየር ነው፡፡ ከዛም አልፎ የትግራይ ብሄራዊ ጥቅም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም ላይ ይደራደራል፡፡ የኦሮሞ ፖለቲከኞችም ትግል ከዚህ ባልተለየ መልኩ የኦሮሞን ክልላዊ (“ብሄራዊ”) ጥቅም ለማስከበር የሚጥር እርምጃ ነው፡፡ ስለዚህ እስካሁን በዋነኝነት የኢትዮጵያ የፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሜዳ ላይ ሲደባደቡ የቆዩት የትግራይ ብሄራዊ ጥቅምና የኦሮሞ ብሄራዊ ጥቅም አስከባሪ ሀይሎች ናቸው፡፡ ሁለቱ በኢትዮጵያም ሆነ በአማራ ብሄራዊ ጥቅም ላይ የየራሳቸውን ጥቅም ለማረጋገጥ ነው ሲንደፋደፉ የቆዩት፡፡ አሁን መሀል ላይ የራሱን ድርሻ የሚያነሳው የአማራ ጥያቄ ወደመድረክ ብቅ ብሏል፡፡ ይሄ ሀይል ደግሞ በእነዚሁ በአማራና በኢትዮጵያ ሜዳ ላይ በብቸኝነት እየተዘባነኑ ሲፎካከሩ በቆዩት የትግራይና የኦሮሞ ብሄረተኝነቶች ላይ የራሱን ተጽእኖ ማሳረፍ ጀምሮአል፡፡ ስለሆነም የወልቃይት ጉዳይ በትግራይ ብሄራዊ ጥቅምና በአማራ ብሄራዊ ጥቅም መካከል ወሳኝ የትግል መስክ ይሆናል ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ብሄራዊ ጥቅሞች ደግሞ ወይ ይሸናነፋሉ ወይ መሰረታዊ ለውጥ ተደርጎ እርስ በእርስ ወደማያፎካክር ኢትዮጵያዊ ብሄረተኝነት ይቀየራሉ፡፡

የትግሉን ሁኔታ ስንገመግመው ግን ህወሀት የትግራይን ብሄራዊ ጥቅም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም አሳልፎ በመስጠት እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ ይተባበራል ተብሎ አይጠረጠርም፡፡ ያም ማለት የትግራይን ተስፋፊነት እና ብሄራዊ ጥቅም ፉክክር አስቁሞ ወደኢትዮጵያዊ ብሄራዊ ጥቅም መረጋገጥ ለማስቀየር የሚያስችለን እድል የለም ማለት ነው፡፡ ይህም ወደመደምደሚያው የግድ መሸናነፍ ወደተባለው የመጀመሪያው የጨዋታ ህግ ይወስደናል ማለት ነው፡፡ ትግራይ ወልቃይትን በሰላም ለአማራ አትመልስም፡፡ አማራ ደግሞ በማንኛውም ዘዴ የተወሰደበትን ታሪክ፣ ክብር፣ ማንነት፣ መሬት መልሶ መረከብ አለበት፡፡ ይሄም የሚጠብቀንን ትግል ከባድ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ስለሆነም መላው አማራ ራሱን ከወዲሁ በሁሉም ረገድ ማዘጋጀት እና ለማሸነፍ መቆም ይጠበቅበታል ማለት ነው፡፡
ከዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት

የአቶ አሰፋ ጫቦ የተባ ብዕር – ስለ ነገም ቢናገር (ይገረም አለሙ)

ይገረም አለሙ

አቶ አሰፋ ጫቦ ከጦቢያ መጽሄት ከህትመት ውጪ መሆን ጋር አብሮ የራቀን ብዕራቸው አልፎ አልፎ በድረ ገጾች ብቅ እያለ እንደናፍቆታችን ባንረካም ከማጣት ይሻል ሆኖን ሰነባብቷል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ አዘውትረው መከሰት ጀምረዋል እና እሰየው ብለናል፡፡ ግና በአብዛኛው  የእገሌ ጽሁፍ/ነገር ኮርኩሮኝ እያሉ  ብቅ የሚሉ በመሆኑ በቅርቡ ደግሞ ይህን ልጻፍ ብየ አስቤ ሳይሆን  ብልጭ ሲልብኝ ወይንም ሲልልኝ ነው የምጽፈው ብለው እቅጩን ስለነገሩን ኮርኳሪ ነገር ከጠፋ ሊጠፉ ነው ብዬ  ሰጋሁ፡፡ ለነገሩ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለተለከፈ ሰው የሚኮረኩረው አይደለም የሚያስቆጣ የሚያስቆጨው ነገር መች ይጠፋና ነው እንደዚህ ማሰቤ ብዬ ራሴን ብታዘበውም ብልጭ ሲል የሚጻፍና ታስቦ የሚጻፍ ልዩነት ስላለው ይህችን መልእክቴን ለመጻፍ ተነሳሳሁ፡፡Ethiopia's veteran activist and former Parlimentarian and Lawye

