ከየት ተነስተን ያለንበት ደረስን? [ክፍል ፬] – አቻምየለህ ታምሩ

አቻምየለህ ታምሩ

እ.ኤ.አ. በ1960 አ.ም. የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርት የነፍስ ወከፍ ድርሻ ከዩናይትድ ስቴትስ አጠቃላይ የነፍሰ ወከፍ ድርሻ [GDP per person or GDP per capita relative to the United States] አኳያ ሲነጻጽር 1/ 32 [አንድ ሰላሳ ሁለተኛ] ነበር። እ.ኤ.አ. በ2016 አ.ም. የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርት የነፍስ ወከፍ ድርሻ ከዩናይትድ ስቴትስ አጠቃላይ የነፍሰ ወከፍ ድርሻ አኳያ ሲታይ ግን ወደ 1/ 56 [አንድ ሀምሳ ስድስተኛ] ወርዷል።

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. እስከ 1974 አ.ም. ድረስ የ14 ወር የውጭ ምንዛሬ ክምችት [forign currency reserve] ነበራት። የዛሬዋ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ክምችት [forign currency reserve] ግን የሁለት ወር ብቻ ነው። ሁለት ወር የሚደርሰውም በራሸን ነው።

የወያኔው ተላላኪ ግዑዙ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የወያኔዋን ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት «ቻይናና ኮርያ አጋጥሟቸው ነበር» ካለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር ሲያነጻጽር ሰማነው።

ከሁሉ በፊት አንድ የአገር ጠቅላይ ሚኒስትር ነኝ የሚል ሰው «ኮርያ» የሚባል አገር እንደሌላ አለማወቁ አሳፋሪ ነው። በአለም ካርታ ሰሜን ኮርያና ደቡብ ኮርያ እንጂ የሚባሉ ሁለት አገራት እንጂ ኮርያ የሚባል አገር የለም። «ኮርያ» በሚል የሚጠራው የኮርያ ልሳነ ምድር [The Korean Peninsula] እንጂ እንደ አንድ አገር የውጭ ምንዛሬ ክምችት ያለው ኮርያ የሚባል አገር የለም። እንደመሰለኝ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ «ቻይናና ኮርያ አጋጥሟቸው ነበር»ሲል መናገር የፈለገው ስለደቡብ ኮርያ መሰለኝ። ይህ ማፈሪያ ደንቆሮ «ቻይናና ኮርያ አጋጥሟቸው ነበር» ስላለው የውጭ ምንዛሬ እጥረት አንድ ተጨማጭ ማስረጃ አቅርብ ቢሉት ከጌታቸው አሰፋ ወይንም ከሳሞራ የኑስ የደንቆሮ ምክር በስተቀር ሊጠቅሰው የሚችለው ማስረጃ የለውም።

በውጭ ምንዛሬ ክምችት ችግር የወያኔዋ ኢትዮጵያ አይደለም ከቻይናና ደቡብ ኮርያ ጋር ልትወታደር በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ከነበረችዋ ኢትዮጵያም ጋር እንኳ ልትወዳደር አትችልም። የድንቁርናው ብዛት ግዑዙ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ Agricultural Development Led Industrialization በሚለው የደንቆሮው መለስ ዜናዊ የጥፋት ፍልስፍ የደቀቀችዋንና ራሷን መመገብ ተስኗት ሩብ የሚሆነውን ህዝቧ በርሀብ አለንጋ የምታስገርፈውን ኢትዮጵያን import substitution and export led industrialization ብለው እድገትና ልማት ጀመረም ለአመታት የሚሆን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከነበራቸው ቻይናና ደቡብ ኮርያ ጋር የሁለት ወር የማይበቃ የውጭ ምንዛሬ ያላት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ የነጻጽራል። የአለም ባንክን ዳታቤዝ ላገላበጠ ቻይናም ሆነ ደቡብ ደቡብ ኮርያ ለአመታት የሚሆን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ነበራቸው። የውጭ ምንዛሬ ክምችት እድገታቸውም እጥፍ ድርብ [exponentially] ነበር። ደንቆሮው ኃይለ ማርያም ግን ይህንን የሚያውቅ የሌለ መስሎት ሊያታልለን ይዳዳዋል። ድንቄም!

ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነንኝ እንዲሉ፤ የአመታት የውጭ ምንዛሬ የነበራቸውን ቻይናና ደቡብ ኮርያን የወያኔዋ ኢትዮጵያ ካጋጠማት የውጭ ምንዛሬ እጥረት ጋር ሲያወዳድር አጠቃላይ ምርት የነፍስ ወከፍ ድርሻዋ ከዩናይትድ ስቴትስ አጠቃላይ የነፍሰ ወከፍ ድርሻ [GDP per person or GDP per capita relative to the United States] አኳያ የተሻለ ደረጃ ላይ የነበረችዋ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴዋ ኢትዮጵያ ለአመታት የሚሆን የውጭ ምንዛሬ ክችምት እንደነበራት የማናውቅ መስሎት በጭንቅ ያውም በራሸን ለሁለት ወር የሚሆን የውጭ ምንዛሬ ብቻ ያላትን የወያኔዋ ኢትዮጵያ ሊያንቆለጳጵስ ስለማያውቀው ነገር ይዘባርቃል። ኢትዮጵያ ኃይለማርያም ደሳለኝን በመሰሉ ሰው መሳይ ግዑዞች ከስራለች።

ከቻት ከአለም ባንክ በተገኘው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያን፣ የኮርያንና የቻይናን የውጭ ምንዛሬ ክምችት የዘመናት አዝማሚያ [trend] ለጥፌያለሁ። ደቡብ ኮርያ፣ ቻይናና የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴዋ ኢትዮጵያ ያላቋረጠ እጥፍ ድርብ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እድገት ሲያሳዩ የወያኔዋ ኢትዮጵያ ግን በወያኔ ድንቁርናና ዝርፊያ ቆርቁዛ ስትድህ እዚህ ደርሳለች። በግብርና ስራ እየዘመነችና በኢንዱስትሪ እየጎለበተች የነበረችዋ ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ እድገቷ ተገትቶ የድሀ መፈልፈያ ጎረኖ ሆናለች።
አቻምየለህ

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s