እውነት እውነት እላችኋለው ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚችል ምንም ኃይል የለም!!! – ከተማ ዋቅጅራ

የመሸ ሌሊት እንደሚነጋ  የሚጠራጠር የለም። በማታ ጨረቃ በቀን ደግሞ ፀሐይን እንደሚወጣ ለደቂቃም የማያምን ከቶውኑ የለም። ምክንያቱም ጨለማን እና  ብርሃንን የሚያፈራርቃቸው የሰው ልጅ ሳይሆን ፈጣሪ ስለሆነ ሳይዛነፍ ውእደቱ ስለሚከናወን። ታዲያ  ኢትዮጵያ  የማን አገር ሆነችና  ነው የፈለገው ተነስቶ ሊያፈርሳት የሚችለው? ብዙዎች ታሪኳን ለማጠልሸት ተነስተው ለመገነጣጠልም ተነስተው ነበር ግን አልቻሉም ለምን ይመስላችኋል? ባላት የጦር መሳሪያ ብዛት ነውን? ወይንስ በሃብት ብዛት ነውን? ወይንስ በሌላ በምድራዊ ኃይል ነውን? አይደለም።  ኢትዮጵያ እስከዛሬ ተከብራ እና ታፍራ የቆየችው ሃገረ  እግዜአብሔር ስለሆነች ብቻ ነው። ይህ በመሆኑ ሊጥሏት ያሰቡት በሙሉ ወድቀዋል፣ ሊያጠፏት የተነሱት በሙሉ ጠፍተዋል፣ ሊበታትኗት የሚመኙም በሙሉ እነርሱ ተበትነው ይቀራሉ እንጂ ኢትዮጵያ አትበተንም።

ስለኢትዮጵያ መፍረስ የሚመኝ ከጥንት ጀምሮ  ብዙ ቢሆኑም አንድ ሁለት አሁን ካሉት ላንሳና ጥቂት ልበል።

አቶ ኩማ ደመቅሳ በአንድ ወቅት ይታማሉ አቶ ኩማ ኦሮሞ ሳይሆኑ ትግሬ ናቸው የሚል ነገር ሲነገር አቶውም የመለሱት መልስ ( የኔን ኦሮሞነት የማትቀበል ኢትዮጵያ ሺ ቦታ ትበጣጠስ) የሚል ነበረ መልሳቸው በጣም አሳፋሪ መልስ ነው። ኢትዮጵያ የመቶ ሚሊዮን ህዝብ የሚኖሩባት አገር ናት። የአንድ ሰው ማንነቱ እንዲህ ነህ ስለተባለ ስለኢትዮጵያ  መፍረስ ይነግረናል። ይህ ግለሰብ ምን ያህል እራሱን እና  ስልጣኑን ከአገር እና  ከህዝቡ በላይ እንደሚወድ ይታያል። እንደነዚህ አይነቶቹ ናቸው  ሃላፊነት የማይሰማቸው ትልቅ  ሃላፊነት ያለበትን ቦታ በመያዝ ስለአገር መበተን እና  መፍረስ በስልጣን ወንበር ተቀምጠው የፈለጉትን በመናገር አገር እና  ህዝብን ለከፋ  ችግር የሚዳርጉት።

ሌላው በሰሞኑ አቶ  ስብሃት ከተናገሩት ጥቂት ላንሳና  ላብቃ

( አሁን  ያለንበት ፈታኝ ነው ከ97ቱ የአሁኑ  ይከፋል) ይህ ማለት ኢህአዴግ በ97ቱ የምርጫ  ዘመን ከፍተኛ  አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው እንደነበረ የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ  ትክክለኛ  ህግ ያለባት አገር ብትሆን ኖሮ  የኢህአዲግ  የስልጣን ዘመን  በ1997 ማብቃት እና  ወደ ሌላ  የስልጣን ቅብብሎሽ  በተገባ  ነበረ። ግና አልሆነም ባለው በሳሪያ  እና ስልጣን በመጠቀም የህዝብን ድምጽ   በኃይል  በመንጠቅ የታሪክ ጠባሳ  ጥለው አልፈዋል በሰላም የስልጣን ሽግግርንም ገድለውታል። ስለዚህ ይሄንን የህውአት የበላይነት ሽንፈትን በኃይል በማፈን ለግዜውም ቢሆን ስልጣናቸው እንዲቀጥል ሆኗል።

የአሁኑ  ይከፋል ያለውን በሁለት መንገድ አየዋለው

የመጀመሪያው በ97ቱ የምርጫ  ዘመን ኢህአዴግ  በሁሉም የምርጫ  ጣቢያዎች በመላው ኢትዮጵያ  በሚያስብል ከ95% በላይ  ታላቅ ሽንፈት ቢገጥመውም  ያላሰጋው  ከሁሉም አቅጣጫ ህዝብን ከህዝብ የማለያየቱ ስራ  ተሰርቶ ነበርና  አማራው የኦሮሞ ጠላት ኦሮሞ የአማራው ጣላት፣ ለደቡቡም፣ ለኡጋዴኑም ለጋንቤላውም ህዝብ እርስ በራሳቸው እንዳይተማመኑ የመከፋፈል ስራ ተሰርቶ  ስለነበረ ሁሉም  አንድ ሆነው በመነሳት ለህውአት አደጋ ሊሆን አይችልም የሚለው እሳቤአቸው በወቅቱ የተነሳውን የህዝብ እንቢተኝነት በዚህ መከፋፈል ሊቀለብሱት ችለዋል። አሁን ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደ ጠላት የቆጠረው ህውአትን ብቻ  ስለሆነ  እና ሁሉም  በአንድነት ጦሩን ወደ እነሱ ስላነሳ ያሁኑ ይከፋል አለ።

