ቤተ ቅኔያችን ብሄራዊ ዓርማችን: ዘመን ጠገብ ፍቱና ችን – ከሥርጉተ ሥላሴ

ከሥርጉተ ሥላሴ 23.01.2017 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

„በዝናብ ቀን በደመና ውስጥ እንደ ቀስተ ደመና አምሳያ፥ እንዲሁ በዙሪያው ያለ ፀዳል አምሳያ ነበረ። የእግዚአብሔር ክብር ምሳሌ መልክ ይህ ነበረ። ባየሁም ጊዜ በግምባሬ ተደፋሁ፥ የሚናገርንም ድምፅ ሰማሁ።“

(ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፳፰)
ይድረስ ለአትሌት ወርቅነሽ ደገፋ – ባለሽበት።

እንዴት ነሽ? ደህና ነሽ ወይ? ከቶ ዕንቅልፍ ወስዶሽ አደረን? ነገንስ በምን አቅም ይሆን እምትራመጂው? ከቶ ስንቅሽ ዬህዝብ ፍቅር ካልሆነ ዬሥነ – ልቦናሽ ሙሉ ጤንነት እንደምን ይሆን? እንደ አንድ ሀገር ዜጋ ተከታዩ ዬህይወትሽ ዑደት አሳሰበኝ –

ጠብታ።
ዬክብር – ቅኔያችን
ነህ ቃለ – ነፍሳችን!
ዬቃና ዬዜማ – ብጡሉ ህብራችን፤
ዬእዮር ስጦታ ትንግርት – ሁነታችን።
እፍታ።

ሀገር ማለት ዬራስ ዬሆነ – በእጅ ዬሚገኝ አሰተማማኝ ዬሆነ፤ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው መሬት ማለት ነው። ህዝብ ማለት ደግሞ ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ባለው ዬወሰን ደንበር በሚገኝ  መሬት ዬሚኖር ዬሰዎች ማህበር ማለት ነው። ሀገር አለኝ ማለት ዬህልውዬ እራስነት እኔው ራሴ ነኝ ማለት ነው። ሀገር ዬመኖር እንደራሴ ነው። ሀገር ማለት እንደራስ ተፈጥሮ መዋለ ህይወትን ማኖርማለት ነው። ሀገር ማለት ከሌላው ሀገር ህዝብ ዬሚለዩበት ዬውስጥ መስታውት ማለት ነው። ሀገር ማለት በሂሳብ ቀመር ትርፍና ኪሳራው ዬማይለካ ወይንም ዬማይሰላ ዬመንፈስ ባለጸጋነት ማለት ነው። ሀገር ማለት ውስጡን እዬኖሩበት ባለበት ጊዜ ሳይሆን – ይልቁንም ያጡትለት ስለ አፈር ልዑላዊነት ቁሞ ዬሚያስተምር ልዑቅ ሐዋርያማለት ነው። ዬሀገር፤ ዬመሬት – ዬአፈር ቋንቋው ፍቅር ዬሆነ ልዩ ዬመኖር ሥጦታ ማለት ነው። ዬጽናት ምልክቱ ደግሞ ሰንደቅ ዓላማው ነው። ዬኃያልነቱ ጉልበታምነት ምንጩ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው ነው። ዬሀገር በነፃነት መኖር መሠረቱ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማው በነፃነት ከፍ ብሎ በብሄራዊ ይሁን በዓለም አደባባይ በነፃነት መውለብለቡ ነው። ዬኢትዮዽያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ህይወቱ ሁልጊዜም አሸናፊነቱ ነው። ዬናቁትን – ዬሚያንበረክክ፣ ዬሚዳፈሩትን በራድ ዬሚያርበደብድ፣ ዬአትንኩኝ ባይነት ዋልታ፤ ዬጀግንነት ወርቅ ነው ብሄራዊ ዓርማችን። ሲያከብሩት – ዬሚያስከብር፣ ሲጥሉት ዬሚቀጣ ዬመንፈስ ችሎት ነው – ባለውለታችን። ምንም ዓይነት ጌጥ እንደ ብሄራዊ ሰንደቃችን ዬሚያደምቅ፣ ዬሚያበራ ዬቀን ዬሌሊት ጸሐይ ዬለም። ልዩ ጀርጋዳ – ዬሁሉም ጸዳላዊ ዬውበት ጸደይ ነው። ፍጹም ዬሆነ ዬሐሤት ፏፏቴ ነው።  

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s