የ20ኛው ክ/ዘመን ናዚ በጀርመን ከ21ኛው ክ/ዘመን ህወሃት/ወያኔ በኢትዮጵያ ጋር ሲነጻጸር

በወልደአብ ደንቡ 

ጀርመን የተልያዩ ዘሮች(races) ፣ቋንቋዎች ፣ባህሎች ፣እምነቶች ፣ፖለቲካዊ  አስተሳሰቦች ወዘተ..የነበራቸው ስዎች እንድ አንድ ሕዝብ የሚኖሩባት አገር ነበረች፤ ከ 1933 -1945 ዓ.ም ሂትለር የፋሺዝምና የናዚዝም የፖለቲካ ርዕዮቶችን መሥርቶና ተጠቅሞ -ጀርመንን ለመግዛትና ዓለምን በቁጥጥሩ ሥር የማድረግ ሙከራ ሲጀምር- መጀመርያ ያነጣጠረው የአርያን ደም(Arayan genetic make up) የላቸውም  ወይም እነዚያ (the other) በሚላቸው ጀርመናውያን ላይ ነበር።The Tigrayan People's Liberation Front (TPLF)

ፋሺምና ናዚዝም- የአንድ ሳንቲም ፊትና ጀርባ ናቸው ፤ ሁለቱም አክራሪ ቀኝ ክንፍ የፖለቲካ ርዕዮቶች ናቸው( they are the two extreme  right wing political ideologies) :: ፋሺም ከአክራሪ የቀኝ ክንፍ ብሄርተኝነት ይፈልቃል ፤ ማለት የፋሺዝም እናት አክራሪ ብሄርተኝነት ነው

አክራሪ ብሄርተኝነት ሌሎችን ወይም እነዚያ (the other) የሚላቸውን ብሄር ብሄረሰብ አባሎችን  ክፉኛ ይጠላል ። የሌሎችን -ቋንቋ ፣ባህል ፣ታሪክ ፣ማንነትና ሕልውና ይንቃል/ይረግጣል ፣ የራሱን የማንነት እሴቶች ያሳብጣል ፤ከማንም /ከምንም በላይ ነኝ ይላል ። የአክራሪ ብሄርተኛ የፖለቲካ ድርጀት አባሎች- የእነሱ ዘውግ ወይም ዘር ያልሆኑትን ሁሉ እንዲጠሉ ስለሚታነጹ – የስብዕና  ንቃተ-ኅሊናና ሕዝባዊ ባህሪ ይጎላቸዋል – ስለሆነም የሌሎ  ችን ብሶት፣ ሃዘንና መከራ አይጋሩም ፤ የእኛ አይደለም/አይደሉም በሚሉት/ሏዋቸው የሰው ልጅ/ልጆች ላይ የሚፈጸምን ግፍ አይሰማቸውም ፤ጨቋኝና ጨካኝ ናቸው  ።

በመሆኑም የጀርመን ፋሺዝምና ናዚዝም- ዋንኛ መርሃግብር (programme) ያተኮረው -በፀረ እነዚያ በሚላቸው ብሄረስብ አባሎች ወይም ዘሮች፣ በፀረ ይሁዳዎች (አንቲ ሰሜትዝም) እና የሌሎችን አገሮች በመውረር ላይ ነበር