ባለፈው ሰሞን አረ ከወራት በፊት ይሆናል የአቶ ግርማ ሰይፉ ጽሁፍ ኮርኩሮኝ ነው ብለው  ተነሳስተው “ትቼው ረስቼው” በሚል ርዕስ ስለ ኢ/ር ኃይሉ (ነብሳቸውን ይማር ከዛ ወዲህ አርፈዋል) ስለ ፕ/ር በየነና ፕ/ር መረራ በጥቅል ትንሽ ፣ግን ጥልቅ መልእክት ያለው ነገር ነገሩን፡፡ ስለ ፕ/ር በየነ ደግሞ ትንሽ ሰፋ አድርገው ትውውቃቸውን፣ የሥልጣን ጥማቸውን ፣ፓርቲ አፍራሽነታቸውን ብሎም በወያኔነት መጠርጠራቸውን ነገሩን፡፡ ይህን ጽሁፋቸውን ተከትሎ አንድም ለመኮርኮር ሁለትም 25 አመት በተቀዋሚ ፓርቲ ሊቀመንበርነት ወንበር ላይ ስላሉት ፕ/ር በየነ  ነካ አድርገው ያለፉትን ሰፋ አድርገው እንዲገልጡት በመጠየቅ  “አቶ አሰፋ ጫቦ ምነው እስካሁን” በሚል ርዕስ መልእክት ብጤ ጻፍኩ፡፡ የጽሁፌ የመኮርኮር አቅም ደካማ ሆኖ ነው መሰል አቶ አሰፋ ምንም አላሉ፡፡

በአቶ አሰፋ የአጻጻፍ ይትብሀል ውስጥ ያየሁት ነገር አንድ፤  በአንድ ጉዳይ ላይ አተኩረው ያንኑ አድምተው ከመግለጽ ይልቅ በአንድ ጽሁፍ ብዙ ጉዳዮችን ነካክቶ በአንባቢው አእምሮ ውስጥ  ጥያቄ ጭሮ የማለፍ ሁለት፤ እመለስባቸዋለሁ እያሉ አንጠልጥሎ የመተው ( ሲጀመሩ ጀምሮ  እመለስበታለሁ ያሉትን አልተመለሱበትም) ዘይቤ ነው፡፡ ሶስተኛው ደግሞ ዛሬ በሚኮረኩራቸው ነገር መነሻነት ትናንት የሆነውን ያዩት የሰሙትን ወይንም ራሳቸው የተካፈሉበትን ነገር ማሳየት ላይ ነው በአብዛኛው የሚያተኩሩት፤ አንዲህ ቢሆን ይሄ ቀርቶ ይሄ ቢደረግ ከዚህ ተምረን አንዲህና አንዲያ ብናደርግ በሚል ለዛሬ መንገዳችን መስተካከልና የነገ ግባችን ከወዲሁ መስመር መያዝ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ብዙም አያተኩሩም፡፡ የእኔ የመረዳት አቅም አላሳይቶኝ ከሆነ ከወዲሁ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡

