በህሊና – አምላክ! – ከሥርጉተ ሥላሴ

ከሥርጉተ ሥላሴ 09.01.2017 (ዙሪክ – ሲዊዘርላንድ)

„በነዚያ፡ ወራቶች፡ ኖኅ፡ ለጥፋት፡ እንደ፡ ቀረበች፡ ጥፋቷም፡ እንደ፡ ቀረበ፡ ምድርን፡ አየ። ከዚያ፡ እግሩን፡ አንሥቶ፡ እስከ፡ ምድር፡ ዳርቻ፡ ድረስ፡ ሄደ። ሄዶ፡ ላያት፡ ለሄኖክ፡ ጮኸ፡ ኖኅም፡ በሚያሳዝን፡ ቃል፡ ሦስት፡ ጊዜ፡ ስማኝ፡ ስማኝ፡ ስማኝ፡ አለ። በዚህ፡ ዓለም፡ የሚሰራው፡ ሥራ፡ ምንም፡ እንደሆነ፡ ንገረኝ፡ አለው።  እንዲህ፡ ለጥፋት፡ ቀርባለችና፡ ተናውጣለችና፡ ወይስ፡ እንሆ፡ ከእሷ፡ ጋር፡ እኔ፡ እጠፋ፡ ይሆን፡ አለው።  በዚያም፡ ጊዜ፡ በዚህ፡ ዓለም፡ ታላቅ፡ ሁከት፡ ሆነ፡ ከሰማይም፡ ቃል፡ ተሰማ።“

                     (መጸሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፲፰ ከቁጥር ፩ እስከ ፮)

እፍታ።

… እጅግ ዬሚገርመው ነገር 26 ዓመት ሙሉ ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ማኒፌስቶ ዬሴራ ዳርቻው ዬማይታወቅ ሽምጥ ሸለቆ ስለመሆኑ አለመረዳታችን ነው። ሥለዚህም ነው ትንተናችን፤ ማብራሪያችን፤ ራዕያችን፤ መርኻ – ህብራችን፤ ዬሥነ – ልቦና አቅማችን፣ መዋለ ኃብታችን ሁሉም ዬአባይ ወንዝ ዕጣ ፈንታ እንዲሆን – ዬተገደደው።

ለመሆኑ ጠንሳሾቹ ሂደታቸውና ትርፋቸው ደንበር ዬተሰራለት ነውን? ይህን ዬፍላጐታቸው ድንበር ዬለሽነት ዬሴራ ሚስጢር አይደለም ሆድ ዕቃውን ቃሉን ለማወቅ ዬተደሞ ጊዜ ዬሚያስፈልግ ይመስለኛል። ለዛ ለቃሉ ራሱ ዝግጅት ለማድረግ እንኳን ዬቻልን አይመስለኝም። ስለምን አይመስለኝም እላለሁ ነው እንጂ። እውነት ለመናገር ዬነፃነት ራዕያችን ዬሚመራው ዓውራው ዬሰው መሪ ሳይሆን ዬሞቅታ ንፋስ ነው። መሪያችን ብርጋዴር ጄኒራል ንፋስ ነው። ይህም ብቻ አይደለም። በራሱ ዬቆመ ዬፍላጎት መንፈስ ዬለንም። ወይ በኤርትራ ወይ ደግሞ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊቃናት አራባና ቆቦ በሚረግጠው ዬማዘናጊያ – ግጥግጦሽ። ለነገሩ ዬኢትዮዽያ ዋንኛ ዬፖለቲካ ዬአማካሪነት ደረጃ መቼ፤ በዬትኛው ዘመን ከኤርትራዊዎች መዳፍ ወጥቶ ሲውቅ ነው? ትብትብ።

እንኳንስ ዬባዕዳን ተስፈኞች ዬወያኔ መስራቾች ከዛ አፈንግጠናል ዬሚሉትን – ሰምተናል። ፍቅራቸውና ራዕያቸው ዬወያኔ ኃርነት ትግራይ ዬሴራው ሚሲጢር ቁልፍ አናቱ እንዲነካ – አይፈልጉም።  ውይይቱ – ትችቱ  – ስላቁ ከማኒፌስቶው ድርሽ ሳይባል ነው። ዬአንደነት ኃይሉም ቢሆን በውኃ አንሽነት ወይም በቅንነት ብቻ በማይታወቅ አዚም ወጣ ወጣ ሲባል ከግራቸው ሥር በርከክ ሲል – ይታያል። ነገም ዬዕዳ አዝመራ ለመሸከፍ – መሰናዶ። ማኽከነ!