ስለሆነም – የአርያን ዘር ‘በተፍጥሮ የጠራ/ንጽህ ዘር’ ነው ፤ በተፈጥሮ ከተበከሉ(polluted) ዘሮች ተለይቶና እርቆ መኖር አለበት – አርያኖች በሥነፍጥረት (በባዮሎጂ) ከሌሎች ዘሮች ከሚተላለፉ – ማንኛውም በሽታ ማጽዳት/መከላከል አለብን ፤ጀርመናዊ አርያን ሃያል ዘር ነው (Germanic Aryan race is master race) ስለሆነም ዓለምን መግዛት እንችላለን ወዘተ..በሚል ቅስቀሳና ፕሮፓጋ ዳ ምክንያት – ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው -ፖሊሽዎችን ፣ሩሲያዎችን፣ ዩክሬኒያዎችን፣ ስላቮችን፣ጥቁሮችን ፣ ጅፕሲዎችን፣ሰርብዎችን ፣ሮማኒያዎችን ፣አካለ ስንኩሎችን ወዘተ..  ያለፍርድ በጅምላ ጨፈጨፉ/መነጠሩ ። የሂትለር ቀኝ እጅ በነበረው- በአዶልፍ ሃይክማን (Adolf Eichman) አዛዥነት 6 ምሊዮን አይሁዶችን በመርዝ ጋዝ አፍነው ሸረከሟቸው ። ድርጊቱ ሆሎኮስት (Holocaust) በአይሁዳዎች ቋንቋ ሸወአህ(Shoah) በመባል ይታወቃል

በ21ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያ የተፈጠረው ናዚዝም ማለት የአክራሪ የቀኝ ክንፍ ብሄርተኛ ወያኔ/ህወሃት በባንዳው መለስ ዜናዊ መሪነት-የፊንፍኔ ቤተገዢዮችን አምባ በቁጥጥር ሥር ካዋለ ማግስት ጀምሮ -በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና ደባ -ናዚዮች በጀርመን ሕዝብና በጀርመን ላይ ከፈጸሙት ግፍና ደባ የከፋ ነው ። እንዴት?

 • ከአንድ ወንዝ ወይም የዘር ኩሬ(genome) የመነጨን ፣(አንድ ብሄራዊ) – ታሪክ ፣ ባህል ፣ ቋንቋ ፣ ሥነልቦና ፣ገድል ወዘተ.. ያለን ፤ ለበርካታ ሺ ዓመታት እንድ አንድ ሕዝብ የኖርን ኢትዮጵያውያን ፤ በጎሳ ቋንቋና በጎሳ ሥነልቦና ተሽንሽነን እንድንኖር ፣እንድን ገጋደልና በጥላቻ ዓይን እንድንተያይ አድርገዋል
 • ጀግኖች ጥንቶቻችን ፣ አያቶቻችንና አባቶቻችንን ለብዙ ሺ ዓመታት ያላስደፈሩትን – አገራዊና ሕዝባዊ ልዑላዊነታችን ፣የባህር በሮቻችን ፣ የመልካአ ምድራችን ዳርድንበሮች   አስደፍሯል ፣አገር አስገንጥሎዋል ፣ ሕዝብ ከፋፍሎዋል ፣ የባህር በር አልባ አድርጎናል ፣መሬቷ ቆራርሶ ለጎረቤት አገርና ለሩቅ ባዕዳን ሽጠዋል  ወዘተ ።

የግብረ ሰናይነት መተክልና የአገሮች ልዑላዊነትን ሕግ የጣስ ቢሆንም -የጀርመኑ ፋሽስቶችና ናዚዮች ጀርመንን ለማስፋፋትና ለማተለቅ ተዋጉ እንጂ-የጀርመንን  ልዑላዊነት ለማስደፈር ፣ የጀርመንን ዳር ድንበር ለመቆራረስ/ለመሸንሽን ፣የጀርመንን የባህር በር ለማስወሰድ ፣የጀርመንን ብሄራዊ ቋንቋ ለማሳነስ ፣የጀርመንን ታሪካዊ ቅርሳ  ቅርስ ለማጥፋት  ወዘተ.. አልተነሱም ፣አልተዋጉም ፤ፖሊሲ አላወጡም ። በዚህ ምክንያት ነው  – ወያኔ/ህወሃት ከጀርመን ፋሽስቶቻና ናዚዮች የከፋ ነው  ያልኩት/የምለው ። አስተውሉ – ከእነዚህ  ግዙፍ ከናዚዮች ታሪክና ለሃያ አምስት ዓመታት ደጋግመን ከሰማነው እኮይ/መሰሪ የወያኔ ታሪክ መቀንጨብ የፈለኩበት ምክንያት ፤ ላስተላልፈው ከፈለኩትን መልዕክት ጋር ስለሚዛመድ ብቻ ነው ( for being contextual with this article`s message)