በቅርቡም “ማነህ ባለሳምንት የመሪ ወር” ተረኛ  የሚል ርዕስ ለሰጡት ጽሁፍ መነሻ ምክንያታቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሹም ሽር ቢሆንም አድምተው አልሄዱበትም፡፡ በተለመደው ዘያቸው ስለ አቶ ይልቃል ትንሽ ነግረውን መሪ መለዋወጥ እንደማይጠቅም ጠቁመው በእግረ መንገድም  አቶ ልደቱን ነካ አድርገው ፕ/ር በየነ ጴጥሮስን ጎሽመው፤ ስለ ምርጫ 97 አንስተው ብልጥ ልጅ እየበላ ያለቅሳልን ተረት አስታውሰው 90 ምናምን ድርጅት በኢትዮጵያ መኖሩን ገልጸው “አንዱ ይህም ሳይሆን አይቀርም ገሸሽ አንድል ያደረገኝ” በማለት ብዙ ጉዳዮችን ነካክተው ነው ያለፉት፡፡ አንደ አቶ አሰፋ የረዥም ግዜ ልምድ ተሞክሮና የጽሁፍ ተሰጥኦ አንጻር የተነካኩት ጉዳዮች ለትውልዱ አስተማሪ አውቆ ለተኛውም ቀስቃሽና ቆስቋሽ ለአጥፊውም መካሪ የሚሆን እያንዳንዳቸው አንዳንድ ጽሁፍ መሆን የሚችሉ ነበሩ፡፡  አቶ አሰፋ ሳይጠገብ የሚያልቀው ትረካቸው ምንም ቢጽፉ ምን አንባቢን ሰቅዞ መያዙ እሙን ነውና እንደነገሩን ብልጭ ሲልባቸው ወይንም ሲልላቸው አለያምኮርኳሪ ነገር ሲገጥማቸው  ብቻ ሳይሆን  አስበውበት ለትናንት የታሪክ ችግራችን መፍትሄ፣ ለዛሬ መንገዳችን እንቅፋት መክሊያ፣ ለነገ ራዕያችን አንድ መሆን የሚያግዝ ጽሁፍ ቢያበረክቱ ጥሩ ይመስለኛል፡፡

ወያኔ ለሀያ አምስት አመት የዘር መርዙን ሲረጭ ኖሮ አሁን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነት የሚል ዜማ እየለቀቀ ነው፡፡በአንጻሩ የዘር መርዙ ምቹ መሬት አግኝቶ የበቀለባቸው ወገኖች ዘረኝነቱን በስፋትና በከፋ መልኩ እያራገቡት ነው፡፡ ነገሩ የተፈጠው በእምነት  ሳይሆን ወንዝ ለመሻገሪያ በተቀመመ ዘዴ ቢሆንም ቦታ መለዋወጥ እየታየ ነው፡፡ ወያኔ ወደ ኢትዮጵያዊነት  አንዳንዱ ወደ ዘረኝነት፡፡ ይህም በመሆኑ  የኢትዮጵያ ችግር መፍትሄው የድርጅት ብዛት ነው የተባለ ይመስል  የጎሳ ድርጅቶች ያውም በመሬት ላይ ሳይሆን በማህበራዊ መገናኛ  ሲፈጠሩ ማደር ከዛም ርስ በርስ መናቆር ብሎም በሌሎች ላይ የቃላት አረር መተኮስ ኢትዮጵያዊነትን ማራከስ ስራ ተደርጎ ተይዟል፡፡

በዚህ ወቅት እንደ አቶ አሰፋ ያለ ሰፊ ልምድና የተባ ብእር ያለው ሰው ተፈላጊ ነው፡፡  የፈረንጅ ድርሰት እያጣቀሱ ሳይሆን የራሳቸውን ተሞክሮ እየገለጹ፣ ቃላት እያነበነቡ ሳይሆን የተግባር ማስረጃዎችን እያጣቀሱ፣ ትናንትን ከዛሬው እያመሳከሩ  የነገው ከዛሬ የባሰ እንዳይሆን ለማስተማር አቶ አሰፋ አንዱና ቀዳሚው ተመራጭ ሰው ናቸው፡፡ እናም ብልጭ ሲልባቸው ብቻ ሳይሆን አስበውና አቅደው ተከታታይነት ባለው ሁኔታ ለዛሬ ልዩነትን የሚያጠብ  ለነገ እኛነታችን መንገድ አመላካች የሆነ መካሪና አስተማሪ ጽሁፍ እንዲጽፉ አንኮርኩራቸው አንገፋፋቸው፡፡