… አሁን እያሰገረ ዬሚነሳው ዬሴራ ቃለ ምልልስ ሰለባነት ዬእኛ ዬድል ርካብ ተደርጎ – ይታያል። ዬሚታፈሰው ዬተዘራ ነገር ሲኖር ብቻ ነው። ፈቅደው ዬሚዘሩት ዬእነ አቦይ ስብኃት መርዝ ብክለት ለቀጣይ ጥቃት ምን ያህል ዝግጁ እንደ ሆን ዬማስተንፈሻና ጊዜ መብያ ሲናርዮ ነው። ዬሂደት ጊዜ ተመህፅኖው ኩልኩሎቻቸውን በአዲስ መልክ ፊት ለፊት አውጥተው በለ ሦስተኛ አማራጮቻቸውን ለቀጣይ ዬምርጫ ዘመን ማራዘሚያ ዬባትሪመሙያ ጊዜ በመሻት ነው። ሌላ ደግሞ ሌላ ዬአልጠግባይነት ዬድግግሞሽ ሴራዊ ካቴና ነው። መቼ ከታቱ ልንወጣ እንደምንችል እዮርን ብንጠይቅ ይሻላል? ምድራዊ ኃይሉማ እዬታዬ ነው። ስለምን …

ዬታላቋ ትግራይ ህልምና ዕድምታው።

„የአማራ ልሂቃን እንደሚታወቀው ከአሁን በፊት በአገር አቀፍ ደረጃ ነው መታገል ይመርጡ የነበረው፤ አሁንም ብዙዎቹ በዚሁ መንገድ ከሌሎችኢትዮጵያውያን ጋራ በአንድነት መታገሉ የሚመርጡ ይመስለኛል። እንደማነኛውም ህዝብ በውስጡ የሚኖረው ሰው ፍላጎቱና አስተሳሰቡ ስለሚለያይየሚያሰባስበው አጀንዳም እንደዚሁ የተለያየ ነው የሚሆነው። ለምሳሌ ሸዋውና በተለያየ ሀገሪቱ አከባቢ የሚኖረው የአማራ ተወላጅ ሰፊዋን ኢትዮጵያትቶ የአንዲት ወረዳ፣ የወልቃይት ጉዳይ የሚመስጠው አጀንዳ ላይሆን ይችላል፤ የወሎውም፣ የጎጃሙም እንደዚሁ። በነገራችን ላይ የጎንደሩእንቅስቃሴም ቢሆን የወልቃይት ጉዳይ ብቻ ከሆነ አጀንዳው የትግሉ ዓላማ የሚያሳንሰው ነው የሚሆነው፤ ሲጀምር የወልቃይት ጉዳይየወልቃይቶች ነው፤ በጎንደር የሚኖር አማራም በአድዋ የሚኖር ትግሬም የሚያገባው ነገር የለም።  ሁሉንም ዜጎች በእኩልነት የሚያይ መንግስትሲመሰረት ኗሪው ህዝብ ነው ወዴት መካለለል እንዳለበት የሚወስነው። ስለዚህ የህዝቡ ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜመፍትሄ የሚሰጠው ጉዳይ ነው የሚሆነው። ከዚያ በኋላ ወልቃይት ወደ ጎንደር ይካለል ወደ ትግራይ ይካለል እንደ ጥንቱ አማርኛ እና ትግርኛየሚናገሩ የአከባቢው ዜጎች በሰላም የሚኖሩበት ምድር ይሆናል።http://www.zehabesha.com/amharic/archives/66974

„ምክር ይፈለግ!    [አስራት አብርሃም] October 4, 2016“

ይህን በምልሰት መቃኜት ግድ ይላል። ይደገም – ይሄን በምልሰት መቃኜት ግድ ይላል። ስለምን? ይህን መመለስ ዬቻለ ዬፖለቲካ አቋም ነገኢትዮዽያን እንደ ሐገር ማስቀጠል – ይቻላል። በስተቀር ኢትዮዽያ ብቻም ሳይሆን ኤርትራ ራሷ አደጋ ላይ – ትወድቃለች። ምን አገባኝ ማለት አይቻልም። ዬመካከለኛው አፍሪካ ሰላም ሆነ ዬአፍሪካ ቀንድ ሰላም ለኢትዮዽያ እጅግ መሰረታዊ ነውና። ይሄ ጂዖ ፖለቲካል አቀማመጥ ያስጣቸው ኃይሎች በተለያዬ ዘመናት ፈተና ሲያመርቱበት ዬኖሩበት አመክንዮ ነበርና። ዬተሳካላቸውን አሳክተው – ዬቀረው ደግሞ በአቶ ሂደት ዬሚታይ ይሆናል። ምልክቶች ዬሉም ማለቴም አይደለም። ጉጥ ጉጥዥ ብለው ዬወጡ ጉልህ ምልክቶች አሁንም አሉ። ወደ ኋላ እመለስበታለሁ።

ዬማከብራቸው ጸሐፊ አቶ አስራት አብርሃም  ዬወልቃይትና ዬጠገዴን ጉዳይ አሳንሰው ሲመለከቱት ሃይ! ያላቸው ዬለም። ስለምን? እኛ ከመሰረታዊ ዬችግራችን ማህጸን ውስጥ ስላልሆን absent። በሚገርም ሁኔታ በተለይ ዬአንድነት ኃይሉ በዚህ አቋም ላይ ስምምነት ያለውም ይመስላል። ይህም ብቻ አይደለም ዬጣሊያን መንግስትን ፍልስፍና መስጥሮ በቅብ ዬተሞሸረው ዬወያኔው ህገ መንግሥትና ዬወያኔው ዬቋንቋ ፌድራሊዝም ዬሚማረኩበት፤ ሰፍ ዬሚሉበት ክታባቸው ሆኖ እያዬነው ነው።