 • ፋሽስቶችና ናዚዮች – የጀርመን አርያን ዘር በስነፍጥረት የጠራ/ንጹህ ዓለምን መግዛት የሚችል ሃያል ዘር (race) ነው እንዳሉ ሁሉ – መለስ ዜናዊ ትግሬ ወርቃማ ዘር ነው ፣ ከዚህ ከወርቃማ ዘር በመፈጠሬ እጅግ በጣም እኮራለሁ ብሎዋል ፤ ማለት ሌሎች የኢትዮጵ   ብሄረሰቦች ሁሉ ከብር ወይም ከነሃስ ስለተፈጠሩ ለእኛ ለትግሬዎች መገዛት አለባቸው ለማለት የተጠቀመበት ቋንቋ እንደሆነ ተረድተናል ። ሌሎች ቁንጮ የወያኔ ገዢዮቻችንም እኛ ትግርረዎች ካልገዛናት ኢትዮጵያ ተበታተናለች ማለታቸው የኢትዮጵያ ሃያል ዘር (Master race) እኛ ነን ማለታቸው እንደሆነ ይገባናል ።
 • ፋሽስቶችና ናዚዮች – 6 ምሊዮን አይሁዳዎችን እንድመነጠሩ ሁሉ ወያኔ ከ2-3 ምሊዮን አማሮችን አጠፋ/መተረ
 • ፋሽስቶችና ናዚዮች – ፖሊሽዎችን ፣ጅፕሲዎችን ፣ ሰርቦች ፣ጥቁሮችን ወዘተ..እንደጨፈጨፉ  ሁሉ ወያኔ/ህወሃት – ኦሮሞችን ፣ጋምቤላዎችን ፣ኮንስዎችን ፣ቤኒሸጎዎችን ወልቃይቶችን ፣ቦረናዎችን ፣በቅርብ ግዜ የዲላ ነዋሪ ጉራጎችን ወዘተ..በጅምላ ጨፈጨፈ
 • ናዚዮች የማይፈልጓቸውን ወይም እነዚያ የሚልዋቸውን ሰዎች የሥነዘር ፍሬ የማምከን ሳይንስ (eugenism/eugenics) እንድተጠቀሙ ሁሉ ወያኔ/ህወሃት በአማራ ብሄረሰብ እናቶች ላይ ዘርን ማምከኛ መርዝ ተጠቅሞዋል
 • ናዚዮች የጀርመን አጎራባች አገሮችና መላውን አውሮጳ እንደወረሩ ሁሉ -ወያኔ/ህወሃት

የትግራይን ግዛት ለማስፋፋት/ለማተለቅ የትግራይ -አጎራባች ክ/ሃገሮችን ድንበር ጥሶ በጠመንጃ አፈሙዝ/ በሃይል –  ከወሎ ፣ከጎንደር ፣ከአፋር ፣ከወልቃይት ከጋምቤላ ወዘተ.. ምርጥና ለም መሬቶች ወስዶ ወደ ትግራይ አካሎዋል ። የወያኔ/የህወሃት ምሥራ  ቾችና የአሁኑ ገዢዮቻችን – በተግባራቸውና በሥነልቦና ፀረ-ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕ   ዝብ ይሁኑ እንጂ በትውልድ (by birth) ኢትዮጵያውያን አይደሉም ብሎ የሚከራከር ያለ አይመስለኝም ። ወያኔ/ህወሃት ኢትዮጵያን ወረረ በማለት ስለሚነሱ – ክርክሮችና አመለካከቶች ከሚመስል የወረራ መስፈርቶች ወይም ማስረጃዎችጋር አጣጥሞ መጻፍ ስለሚያስፈልግ በሌላ ግዜ እመለስበታለሁ።