በእኔ በኩል ኩርኮራየን ሁለት ስል ይችኛዋም መልእክቴ እንደ መጀመሪያዋ አቅመ ደካማ ሆና አቶ አሰፋ  የመኮርኮር አቅም እንዳታጣ  ኩርኮራየን ወደ ጥያቄ ልቀይረውና በቅድሚያ ማነህ ባለ ሳምንት የሚለውን ጽሁፋቸውን መነሻ በማድረግ ጥያቄየን ልሰንዝር፡፡

 አንደኛ፤ አሁኑ ያሉት ድርጅቶች ከሌላው አለም ተምክሮ አለመማመር ብቻ ሳይሆን ባለፈው 50 አመታት በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ከሆነውም አልተማሩም። ከሌላው ስህተት አለመማር ብቻ ሳይሆን ተትላንት ጥዋት ራሳቸው ከስሩትም የተማሩ አልመስለኝም። ብለዋል እውነት ነው፡፡ፖለቲከኞቻችን ከሌላው አይደለም ከደረሰባቸውና ካደረሱትም የሚማሩ አይደሉም፡፡ ሁሉም ራሳቸውን ትክክል በማድረግ በሌላው ላይ ጣት መቀሰር ነው የሚቀናቸው፡፡ ለዚህም ነው የድርሻ ድርሻችንን እንውሰድ የሚለው የአቶ አሰፋ ጩኸት ሰሚ ያጣው፡፡ ታዲያ  አንደ  አቶ አሰፋ ያሉ ዜጎች  አካፋውን አካፋ በማለት ይህን ገልጦ ገላልጦ ትውልዱ እንዲማርበት በማሳየት አለበባሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ አይነት ጉዞ አንዲያበቃ የማድረግ  ኃላፊነት የለባቸውምን?

ሁለተኛ፣  “ካህናቱ “ገዝቻለሁ!” የሚሉትም አላቸው። ይህ የሚሆነው ተመክሮ ተዘክሮ አልመለስ ያለውን ዳግም እዚያች ቦታ/ ድርጊት ድርሽ እንዳትል ብሎ ቁልፍ መቆለፍ ማለት ነው።” ብለዋል፡፡  ይህን ወደ ፖለቲካው እናዙረውና በየዘመናቱ ከፖለቲካው መድረክ የማይጠፋትን ግን የህዝቡን ትግል ሲጎዱ እንጂ አንዳች ረብ ያለው ተግባር ሲያከናውኑ የማይታዩትን ከዚህ በኋላ በፖለቲካው መድረክ ድርሽ እንዳትሉ ማለት ባይቻል እንኳን ሕዝቡ ትክክለኛ ማንነታቸውን አውቆ በእነርሱ ከመታለልና ከመደለል ራሱን እንዲያቅብ ለማድረግ አቶ አሰፋ የፖለቲካው ካህን መሆን አይችሉምን  ?

ሶስተኛ፤አሁን በፈነዳው የሕዝብ ቁጣ ሳቢያ ዛሬ ኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ “ጽንፍና መሀል” መለየት አጉልቶ የሚያሳይ መነጽር ሳያስፈልግ የሚቀር አይመስለኝም። አንዱ ይህ የመስለኛል ገሸሽ እንዲል ያደርገኝ። ብለዋል፤ ገለል ማለቱ መፍትሄ ይሆናል የህሊና ነጻነትስ  ያስገኛል? እኔ ግን ያ አጉልቶ የሚያሳይ መነጽር ርስዎ ነዎትና አይተው ያሳዩን እላለሁ፡፡

አራተኛ፤ የአሁኑ ውዝግብ ዘመነ ደርግን ያስታውሰኛል።በየቀኑም ባይሆን በየሳምንቱ አዲስ ድርጀት ወይም ስንጣቂ ተመሥርቶ ወረቀት ይበትንና ያንን አገኘው ነበር። የሚደራጅ ሳይሆን የሚፈለፈሉ የሚመስል ነገር ነበረውና “ማለቂያ የለውም እንዴ!” የሚያሰኝ ነገር ነበረው። እንዳያልቅ የለምና እንዳይሆን ሁኖ አለቀ፡፡ የአሁኑም አንደትናትናው እንዳይሆን ሆኖ አንዳያልቅ የበኩልዎን የማድረግ ኃላፊነት የለብዎትም?