ኢትዮዽያ ዬጥቁር ህዝብ ዬነፃነት ዓርማነቷን ያጨለመው፤ ዕሴቶቿን ዬበከለው፤ ዬቅኝ ግዛት መንፈስ ሰርግና መልስ ዬሆነው ዬነ ቤቶ ሞሶሎኒ ምስል ቅኝትን ሁነኛ ቀልብ ለመዋስ ፈቃድ ያገኘም – ይመስላል። ዬኢትዮዽያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ቅኝ ምኞትን አፈር ያስጋጣ ዛሬም ደም እዬተገበረበት መሆኑ እዬታወቀ ለደሙ ዋጋ ነገ ለድምፅ ይቀርባል ሲባል ቅጭጭም – አላላቸውም። ገፃቸው ሲለዋወጥ – ዬአባቶቹን ወኔ ሲጠራ – አላዬንም። አቦ ሌንጮ ለታ ዬአሜሪካን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ተለዋዋጭ ባህሬን ለምሳሌ አቅርበዋል። ዬአሜሪካ ሐገር ዬመሆን አፈጣጠር ከኢትዮዽያ ጋር በፍጹም ሁኔታ ዬሚመጣጠን አይደለም። ኢትዮዽያ እኮ ዬሰው ልጆች መፈጠሪያ ናት። ከተለያዬ ሐገር ዬፈለሱ ዬተለያዩ ሀገር ዜጎች በግጥምጥሞሽ ዬመሰረቷት ሀገር አይደለችም። ስለዚህ ዬራሷ በሆነ ተፈጥሮ ዬበቀለ፤ ዬጸደቀ፤ ያፈራ ልዩ ዬሆነ ማንነት ያላት ሀገር ናት። ኢትዮዽያ ቅጂ አይደለችም። ኢትዮዽያ ዬትውስት ሀገርም አይደለችም። ለዚህም ነው ዬውጪ ኃይሎች ሁሉም እሷን እንደተራበ ኑሮ፤ በኃይል አልሳካለት ሲል አጋድሞ ሁለመናዋን ዬሚያርድ ዬውስጥ ሽንክ አሸኖችን ማምረት ዬጀመሩት። ስኬታቸው ይሄ ነው።

ዬአቶ አስራት አብርሃም ጹሁፍ ራሮት ዬተማጸነው ዬወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ዬእኔ አይደለም ተብሎ እንዲገፋና፤ ዬታላቋ ትግራይ ህልም በቂ ጊዜ አግኝቶ በተንሰራራ ብቃት እንዲንሰራራ ዬፈለጉት አብይ ዶግማም ይሄው ነው። ይህ እያለሳለሱ ዬመሰርሰር ሴራዊ ጉዞ በተቋም ደረጃ ዬኤርትራው ቅልብ ቲፒዴኤምም ዬሚጋራው ነው። ዙሪያ ገባው በሴራ በታጠረ ጉዞ ዬነፃነት ራዕይ ለማስፈጸም ከፍላጎቱ አናት መነሳት ያልተቻለበት በአንድም በሌላ አዟሪቱን ጥሶ ዬመውጣት ዬአቅም አለመመጣጠን ራዕያችን ስለሚንጠውም ነው። አቅም ያለበትን ቦታ ብቻ እያሸተተ ዬሚባዝነው ራዕያችን ሁልጊዜም ዬጥገኝነቱ ሰለባ ይሄው ነው። በባዶ እጅ ወረቀትና ቀለም ያልቃል። ከዛን ሜዳ ላይ ዬበቀሉትን ለመቧጠጥ ሽምያ – በሽሚያ፤ ፍጻሜው ሃቅን አብዝቶ መፍራት። ዋናውን ችግር ከነመፍትሄዎቹ ዬመድፈር አቅም – መሟሸሽ። ዕውነቱ ይሄው ነው። ሌላው በጋብቻ፤ በግል ግንኙነት ያሉ ግንኙነቶችም ወደፊት እንዳንራመድ መንገዱን ግድግድ አድርገው ዘግተው ዬጠላታችን ብልት በውል እንዳናውቅ ግርዶሽ ሰርቶበታል። እርግጥ ነው ከዛ ያመለጡ ዬአንድነቱ ልዑል ዬአሉላ አባ ነጋ ልጆች ዬሉም ማለት ግን አንችልም። ጥቂቶችም ቢሆኑ አሉን – ዬኛዎቹ – ማገሮች።

„አንቀጽ 39“ ለማን?

„አንቀጽ 39ማንም ዬማይደፍረው ለሌላው እንደ አሞሌ ጨው ለእቃ ዕቃ ጨዋታ መላሾ ዬተሰናዳ፤ ምን በመሰለ ፍሬም ግድግዳ ላይ ለምስል ዬተለጠፈ ፖስተር ነው። እንዲመለክበት፣ እንዲሰገድበት ዬተሰራ ዬወረቀት ሃውልት። „ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን ዬማላይ ዓይነት።“ ለታላቋ ትግራይ ግን ዬህልም መፍቻ ተቀማጭ ወርቅ። ኢትዮዽያ ውስጥ ያለው ውጥረት ሀገራዊ መልክ ኑሮት መናድ ከጀመረ፤ ዬማሌሊት ፓርቲ ህልመኛ ተጨማሪ ዬመቶ ዓመት ዬቤት ሥራ ሰጥቶ ወደ ሌላ ምዕራፍ ሽው። ዬቀቀለውን – ቀቅሎ፤ ያጠነዛውን አጠንዝቶ፤ ያሻገተውን – አንሸዋርሮ።

