የወልቃይትን ‹‹ታሪካዊና ባሕላዊ ትግሬነት ለማረጋገጥ›› ጥናት ለሚሠሩ ተማሪዎች የተለየ በጀት መመደቡ ተሰማ፤ – ሙሉቀን ተስፋው

ሙሉቀን ተስፋው

በኢትዮጵያ ባሉ ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩ የትግራይ ተማሪዎች የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ማሙያ ጽሑፍ ሲያዘጋጁ የወልቃይትን ታሪካዊና ባሕላዊ ትግሬነት ለማሳየት የሚሠሩ ተማሪዎችን ሙሉ ወጪ እንደሚሸፈንላቸው በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የሚማሩ የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች አስታወቁ፡፡

በፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ በሕዝብ አስተዳደር፣ በፌደራሊዝም፣ በባሕልና ፎክለር፣ በሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር፣ በሰላምና ግጭት (ፒስ ኤንድ ኮንፍሊክት)፣ በታሪክ እንዲሁም በተያያዥ የትምህርት መስኮች የሁለተኛና የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ለሚሠሩ የትግራይ ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሑፋቸውን ከወልቃይት ጋር ካያያዙት የተለየ የገንዘብና የቁሳቁስ እግዛ እንደሚደረግላቸው መረጃ ሰጪዎቻችን ገልጸዋል፡፡
እንደመረጃ ሰጪዎቻችን የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው የትግራይ ተማሪዎች በዩንቨርሲቲ ወይም በሚስተምራቸው ድርጅት ከሚመድብላቸው የስኮላርሺፕ ክፍያ በተጨማሪ ማበረታቻ ነው ተብሏል፡፡ በሕወሓት ጽ/ቤት እንደ ቁልፍ ተግባር ተይዞ እየተሠራበት ያለው ይህ ፕሮጀክት በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ዩንቨርሲቲዎች ላይ ትኩረት ተደርጓል ተብሏል፡፡

Sponsored by Revcontent
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s