አምስተኛ ፤  “ከፍተን ብናየው ? ሻዕቢያና ኦነግ” በሚለው ጽሁፍዎ ኦነግ ከኢሳይያሰ ጋር ስላለው ዝምድና አሳይተውናል፡፡ኦነግ አዲስ አበባ የደረሰው ከሻዕቢያና ከወያኔ ጋር እንደሆነ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ በአፍሪካ አዳራሽ ስብሰባ ላይ አንድ ጋዜጠኛ “ከእናነተ  ጋር ሳይሆን  ኦነግ ከወያኔና  ከሻቢያ  ጋር ነው የወገነው!” አለኝ”  ማለትዎ ኦነግ ከእናንተ ጋር ምን ውል ቢኖረው ነው ? ይህ አባባልዎ ኦነግ የተመሰረተው ርስዎ ቢሮ እንደሆነ የሚነገረውን ያስታውሳል፤   እውነት ከሆነ ኦነግ በመነሻው ምን ነበር ዓላማው? በሂደት የለወጠው ነገርስ አለ? ይህን ያህል ዘመን ለውጤት ያለመብቃቱ ምክንያት ምን ይሆን ? ወያኔ ለድል የበቃው በጎሳ ተደራጅቶ አማራን በጠላትነት ፈርጆ ነው በማለት ይህን አንደ መልካ ልምድ ወስደው በጎሳቸው መደራጀትንና ትግሬን በጠላትነት መፈረጅን የመረጡ ወገኖች   ከኦነግ ምን መማር አለባቸው ይላሉ?

ስድስተኛ ፤ ይህኛው ከጽሁፉ ውጪ ነው፡፡ ወያኔ አዲስ አበባ እንደገባ ለፖለቲካው ጨዋታ በየጎሳችሁ ተደራጁና ኑ ሲል በአንድ ጀንበር ሊባል በሚችል መልኩ ከደቡብ ወደ አስራ አምስት  ድርጅቶች ተመሰረቱ፡ ከእነዚህ አንዱ የርስዎ ነበር፤ያንን ማድረጋችሁ የወያኔ የዘር ፖለቲካ ጠንካራ መሰረት እንዲኖረው አልረዳም ይላሉ ? ወያኔ ከሀያ አምስት አመት በኋላ ዘረኝነቱ አላዋጣ ብሎት ወይንም የዘረኝነት አጀንዳውን ጨርሶ ኢትዮጵያዊነትን ማዜም ጀምሯል፤የተገላቢጦሽ ሌሎች ዘረኝነትን አክረው ይዘውታል፡፡ርስዎ  ኢትዮጵያዊነትንም አቀንቃኝ የጎሳ ድርጅትም መሪ ነበሩና ምን ይመክራሉ?

ሰባተኛ፣የሰኔው ኮንፈረንስ ተሳታፊ ነበሩ? ከሆነ በዛ ጉባኤ ተቃውሞ ያሰሙና ድምጸ ተአቅቦ ያደረጉት ፕ/ር ዓሥራት ወልደየስ ብቻ እንደበሩ ይታወቃል፣ የርስዎ አቋም ምን ነበር? ይፈጥን የዘገይ እንደሁ አንጂ ለውጥ መምጣቱ አይቀሬ ነውና ለመጪው የሥርዓት ለውጥ ከዛ የሚቀሰም ትምህርት ይኖራል?

ሰምንተኛ፤ እንደ ልምድዎና አዛውንትነትዎ ምነዋ  ስለነገዋ ኢትዮጵያ እንዴትነት በሚመከርበት መድረክ፤ድርጅቶችን ለማቀራረብ በሚጣርበት አውድ አናየዎት? አንደ አያያዛችን ካለፈውም ሆነ ከአሁኑ የነገው ይባስ የሚያሰኝ ነውና አቶ አሰፋ ጫቦን መሰል እውቀቱ ልምዱ የመጻፍ ክህሎቱ የሀገር ፍቅርና የህዝብ ወገንተኝነቱ ያላችሁ ወገኖች ድምጻችሁ ይሰማ፣ ብዕራችሁም ቀለም ይተፋ ዘንድ ከዚህ የባሰ ግዜ የሚኖር አይመስለኝምና እባካችሁ ንቁ ትጉ፡፡             ፤                            እድሜና ጤና ለሀገር ተቋርቋሪዎችና ባለውለታዎች