ንቃተ ህሊና ያላቸዉን ዜጎችን የማጥፋት ዘመቻ:- ዶ/ር ጋሹን እንደ ማሳያ – ሸንቁጥ አየለ

ዲሞክራሲያዊ መብትን መጠዬቅ: ሰበአዊነትን መጠዬቅ እና በጣም ቀላል የመብት ጥያቄዎችን በስህተት እንኳን ማንሳት በኋላ ቀሮቹ ወያኔዎች የጭካኔ ሰንሰለት ውስጥ ለመዉደቅ በቂ ምክንያት ናቸዉ::ኢትዮጵያ ዉስጥ በአለም ዙሪያ የተከበሩት ብሎም ሰዉን የሚያስከብሩት የስልጣኔ እሴቶች ሁሉ በወንጀለኝነት ለመፈረጃነት በቂ ምክንያት እየሆኑ ሀያ አምስት አመታት አልፈዋል::በሞያዉ ላይ ከበሬታ ያተረፈ እና በተሰማራበት ሞያ ላይ እዉነቱን ቁልጭ አድርጎ የሚናገር ባለሞያ የወያኔ ጠላት ነዉ::የህክምና ዶክተር የሆነ ሰዉ በጤናዉ ዘርፍ በህዝቡ ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን አብራርቶ ከተናገረ ያ ምሁር የወያኔ ስርዓት ጠላት ነዉ::

በእስር ቤት ከታሰረዉ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በተጨማሪ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ እንደታሰረ ለማመልከት ብሩህ አዕምሮ ያላቸዉ የዞን 9 ጦማሪ ወጣቶች “ዞን ዘጠኝ” የሚለዉን ሀሳብ ይዘዉ ብቅ ብለዉ ነበር::ወያኔ እነሱንም ለእስር ቤት መከራ ዳረጋቸዉ እንጅ::

ዶክተር ጋሹ ክንዱ ብሩህ አዕምሮ ያለዉ : ቆፍጣና እና ንቃተ ህሊናዉ የዳበረ ዜጋ ነዉ::ይሄዉ ብሩህ ዐእምሮ ያለዉ ወጣት የአማራ ሃኪሞች ማህበር ፕሬዚዳንት በመሆን እያገለገለ ያለ እና በህክምና ሞያዉም ምስጉን ዜጋ ነዉ:: ዶ/ር ጋሹ በሞያዉ ዘርፍ ያሉትን እጸጾች በሞያዊ ዲሲፕሊን በመመራት ለመግለጽ ብሎም መፍተሄ እንዲበጅላቸዉ ለማስረዳት ወደኋላ የማይል ምስጉን ባለሞያ ነው:: ወያኔ ይሄን ወጣት እና ይሄን የመሳሰሉ የሀገሪቱን ባለ አዕምሮዎች በሙሉ ከምድረ ገጽ ሳያጠፋ ይተኛል ብሎ የሚያስብ ሰዉ ካለ ሞኝ ነዉ::ተራዉን የመጠበቅ ጉዳይ እንጂ እንደዚህ ንቃተ ህሊና ላይ የደረሱ : የተማሩ ወጣቶችን ማጥፋት ዋናዉ የወያኔ ስራ ነዉ::ለምን? ሀገሪቱ መሪ እንዳይኖራት:: የወያኔን ወንጀል የሚጠይቅ ዜጋ እንዳይኖር:: በየማህበረሰቡ ዉስጥ ንቃተ ህሊናዉ ከፍ ያለ ዜጋ እንዳይኖር:: ብሎም ወያኔ እድሜ ልኩን ህዝቡን ባሪያ አድርጎ ለመኖር::

ይሄ ክፉ ሀይል ኢትዮጵያን በአንባገነንነት: በዘረኝነት እና በመደብ የፖለቲካ ህሳቤዎች ከፋፍሎ ጠርንፎ ይዟታል እና የዶክተር ጋሹ ከአማራ ማህበረሰብ የመመዘዝ እዉነታ ደግሞ የዚህን ባለ ብሩህ አዕምሮ ወጣት መከራ የበረታ እንዲሆን ያደርገዋል:: ለዚህም ዘረኛ የጭካኔ ምግባርም ማሳያ የሚሆነን የራሱ የወያኔ ማኒፌስቶ አማራ ጠላቴ ነዉ ስለሚል እና ባለፉት 25 አመታት ዉስጥ በብዙ ሚሊዮን አማራ ላይ የዘር ማጥፋት ስራ ስላከናወነ ብቻ ሳይሆን ወያኔ የፖለቲካ ቀዉስ በገጠመዉ ቁጥር ወደ አማራ ምሁራን ላይ መሳሪያ አንስቶ የጅምላ ርሸና ስራ እንደሚያከናዉን በገሃድ ስለሚታወቅ ነዉ::

ስለሆነም በኢትዮጵያዊነትም ሆነ በአማራነት የተደራጃችሁ ሀይሎች የዶክተር ጋሹን ጉዳይ ለአለም አቀፉ ማህበረሰቡ እንዲሁም ለአለም አቀፉ ፍርድ ቤት የማሳወቅ ሚናችሁን ምን ያህል እየተወጣችሁ እንደሆነ በደንብ አጢኑት::ይሄን ወጣት እየገጠመዉ ያለዉን እና ሊገጥመዉ የሚችለዉን ኢሰበአዊ አያያዝ ሁሉ አብራርታችሁ ለማሳወቅ መፋጠን ይገባችኋል::ጉዳዩ ከዘር ማጥፋት ጋር እንደሚያያዝ ጭምር ለአለም ማህበረሰብ ማስረዳት ያስፈልጋል::

ሸንቁጥ አየለ

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s