ከወያኔ ጋር ድርድር ምን ይጠቅማል? | መንግስት በአዲስ አበባ ከተቃዋሚዎች ጋር ዛሬ ጀመርኩት ባለው ድርድር ዙሪያ ወቅታዊ ዕይታ

ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ | ለገሠ ወ/ሃና

ከወያኔ ጋር ድርድር ለኢትዮጵያ ይጠቅማታል ወይ የሚለው በደንብ መታየት ያለበት ቢሆንም በእኔ እምነት ጥቅም ያለው መስሎ አይታየኝም ድርድር መቼና በምን ሁኔታ ላይ ይደረጋል ? ምንስ ይጠቅማል ? በሌላ ጊዜ በሰፊው ልንመለስበት እንችላለን ለዛሬ ባጭሩ ድርድር ሁለትና ከሁለት በላይ በሆኑ ሀይሎች መካከል በጋር ለመስራት ፣ በመካከላቸው አለመግባባት ካለ ለመፍታት ፣ለጋር ጥቅም በጋራ ለመስራት ፣ በእኩልነት ለውይይት የሚቀመጡበት አሰራር ነው አንዱ ካንዱ አይበልጥም አያንስም ሂደቱ በራሳቸው ወይም በሶስተኛ አካል አማካኝነት ሊደረግ የሚችል ነው ፡፡

በኢትዮጵያ ሁኔታ ግን ከዚህ የተለየ ነው በተለይ ከህወሓት ጋር የሚደረግ ውይይት ከሆነ አሸናፊው ከተሸናፊው ጋር ለውይይት እንዲቀርብ ይደረግና አሸናፊው ተሸንፎ እንዲወጣ የሚደረግበት አካሄድ የተለመደ ነው ፡፡

ህውሃት ሁልጊዜ እንደሚያደርገው ለስልጣኑ አስጊ ሁኔታ ሲፈጠር የእንደራደር ጥያቄ ይዞ ብቅ ይላል በ1997 ዓም ምርጫ ከተሸንፈ በኋላ በነበረው ሂደት አጣብቂኝ ውስጥ የገባው የህወሓት “መንግሥት ከፀሃይ በታች ባለ ነገር ሁሉ እንደራደራለን “ማለቱ ይታወቃል ፡፡ በወቅቱ የቅንጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት በአግባቡ ተወያይተው ውሳኔ ሳያልፍ ጥቂት ሰዎች ወደ ድርድር ሄደው ለድርድር ተቀመጡ መለስ ዜናዊ ቅንጅት ጥቅምት 22/1998 ዓም የጠራውን የቤት ውስጥ አመጽ እጅግ ስላስደነገጠው የህወሓት አገዛዝ ልጡ የተራሰ መቃብሩ የተማሰ መሆኑን ስለተገነዘበ በእንደራደር ሰበብ ወጥመድ ውስጥ አስገብቶ የተጠራውን የቤት ውስጥ አመጽ እንዲያራዝሙ አግባብቶ እሱ ከውይይቱ ጀርባ ሠራዊቱንና ደህንነቱን በማጠናከር መንግሥት እየመሠረተ ነበር በቅንጅት የተጠራው የቤት ውስጥ አመጽ እንዲቀር ከተደረገ በኋላ የቅንጅትን አመራር ከያሉበት ለቃቅሞ እንዴት እንዳሰራቸው እንኳን እኛ አለም የሚያውቀው ሀቅ ነው አሸናፊው ወደ እስር ቤት ተሸናፊው ወደ ቤተ መንግሥት ይህ በኛ ዘመን የታየ እውነት ነው ፡፡

ህውሃት ዛሬ ያቀረበው ከተቃዋሚዎች ጋር እንደራደር ጥያቄ ካባለፈው የሚለየው እውነተኛ ታጋዮችን ፣አስሮ ፣ አሳዶ መሆኑ ነው ለምሳሌ እንደ መኢአድ ፣አንድነት አይነቱን ጠንካራ ድርጅት በጠራራ ፀሀይ ዘርፎ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደከመኝ ሠለቸኝ ሣይሉ የደከሙትን ሠላማዊ ታጋዮች እያሳደደ የራሱን ሰዎች ሾሞ ሌሎችን አባሮ ነው ፡፡