ሁለተኛው እና  ዋንኛው በአሁኑ ግዜ  ህውአትን እየተፋለመ  ያለው ሙሉ የኢትዮጵያ  ህዝብ ሆኖ የሚታገለው ደግሞ  እንደ  97ቱ በባዶ  እጁ ሳይሆን መሳሪያ  ታጥቆ  በመሆኑ የዘንድሮ  አደጋው  ከፍ ያለና አይቀሬ ለውጥ የሚያመጣ ትግል ውስጥ የተገባበት በመሆኑ እና ዘርን ከዘር ብሄርን ከብሄር አጋጭተን የሚለው ሃሳብ በመክሸፉ ሁሉም  ኢትዮጵያዊ መሳሪያውን ወደ  ህወአት በማዞር በሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ  ጥቃቶች እየተሰነዘሩበት እና  ሽንፈቶችን እያስተናገደ በመሆኑ በቅርቡ ህወአት  ሊያስተዳድረው የሚችል የኢትዮጵያ  መሬት ሊኖር እንደማይችል የተገነዘበው ስብሃት የዘንድሮው አደጋ ለህወአቶች የመጨረሻቸው እንደሆነ በመረዳቱ ነው የአሁኑ ይከፋል ያለው።

ሌላው ደግሞ  አቶ ስብሃት እንዲሁም ሌሎቹ ኢህአዴግ ችግር ውስጥ ሲገቡ ኢትዮጵያ  ትፈርሳለች ህወአት ችግር ውስጥ ሲገባ የትግራይ  ህዝብ ይጠፋል የሚሏት ፈሊጥ ምንን ያመለክታል ካሉ እንዲህ ነው።

ኢህአዴግ ማለት ኢትዮጵያ፣ ህውአት ማለት የትግራይ ህዝብ የሚሏት አገላለጽ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል ሆኖም የማያውቅ ነው። ኢህአዴግ ብለው ከመሰባሰባቸው በፊት ኢትዮጵያ  ለሺ ዘመናት ነበረች ኢህአዴግም ካለፈ በኃላ ትኖራለች፣ ህወአት ብለው ለትግል ከመሰባሰባቸው በፊት ለሺ ዘመን የትግራይ ህዝብ ነበረ  ህውአትም ካለፈ በኋላም ይኖራል። ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ መፍረስ ጋር ህወአት ከትግራይ መጥፋት ጋር የሚያገናኙት ኢህአዲግ በምትለዋ ጭንብል ህወአት እንዳትገለጽ እና ህወአት በምትለው ጭንቢል በትግራይ ህዝብ ስም ስልጣናቸውን እስከመጨረሻው ለማቆየት የትግራይ ህዝብን አገልጋይ ወይንም አጋር ሆነው መኖር አለባቸው ብለው ስለሚያስቡ ነው። ነገር ግን በትግራይ ህዝብ ላይ ሊመጣ የሚችለውን ከፍተኛ  አደጋ  ምንም ሳይመስላቸው የስልጣን ግዜአቼውን ለማራዘም በመፈለግ የትግራይ ህዝብን መደበቂያ ህዝቡን ለከፋ  አደጋ በመጋበዝ ላይ ናቸው።

ግና  እውነቱ በኢትዮጵያ  ምድር ህወአት ይጠፋል …. አዎ ይጠፋል። ነገር ግን የትግራይ ህዝብ ግን አብሮ አይጠፋም። ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ  ይጠፋል ….. አዎ ይጠፋል። ነገር ግን ኢትዮጵያ አትጠፋም ምክንያቱም በእግዜአብሔር የተመረጠች በአባቶቻችን ደም የጸናች አገር እንጂ ማንም ግለሰብ ቅዠቱን በመናገር የምትፈርስ አገር አይደለችምና ነው።

ሳጠቃልለው እውነት ይዘገያል እንጂ ሁል ግዜ አሸናፊ ነው። ኢትዮጵያ ደግሞ  እውነት ናት ምክንያቱም አገረ  እግዚአብሔር ስለሆነች ማንም ተነስቶ ሊያፈርሳት ከቶውን አይቻላቸውም። ኢትዮጵያን ሊያፈርስ የሚነሳ  እና  የሚመጣ እራሱ ይፈርሳል ሊያጠፋት የሚመጣም እርሱ እራሱ ይጠፋል ምክንያቱም በኢትዮጵያ  የሚመጣ እንኳን ሰዉ ምድሪቷም ተዋጊ ናትና። አበቃው!!!

ከተማ  ዋቅጅራ

10.01.2017

Email- waqjirak@yahoo.com

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s