ወግ እድገት  ወይስ የእድገት ኮፒ – በነጋ ደምሴ 

እድግት ይሚባለው ነገር የሚሰጠው ትረጓሜ እንደየ ሀገሩ ባህል፣ ቋንቋ እና የአኗኗር ሁኔታ በቃላት፣ ሃረጋት ና በዓ.ነገረ ቢለያይም እንኳን ሃሳቡ እና የመጨረሻ አንድምታወ ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን፣ የመጨረሻድምዳሜዉም ከነበረው መሻሻል ማደግ እንደሆነ ሊካድ የማይገባው የአደባባይ ሀቅ ነዉ።   ይሄውም እድግት በቴክኖሎጅ፣ ባስተሳሰብ በመሰረተ ልማት፣ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ በማህበራዊ ህወት፣ በሚድያ እና  በመሳሰሉ ነገሮች ከነበረበት መሻሻል ሲያሳይ አና በጥራቱም በይዘቱም ከነበረው በልጦ ሲገኝ እደገት አለ ማለት እንችላለን

“ቢዮንድ ኢኮኖሚክ ግሮውዝ” የሚል አንድ መጣጥፍ ሲተነትነው በቂ የሆነ የትምህርት፣ የጤና ፣ንፁህ እና በቂ የመጠጥ ውሃ እንድሁም እኩል የሆነ የሃብት ክፍፍል በማህበረሰቡ ውስጥ የሚኖር ከሆነ እና የሚመረተው ምርት ለተጠቃሚው በበቂ ሁኔታ ማዳረስ ከተቻለ እንድሁም ተጠቃሚውን እና የሚመረተውን ምርት ማመጣጠን ከተቻለ፣ ሀገሪቱ ለሰራ የተመቻቸ የሰራ እድል መፍጠር ከቻለች፣  የስራ አጥነት በሃገሪቱ ካልተስፋፋ፣ ወዘተ እያለ እድገት የሚባለው ነገር መለኪያወቹን ያስቀምጥልን እና እኒህን ባግባቡ ያሟሉ ሃገሮች አደጉ ልንል እንችላለን ይላል  ሌላው “ማሪም ዌብስተር” የተባለ ዌብሲት  የአንድ ነገር ከነበረበት የመሻሻል የማደግ  ሂደት ነው   ነው ይለዋል  በዚህ መሰረት ለምሳሌ እድገት በመሰረት ልማት ዘርፍ ያለውን ብንመለከተው  አንድ ሀገር የተሟላ መሰረተ ልማት አላት እምንለው ከላይ ያሉትን የመጠጥ የመብራት የሆቴል የትራንስፖርት የጤና እና የመሳሰሉት ነገሮች በጥራትም በብዛትም በፊት ከነበረው ሻል ብለው ሲቀርቡና ከነበሩት በልጠው ሲገኙ እንጅ በሳምንት አንድ ጊዜ እንደቀናቶች የምትምጣ ውሃ ሲኖር፣ እንደፀሃይ መውጣትና መግባት በናፍቆት የሚጠበቅ መብራትን ይዞ ፣ ማታ ተሰርቶ ጠዋት የሚፈርስ መንገድ እየሰሩ፣ ሆስፒታል ገንብቶ ዶክተር የለም ፣……….እያሉ እድገት ነው የምንል ከሆነ እድገት የሚባለው ትርጉም ጋር ይጣረስብን እና የእድገት ትርጉሙ ይጠፋብናል ይህም ኦርጅናል ና ኮፒ እንደሚባለው ማለት ነው።

የሃገራችንን እድገት ለምሳሌነት ብነወስድ በተለያዩ ሚድያወች እያደገች እንደሆነ ይነገርላታል ውነት ነው ማደጓና ከነበረችበት መሻሻሏ የአደባባይ እውነታ ነው ነገር ግን ያደገችበትን ሁኔታ ስናይ ብዙ ጥያቄወች ይመጡብናል ። ማደግ ማለት ውነት መንገድ መስራት ብቻ ይሆን ወይስ የውሃ ቧንቧ መዘርጋት ነው?  የመብራት እና የኔትወርክ  መስመር ዘርግቶ  ቢጠፋ ቢጠፋ የማይሰለቸው እየተባለ ሲቀለድ ኢትዮጲያ ከሆነ መብራትና ኔትወርክ ነው  እየተባለ ማሾፊያ መሆናችንስ የሚመለከታቸው የሀገሪቱ ባላደራወች ያውቁት ይሆነ? በርግጥም ብዙ መንገዶች ተሰርተው የማይገናኙ የነበሩ ቦታወችን አገናኝተዋል ነገር ግን የጥራታቸው ሁኔታ አይነሳ ነው ተሰረተው አንድ ክረምት እንኳን ሳያሳልፉ የሀገሪቱን ሃብትና መዋለ ንዋይ እላያቸው ላይ ካፈሰሱ በኋላ  እነዳልነበሩ  ይሆናሉ።