 • ገስታፖ ለፋሽስት/ናዚ- ጀርመኒ = ካድሬ ለኢትዮ-ወያኔ ፤ ገስታፖ በመባል ይታወቁ/ይጠሩ የነበሩት ፀረ- ሕዝብ የፖለቲካ ሰላይ ፖሊሶች ፤ (1) የጀርመን ሕዝብ -የሚያወራውን ፣ የሚያደርገውን ፣ የሚያስበውን ፣የሚበላውን ፣ የሚጠጣውን ወዘተ.. በመሰለል  (2) በፖለቲካና በሲቪክ ተቃዋሚ ድርጅቶች ውስጥ ሰርገው በመግባትና በገሃድ በማዳከም እና የጀርመንን ፋሽስታዊ ሥርዓት ዕድሜ በራዘም ቁልፍ ሚና ተጫውቷል ። ሁላችንም እንደምናውቀው  አንድ ለአምስት የተደራጁትን ፀረ-ሕዝብ የወያኔ/ህወሃት  ካድሬዎችም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የገስታፖዎች ሚና ተጫውቷል እየተጫወቱም ነው ፤ የአንድ የጋለ ምጣድ ፊትና ጀርባ ናቸው ።
 • ኤሰ ኤስ (SS) ለናዚ ጀርመኒ = አጋዚና የፈደራል ፖሊሶች ለኢትዮ-ወያኔ ፤ SS(Corps of Nazi party)ማለት ነው ። የገፍና የግፍ  ግዲያ እንደ ሆሎከስት (Holocaust) ዓይነቱ ፣ ሕዝባዊ አመጽ የማፈን  የገፍ እሥር ቤቶች/ኮንሴትሬሽን ካምፕ የማስተዳደር ፣ የዘረኝነት ፖሊሲ ወይም መመርያ የማስፈፀሜያ ወዘተ.. መሣሬያ ነበሩ ።አጋዚና የፌደራል ፖሊስ ተብዮች ከሞላ ጎደል ተመሣሳይ ሥራ ነው የሚሰሩት
 • ሶንደርገሪችት (Sondergricht) ለናዚ-ጀርመኒ = ለኢትዮ-ወያኔ ፍርድ ቤት ፤ በጀርመኖ ች ቋንቋ ሶንደርገሪችት ማለት- የሕዝብ ፍርድ ቤት (the people`s court) ማለት ነው ። የናዚ ጀርመኒ ፍርድ ቤቶች – ፕሬዝዴንቶችና ዳኞች ለሞትም ሆነ ለእሥር ቅጣት ሲፈርዱ የጀርመንን የዳኝነት ሕገ-መንግሥት ህግ ተከትለው  ሳይሆን የናዚ ፓርቲ በሚ  -ሰጣቸው መመርያና ትእዛዝ ነበር ። በተመሳሳይ  የዘመነ ወያኔ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ዳኛ ተብዮችም በዜጎች ላይ የሚፈርዱት – የፍትህን መተክል ወይም መርህ ተከትለው ሳይሆን -የወያኔ/ህወሃት ፓርቲ ሹሞች በሚሰጥዋቸው ትእዛዝ ነው ። ሁለቱም የካንጋሮ ፍርድ ቤት ተምሳሊት ናቸው ። የካንጋሮ ፍርድ ቤት (kangaroo court) ከአሜሪካ /ኢ-ይፋዊ እንግሊዝኛ (illiterary English) የመነጨ ሲሆን – (የቀልድ ፣የይስሙላ ፣ የፍርደ-ገምድል ፣ የኢ-ፍትህ ፣ የሩጫ ፣ የጭካኔ ፣ የአድሎ ፣ የበዘፈቀድ ፣ ቅንነት የጎደለው ወዘተ…ፍርድ የሚሰጥበት ፍርድ ቤት እንደማለት ነው) ።
 • ሂትለር የጀርመን ቻንስለር በመሆን ለከፍተኛ የፖለቲካ ሥልጣን የበቃው እ.አ.አበ1933ዓ.ም ነው ። የዚያን ጊዜ ጀርመን የዊመር ሪፐብልክ (The Weimer Republic)በመባል ይጠራ ነበር ። የጅርመን ብሄራዊ ባንድራ/ፍላግ – ከጥቁር፣ከቀይና ከወርቃማ ብጫ ቀለሞች የተሠራ ነበር ። ………ከ 1935 -1945 ዓ.ም የጀርመን ባንድራ በስዋስቲካ(Swastika) ማለት ከዚህ ዝቅ ብሎ በሚታየው ምልክት ተተካ ።የምልክቱ ትርጉም‘ መልካም ዕድል/good luck’ የሚል ሲሆን – በቃላት ለመግለጽ  ሚያስቸግር መዓት/ቁጣ አስከትልዋል ።