አሁን ግን በተደላደለው ዬኢትዮዽያ ሥልጣነ – ግዛት አቅም ላይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በኢትዮጵያ ኪሳራ መዲናውን በሁሉም ዘርፍ በብቃት አሳምሮ እያደራጀ ነው። ዬወያኔ ሃርነት ትግራይ ዬግብጽ ራዕይ ህልም አባይን ከነምንጩ ዬመቆጣጠር ራዕይን ገና ማኒፌስቶውን ሲነድፍ ያሰላው መዳረሻውነው። ለዚህ ደግሞ ሊንኩ ዬአማራ መሬት ነው። ይህን ተውት ነው ዬሚሉን እነ አቶ አስራት አብርኃና – መሰሎቻቸው።

አባይን ከነምንጩ ብቻም አይደለም ዬሥነ ልቦና ወረራው ሌላው ዬጥቃት ጎል ነው። ትግሪያዊነትን ማስፈን።   ይህ ደግሞ ዬአማራን ህዝብ ማንነት ጠፍጥፎ እንደገና ፎርም ማድረግ፣ በዲያጎናል ሆነ በትረያንግል ። ይህ ለሌላውም ማህበረሰብም ቢሆን በረጅሙ ዬታሰበበት ዬሩቅ ህልም ነው። ሌላው በአማራ መሬት በዓለም ዬባሕልና ዬቅርስ ውርርስ በዩንሲኮ ዬተመዘገቡት ዬስሜን ፓርክና ፋሲል ግንብ ለወያኔ ረመጡ ነው።  ሌላም ዬሩኃ ቀደምትነት፤ ዬላሊበላ ቅርስነት ዬሥልጣኔ ዬእኛነት መሰረታዊ አመክንዮ ሌላው ዬትግራይ ሃርነት ትግራይ ዬበታችነት ስሜት ጥንስስ ነው። ይህ ዬኢትዮጵያ መመኪያ ዬሆኑ ጥልቅ ዬሁለመናችን መለያ ነው። ስለዚህም ዬታላቋ ትግራይ ህልም መከነ ማለት ሃብታችን በቋሚነት ዬእኛነት መግለጫ ሆነው ይቀጥላሉ ማለት ነው። ይህንን ባለቤቱ እራሱ ህዝቡ እዬታገለበት ቢሆንም ግንዛቤውን ለማደፍረስ ባሉ ዕሳቤዎች ዙሪያ ግን ጉዳዩን ዬእኔ ብሎ መያዝ ዬኢትዮዽያን ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቅ ማለት መሆኑ እኩል ግንዛቤ ዬለም። ሂደቱ ብልህነት ዬጎደለው ነው። ግቱም ሥልጣኔ አልቦሽነት ይመስለኛል። ቅንነቱም በተቀናቃኝነት ስሜት ዬማዬት ዝንባሌ ይታያል። በሌላ በኩልም „አውቆ ዬተሸሸገ ቢጠረቱ አቤት አይልም“ እንዲሉም … ዬትግሉ ስትራቴጂና ታክቲክ አቅጣጫ ዬትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይን ማኒፌስቶ አንጎል መመርመር ያስፈልጋል። ይሄ ዬውሉ ውል ነው።

እስኪ ዬአማራ ዬተባለውን ዓርማና ዬወያኔ ሃርነት ዓርማ ዬሰራ አካላትን ጎን ለጎን አድርጋችሁ እዩት ህልሙን አሳምሮ ይፈታላችኋል። ከዛ ሽንጥ ለሽንጥ ወለጋን ይዞ እስከ ጋንቤላ ዬሚደርስ ግዛት ይስፋፋል፤ በወሎ በኩልም እስከ አሰብ አይቀሬ ጉዞ ይኖራል፤ በአፋርም ዓዋሽ አናቱን፤ ዛሬ ትግረኛ ተናጋሪ ናችሁ ተብለው ዬዘር ማጥፋት ዬታወጀባቸው ልክ እንደ ወልቃይት ጠገዴ፣ ራያና ዘቦ ሁሉ ነገ ደግሞ ትግረኛ ቋንቋ በሚናገሩት ኤርትራውያንም ቢሆን ዬይገባኛል ጥያቄ ማን ያውቃል? አዲስ አበባ ክ/ ከተማ መባሉ – በደረሱት ቦታ ስም ዬሚቀይሩት ያለ ምክንያት አይደለም። ዬረጅም ጊዜ ዬመስፋፋት ህልማቸው ዬመመሪያው ቡራኬ ነው። ይህ ሁሉ በኢትዮዽውያን አንጡራ ሃብት ለነገ ዬታላቋ ትግራይ ራዕይ አስኳል ነው። ዬወያኔ ዬአልጠግብ ባይነት መስፋፋት አይደለም ለኢትዮዽያ ለመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ዬጤና ቀጠና አይሆንም። ስለሆነም ሥሩ ዝርግ ላልሆነ ዬተቆለፈ ሳጥን ዬሚመጥን ዬግንዛቤ ደረጃ ፊደል መቁጠር ገና አልጀመርንም። መሪያችን ዬወቅት አውሎ ብቻ ነውና።