በተለይም ይሄ ሁኔታ ያፍሪቃ መድናን እምታክል  አድስ አበባችን መከሰቱ ህመም ነው  ጣሊያን ያኔ ሃገራችን በወረረ ጊዜ አላማውን ለማሳካት የሰራቸው መንገዶች  እና ድልድዮች ብዙ አስርት አመታቶችን ተሻግረው ዛሬም ጣሊያን የሰራው እየተባሉ ምንም ሰይፈርሱ እናያለን። እኛው ለኛው ለትውልድ ትውልድ ይተላለፋል እያልን የምንሰራቸው መንገዶች ግን ለትውልድ መተላለፋቸው ቀርቶ እኛን እኳን ማሳለፍ አልችል ብለዋል። ከናካቴው መንገድን ጣሊያን ይስራው እንጅ ፣”ጣሊያን አገናኘኝ ከዛማዶ መንደር ክረምት ሲገባ ሳላያት እንዳልቀር” ተብሎ ሲዘፈንለት  ተሰርቶ ሳያበቃ የፈረሰው የአሁን ጊዜ መንገዳችንስ ምን ይባል ይሆን? ነው አሁን አሁን በሃገራችን የመንገድ ሀይ ኮፒ ገባ ይሆን?  ከአድስ አበባችን የማያልፍላቸው መንገዶችን ለአብነት የቤቴል አለም ገና እና የአቃቂ ካሊቲ መንገዶች ማንሳት ይቻላል  ስም ይወጣ ከቤት ይከተል ጎረቢት እንድሉ የአቃቂ ካሊቲን መንገደ ከማሰልጠኛ አንስቶ እስከ ቶታል ድረስ አያልፍልሽ የሚል ስም ወጥቶለታል። እንደውም ቆየት ካለ የወደፊት መጠሪያው እንዳይሆን ያስፈራል።  እውነት ግን ተሰርቶ ሳያበቃ የሚፈርስበት ምክናየቱ ምን ይሆን?  በርግጥም የከባድና ቀላል የሰውና የፈሳሽ ጭነት መኪኖች መግቢያ ኬላ መሆኑ የታወቃለል። ቅሉ ግን ይህ አይደለም  በእውነት ግን  በየጊዜው ለማስጠገኛ እየተባለ የሚወጣው ወጭ ምን ያክል ይሆን? መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ወደዚያ ሂዶ ያውቅ ይሆን ችግሩንለመፍታትስ ምን እየተካሂያደ እንደሆን የሚመለከታቸውአካላት ጋር ይነጋገር ይሆን? የሚመለከታቸው አካላትስ ስለመንገዱ ጥራትና ብቃት ተሰርቶ ሲያበቃ እንደት ነው የጥራት ማረጋገጫ የሚሰጡት ነው ለመንገድ ስራ ጥራት ማረጋገጫ የለውም? የሚሰራውን ኮንትራክተር ፣አማካሪና እና ስራው ላይ የሚሳተፉ አካላትንስ በበላይ የሚቆጣጠር አካል የለም ማለት ይሆን? ወይስ ሸብ ሸብ አርጎ እንደሰፋለት ልብስ ሰፊ ስፌቱ ሲለቅብህ ናቶሎ ነው ነገሩ።