በተመሳሳይ፥ የ21ኛው መቶ ክ/ዘመን የኢትዮጵያው ፋሽስት- ናዚ ማለት ወያኔ/ህወሃት ከሁሉም አገራት  ባንድራዎች ቀደምትነት ያለው መሆኑን የሚታወቀው ፤ቢያንስ እ.አ.አ ከ1900 ዓ.ም ጅምሮ ማለት እ.አ.አ  ሰኔ (June) 28/1919 ከተመሰረ ተው  (League of Nations) በመባል ከሚታወቀው – የያኔ የዓለም መንግሥታት ድርጅት ከመመስረቱ በፊት -እውቅና ያገኘው `ሰንደቅ ዓላማችንን  የመቶ ዓመት ታሪክ ያለው አገር የሚወክ  ል ጨርቅ በመሆኑ – ወያኔ/ህወሃት ለሚገዛው ኢትዮጵያ አይወክልም በማለት  በምትኩ  የሰይጣናዊ መንፈስ እምነት (satanic cult) ተከታዮችን ምልክት/ሲምቦል በሆነው – ባንድራ ተካው (ወያኔ/ህወሃት) ፤ ባንድራ  የጣሊያን ስም መሆኑን ለሁላችንም ግልጽ ይመስለኛል ፤ እዚጋ ባንድራ ስል ወያኔ ሆኜ መናገሬ ነው።

ለ 25 ዓመታት ዓይተነው  ዓይተነው የሰለቸን ሰለሆነ  – ምስሉን እዚህ ጋ መለጠፈ አልፈለኩም። Satanic cult ritual  (SRA), sometimes known as ritual abuse, ritualistic abuse, organised abuse, sadistic ritual abuse and other variants) was the subject of a moral panic that originated in the United States in the 1980s; spreading throughout the country and eventually to many parts of the world by the late 1990s.  

ግልጽ እንግሊዝኛ ስለሆነ ወደ አማርኛ መተርጎም  አልፈለኩም ።

ወያኔዎችም  ጫካ  እያሉ በሚሠርዋቸው -ተንኮሎች ፣ በሚፈጽሟቸውን ግፎች ፣ባፈሰሱት የሰው ደም  ወዘተ… ሲሸበሩና ሲደናገጡ –  ለሰይጣናዊ  ለ(satanic cult) እምነት የሆነው  ምስል/symbol  ይማጸኑ  ነበር ማለት ነው ።  ስለሆነም  ቀንቷቸው  የፖሊቲካ  ስልጣን  ሲጨብጡ   ባንድራቸ ው  አደረጉት ማለት ነው ።ይህንን  አስመ   ልክቶ በርካታ አተያይ/ቪዩ  ማስቀመጥ የሚቻል ቢሆንም ፤ አንባቢ ላለማስልቸትና ጊዜ ከመቆጠብ  አንጻር ማሳጠሩን መርጥኩ ።