ሰራዊቱም ይህንን ልብ እንዲለው ማድረግ አልተቻለም። ስለምን? ዬራዕያችን ጠቅላይ አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ንፋስ ነው። ሞቅ ደመቅ ሲል ለሠራዊቱ ጥሪ ሲደረግ – አዳምጣለሁ። ነገር ግን ከጠላት ወረዳ ዬሴራ አንጎል ያልተነሳ ፍላጎት መቼውንም ተደማጭነትንም ሆነ አሸናፊነትን ሊያመጣ አይችልም። በዓዋጅ ሥርዓት አይፈርስም በዓዋጅም ሥርዓት አይገነባም። ሁሉን ዬቀደመ፤ መጪውን ያሰላ፤ መሰረታዊ ችግሩ ላይ ዬተነሳ ብቻ ለድል ይበቃል። በዚህ ላይ ማራኪና ሳቢ፤ ሃሳብ ሰብሳቢ ዬህሊና ተግባር – አልተሰራም። እርግጠኛ ዬሚያደርግ ግልጽነትም ዬለም። እዬተንጠባጠቡ ዬሚወጡ መረጃዎች ዬሚያመለክቱት ይህንኑ ነው።። አሸናፊ ሃሳብን አቅዶ በተከታታይ ሥራ ላይ ማዋል አልተቻለም። ሠራዊቱ ራሱ ዬሙያው ሥነ – ልቦናዊ ማንነት ዬራሱ ስላለው ከምንጩ ካልሆነ ዬሚሆንም አይደለም። በወታደራዊ ሥነ-ምግባሮች ተፈጥሮ ውስጥ መኖር ዬሚጠይቁ በርካታ አመክንዮች አሉት። ሳይንስን ባሻጋሪ ዬራስ ሃብት ለማድረግ ማለም ጋዳ ይመስለኛል። አሁን ያለው ዬነፃነት ትግል ሙቀት ሩህ ዬተንጠለጠለው ህዝብ ከመከፋቱ ብዛት በተነሳ፤ ህዝቡ በራሱ ጊዜ ከፈቀደው ዬመስዋዕትነት ሙቀት መግቦት ዬፈለቀ እንጂ፤ በራስ ፈጠራና ጥረት ዬተገኜ ዕሴት እንብዛም ነው።

ስለሆነም ዬአማራ ተጋድሎ መርህ ከአናቱ ከችግሩ አንጎል መነሳቱ ደመመን ዬተጫነውን ዬተስፋ መስመር አቮሎ ሁኖለታል። ዬአማራ መሬት ለጥቃትም – ለማሸንፍም ሊንክ ነው። ቢገባን! ዬማዬውና ዬማደምጠው ግን ዬዘበጠ ጉድን ነው። ይህንን ስለሚያውቁ ነው አቦይ ስብኃት እንደ ገና ህውሃት ዬሚንሰራራ ስለመሆኑ ዬሚተርኩልን። ዬትኛውም ዬፖለቲካ ድርጅት ያልደፈረው ዕውነት እንዳለ ያውቃሉ። „በአማራ መቃብር ላይ“ ብለው ሲነሱ አማራ ከሞተ ኢትዮዽያዊነት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ – አሳምረው ዬተሰጣቸውን ዬባንዳነት ዬቤት ሥራ ያውቃሉ። ስለሆነም ነው 40 ዓመት ሙሉ አማራውን ሲጨርሱት ዬኖሩት። እሱም ውሉ በላላ ዬአንድነት ኃይል መዋለ ንዋዩን፤ ህይወቱን ሲገብር ዬኖረው። ዛሬ ግን ትናንት ዛሬ አይደለም። ስለዚህም አማራው በተነሳ ማግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያወጣ ወያኔ ተገደደ። ምዕራብውያን ሊደነግጡ ይገባቸዋል። ጡጦው መጨመታተር – ጀመረ። ግድ ዬሚላቸው ነገር ከመጣም በማርክ ልዩነት መሰሉን ሊያደራጁ – ይገደዳሉ። ኢትዮዽያ እኮ ስሟ እራሱ ገናና ነው። መንፈሱም ኃይል አለው።

አሳዛኙ ዬክህደት አዟሪት – ዬፊት ለፊት ጠንቅ። 

አውሮፓ ኮሚሽን ግንዛቤና ዬኢትዮዽያ ወቅታዊ ዬፈተና ዕይታ አያያዝ ወጣ ገብነት …..

(„MOTION FOR A RESOLUTION“)

European Parliament resolution on the situation in Ethiopia (2016/2520(RSP))

በተመስጦ ሁኜ – አነበብኩት። ተስፋዬ ከብዶትም – አዬሁት። ነገም ተክዞ – ተመለከትኩት። ህይወት ዬዕቃ ዕቃ መጫዎቻ ስለመሆኑም – ተደመምኩበት። ዬብልሃቱ መፍቻ ዬዓውራ በር ቁልፍ ዬእርቀቱ ዲካ – ለካሁበት። ትልልፋንና ክህደቱንም ያመጣው ስለመሆኑም – አስተዋልኩበት። ውስጤን አብዝቶ – መረመረኝ። ዬት ላይ እንደቆምኩም ከተስፋዬ ጋራ መፈታተሽ እንዳለብኝ – አስተማረኝ።