እንደ በፊቱ በአሁኑ ሰዓት የህውሀትን አገዛዝ ከትግሉ ባለቤት ጋር እያሽመደመደው ያለው የህዝብ ትግል እንጅ የፓርቲ ፓለቲካ አይደለም ህውሃትን በጦር ሜዳ እያሸመደመዱት ያሉት ጀግኖቹ የጎንደር ገበሬዎች እንጂ ፓለቲከኞች አይደሉም ህውሃትም እየተዋጋ ያለው ከማን ጋር እንደሆነ ያውቃል ፡፡

ከጉዳዩ ምንም ግንኙነት ከሌላቸው ከማይመለከታቸው ጋር ልደራደር ነው ማለቱ በጣም ያስቃል ፡፡

ድንቅ የሚለው ህውሃት ተቃዋሚ የሚላቸው ህዝቡ ያነሳውን የነፃነት ጥያቄ ያልጠየቁ ፣ ነለፃነት ትግሉ ምንም አስተዋጽኦ የሌላቸው ፣ የትግሉ አካል ያልሆኑ መሆናቸው ነው ፡፡ አገዛዙ በምሳሌው የፈጠራቸው የራሱ የእጅ ስራዎችን ነው ለድርድር የጋበዘው እነዚህ የተቃዋሚን ካባ የለበሱት የስርዓቱ ደጋፊዎች ህውሃት ከገባበት አዘቅት ሊያወጡት አይችሉም እነሱ ከህወሓት ጋር የሚያደርጉት ውይይት ፣ ድርድር ፣ ስምምነት ወዘተ የሚወስኑትን ውሳኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ውሳኔ አይደለም ተቀባይነትም የለውም ፡፡

እነዚህ ተቃዋሚ መሰል ስብስቦች አገዛዙን ከመውደቅ እንደማያድኑት አውቀው የተጀመረው ትግል በነሱ ምክንያት የማይቆም መሆኑንም በመረዳት ቢተውት ጥሩ ነው ፡፡
የነሱ በህውሃት ግብዣ ላይ መገኘት የሚጨምረውም ሆነ የሚቀንሰው አንዳች ነገር እንደሌለው ሊያውቁት ይገባል የህወሓትን ግብዣ ባይቀበሉ ይሻላቸዋል ፡፡

ህውሃትም ከነዚህ ሠዎች ያሰበውን የፓለቲካ ጨዋታ በመተው በኢትዮጵያ ውስጥ በፓለቲካ አመለካከት የታሰሩትን በሙሉ በመፍታት ፣ ድርጅቶች እንዲደራጁ በመፍቀድ በጉልበት የያዙትን ስልጣን ለህዘብ በመስጠት ራሳቸውን ቢያገሉ ቢያንስ ከዚህ በፊት በሠሩትን ወንጀል ብቻ ይጠየቃሉ ወይም የኢትዮጵያ ህዝብ በይቅርታ ሊያልፋቸው ይችላል ወደ ፌት የሚፈጠረውንም አስቸጋሪ ሁኔታ ይቀንሳሉ ብየ አስባለሁ ከነዚህ እራሳቸው ከፈጠሯቸው ተቃዋሚዎች ጋር ተወያይቶ ምንም ሊያገኝ ይችላል ብለን ስናስበው የሚገኝ ነገር የለም ምንአልባት ሊያገኘ የሚችለው ነገር በህዝብ ሀብት የሚንቀሳቀሰውንና በጉልበት በተቆጣጠሩት ቴሌቭዥንና እሬዲዮ ከተቃዋሚዎች ጋር እንዲህ ተደረገ ወዘተ ሊያወሩ ይችላሉ ለደጋፊዎቻቸውም ለማሳየት ይጠቀሙበት ይሆናል ይህ የተነሳውን የነጻነት ትግል የበለጠ ያቀጣጥለዋል እንጂ አያበርደውም ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s