 • አዶልፍ ሂትለር  ነገደ  እስራዔሎችን  ከጠላበት አሥር ምክንያቶች  አንዱ -በዋናነት  በንግድ ላይ ተሠማርተው  በጀርመን የኢኮኖሚዩን ዘርፍ  ትልቁን ድርሻ በመያዛቸው፣ ሃብታም  በመሆናቸውና – ይህዳውያን  ከአርያኖች የተሻል ኑሮ በመንራቸው  ቀንተው  ባቸው  ነው ይላሉ  ታሪክ ፀሃፊዮች ። በተመሳሳይ ህወሃት የኢትዮጵያ ሥርወ-መንግሥ  ት በያዘ ማግሥት –  ፖለቲካውን  ከአማራ የንግዱን ዘርፍ ከጉራጌ  መንጠቅ  ቀደምት  ዓላማው እንድሆነ አወጀ ።

በዲሞክራሲያዊ  ሕገመንግሥት ሥርዓት – በዜግነት ፖለቲካ  ለሥልጣን  መወዳደር በማይቻልባቸው  ፤ በጠመንጃ አፈሙዝ  የፖለቲካውን ሥልጣን  በአምባገነን ንጉሣዊ (absolute monarchy) ሥርዓት ፣ ህዳጣን  ብሄር /ብሄረሰቦች እና ወታደራዊ መንግ   ሥት በሚፈራረቁበት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች – ከፖልቲካ ሥልጣን የተገለሉ ወይ   ም እዚያ መድረስ የማይችሉ  የአናሳ ብሄረሰበ  አባሎች – በንግድና  በተራ ሥራ ዘርፍች እንድሚሠማሩ  ከአንዳንድ ግራ ዘመም የፖለቲካ  ሳይንስ መፅሃፍት መማር ይቻላል ።

በመሆኑም አሁን እስከ ደረስንበት 21ኛው መቶ ክ/ዘመን – የጉራጌ ብሄረሰብ የጠመንጃ አፈሙዝ ተጠቅሞ ለፖለቲካ ሥልጣን ከማይወዳደሩ አናሳ ብሄረሰቦች አንዱ ለመሆኑ ምስክሩ የኢትዮጵያ ታሪክ ነው ። ምክንያቱ/መነሻው  ለምን እንድሆነ ባይታወ  ቅም – የጉራጌ ብሄረስብ ሥራ ወዳድነት  ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ የተለየ  ስለመሆኑ  እዚህ ጋ መግለጽ ለቀባሪ መርዶ ማርዳት ይሆንብኛል ፤ “necessity is the mother of invention” ማለት ችግር ብልሃት ያስተምራል ስለሆነ ይሆን ?         “Labour created man himself” (Frederick Engels) ማለት  ‘ሰውን ሰው ያደረገው ሥራው ነው’ የተሰኘው (የፌደሪክ ኤንጅልስን) ጥቅስ ወይም መርህ የሥራ ባህላቸው  ያደረጉት  ፈሬደሪክ ኤንግልስ ገና ሳይወለድ ነው ።

 

ከጫማ ጠራጊነት አንስቶ  በየትኛውም  ዝቅተኛ የሥራ ዘርፎች ተሠማርተው  በመስራት – የሥራ ክቡርነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስተምረዋል ። ከተሰማሩባቸው የሥራ ዘርፎች  አንዱ ነግደው የመኖር  ዘርፍ ሲሆን – ከሱቅበደረቴነት ንግድ  እስከ አስመጪና ላኪ (exporters and importers) ለመሆን በቅቷል ። በቅድመ ወያኔ/ህወ   ሃት በኢትዮጵያውያን የሃብት አሰላለፍ በርካታ ጉራጌዎች – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ከበርቴ  ለመሆን በቅተው ነበር ። አሁን ግን እንኳንስ  የኢትዮጵያ የአንድ መንደር ከበርቴ የሆነ ጉራጌ የለም ።