ባለቤት ለሌላቸው ግን ዬዕንባ ማህበርተኛ ዬሆኑ ዬሀገሬ ዬኢትዮዽያ ሴቶች እዬሞቱ – እዬታሰሩ፣ እዬተደፈሩ፣ በጭካኔ እዬተደበደቡ፤ በአረመኔዎች ልጆቻቸውን እዬተነጠቁ፣ ልጆቻቸው በመርዝ እያለቁ፣ ልጆቻቸው እዬታደኑ፣ ትዳራቸው እቤታቸው ውስጥ በገዳዮች – እዬተገደሉ፤ እነሱም ሁሉንም መከራ እዬተቀበሉ እነሱን ወክለው ለታሰሩ ሴት ፖለቲከኞች፣ ሴት አክቲቢስቶች እንኳን አስተዋሽ – አልተገኘም። በሌላ በኩል ያን ያመሰለ ዬገዘፈ ፈተናን ያስተናገደው „ዬድምፃችን ይሰማ“ መከራም እንደ ዋዛ ነገር – ተዘሏል።

ዛሬ ሞቅ ደመቅ ላለው ጭብጨባ ባጃቢነት ዬታጨው – ዘሩ እንዲጠፋ ታውጆበት ሌትና ቀን ከጠላቶቹ ጋር በመፋለም ላይ ዬሚገኘው ዬአማራ ተጋድሎና እስከ 20,000 ሺህ ታሳሪ አለ ዬሚባልለት ዬ35,000,000 -40,000,000 ዬሚጠጋው ተጋድሎም ውሾን ያነሳ ውሾ – ሆኖል፤ ዬተዋህዶ ግማድም ባለቤት ዬለሽነቱ ተስተውሏል። ዬዛ ሳተና ወጣት ፖለቲከኛ ዬአቶ አንዶአለም አራጌ፤  ዬወቅቱ ዬጎንደር አብዮት ዬአማራ ተጋድሎ ሁነኛም ዬኮነሬል ደመቀ ዘውዴ ጉዳይ እንዲሁ ተዘንግቷል ወይንም ሥሙ እንዲነሳ አልተፈለገም።  በ8 ገጽ ውስጥ 9 ጊዜ ኦሮምያና ዬኦሮሞ ማህበረሰብ ተጋድሎ በሰል ባለ መልኩ፤ ጠንክሮና ጎልቶ ዬአድማጭን ቀልብ በሚስብ መልኩ  – ቀርቧል። ይሄ በብቃት ባለቤት ያገኘ አመክንዮ ስለመሆኑ ለአውሮፓ መንግሥታት በቀዳሚነት ቀርቧል። ትልቁ ዬቤት ሥራ በዚህ ዘርፍ ተሰርቷል። ማለፊያ! በሌላ በኩል ዬወልቃይትና ዬጠገዴ ዬአማራ ዬማንነት ጥያቄም ዝር ያልተባለበት ጉዳይም ነው። ዬስቃይ፤ ዬጭቆና፤ ረገጣም ዬእንጀራ ልጅ ሆኖል።

በተጨማሪ ኡጋዴ 2 ጊዜ 1 ጊዜ ጋምቤላ ተጥቅሰዋል። ዬኮንሶ ጉዳይ ከአንባ ጊዮርጊሱ ጋር ተመሳሳይ ነው።  በውጪ ሀገር  በሱዳን ታጣቂዎች ነውዬዘር ማጥፋት፤ ዬጅምላ ጭፍጨፋ ዬተካሄደባቸው። በልዩ ሁኔታ ሊታይ ዬሚገባው ጉዳይ ነበር። እሱም ባለቤት አላገኘም። ከቁጥርም አልገባም። ለእኔ ዬታዬኝ ዬተስፋችን መጠጊያ ሃሳብ በአንድ እግር እጣት ዬቆመ መሆኑን ነው። ዬአውሮፓ ኮሚሽን ፓርላሜንት በኦሮሞና በሌሎች ዬኢትዮዽያ ክልሎች እያለ ነው፣ ቅድመ ዕሳቤው ዬሚያልፈው።

መረጃውን ለአውሮፖ ዬመገቡት አካላት „ዳሩ ሲደፈር ማህሉ ዳር መሆኑን“ ያስተዋሉት አይመስለኝም። ቤተ መንግስት ወይንም ከአራት ኪሎ ያለፈ ራዕይን ሁለ አቅፍ በሆነ መልኩ ለማሰብ ገና ልጅ ዬሆነ ዕሳቤ እንዳለ ተገንዝቤበታለሁ። አብሶ ዬሴቶች ጉዳይና ዬአማራ ማህበረሰብ ጉዳይ ዬትሜና ዬተወረወረበት ጉዳይ አልገባኝም። ቢያንስ በወያኔው ግዛት ዬተደፈረው 2.4 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ መጥፋት እንደ አብይ አጀንዳ አለመያዙ ዬጉዳዩን፣ ዬጉዟችን አብሮነት አደጋ ላይ ዬሚጥለው አንኳር አመክንዮ ይመስለኛል። አማራ ዬሚል ቃል እንዳይገባ በጣም በጥንቃቄ ዬተሰራ ይመስላል „ዬነፃነት ኃይሉ“ እንደሚሉን።