ወደቃሊቲ ለመሄድ ወይም ከካሊቲ ለመምጣት  በተለይ ጠዋት ከ አንድ እስከ ሶስት ማታ ከ አስራ አንድ እስክ አንድ ሰአት ከታሰበ ከመኪና እግረኛ ይሻላል ያስብላል በዛላይ በበጋ አቧራው በክረምት ጭቃው ምነው በቀረብኝ ያሰኛል ይሄ የመንገድ ጉዳይ መፍትሄ ጠፋለት እንጅ ብዙ ጊዜ በሚዲያ ሲወራ ነበር  ለአብነት ያክል በሸገር ሚዲያ በዜና፣  በወግ ፕሮግራም ቀረቦ ነበረ ነገሩ ግነ ጆሮ ዳባ ልበስ እንድሉ ችግሩ እስካሁን አለ ።  ክብር ይግባቸው እና የቀድሞው የአድስ አበባ ከንቲባ አርከበ እቁባይ ቁመው አሰሩት እየተባለ የሚሞካሹበት ከመገናኛ ዳስፖራ አደባባይ እሰከ አራት ኪሎ ያለው መንገደ ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድመ እንድሉ በጥራት መስራት እንደምንችል ምስክር መሆን ይችላል። በየቦታው የተሰሩት አስፓልቶች አንድ ክረምት ሳያሳልፍ ሲመነቋቆሩ ይሄ መስመር እስካሁን ተበላሺቶ አያውቅም።

ያኔ ቴክኖሎጅ በለለበት የተሰሩት የላሊበላ፣ ክሱም እና ሀረር ግንቦች በመቶ የሚቆጠሩ አመታቶችን አልፈው ትውልድን ሲኮሩ ቴክኖሎጅ ተጠቅመን የምንሰራቸው ያሁን ጊዜ ሰራወቻችን የጧት ጤዛ የሆኑብን ለምን ይሆን። ዘምነናል ባልንበተ ወቅት እየገነባን ባለንበት ሳንጨርሳቸው የሚፈርሱት ህንፃወቻችን እና መንገዶቻችን በሸታቸው ምን ይሆን? አባት እና እናቶቻችን እኛ ቀርቶ አለምን እሚያኮራ ስራ ሰርተው ለትውልድ ትውልድ ሲያስተላልፉልን የኛን እድሜ የማይጨርስ መጭውን ትውልድ ግምት ውስጥ ያለስገባ እኔ ብቻ ልብላው አይነት የኛ ስራስ በታሪክ ምን ተብሎ ሊፃፍ ነው? ለዚህ ጉዳይ ተጠያው ማን ይሆን? ህዝቡ፣ ባለስልጣናቱ ነዉ  ሃላፊነት ወስዶ የሚሰራው አካል? እንደው ለምሳሌ መንገድን አነሳን እንጅ የሚሰሩትን ህንፃወቻችን፣በፋብሪካ ተፈብርከው የሚወጡ ምርቶችን፣ በትምህርት ጥራቱ፣ በሆስፒታሉአገልግሎት  ከአፍሪካ አንደኛ እየተባለ የሚሞካሸው አየር  ምንገዳችን አገልግሎት ሳይቀር  ብናየው ብዙ ችግሮችን ማውጣት ይቻላል ነገር ግን መልካሙን ነገር ትንሿ ጥፋት ታጠላዋለች እንድሉ የተሰሩትን መልካም ስራወቸ ማበረታታት ሰለሚያስፈልግ እና እውቅና መስጠት ስለሚገባ ትኩረቱን መሻሻል ወደሚገባቸው እንደነ መብራት ውሃ እና መንገድ የመሳሰሉት ማድረግ ተገቢ አልን እንጅ ሌሎቹ ችግር የለባቸውም ማለት አይደለም

ሁሉም ሰው ይሄ የኔ ሃላፊነት ነው ብሎ ካልተነሳ፣ኘ ባለሰልጣናቱ የተጣለበትን አደራ ጠዋት ማታ በልቡ አስቀምጦ ለማስፈፀም ካልታተረ፣  ሃላፊነት የወሰደው አካል በሀቅ ቃሉን ጠብቆ ካልሰራ፣  ህዝቡ የኔነት ስሜት ተሰምቶተ ካልተቆጣጠረ ሀገሬን እወዳታለሁ ማለት በዘፈን ፣በድራማ ፣በፊልም በስብሰባ፣ በፓናል ውይይት በተመረጡ ቃላት ማሞካሸት ሊፈይድላ የሚችለው ነገር ትርፉ ትዝብት ነውና ሁሉም ሊተባበር ይገባል

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s