ጎንደር እስከ ደባርቅ የግፍ ፅዋው ሞልቶ እየፈሰሰ ነው! – ሙሉነህ ዮሃንስ

በግፍ አፈሳ ጎንደር ከተማ ላይ የተያዙትን ወገኖች ቤተሰባቸው እስር ቤት ሊጠይቁ ሄደው ነበር። ዛሬ ጭራሽ አይደለም ምግብ እነሱን ማየት አትችሉም ተብለው ተመልሰዋል፡፡ እናቶች እያለቀሱ ተመልሰዋል። ዛሬ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የባንክ ማናጀሮች ሁሉ ነው የታሰሩት። እናቶች ከአንድ ላይ ሆነው አልቅሰው ልጆቻችንን አሳዩን ቢሉም የወያኔ ወታደሮች እያዳፉ መልሰዋቸዋል።

ዛሬ ደባርቅ ላይ የዳባት ከነማ እና ደባርቅ ከነማ ጭዋታ አለ፡፡እናም ወያኔ ሆን ብለው ከሚጨፍሩበት በመግባት ፀብ ለማስነሳት ሲሆን ህዝቡም በሃይለኛው ተቃውሟል ይህ ድርጊት ሆን ተብሎ ደባርቅና ዳባትን ለማጋጨት ነው በማለት ሲሆን ብዙ ወታደሮችም ተመድበዋል፡፡ አሁን ጭዋታው ተጀምሯል፡፡ የእግር ኳስ ሜዳወች ብሶት ማሰሚያ ብቸኛ መድረኮች ሁነው እያገለገሉ ነው። የወያኔን ሴራና ዘረኛ አገዛዝ በህዝብ ትግል እንገረስሳለን ሲሉ ሪፖርቱን ያቀበሉን የደባርቅ ወጣቶች በቁርጠኝነትና በእልህ ገልፀዋል።
የነፃነት ጥያቄ በአፈና አይመለስም!
ህዝብ ያሸንፋል©!
ሙሉነህ ዮሃንስ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s