ለነገሩ ዬጎንደር ማህበርም አማራ ዬሚለውን መድፈር ተስኖት „ዱር ቤቴ ካሉት አርበኞች (የነጻነት ታጋዮች“) ዬደንቆሮ ጩሆት መልሶ መላልሶ“እንዲሉ ባለፈው ሳምንት አንድ ዘገባ – አስነብቦናል። ሊንኩን መጨረሻ ላይ እለጥፋለሁ። እሱም ከዚህ ክህደት ማጥ አላመለጠም – እንደ ማለት። ለዛሬ ይፈለጋል። ለነገ ስንብትን – ይጠብቅ። መናጆነት ጥብቅና ዬመቆም አቅሙ ምክነት ዬጨረፈበት ዬጸጸት ዕዳ ነው።

እጅግ ዬማከብራችሁ ዬሐገሬ ልጆች ….

አውሮፓ ኮሚሽን ለዓለም ህዝብ ልቡ ሆኖ ሳለ፤ በበዛ ሁኔታ ዬኢትዮዽያን ችግር ለመፍታታ ከተዘጋጀው ዬመነሻ ሃሳብ ስነሳ ዬሴራ ድር እያደራ መሆኑን – ተመልክቼበታለሁ። በተለዬ ለአማራ ፤ ለኦርቶዶክስና ለእስልምና እንዲሁም ለሴት ኢትዮዽውያን ዬተስፋ መንፈስን ዬሚሰለስል ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ዕምነት ሰቆቃና ስደት አመክኖአዊ ዕድምታው ምንም ነው። እንደ ዜጋ በደሉ በነዶ መልክ ቀርቧል። ግን ሥሩን አልደፈረውም። ዬአንድ ጎሳ ዬበላይነትንና ጨቋኝነት አልተብራራም። ይሄም ዬመረጃ አቅርቦቱን ሰላላነትን ያመለክታል። እርግጥ ነው በሰባዕዊነት ከሚንቀሳቀሱ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችም ጋር አብሮ ዬመስራቱም ሂደት ላይ አቅም ያነሰን ይመስለኛል። ለአውሮፓ ኮሚሽን አንዱ ዬመረጃ ፍሰት እነሱም በመሆናቸው።

ዬሆነ ሆኖ ከአውሮፓ ኮሚሽን ጋር ተቀራርበው ዬሚሰሩትም ቢሆን ልጅና እንጀራ ልጅ እንዳላቸው ብቻ ሳይሆን፤ አጋጣሚ ከተገኜም ዬነገ ዕጣ ዬወሳኝነት አቅም አቅጣጫም ጠቋሚ ይመስለኛል። ነገም እያረሩ መትከን። እያለቁ መፍለስ እጮኛ እንዲሆን ይለፍ ያገኜ ይመስላል። ስለሆነም  ከማን ጋር ስለምን እንደተቆመ  – በርጋታ፣ በጥሞና፤ በማስተዋል፤ በብልህነት መመርመር – ይኖርብናል። በተጨማሪም ዬአውሮፓ ኮሚሽን ውሳኔ ዛሬ ባለበት ዬስደተኛ ጫና ምን ሊወስን እንደሚችል ማሰብ ያለብን ይመስለኛል። ሌላው ሀገር አለው እኛ ግን ዬለንም። አማራው እንደ ኩርድሽ ህዝብ ብን ብሎ እንዲጠፋ በህግ ደረጃ እዬተሰራበት ባለበት በአሁኑ ወቅት አውሮፓ ኮሚሽኑም በዚህ መስመር እንዲሄድ ቦይ – ተቀዶለታል። ለነገም ዬታጨልን መድረሻ አልባነትን ይሆን? መርምሩት የሀገር ልጆች።

ምን ይደረግ?

„ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ወጪት ጥዶ ማልቀስ“ ከመሆኑ በፊት ጉዳዩ በቀጥታ ዬሚመለከታችሁ አካላት በመረጃና በፋክት ዬተደገፈ በቀጥታ ደብዳቤ መፃፍ ለአውሮፓ ኮሚሽ ያለባችሁ ይመስለኛል። ካለ ቀነ ቀጠሮ። ያዬሁት ያጋደለ ጭብጥ ነው። ዬወደፊት ዬኢትዮዽያ ዕጣ ፈንታ ችግሮቿን በእኩልነት ሊፈታ በሚያስችል ዝንባሌ ላይ አይደለም። እርግጥ አሁንም በተደራጀ ሁኔታ ጉዳዩ ባለቤት አግኝቶ ዬተሟላ፤ ዓይን ዬሚከፍት እርብርብ ከተደረገ ማስተካከል፤ ሚዛኑን እንዲጠብቅ ዬሚቻል ይመስለኛል። አብሶ ባለቤት ለሌላቸው ግዙፍ ዬተጋድሎ ገድሎች ዬተጨበጠ ፋክት ስላለ – በሩን ማስከፈት ዬሚያስችል አቅም ማመንጨት ዬሚያስችል – ይመስላል። ነገር ግን ፍጥነት ይጠይቃል። „Action is everything“ ፍጥነት!  ዬዛሬ ተኝተህ በለኝ – ዬነገ ዬመንታ ዬምጥ ቀን ነውና። ዬተስፋ ጉዞ ዬጨበራ ተዝካር ከመሆኑ በፊት – ድረሱለት። እባካችሁን! ዬብል ግብር እዬተሰናዳ ነውና።