ሂትለር አይሁዶዎችን ከጠላበት ምክንያቶች አንዱ ሃብታም በመሆናቸው ቀንቶባቸው እንድ ነበረ ከላይ ጠቅሼአለሁ ።ወያኔ/ህወሃት  ጉራጌዎች የጠላበት ምክንያቶች ሁለት ናቸው  ። (1) በንግዱን ዘርፍ ቀንና ለሊት ሠርትው  – በሃብት ከሌሎች ብሄረሰቦች በልጠው በመገኘታቸው  ቀንቶባቸው  ነው ። ጉራጌዎችን በንግዱ መሥክ የነበራቸውን   የበላይነት ለማዳከምና ከዚያ ለማፈናቀል ፤  ከአቅማቸው በላይ የሆኑ -ግብሮች፣ ቀረጦ  ችና  የባንክ ወለዶች  ጫነባቸው  ። የማይችሉትን የቤት ክራይ በማስከፈል ለንግድ ምቹ ከሆኑ ቁልፍ ቁልፍ መናኽርያዎች አፈናቀላቸው ፤ በሱቅበደሬተነት – ከቦታ ቦታ በመዘዋወር ይነግዱ የነበሩትንም  እነሱን ለማባረር በተመደቡትን ፖሊሶች -በየእለቱ ይደርሥባቸው በነበረው ዱላ ድብደባ ተማ ርረው – ወደ ለምኖ የመኖር ሕይወት ተሰማሩ ።

ህወሃት  የጉራጌ ነጋዴዎችና ቤተሰባቸው ሰብስቦ  እንደ ሂትለር መርዛማ ጋዝ አሳጥኖ ባይፈጃቸውም – በረሃብ ፣በድኅነትና  በእነዚህ  ምክንያቶች በሚመጡ በሽታዎች በቀስ በቀስ ወይም ባዝጋሚ ሞት እንዲያልቁ አደረገ ። የንግዱን ዘርፍ – በህወሃት የንግድ ተቋ  ም ፣የህወሃት የፕለቲካ አቅም በሚያጠናክሩ ትውልደ ትግራይ በሆኑትን ኩባኒያዎች ፣ ቡድኖች ፣ግለሰዎችና ካድሬዎች ተተካ  (2) ህወሃት ጉራጌዎችን የጠላበት ሁለተኛው  ምክንያት -አማራን ወግነው ፀረ-ህወሃት አቋም አላቸው በሚል ነው ። አዎን ወያኔ የኢ   ትዮጵያ ሕዝብ በጎሣ ክልል ሸንሽኖ ማስተዳደርን አስመልክቶ ጉራጌዎች ቶሎ አሚን እንዳላሉትና እንደተፋለሙት በአንድ መጽሄት ተጽፎ አንብቤያለሁ  ፤ “ከሰሜን የአገራ  ችን ጫፍ እስከ ደቡብ የአገራችን ጫፍ ፤ ከምሥራቅ የአገራችን ጫፍ እስከ ምዕራብ    የአገራችን ጫፍ ተዘዋውረን መኖርና መሥራት በትውልድ ዜግነት ያገኘነው መብታች” ነው የሚል ሙግት እንድገጠሙት  ለግዜው ስሙን በረሳሁት አንድ የአማርኛ መጽሄት  ውስጥ አንብቤያለሁ ።

ሂትለር የሃያላን ምዕራብ መንግሥታት አገሮች ማለት ታላቋ እንግሊዝ ፣ ፈራንሳይና  የሶቭየት ኅብረትን በመውረሩና  የእነዚህን አገሮችና የአሜሪካ – የኢኮኖሚ ጥቅሞች ለመሻማት በመዳፈሩ ፋሽስት አሉት እንጂ ፤ ሂትለር በጀርመንና በጀርመን ሕዝብ ላይ     የፈጸመው ግፍ  – ወያኔ/ህወሃት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከፈጸመው ግፍ በልጦ አይደለም  ። ወያኔ/ህወሃት በእነዚህ ሃያላን መንግሥታት ጫማ ሥር በመውደቁ  ና ለእነሱ ጥቅም  የሚገለባበጥ በመሆኑ  – መቶውኑ ምሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢግል/ቢጨፈጭፍ  ፋሽስት አይሉትም ።

ወልደአብ ደንቡ

– See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17362/#sthash.NLTeudO7.dpuf

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s