ዬስንጥር – ብጥር

ክህደትን – መንጥር።

ኢትዮዽያን ከማንኛውም ጥቃት ማዳን ማለት ይሄ ነው። ለሞጋች አምክንዮ ሞጋች ሃቅን አቅርቦ ገደሉን ደልድሎ ብቃትን መውለድ ግድ ዬሚል ይመስለኛል። ዬውጪ ሀገር ኢትዮዽያዊ ድርጅቶችም ተግባራት ይሄው ነው። ቢያንስ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ፈር ዬለቀቁ ዕሳቤዎችን መልክ ማስያዝ።መሸነፍ በማይቻል ነገር ላይ አይጎረብጥም። በሚቻል ነገር ላይ መሸነፍ ግን አደራ በላነት ነው። ለሚሊዎኖች ዬኢትዮዽያ ዕናቶች ዕንባ ጥብቅና መቆም ዬጽድቅ መንገድ ነው። ዬህሊና አምላክም  – ያግዘናል።

እንደ መቋጫ።

እርግጥ ነው ዬአውሮፓ ኮሚሽን ጥቅል ዬሆኑ ችግሮችን አላነሳም ማለት አይቻልም። ነገር ግን ዬአትኩሮት መመጣጠን አይታይበትም። በዋናነት ሊታዩ ዬሚገባቸው ጉዳዮች እኩል እውቅና አላገኙም። ስለዚህም ዬጎደለው ወይንም በሲሶ ዬሚታዩ ጉዳዮች ሙሉ አቅም ኖሯቸው እኩል አድማጭ እንዲኖራቸው ለማድረግ ጥረትን አቀናጅቶ በትጋት መተግበር በእጅጉ ያስፈልጋል። ጥረቱ ተከታታይነት ያለውም ሊሆን ይገባል። ችግሩ ከውስጣችንም ዬነፈሰበት ዬፍላጎት ድር እንዳደራበት ማሰብ ዬተገባ ይመስኛል። ለኢትዮዽውያን ከኢትዮዽውያን ዬሚቀርበው ዬጥናትና ዬምርምር አጋላጫዊ ዬወያኔ ዬአገዛዙ ዬአንድ ፓርቲ መዋቅራዊ ዕድምታና ለነጮች ዬሚቀርበው ዬመረጃ ፍሰት ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ ባህካል ዬውጫሌ ውል ዬአንቀጽ 17 ዓይነት ዬድብብቆሽ ጨዋታ ዓይነት ነው ዬሆነብኝ።

ዬአውሮፓ ኮሚሽን ዬሚያምነው በህብረ ብሄር ፓርቲ (በኢህድግ ) ጭቆና እንዳለ እንጂ በትግራይ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስለመሆኑ አይደለም። ይህ ዬለብዮሽ ጉዞና ሲናሪዮ ትርፍና ኪሳራው በውል ሊመረመር ይገባል ባይ ነኝ። ማንን ለማስታመም እንደታለመ ግልጽነትም ቀጥተኝነትም ይጎድለዋል።ይሄ አሁን ያለው አካሄድ ለጊዜያዊ ሹም ሽር ዬሥልጣን ሽሽግሾ ሊጠቅም ይችላል። ዘላቂ መፍትሄ አምንጭነቱም ሆነ ዬቋሚ ተስፋ ብራ አንባርነቱ ግን በዕምቅ ኢጎና ዬግል ዝና ዬተናጠ ነው። ስለምን? በችግሮች ተፈጥሮ ላይ ዬድፍረት አቅም አናሳነት ስላለበት። ደም ማነስ አለበት። ዬህሊና አምላክን ትዕዛትንም ትልልፍ አለበት። ለአክባሪዎቹ ቆራጣ ዬርህራሄ አንጀት አልፈጠረለትም። ይህብቀጠናውን በትክክልብ ያልመረመረ መንፈስ ዬአውሮፓ ኮሚሽንን ዬዕውቅና ሀብል ለማጥለቅ ሲያደባ በእጁ ዬነበረ ሀገር በቀል ወርቅ እዬቀለጠ መሆኑን ያሰበበት አይመስልም። ከዛስ ምን? … ከዛማ „ዬፈሰሰ ያልታፈሰ“ ይሆናል። አቤቱ አድነን ዬህሊና አምላክ። ህሊናችነንም ወደ ሃብቱ መልስልን አሜን! እንዲህ ዬተስፋዬና ዬራዕይ መቦርቦር ለነገ ዬቃሬዛ ጉዞ ይሆን? ስጋቴ ጆንያ ሙሉ ነው። ክብር ማህበረሰብ ፍቅርም ዬወንዝ ሽታ ነበር።

ዬጎንደር ህብረት እና አማራነት ዬጎባንነት ጉዞ ….

„ሕወሓት የአርበኛ ጎቤ መልኬ ቤተሰቦች ጋር የሚያሸማግሉትን ላከ“

http://www.satenaw.com/amharic/archives/28476

እግዚአብሄር አምላክ ከአደራ በይነት ያድነን! አሜን!

ኃላፊነት ዬሁሉም ኃላፊነት ነው።

መሸቢያ ጊዜ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s